cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Hule Addis Media ( ሁሌ አዲስ ሚዲያ)

ትክክለኛዉ የሁሌ አዲስ ሚዲያ ገፆች Facebook : bit.ly/42rUuKj WhatsApp : bit.ly/Huleadis_whatsapp YouTube : bit.ly/3p7kj3N Twitter : bit.ly/3NVMRrB Telegram: bit.ly/Huleadis_tele ለጥቆማ ና አስተያየት እንዲሁም ለማስታወቂያ ስራ ተከታዮን አድራሻ ይጠቀሙ bit.ly/3VMy7x7

إظهار المزيد
Advertising posts
3 207المشتركون
لا توجد بيانات24 hour
-57 يوم
-330 يوم

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

ኢራቃዊያን ተመሳሳይ ፆታን አውግዘዋል።ኢራቅ ውስጥ ለግብረ ሰዶማዊነት ቦታ የለም ብለዋል። የኢራቅ ፓርላማ የግብረ ሰዶናዊነት / የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ተግባርን ከ10 እስከ 15 ዓመት በሚደርስ እስር የሚቀጣ አዲስ ሕግ አርቅቋል። በአዲሱ ሕግ ጾታቸውን የቀየሩ ሰዎች ከ1 እስከ 3 ዓመት እርስ ቤት ይወረወራሉ። እንዲሁም፦ ✔ግብረ ሰዶማዊነት / የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን የሚያበረታቱ፣ የሚያስተዋውቁ፤ ✔ሴተኛ አዳሪነትን የሚያራምዱ ✔ጾታ ለመቀየር ቀዶ ህክምና ሚያደርጉ ዶክተሮች ✔ሆን ብለው ልክ #እንደ_ሴት_የሚሆኑ ወንዶች እና " በሚስት መለዋወጥ " ላይ የተሠማሩ ሰዎች እስራት ይጠብቃቸዋል ፤ ዘብጥያም ይወርዳሉ። የኢራቅ ፓርላማ ተጠባባቂ አፈጉባኤ ሞህሰን አል-ማንዳላዊ " ይህ አዲስ ሕግ የህብረተሰቡን የሞራል / የግብረገብ / የስነምግባር መዋቅር ለመጠበቅ ያለመ ነው " ብለዋል። "በኢራቅ ውስጥ ለግብረ ሰዶማዊነት ቦታ የለም " ያሉት አል-ማንዳላዊ " ይህ የኢራቅ ምድር የነቢያት፣ የንፁህ ኢማሞች ፣ የጻድቃን እንዲሁም ቅዱሳን ምድር ነው " ነው ሲሉ ተናግረዋል።(ቲክቫህ ኢትዮጵያ)
إظهار الكل...
👍 1
ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ አሳፋሪ ልማዶች አንዱ የሆነውን የመንገድ ላይ መፀዳዳትን እስከመጨረሻው ለማስቀረት በሺዎች የሚቆጠሩ የህዝብ ዘመናዊ መፀዳጃ ቤት ቤቶችን ለመገንባት በጠ/ሚ አብይ አህመድ የ“ጽዱ ጎዳና - ኑሮ በጤና” ንቅናቄን ይፋ አድርገዋል ። ጽዱ ኢትዮጵያን ለመገንባት የሚውለውን በጀት ለማሰባሰብ የጠ/ሚ ፅ/ቤት በዛሬው ዕለት ዲጂታል ቴሌቶን አስጀምሯል። ይህን ተከትሎ ብዙዎች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተው ሂሳብ ቁጥር 1000623230248 የድርሻቸውን በማበርከት ላይ ይገኛሉ።     
إظهار الكل...
የቦንዳ አልባሳት የሀገሪቱን የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ገበያ 53 በመቶ ድርሻ መያዙ ጥናት አመላከተ የኢትዮጵያ ጨርቃጨርቅ አምራቾች ማህበር በተጠናቀቀው ዓመት አደረኩት ባለዉ ጥናት ለሁለተኛ ጊዜ ጥቅም ላይ የሚዉሉ ልብሶች በሀገሪቱ ለሚገኙ የጨርቃጨርቅ አምራች ኢንዱስትሪ ገበያውን ይበልጥ ፈታኝ" እንዲሆን እያደረገው እንደሚገኝ ገልጿል። ማህበሩ በዚሁ ጥናቱ በተለምዶ ቦንዳ በሚል መጠሪያ የሚታወቁት አልባሳት የሃገሪቱን የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ገበያን 53 በመቶ ድርሻ መያዛቸዉን አስታዉቀዋል ። እነዚሁ ልብሶች ዋጋቸዉ ዝቅተኛ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በማህበረሰቡ ዘንድ በጥራት የተሻለ ወይም ተቀባይነት ባላቸው አምራቾች የተመረቱ ናቸዉ በሚል አመለካከት ፍላጎቱ ከፍተኛ እንዲሆን አድርጎታል። እንደ ጥናቱ ከሆነ በአለም አቀፍ ደረዳ ለሁለተኛ ጊዜ ጥቅም ላይ የዋሉት አልባሳት ገበያ 71.22 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ እንዳለው እና እኤአ በ2030 ደግሞ ወደ 282.7 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል። የኢትዮጵያ የአልባሳት ገበያ በአሁኑ ወቅት ከአዉሮፓ እና አሜሪካ በመጡ ርካሽ ልብሶች መሞላታቸዉን በጥናቱ ተመላክቷል ። የቦንዳ ልብሶች ወደ ሀገር ዉስጥ በተለያዩ መንገዶች የሚገብ ሲሆን ከእነዚህ ዉስጥ ዋነኛውን ድርሻ የሚይዘው በሞያሌ ፣ በድሬዳዋና በሌሎች የድንበር ከተሞች ከሚባሉት በተጨማሪ በኢትዮጵያ አየር መንግድ በኩል በተለያዩ ሁኔታዎች ሲገቡ ይስተዋላል ። ሀገሪቱ በአማካኝ 54 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት የጨርቃጨርቅ አልባሳት ያለ ክፍያ ( በዜሮ ወጪ) ድንበር አቋርጠው ይገባሉ፤ በዚህም ኢትዮጵያ በዓመት ከታክስ ገቢ 2.5 ቢሊዮን ብር ኪሳራ እንደሚደርስባት ይገመታል ። እንደ ጨርቃጨርቅ አምራቾች ማህበር ጥናት በህገወጥ መንገድ የሚገብ ልብሶች ኢንዱስትሪውን መፈታተናቸዉን መቀጠላቸውን እና ለኪሳራ እንዲዳረጉ እያደረገ በመሆኑ ማህበሩ በተደጋጋሚ ለሚመለከተው አካል ቅሬታዎችን ያቀረበ ቢሆንም ምላሽ ማግኘት እንዳልቻለ ጠቁሟል ሲል የዘገበው ካፒታል ጋዜጣ ነዉ።
إظهار الكل...
👍 1
ሳያት ደምሴ ከለዛ ሽልማት መውጣቷን አዘጋጁ ገለፀ ተዋናይት ሳያት ደምሴ ከማንኛውም የሀገር ውስጥ ውድድር ራሷን ማግለሏ የዛሬ 2 ዓመት ገደማ ማሳወቋን ይታወቃል:: ይህንን ተከትሎ የለዛ ሽልማት እስከ አሁን ድረስ እያወዳደራት የነበረ ቢሆንም የእሷን ሀሳብ በማክበር አዘጋጁ ብርሀኑ ድጋፌ በማህበራዊ ገፁ ላይ ይህንን አስፍሯል:: ምርጥ ተዋናይት ምድብ ዕጩዎች 4 ቀርተዋል:: ይህም የሆነው ከአክብሮት ጋር በሚል ተዋናይት ሳያት ደምሴ ከማንኛውም የአገር ውስጥ ውድድር ራሴን ማግለሌ ይታወቅልኝ ባለችው መሠረት ነው ይህ የሆነው :: ሃሣቧን እናከብራለን :: 13ኛው የለዛ ሽልማት የመጨረሻ ዙር እጩዎች ድምፅ መስጠት ሚያዚያ 23 ያበቃል! ብርሀኑ ድጋፌ የለዛ ሽልማት
إظهار الكل...
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለግሰዋል 👏🙄 በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ የሆነውን የ“ጽዱ ጎዳና - ኑሮ በጤና” ንቅናቄን በመቀላቀል በርካቶች ድጋፍ ማድረጋቸውን እየሰጡ ነው። ከንቲባ አዳነች አቤቤም የተጣራ የአንድ ወር ደመወዛቸውን አስተዋጽኦ በማድረግ ንቅናቄውን መቀላቀላቸውን አስታውቀዋል፡፡
إظهار الكل...
🔴 የውጪ ባለሃብቶች በተከለሉ የወጪ፣ የገቢ፣  የጅምላ እና የችርቻሮ ንግድ ኢንቨስትመንቶች የሚሳተፉባቸው ሁኔታዎች ምን ምን ናቸው? ከላይ የተያያዘውን መረጃ ይመልከቱ
إظهار الكل...
ፈተናው በኦላይን ይሰጣል ተብሏል የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦን ላይን ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ተገልጿል። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ምክክር መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል ። የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ለመስጠት ባይቻልም በሁሉም ክልሎች በተመረጡ ከተሞች ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም በሁሉም ክልሎች ያሉ የተመረጡ ተማሪዎች በኦንላይን ፈተናቸውን የሚወስዱ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ በተለመደው አግባብ ፈተናቸውን ይወስዳሉም ብለዋል። የሀገር አቀፍ ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር (ዶ/ር) እሸቱ ከበደ በበኩላቸው ፈተናውን በኦንላይን ለመሥጠት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል። ተማሪዎች የሙከራ ፈተና የሚለቀቅላቸው ሲሆን ደጋግመው እንዲሞክሩና እንዲለማመዱ ይደረጋልም ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል። ለዚህም እንዲረዳ የአሰልጣኞች ስልጠና በመሥጠት ተማሪዎች ተደጋጋሚ ስልጠና እንደሚሠጣቸውም ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል። ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት እንደሚጀምርም በመድረኩ ተገልጿል።
إظهار الكل...
👍 3