cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

በአሏህ ፍቃድ የጠራች ሱናን መድረስ ለሙስሊሞች

ይህ ቻናል ከአህለ ሱና ወልጀመአህ ቻናል የታወሰዱ ጠቀሚ ትምህርቶች ሙሀደረዎች ፁፎች የሚለቀቁበት ቻናል ነው ጆይን ቢቻ ይበሉት https://t.me/joinchat/AAAAAE-FtUAYmeQV5YRkRQ ለሌሎችም ይሄንን ሊንክ በመላክ የኸይር ታከፋይ ይሁኑ ያረቢ #ስተቴን በቁርአን በሀዲሰ አርሞ ለነገረኝ (ላረመኝ) ይህ ተሳስተሀል በዚ በዚ መረጃ ብሎ ላመላከተኝ አንተ እዘንላት @IBRLIA

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
1 039
المشتركون
+1624 ساعات
+257 أيام
+3030 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

✍     ወደ ሱትራ መስገድ: የተረሳው ሱና!! ⭕️ሱትራ ማለት፦    አንድ ሰጋጅ ለሰላት በሚቆምበት ጊዜ ከፊት ለፊቱ ሰውም ይሁን እንስሳ ሰላቱን እንዳይቆርጥበት ከለላ እንዲሆን የሚጠቀመው የሚያስቀምጠው የሆነ ነገር ነው። ይህ ሱትራ መጠቀም ፍርዱ ምንድን ነው በሚለው ከፊል ዑለማዎች "የጠነከረ የማይተው ሱና ነው" ሲሉ ከፊሎቹ "ከዚህም ከፍ ብሎ ግዴታ የሆነ ነገር ነው" ይላሉ። በሁለቱም ብይን ከሄድን የአላህ መልእክተኛﷺ አጥብቀው ያዘዙበት ተግባር ስለሆነ ለየትኛውም ሰጋጅ ቸላ ሊለው አይፈቀድለትም። ኢማሙ ቲርሚዚ በዘገቡት እና አቡ ሰዒድ ባስተላለፈው የተረጋገጠ ሓዲስ ነብዩﷺ እንዲህ ይላሉ፦ 📚 «إذا صلى أحدكم فليصل إلى سترة، وليدن منها» «አንደኛችሁ በሰገደ ጊዜ ወደ ሱትራ ይስገድ፤ ወደ እሷም ይጠጋ።»   ግልፅ በሆነ ትዕዛዝ ስንሰግድ ሱትራ እንድናደርግ እና ወደ እሱም እንድንጠጋ አዘውናል። ⭕️የሱትራው መጠን በተመለከተ………   በሓዲስ በመጣው መሰረት የኮርቻ የኋለኛው ያህል ቁመት ሊኖረው ይገባል። የዚህ መጠን ግልፅ ለማድረግ ዑለማዎች እንደሚያስቀምጡት የአንድ ክንድ ያህል ወይም የክንድ 2/3ኛ ያህል መሆን አለበት ይላሉ። መልእክተኛውﷺ እንዲህ ይላሉ፦ 📚«إذا وضع أحدكم بين يديه مثل مؤخرة الرحل فليصل ولا يبال من مر وراء ذلك» «አንደኛችሁ ከፊት ለፊቱ የኮርቻ መደገፊያ ያህል ካስቀመጠ: ከዚህ በስተጀርባ ስለ ሚያልፈው ሳይጨነቅ ይስገድ።»   ሱትራ ከተደረገ በኋላ ከሱትራው ወድያ በኩል ምንም ነገር ቢመላለስ ቢተላለፍ የሰጋጁ ሰላት ላይ የሚያመጣው እንከን የለም። ⭕️በሱትራው እና በሰጋጁ መሃል ለማለፍ የሚሞክር ካለ:   ሰጋጁ በተቻለው ልክ ሊያልፍ የፈለገውን አካል እንዳያልፍ ይከለክላል። ከተግባቡ እጁ አንስቶ ምልክት ይሰጠዋል፤ ካልገባው ሊያልፍ ሲል እጁ ዘርግቶ ይከላከለዋል፤ እምቢ ብሎ ቢታገል እንኳ ሰላቱ ላይ ባለበት ታግሎም ቢሆን ይመልሰዋል። ነብዩﷺ እንዲህ ብለዋል፦ 📚«إذا صلى أحدكم إلى شيء يستره من الناس، فأراد أحد أن يجتاز بين يديه فليدفعه، فإن أبى فليقاتله، فإنما هو شيطان» «አንደኛችሁ ከሰዎች ወደ ሚከልለው ነገር ተቀጣጭቶ እየሰገደ ባለበት አንዱ ከፊት ለፊቱ ሊያልፈው ቢሞክር ይመልሰው፤ እምቢ ካለውም ይጋደለው (ይታገለው)፤ ምክንያቱም እሱ ሸይጣን ነው።» ⭕️ሰጋጁ ሱትራ ሳያደርግ እየሰገደ ወይም ሱትራ አድርጎ በሱትራው እና በእሱ መሃል የሆነ ነገር ቢያልፍ ሰላቱ ውድቅ አይሆንበትም፤ አጅሩ ግን ይቀንስበታል፤ ያለፈው ሰው ከሆነም ወንጀለኛ ይሆናል; ከሦሥት ነገሮች አንዱ ካለፈ ግን ሰላቱ ውድቅ ይሆንበታል። በሐዲስ እንደመጣው፦ 📚«يقطع صلاة المرء المسلم إذا لم يكن بين يديه مثل مؤخرة الرحل المرأة والحمار والكلب الأسود» «አንድ ሙስሊም ከፊት ለፊቱ የኮርቻ መደገፊያ ያህል ነገር ሳይኖር እየሰገደ ሴት፣ አህያ እና ጥቁር ውሻ ካለፉ ሰላቱ ይቆረጥበታል።»   ከተጠቀሱት ውስጥ ከሦሥት አንዳቸው ሰጋጁ እና ሱትራው መሃል ካለፉ: ሰላቱ ውድቅ ስለሚሆንበት ያቋርጥና በአዲስ ሀርሞ ይሰግዳል። ⭕️ሱትራ መሆን የሚችሉት፦   ከላይ የተጠቀሰው ልክ ያህል ቁመት ያለው ነገር በአጠቃላይ ሱትራ መሆን ይችላል። ግድግዳ, ምሶሶ, የተቀመጠ ሰው, ወንበር, ዱላ, የትኛውም ወደላይ የሚረዝም ዕቃ, ፣፣፣፣፣፣ ሱትራ አደርጎ መጠቀም ይችላል። ⭕️ሱትራ ከማድረግ መጠንቀቅ ያለበት፦ 📖ቁርኣን እና የሓዲስ ኪታቦች: ያላቸው ክብር ከመጠቃቀሚያነት ከፍ ያለ ስለሆነ። 👟ጫማ: ነብዩﷺ ያዘዙን ለብሰነው እንድንሰግድ ካልሆነም ከበስተ ግራ ወይም እግሮቻችን መሃል እንድናስቀምጠው ነው። 🔥የእሳት ማንደጃ እና መሰል ነገሮች: ከአላህ ውጭ የሚሰገድላቸው ነገሮች ስለሆኑ ከከሓዲያኖች ጋ መመሳሰል እንዳይሆን።   ነብዩﷺ ከቤት ሲወጡ ወይም ከከተማ ሲርቁ ይዘውት የሚንቀሳቀሱ ዱላ ነበረቻቸው። ዱላው ንግግር ሲያደርጉ ይደገፉበት ከነበረው በተጨማሪ ይሰጣቸው የነበረው ትልቁ አገልግሎት: ሜዳ ላይ ወይም ምንም ነገር በሌለበት ቦታ ላይ መስገድ ከፈለጉ ሱትራ አድርገው ይጠቀሙበት ነበር ነው። ይህ የሚያመለክተው ነገር ቢኖር የሱትራ አሳሳቢነት እና ያለው ደረጃ ነው። ⭕️ያስተውሉ!!   ሱትራ ማድረግ ግድ የሚሆነው ኢማም በሆነ ሰው ላይ እና ብቻውን በሚሰግድ ሰው ላይ ነው። ከኢማም ኋላ ተከትሎ የሚሰግድ ሰው ኢማሙ ያደረገው ሱትራ ለሁሉም ስለሚያብቃቃ እያንዳንዱ ላይ ግዴታ አይሆንም። በዚህም መሰረት ጀምዐ እየተሰገደ ከኋላ በሚሰግዱ ሰዎች (በሰፍ መሃል) መሄድ ማለፍ ይቻላል። ምክንያቱም የኢማሙ ሱትራ ስላለ ከኢማሙ ኋላ ያሉ ሰዎች ከፊታቸው ቢታለፍም ችግር የለውም።
ወደ መልካም ያመላከተ የሰሪው ምንዳ ያገኛልና ሌላውንም አስታውሱ!!
🖊ሐምዱ ቋንጤ ከፉርቃን ሰማይ ስር!! https://t.me/hamdquante https://t.me/joinchat/AAAAAE-FtUAYmeQV5YRkRQ
إظهار الكل...
🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

ይህ ቻናል ቁርኣን እና ሐዲስ መሰረት በማድረግ የመልካም ቀደምቶቻችን ፋና በመከተል ስለ እስልምናችን የምንማማርበት እና የምንመካከርበት ቻናል ነው። ✍እስልምና አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው‼ 👇🏾👇🏾👇🏾 @hamdquante አስተያየትዎ ይበልጥ ይገነባናል 👉🏿 @hamdquante_bot👈🏿

03:07
Video unavailable
📻የስሜት ባልተቤቶች ባህሪ . 🎙በኡስታዝ አቡ ሙሀመድ ሙሀመድ ሰዒድ حفظه الله . ↪️ https://t.me/fahemuselef ┈┉┅━❀🍃🌸🍃❀━┅┉┈ 🔗 t.me/Abu_Muhammed_MuhammedSed/3865
إظهار الكل...
3.57 MB
                     🥀ፅናት🥀                                        🔺ለምነቱ ብሎ ወደ  ሀበሻ ተሰዶ ብዙ እንግልት ያሳለፈው አብደላህ ኢብኑ ጃህሽ                                     🔺 ወደ ክርስትና በመግባት ያገኝውን    አግኝቶታል                             🔺ጥሩ ቦታ ላይ ተቀምጫለሁ ብለህ አትሸወድ ከጀነት የሚሻል ቦታ የለም ሆኖም           🔺አባታችን ኣደም በትንሽ ወንጀል ያገኘውን አግኝቷል ። 🔺 ብዙ ዒባዳ ሰርቻለሁ ብለህ አትሸወድ                    🔺ኢብሊስ በዒባዳ ኖሮ በአንድ ቀን ወንጀል ያገኘውን አግኝቷል ። 🔺 ብዙ ዕውቀት አለኝ ብለህ አትሸወድ                              🔺በልዓም ብኑ ባዑራ ያ ግዙፍ እውቀት ኖሮት ያገኘውን አግኝቷል 🔺 ከዳጋጎች በመቀማመጥህ አትሸወድ                                 🔺ከነቢዩ(ﷺ ) የሚበልጥ ደግ የለም                                 🔺ሆኖም ከእርሳቸው ይቀመጡ የነበሩት ሙናፊቆችያገኙትን አግኝተዋል                                                       🔺አንተ ልቦችን ገለባባጭ የሆንከው ጌታችን ሆይ  ልበችን በዲናችን ላይ አፅናን!!   رَّبَّنَآ إِنَّنَا سَمِعْنَا مُنَادِيًۭا يُنَادِى لِلْإِيمَٰنِ أَنْ ءَامِنُوا۟ بِرَبِّكُمْ فَـَٔامَنَّا ۚ رَبَّنَا فَٱغْفِرْ لَنَا ذُنُوبَنَا وَكَفِّرْ عَنَّا سَيِّـَٔاتِنَا وَتَوَفَّنَا مَعَ ٱلْأَبْرَارِ «ጌታችን ሆይ! እኛ በጌታችሁ እመኑ በማለት ወደ እምነት የሚጠራን ጠሪ ሰማን፡፡ አመንም፡፡ ጌታችን ሆይ! ኃጢአቶቻችንንም ለኛ ማር፡፡ ክፉ ሥራዎቻችንንም ከኛ አብስ፡፡ ከንጹሖቹም ሰዎች ጋር ግደለን፤»                                        [ሱረቱል ኢምራን:193📚]    👉🏿@tewihd https://t.me/joinchat/AAAAAE-FtUAYmeQV5YRkRQ
إظهار الكل...
በአሏህ ፍቃድ የጠራች ሱናን መድረስ ለሙስሊሞች

ይህ ቻናል ከአህለ ሱና ወልጀመአህ ቻናል የታወሰዱ ጠቀሚ ትምህርቶች ሙሀደረዎች ፁፎች የሚለቀቁበት ቻናል ነው ጆይን ቢቻ ይበሉት

https://t.me/joinchat/AAAAAE-FtUAYmeQV5YRkRQ

ለሌሎችም ይሄንን ሊንክ በመላክ የኸይር ታከፋይ ይሁኑ ያረቢ #ስተቴን በቁርአን በሀዲሰ አርሞ ለነገረኝ (ላረመኝ) ይህ ተሳስተሀል በዚ በዚ መረጃ ብሎ ላመላከተኝ አንተ እዘንላት @IBRLIA

ወሬ ይሻላል❓ ምክር ለምን ወሬ ዝባዝንኬ፣ ስድብ ጭቅጭቅ የሚበዛበት ቦታ ላይ እንሰባሰባለን ❓ለምን❓ እንደው ለዲናችን ጠቃሚ ነገራቶችን ልናገኝባቸው የሚችሉ ጥሩ ጥሩ ግሩፖች እያሉ ለምን በፊትና የተሞሉ በስድብና በዘለፋ የታጨቁ ጉሩፕችን ታሞቃላቹ ። አንድ ነገር እወቁ ምታዩትን ነገር ኢንካር ማድረግ ካልቻላቹ ወይም ካልጠላቹ ወይም ደግሞ ትታችሁ ካልወጣችሁ ቀስ በቀስ የሰዎቹን በሽታ መሸከማቹ አይቀርም ልብ ደካማ ናት ሹብሃ ደግሞ ትቀጥፋለች❗️ ውሸት ሲደጋገም እውነት እየመሰለ ይሄዳል ውስጥህ ይሸረሸራል ትጎዳለክም መጎዳት ብቻም አይደለም በጣም ከባድ የሆነ የአመለካከት ችግር ውስጥ ትገባለህ ። ማመን ያለብህን ትተህ ማመን የሌለብህን ሰው ታምናለክ የእሱ ጭራ ትሆናለክ ምን ይሄ ብቻ አግዝፈህ ምታያቸው እንደው ስታያቸው ሁላ በስስት የምትመለከታቸውን ዑለሞች ለመጥላት ትገደዳለህ ዑለማን መጥላት ዲንን መጥላት ነው፣ ዑለማን መስደብ ዲንን መስደብ ነው። ምክንያቱም የተሸከሙት ዲንን ስለሆነ ወንድሜ እንዲህ አይነት ዑለሞችን የሚያንቋሽሽ መጅሙዓ መከታተተል ልብህን ያደርቅብሃል። ትሰማለህ ወንድሜ ሁሉ ነገር ልክ አለው የተበደለ ሰው በደሉን ሚገልፅበት መንገድ አለው እውነት ይህ አካል ተበድሎ ከሆነ ። ዑለሞቹ በህይወት አሉ ። እነዚህ አካሎች እውነት ከዳዕዋው ጋር የመሄድ ፍላጎት ቢኖራቸው ኖሮ መክፈል የነበረባቸውን መስዋእት ይከፍሉ ነበር። ግና ሁሉም አትንኩኝ ባይ ሆነ ። ኡስታዞቻችን ከሚባለው በላይ ትግስት አድርገዋል ባይሆን ኖሮ ድሮ ነበር የራሱ ጉዳይ ብለው ሚተውት ነገር ግን ከዛሬ ነገ ይስተካከላል አንድ አቋም ላይ ይደረሳል በማለት በጣም ብዙ ጥረት አድርገዋል። አንዳንድ ሰዎች ከሩቅ ሆናችሁ አትፍረዱ ኡስታዞቻችሁ ነገሩን ተኝተው አይደለም ያሳለፉት ወላሂ ታግለዋል እንቀልፍ አጥተዋል መስራት ያለባቸውን ነገር ጥግ ድረስ ሰርተዋል። አመድ አፋሽ አታድርጓቸው እነሱም እንደኛ ቤተሰብ አላቸው ቤተሰቦቻቸውን ጥለው ሳይተኙ ሚያድሩት ብር ሊሰበስቡ አይደለም ዑማውን ለመሰብሰብ ቢሆን እንጂ አንድ ነገር ሳናደርግ ዘሎ አስተማሪዎቻችንን መጠራጠር ትልቅ ድፍረት እንዲሁም አሳፋሪ ተግባር ነው። አንድ ሁለት ቀን ቁጭ ብለህ ተወያይ ብትባል ምን አልባትም ራስህን ሊያምህ ይችላል ። እናስብ እንጂ ወገን ውለታ ሚባል ነገር አለ ስንት ትምህርት ወስደህባቸዋል ስንትና ስንት አመት አብረካቸው አሳልፈሃል ዛሬ ስለ ምንም ነገር ግድ የማይሰጠው "ሰው ጤፉ" ከሆነ አካል ጋር አሸሼ ገዳሜ ማለት ያሳፍራል። ወንድሜ ነገሩ የስሜት አይደለም❗️ ተበድሏል ካልክ ጠይቅ ዑለሞችን እነሱን መጠየቅ ካልቻልክ በጉዳዩ ላይ ለረጅም ጊዜ ያለውን ነገር ሲከታተሉ የነበሩ ወንድሞችን ጠይቅና ተረዳ። ከዛም ተበድለዋል የሚልን ነገር ከተረዳክ የተበደለ ሰው በዚህ ልክ በምንም ከማይገናኛቸው ዓሊሞች ጋር እንዲህ አፍ መካፈት አለበት❓ ነገሩን ማስተካከያ መንገድ የለምን ❓ እንዴት በዚህ ልክ ለጆሮ በሚሰቀጥጥ መልኩ ስድብና ዘለፋ እንዲሁም ማንቋሸሽ ይከሰታል ትላንትና ስታወድሳቸው የነበሩ ዑለሞች ዛሬ ተራ ሰው ሆነው ለተራ ሰው ራሱ ማይባሉ ስድቦች ተሰደቡ ❗️እስቲ ማናቹ ❓እናንተ ለደዕዋ ሰለፊያ ምን አደረጋቹ❓ እስቲ መፅሃፎቻችሁን አሳዩን፣ ወዘተ ሚገርመው ግን ብዙ ጊዜ እንዲህ አይነት ነገር ሲከሰት ወጣ ይሉና ድሮም እናውቃችኋለን እነ ኢብን ሂዛም ከዳዕዋው የወጡት ተገፍተው ነው እነ ዓብድረህማን አል ዐደኒ እነ ፉላን እያሉ ለራሳቸው ማስረጃ ያደርጋሉ ። ሱዳን ላይ ያሉ ሰዎች ከነ ሸይኽ አቢ ዓምር ጋር ሳይስማሙ ሲቀሩ ወዲው የሄዱት ዑለሞችን ወደ መዝለፍ ነበር ከዛም እነሱን ትተው እነ ዑበይድ አልጃቢሪን፣ እነ ረስላንን ማወደስ ጀመሩ ። ነገሩ እንዲህ ነው እነዚህ ሰዎችማ ጭራሽ አብሰውታል ዑለሞችን በጣም እያሳነሱ እያንቋሸሹ ጭራሽ እንደ ጭራቅ እንድትቆጥራቸው ለማድረግ በጥረት ላይ ናቸው። ወንድሜ ይህን ዳዕዋ የወደድነው በዑለሞች ነው የነሱ መልካም ስብእና ነው ከተለያዩ የአለም ክፍሎች ሰውን በአንድ ቦታ እንዲሰበሰብ ያደረገው❗️ ምንኛ ያማረ ደዕዋ ነው በእዝነት የተሞላ ወላሂ ዑለሞቻችን ሙተዋዲዕ ናቸው በጣም ዝቅ ብለው ተናንሰው የሚኖሩ ናቸው። ሀገራቹ መጥተው አይተሃል መቼም አትክድም ባለ 5 ኮከብ ሆቴል ላይ አይደለም ያረፉት አንተን መስለው አንተን ሆነው ነው አስተምረውክ የተመለሱት። መቼም ይህን አትረሳውም ዛሬም ብዙ ደረሶች ያሉት አንተ እንደ ቆሻሻ የምትገልፃቸው ዑለሞቻችን ዘንድ ናቸው እንደው ትንሽ አያሳፍርም የአስተማሪያችሁን ምግብ እየበላችሁ እዛው እያደራችሁ ደርስ ላይ ለመውጣት ስትሞክሩ ይሄ ጨለምተኝነት ነው ። ካልፈለክ ለቀህ መውጣት ወይም ስርኣት ይዘክ ተቀመጥ ባሉክ መሰረት መቀመጥ እንጂ በዚህ ልክ አስተማሪህን እየዘረጠጥክ ከጎናቸው ለመቀመጥ መሞከር በራሱ የሆነ የተዛባባቹ ነገር እንዳለ ያመላክታል። ለዳዕዋ ምታስቡ እንዲሁም አንድነትንት ምትፈልጉ በነበር የተመከራችሁትን ምክር ለመተግበር ትሞክሩ ነበር። ።።።።።።።።። እንደው ትንሽ እንኳን ለተሸከማችሁት ዳዕዋና ከኋላ ለሚከተላቹ ሰው እንኳን አታስቡም ለምን ተነካው ብላችሁ መጮሁ መሳደቡ የሆነ የተደበቀ አጀንዳ ያለ ያስመስላል። 👉 በመጨረሻም ውድ ሰለፍዮች ዑለሞችን እንዲሁም ዱዓቶችን አክብረህ ይህን ከብዙ ነገር በአላህ ፍቃድ የጠበቀህን ዳዕዋ እንደወደድከው መቀጠል ከፈለክ ነገ ዛሬ አትበል አሁኑኑ ይህን መንጀኒቅ የተባለ የስድብ ቋት ለቀህ ውጣ ይህን ካላረክ እመነኝ ነገ ዑለሞች መጡ ሲባል ግድ አይሰጥህም ለዛ ነው ኢብን ዑሰይሚን ዑለሞችን ስለመሳደብ ሲናገሩ እንዲህ ያሉት፦እነሱን መስደብ አንድ ተራ ሰውን እንደመስደብ አይደለም ዑለሞችን መስደብ ዲንን መስደብ ነው። አንድ ተራ ሰውን ብትሰድብ ስድቡ እሱ ላይ ይቀራል ዑለሞችን ስትሰድብ ግን እነሱን በሚከተሉ ሰዎች ዘንድ ያላቸውን ተቀባይነትና ተሰሚነት ያሳጣል ይሄ ደግሞ ዲንን ይጎዳል ❗️ ነገሩ ይህ ከሆነ ወንድሜ የዚህ ወንጀል ተካፋይ አትሁን ቶሎ ለቀህ ውጣ ❗️ 👉https://t.me/AbuEkrima
إظهار الكل...
03:23
Video unavailable
3.89 MB
"ዓሹራ በአህለል ሱናዎች እና በሺዓዎች ዕይታ" ” عاشوراء بين السنة والشيعة “ 👂 ይደመጥ‼ ከምናምን አመት በፊት የተደረገ ወሳኝ ሙሀደራ በሸይህ አቡ ዐብዱረሕማን ኢብራሂም https://t.me/ustazabrar/244
إظهار الكل...
عاشوراء بين السنة والشيعة.mp38.62 MB
🌺 «ተ ጀ መ ረ» «ተ ጀ መ ረ» « ተ ጀ መ ረ » ✅ ከአስር ቡሀላ በቀጥታ ስርጭት ሚተላለፈው የሴቶች ደርስ ፕሮግራም! 🎙 በኡስታዝ አቡ መሓመድ ሙሓመድሰዒድ ቢን በድሩ አላህ ይጠብቀው። 🕌 ከሱና መስጂድ አላህ ይጠብቃት። 👇በቀጥታ ደርሱን ለመከታተል👇 🔗 https://t.me/Abu_Muhammed_MuhammedSed?livestream
إظهار الكل...
📮የዓሹራ ቀን ፆምና ሙሀረም! 🔜 የዓሹራ ፆም መቼ ነው የተጀመረው? 🔜 እነማን ናቸው የጀመሩት? 🔜 ነብዩ ﷺ እንዴት ነው የፆሙት? 🔜 ሁክሙስ በዚች ኡማ ላይ እንደት ነው የነበረው? ✅ እነዚህን እና ሌሎችም ነጥቦች ስለ አሹራ ፆም በሰፊው የተዳሰሰበት ወቅታዊ የሆነ ሙሐደራ። 🎙 በኡስታዝ አቡ የህያ ኢልያስ ቢን አወል አላህ ይጠብቀው። 🕌 በፉርቃን መስጅድ [አለም-ባንክ] 📎 https://t.me/Al_Furqan_Islamic_Studio/16810 ♡ㅤ   ❍ㅤ     ⎙ㅤ     ⌲  ˡᶦᵏᵉ  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ     ˢʰᵃʳᵉ
إظهار الكل...
የአሹራ ቀን ፆም እና ሙሀረም.mp311.64 MB
05:19
Video unavailable
6.02 MB
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.