cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Hule Addis Media ( ሁሌ አዲስ ሚዲያ)

ትክክለኛዉ የሁሌ አዲስ ሚዲያ ገፆች Facebook : bit.ly/42rUuKj WhatsApp : bit.ly/Huleadis_whatsapp YouTube : bit.ly/3p7kj3N Twitter : bit.ly/3NVMRrB Telegram: bit.ly/Huleadis_tele ለጥቆማ ና አስተያየት እንዲሁም ለማስታወቂያ ስራ ተከታዮን አድራሻ ይጠቀሙ bit.ly/3VMy7x7

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
3 180
المشتركون
+124 ساعات
-127 أيام
-1930 أيام
توزيع وقت النشر

جاري تحميل البيانات...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
تحليل النشر
المشاركاتالمشاهدات
الأسهم
ديناميات المشاهدات
01
ማንችስተር ሲቲ የሊጉን መሪነት ተረከበ ! ማንችስተር ሲቲ ከቶተንሀም ጋር ያደረገውን የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ሰላሳ አራተኛ ሳምንት ተስተካካይ መርሐ ግብር 2ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የሊጉን መሪነት መረከብ ችለዋል። የማንችስተር ሲቲን የማሸነፊያ ግቦች ኤርሊንግ ሀላንድ 2x ከመረብ ማሳረፍ ችሏል። ኬቨን ዴብሮይን አንድ መቶ አስራ ሁለተኛ ለግብ የሆነ ኳሱን አመቻችቶ በማቀበል በሊጉ ታሪክ ብዙ አመቻችቶ ያቀበለ #ሁለተኛው ተጨዋች ሆኗል። ኖርዊያዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኤርሊንግ ሀላንድ በውድድር ዘመኑ ሀያ ሰባተኛ የሊግ ግቡን ማስቆጠር ችሏል። ማንችስተር ሲቲ በአዲሱ የቶተንሀም ስታዲየም የመጀመሪያ የፕርሚየር ሊግ ጎል ማስቆጠር ችሏል። በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ስንተኛ ናቸው ? 1️⃣ ማንችስተር ሲቲ :- 88 ነጥብ 5️⃣ ቶተንሀም :- 63 ነጥብ ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ? እሁድ - ማንችስተር ሲቲ ከ ዌስትሀም ዩናይትድ እሁድ - ሼፍልድ ከ ቶተንሀም
460Loading...
02
በኢትዮጵያ 95 በመቶ የሚሆኑት የቴሌቭዥን ተጠቃሚዎች በኢትዮ-ሳት ስርጭት እያገኙ መሆኑ ተገለፀ በኢትዮጵያ ከ18.2 ሚሊዮን ቲቪ ተጠቃሚዎች መካከል 17 ሚሊዮን ወይም 95 በመቶ የሚሆኑት በኢትዮ-ሳት ስርጭት እያገኙ መሆኑን የዓለም አቀፉ የሳተላይት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት አቅራቢ (SES) አስታወቀ። በኢትዮጵያ የቴሌቪዥን ተጠቃሚዎች ቁጥር በ 2017 ከነበረበት በ400% አድጎ ተጠቃሚዎቹ 18.2 ሚሊዮን መድረሳቸው ሲገልፅ ከ2021 ጀምሮ የኢትዮ ሳት የኤችዲ ቲቪ ቻናሎች ከ15 በመቶ ወደ 62 በመቶ ማደጉ ተነግሯል። በአሁኑ ወቅት በሳተላይቱ 136 ቻናሎች ለ17 ሚሊዮን የቴሌቪዥን ባለቤቶች እየተሰራጩ ሲሆን ከ136 የሬዲዮና የቴሌቪዥን ቻናሎች መካከል ደግሞ 70 የሚሆኑት የሀገር ውስጥ ቻናሎች መሆናቸው ተጠቁሟል። 'ኢትዮ-ሳት' ን የኢትዮጵያ ሚዲያ ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ)፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስተሮች ማህበር (ኤቢቢ) እና SES በጋራ በመሆን ከ4 አመት በፊት ይፋ እንዳደረጉት ይታወሳል።
680Loading...
03
በፕሮጀክት ስም የሚወጣው ገንዘብ ? በየዩኒቨርሲቲዎች " ለሥራ ኃላፊዎች የሚከፈል ክፍያ " በሚል የሚመዘበረው ገንዘብ  ከፍ ያለ ነው። ሰዎቹ ከመንግሥት በጀት / አካል ውጭ ተጻጽፈን በሚመጣልን ድጋፍ ፕሮጀክት እየሰራን ብር ይከፈለናል ነው የሚሉት። ክፍያው ግን እጅግ የተጋነነ ከመሆኑ የተነሳ ግልጽነት የጎደለው፣ ብዙ ጥርጣሬንም የሚያጭር ነው። መንግሥት ደመወዛቸውን እየከፈላቸው እያለ " ላስተባበሩበት " በሚል እዛው ግቢያቸው ውስጥ ለሚሰራ ስራ የሚከፈላቸው ብር ብዛት የሚገርም ነው። ለአብነት፦ ሰሞኑን ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲው ውስጥ ስለሚፈጸም አይን ያፈጠጠ የለየለት የህዝብ ሀብት ምዝበራን በተመለከተ በተሰራጨው የፋና ምርመራ ዘገባ ላይ ዶ/ር ተመስገን ቶማስ በሰኔ ወር 2013 ዓ/ም ብቻ የተከፈላቸው ገንዘብ በርከት ያለ ነው። ዶክተሩ ምንም እንኳን " ቁጥሩም እኮ ሳይገለጽ መነጋገር እንችላለን " ቢሉም አይገለጽ ያሉት ቁጥር ግን ይህንን ይመስላል። ➡ 19,500 ብር (ሰንድ 1) ➡ 11,700 ብር (ሰንድ 2) ➡ 23,212 ብር (ሰንድ 3) ➡ 19,500 ብር (ሰንድ 4) ➡ 7,800 ብር (ሰንድ 5) ➡ 23,400 ብር (ሰንድ 6) ➡ 19,500 ብር (ሰንድ 7) ➡ 19,500 ብር (ሰንድ 8) ➡ 15,600 ብር (ሰንድ 9) ➡ 14,644 ብር (ሰንድ 10) ➡ 14,644 ብር (ሰንድ 11) ➡ 22,000 ብር (ሰንድ 12) ➡ 17,500 ብር (ሰንድ 13) ➡ 23,400 ብር (ሰንድ 14) ➡ 39,000 ብር (ሰንድ 15) ➡ 19,500 ብር (ሰንድ 16) ➡ 14,644 ብር (ሰንድ 17) ➡ 19,500 ብር (ሰንድ 18) ➡ 14,644 ብር (ሰንድ 19) ➡ 21,450 ብር (ሰንድ 20) እኚህ ሁሉ በሰኔ ወር 2013 የተከፈሉ ናቸው። ዶክተሩ ግን እስቲ ልየው 😳 በሰኔ ወር ነው የተከፈለው ? ብለው ይጠይቃሉ ዶክመቱም ይሰጣቸዋል፤ በኃላም ዶክመንቱን ያገላብጡና " እስቲ 2013 የሚለው የታለ ? " ሲሉ ድጋሜ ይጠይቃሉ " ይኸው ! " ይባላሉ ፤ በዝምታ ከተዋጡ በኃላ " እ ! " ብለው ዶክመንቱን መልሰዋል። ዶ/ር ተመስገን በተለያየ ጊዜ የተባከ ክፍያ የፋይናንስ ባጀት ስለሌለ በአመቱ መጨረሻ ባጀት ሲያገኝ ገብቶ ነው እንጂ በአንዴ የተላከ አይደለም ብለው ተከራርክረዋል። ሌላው የዩኒቨርሲቲው የፋይናንስ ዳይሬክተር ማርቆስ ዮሐንስ ብዙ ገንዘብ የተከፈላቸው ሲሆን " እኔ ብዙ ፕሮጀክት ስለምሰራ ነው። ቀንም ማታም ቅዳሜና እሁድም በፕሮጀክት  ላይ ሰራው ከመንግስት ስራ ሰዓት ውጭ ለዛ ነው የተከፈለኝ ባይ ናቸው። ዳይሬክተሩ በቀን 18 ሰኔ ወር 2013 ዓ/ም 13,650  ብር እንዲገባላቸው የታዘዘበት ዶክመት የተገኘ ሲሆን በቀን 23 / 2013 ዓ/ም 15,600 ብር እንዲገባላቸው ታዟል በተመሳሳይ ቀን 19,600 ብር እንዲገባላቸው ተደርጓል። ሌሎችም በርካቶች ናቸው ነው ያሉት። ዶ/ር ተመስገን ጨምሮ አሁን ስልጣን ላይ ያሉትን ዶክተር ሀብታሙ አበበ ጋር የፋይናንስ ዳይሬክተሩ ስም በክፍያ ዶክመት ላይ " ፕሮጀክት " ተብሎ ተገኝቷል። በአጠቃላይ በዋቸሞም ሆነ በመሰል ተቋማት በፕሮጀክት ስም የሚወጣው ብር እጅግ ብዙ ፣ ከደመወዛቸው እጥፍ፣ ግልጽነት የጎደለው ነው። ሌሎቹ ዩኒቨርሲቲዎችስ ?
2060Loading...
04
Media files
1850Loading...
05
ማይክ ሀመር ከኦሮሞ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ከፕሮፌሰር መረራ ጉዲና እና ዳውድ ኢብሳ ጋር መምከራቸው መከሩ የአሜሪካን መንግስት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ማይክ ሀመር #ከኦሮምያ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር ተወያዩ። ሀመር የመከሩት ከኦፌኮ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና እና ከኦነጉ ሊቀመንበር ዳውድ ኢብሳ ጋር መሆኑም ታውቋል። የኦፌኮ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ከማይክ ሀመር ጋር በሀገራዊ እንዲሁም በኦሮምያ ክልል ወቅታዊ ጉዳዮች መምከራቸውን ለአዲስ ስታንዳርድ አረጋግጠዋል። በሀገራዊ እና በኦሮምያ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለማይክ ሀመር ሙሉ ገለጻ እንዳደረጉላቸው ፕሮፌሰር መራራ ለአዲስ ስታንዳርድ አስታውቀዋል። ከማይክ ሀመር ጋር በነበረን ቆይታ ዋነኛ አጀንዳ የነበረው ሀገራዊ ምክክሩ ነበር ሲሉ የገለጹልን ፕሮፌሰር መረራ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ "ኢትዮጵያን የትም አያደርሳትም፣ ምክንያቱም ደግሞ ሁሉን ያሳተፈ አይደለም፣ በሁሉም ዘንድ ደግሞ እምነት የሚጣልበት አይደለም" ሲሉ እንደገለጹላቸው ለአዲስ ስታንዳርድ አስታውቀዋል። ሌላኛው ከማይክ ሀመር ጋር በነበረን ውይይት የተነሳው ነጥብ የበቴ ኡርጌሳ ግድያ ነበር ያሉት መረራ ጉዲና የፈጠረባቸውን ድንጋጤ እና የቤተሰቦቹ እስር እንዳሳዘናቸው በመግለጽ ስሜቴን ለልዩ ልዑኩ አጋርቻለሁ ብለውናል። በተያያዘ ዜና የአሜሪካ መንግስት ልዩ ልዑኩ ማይክ ሀመር በአዲስ አበባ በሚገኘው የአሜሪካን ኤምባሲ ከኦነጉ ሊቀመንበር ዳውድ ኢብሳ ጋር መምከራቸውም ከፓርቲያቸው ቃል አቀባይ ለሚ ገመቹ የኤክስ ማህበራዊ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያሳያል። ዳውድ ኢብሳ እና ማይክ ሀመር በምን ጉዳዮች ላይ እንደመከሩ ቃል አቀባዩ ያሉት ነገር የለም።   
1900Loading...
06
Media files
1780Loading...
07
በሰሜን ሸዋ ዞን ሁለት ወረዳዎች ዉስጥ በሚገኙ ት/ት ቤቶች የድሮን ጥቃት መፈጸሙ የተነገረ ሲሆን በጥቃቱ ንጹሃን ገበሬዎች ሲገደሉ ፤ አንዲት መምህርት ተጎድታለች ተባለ 👉🏼 ጥቃቱ በቀወት እና ጣርማበር ወረዳዎች ተፈጽሟል በትናንትናው ዕለት በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ቀወት ወረዳ ተሬ ቀበሌ ልዩ ስሙ ጉሎ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ የድሮን ጥቃት መፈጸሙን ነዋሪዎች ለአል ዐይን አማርኛ ተናግረዋል፡፡ ለደህንነቱ በመፍራት ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ የተሬ ቀበሌ ነዋሪ እንዳለው “ትናንት ግንቦት 4 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 ላይ በመንደራችን ከባድ ፍንዳታ ተፈጥሮ ነበር። እኔን ጨምሮ የሰፈራችን ነዋሪዎች ፍንዳታው ወደ ተሰማበት ስፍራ ስንሄድ ጥቃቱ ጉሎ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ እንደተፈጸመ አየን” ሲል ተናግሯል፡፡ አስተያየት ሰጪው አክሎም “በዚህ የድሮን ጥቃት ሶስት አርሶ አደሮች ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ በትምህርት ቤቱ ውስጥ ትኖር የነበረች ሴት መምህር ከባድ ጉዳት ደርሶባት ወደ ሆስፒታል ተልካለች” ሲልም አክሏል፡፡ “አንድ ሌላ አርሶ አደር በተመሳሳይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶበት ወደ ሆስፒታል መወሰዱን አውቃለሁ” ያለን ይህ የአይን እማኝ አንድ አርሶ አደር ደግሞ ቀላል ጉዳት እንደደረሰበትም ተናግሯል፡፡ በአካባቢው በመንግስት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ ከተጀመረ አንድ ዓመት እንደሆናቸው የሚናገሩት እኝህ ነዋሪ የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች አልፎ አልፎ ብቅ እያሉ ንጹሃን ሰዎችን ፋኖን ትረዳላችሁ እያሉ ወጣቶችን ይገድላሉ ብሏል፡፡ በዚህ ምክንያት የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች መጡ ሲባል በተለይም ወጣቶች ወደ ጫካ እንደሚሄዱ እና እንደሚደበቁም ይህ አስተያየት ሰጪ ተናግሯል፡፡ በተመሳሳይ በዞኑ በጣርማበር ወረዳ በሚገኘው የመዘዞ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ የድሮን ጥቃት መፈሙን ስማቸውን እንዳይጠቀስ የፈለጉ ነዋሪ ለአል ዐይን አማርኛ መናገራቸውን ሁሌ አዲስ ሚዲያ ከዘገባው ተመልክቷል። ነዋሪው እንደገለጹት በዚህ የድሮን ጥቃት በሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል። ጥቃቱ ትናንት ግንቦት 5 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ ሰባት ሰአት ላይ መድረሱን የገለጹት እኝህ ነዋሪ በጥቃቱ የተጎዱ ሰዎች ወደ ጤና ጣቢያ ሲገቡ መመልከታቸውን ተናግረዋል። የሰሜን ሸዋ ዞን ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ እና የሀገር መከላከያ ሰራዊት ተፈጸሙ ስለተባሉ የድሮን ጥቃቶች ያለውን ምላሽ ለማካተት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም ብሏል የዜና ምንጩ፡፡ በአማራ ክልል በተደጋጋሚ በተፈጸሙ የድሮን ጥቃቶች ንጹሃን ዜጎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽንን ጨምሮ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማት እና ምዕራባዊያን ሀገራት ባወጧቸው ሪፖርቶች ላይ ጠቅሰዋል፡፡እነዚህ ተቋማት እና ሀገራት የድሮን ጥቃቶች እንዲቆሙ ንጹሃን ዜጎችም ከጥቃት እንዲጠበቁ ቢጠይቁም የሀገር መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የድሮን ጥቃቱ እንደሚቀጥል እና ኢላማውን የጠበቀ ጥቃት ማድረሳችንን እንቀጥላለን ሲሉ ምላሽ መስጠታቸው አይዘነጋም፡፡ በክልሉ በፋኖ ታጣቂዎች እና በመንግስት ወታደሮች መካከል የተቀሰቀሰውን ግጭት ተከትሎ ከሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁ የሚታወስ ሲሆን ለተጨማሪ አራት ወራት የተራዘመ መሆኑ አይዘነጋም። ሆኖም ይህ አዋጅ አሁን ላይ ሊጠናቀቅ ሶስት ሳምንታት ቀርቶታል።
2060Loading...
08
Media files
1750Loading...
09
በሱዳን ጥገኝነት ለጠየቁ የቀድሞ ሰላም አስከባሪዎች ጥበቃ እንደሚያደርግ የስደተኞች ተቋሙ ገለጸ! በሱዳን በጥገኝነት እየኖሩ ያሉ የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ አባላት፣ ተፋላሚው የሱዳን "ፈጥኖ ደራሽ ኀይሎች"፣ በሰሞኑ መግለጫው ካቀረበው የጣልቃ ገብነት ክስ ጋራ ተያይዞ የደኅንነት ስጋት እንዳደረባቸው ገለጹ፡፡ ለደኅንነታቸው በመስጋት ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁን የትግራይ ተወላጅ የሰላም አስከባሪ አባላት፣ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃለ መጠይቅ፣ የሱዳን "ፈጥኖ ደራሽ ኀይሎች" ባወጣው መግለጫ፣ የህወሓት ታጣቂዎች በሱዳኑ ጦርነት እየተሳተፉ እንደኾነ ያቀረበው ክስ፣ “በመጠለያ ጣቢያዎች ያለነውን ስደተኞች ለጥቃት እንዳይዳርገን ስጋት ፈጥሮብናል፤” ብለዋል፡፡ ስለ ጉዳዩ ለአሜሪካ ድምፅ በኢሜይል አስተያየት የሰጠው የተባበሩት መግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር በበኩሉ፣ “የስደተኞቹን የደኅንነት ስጋት እረዳለኹ፤ ኹኔታውን የተመለከተ መፍትሔም እያፈላለግኹ ነው፤” ብሏል፡፡ [VoA]
1780Loading...
10
በጅግጅጋ ከተማ የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ ተመረቀ! በጅግጅጋ ከተማ የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ በሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ ተመርቆ ስራ ጀምሯል።በ250 ሚሊየን ብር ካፒታል የተከፈተው ፋብሪካው በቀን እስከ 10 መኪኖችን የመገጣጠም አቅም እንዳለው ተገልጿል። ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ ፋብሪካውን መርቀው በከፈቱበት ወቅት እንዳሉት በክልሉ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎለበተ ይገኛል። ፋብሪካው ለዜጎች የስራ እድል ከመፍጠር ባለፈ የውጭ ምንዛሬ ወጪን በመቀነስ ረገድ ፋይዳው የላቀ መሆኑን ጠቁመው የክልሉ መንግስትም ለግሉ ዘርፍ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥል ብለዋል።
1630Loading...
11
በገጠር የመሬት ሽያጭ እና ግዢ የሚያከናውኑ ሰዎችን እስከ አምስት አመት በእስር የሚያስቀጣ አዋጅ በፓርላማ ጸደቀ የገጠር መሬትን በሸጠ ወይም በገዛ ማንኛውም ሰው ላይ እስከ አምስት ዓመት የሚደርስ ፅኑ እስራት ቅጣት የሚጥል አዋጅ በተወካዮች ምክር ቤት ጸደቀ። አዲሱ አዋጅ የግል፣ የወል ወይም የመንግስት ይዞታን በህገ ወጥ መንገድ ወርሮ ለተገኘ ሰውም ተመሳሳይ የእስራት ቅጣት ደንግጓል። የተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 6፤ 2016 በነበረው መደበኛ ስብሰባው በሙሉ ድምጽ ያጸደቀው ይህ አዋጅ፤ ከ18 ዓመት በፊት የወጣውን የገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም አዋጅን ያሻሻለ ነው። አዲሱ አዋጅ አርሶ አደሮች፣ አርብቶ አደሮች እና ከፊል አርብቶ አደሮች በመሬት ላይ ያላቸውን መብቶች ያሻሻለ ሲሆን፤ የሴቶች እና ድጋፍ የሚሹ ሰዎችን የመሬት ተጠቃሚነት መብት ያረጋገጡ ድንጋጌዎችንም አካትቷል። አዋጁ በረቂቅ ደረጃ ለፓርላማ ከቀረበ በኋላ ከተደረጉ ማሻሻያዎች መካከል፤ “የወንጀል ተጠያቂነት” በሚመለከተው የተጨመረው አንቀጽ ይገኝበታል። “ከመሬት ጋር ተያይዘው የሚፈጸሙ ወንጀሎች ላይ አስተማሪ እና ተመጣጣኝ ቅጣት ማስቀመጥ አስፈላጊ በመሆኑ” ምክንያት እንደተካተተ የተነገረለት ይህ ድንጋጌ፤ ከመሬት ወረራ እስከ መሬት ሽያጭ ድረስ ያሉ የህግ ጥሰቶች የሚያስከትሏቸውን ቅጣቶች ዘርዝሯል። ማንኛውም ሰው መሬት የሸጠ ወይም የገዛ እንደሆነ፤ ከ100 ሺህ እስከ 200 ሺህ ብር ወይም ከ1 ዓመት እስከ 5 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ወይም በሁለቱም ሊቀጣ እንደሚችል በአዲሱ ድንጋጌ ላይ ሰፍሯል። በኢፌዲሪ ሕገ መንግስት መሰረት “መሬት የማይሸጥ፣ የማይለወጥ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የጋራ ንብረት ነው”። ሕገ መንግስቱ የገጠርም ሆነ የከተማ መሬት የባለቤትነት መብትን የሰጠው “ለመንግስት እና ለህዝብ” ነው። ዛሬ በጸደቀው አዋጅ የግል፣ የወል ወይም የመንግስት ይዞታን በህገ ወጥ መንገድ የወረረ ማንኛውም ሰው፤ ከ1 ዓመት እስከ 5 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት አሊያም ከ30 ሺህ እስከ 100 ሺህ ብር ቅጣት ሊጣልበት እንደሚችል ተደንግጓል። በእነዚህ ይዞታዎች ላይ ጉዳት አድርሶ የተገኘ ማንኛውም ሰው፤ ከ3 ዓመት እስከ 7 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ወይም ከ50 ሺህ እስከ 150 ሺህ ብር እንደሚቀጣም በአዋጁ ላይ ተቀምጧል። ባልተፈቀደ ቦታ ላይ ማንኛውንም ግንባታ የሰራ ወይም እንዲሰራ የፈቀደ ሰው ደግሞ በአዲሱ አዋጅ መሰረት ከ1 ዓመት እስከ 3 ዓመት በሚደርስ እስራት አሊያም ከ25 ሺህ እስከ 50 ሺህ ብር ይቀጣል። እነዚህ ቅጣቶች፤ ከመሬት አጠቃቀም ዕቅድ ውጪ ይዞታውን ጥቅም ላይ አውሎ የተገኘ ሰው ላይ በተመሳሳይ መልኩ ተግባራዊ የሚደረጉ ይሆናል። ሀሰተኛ የመሬት ይዞታ ማስረጃ ያቀረበ ባለይዞታ እንዲሁም ማስረጃ የሰወረ ወይም የተሳሳተ ማስረጃ የሰጠ ባለሙያ ላይ የሚጣለው እስራት ከላይ እንዳሉት የህግ ጥሰቶች ተመሳሳይ ቢሆንም የገንዘብ ቅጣቱ መነሻ ግን ወደ 20 ሺህ ብር ዝቅ ብሏል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
1670Loading...
12
Media files
1470Loading...
13
ኩዌት ኢትዮጵያውያን ሰራተኞችን በሀገሯ ለማሰራት የሰራተኛ ምልመላ ልትጀምር ነው ተባለ ኢትዮጵያ እና ኩዌት ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች በኩዌት ሀገር የስራ አድል አንዲያገኙ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነቱን ለማጠናቀቅ የመጨረሻው ሂደት ላይ መሆኑን የሀገሪቱ የዜና ምንጮች ዘግበዋል፡፡ የመግባቢያ ስምምነቱ በዚህ ወር መጨረሻ ይፈረማል የተባለ ሲሆን ስምምነቱ የሰራተኞችን መብት፤ አሰሪዎች የስራ ውል በሚያቋርጡበት ጊዜ ሰራተኞች ስለሚያገኙት ክፍያ፤ የሰራተኞች የሳምንት፣ የአመት እረፍት እና ተያያዥ ስምምነቶችን የያዘ መሆኑ ተነግሯል፡፡ የሰራተኛ ምልመላው ስምምነቱ እንደተፈረመ ይጀመራል የተባለ ሲሆን ስምምነቱ ኩዌት ያጋጠማትን የሰራተኞች እጥረት ይቀርፋልም ነው የተባለው፡፡
1561Loading...
14
Media files
1961Loading...
15
በኢትዮጵያ ህገ መንግስት የተደነገገውን የሜዳይ፣ የኒሻን እና የሽልማት አሰጣጥ ተግባራዊ ማድረግ የሚያስችል አዋጅ ፀደቀ፡፡ በኢትዮጵያ ህገ መንግስት የተደነገገውን የሜዳይ፣ የኒሻን እና የሽልማት አሰጣጥ ስርዓት ተግባራዊ ማድረግ በሚያስችለው በዚህ ረቀቅ አዋጅ ላይ ውይይት ካደረገ በኃላ በሙሉ ድምፅ አፅድቆታል፡፡ የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የህግ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ይህንን የኒሻን እና ሜዳይ ሽልማትን በተመለከተ ውይይት እና አስተያየት ከተደረገበት በኃላ አዋጁ እንዲፀደቅ ጠይቀዋል፡፡ በዚህም የምክር ቤቱ አባላት የሜዳይ፣ የኒሻን እና የሽልማት አሰጣጥ ስርዓትን በተመለከተ ያለውን አዋጅ በሙሉ ድምፅ እንዲፀድቅ ተደርጓል፡፡ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔውን ያሳለፈው ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 6 2016 ባደረገው 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 26ኛ መደበኛ ስብሰባውን ባደረገበት ወቅት ነው፡፡ የሜዳይ ወይም ኒሻን ተሸላሚ የሚሆኑ አካላት በህዝብ መገልገያ ቦታዎች ላይ ቅድሚያ ይሰጣቸዋል እንዲሁም ከእዚህ ዓለም በሚያርፉ ግዜ በክብር እነዲሸኙ የሚያስችልም አዋጅ የተካተተበት መሆኑ ተገልፃል፡፡
2231Loading...
16
የአገር ውስጥ በረራ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር በተለያዩ አከባቢዎች ከተፈጠረው የፀጥታ ችግር ጋር ሊገናኝ እንደሚችል ተጠቆመ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተጓዦች ቁጥር እንዲጨምር ያደረገው በሀገሪቱ በተከሰቱ የፀጥታ ችግር መንገዶች በመዘጋታቸው እንዲሁም በሌሎች በብዙ ምክንያቶች መሆኑን አስታዉቋል ። የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰዉ በተለይ ለካፒታል እንደተናገሩት " የሀገር ዉስጥ የአየር ትራንስፖርት ፍላጎት ለማደጉ የፀጥታ ችግር እንደ አንድ ምክንያት ሊጠቀስ እንደሚቻል ጠቁመዉ ከዚህ በተጨማሪ ግን ደንበኞች ለመጓጓዣነት አዉሮፕላንን ምርጫቸዉ በማድረጋቸው በሌላ በኩል ደግሞ የተጓዦች የገቢ መጨመር በመኖሩ ነዉ" ብለዋል። ይህም ቢሆን በፀጥታ ምክንያት መንገዶች ሲዘጉ የአየር ትራንስፖርት መጠቀም እንደ አማራጭ መታየቱን ዋና ስራ አስፈጻሚዉ ተናግረዋል ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ባለፈው ወር እንደገለጹት እየተጠናቀቀ ባለው በጀት አመት የአገር ውስጥ ተጓጓዦች ቁጥር 3.5 ሚሊየን ይደርሳል ብሏል። ይህ መጠን ከ2015 በጀት አመት አንጻር የ34.6 በመቶ ጭማሪ ይኖረዋል ያሉት አቶ መስፍን ጣሰዉ በቀደመው አመት በአገር ውስጥ በረራ የተስተናገዱት ተሳፋሪዎች 2.6 ሚሊየን እንደነበሩ አስታዉሰዋል። (ካፒታል)
2112Loading...
17
ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ? በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ሲፈጸም እንደቆየ የተነገረለት እጅግ በጣም የለየለት የህዝብ ገንዘብ እና ሀብት ምዝበራን የሚያሳይ የ " ፋና ቴሌቪዥን " የምርመራ ዘገባ ስራ ከሰሞኑን ለህዝብ ተሰራጭቶ ነበር። 👉 በአበል መልክ የሚመዘበረው ገንዘብ ፦ የተቋሙ ገንዘብ በአበል መልክ ይመዘበራል። ለአብነት ሁለት የፋይናንስ ቡድን መሪዎች ከፍተኛ አበል ለራሳቸው ከፍለዋል። አቶ መሰረት ለማ የተባሉት ግለሰብ በ6 ወራት ብቻ የ1 ሺህ 496 ቀን ይህ ማለት 1 ሚሊዮን 56 ሺህ 854 ብር አበል ተከፏላቸዋል። አቶ ደስታ ደቦጭ የሚባሉት ደግሞ የ940 ቀን አበል ወስደዋል። ➡️አቶ ደስታ የስንት ቀን አበል ወሰዱ ? ሲባሉ " የ790 ቀን ነው የወሰድኩት " ብለዋል። ወስደዋል እንዴ ? ተብለው በመርማሪ ጋዜጠኛው ሲጠየቁ " #አልወሰድኩም " ሲሉ ቃላቸውን አጥፈው ተናግረዋል። ➡️አቶ መሰረት የ1 ሺህ 496 ቀን አበል ወደ አካውንቶ ገብቷል ? ተብለው ሲጠየቁ " ይሄ ስህተት ነው የተሰሳሳተ ነው " ሲሉ መልሰዋል። የተቋሙ ፋይናስ ዳይሬክተር አቶ ማርቆስ ዮሐንስ ፥ " እኔ ለረጅም ወራት ፍቃድ ላይ ነበርኩኝ የህመም ፍቃድ ላይ ከመጣሁ በኃላ ነው እንደዚህ አይነት ነገር እሰማ ነበር " ብለዋል። አቶ ደስታ ግን በዚህ አይስማሙም፤ አቶ ማርቆስ ታመው ቤት የተቀመጡት 2 ወር ብቻ እንደነበር የወጣው ደግሞ የ5 ወር መረጃ እንደሆነ ገልጸዋል። 3 ወር የሰራው እራሱ ነው ሲሉ አጋልጠዋል። ቀደም ሲል " እኔ አበል አልወሰድኩም " ያሉት አቶ ደስታ 3 ወር የሰራው እራሱ ነው ሲሉ እሱ እያለ ነው የተከፈሎት ? ተብለው ሲጠየቁ " ምኑን ? እንደ ስራ ባህሪ የተከፈለኝ ነገር ሊኖር ይችላል " ሲሉ መልሰዋል። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዜዳንት ሀብቶሙ አበበ (ዶ/ር) ፥ " በሰነድ የተረጋገጠ ነው ብሎ የውጭ ኦዲት ያመጣውን ያክል አስመልሰናል ሰራተኞቹ ከስራ እንዲታገዱ ተደርጓል፤ በዲስፒሊም እየተጠየቁ ናቸው የኛ ኦዲት ያመጣውን የትራዛክሽኑን ቼክአፕ በህግ እንዲጣራ ክትትል እየተደረገ ነው " ብለዋል። የፋይናስ ስርአታቹ ክፍተት ያሉት ይመስላል ሲባሉ " በፍጹም በፍጹም !! " ሲሉ መልሰዋል። 👉 ከ1 ቢሊዮን ብር በላዩ ፕሮጀክት ፦ ለኦክስጅን ማምረቻ በሚል ከ1.4 ቢሊዮን ብር በላይ ግልጽነት በጎደለው መልኩ ተፈጽሟል። በዚህ ጉዳይ ፕሬዜዳንቱ እና የፋይናንስ ዳይሬክተሩ እርስ በእርስ የሚያወዛግብ ምላሽ ነው የሰጡት። የፋይናንስ ዳይሬክተሩ ያለ ሰነድ ከእውቅናቸው ውጭ ገንዘቡ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ ይገልጻሉ። ክፍያ ሲፈጸም ሰነድ እጃቸው ላይ እንደሌለ እና እሳቸውም እንዳልተሳተፉ ተናግረዋል። የፋይናንስ ዳይሬክተሩ " እኔ እኮ ዝርዝር መረጃ አልተሰጠኝም ፤ እንደሚንቀሳቀስ አያለሁ እሰማለሁ " ብለዋል። ገንዘቡን እኔ አላንቀሳቅስም ነበር ብለዋል። ፕሬዜዳንቱ ግን የኦክስጂን ፕሮጀክት በጀቱ ሲመራ የነበረው በፋይናንስ ነው ብለዋል። የፋይናንስ ዳይሬክተሩ እኔ ሳላውቅ ነው ክፍያው የተፈጸመው ሲሉ ተናግረዋል። የቀድሞ ም/ፕሬዜዳንት ፀደቀ ላምቦሬ (ዶክተር) ፤  የአካውንቱ ጉዳይ በዋነኝነት የሚመለከተው ፕሬዜዳንቱን እንደሆነ ገልጸዋል። ▪️ለኦክስጅን ማምረቻው መሳሪያውን ያቀረበው ያለጨረታ ያለፍቃድ ያለውድድር 240 ሚሊዮን 988 ሺህ ብር ተሰጥቶታል። ለድርጁ ሙሉ ክፍያ ቢከፈልም ዝርጋታው ግን አላለቀም ስራውም አልተሰራም። ከተጀመረ 2 ዓመት አልፎታል። (አዘጋጅ ፦ ጋዜጠኛ አፈወርቅ እያዩ) Tikvahethiopia
1880Loading...
18
Media files
1950Loading...
19
ዜና: #በአዲስ አበባ በሻማ ፋብሪካና ጋራዥ ላይ በተነሳ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ፣ በአደጋዉ በሰዉ ላይ የደረሰ ጉዳት የለም ተብሏል በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ-ከተማ ወረዳ አምስት ኢንዱስትሪ መንደር ትላንት ግንቦት 5 ቀን 2016 ዓ.ም ሌሊት ላይ በሻማ ፋብሪካና ጋራዥ ላይ የተነሳዉ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ከባድ ጉዳት ማድረሱን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳወቀ። በእሳት አደጋዉ አክማ የተባለዉ ሻማ ፋብሪካ አብዛኛዉ ክፍል የወደመ ሲሆን በፋብሪካዉ አጠገብ በነበረዉ ጋራዥ ዉስጥ የነበሩ አምስት ተሽከርካሪዎች ላይም ከባድ ጉዳት ደርሷል። የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር አምስት የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪና 40 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የተሰማሩ ሲሆን፤ የእሳት አደጋዉ በአቅራቢያ ወደ አሉት ፋብሪካዎች ሳይዛመት መቆጣጠር ተችሏል። የፋብሪካዉን ከፊል ማሽነሪዎችን በጋራዡ የነበሩ በርካታ ተሽከርካሪዎችንም ማዳን ተችሏል። በፋብሪካዉ የነበሩ ጥሬ ዕቃዎችና ተቀጣጣይ ኬማካሎች ለእሳቱ መባባስ አስተዋጾኦ ማድረጉ ተጠቁሟል። የአደጋዉ መንስዔ በፖሊስ እየተጣራ መሆኑን እና በአደጋዉ በሰዉ ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን የኮሚሽኑ ህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ መግለጻቸውን ከኢፕድ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
2571Loading...
20
በአፍሪካ ወደ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ለሚደረገው ፈጣን ሽግግር ኢትዮጵያ ማሳያ ናት ተባለ ** ኢትዮጵያ በነዳጅ ከሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ይልቅ በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን የመጠቀም ልምድ እንዲያድግ የወሰደችው እርምጃ በአፍሪካ ጥሩ ምሳሌ መሆኑን ግሪን ቴክኒካ የተሰኘ የዜና አውታር አስታውቋል፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚሰሩ የአረንጓዴ ልማት ሥራዎች ላይ ትኩረት በማድረግ ዘገባዎችን የሚሰራው ግሪን ቴክኒካ፤ ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት 10 ዓመታት ውስጥ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሸከርካሪዎችን ቁጥር 148 ሺህ ለማድረስ ማቀዷን ዘግቧል። አገሪቱ ባለፉት 2 ዓመታት ብቻ በሀገሪቱ ያሉ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሸከርካሪዎች 100 ሺህ እንዲደርሱ ማድረጓ ለአረንጓዴ ልማት ምን ያህል ቁርጠኛ መሆኗን ያሳያል። በኢትዮጵያ ጎዳናዎች ከሚነዱ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች መካከል 10 በመቶ ያህሉ በሀገር ውስጥ የተገጣጠሙ መሆናቸው "አስደሳች ዜና ነው" ሲል ገልጾታል ተቋሙ፡፡ ኢትዮጵያ በሀገር ውስጥ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ለሚያመርቱ ኩባንያዎች ልዩ ድጋፍ እንደምታደረግ ይፋ ማድረጓን ተከትሎ በዘርፉ ላይ የተሰማሩ ኩባንያዎች ቁጥር እያደገ መምጣቱን በዘገባው ተመላክቷል።
3270Loading...
21
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ትናንት እኩለ ላሊት ላይ በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 9 የተለካ ርዕደ መሬት ተከስቷል። የርዕደ መሬቱ ማዕከል በና ጸማይ ወረዳ ከከርሰ ምድር 10 ኪሎ ሜትር ጥልቀት ላይ ሲኾን፣ ክስተቱ ግን ባጠቃላይ በዞኑ አራት ወረዳዎችና ጂንካን ጨምሮ በኹለት ከተምች እንደተከሰተ የአካባቢው አስተዳዳሪዎች ለአገር ውስጥ ዜና ምንጮች ተናግረዋል። ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ዳውሮ ዞን፣ በሬክተር ስኬል 3 ነጥብ ዜሮ  የተለካ ርዕደ መሬት ተከስቶ እንደነበር አይዘነጋም። የርዕደ መሬቱ ንዝረት በ474 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው አዲስ አበባ እንዲኹም በኦሮሚያ ክልል መተሃራ ከተማ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዲላ ከተማና ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሬክተር ስኬል 3 ነጥብ ዜሮ ርዕደ መሬት በተከሰተበት ዳውሮ ዞን ጭምር መሰማቱን ዓለማቀፍ የርዕደ መሬት ተከታታይ ተቋማት ገልጸዋል።
2950Loading...
22
Update ከሐዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበረዉ አዉሮፕላን ዉስጥ ታይቷል የተባለዉ ጭስ በዉስጡ ያለዉ ዘይት በመቃጠሉ የተነሳ መሆኑ ተገለፀ! የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰሞኑ በአዉሮፕላኑ ላይ የተከሰተው ጉዳይን አስመለክቶ እንዳስታወቀው ከእሳት ወይም ከሌላ ነገር ጋር የተያያዘ ሳይሆን አዉሮፕላን ዉስጥ ያለዉ ዘይት ተቃጥሎ ነዉ በወቅቱ የተከሰተው ጭስ ሊፈጠር የቻለዉ ይህም አልፎ አልፎ የሚያጋጥም ችግር ነዉ ብሏል። የአየር መንገዱ ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰዉ በተለይ ለካፒታል እንደተናገሩት " በአዉሮፕላኑ ዉስጥ ያለዉ ዘይት መጋጠሉ እና ከእርሱ ጋር ተያይዞ የተፈጠረ ጭስ ነዉ ይህ ደግሞ የተለመደ ነዉ ብለዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ET154 ሚያዝያ 29፣ 2016 ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ እያለ በአውሮፕላን ውስጥ ጭስ መታየቱን አስታዉቆ እንደነበር ይታወቃል። via Capital
3430Loading...
23
Media files
3390Loading...
24
በኢትዮጵያ ዉስጥ የሚገኙ ከ 6 ሺህ በላይ ሱዳናዉያን ስደተኞች በዉሃና በምግብ እጦት እንዲሁም በከፋ የፀጥታ ችግር ምክንያት ህይወታቸው ለአደጋ መጋለጡን አስታወቁ ከግንቦት ወር መጀመሪያ ጀምሮ በኢትዮጵያ ዉስጥ የሚገኙ ከ 6 ሺህ የሚበልጡ ሱዳናዉያን ስደተኞች በሀገሪቷ ታጣቂዎች የጥቃት ሰለባ ከመሆናቸው በላይ ከፍተኛ የምግብ እጥረት እና የህክምና አገልግሎት እጦት አጋጥሞናል ብለዋል። በሱዳን በጦር ኃይሎች እና ፈጣን ድጋፍ ሰጭ ሃይሎች መካከል እኤአ በሚያዝያ 2023 ጦርነት ከተቀሰቀሰበት ጊዜ ጀምሮ ኢትዮጵያውያን በአማራ እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በሚገኙ ካምፖች ውስጥ ስደተኞችን መቀበላቸው ይታወቃል ። በአማራ ክልል ኦላላ እና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ካርሙክ መጠለያ ካምፕ ዉስጥ የሚገኙት እነዚህ በሺዎች የሚቆጠሩ ሱዳናዉያን ስደተኞች ለሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን እንደተናገሩት በውሃ እጥረት እና በኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች ሳቢያ ህይወታቸው ለአደጋ ተጋልጧል። የችግሩን አሳሳቢነት በማረጋገጥ ትኩረት እንዲሰጣቸው የጠየቁት ስደተኞቹ በካምፕ ዉስጥ እየገጠመው ካለዉ ችግር ለመሸሽ በማለት ወደ ጫካ በመሰደድ ላይ መሆናቸው ታዉቋል። የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ኤጀንሲ (UNHCR) በአማራ ክልል 27,000 ሱዳናውያን ስደተኞች እና 20,000 በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እንደሚገኙ ግምቱን አስቀምጧል ። ካፒታል
2940Loading...
25
በቻይና የተገነባው ግዙፉ የኢትዮጵያ-ጁቡቲ የባብር መስመር ከግማሽ ሚሊዮን በላይ መንገደኞችን እና 9.5 ሚሊዮን ቶን ጭነት ማጓጓዝ መቻሉ ተነገረ የኢትዮጵያ -ጁቡቲ የባቡር መስመር የመንገደኞች እና የጭነት አገልግሎት የንግድ ስራ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ 9.5 ሚሊዮን ቶን ጭነት ያላቸው 7,700 የእቃ ማጓጓዣ ባቡሮች አገልግሎት መስጠት መቻላቸው ታዉቋል። በቻይና የተገነባዉና ሁለቱ ሀገራትን የሚያገናኘዉ የባቡር መንገዱ 752 ኪሎሜትር ርዝመት ያለዉ ሲሆን ስራ ከጀመረበት ዓመታት ወዲህ 2,500 የመንገደኞች ባቡሮችን እና  7,700 የጭነት ባቡሮች ማስተናገድ መቻሉንና 680 ሺህ መንገደኞች መጓጓዛቸዉን ካፒታል ያገኘው መረጃ ያመለክታል ። የአዲስ አበባ ጅቡቲ የባቡር መስመር ሥራ ከጀመረ ወዲህ የጅቡቲ ወደቦች የትራንስፖርት መጠን 20 በመቶ ገደማ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን የንግድ ትራንስፖርት ገቢም 11.3 ቢሊዮን ብር  በተመሳሳይ ጊዜ ውስጥ መገኘቱን የባቡሩ ማኔጅመንት ቡድን አስታውቋል ። መረጃዎች እንደሚያመላክቱት የባቡር መስመሩ የተገነባው ከቻይና ኤክስፖርትና ኢምፖርት ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በ4 ቢሊዮን ዶላር ብድር ነዉ። እ.ኤ.አ. በ2011 ከአዲስ አበባ ወደ ጁቡቲ የሚደረገው የባቡር ኮንትራት ግንባታ በሁለት የቻይና መንግሥታዊ ኩባንያዎች ማለትም በቻይና ምድር ባቡር ግሩፕ (CREC) እና በቻይና ሲቪል ኢንጂነሪንግ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የተጀመረ ሲሆን እኤአ በጃንዋሪ 2018 የመጓጓዣ አገልግሎት መጀመሩ ይታወቃል ። ካፒታል
2831Loading...
26
ግብጽ፣ እስራኤል በጋዛ በምታካሂደው ጦርነት የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጵማለች በማለት ደቡብ አፍሪካ በተመድ ፍርድ ቤት የመሠረተችውን ክስ እንደምትቀላቀል ትናንት አስታውቃለች። ግብጽ ይህን አቋሟን የገለጠችው፣ እስራኤል ጦሯን ለግብጽ አዋሳኝ ከኾነው ራፋህ አካባቢ እንድታስወጣ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ እንዲሰጥ ደቡብ አፍሪካ በጠየቀች ማግስት ነው። ካኹን ቀደም ኮሎምቢያና ቱርክ የደቡብ አፍሪካን ክስ መቀላቀላቸው አይዘነጋም። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ጦርነቱ የኹለትዮሽ ግንኙነታችን ንፋስ እንዲገባው አድርጓል በማለት የግብጽ ባለሥልጣናት ለእስራኤል ባለሥልጣናት ቅሬታቸውን እንደገለጡ መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። [ዋዜማ]
2780Loading...
27
ታጣቂ ኃይሎች ወደ ሰላማዊ ሕይወት እንዲመለሱ ትናንት በባሕርዳር ተገኝተው በአዲሱ የአባይ ድልድይ ምረቃ ላይ ባደረጉት ንግግር ጥሪ አቅርበዋል። ዐቢይ በዚኹ ንግግራቸው፣ "በማይገባ ነገር መገዳደል ይብቃ” የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ፣ ታጣቂ ኃይሎች ወደ ሰላም ተመልሰው ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ጋር ከሠሩ፣ ፌደራል መንግሥቱም የራሱን ትብብር ለማድረግ ዝግጁ እንደኾነ ገልጸዋል።
2950Loading...
28
ኢትዮጵያውያን ታዳጊ ህፃናት በአሜሪካ በተካሄደው የአለም አቀፍ የሮቦ ፌስት ውድድር አሸናፊ ሆኑ ኢትዮጵያውያኑ ሶስት ሽልማቶችን የግላቸው ያደረጉ ሲሆን የመጀመሪያው ከ 10 አመት በታች በተወዳደሩበት ሮቦ ፓሬድ የውድድር ዘርፍ ተሸልመዋል። ሁለተኛው ደግሞ በሲንየር ኤግዚቢሽን ከ14 -16 አመት ስፔሻል አዋርድ ሽልማትንም ማግኘት ችለዋል። በጁንየር ኤግዚብሽን ዘርፍ ደግሞ በአለም አቀፍ ውድድሩ የሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል።
3170Loading...
29
መድፈኞቹ ቀያዮቹ ሴጣኖችን ረቱ! በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የሰላሳ ሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር አርሰናል ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል። የመድፈኞቹን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ሊያንድሮ ትሮሳርድ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል። ሊያንድሮ ትሮሳርድ በዘንድሮው የውድድር አመት ለአርሰናል በሁሉም ውድድሮች አስራ ሰባት ግቦችን ማስቆጠር ችሏል። 👉 አርሰናል በ86 ነጥብ ሊጉን ዳግም መምራት የጀመረ ሲሆን እሁድ ከ ኤቨርተን የሊጉን የመጨረሻ ጨዋታ ያደርጋል።
3070Loading...
30
የዛሬ ጀምበር ወጥታ እስክትጠልቅ ለ #ጽዱኢትዮጵያ ስራችን ሃምሳ ሚሊዮን ብር ኢትዮጵያውያን ሁሉ ልናዋጣ አቅደን ነበር። ያሰብነውን ሳናሳካ ጀምበር የሚጠልቅብን አይደለንምና በአንድ ጀምበር ከ154 ሚሊዮን ብር በላይ ማዋጣት ችለናል። ኢትዮጵያን ሲያኮሩ የኖሩ አትሌቶች፣ ስፖርተኞች እና ደጋፊዎች፣ የዘወትር አገልጋይ የታክሲ አሽከርካሪዎች፣ ለኅሊናም ለአካባቢም ንፅህና የሚቀኙ ከያንያን፣ ምሁራን፣ ባለሃብቶች በቴሌቶኑ ስፍራ በመገኘት ላደረጉት አስተዋጽዎ እነሆ ምስጋና። በመላው አለም ሆነው በዛሬዋ ጀምበር በዲጂታል ቴሌቶኑ የተሳተፉ ከአርባ ሺህ በላይ ዜጎች ለፅዱ ኢትዮጵያ ያላቸው ምኞት መግለጫ የሆነው አስተዋፅዖ በተግባር በየአካባቢው በሚገነቡ የሕዝብ መፀዳጃዎች ይታወሳል። ይህ ትውልድ ጀምበር ወጥታ በገባች ቁጥር ለመጪው ትውልድ መስፈንጠሪያ የሚሆን ብሩህ እና ፅኑ መሰረት ደልድሎ ያወርሳል። ምኞት ተግባራችን ሁሉ የተሻለች ኢትዮጵያን በኅብረት ገንብቶ ማቆየት ነው። ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ
3030Loading...
31
Media files
3190Loading...
32
አዲስ አበባ, ጎሮ ገብርኤል በተክርስቲያን አጠገብ የተፈጠረ የእሳት አደጋ ትላንት ለሊት ከምሽቱ 6:30 ገደማ የተቀረፀ ቪዲዮ 4 :- ዛሬ የተቀረፀ ምንጭ:- ሀብታሙ
3340Loading...
Photo unavailableShow in Telegram
ማንችስተር ሲቲ የሊጉን መሪነት ተረከበ ! ማንችስተር ሲቲ ከቶተንሀም ጋር ያደረገውን የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ሰላሳ አራተኛ ሳምንት ተስተካካይ መርሐ ግብር 2ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የሊጉን መሪነት መረከብ ችለዋል። የማንችስተር ሲቲን የማሸነፊያ ግቦች ኤርሊንግ ሀላንድ 2x ከመረብ ማሳረፍ ችሏል። ኬቨን ዴብሮይን አንድ መቶ አስራ ሁለተኛ ለግብ የሆነ ኳሱን አመቻችቶ በማቀበል በሊጉ ታሪክ ብዙ አመቻችቶ ያቀበለ #ሁለተኛው ተጨዋች ሆኗል። ኖርዊያዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኤርሊንግ ሀላንድ በውድድር ዘመኑ ሀያ ሰባተኛ የሊግ ግቡን ማስቆጠር ችሏል። ማንችስተር ሲቲ በአዲሱ የቶተንሀም ስታዲየም የመጀመሪያ የፕርሚየር ሊግ ጎል ማስቆጠር ችሏል። በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ስንተኛ ናቸው ? 1️⃣ ማንችስተር ሲቲ :- 88 ነጥብ 5️⃣ ቶተንሀም :- 63 ነጥብ ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ? እሁድ - ማንችስተር ሲቲ ከ ዌስትሀም ዩናይትድ እሁድ - ሼፍልድ ከ ቶተንሀም
إظهار الكل...
👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
በኢትዮጵያ 95 በመቶ የሚሆኑት የቴሌቭዥን ተጠቃሚዎች በኢትዮ-ሳት ስርጭት እያገኙ መሆኑ ተገለፀ በኢትዮጵያ ከ18.2 ሚሊዮን ቲቪ ተጠቃሚዎች መካከል 17 ሚሊዮን ወይም 95 በመቶ የሚሆኑት በኢትዮ-ሳት ስርጭት እያገኙ መሆኑን የዓለም አቀፉ የሳተላይት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት አቅራቢ (SES) አስታወቀ። በኢትዮጵያ የቴሌቪዥን ተጠቃሚዎች ቁጥር በ 2017 ከነበረበት በ400% አድጎ ተጠቃሚዎቹ 18.2 ሚሊዮን መድረሳቸው ሲገልፅ ከ2021 ጀምሮ የኢትዮ ሳት የኤችዲ ቲቪ ቻናሎች ከ15 በመቶ ወደ 62 በመቶ ማደጉ ተነግሯል። በአሁኑ ወቅት በሳተላይቱ 136 ቻናሎች ለ17 ሚሊዮን የቴሌቪዥን ባለቤቶች እየተሰራጩ ሲሆን ከ136 የሬዲዮና የቴሌቪዥን ቻናሎች መካከል ደግሞ 70 የሚሆኑት የሀገር ውስጥ ቻናሎች መሆናቸው ተጠቁሟል። 'ኢትዮ-ሳት' ን የኢትዮጵያ ሚዲያ ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ)፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስተሮች ማህበር (ኤቢቢ) እና SES በጋራ በመሆን ከ4 አመት በፊት ይፋ እንዳደረጉት ይታወሳል።
إظهار الكل...
በፕሮጀክት ስም የሚወጣው ገንዘብ ? በየዩኒቨርሲቲዎች " ለሥራ ኃላፊዎች የሚከፈል ክፍያ " በሚል የሚመዘበረው ገንዘብ  ከፍ ያለ ነው። ሰዎቹ ከመንግሥት በጀት / አካል ውጭ ተጻጽፈን በሚመጣልን ድጋፍ ፕሮጀክት እየሰራን ብር ይከፈለናል ነው የሚሉት። ክፍያው ግን እጅግ የተጋነነ ከመሆኑ የተነሳ ግልጽነት የጎደለው፣ ብዙ ጥርጣሬንም የሚያጭር ነው። መንግሥት ደመወዛቸውን እየከፈላቸው እያለ " ላስተባበሩበት " በሚል እዛው ግቢያቸው ውስጥ ለሚሰራ ስራ የሚከፈላቸው ብር ብዛት የሚገርም ነው። ለአብነት፦ ሰሞኑን ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲው ውስጥ ስለሚፈጸም አይን ያፈጠጠ የለየለት የህዝብ ሀብት ምዝበራን በተመለከተ በተሰራጨው የፋና ምርመራ ዘገባ ላይ ዶ/ር ተመስገን ቶማስ በሰኔ ወር 2013 ዓ/ም ብቻ የተከፈላቸው ገንዘብ በርከት ያለ ነው። ዶክተሩ ምንም እንኳን " ቁጥሩም እኮ ሳይገለጽ መነጋገር እንችላለን " ቢሉም አይገለጽ ያሉት ቁጥር ግን ይህንን ይመስላል። ➡ 19,500 ብር (ሰንድ 1) ➡ 11,700 ብር (ሰንድ 2) ➡ 23,212 ብር (ሰንድ 3) ➡ 19,500 ብር (ሰንድ 4) ➡ 7,800 ብር (ሰንድ 5) ➡ 23,400 ብር (ሰንድ 6) ➡ 19,500 ብር (ሰንድ 7) ➡ 19,500 ብር (ሰንድ 8) ➡ 15,600 ብር (ሰንድ 9) ➡ 14,644 ብር (ሰንድ 10) ➡ 14,644 ብር (ሰንድ 11) ➡ 22,000 ብር (ሰንድ 12) ➡ 17,500 ብር (ሰንድ 13) ➡ 23,400 ብር (ሰንድ 14) ➡ 39,000 ብር (ሰንድ 15) ➡ 19,500 ብር (ሰንድ 16) ➡ 14,644 ብር (ሰንድ 17) ➡ 19,500 ብር (ሰንድ 18) ➡ 14,644 ብር (ሰንድ 19) ➡ 21,450 ብር (ሰንድ 20) እኚህ ሁሉ በሰኔ ወር 2013 የተከፈሉ ናቸው። ዶክተሩ ግን እስቲ ልየው 😳 በሰኔ ወር ነው የተከፈለው ? ብለው ይጠይቃሉ ዶክመቱም ይሰጣቸዋል፤ በኃላም ዶክመንቱን ያገላብጡና " እስቲ 2013 የሚለው የታለ ? " ሲሉ ድጋሜ ይጠይቃሉ " ይኸው ! " ይባላሉ ፤ በዝምታ ከተዋጡ በኃላ " እ ! " ብለው ዶክመንቱን መልሰዋል። ዶ/ር ተመስገን በተለያየ ጊዜ የተባከ ክፍያ የፋይናንስ ባጀት ስለሌለ በአመቱ መጨረሻ ባጀት ሲያገኝ ገብቶ ነው እንጂ በአንዴ የተላከ አይደለም ብለው ተከራርክረዋል። ሌላው የዩኒቨርሲቲው የፋይናንስ ዳይሬክተር ማርቆስ ዮሐንስ ብዙ ገንዘብ የተከፈላቸው ሲሆን " እኔ ብዙ ፕሮጀክት ስለምሰራ ነው። ቀንም ማታም ቅዳሜና እሁድም በፕሮጀክት  ላይ ሰራው ከመንግስት ስራ ሰዓት ውጭ ለዛ ነው የተከፈለኝ ባይ ናቸው። ዳይሬክተሩ በቀን 18 ሰኔ ወር 2013 ዓ/ም 13,650  ብር እንዲገባላቸው የታዘዘበት ዶክመት የተገኘ ሲሆን በቀን 23 / 2013 ዓ/ም 15,600 ብር እንዲገባላቸው ታዟል በተመሳሳይ ቀን 19,600 ብር እንዲገባላቸው ተደርጓል። ሌሎችም በርካቶች ናቸው ነው ያሉት። ዶ/ር ተመስገን ጨምሮ አሁን ስልጣን ላይ ያሉትን ዶክተር ሀብታሙ አበበ ጋር የፋይናንስ ዳይሬክተሩ ስም በክፍያ ዶክመት ላይ " ፕሮጀክት " ተብሎ ተገኝቷል። በአጠቃላይ በዋቸሞም ሆነ በመሰል ተቋማት በፕሮጀክት ስም የሚወጣው ብር እጅግ ብዙ ፣ ከደመወዛቸው እጥፍ፣ ግልጽነት የጎደለው ነው። ሌሎቹ ዩኒቨርሲቲዎችስ ?
إظهار الكل...
👍 3 1
Photo unavailableShow in Telegram
ማይክ ሀመር ከኦሮሞ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ከፕሮፌሰር መረራ ጉዲና እና ዳውድ ኢብሳ ጋር መምከራቸው መከሩ የአሜሪካን መንግስት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ማይክ ሀመር #ከኦሮምያ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር ተወያዩ። ሀመር የመከሩት ከኦፌኮ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና እና ከኦነጉ ሊቀመንበር ዳውድ ኢብሳ ጋር መሆኑም ታውቋል። የኦፌኮ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ከማይክ ሀመር ጋር በሀገራዊ እንዲሁም በኦሮምያ ክልል ወቅታዊ ጉዳዮች መምከራቸውን ለአዲስ ስታንዳርድ አረጋግጠዋል። በሀገራዊ እና በኦሮምያ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለማይክ ሀመር ሙሉ ገለጻ እንዳደረጉላቸው ፕሮፌሰር መራራ ለአዲስ ስታንዳርድ አስታውቀዋል። ከማይክ ሀመር ጋር በነበረን ቆይታ ዋነኛ አጀንዳ የነበረው ሀገራዊ ምክክሩ ነበር ሲሉ የገለጹልን ፕሮፌሰር መረራ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ "ኢትዮጵያን የትም አያደርሳትም፣ ምክንያቱም ደግሞ ሁሉን ያሳተፈ አይደለም፣ በሁሉም ዘንድ ደግሞ እምነት የሚጣልበት አይደለም" ሲሉ እንደገለጹላቸው ለአዲስ ስታንዳርድ አስታውቀዋል። ሌላኛው ከማይክ ሀመር ጋር በነበረን ውይይት የተነሳው ነጥብ የበቴ ኡርጌሳ ግድያ ነበር ያሉት መረራ ጉዲና የፈጠረባቸውን ድንጋጤ እና የቤተሰቦቹ እስር እንዳሳዘናቸው በመግለጽ ስሜቴን ለልዩ ልዑኩ አጋርቻለሁ ብለውናል። በተያያዘ ዜና የአሜሪካ መንግስት ልዩ ልዑኩ ማይክ ሀመር በአዲስ አበባ በሚገኘው የአሜሪካን ኤምባሲ ከኦነጉ ሊቀመንበር ዳውድ ኢብሳ ጋር መምከራቸውም ከፓርቲያቸው ቃል አቀባይ ለሚ ገመቹ የኤክስ ማህበራዊ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያሳያል። ዳውድ ኢብሳ እና ማይክ ሀመር በምን ጉዳዮች ላይ እንደመከሩ ቃል አቀባዩ ያሉት ነገር የለም።   
إظهار الكل...
በሰሜን ሸዋ ዞን ሁለት ወረዳዎች ዉስጥ በሚገኙ ት/ት ቤቶች የድሮን ጥቃት መፈጸሙ የተነገረ ሲሆን በጥቃቱ ንጹሃን ገበሬዎች ሲገደሉ ፤ አንዲት መምህርት ተጎድታለች ተባለ 👉🏼 ጥቃቱ በቀወት እና ጣርማበር ወረዳዎች ተፈጽሟል በትናንትናው ዕለት በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ቀወት ወረዳ ተሬ ቀበሌ ልዩ ስሙ ጉሎ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ የድሮን ጥቃት መፈጸሙን ነዋሪዎች ለአል ዐይን አማርኛ ተናግረዋል፡፡ ለደህንነቱ በመፍራት ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ የተሬ ቀበሌ ነዋሪ እንዳለው “ትናንት ግንቦት 4 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 ላይ በመንደራችን ከባድ ፍንዳታ ተፈጥሮ ነበር። እኔን ጨምሮ የሰፈራችን ነዋሪዎች ፍንዳታው ወደ ተሰማበት ስፍራ ስንሄድ ጥቃቱ ጉሎ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ እንደተፈጸመ አየን” ሲል ተናግሯል፡፡ አስተያየት ሰጪው አክሎም “በዚህ የድሮን ጥቃት ሶስት አርሶ አደሮች ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ በትምህርት ቤቱ ውስጥ ትኖር የነበረች ሴት መምህር ከባድ ጉዳት ደርሶባት ወደ ሆስፒታል ተልካለች” ሲልም አክሏል፡፡ “አንድ ሌላ አርሶ አደር በተመሳሳይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶበት ወደ ሆስፒታል መወሰዱን አውቃለሁ” ያለን ይህ የአይን እማኝ አንድ አርሶ አደር ደግሞ ቀላል ጉዳት እንደደረሰበትም ተናግሯል፡፡ በአካባቢው በመንግስት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ ከተጀመረ አንድ ዓመት እንደሆናቸው የሚናገሩት እኝህ ነዋሪ የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች አልፎ አልፎ ብቅ እያሉ ንጹሃን ሰዎችን ፋኖን ትረዳላችሁ እያሉ ወጣቶችን ይገድላሉ ብሏል፡፡ በዚህ ምክንያት የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች መጡ ሲባል በተለይም ወጣቶች ወደ ጫካ እንደሚሄዱ እና እንደሚደበቁም ይህ አስተያየት ሰጪ ተናግሯል፡፡ በተመሳሳይ በዞኑ በጣርማበር ወረዳ በሚገኘው የመዘዞ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ የድሮን ጥቃት መፈሙን ስማቸውን እንዳይጠቀስ የፈለጉ ነዋሪ ለአል ዐይን አማርኛ መናገራቸውን ሁሌ አዲስ ሚዲያ ከዘገባው ተመልክቷል። ነዋሪው እንደገለጹት በዚህ የድሮን ጥቃት በሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል። ጥቃቱ ትናንት ግንቦት 5 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ ሰባት ሰአት ላይ መድረሱን የገለጹት እኝህ ነዋሪ በጥቃቱ የተጎዱ ሰዎች ወደ ጤና ጣቢያ ሲገቡ መመልከታቸውን ተናግረዋል። የሰሜን ሸዋ ዞን ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ እና የሀገር መከላከያ ሰራዊት ተፈጸሙ ስለተባሉ የድሮን ጥቃቶች ያለውን ምላሽ ለማካተት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም ብሏል የዜና ምንጩ፡፡ በአማራ ክልል በተደጋጋሚ በተፈጸሙ የድሮን ጥቃቶች ንጹሃን ዜጎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽንን ጨምሮ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማት እና ምዕራባዊያን ሀገራት ባወጧቸው ሪፖርቶች ላይ ጠቅሰዋል፡፡እነዚህ ተቋማት እና ሀገራት የድሮን ጥቃቶች እንዲቆሙ ንጹሃን ዜጎችም ከጥቃት እንዲጠበቁ ቢጠይቁም የሀገር መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የድሮን ጥቃቱ እንደሚቀጥል እና ኢላማውን የጠበቀ ጥቃት ማድረሳችንን እንቀጥላለን ሲሉ ምላሽ መስጠታቸው አይዘነጋም፡፡ በክልሉ በፋኖ ታጣቂዎች እና በመንግስት ወታደሮች መካከል የተቀሰቀሰውን ግጭት ተከትሎ ከሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁ የሚታወስ ሲሆን ለተጨማሪ አራት ወራት የተራዘመ መሆኑ አይዘነጋም። ሆኖም ይህ አዋጅ አሁን ላይ ሊጠናቀቅ ሶስት ሳምንታት ቀርቶታል።
إظهار الكل...
💩 2