ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ
الذهاب إلى القناة على Telegram
ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።
إظهار المزيد608
المشتركون
-124 ساعات
-37 أيام
-1130 أيام
أرشيف المشاركات
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ታኅሣሥ ፲፫ (13) ቀን።
❤ እንኳን #ለታላቁ_አባት_ቆቅ ሲመገብ ለነበሩት #ለአባ_መቃርስ ወደ ብሔረ ሕያዋን ለገባበት በዓል፣ በስላሞች ዘመን በሰማዕትነት ለዐረፈ #ለአባ_በጽንፍርዮስና ከላይኛው ግብጽ ለሆነ #ለቅዱስ_አባት_ለአባ_አብራኮስ ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦#ቅድስት_ሐና እመቤታችንን ቅድስት ድንግል ማርያም ጸነሰቻት የሚሉ አሉ፣ በደብረ ቀልሞን ከሚኖር ከገዳማዊ #ከአባ_ሚካኤል ዕረፍት፣ #ከሰማዕት_ቅዱስ_አብራቂስ_ከሐርስፎስ፣ #ከመኰንኑ_ቆርኔሌዎስ_ከወርቅጥጶስና_ከአፍሬ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #ቆቅ_ሲመገብ_የነበረው_አባ_መቃርስ፦ ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ ጀምሮ ሕያው እግዚአብሔርን መከተል ፈልገ የቤተ ክርስቲያንንም ትምህርት መጻሕፍትንም ተማረ የዚህንም ዓለም ኃላፊነቱን ለጻድቃንም በጎ ዋጋ ለኃጥአን ቅጣት እንዳለም አስተዋለ ስለዚህም ዓለምን ትቶ በአንድ ገዳም ውስጥ መነኰሰ ከዚያም ወጥቶ የዐሥር ቀን ጎዳና ተጓዘና በውስጡ ኲዕንትና ቆቆች ውኃም ካለበት ተራራ ደረሰ። አስቦ እንዲህ አለ "ኵዕንት ወደመልቀም ብሰማራ የስግደቴና የጸሎቴ ሥራ ይቋረጣል ሰብስቦ የሚያስገባልኝ ረዳት የለኝም ብቸኛ ነኝኛ ሥጋ አትብላ ያለውስ የባልንጀራችንን ሥጋ በሐሜት የምንበላውን አይደለምን ሌላ ምግብም እንደሌለኝ ፈጣሪዬ ያውቃል" ብሎ ከዚያችም ዕለት ወዲህ ቆቆችን የሚያጠምድ ሁኖ በየቀኑ አንዳንድ የሚያዙለት ሆነ። እርሳቸውንም እየተመገበ ከዚያ ውኃም እየጠጣ በማመስገን ኖረ በቀንና በሌሊትም በጸሎትና በስግደት በመትጋት ወደ እግዚአብሔርም እየለመነ ብዙ ዘመናት ኖረ የሰውንም ጽምፅ አይሰማም የሰውንም ፊት አያይም ሐሜትንም ሆነ ስድብን በማንም ላይ አብሮ አይነጋገርም ከሰው ጋር ከልሆነ በቀር ሰይጣን አይመጣም ይባላልና።
❤ ከዚህም በኋላ ከቊስጥንጥንያ ከተማ አንድ መነኵሴ ዋሻ እየፈለገ አባ መቃርስ ከአለበት ደርሶ ቆቅን ሲያጠምድ አየው ያን ጊዜ አልታገሠም ግን ወንድሙን በሐሜት እስከሚገድለው ቸኰለ ወደ የቊስጥንጥንያ ከተማ ወደ ሊቀ ጳሳሳቱ ተመልሶ እንዲህ ብሎ ነገረው "እኔ ዋሻ እየፈለግሁ ወደ በረሀ ሔድሁ በዚያም ሥጋ ሊበላ ቆቅን ሲያጠምድ መነኵሴውን አየሁት የሚሠራውን ሲያዩ በአሕዛብ ዘንድ ሊያስነቅፈን ነው" አለው።
❤ ሊቀ ጳጳሳቱም ይህን ነገር በሰማ ጊዜ ነገሩ እውነት እንደሆነ ያውቅ ይረዳ ዘንድ ከዚያ ከነገረው መነኰሴ ጋር ሌላ መነኵሴ ላከ። እነርሱም በጒዞ ላይ በጐዳና ሳሉ ገና ሳይደርሱ አባ መቃርስ እንደልማዱ ወደ ወጥመዱ ሔደ በአንዲት ወጥመድ የተያዙ ሦስት ቆቆችን አገኘ እንዲህም ብሎ አሰበ "ጌታዬ እሊህን የሰጠኝ እኔን ሊፈትነኝ ነውን። ወይስ ከዚች ዕለት በፊት ሆዴ ያልጠገበች ኑራለችን ወይስ ለሌላ ነው እንዳልል በዚህ በረሀ ውስጥ ከሰው ወገን ያየሁት የለም"። እንዲህም እያሰበ ሳለ ከሊቀ ጳጳሳቱ የተላኩት እሊህ መነኰሳት ደረሱ በአያቸው ጊዜ ደስ አለው "ችግረኞነቴን አውቀህ ለአገልጋዩችህ ቅዱሳን ምግባቸውን የሰጠኸኝ አቤቱ አመሰግንሃለሁ" ብሎ ሰገደ። እነርሱ ግን ማዕድ ሠርቶ አዘጋጅቶ እስከአቀረበላቸው ድረስ ይጠቃቀሱበት ነበር።
❤ ከዚህም በኋላ አቅርቦላቸው "ንሱ አባቶቼ ባርኩና ተመገቡ" አላቸው እርሱም የራሱን ድርሻ ይዞ እስከጨርስ ያለ መነጋገር በጸጥታ ተመገበ። ከዚህም በኋላ ዓይኖቹን ቀና ቢያደርግ እንዳልበሉ አየ "አባቶቼ እንዴት አልበላችሁም" አላቸው "እኛ መንኰሳት ስለሆን ሥጋ አንበላም ትኅርምትም አለን" አሉት እርሱም ተዋቸው አላስገደዳቸውም እነዚያን ያበሰላቸውን ቆቆች አንሥቶ ሦስት ጊዜ እፍ አለባቸው ያን ጊዜም ድነው በረሩ ወደ ቦታቸውም ሔዱ እነዚያ መነኰሳትም ይህን ተአምር አይተው ደነገጡ "የእግዚአብሔር ቅዱስ ሆይ በደላችንን ይቅር በለን ብለው" ሰገዱለት እርሱም "የሁላችንንም በደል እግዚአብሔር ይቅር ይበለን" አላቸው።
❤ ከዚህም በኋላ ወደ አገራቸው ተመልሰው ያዩትን ይህን ድንቅ ተአምር ለሊቀ ጳጳሳቱ ነገሩት እርሱም ሰምቶ አደነቀ ወደ ንጉሡም እንዲህ ብሎ ላከ "በዘመናችን ጻድቅ ሰው መነኰስ ተገኝቷልና አንተም ና ሒደን በረከቱን እንድንቀበል" አለው። ወዲያውኑ ንጉሥ ከሠራዊቱ ጋር ተነሣ ሊቀ ጳጳሳቱም ከካህናቱ ጋር አባ መቃርስ ወዳለበት እነዚያ መነኰሳት እየመሩአቸው ሔዱ ወደርሱም ሲቀርቡ ወደ ብሔረ ሕያዋን ያደርሰው ዘንድ መልአክ አንሥቶ በክንፎቹ ተሽክመው ሲያርግም በአዩ ጊዜ "የእግዚአብሔር ቅዱስ ሆይ ባርከን የምንድንበትን አንዲት ቃል ንገረን" ብለው ጮኹ። እርሱም "ከሐሜትና ከነገር ሥራ አንደበታችሁ ይከልከል። ካህን ብዙ ባይማር ትዕቢትና መታጀር ባልመጣበት ነበር መነኵሴም ትኅርምት ባያበዛ ባልተመካም ነበር ርስበርሳችሁ ተፋቀሩ እግዚአብሔርም አድሮባችሁ ይኑር" አላቸው። ይህንንም ብሎ ዐረገ ከዐይናቸውም ተሠወረ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ መቃርስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #አባ_በጽንፍርዮስ፦ ይህም የከበረ መነኰስ በምስር አገር በወንዝ ዳር በአለች በሊቀ መላእክት በቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ መንኵሶ ታላቅ ተጋድሎን ሲጋደል ኖረ ስቀናች ሃይማኖትም ከእስላሞች መሳፍንት ጋር ተከራከረ የጌታችን ክርስቶስንም መለኮቱን ገለጠላቸው አምላክነቱንም አስረዳቸው ስለዚህም እስላሞች በአፈሩ ጊዜ ተቆጡ ጽኑዕ ሥቃይንም አሠቃዩት ራሱንም በሰይፍ ቆረጡ የሰማዕትነት አክሊልን በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም አባ በጽንፍርዮስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #አባ_አብራኮስ፦ ይህም ቅዱስ አባት ከላይኛው ግብጽ ነው። ዕድሜው ሃያ ዓመት ሲሆን መንኵሶ መልካም የሆነ ታላቅ ተጋድሎን ተጋደለ። ሰይጣንም ከእርሱ ጋር በመጣላት በተሸነፈና በደከመ ጊዜ በእርሱም ላይ ምንም ምን ማድረግ ባልተቻለው ጊዜ ፊት ለፊት ተገልጦ መጥቶ "እነሆ ከዚህ ዕድሜህ ሌላ ኀምሳ ዓመት ቀረህ" አለው። በዚህም ወደ ስንፍና ሊጥለው ወዶ ነው ሽማግሌውም እንዲህ ብሎ መለሰለት "አሳዘንከኝ እኔ ሌላ መቶ ዓመት እኖር ዘንድ ስለአሰብኩ ቸለል ብያለሁ አንተ እንዳልከው ከሆነ ከቀድሞው እጅግ አብዝቼ እጋደል ዘንድ ይገባኛል"። ከዚህም በኋላ ተጋድሎውንና በገድል መጸመድ አበዛ ሰባ ዓመታትም ከተጋደለ በኋላ በዚያች ዓመት ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ አብራኮስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የታኅሣሥ13 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለመቃርዮስ_ዘተመሥጠ_መልዕልተ። በቅድመ ጉቡአን ይንብብ ዘይብል ቃላተ። እምኢያእመሩ ትዕቢተ ወዘይመስሎ ትምክህተ። እመ ኢያፈድፈደ ካህን ትምህርተ። ወእመ ኢያብዝኀ ካዕበ መነኰስ ትኅርምተ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የታኅሣሥ_13።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ታኅሣሥ ፲፫ (13) ቀን።
❤ እንኳን #ለሊቀ_መላእክት_ለፈታሔ_ማሕፀን_ለቅዱስ_ሩፋኤል ለቅዳሴ ቤቱና ተአምር ላደረገበት ዓመታዊ መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ በዓል በሰላም አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ #የመላእክት_አለቃ_የከበረ_መልአክ_የቅዱስ_የሩፋኤል_የቅዳሴ_ቤት_ክብርና_ያደረገው_ተአምር፦ ከእስክድርያ ውጭ በደሴት የታነፀች ቤተ ክርስቲያኑ በከበረ ሊቀ ጳጳሳት ቴዎፍሎስ ዘመን በውስጧ ተአምር የተገለጸባት የከበረችበት፦ ይህም እንዲህ ነው ሀብታም ሴት ወደ ሊቀ ጳጳሳት አባ ቴዎፍሎስ መጥታ ሳለ ከእርሷ ጋርም ብዙ ሰው ነበር። ከባሏም የወረሰችው ብዙ ገንዘብ አላት በሊቀ ጳጳሳቱ ቤት አንጻር ያለውን ኮረብታ አስቆፈረች በጥቅምት ወር ዐሥራ ስምንት ቀን እንደጻፍን የወርቅ መዝገብ ተገለጠ።
❤ በዚያም ወርቅ ብዙዎች አብያተ ክርስቲያናትን አነፀ ከእርሳቸውም አንዲቱ የመላእክት አለቃ በሆነ በከበረ መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል በስሙ የታነፀች ይህች ናት። ሥራዋንም በፈጸመ ጊዜ እንደዛሬው በዚች ቀን አከበራት። ብዙ ምእመናንም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እያሉ ቤተ ክርስቲያኒቱ ፈጽማ ተናወጸች ያቺ ደሴት በታላቅ አንበሪ ጀርባ ላይ የቆመች ናትና። የሰዎች ብዛትም በከበደው ጊዜ ቤተ ክርስቲያኒቱን ያፈርሳት ዘንድ ሰይጣን አነሣሣው። ወደ ክብር ባለቤት እግዚአብሔርም በከበረ መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ስም ጮኹ ያን ጊዜ ይህ የከበረ ቅዱስ ሩፋኤል ያንን አንበሪ በጦሩ ወግቶ እንዲህ አለው "እግዚአብሔር አዞሃልና ከቦታህ ሳትናወጽ ጸጥ ብለህ ቁም"። አንበሪውም ጸጥ ብሎ ቆመ አልታወከም በውስጧም ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ ለሕሙማንም ፈውስ ሆነ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ሩፋኤል አማላጅነት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጳጒሜን 3 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "እስመ ለመላእክቲሁ ይኤዝዞሙ በእንቲአከ። ከመ ይዕቀቡከ በኵሉ ፍናዊከ። ወበእደሆሙ ያነሥኡከ"። መዝ 90፥10-11 ወይም 36፥4 የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 16፥16-25 ወይም ማቴ 10፥26-34።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@Zarsema =shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ታኅሣሥ ፲፪ (12) ቀን።
❤ እንኳን #ለኢትዮጵያኑ_ጻድቃን ታላቁ ዋልድባ ገዳምን ላቀኑ ምድራን እንደ መሶበ ወርቅ ከፍ አድርገው ላስባረከ አራዊተ እንስሳ ለሚታዘዝላቸው አንበሳን እንደ ፈረስ ሲያገለግላቸው ለነበረ ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ_ለዕረፍት_በዓል፣ #ለዳግማዊ_ቂርቆስ_ለቅድስት_ክርስቶስ_ሠምራ_ልጅ ብሔረ ብፁዓን ለገባበት መታሰቢያ ቀንና ከአጽማቸው ጠበል ላፈለቁት ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ቶማስ ለዕረፍት እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ #አባ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ፦ ለዚህም ቅዱስ የአባ ስም እስጢፋኖስ የእናቱ ስም አመተ ማርያም ነው። እነርሱም በዘመድ የከበሩ ደጎች ናቸው በአክሱም6 ምድርም ወለዱት በአደገ ጊዜም የቤተ ክርስቲያንን መጸሐፍት አስተማሩት አባቱና እናቱም በሞቱ ጊዜ ወደ ደብረ በንኰል ገዳም ወደ አባ መድኃኒነ እግዚእ ሒዶ የምንኵስና ልብስን ለብሶ በጾምና በጸሎት እየተጋደለ ኖረ። ፈጽሞ ከሻገተ ጎመን በቀር አይበላም የሚጠጣውም ውኃ ነው እህል በመፍጨትና ውኃ በቅዳት ሥራ መነኰሳትን ይረዳቸው ነበር።
❤ ዘመዶቹም ወደርሱ እየመጡ በአስቸገሩት ጊዜ ወደሌላ ቦታ ሔደ እግሮቹም እስቲያብጡ ድረስ በጾም በስግደት በመቆም ተጋደለ ከዚያም ወደሌላ በረሀ ሒዶ አርባ መዓልት አርባ ሌሊት ምንም ምን ሳይቀምስ ኖረ አንበሶችና ነብሮች የሚያስፈሩም አራዊት ሁሉ ወደርሱ በመምጣት ይሰግዱለታል የእግሮቹን ትቢያ ይልሱ ነበር። በአንዲት ዕለትም በጐዳና ሲጓዝ ታላቅ ወንዝን ውኃው መልቶ አገኘ መጽሐፍና እሳትም ከእርሱ ጋር ነበር ጸሎትንም አድርጎ ወደ ውኃው ገባ ውኃውም ዋጠውና ወደታች አወረደው በእግዚአብሔርም ኃይል ወደማዶ በጣለው ጊዜ መጽሐፉ ሳይደመሰስ እሳቱም ሳይጠፋ አገኘው።
❤ ሰይጣንም በሚያስፈራ አራዊት እየተመሰለ ይፈታተነው ነበር እርሱ ግን ፈጣሪውን በመታመን ልቡ የታሠረና የጸና ስለሆነ አይፈራም። እርሱም ሲጸልይ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደርሱ መጣ በምራቁም መላ ሕዋሳቱን ቀብቶ ኃይልን አሳደረበት ከዚያችም ዕለት ጀምሮ እግሮቹን የሚያሥር ሆነ። ማቅንም ለብሶ በየሌሊቱ ሁሉ ከውኃ ውስጥ በመግባት የዳዊትን መዝሙር አምስት ጊዜ ያደርሳል ቊጥር በሌለውም ግርፋት ጀርባውን ይገርፍ ነበር።
❤ አንበሶችም በበዓቱ አጠገቡ ይሰማራሉ እርሱም አካላቸውን ይሰፍራል ይለካል ቊስላቸውንም በጥቶ እሾህና አሜከላ ያወጣላቸዋል። ከዚህም በኋላ ብዙ ደቀ መዛሙርት ወደርሱ ተሰበሰቡ በተጋድሎም ተጠመዱ ከእርሳቸውም የመጀመሪያው አባ ዘሩፋኤል ነው። በአንዲትም ዕለት በገዳመ ለጋስ የሚኖር ከአባ ገብረ መስቀል ጋር ተገናኘ ከዚህም በፊት አልተያዩም ነበር የእግዚአብሔርንም ገናናነት ሲጨዋወቱ ዋሉ በራት ጊዜም ጸሎትን ሲያደርጉ የተዘጋጀ ማዕድ ወርዶላቸው ተመግበው እግዚአብሔርን አመሰገኑ።
❤ ከዚህም በኋላ በአንዲት ዕለት ከአንድ ገዳማዊ ጋር ተገናኘ እግዚአብሔርም ያደረገላቸውን ምሥጢር በሚነጋገሩ ጊዜ አባታችን አባ ሳሙኤል እንዲህ አለ "እንሆ እኔ በአርያም ቁሜ ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ጋር የአምላክን መንበር ሳጥን ዐሥራ ሁለት ዓመት ሆነኝ"። ለመቀደስም በሚገባ ጊዜ ኅብስትና ወይንን የተመላ ጽዋ ይወርድለታል። የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ውዳሴዋን ሲያነብ ክንድ ያህል ከምድር ወደ ላይ ከፍ ከፍ ይላል እመቤታችን ማርያምም ወደ ርሱ መጥታ የሚያበራ ዕንቊንና ንጹሕ ዕጣንን ሰጠችው።
❤ ፍልሰቱም ሲቀርብ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በክንፎቹ ተሸክሞ አወጣው ሰማያዊት ኢየሩሳሌምን ተድላዋን ሁሉ አሳየው ወደ ልዑል እግዚአብሔርም ዙፋን ፊት አቅርቦት ስሙን ለሚጠራ መታሰቢያውንም ለሚያደርግ ቃል ኪዳን ተቀበለ ወደ በዓቱም ሲመለስ ለደቀ መዛሙርቱ ነገራቸው ከዚህም በኋላ ታኅሣሥ12 ቀን በሰላም አረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ሳሙኤል ጸሎት ይማረን በረከቱ ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የታኅሣሥ12 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ #ዳግማዊ_ቂርቆስ_ዘብሔረ_ቡልጋ፡- የታላቋ እናት የቅድስት ክርስቶ ሠምራ የመጨረሻ ልጇ ነው። አባቱ ሠምረ ጊዮርስ የተባለ ጻድቅ ጻድቅ ሲሆን እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ዐሥራ አንድ ልጆችን ወልዳ በትዳሯ እጅግ የተመሰገነች ሆና ትኖር ነበር።
❤ ከዕለታት አንድ ቀን እንዲህ ሆነ ብፅዕት ቅድስት እናታችን ክርስቶስ ሠምራ ከአገልጋዮቿ መካከል አንዷ ምግባሯ የከፋ ነበርና በጣም ስላበሳጨቻት በዚያች አገልጋይ አፍ ውስጥ የእሳት ትንታግ ጨመረችባት፡፡ ያም የእሳት ትንታግ እስከ ጉሮሮዋ ዘለቀና አገልጋይዋን ገደላት፡፡ በዚህ ጊዜ ብጽዕት ክርስቶስ ሠምራ ደንግጣ ወደ ሌላ ክፍል ገባችና ኃጢአቷን ለእግዚአብሔር እየተናዘዘች እጅግ በጣም አዝና ጥፋቷ እንደ ጸጸታትና እግዚአብሔር አምላክም በእጇ የሞተችውን አገልጋይዋን ከሥጋዋ አዋሕዶ ቢያሥነሳላት ያላትን ገንዘብና ሀብት ትታ ባላት ዘመኗ ሁሉ አገልጋዩ እንደምትሆን ብጽዓት (ስዕለት) አደረገች፡፡ እግዚአብሔርም ጸሎቷን ሰምቶ አገልጋይዋን ከሞት አሥነሳለት፡፡ እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ "ልመናዬን ቸል ያላለ ቸርነቱንም ከእኔ ከባሪያው ያላራቀ አምላክ ይክበር ይመስገን" ብላ በታላቅ ምስጋና እግዚአብሔርን ካመሰገነች በኋላ አስቀድማ የገባችውን ቃል አስባ ልብሰ ምንኩስናዋን አዘጋጀች፡፡ ሕፃን ልጅዋንም ይዛ ወደ ደብረ ሊባኖስ ሄደች፡፡ ስትሄድም በልስላሴና በእንክብካቤ የኖረ እግሯ ከመንገዱ ብዛት ከእንቅፋቱም የተነሳ ፈለግ ሲያወጣ ሥጋውን እየቆረጠች ስትጥለው ደሟ መሬት ለመሬት እየፈሰሰ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ደረሰችና አስቀድማ ያዘጋጀችውን ልብሰ ምንኩስናዋን ለብሳ ከሴቶች ገዳም ገባች፡፡
❤ ቅድስት እናታችን ይዛው የተሰደደችውን የ3 ዓመቱ ሕፃን ግን ወንድ ስለሆነ ከደጅ ላይ አስቀምጣው ስለገባች ሕፃኑ አምርሮ አለቀሰ፡፡ በዚህም ጊዜ ከመነኮሳይያቱ አንዲቷ "ሕፃኑ ሲያለቅስ ከሚያድር" ብላ ወደ በአዓቷ ልታስገባው ስትል የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ሕፃኑን ነጥቆ ወስዶ በገነት አስቀመጠው፡፡ እርሱም ታኅሣሥ 29 ቀን ተወልዶ በ3 ዓመቱ ታኅሣሥ 12 ቀን ብሔረ ብፁዓን ገብቷል፡፡ እጅግ አሳዛኝ ገድሉ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ይገኛል፡፡ ምንጭ፦ ገድለ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራና መዝገበ ቅዱሳን።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለከ_ዘፈረይከ_ሕገ። #ሳሙኤል_ዘኮንከ ለአስካለ ወይን ሐረገ። በረድኤትከ ክፍለኒ ወእደ ሀሎከ ዐሪገ። ረድኤትከሰ ወለተ ከለባት መዘገ። ምስለ ክቡራን ከመ ተሀሉ ደርገ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የታኅሣሥ_12።
ታሕሳስ ፲፩ /11/በዚች ቀን የግብጽ ደቡብ ከሆነ ከመጺል አውራጃ ከሬስ ከተማ ሰዎች ወገን የሆነ ቅዱስ አባት አባ በኪሞስ አረፈ። እርሱም የአባቱን በጎች የሚጠብቅ ነበር ዕድሜውም 12 ዓመት ሲሆነው የእግዚአብሔር መልአክ በጐልማሳ አምሳል ተገለጠለትና ሒደን እንመነኵስ ዘንድ ትሻለህ አለው። ሁለቱም ተስማምተው ወደ አስቄጥስ ገዳም ተጓዙ አባ በኪሞስም በዚያ መነኮሰ። በዚያም ሃያ አራት ዓመታትን ኖረ። በአንድ ወቅትም አባ ሲኖዳ በራእይ ምሰሶ አየና ይህ ታላቅ ምሰሶ ምንድን ነው ብሎ ደነገጠ የእግዚአብሔርም መልአክ ተገልጦ ይህ አባ በኪሞስ ነው አለው።ከዚያችም ቀን በፊት ከቶ አላየውም ነበር በተገናኙም ጊዜ እርስበርሳቸው ሰላምታ ተሰጣጡ። ዳግመኛም በአንዲት ቀን በአንድነት ሲጓዙ የሞተ ሰው ራስ አገኙ አባ ሲኖዳም በበትሩ ነቅነቅ አደረገውና ምውት ሆይ ያየኸውን ትነግረንና ታስረዳን ዘንድ ተነሣ አለው በዚያን ጊዜ ነፍሱ ወደ ዐፅሙ ተመልሳ ሥጋ ለብሶ ተነሣና ሰገደላቸው በሲኦል የሚሠራውንም ሁሉ በየወገናቸውም በውስጧ የሚሠቃዩትን እርሱም አረማዊ እንደሆነ ነገራቸው። በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ያመኑ ትእዛዙን ግን ያልጠበቁ በአሕዛብ ሥራና በአረማውያን ርኵስት የኖሩ ከእኛ በታች የሚኖሩ ክርስቲያኖች አሉ አለ ቅዱሳኑም ተመልሰህ ተኛ አሉት ወዲያውኑ እንደ ቀድሞው ሆነ። ዕረፍቱም በቀረበ ጊዜ በሆድ ዝማ ሕመም ጥቂት ታመመ። ቅዱሳንን በአንድነት ወደርሱ ሲመጡ ባያቸው ጊዜ ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ።መላእክትም ወደ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት እያመሰገኑ አሳረጓት። መላ ዕድሜውም ሰባ ዓመት ሆነ 12 ዓመት በዓለም ውስጥ 58 ዓመት በምንኵስና ሥራ ኖረ። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
ታሕሳስ ፲ /10/በዚችም ቀን ቅዱሳን ተላስስና አልዓዛር በሰማዕትነት አረፉ። ይህም ተላስስ ከነነዌ አውራጃ ከባቢሎን ሰዎች ወገን ነው የፋርስ ንጉሥ ሳቦርም ይዞት ለእሳት ስገድ ለአማልክትም ሠዋ አለው ቅዱስ ተላስስም እኔስ ለፈጣሪዬ እግዚአብሔር እሰግዳለሁ ለእርሱም እሠዋለሁ እንጂ ለጣዖት አልሠዋም አለው ። ያስፈራውም ዘንድ የቅጣት መሣሪያዎችን አስመጣ እርሱ ግን አልፈራም መቶ ግርፋትንም ለረዥም ጊዜ እንዲገርፉት አዘዘ ከዚህም በኋላ ተላስስ ሆይ ከዚህ ሥቃይ እንድታርፍ ለአማልክት ሠዋ አለው እርሱም ፈጣሪዬ ስለሚጠብቀኝ ለእኔ ሥቃይህ አልታወቀኝም አለው። በዚያንም ጊዜ ሁለት መቶ ጊዜ ገረፉት በዐይኖቹም ውስጥ የብረት ችንካሮችን ተከሉ መናገርም እስከሚሳነው በነሐስ መክደኛ ሸፍነው ደበደቡት ራሱንም በሰይፍ ቆረጡ። ከዚህም በኋላ አልዓዛርን አቀረቡት ንጉሥ ሳቦርም ለአማልክት ሠዋ አለው ለረከሱ አማልክቶቹም መሠዋትን እምቢ ባለው ጊዜ ወዲያውኑ ወደ እሳት ወረወረው ያማረ ምስክርነቱንም ፈጸመ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕታት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
ሐዋርያው ቅዱስ ማትያስ
ማትያስ ማለት ምትክ ማለት ነው። ሐዋርያው ማትያስ ጌታን በሸጠው በአስቆሮቱ ይሁዳ ምትክ የተሾመ ሐዋርያ ነው፡፡ በቤተክርስቲያን ፀሐፊነቱ የታወቀው አውሳብዮስ ቅዱስ ማትያስ ከሰባው አርድእት አንዱ እንደነበር ጽፏል። ይህም ሐዋርያ ሰውን ወደሚበሉ ሰዎች አገር ወንጌልን ይሰብክላቸው ዘንድ በሔደ ጊዜ ወዲያውኑ ይዘው ዐይኖቹን አውልቀው አሠሩት ምግባቸው የመጻተኛ ሰው በድን ስለሆነ ልማዳቸውም እንዲህ ነው።
መጻተኛ ሰው ሲይዙ ዐይኖቹን አውልቀው በእሥር ቤት ያኖሩታል ። የያዙበትንም ቀን ይጽፋሉ ሠላሳ ቀንም እስቲፈጸም ሣር ያበሉታል ከዚያ በኋላም አውጥተው አርደው ይበሉታል ።
ሐዋርያ ማትያስም ታሥሮ ሳለ ሠላሳው ቀን ሳይፈጸም በጌታችን ትእዛዝ ሐዋርያው እንድርያስ ወደርሱ ደረሰ የአገሩ ሰዎች የሚሠሩትን ክፉ ሥራ አይቶ አደነቀ እጅግም አዘነ እሥረኞችንም ሁሉ አውጥቶ የአገር ሰዎች ወደማያገኙአቸው ቦታ አኖራቸው።
እነርሱ ግን ሁለቱ ሐዋርያት እንድርያስና ማትያስ ተገለጡላቸው የአገሩም ሰዎች ያዙአቸው በአንገታቸውም ገመድ አስገብተው እስከ ሦስት ቀን በአገሩ ጥጋጥግ ጐተቱአቸው ሐዋርያት ስለዚያች አገር ሰዎች ስለድኅነታቸው ወደ እግዚአብሔር ጸለዩ ያንጊዜ ከወህኒ ቤቱ ምሰሶ ሥር ውኃን አፈለቁ ውኃውም ከፍ ከፍ ብሎ በሀገር ውስጥ እሰከሚአጥለቀልቅና ወደ ሰዎች አንገት እስከ ደረሰ እየበዛ ሔደ።
በተጨነቁና የሕይወታቸውን ተስፋ በቆረጡ ጊዜ ወደ ሐዋርያት መጡ በፊታቸውም ኃጢአታቸውን እየተናዘዙ አለቀሱ ሐዋርያትም በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እመኑ እናንተም ትድናላችሁ አሉአቸው እሊያ ሁሉም በክብር ባለቤት በጌታችን አመኑ።
ሐዋርያትም አስተማሩአቸው ገሠጹአቸውም የአንድነትን የሦስትነትን የመድኃኒታችን ሰው የመሆኑን ምሥጢር ገለጡላቸው ደግሞም ይህን የአራዊት ጠባይ ጌታችን ከእነርሱ ያርቅ ዘንድ ጸለዩላቸው ከዚህ በኋላ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቋቸው ያ የአውሬ ጠባይ ከእርሳቸው ርቆ ሰው የሚመገበውን የሚመገቡ የዋሆች ቅኖች ሆኑ።
ኤጲስቆጶሳትን ቀሳውስትንና ዲያቆናትንም ሾሙላቸው በቀናች ሃይማኖትም እያጸኑአቸውና እያስተማሩአቸው ሠላሳ ቀኖች ያህል ከእሳቸው ጋራ ኖሩ ከዚያም ወጥተው ሔዱ የአገር ሰዎች ግን በሌላ ጊዜ ወደ እነርሱ እንዲመለሱላቸው ሐዋርያትን ለመኑአቸው።
ሐዋርያ ማትያስ ግን ወደ ደማስቆ ከተማ ገብቶ በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰበከ። የአገርም ሰዎች ይዘው በብረት ዐልጋ ላይ አስተኝተው በበታቹ ስድስት ቀን ስድስት ሌሊት እሳት አነደዱ ሊአዩትም ወደርሱ በመጡ ጊዜ ፊቱ እንደ ፀሐይ ሲበራ አገኙት ሥጋውንም ሆነ የራስ ጠጉሩን ወይም ልብሶቹን ምንም ምን እሳት አልነካውም እጅግም አደነቁ። አሁንም ዳግመኛ ሃያ አራት ቀን እስኪፈጸም ድረስ ሐዋርያ ቅዱስ ማትያስ በተኛበት በዚያ የብረት ዐልጋ በታች እሳትን አነደዱ።
ከዚህ በኋላም ከእሳቱ ባወጡት ጊዜ ያለ ምንም ጉዳት ጤነኛ ሆኖ አገኙት እጅግም አደነቁ በክብር ባለቤት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ። እርሱም በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቃቸው ካህናትንም ሾመላቸው በቀናች ሃይማኖትም እያጸናቸው ከእርሳቸው ጋራ ኖረ።
ከዚያም ተነሥቶ ስሟ ፊላዎን ወደሚባል ከአይሁድ አገሮች ወደ አንዲቱ ሔደ በዚያም በጎ ዕረፍትን አረፈ ሥጋውንም በመልካም ቦታ አኖሩ ከሥጋውም በሽተኞችን በመፈወስ ታላላቅ የሚያስደንቁ ተአምራት ተገለጡ። ልዩ የሆነች በረከቱም ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ትኑር አሜን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ የ/መ/ገ/ጽ/ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ሰ/ት/ቤ እና መጽሐፈ ስንክሳር
ታሕሳስ ፱ /9/በዚች ቀን ያለ ደም መፍሰስ ታማኝ የሆነ ቅዱስ አባት አባ በአሚን በሰማዕትነት አረፈ ። እርሱም በደቡብ ግብጽ በእስሙናይን አውራጃ ለሀገረ ቴርሳ አቅራቢያ ከሆኑ ከሐፂብ ተወላጆች ወገን ነው ለአንድ ባለጸጋም በጅሮንድ ሆኖ ሳለ ስለ ንጽሕናውና ስለ ቅድስናው በሁሉ ዘንድ ተወዳጅ ሆነ የባለ ጸጋውም ሚስት አባ በአሚንን እጅግ የምትወደውና የምትተማመንበት ሆነች ። እርሱ ግን የዚህን ዓለም ፍጻሜ አሰበ የባለጸጋውንም አገልግሎት ትቶ ወደ ገዳም ሒዶ መነኰሰ ባለጸጋውም መሔዱን በሰማ ጊዜ እጅግ አዘነ ሚስቱንም ይዞ አባ በአሚን ወዳለበት በአንድነት ሔዱ ወደ እርሳቸው እንዲመለስም ለመኑት እንዲህም አሉት ከአንተ እንለይ ዘንድ ከቶ አንችልም ስለዚህ አንተውህም አሉት ። አባ በአሚንም እኔ ራሴን ብፅዓት አድርጌ ለእግዚአብሔር ሰጥቻለሁ እኮን አላቸው ይህንንም ሲሰሙ ከእርሱ በመለየታቸው እያዘኑ ተትውት ተመለሱ ። ከዚህም በኋላ ስለ ጌታችን ብዙ መከራዎችን ተቀበለ። ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፈቃድ ዲዮቅልጥያኖስ ያሠራቸውን እሥረኞች ሁሉ ቆስጠንጢኖስ እንዲፈቷቸው አዘዘ ጌታችንም ለአባ በአሚን ተገለጠና ከሰማዕታት ጋር እንደቆጠረው አስረዳው። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
ታሕሳስ ፰ /8/በዚች ቀን የእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባት አባ ያሮክላ አረፈ እርሱም ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ዐሥራ ሦስተኛ ቊጥር ነው። የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ አስቀድሞ አረማውያን ነበሩ በወለዱትም ጊዜ የአረማውያንን ትምህርት መጻሕፍቶቻቸውንም ሁሉ አስተማሩት። ከዚህም በኋላ አምነው ተጠመቁ ይህን ልጃቸውንም የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት አስተማሩት የሐዋርያትንም መጻሕፍት አጠና ሊቀ ጳጳሳት ድሜጥሮስም ዲቁና ሾመው ከዚህም በኋላ በእስክንድርያ አገር ቤተ ክርስቲያን ቅስና ሾመው መንጋውንም በመልካም አጠባበቅ ጠበቀ። ሥራውንም ፈጸመ የቤተ ክርስቲያንንም ሕግ ጠንቅቆ አወቀ። አባት ድሜጥሮስም በአረፈ ጊዜ ይህን አባት መርጠው በእስክንድርያ አገር ላይ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት እርሱም ክብር ይግባውና የክርስቶስን መንጋዎች በቀናች ሃይማኖት አጽንቶ ጠበቀ ከአረማውያንም ብዙዎችን ክብር ይግባውና ክርስቶስን ወደ ማመን መልሶ የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃቸው። ለቅዱስ ዲዮናስዮስም ለምእመናን እንዲፈርድ ሥልጣን ሰጠው እርሱ ግን ዓላውያንን ወደ ቀናች ሃይማኖት እስከሚመልሳቸው ድረስ ያስተምራቸውና ይገሥጻቸው ነበር። በወንጌላዊ ማርቆስ ወንበርም ዐሥራ ሦስት ዓመት ኑሮ በሰላም አረፈ። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
ታሕሳስ ፯ /7/በዚች ቀን በአባ መቃርስ ገዳም በደብረ ሲሐት የሚኖር አባ ዳንኤል አረፈ። ይህም አባ ዳንኤል ስሟን እንጣልዮስ አሰኝታ የነበረች ንግሥት በጥሪቃን የገነዛት ነው እርሷም ከሞቷ በኋላ እንጂ ሴት እንደሆነች አልታወቀችም ነበር። በአንዲት ቀንም ወደ እስክንድርያ አገር ከረድኡ ጋር ሲጓዝ ስሙ ምህርካ የሚባል እብድ አገኘ ብዙ እብዶችም ይከተሉታል ለአገር ሰዎችም በእውነት ያበደ ይመስላቸው ነበር። አባ ዳንኤልም እጁን ይዞ ወደ ሊቀ ጳጳሳቱ ወስዶ ትሩፋቱን ተጋድሎውን ነገረው እንዲነግራቸውም በአማሉት ጊዜ ከዝሙት ጦር በመሸሽ ራሱን እብድ እንዳስመሰለ ነገራቸው ሰምተውም እግዚአብሔርን አመሰገኑት። ዕረፍቱም በቀረበ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ነገረው ጥቂት ጊዜም ታመመ ክብር ይግባውና ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጸለየና በሰላም አረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ጻድቅ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
ታህሳስ 6 ቅድስት አርሴማ(ቅዳሴ ቤቷ)
እናታችን ቅድስት አርሴማን በምን እንመስላታለን? እርሷ በአድማስ ላይ ተቀምጦ እንደሚያበራ እንቁ ናትና ክብሯ ብዙ ነው።
መድኃኒታችን ክርስቶስ በወንጌል እንዳለው "በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሠወር አይቻላትምና"(ማቴ. ፭፥፲፩) የሰማዕቷ ሕይወት በፊታችን እንደ ብርሃን ተገልጦ ይታያል ቅድስት አርሴማ እንደ ልጅ ወላጆቿን በመታዘዝ ደስ ያሰኘች ቡርክት ናት ቅድስት አርሴማ ይህ ቀረሽ የማይሏት ውብ ናት።
ቅድስት አርሴማ ድንግል ናት ቅድስት አርሴማ ባሕታዊት ጻድቅ ናት ቅድስት አርሴማ ኃያል ሰማዕት ናት ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ፦ አበው በትውፊት እንደ ነገሩን ቅዱሱ ጐርጐርዮስ የታላቋ ሰማዕት ቅድስት አርሴማ ትልቅ ወንድም ነው በዜና ሰማዕታት ተጽፎ እንደሚገኘው በዚያ የመከራ ዘመን ቅዱስ ጐርጐርዮስ ሦስት ኃላፊነቶች ነበሩበት፦
፩.ቅድስት አርሴማን ጨምሮ ደናግሉን ማጽናት
፪.ትምሕርተ ቤተ ክርስቲያንን በሚገባ ማጥናት
፫.የሚመጣውን መከራ ለመቀበል ራሱን ማዘጋጀት ቅዱሱ ሦስቱንም ኃላፊነቶች በሚገባ በመወጣቱ ከራሱ አልፎ ለሌሎቹ አርአያ መሆን ቻለ ያቺን ንጽሕት አርበኛ ቅድስት አርሴማንም አጽንቶ የደናግሉ መሪ አደረጋት።
መከራው ገፍቶ እስከ መጣበት ጊዜ በአንድ የደናግል ገዳም ውስጥ ሆነው ይጸልዩ፣ ይጾሙ፣ ገዳማዊ ሥራንም ይሠሩ ነበር ለዚህም ነው ቅድስት አርሴማና ቅዱስ ጐርጐርዮስን ጻድቃን የምንላቸው በኋላ ግን ማኅደረ ሰይጣን ዲዮቅልጢያኖስ በመልኳ ተማርኮ ቅድስት አርሴማን ካላገባሁ በማለቱ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ድንግሏን አርሴማን ጨምሮ ክርስቲያኖችን ይዞ ወደ አርማንያ ተሰደደ በአርማንያም በአንድ ገዳም ውስጥ ተደብቀው በጾምና በጸሎት ለጥቂት ጊዜ ቆዩ ነገር ግን ረሃብ ፈጃቸው የሚላስ የሚቀመስ ነገር በአካባቢው ባለ መኖሩ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ወደ ከተማ ለመውጣት ተገደደ በዚያም በድርጣድስ ቤተ መንግሥት ውስጥ ባርነት ተቀጠረ በሚያገኛት ገንዘብም ወገኖቹን ይረዳ ነበር መከራው ግን አለቀቃቸውም።
ርጉም ዲዮቅልጢያኖስ ቅዱሳኑ ወደ አርማንያ መሔዳቸውን ስለ ሰማ ይዞ እንዲልክለት ድርጣድስን ላከው ድርጣድስ ግን ቅድስት አርሴማን ባያት ጊዜ ከውበቷ የተነሳ መታገስ ባለመቻሉ "ካላገባሁሽ" አላት ድንግሊቱ ግን "እኔ የክርስቶስ ሙሽራ ነኝ አይሆንም" አለችው። ሊያስፈራራት ሞከረ ዓይኗ እያየ ደናግሉን ጨፈጨፋቸው አልሳካልህ ቢለው በአደባባይ በግድ ሊያገባት ቢሞክር እጁን ጠምዝዛ በሰው ሁሉ ፊት መሬት ላይ ጣለችው። እጅግ ስላፈረ አስገረፋት፣ አሰቃያት፣ ዓይኗንም አወጣ። በመጨረሻም አንገቷን አስቆርጦ ከሰማዕታቱ ጋር ተራራ ላይ ጣላት ከነገር ሁሉ በኋላ ድርጣድስና ባለሟሎቹ ለአደን በሔዱበት ርኩስ መንፈስ ወደ አውሬነት (እሪያነት) ቀየራቸው።
የንጉሡ እንስሳ (አውሬ) መሆን በአርማንያ ታላቅ ድንጋጤን ፈጠረ የንጉሡ እኅት ስታለቅስ በራእይ "ለእመ ኢያዕረግምዎ ለጐርጐርዮስ አልብክሙ ድኂን - ጐርጐርዮስን ከተቀበረበት ካላወጣችሁት አትድኑም" አላቸው ወዲያውም ቆፍረው አወጡት ቅዱሱ እንደ ወጣ ዕረፍትን አልፈለገም።
ለአሥራ አምስት ዓመታት ቀባሪ አጥቶ የተበተነውን የቅድስት አርሴማንና የሰማዕታቱን አጽም ሰብስቦ በክብር አኖረው ድርጣድስና ባለሟሎቹንም ወደ በርሃ ሒዶ ፈወሳቸው የሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ አጽም በአሥራ አራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከሌሎች ሰማዕታት አጽም ጋር ኢትዮጵያ እንደ መጣ አባቶቻችን በትውፊት ነግረውናል ለዚህም ነው ቡርክቷ እናታችን ከሌሎች ሃገራት ለይታ ለኢትዮጵያውያን ልዩ ፍቅር ያላት።
በዋናው ገዳሟ (ወሎ /ኩላማሶ/ ስባ ውስጥ የሚገኝ ነው።) ጨምሮ ስሟ በተጠራበት ሁሉ ኃይልን ታደርጋለችና ከሰማዕቷ ጋር የመንፈስ እናቷን ቅድስት አጋታን ልናስባት ይገባናል ይህች እናት እመ ምኔት ስትሆን ቅድስት አርሴማን ታስተምራት፣ ታጸናት፣ ከጐኗም ትቆምላት ነበር።
ረሃቧን፣ ጥሟን፣ ስደቷን፣ መከራዋንም ሁሉ አብራት ተሳትፋለች በፍጻሜውም አብራት ተሰይፋለች ይህች ዕለት ለቅድስት አርሴማና ለተከታዮቿ ሰማዕታት የፍልሰትና የቅዳሴ ቤት መታሰቢያ ናት።
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
ስርአተ ማህሌት ዘታህሳስ አርሴማ
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ (ሥርዓተ ነግሥ) ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሉ አለም፤በአሐቲ ቃል።
ሰላም ለአብ ገባሬ ኩሉ ዓለም፤ለወልድ ሰላም ወለመንፈስ ቅዱስ ሰላም፤ለማርያም ሰላም ወለመላእክት ሰላም፤ሰላም ለነቢያት ወለሐዋርያት ሰላም፤ለሰማዕታት ሰላም ወለጻድቃን ሰላም።
ዚቅ
አርሴማኒ ተወፈየ ሠለስተ ለቤተክርስቲያን ሃይማኖት ወተስፋ ወፍቅር ሃይማኖት ዲበ አብ ወተስፋ ዲበ ወልድ ተፈጻሜተ ፍቅር ዘመንፈስ ቅዱስ፤እንዘ ይብል አሐዱ እግዚአብሔር፤አንሰ አስተብቋዕክዎ
ዚቅ ዓዲ
፩ዱ አብ ቅዱስ ፩ዱ ወልድ ቅዱስ፤፩ዱ ዉእቱ መንፈስ ቅዱስ ዘአድኃኖሙ ለሰማዕት።
መልክዐ ሚካኤል
ሰላም ለአዕጋሪከ በክነፈ ነፋስ እለ ይረውፃ፤አብያተ ግፉአን የሐውፃ፤ሚካኤል የዋህ ወኅሩም እምነ ዓመፃ፤ተኖለው አዕጋርየ ለፍኖተ ስህተት እምዳኅፃ፤ወኀበ ምድረ ጽድቅ ምርሐኒ ከመ እብላዕ ሠርፃ
ዚቅ
ይሔውፅዋ መላእክት አንተ በሰማያት፤ይሔውፅዋ መላእክት እስመ ማኅደረ መለኮተ ዖድክዋ ዖድክዋ ዖድክዋ ወርኢኩ ስነ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ምስእል ወምስጋድ፤ወምለት ሥራየ ኀጢአት ይዕቲ ቅድስት ደብተራ
ዘጣዕሙ
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤መሠረተ ህይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።
ዚቅ፦
አክሊሎሙ አንተ ለሰማዕት ሠያሜሆሙ ለካህናት ወልደ እግዚአብሔር
ዓዲ ዚቅ፦
ወመሠረቱ ወመሠረቱ ለዓለም አንቲ፤ዕጔለ አንበሳ ዕጔለ አንበሳ በከርሥኪ ፆርኪ፤እምአንስት ቡርክት አንቲ፤ለመሠረትኪ የኃትዎ ዕንቊ ክቡር፤አንቲ ዉእቱ መንፈሳዊት ሀገር ንጽሕት ፀምር፤ዘኃረያ ፀባዖት አማኑኤል።
መልክአ አርሴማ
ሰላም ለዝክረ ስምኪ በሰንዱነ ኪዳን ጥብሉል፤ወለስዕርትኪ ሰላም ዘፅርየተ ሕብሩ ፅዱል፤ሥርጉት ትዕግሥት አርሴማ ወዑፅፍተ ሐዲስ ገድል፤ይጸሐፍ በልሳንየ ወዘበእንቲአየ ቃለ፤መፆር ትርጓሜ ረቂቅ ኃይልኪ ፊደል
ዚቅ
አርሴማ እምነ በሀ፤ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሥርጉት በስብሐት፤ዓረፋቲሃ ዘመረግድ ሥርጉት በስብሐት፤ወማኅፈዲሃ ዘቢረሌ ሥርጉት በስብሐት፤ እምስነ ገድሎሙ ለሰማዕት ሥርጉት በስብሐት፤ታቦተ ሕጉ ለንጉሥ ዐቢይ ሥርጉት በስብሐት፤እንተ ክርስቶስ መሠረትኪ ፤ ፀሐየ ጽድቅ ያበርህ ለኪ፡፡
ወረብ፦
እንተ ክርስቶስ መሠረትኪ ፀሐየ ጽድቅ ያበርህ ለኪ ፀሐየ ጽድቅ/፪/
ታቦተ ሕጉ ለንጉሥ ዐቢይ አርሴማ ሰማዕት/፪/
መልክአ አርሴማ
ሰላም ለአዕጋርኪ...
ዚቅ
ሃሌ ሃሌ ሉያ ቤተክርስቲያን መርዓቱ ለአልፋ ታቦቱ መኃትዊሃ ፯ቱ ከዋክብቲሃ ሰማዕታት እሙንቱ
ወረብ፦
ቤተክርስቲያን መርዓቱ ለአልፋ ታቦቱ ቤተክርስቲያን/፪/
መኃትዊሃ ሰብዓቱ ከዋክብቲሃ ሰማዕታት እሙንቱ/፪/
መልክአ አርሴማ
ሰላም ለበድነ ሥጋኪ ዘተሠርገወ ብናሴ፤ወለግንዘትኪ ዘኮነ በእደ መላእክት ሕዝበ ቅዳሴ፤አርሴማ ቅድስት በስብሐት ወበዉዳሴ፤ለፀላእትየ በባሕረ እሙቅ ድምሳሴ፤ያስጥሞሙ ኪዳንኪ ወኃይልኪ ሙሴ።
ዚቅ
በሐ በልዋ ተሳለምዋ፤ዕግትዋ ለጽዮን ወሕቀፍዋ፤ደዩ ልበክሙ ውስተ ኃይላ፤እንተ ተሐንጸት በስሙ፤ወተቀደሰት በደሙ፤ወተአትበት በዕጸ መስቀሉ፤ጌሡ ኃቤሃ እስመ ሃይለ እግዚአብሔር ላዕሌሃ።
ወረብ
"በሐ በልዋ"/፪/ ተሳለምዋ/፪/
ዕግትዋ ለጽዮን ወሕቀፍዋ ደዩ ልበክሙ ውስተ ሃይላ ለቤተክርስቲያን/፪/
መልክአ አርሴማ
ሰላም ለፍልሰተ ሥጋኪ በቃለ ፈጣሪ ዘተቀደሰ፤ወንብረተ ዝንቱ ዓለም እንተ ኢኀሠሠ፤አርሴማ ብፅዕት ከመ ኢይርአይ ተፅናሰ፤ሴስይኒ እመዝገብኪ እስመ ኢይክል ሐሪሰ፤ወእስእለኪ ተሀብኒ ሐፍሰ።
ዚቅ
ብፅዕት ከርሥ እንተ ፆረትኪ፤ወብፁዓት አጥባት እለ ሐፀናኪ፤ ተክዕወ ሞገስ እምከናፍሪኪ
ወረብ፦
ብፅዕት ከርሥ ብፅዕት ከርሥ እንተ ፆረተኪ አርሴማ ቅድስት/፪/
ወብፁዓት አጥባት እለ ሐፀናኪ ተክዕወ ሞገስ እምከናፍሪኪ/፪/
ምልጣን
አርሴማ ቅድስት ሥርጉት በሃይማኖት ወበመንፈስ ቅዱስ ክልልት ከመ ቂርቆስ ሕጻን ኢያፍርኃ ነበልባለ እሳት እስመ አጽንዓ ኃይለ አማኑኤል ጸባዖት
አመላለስ፦
እስመ አጽንዓ ኃይለ አማኑኤል እስመ አጽንዓ/፪/
ኃይለ አማኑኤል ጸባዖት/፬/
ወረብ፦
አርሴማ ቅድስት ሥርጉት በሃይማኖት ወበመንፈስ ቅዱስ ክልልት/፪/
ከመ ቂርቆስ ሕጻን ኢያፍርኃ ነበልባለ እሳት/፪/
እስመ ለዓለም ዘሰንበት
ይቤ ዳዊት በመዝሙር ፤መሠረታቲሀ ውስተ አድባረ ቅዱሳን፤ወካዕበ ይቤ ቀደሰ ማህደሮ ልዑል ፤ ወይቤ ዝየ አኃድር እስመ ኃረክዋ፤ ማ፦ እግዚአ ለሠንበት በከርሣ ተፀውረ ፤ሰማየ ወምድር ዘውእቱ ፈጠረ
🍀🍀🍀
መዝሙር
🌺🌺🌺
ሠርዓ ሰንበት ለሰበእ ዕረፍተ፤ለእለ በሰማይ ወለእለ በምድር ለእለ በባሕር ወለእለ በየብስ ፣ሠርዓ ሰንበት ለሰበእ ዕረፍተ፤ለአበዊነ ነቢያት ወለሐዋርያት ሠርዓ ሰንበት ለሰበእ ዕረፍተ፤ለጳጳሳት ወለቀሳውስት ለዲያቆን ወለመነኮሳት ሠርዓ ሰንበት ለሰበእ ዕረፍተ፤ለጻድቃን ወለኃጥአን ለሙታን ወለሕያዋን ሠርዓ ሰንበት ለሰበእ ዕረፍተ፤ሰንበቱሰ ለክርስቶስ ይእቲ ወማኅደረ ስሙ ለልዑል
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
ሥርዓተ ዋዜማ ዘታህሳስ በዓለ ቅድስት አርሴማ
🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀
በ፩
ሃሌ ሉያ ሐነጽዋ ወሣረርዋ ለቤተክርስቲያን፤ከመ ትኩን አርአያ ዘበሰማያት፤ወከመ ትኩን ምሥተስራየ ኃጢአት፤ዳዊትኒ ይቤ ዛቲ ይእቲ ምዕራፍየ ለዓለም።
ምልጣን
ወከመ ትኩን ምሥተስራየ ኃጢአት፤ዳዊትኒ ይቤ ዛቲ ይእቲ ምዕራፍየ ለዓለም፤ዛቲ ይእቲ ምዕራፍየ ለዓለም።
አመላለስ
ዛቲ ይእቲ ምዕራፍየ ለዓለም/፪/
ዛቲ ይእቲ ምዕራፍየ ለዓለም/፬/
በ፭ ለእግዚአብሔር ምድር በምልዓ
እንተ ተሐንጸት በስሙ፤ወተቀደሰት በደሙ፤እንተ ተሐንጸት በስሙ።
እግዚአብሔር ነግሠ
አመ የሐንፃ እግዚአብሔር ለጽዮን፤ወይቄድሳ ለኢየሩሳሌም፤ኢየሱስ ክርስቶስ ምስለ መላእክቲሁ ዖደ፤በደሙ ቀደሳ፤በዕጸ መስቀሉ ዓተባ።
ይትባረክ፦
ተለዓለ ቃሎሙ ለእለ ይሴብሑኪ፤ኢይትዓጸው አናቅጽኪ።
ሰላም
ሐነጽዋ ለቤተክርስቲያን፤ወሣረርዋ በመንፈስ ቅዱስ፤ከመ ትኩን አርአያ ዘበሰማያት፤ከመ ታድኅነነ እምዕቶነ እሳት፤ተሀበነ ፍሥሐ ጽድቅ፤ወሰላመ በዲበ ሰላም፤ዘይክል ኲሎ ወአልቦ ዘይሰዓኖ።
አመላለስ፦
ተሀበነ ፍሥሐ ጽድቅ ወሰላመ በዲበ ሰላም/፪/
ዘይክል ኲሎ ወአልቦ ዘይሰዓኖ/፬/
ወቦ ዘይቤ ሰላም፦
በፍስሀ ወበሰላም ቦኡ ሰማእት ሀገር ቅድስት በገድሎሙ ወበትእግስቶሙ እምጸሀይ ያበርህ ገጾሙ በሠላም ቦኡ ሀገሮሙ
አመላለስ፦
እምጸሀይ ያበርህ ገጾሙ/፪/
በሠላም ቦኡ ሀገሮሙ/፬/
