cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Quran darul furkan Media

ከቁርአን አንድን አንቀፅ ያዳመጠ ሰው የቂያማ ቀን ብርሃን ትሆንለታለች!!!( ሰሂህ ሙሰነፍ አብዱረዛቅ ሐዲስ ቁጥር 6012) https://t.me/joinchat/UOnYamyBDDGx7ANR https://t.me/joinchat/UOnYamyBDDGx7ANR በዋሳፕ https://chat.whatsapp.com/DaCq8IiFKFo8W3VNRplAC7 በዩቶ Youtube https://youtu.be/4yLHfwgtiGQ

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدلم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
225
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

የረመዷንን ፆም በተመለከተ ወደ አማርኛ የተተረጎሙ ሀዲሶች በpdf! ---------------------------------- https://t.me/joinchat/TCEdrT16en4tGrEB
إظهار الكل...
4_6034835311836531138.pdf9.64 KB
✅ አማኝ እና ብልጥ ሴት ረመዷንም ሆነ ከረመዷን ውጪ በአጅር ከወንድ ልትበልጥ ትችላለች‼️ ➡️ይህም ሚሆንበት ምክንያት 📌ለባሏ ለቤተሰቦቿ ለአሰሪዎቿ በአጠቃላይ እሷን ለሚመለከታት ሁሉ ትሀድማለች፣ በቂ ምግብ ታዘጋጃለች፣ ልብሳቸውን ታጥባለች፣ ሚተኙበት እና ሚበሉበት ነገር ሁሉ ታፀዳለች ይህ ተግባሯ ንያ ካከለችበት ከአላህ ዘንድ አጅር ምታገኝበት ኢባዳ ይሆንላታል። ➡️ እላይ በጠቀስናቸው ስራዎች ምንዳዋን እጥፍ ድርብ ታደርጋለች። ብዙ ኸይርን ታፍሳለች ግን ለማንም ሴት አይደለም ከአላህ አጅርን ፈልጋ በኢኽላስ ጥርት አድርጋ ለሰራች ሴት ብቻ ነው። ➡️ማንኛውም ተቀጥረንም ከዛ ውጪ ምንሰራቸው ስራዎች ላይ ዱንያዊ ደሞዙን ብቻ ማየት የለብንም አጅሩንም ልንነይትበት ይገባል። ➡️በተጨማሪም ማንኛውም ስራ እየሰራች ምላሷ ከዚክር አይለይም አላህን ታወሳለች። 👉እቃ እያጠበች ትዘክራለች 👉ወጥ እየሰራች አላህን ታወሳለች 👉ቤት እያፀዳች ምላሷ ከዚክር አይርቅም 👉ስትላክ፣ ስትወጣ ስትወርድ የሀፈዘችውን ቁርአን ትቀራለች ⚡️በዚህም ተጨማሪ አጅር ታፍሳለች ⚡️ማንኛውም ስራ አላህን ካማውሳትና መልካም ከመስራት አያግዳትም። ➡️ ሱብሀን አላህ እንዲህ አይነት ሴት ምንኛ የታደለችና አላህ መልካም የሻላት እንቁ እንስት ነች ። ▪️ይህቺ ናት ሱመያ ሊሏት ሚገባው ▪️ይህቺ ናት የነ አኢሻ የሌሎችንም ሰሀቢያት ተከታይ የታዘዘችውን አቅሟ በቻለው ትሰራለች ▪️ሰላቷን በወቅቱ ትሰግዳለች ▪️ቀብልያ ባእዲያ አያመልጣትም ▪️ሰላተ ዱሀ ትሰግዳለች ▪️የጠዋትና የማታ ዚክር ወቅቱን ጠብቃ ትላለች ▪️የባሏንና የቤተሰቦቿን ሀቅ ትጠብቃለች ▪️በቀን ቁርአን ሳትቀራ አትውልም ▪️ዲኗን ለመማር ጥረት ታረጋለች ▪️በዲኗ ላይ አትደራደርም ▪️በኒቃቧ ደምቃለች ኒቃቧን ሲነኩባት አቶድም ▪️አላህን ትፈራለች ▪️ሀያእ የተላበሰች ናት። 📌በተቃራኒው አላህ ከከለከላት ነገር ሁሉ ትርቃለች ♦️ከአጅነብይ ወንድ ጋር ቀልድ አታውቅም ♦️ፊልም፣ ድራማ፣ ሙዚቃ፣ ነሺዳ በደረሱበት አትደርስም ♦️ከዝሙት እጅግኑ የራቀች ነች ♦️አትዋሽም ♦️አታጭበረብርም ♦️እምነቷን አታጎልም ♦️ከሰዎች ተደብቃ ምንም ወንጀል አትሰራም ♦️በየሚዲያው አጅነብይ የሆነን ወንድ ታግ በማረግ kkkkkkkk ክክክክክክ ሀሀሀሀሀሀሀሀ ቂቂቂቂቂቂቂ እያለች ጊዜዋን አትገልም ♦️ፎቶዋን ፕሮፋይል አታረግም፣ በየሚዲያው አትበትንም ♦️ወንዶችን ላለመፈተን ጥረት ታደረጋለች ♦️አታስመስልም ♦️እህቷን አታማም፣ በመጥፎ አትጠረጥርም። ▪️እናማ ውድ እህቴ ብልጥ ሁኝ። ➡️አላህ ሆይ እኔንም ወንድም እህቶቼን ከወንጀል ጠብቀን። በትክክለኛው ተውባ ወዳንተ ከሚመለሱት ባሮችህ አድርገን። https://t.me/+RfyKpX58WdyZQo4P
إظهار الكل...
🇸🇦ተውሒድ የጀነት ዋጋ ነው !!🇸🇦 ኢብኑ ተይሚያ እንድህ አሉ

የተውሂድ አሳሳቢነት"!! ሸይኸ ኢብኑ ዑሰይሚን ረሂመሁሏህ እንዲህ ይላሉ አንድ ሰው ጌታውን ሲገዛው በእውቀት ላይ ይሆን ዘንድ የተውሂድንና የአቂዳን ትምህርት መማሩ በሱ ላይ ግደታ ነው!!! ( 📚መጅሙዕ አል'ፈታዋ(2/78) 👉ምክረ አስታያት ካላቹ መልክታቹ በዚህ ሊክ ይደረሰኛል👇👇 @Umu_hebtullah_Aselfyah

Audio from ام هبةلله إن شاء الله
إظهار الكل...
AUD-20220408-WA0027.mp32.31 MB
◾️ሀይደኛና ኒፋስተኛ ሴትና ስጁዱ ቲላዋ ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ 🌐ኢብኑ ባዝ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ተብለው ተጠየቁ፦ ➡️ ጥያቄ‼️ ♦️ሴት ልጅ ወርሀዊ ኡዝር ላይ በምትሆንበት ወይም ውዱእ በሌላት ጊዜ ስጁድ የሚደረግበት አንቀፅ ላይ ስትደርስ ስጁድ ማድረግ ትችላለች? ➡️ መልስ‼️ ♦️አዎ ትችላለች። ስጁዱ ቲላዋ ለመውረድ ውዱእ ማድረግ ግድ አይልም። ስጁዱ ቲላዋ ከዚክር ምድብ የሚመደብ ስለሆነ አንድ ሰው ውዱእ ባይኖረውም ማድረግ ይችላል። ትክክለኛው አቋም ይህ ነው። ሀይድ ላይ ያለች ሴት ቁርአን በምትቀራ ጊዜ ስጁዱ ቲላዋ ያለበት ቦታ ስትደርስ ስጁድ ማድረግ ትችላለች። ልክ እንደዚሁ ጀናባ ላይ ያለ ሰው ሲቀር ውዱእ የሌለው ሰውም ቢሆን ማድረግ ይችላል። ጀናብ የሆነ ሰው ግን ቁርአን ስለማይቀራ አያደርግም። 📚المــصــــــدر "فتاوى نور على الدرب https://t.me/+RfyKpcYtbiP7Fu1W
إظهار الكل...
🇸🇦ተውሒድ የጀነት ዋጋ ነው !!🇸🇦 ኢብኑ ተይሚያ እንድህ አሉ

የተውሂድ አሳሳቢነት"!! ሸይኸ ኢብኑ ዑሰይሚን ረሂመሁሏህ እንዲህ ይላሉ አንድ ሰው ጌታውን ሲገዛው በእውቀት ላይ ይሆን ዘንድ የተውሂድንና የአቂዳን ትምህርት መማሩ በሱ ላይ ግደታ ነው!!! ( 📚መጅሙዕ አል'ፈታዋ(2/78) 👉ምክረ አስታያት ካላቹ መልክታቹ በዚህ ሊክ ይደረሰኛል👇👇 @Umu_hebtullah_Aselfyah

📚ቁርአን በረመዷን አብረንእናኽትም! ➡️ ጁዝ አራት ⬅️الليلة (4) 🌐رمضان 🎙الشيخ علي الحذيفي حفظه الله 🎧ይቀጥላል ኢንሻ አላህ.......... ➳ተከታታዩን ለማግኘት ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ ➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴ https://t.me/+45kaaPfry4o5Yzk8
إظهار الكل...
ቁርአን ጁዝ ⓸.mp39.48 MB
إظهار الكل...
4_6039367013434919824.pdf5.91 KB
Photo unavailable
#ሴቶች_እቤታቸው ውስጥ አጫጭር ልብሶችን መልበስ ይፈቀድላቸዋልን❓ ✅“በቤቷ ከሆነና ከባሏ ውጭ ሌላ ወንድ የሌለ ካልሆነ በስተቀር አጭር ልብስ መልበስ አይገባትም። (ባሏ) ከሌላ ሰው ጋር ባለበት ሁኔታ አጭር ልብስ ወይም ጠባብ እንዲሁም ገላዋን የሚያሳይ ስስ የሆነ ልብስ መልበስ አይፈቀድላትም። ↪️ነቢዩ ﷺ “የእሳት ሰዎች የሆኑ  ሁለት አይነት ሰዎች ካሉ በኋላ ለብሰው ያልለበሱ ሴቶች …፣ ጀነትን አይገቧትም። ሽታዋንም አያገኟትም።” ብለዋልና። በመሆኑም ሴት ልጅ አጭር ልብስ ወይም ጠባብ ወይም ከውስጡ ቆዳን የሚያሳይ ስስ ልብስ ከለበሰች በትክክልም ይህች ሴት “ለብሰው ያልለበሱት ሴቶች” ከተባሉት ትመደባለች። በላይዋ ላይ ልብስ ስላለ ለብሳለች ይባላል። ልብሱ ግን (ገላዋን ለመደበቅ) ምንም ስለማይጠቅማት አልለበሰችም።”         ምንጭ ☞⇘⇘ مجموع فتاوى ابن عثيمين (12/268) ከቻናላችን ከሌሉ #join በማለት ይቀላቀሉ⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️ https://t.me/joinchat/LeaHujDAv-UxZDBk
إظهار الكل...
የመጨረሻ የውይይት ጥሪ ~ ~~~~ بسم الله الرحمن الرحيم ከሆነ ጊዜ ወዲህ ያለውን ንትርክ ውል ለማስያዝ ብለን የውይይት ጥሪ ያደረግንላቸው አካላት እስካሁን ድረስ ሰበብ እየደረደሩ ማሰናከሉን ተያይዘውታል። አሁን ደግሞ "ህዝብ ምን ያውቃልና ነው ዳኛ የሚሆነው?" በማለት ለህዝብ ክፍት መሆኑን እየነቀፉ ነው። በጉዳዩ ላይ ግር ያለው ሁሉ ከአሉባልታ ባለፈ በቀጥታ በመከታተል የጠራ አቋም ይይዝ ዘንድ ለህዝብ ክፍት ይሁን አልን እንጂ ህዝብ ዳኛ ሆኖ ነጥብ ይስጠን አላልንም። በዚያ ላይ ካልተግባባን የደረስንባቸውን ነጥቦች በጋራ ፅፈን በጋራ ለምናምንባቸው ዓሊሞች እናቅርባለን ብለናል። አንድ ጫፍ ላይ ሳንደርስ "ዓሊም እናስመጣለን" ወይም "ወደ ውጭ እንሄዳለን" ማለት መሸሻ ሰበብ እንጂ መፍትሄ መሻት አይደለም። ይህን ያክል ጉዳዩ ለታላላቅ ዓሊሞች እንዲቀርብ ብትፈልጉ ኖሮማ ተብዲዕ ውስጥ ከመዋኘታችሁ በፊት ተረጋግታችሁ ትጠብቁ ነበር። ደግሞስ ከዚህ በፊት ለተለያዩ ወገኖች በግልፅ የውይይት ጥሪ ስናደርግ እንደነበር ይታወቃል። ለምን ያኔ አትነቅፉም ነበር? ጉዳዩ ወደናንተ ሲመጣ ነው ሰበብ የምትደረድሩት? ለማንኛውም "ውይይቱ በአካል ቢሆን" ስትሉ ለነበራችሁ አካላት ሁሉ! ይሄው ጥያቄያችሁን በበጎ በማየት አንድ እርምጃ ለመቅረብ ወስነናል። ስለዚህ ሁለት ወይም ሶስት ሆነን ወደ ባህርዳር እንሄዳለን፣ ኢንሻአላህ። ይሁን እንጂ በር ዘግተን ከጥቂት ሰዎች ጋር ብቻ የምናወራበት ሁኔታ አይኖርም። በእንዲህ አይነት አካሄድ በተደጋጋሚ ተነድፈናል። ስለዚህ ባህዳር ውስጥ ካሉ መስጂዶች ውስጥ በአንዱ ይመቻች። የፈለገ ይታደምበት ዘንድ በሩ ክፍት ይሁን። ውይይቱን መቅዳትም፣ ቀጥታ ማስተላለፍም ለፈለገ አካል እንዲሁ ክፍት እንዲሆን እንፈልጋለን። ውይይቱን ለመምራትም የውጭ ሰው እንዲሆን አንጠይቅም። እዚያው ባህርዳር ያሉ መሻይኾች (ሸይኽ ዐብደላህ፣ ሸይኽ አሕመድ፣ ሸይኽ ሙሐመድ አወል፣ ኡስታዝ ዩሱፍን ጨምሮ) ይምሩት። ለመረጃ ያክል ከውስጣችሁ ከኢኽዋን ጋር በግልፅ ውይይት ያደረገ ሰው አውቃለሁ። ይህንን የማነሳው ጥሪያችንን በሆነ ማመሀኛ እንዳትገፉት ነው። NB፦ ~~ በነገራችን ላይ ሰሞኑን በሕሩ የለቀቀውን ድምፅ አልሰማሁትም። የሰሙ ሰዎች ሲነግሩኝ ግን በዚህ መጠን መድረሱ ገርሞኛል። እንዲህ አይነቱን የዙልም አካሄድ ለህዝብ መበተኑ "ለአኺራዬ ያዋጣኛል" ካለ ምርጫው የራሱ ነው። ለጊዜው ግን ለራሴ እየተከላከልኩ ምላሽ በመስጠት ዋናውን የውይይት አጀንዳ ማደብዘዝ አልፈልግም። እቅጩን ስናገር ከውይይቱ ጥሪ ሰበብ እየደረደሩ የሚሸሹት የያዙት አቋም ሆድ የሚያስነፋ እንዳልሆነ ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ነው። ስለዚህ የሚፈልጉት ወይ በተዘጋ ክፍል ውስጥ ወይ ደግሞ ጭፍን ደጋፊ ብቻ ባለበት ቦታ ያለ ጠያቂ፣ ያለ ሞጋች እንደፈለጉ መወንጀል ነው። በዚሁ መልኩ ብቻ ነው የምንቀጥለው ካሉ፣ ለህሊናቸው ካልጎረበጣቸው መንገዱን ጨርቅ ያድርግላቸው። "እናንተ ዘንድ የሌላ እውነት አለን" ካሉ ይሄው ለመታረም ዝግጁ ነን እያልን ነው። እኛ እጅ ለመስጠት ፈቃደኞች ካልሆንም "እውነታቸውን" ገልጠው እንደሚያስቡት በኛ የተሸወዱትን አካላት የሚያተርፉበትን እድል ይጠቀሙበት። የቀደመ አቋሙን የቀየረው ማን እንደሆነ ይለይ። እዚያም እዚህም የምንሰማው የተምይዕ ውንጀላም ተፍረጥርጦ ይውጣ። ይሄ ወደ ሱና በመጣራትና ቢድዐን በመዋጋት ጭንብል የተንሰራፋው ውሸትም ይጋለጥ። ባጭሩ እንገናኝና ወይ አጥፊው ይታረም፤ ወይ ውሸታሙ ይፈር። ~ ሰላም ~
إظهار الكل...
➲በሚስት ገንዘብ ላይ ባል ሀቅ አለው? ➾በስራ ላይ ካሉ ሴቶች በተደጋጋሚ የሚመጣልኝ ጥያቄ በመሆኑ ሁሉም ሸሪአዊ ብይኑን ያቁት ዘንድ የተወሰኑ ማብራሪያዎችን ልፅፍ ወሰንኩ! . ➻በዚህ ርእስ ላይ ሶስት ነጥቦችን ለመዳሰስ እወዳለሁ ሙሉውን በጥሞና አንብቡት . ❶ ሚስት ሀብትና ንብረት ካላት ለቤት ወጪ የማድረግ ግዴታ አለባት ወይ? . ➻በእስልምና ለቤተሰብ የሚያስፈልገውን ወጪ በሙሉ የማሟላት ግዴታ የተጣለበት ባል ላይ ነው። . ➻የቤተሰብ ወጪ ሲባል ምግብ መጠለያ እና ልብስ የመሳሰሉ ለራሱ ለሚስቱ እና ለልጆቹ የሚያስፈልጉ ነገሮችን በሙሉ ያካትታል። . ▹ማስረጃውም . ➧ከቁርአን . { ٱلرِّجَالُ قَوَّٰمُونَ عَلَى ٱلنِّسَآءِ بِمَا فَضَّلَ ٱللَّهُ بَعْضَهُمْ عَلَىٰ بَعْضٍۢ وَبِمَآ أَنفَقُوا۟ مِنْ أَمْوَٰلِهِمْ ۚ....} . {ወንዶች በሴቶች ላይ ቋሚዎች (አሳዳሪዎች) ናቸው፡፡ አላህ ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ በማብለጡና (ወንዶች) ከገንዘቦቻቸው(ለሴቶች)በመስጠታቸው ነው፡፡ } (ኒሳእ 34) . ‏{وَعَلَى ٱلْمَوْلُودِ لَهُۥ رِزْقُهُنَّ وَكِسْوَتُهُنَّ بِٱلْمَعْرُوفِ} . {ለተወለደለት (ለአባት) (የልጁ) ምግቡም ልብሱም በመልካም አለበት} (በቀራ 233) . ▹ከሀዲስ . ➲የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲ ብለዋል፦ ".... ﻭﻟﻬﻦ ﻋﻠﻴﻜﻢ ﺭﺯﻗﻬﻦ ، ﻭﻛﺴﻮﺗﻬﻦ ﺑﺎﻟﻤﻌﺮﻭﻑ " ﺭﻭﺍﻩ ﻣﺴﻠﻢ 8/183 ." . "... ለነሱ በናንተ ላይ በመልካሙ (በተለመደው መልኩ) ሪዝቃቸውና ልብሳቸው አለባችሁ። 📚(ሙስሊም 8/183) . ➲በዚህ ላይ የመጡ ሌሎችም በርካታ ሀዲሶች አሉ። . ▹ከኡለሞች ጥቅል ስምምነት (ኢጅማእ) . ➧ኢብን ቁዳማ እንዲህ ይላል፦ . "የሚስት ነፈቃ በባል ላይ ግዴታ እንደሆነ የእውቀት ባለቤቶች በሙሉ ተስማምተውበታል። 📚(ሙግኒ 7/564) . ➧ኢብን ሀጀር እንዲህ ይላል፦ . "በቤተሰብ ላይ ነፈቃ ማድረግ በኡለሞች ጥቅል ስምምነት መሠረት ግዴታ ነው።" 📚(ፈትህ 9/498) . ➧ ከላይ በጠቀስናቸው የቁርአን የሀዲስና የኢጅማእ ማስረጃዎች መሰረት በገንዘብ ቤተሰቡን የማስተዳደር ግዴታ ያለው በባል ላይ ነው። ▹በዚህ ላይ ኡለሞች አይከራከሩበትም ▯ ➧ለቤት የሚያወጣው ወጪ ከማባከንም ይሁን ከስስት የጠራ መሀከለኛ ሆኖ ሀገሩ ላይ በሱ አቅም ያሉ ሰዎች ቤታቸውን በሚያስተዳድሩበት መልኩ መሆን አለበት። 📚(ተፍሲር ኢብኑ ከሲር 1/634) . ➧በመሆኑም ▯ ⓵ ሚስት በንግድም ይሁን በስጦታ ወይም በውርስ ወይ ደግሞ በመህር ባገኘችው ገንዘብ ላይ ባል ሀቅ የለውም። የሚስት ገንዘብ ላይ ባል ሀቅ ቢኖረው ኖሮ ሚስት ስትሞት ሙሉ ገንዘቧን እሱ ይወርስ ነበር። ነገር ግን የሚስትን ገንዘብ በምትሞት ግዜ አባቷ፣ እናቷ እና ልጆቿ በውርስ ይጋሩታል። በመሆኑም ያለ እሱ (ያለ ባሏ) ፍቃድ ገንዘቧን እሷ ለፈለገችው ተግባር ማዋል ትችላለች። ▯ ⓶ ሚስት ምንም ያክል ሀብት ቢኖራት በባል ላይ እሷን የማስተዳደር ግዴታው አይወድቅለትም። እሷ ሀብት ስላላት ተብሎ ነፈቃ በማድረግ ላይ አትገደድም። ▯ ⓷ በራሷ ፍላጎት ግን ነፈቃ ካደረገች የሚበረታታ ተግባርን ሰርታለች። እንደ ሰደቃም ይቆጠርላታል በሀዲስ እንመጣው ራቅ ላለ ሰው ከምታደርገው ሰደቃ ይልቅ ለባሏ ምታደርገው ይበልጥላታል። ▯ ⓸ ሚስት ከቤት ወጥታ ስራ እንድትሰራ ባል ማስገደድ አይችልም። እሷን ማስተዳደር ካቃተው ሚስት ምርጫ አላት ፍቺን መጠየቅ ትችላለች። ▯ ❷ ትዳር ካደረገች በሗላ ሰርታ ያገኘችውን በተመለከተ .➧ኒካህ ሲያስሩ ስራ እንደምትሰራ ተነጋግረው ይህን መስፈርት አስቀምጣ ከነበረና እሱ በዚህ ተስማምቶ ከገባ ከዚህ ስራ መከልከል አይችልም። . ➧ ማስረጃው ከቁርአን . ‏( ﻳَﺎ ﺃَﻳُّﻬَﺎ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﺁﻣَﻨُﻮﺍ ﺃَﻭْﻓُﻮﺍ ﺑِﺎﻟْﻌُﻘُﻮﺩِ ‏) . (እናንተ ያመናችሁ ሆይ በቃል ኪዳን ሙሉ) . ➧ከሀዲስ . የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲ ብለዋል . ( ﺍﻟﻤُﺴْﻠِﻤُﻮﻥَ ﻋَﻠَﻰ ﺷُﺮُﻭﻃِﻬِﻢ ‏) . (ሙስሊሞች በመስፈርታቸው ላይ ናቸው) 📚(አቡ ዳውድ 3594 አልባኒ ሰሒሕ ብለውታል) . ➲ከነዚህ ምንረዳው በገቡት ቃል መገኘት የተስማሙበትን መስፈርትም ማሟላት በሙእሚኖች ላይ ግዴታ መሆኑን ነው። ስለዚህ መጀመሪያ ኒካህ ሲያስሩ ስራ እሰራለሁ የሚል መስፈርትን አስቀምጣ በዛ ተስማምተው ከነበረ መከልከል አይችልም። . ➲ነገር ግን ስራዋ ሀራም ከሆነ ከዚህ ስራ መከልከል ይችላ መከልከልም ይኖርበታል። . መልእክተኛው ﷺ በሀዲሳቸው ላይ እንዲህ ብለዋል . ( ﻣَﻦْ ﺍﺷْﺘَﺮَﻁَ ﺷَﺮْﻃًﺎ ﻟَﻴْﺲَ ﻓِﻲ ﻛِﺘَﺎﺏِ ﺍﻟﻠَّﻪِ : ﻓَﻠَﻴْﺲَ ﻟَﻪُ ، ﻭَﺇِﻥْ ﺍﺷْﺘَﺮَﻁَ ﻣِﺎﺋَﺔَ ﺷَﺮْﻁٍ ‏) . "➧በአላህ ኪታብ ላይ የሌለ መስፈርትን ያስቀመጠ ሰው ለሱ የለውም መቶ መስፈርት ቢያስቀምጥ እንኳን" 📚(ቡኻሪና ሙስሊም) . ➧በዚህ መልኩ መጀመሪያ በተከሰተ ስምምነት መሠረት በምትሰራው ሀላል ስራ የምታገኘው ገቢ የራሷ ነው ባል በዛ ላይ ሀ የለውም። . ➧በራሷ ፍቃድ ግን ከደሞዟ ብትሰጠው ችግር የለውም . ➬ኢብን ባዝ እንዲህ ይላሉ፦ . "በፍቃዷ (በፍላጎቷ) የሚስትህን ደሞዝ ብትጠቀም ችግር የለውም።" 📚(ፈታዋ ሸይኽ ኢብን ባዝ 20/44) ▯ ❸ መጀመሪያ ስምምነት ሳይኖራቸው ከተጋቡ በሗል መስራትን ከፈለገች . ➲በዚህን ግዜ ባል ሚስቱን ውጪ ወጥታ እንዳትሰራ መከልከል ይችላል።ምክንያቱም መጀመሪያ ስምምነት የላቸውም።በምትወጣ ግዜ ደግሞ ሀቁ ይጓደላልና። . ➾ቡሁቲ እንዲህ ይላል፦ . "➛ሴት ልጅ ኒካህ ካሰረች በሗላ ያለ ባሏ ፍቃድ ተቀጥራ መስራት አትችልም።የባሏን ሀቅ ስለምታስመልጥ" 📚(ረውደቱል ሙረባእ 271) . ➧ከፈለገ ደግሞ እንድትሰራ ፈቅዶላት ከዛም ሰርታ ከምታገኘው ገቢ የተወሰነውን ለሱ እንድትሰጠው መስማማት ይችላሉ። ምክንያቱም ለስራ በምትወጣ ሰአት የሱ ሀቅ የሆነውን የተወሰነ ሰአት ታሳጣዋለችና ለዛ ማካካሻ ከምታገኘው ገቢ በስምምነት ለሱ ተቆራጭ ማድረግ ይችላሉ። . ➧በዚህም ግዜ ቢሆን ግን የማስተዳደር ግዴታ ያለበት በባል ላይ ነው። . ➧ኢብን ኡሰይሚን እንዲህ ይላሉ፦ . "በወንዶች ላይ ለቤተሰቡ ማለትም ለሚስቱና ለልጆቹ በመልካም ነፈቃ የማድረግ ግዴታ አለበት። ➾ሚስቱ ሀብታም ብትሆን እንኳን ባል ነፈቃ የማድረግ ግዴታ አለበት። ከዚህ ውስጥ የሚገባው ሚስቱ አስተማሪ ብትሆንና መጀመሪያ ላይ ለማስተማር እንደሚፈቅድላት ተስማምተው ከሆነ እሷ በምታገኘው ገቢ ላይ ምንም ሀቅ የለውም ግማሹንም ይሁን ከግማሽ በታች የመውሰድ መብት የለውም። ደሞዟ የራሷ ነው።...... ነገር ግን መጀመሪያ ላይ እንድታስተምሪ እፈቅድልሻለሁ ብሎ ካላለ ከዛ በሗላ አታስተምሪም ብሎ ከከለከላት በፈለጉት መልኩ ስምምነትን መፈፀም ይችላሉ። ለምሳሌ እንድታስተምሪ ፈቅድልሻለሁ ግን ከደሞዝሽ ግማሹን ወይም ⅓ ወይም ¾ ወይም ¼ የመሳሰሉትን ልትሰጪኝ ብለው በተስማሙበት መጠን ቢስማሙና ብታስተምር ይችላል። ነገር ግን መጀመሪያ ለማስተማር መስፈርት አድርጋ ተስማምቶ ከነበረ ከደሞዟ ሊቀበላት አይፈቀድለትም። 📚 (ሸርህ ሪያድ 6/143 - 144) https://t.me/+RfyKpcYtbiP7Fu1W https://t.me/+RfyKpcYtbiP7Fu1W
إظهار الكل...
🇸🇦ተውሒድ የጀነት ዋጋ ነው !!🇸🇦 ኢብኑ ተይሚያ እንድህ አሉ

የተውሂድ አሳሳቢነት"!! ሸይኸ ኢብኑ ዑሰይሚን ረሂመሁሏህ እንዲህ ይላሉ አንድ ሰው ጌታውን ሲገዛው በእውቀት ላይ ይሆን ዘንድ የተውሂድንና የአቂዳን ትምህርት መማሩ በሱ ላይ ግደታ ነው!!! ( 📚መጅሙዕ አል'ፈታዋ(2/78) 👉ምክረ አስታያት ካላቹ መልክታቹ በዚህ ሊክ ይደረሰኛል👇👇 @Umu_hebtullah_Aselfyah

ቁርኣን እያስተማሩ ደመወዝ መቀበል ~ ጥያቄ፦ ህፃናትን የከበረውን ቁርኣን በማሰሐፈዝ ደመወዝ መቀበል ብይኑ ምንድነው? "ይቻላል" የምትሉ ከሆነ ወርሃዊ ደመወዝ የሚቀበል አስተማሪ ከአላህ ዘንድ ምንዳ ይኖረዋል ወይ? መልስ፦ የከበረውን ቁርኣን መማርና ማስተማር - ኒያ ከተስተካከለ - ከትልልቅ ወደላቀውና ከፍ ያለው አላህ መቃረቢያዎች ውስጥ ነው። ነብዩም (ﷺ) {ከናንተ በላጫችሁ ቁርኣንን ተምሮ ያስተማረ ነው} በማለት ቁርኣንን በመማርና ማስተማር ላይ አነሳስተዋል። የቁርኣን አስተማሪዎች በማስተማራቸው የተነሳ ደመወዝ መቀበላቸው ምንዳ ከመገኘቱ ጋር የሚቀረን አይደለም። ከአላህ - ጀለ ወዐላ - ምንዳ የሚገኘው ኒያው የጠራ (ለአላህ ብቻ የሆነ) ከሆነ ነው። ... " ምንጭ [ፈታዋ ለጅነቲ ደኢማህ፡ 15/ 99] ፈትዋውን የሰጡት 1- ዐብዱልዐዚዝ ብኑ ዐብዲላህ ብኒ ባዝ 2- ዐብዱልዐዚዝ ኣሊ ሸይኽ 3- ዐብዱላህ ብኑ ጉደያን 4- ሳሊሕ አልፈውዛን 5- በክር አቡ ዘይድ = https://t.me/Aselfyah
إظهار الكل...
የስለፊያ ጎዳና ትክክለኛዋ ጎዳና ናት።

#ለሰለፍያ #አንገታችንን #እንሰጣለን | #ለሰለፍያ #ህይወታችንን #እንሰጣለን | ሰለፍያ ማለት ያ ነብዩና የነብዩ ባልደረቦች የነበሩበት ትክክለኛው እስልምና ማለት ነው ፡፡ የአላህ ሶለትና ሰላም በነብዩና በነብዩ ባልደረቦች ላይ ይሁን | ይህች ዑመት ከማንኛውም አደጋ ሰላም ምትሆነው ብቸኛውን የሰለፎችን መንገድ ስትከተል ብቻና ብቻ ነው !!

https://t.me/Aselfyah