cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ታሪክ ወጥበብ ዘኢትዮጵያ

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدلم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
222
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

ስንቶቻችን ለሞዐ ተዋህዶ ፊርማችንን አስቀምጠናል! https://chng.it/4CmF2rYk
إظهار الكل...
Sign the Petition

Prevent Cultural and Religious Based Genocide of Ethiopian Orthodox Christians.

የካቲት 16 ኪዳነ ምህረት ‹ ኪዳን › የሚለው ቃል ‹‹ ተካየደ – ተዋዋለ ፤ ቃል ኪዳን ተጋባ ፤ ተማማለ ›› ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲኾን ፣ ትርጕሙም ኪዳን፣ ውል ፣ መሐላ ፣ ቃል ኪዳን ፣ የውል ቃል ማለት ነው /ዘዳ.፳፱፥፩፤ ኤር.፴፩፥፴፩-፴፫፤ መዝ.፹ ፰፥፫/፡፡ በሌላ በኩል ኪዳን የጸሎት ስም ሲኾን፣ ጌታችን ሞትን ድል አድርጎ ከተነሣ በኋላ፣ ከማረጉ በፊት ለሐዋርያት ያስተማራቸው ጸሎት ኪዳን ይባላል፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ ከወዳጇ ከጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የምሕረት ቃል ኪዳን (ውል ፣ ስምምነት) የተቀበለችበት ዕለት (የክብረ በዓል ስም) ደግሞ ኪዳነ ምሕረት ይባላል፡፡ በየዓመቱ የካቲት ፲፮ ቀን የምናከብረው ይህ በዓል እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በጎልጎታ በልጇ በመቃብር ላይ ኾና ‹‹ ኦ ወልድየ ወፍቁርየ እስእለከ በእንተ ዘተሰባእከ እምኔየ ወበማኅፀንየ ዘጾረተከ፤ ልጄ ወዳጃ ሆይ ከሥጋዬ ሥጋ ፣ ከነፍሴ ነፍስ ነሥተህ ሰው ስለመኾንህ ፤ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ስለቻለችህ ማኅፀኔ ፤ ከአንተ ጋር ከአገር ወደ አገር ስለመሰደዴ መጥተህ ልመናዬን ትሰማኝ ዘንድ እለምንሃለሁ ›› እያለች ስትጸልይ ጌታ እልፍ አእላፍ መላእክቱን አስከትሎ ወደእርሷ መጥቶ ‹‹ ሰላም ለኪ ማርያም እምየ ፤ እናቴ ማርያም ሰላም ላንቺ ይኹን! እንዳደርግልሽ የምትለምኚኝ ምንድን ነው? ›› አላት፡፡ እመቤታችንም በስሟ የሚማጸኑትንና መታሰቢያዋን የሚያደርጉትን፣ ለችግረኛ የሚራሩትን፣ ቤተ ክርስቲያን የሚያንጹትን ፤ ዕጣን ዘይትና መብአ ለቤተ ክርስቲያን የሚሰጡትን ፤ ለእመቤታችንና ለሃይማኖታቸው ካላቸው ፍቅር የተነሣ ልጆቻቸውን በስሟ የሰየሙትን ዅሉ እንዲምርላትና ከሞተ ነፍስ እንዲያድንላት ጠየቀችው፡፡ ጌታችንም ‹‹ ይህን ዅሉ እንዳደርግልሽ መሐልኩ ለኪ በርእስየ ወበአቡየ ወበመንፈስ ቅዱስ ሕያው፤ በራሴ፣ በአባቴ እና በመንፈስ ቅዱስ ማልኩልሽ›› ብሎ ቃል ኪዳን ገብቶላት ወደ ሰማይ ዐርጓል፡፡ ለዚህም ነው ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ በቅዳሴው ‹‹ … ዳግመኛም በእናትህ በማርያም ተማፅነናል፤ ይህችውም አንተን በመውለድ እመቤታችንና የባሕርያችን መመኪያ ናት፡፡ አንተ ‹ መታሰቢያሽን ያደረገ ፣ ስምሽንም የጠራ ፣ የዘለዓለም ድኅነትን ይድናል› ብለሃታልና …፤›› በማለት የሚማጸነው፡፡ በተአምረ ማርያም መጽሐፍ እንደተመዘገበው በዚህ ዕለት የሚታሰቡ ሁለት ተአምራት አሉ፤ ከእነዚህም አንደኛው የስምዖን ታሪክ ነው፡፡ ስምዖን የሚባል እንግዳ ተቀባይ ደግ ሰው ነበር፡፡ ሰይጣን ለምቀኝነት አያፍርምና ከዕለታት አንድ ቀን በእንግድነት ከቤቱ ገብቶ ‹‹ልጅህን አርደህ ካላበላኸኝ ሌላ ምግብ አልበላም›› አለው፡፡ በዚህ ጊዜ ስምዖን ሲያወጣና ሲያወርድ ቆየና ‹‹አብርሃም ልጁን ሰውቶ ነው የእግዚአብሔር ሰው የተባለው ›› በማለት፣ ‹‹ የእግዚአብሔርን እንግዳ›› ላለማሳዘን ሲል ልጁን አርዶ አቀረበለት፡፡ እንግዳ መሰሉ ሰይጣንም ሥጋውን ቅመስልኝ ብሎ ግድ አለው፡፡ ስምዖንም (በላዔ ሰብእ) አርዶ ያዘጋጀውን የልጁን ሥጋ በቀምሰ ጊዜ ሰይጣን ስላደረበት (ስለተዋሐደው) ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ቤተሰቦቹን፣ ጎረቤቶቹንና መንገደኛውን ዅሉ ይበላ ጀመር፡፡ በአጠቃላይ ፸፰ ሰዎችን ከበላ በኋላ አንድ በቍስል የተመታ ሰው አገኘና ሊበላው ሲል ‹‹ውኃ አጠጣኝ›› ብሎ በሥላሴ፣ በቅዱስ ሚካኤል፣ በቅዱስ ገብርኤል ስም ለመነው፤ እርሱም ዝም አለው፡፡ በመጨረሻም ‹‹ በድንግል ማርያም ስም ›› አለው፡፡ ስምዖን የእመቤታችንን ስም በሰማ ጊዜም ወደ ልቡናው ተመልሶ ‹‹እስኪ ቃሉን ድገመው ›› አለው ፤ በሽተኛውም መልሶ ‹‹ ስለ ድንግል ማርያም ውኃ አጠጣኝ›› ብሎ ለመነው፡፡ ያን ጊዜ ‹‹ይህችስ እንደምታስምር በልጅነቴ ሰምቻለሁ ›› ብሎ ጥቂት ውኃ ሰጠው ፤ ውኃው ጕሮሮውን እንኳን ሳያርስለት ‹‹ ጨረስህብኝ ›› ብሎ ነጥቆት ሔደ፡፡ በሌላ ቦታም አንድ ገበሬ አግኝቶ ሊበላ ሲል ገበሬው ‹‹በላዔ ሰብ የምትባል አንተ ነህ? ›› ባለው ጊዜ ‹‹ ለካስ አመሌን ሰው ዅሉ አውቆብኛል ›› ብሎ ዋሻ ገብቶ በመጸጸት በዚያው ሞተ፡፡ ነፍሱንም መላእክተ ጽልመት መጥተው ሲወስዷት እመቤታችን ‹‹ልጄ በማይታበል ቃልህ ይህችን ነፍስ ማርልኝ? ›› አለችው፡፡ ጌታችንም ‹‹ ሰባ ስምንት ነፍስ ያጠፋ፣ ፈጣሪውን የካደ ሰው ይማራልን? ›› አላት፡፡ እመቤታችንም ‹‹በስሜ የተጠማውን ውኃ አጥጥቶ የለምን?›› ብላ ስምዖንን (በላዔ ሰብእን) አስምራዋለች፡፡ ነፍሱንም መላእክተ ብርሃን መጥተው ወደ ገነት አስገብተዋታል፡፡ ሁለተኛው ተአምር ደግሞ ከብሮ ከኖረ በኋላ ለድህነት በተጋለጠ አንድ ምእመን ላይ የተደረገ ነው ፤ ከክርስቲያን ወገን የኾነ ሀብት አግኝቶ ያጣ አንድ ሰው ነበር፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ‹‹ ከብሬ በኖርኹበት አገር ተዋርጄ አልኖርም ›› ብሎ ጓዙን ጠቅልሎ ከአገሩ ወጥቶ ሲሔድ ሰይጣን ያዘነ ሰው መስሎ ደንጊያውን በምትሐት ወርቅ አስመስሎ ‹‹ ሥላሴን ፣ ጻድቃንን ፣ ሰማዕታትንን ፣ መላእክትን ካድልኝና ይህን ወርቅ እሰጥሃለሁ ›› አለው፡፡ ዅሉንም ካደለትና ወርቁን ተቀብሎ ዞር ሲል ‹‹ ምእመናን የሚመኩባት ድንግል ማርያም ‹ የአምላክ እናት አይደለችም› ብለህ ካድልኝ ›› አለው፡፡ ሰወየውም ‹‹ እርሷንስ አልክድም ›› ስላው በደንጊያ ቀጥቅጦ ገደለው፡፡ መላእክተ ጽልመት የሟቹን ነፍስ ሊወስዱ ሲሉ መላእክተ ብርሃንም አብረው ቀረቡ፡፡ እመቤታችንም ጌታችንን ‹‹ ልጄ ይህችን ነፍስ ማርልኝ?›› አለችው፡፡ እርሱም ‹‹ከልብኑ ይትመሐር እምየ፤ እናቴ፣ ውሻ ይማራልን?›› አላት፡፡ እመቤታችንም፡- ‹‹‹ ስምሽን የጠራውን፣ መታሰቢያሽን ያደረገውን እምርልሻለሁ › ያልኸው ቃል ይታበላልን? ›› አለችው፡፡ በዚህ ጊዜ ‹‹ምሬልሻለሁ›› አላት፡፡ እግዚአብሔር አምላካችን ‹‹ ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳን አደረግሁ ›› ባለው መሠረት ከቅዱሳን ጋር ያደረጋቸው ቃል ኪዳኖች ብዙዎች ናቸው፡፡ ከእነዚህም መካከል ከላይ በተአምራቱ እንደተመለከትነው አንዱ ለእመቤታችን የሰጠው የአማላጅነት ኪዳን ነው፡፡ ማማለድ ማለት ስለሌላው መጸለይ፣ መለመን ፣ የደረሰውን ችግር እንዲወገድ ማድረግ ፣ ማስማር ( ይቅርታ ማሰጠት ) ማለት ነው፡፡ በዚሁ መሠረት ከእግዚአብሔር በታች ከቅዱሳን ዅሉ በላይ ከፍ ከፍ ያለችና የከበረች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከእግዚአብሔር በተሰጣት የማማለድ ሥልጣን ‹‹ ሰአሊ ለነ ቅድስት ፤ ቅድስት ሆይ ለምኚልን ›› እያሉ ለሚለምኗት ዅሉ ከእግዚአብሔር እያማለደችና እየለመነች ምሕረትን እንደምታሰጥ ቀናውንና የተመሰገነውን ሃይማኖት የምንከተል ምእመናን ዅሉ እናምናለን፡፡ ምክንያቱም ቅድስት ድንግል ማርያም የእግዚአብሔር እናትና አገልጋይ እንደመኾኗ ከዅሉም ቅዱሳን በበለጠ ለእግዚአብሔር ቅርብ ናትና፡፡ በእግዚአብሔር ዘንድም ኾነ በሰው ዘንድ ባለሟልነትን ማግኘት ወይም ቅርብ መኾን ደግሞ አንድን ጉዳይ በቀላሉ ለማስፈጸም ይጠቅማል፡፡ ለምሳሌ፡- 👉 መልአኩ ቅዱስ ገብርአል በእግዚአብሔር ፊት የሚቆም ባለሟል በመኾኑ የድኅነትን ምሥጢር አብሣሪ ኾኗል /ሉቃ. ፩፥፲፱-፳፮/፡፡ 👉 አስቴር የንጉሡ አርጤክስስ ሚስት በመኾኗ በወገኖቿ አይሁድ የታወጀውን የሞት አዋጅ አስለውጣለች /መጽሐፈ አስቴር ፫፥፲/፡፡ 👉 ነቢዩ ሙሴ በእግዚአብሔር ፊት ባለሟል በመኾኑ ‹‹ይህንን ኀጢአታቸውን ይቅር በላቸው፤ ያለዚያ ግን እኔን ከጻፍከው መጽሐፍህ እባክህ ደምስሰኝ?›› በማለት ለእስራኤላውያን ምሕረትን አሰጥቷል /ዘፀ.፴፪፥፲፬/፡፡
إظهار الكل...
የቀጠለ... ሌላኛዋ ሀገር ወይም አህጉር ኢትዮጵያን በራሳቸው መጠርያ ከሚጠሩ መካከል አውሮፓውያን ናቸው ከግሪክ ውጪ ምክንያቱም ግሪክ ኢትዮጵያን አቶስ እያለች ነው የምትጠራት ትርጉሙም ጠይም ማለት ነው አንዳንድ የታሪክ መጻሕፍት ላይ የተቃጠለ ፊት በው ይተረጉሙታል ። ወደ ቀደመ ነገር ስንመለስ አውሮፓውያን አቢሲንያ እያሉ ነው የሚጠሯት ይኽም ኹለት ትርጓሜ አለው አንድ አቢስ የሚባል እጽ በብዛት ስለሚበቅልባት ነው (ስለዚኽ እጽ ወደፊት የምናነሳ ይኾናል) በዚኽም በስያሜ አቢሲንያ ብለዋታል ይላሉ አንድም አቢስ የሚባል ድንቅ ብርቱ ንጉሥ ነግሦባት ስለነበር በርሱ አቢሲንያ ተብላለች በሰው ስም ለሀገር መሰየም ልማድ ነው በ አማሌቅ አማሌቃውያን በአሶር አሶራውያን በሌዊ ሌዋውያን እንደተባለ። ይቀጥላል....
إظهار الكل...
Watch "እስክንድርን ያስደነገጠችው ታላቋ ሕንደኬና ጥበቧ" on YouTube https://youtu.be/Q-MRCBuf4xY
إظهار الكل...
እስክንድርን ያስደነገጠችው ታላቋ ሕንደኬና ጥበቧ

የኢትዮጵያ ሴት ሕንደኬዎች የነበራቸው ኃያልነትና ጥበብ

ኢትዮጵያ ሀገራችን እኛ በምናውቀው በሱባ ቋንቋ ይኽንን ትርጓሜ እና ስያሜ ታግኝ እንጂ በተለያዩ ሀገራት ስያሜ ተሰጥቷታል ቀጥሎ በመጠን ለመመልከት እንሞክራለን በታላቋ አፍሪካውት ሀገር የስልጣኔ መሰረት ተብላ ከሚነገርላት ሀገር ግብጽ ኢትዮጵያን በራሳቸው ስያሜ ቶኔቶር ብለው ነው የሚጠሯት ትርጓሜውም ሀገረ እግዚ አብሔር ማለት ነው ይኽንንም ያሉበትን ምክንያት የታሪክ ልሒቃን ሲያስረዱ የዐባይ መነሻ የብዙ የከበሩ ማእድናት ባለቤት በተለይ ቢጫ ወርቅ ወይም ዮጵ የተለያዩ የእጽዋት ውጤቶች መገኛ በተለይ ለአምልኮ የሚጠቀሙበት ማእጠንት የሚፈጽሙበትን እጣን የሚያገኙት ከኢትዮጵያ ነበር እና በዚኽ ምክንያት ድንቅ ሀገር ሞኾኗን ሕዝቦቿም ኾነ ምድሯ በእነሱ አጠራር የአሙን(አሞን) ሀገር መኾኗን ለማስረዳት ይኽን ተናግረዋል አሙን ሰው እንጂ አምላክ ባይኾንም የእግዚ አብሔር ሀገር ምኾኗን ግን እኛም እናምናለን። በቀጣይ አቢሲኒያ ተብላ ስለመጠራቷና እና ተያያዥ ምክንያቶችን እናቀርብላችኋለን።
إظهار الكل...
ይቀጥላል
إظهار الكل...
ኢትዮጵ ግዮን እንቆጳዝዮን ማለት ነው። ኢትዮጵያ ማለት አንድም ኢት - ማለት ስጦታ ዮጵ - ቢጫ ወርቅ እንቁ ግዮን - ፈሳሽ ወንዝ ኢትዮጵ ግዮን ማለት ነው ትርጓሜውም ከግዮን የተገኘች የወርቅ የእንቁ ስጦታ ማለት ነው ይኽም በሱባ ቋንቋ ነው። አንድም የግዮን ምንጭ ማለት ነው። አንድም የግዮን ወርቅ ስጦታ ማለት ነው። አንድም ኢትዮጵያ ማለት ሲተነተን በነገራችን ላይ ማንዘነጋው ነገር ኢትዮጵያ የሚለው ቃል የሱባ ቋንቋ መኾኑን መዘንጋት የለብንም። ኢት ማለት አምሐ ለእግዚ አብሔር ዮጵ ቢጫ ወርቅ ያ አመልካች ናት ሲቀመርም ለእግዚ አብሔር የምትሰጥ የወርቅ ስጦታ ማለት ነው።
إظهار الكل...
ኢትዮጵያ ማለት ምን ማለት ነው ? ቅድመ ቃል ትንታኔ ስናደርግ ኢትዮጵያ የሚለው እያንዳንዱ ፊደል ይኽንን ፍቺ ይሰጠናል ኢ = አሐድ አምላክ ት = ትጉህ አብ ዮ = ዮድ የማነ እግዚ አብሔር ብሒል በልሳነ ዕብራይስጥ ጵ = ጰራቅሊጦስ ያ = የአንዱ አምላክ የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ሀገር ማለት ነው። የቀሩትን ትንታኔዎች በሚቀጥለው ጊዜ እናቀርባለን
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.