cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ፍሬ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት - ሐረር

ይህ በኢት/ኦ/ተ/ቤ/ክ የምሥ/ሐ/ሀ/ስ ጥንተ አድባራት ወገዳማት አቦከር ደብረ ፀሐይ ቅ/ጊዮርጊስ እና ሐኪም ጋራ ደብረ አድኅኖ ቅ/ገብርኤል አብያተ ክርስቲያናት ፍሬ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት ገጽ ነው። ፨ ለመቀላቀል፡ 👉https://t.me/frehaymano ሀሳብ እንዲሁም አስተያየት ካሎት : 👉 @Frehaymanot1923 ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ "አገልግሎት ሕይወቴ ካልሆነ ፤ መኖር ለእኔ ሞቴ ነው"

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
572
المشتركون
+224 ساعات
-17 أيام
+1630 أيام
توزيع وقت النشر

جاري تحميل البيانات...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
تحليل النشر
المشاركاتالمشاهدات
الأسهم
ديناميات المشاهدات
01
የፍጥረት እንጀራ ብዙ ስሞች ሲገኑ አይታችሁ ሊሆን ይችላል ፣ ግን ሲያድኑ አላያችሁም ፣ ስሙን በመጥራት አጋንንት አንገታቸውን ደፍተው አልቅሰው ተዋርደው ወደ ቤታቸው ገብተዋል ። ይገርማችኃል የእርሱን ስም በመጥራት ነፍሳችን ትረካ ነበረ ። ሰዎች ብቻ የሚያውቁት ስም አይደለም አጋንንት ራሱ ስሙን ያውቁታል ደንግጠውም ይሄዳሉ ። በሽተኞችም የእርሱን ስም ሰምተው ድነዋል ። ይህ ስም ግን የማን ይመስላችኃል ? ታሪካችን ብቻ ሳይሆን ሕይወታችንም ሠላምን አገኝ ። ለዚህ አምላክ ታዲያ እኛ ብቻ አይደለንም ሠላሳ ስምንት ዓመታትን በአንዲት አልጋ ላይ ያስቆጠረው መፃጉዕም ይመሰክራል ፤ ምክንያቱም መፃጉዕ የተፈወሰው በእርሱ ነውና ። አሁን ሁላችሁም ለዚህ ስም መዘመር ጀምሩ ፤ ምክንይቱም ነገ መድኃኔዓለም ነውና ። ማለታቸው አይቀርም ቅዱሳን ሐዋርያት ስለ መድኃኔዓለም ተናገሩ ብንላቸው ። እንኳን ለመድኃኔዓለም ወርሃዊ በዓል አደረሳችሁ ። ጸሐፊ ፥ ናሆም መስፍን ግንቦት 2016
1012Loading...
02
🌾🍇ውድ የፍሬ-ሃይማኖት ቤተሰብ ፨፨፨ የምህላ ጸሎት መርሐ ግብር ነገ ማለትም በ27 እና በ28 እለት ። በህመም ውስጥ ለሚገኙት እናታችን ሲባል ባዘጋጀነው የ ጸሎት መርሐ ግብር ላይ ከጠዋቱ 12 ሰዓት እስከ 1:00ድረስ ብቻ የሚቆይ የምህላ ጸሎት ስለተዘጋጀ ከነገ ጠዋት ጀምሮ እንድንገናኝ ። በጠዋት ጸሎት ማድረግ አጋንንትን ያስደነግጣል ፤ እና ጠላትን መጣል ከፈለጋችሁ በጠዋት ጸሎት አድርሱ ፤ ደስ ብሏችሁ እንድትውሉ ቀናችሁን በምሕላ ጸሎት ስትጀምሩት ሁሉ መልካም ይሆናል ። ብቻችንን ቆመን ከምናደርገው ጸሎት ይልቅ የማኅበር ጸሎት እጅግ ኃይል አላት ።
1300Loading...
03
🌾🍇ሰላም እንደምን አመሻችሁ ውድ የፍሬ-ሃይማኖት ቤተሰብ ፨፨፨ ነገ 25/2016 ወርሃዊ የሰማዕቱ ቅ/መርቆሬዎስ ዝክር ቀን ስለሆነ የሰ/ት/ቤት መ/ግብራችን 8:30 ተጀምሮ 10:40 ይጠናቀቃል። መ/ግብር እንዳለቀ አንድ ላይ ወደ መንበረ ጵጵስና ጌቴሴማኒ ቅ/ኪዳነምህረት ገዳም በሰ/ት/ቤቶች አንድነት ኅብረት የተሰናዳውን ዝክር ለመሳተፍ እንሄዳለን። ፨፨፨ የሰማዕቱ ምልጃ እና በረከት አይለየን🙏
2100Loading...
04
👋 ውድ የፍሬ-ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት አባላት የዛሬው የጸሎት መርሐ ግብራችን የሚሆነው ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ-ክርስቲያን ስለሆነ ። በጊዜ ልክ 10:30 ላይ የጸሎት መርሐ ግብራችንን ስለምንጀምር በተባባልንበት ሰዓት እንገናኝ ። ጊዜው የጠላታችን ቢሆንም ፤ በጸሎት ሁሉን ማድረግ ስለሚቻል እንዳትቀሩ ! ይህንንም እያሰባችሁ ራሳችሁን ለጸሎት አዘጋጁ ይለን ነበረ ። የአትሮኖሱ ንጉሥ ( ዩሐንስ አፈወርቅ ) ጸሎት ማድረግ ጠንካራ ክርስቲያን እንደሚያደርገን እየመከረን ፤ ይቆይ ነበረ ጸሎት ሲደርስ ሌላ ሥራ መሥራት ለሚያምረን እየነገረን ።
2820Loading...
05
👋ሰላም እንደምን አረፈዳችሁ ውድ የፍሬ-ሃይማኖት ቤተሰብ እንኳን ለሊቀ ሰማዕታት ቅ/ጊዮርጊስ ወርሀዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን🙏 📌 ዛሬ በቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሰርክ መርሃ ግብር ላይ አገልግሎት ስላለን ሁላችንም በጊዜ በመገኘት እንድናገለግልና የበረከቱ ተካፋይ እንድንሆን አምላካችን ይርዳን 🙏🙏🙏 አሜን 📌የሚቀርቡ ዝማሬዎች   1. ህያውን ከሙታን 2. ማዕዶቴ ነሽ 3. እርሱ እንደ ንብ አውራ ዝማሬዎቹን ተዘጋጅተን እንምጣ መልካም ቀን ሰላም ዋሉ 🙏🙏🙏
2711Loading...
06
👋ሰላም እንደምን አረፈዳችሁ ውድ የፍሬ-ሃይማኖት ቤተሰብ እንኳን ለሊቀ ሰማዕታት ቅ/ጊዮርጊስ ወርሀዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን🙏
10Loading...
07
🌾🍇 ውድ የፍሬሃይማኖት ቤተሰብ 👋 ከዚህ በታች ስማችሁ የተጠቀሰ የመርኃ ግብር መሪዎች ናችሁ ቅዳሜ ===== 📌ቅዱስ ጊዮርጊስ ሕፃናት ናትናኤል ስንታየሁ 📌ቅዱስ ጊዮርጊስ አዳጊ አብርሃም ላሜሮ 📌ቅዱስ ገብርኤል ሕፃናት ሄኖክ አሸናፊ 📌ቅዱስ ገብርኤል አዳጊ አማኑኤል አይተንፍሱ 📌ቅዱስ ገብርኤል ወጣት ዲ/ን አቤኔዘር አጥላባቸው እሁድ ===== 📌ቅዱስ ጊዮርጊስ ሕፃናት አራርሶ ተስፋዬ 📌ቅዱስ ጊዮርጊስ አዳጊ ናሆም መስፍን 📌ቅዱስ ገብርኤል ሕፃናት ፍጹም ጌታቸው 📌ቅዱስ ገብርኤል አዳጊ ወንድሜነህ ማሩ 📌ቅዱስ ገብርኤል ወጣት ዲ/ን አብርሃም ፨፨፨፨፨፨፨ ጥያቄ ወይም ሀሳብ ለማቅረብ ☎️ +251953409521 ☎️ +251923462089 ፨፨፨፨፨፨፨ "ማንም ሲያገለግል ፤ የአገልጋዩ ማንነት ይገለጥ ዘንድ ሳይሆን የእግዚአብሔር ክብር ይገለጥ ዘንድ ነውና ፤ ሁሉን በትህትና እና በፍቅር እናድርግ"
3260Loading...
08
👋 ሰላም እንደምን ዋላችሁ ውድ የፍሬ-ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት አባላት 📌📌📌 የዛሬው የረቡዕ መዝሙር ጥናት መርሃ-ግብር አይኖረንም ላልሰሙት በመንገር እንተባበር። መልካም ጊዜ🙏🙏
2790Loading...
09
#ለሰማዕቱ ለቅዱስ መርቆሬዎስ ወዳጆች #ሐረር #ጀምረነዋል እና እንጨርሰው ዘንድ ይገባናል" የሰማዕቱ የቅዱስ መርቆሬዎስ ወዳጆች ሰላም ለእናንተ ይሁን እያልን የቢርቢርሳ ቅዱስ መርቆሬዎስ ቤተ-ክርስቲያን ግንባታ ከታች በፎቶ እንደምትመለከቱት ደርሷል ይህን የበረከት ስራ ያስጀመረን ልዑል እግዚአብሔር እንደሚያስፈፅመን ባለ ሙሉ ተስፉ ነን ነገር ግን ግንባታው እዚህ የደረሰው በሰማዕቱ እርዳታ እና በእናንተ ድጋፍ ነውና ስራውን ከፍፃሜ ለማድረስ አሁንም የናንተ ድጋፍ ያሻናልና ይህን ፅሁፍ የምታነቡ ሁላችሁ የዚህ የበረከት ስራ ተሳታፊ እንድትሆኑ በገጠሪቷ ቤተ ክርስቲያን ስም መንፈሳዊ ግብዧችንን እናቀርባለን::       ልዑል እግዚአብሔር በብዙ ፀጋ የጎበኛችሁ ሰማዕቱ የደረሳላችሁ ሁላችሁ አቅም በፈቀደ መጠን እጃችሁን ዘርጉልን:: ከዚህ በፊት በተለያየ ሁኔታ ድጋፋችሁን የቸራችሁን ሁላችሁ መንፈሳዊ ዋጋ ከፋይ ልዑል እግዚአብሔር ነውና ዋጋችሁን በረከታችሁን ይስጥልን::
3780Loading...
10
Media files
2690Loading...
11
Media files
2760Loading...
12
ደብረ ምጥማቅ ግብጽ በምትገኘው በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም በተሠራችው ደብረ ምጥማቅ ቤተ ክርስቲያን ጉልላት ላይ ድንግል ማርያም ከግንቦት ፳፩ ጀምሮ እስከ ፳፭ ቀናት በተከታታይ በመገለጧ ሕዝበ ክርስቲያን በዓሏን ያከብራሉ፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ወደ ምድረ ግብጽና ኢትዮጵያ በተሰደደች ጊዜ በአሁኑ ጊዜ ደብረ ምጥማቅ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ ዐርፈው ነበር:: ጌታችንም ቦታውን ባርኮ የእርሷ መገለጫ እንዲሆን ቃል ኪዳን ገብቶላት ስለነበር ጊዜው በደረሰ ሰዓት ደብረ ምጥማቅ ተገድሞ የበርካታ መነኮሳት በዓት ሆነ:: በደብረ ምጥማቅም እመቤታችንም ቅድስት ድንግል ማርያም ብርሃን ተጎናጽፋና በሠራዊት መላእክት ታጅባ ተገልጣለች፤ በዚያን ጊዜም ሱራፌል ማዕጠንታቸውን ይዘው ሰገዱላት፤ እንዲህ እያሉም አመሰገኗት፤ ‹‹አብ በሰማይ አይቶ እንዳንቺ ያለ አላገኘም፤ ባንቺም ሰው ሆነ፡፡›› (መጽሐፈ ስንክሳር ግንቦት ፳፩ ገጽ. ፫፻፲፰) ሰማዕታትም እንደየክብራቸው ማዕረግ ለእመቤታችን ድንግል ማርያም ሊሰግዱ ረቂቃን በሆኑ ፈረሶቻቸው ተቀምጠው ወደ እርሷ ቀረቡ፤ በመጀመሪያ ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሁሉም ቀድሞ ከሰገደላት በኋላ ሌሎቹም በተመሳሳይ መልኩ ሰገዱላት፡፡ ከዚህም በኋላ ቅዱስ መርቆሬዮስ በዱሪ ፈረስ ተቀምጦ ወደ እርሷ በመምጣት ሰገደላት፡፡ ጻድቃን በአንድነት ቀርበው ለክብሯ ሰገዱላት፤ ቀጥሎም በንጉሥ ሄሮድስ በግፍ የተገደሉት ሕፃናት ለእርሷ ሰገዱ፤ በደስታና በፍቅርም ተጫወቱ፡፡ በዚያ የተሰበሰቡትም ክርስቲያኖች፣ እስላሞችና አረማውያን ይህን በአዩ ጊዜ ደስታ ሞልቶባቸው በተለየ ዓለም ያሉ ይመስላቸው ነበር፡፡ (መጽሐፈ ስንክሳር ግንቦት ፳፩ ገጽ. ፫፻፲፰) አባ ጽጌ ድንግልም በደብረ ምጥማቅ በታላቅ ክብር ለምእመናን የታየችው የአምላክ እናት የድንግል ማርያምን መገለጥ በማኅሌተ ጽጌ ድርሰቱ እንዲህ በማለት ገልጾታል፤ ‹‹አመ ትበርቂ በደብረ ምጥማቅ ኀምሰ ዕለታተ፣ ትእምርተ ገጽኪ ይርአይ እስከ ይትነሣእ ዘሞተ፣ሚ መጠነ ማርያም ታሥተፌሥሒ ትፍሥሕተ፣ ኅድጊሰ ጽጌ ፍቅርኪ በጊዜ ንቃሁ መዓልተ፣ ብፁዕ ዘርእየኪ በሕልሙ ሌሊተ፤ የፊትሽን መልክ ያይ ዘንድ የሞተ ሰው እስኪነሣ ድረስ በደብረ ምጥማቅ ለአምስት ቀናት ያህል በተገለጽሽ ጊዜ ማርያም ምን ያህል ደስ ታሰኚ ኖሯል! በቀን የታየው የፍቅርሽ አበባ ይቅርና ሌሊት በሕልሙ ያየሽ ምስጉን ነው፡፡›› (ማኅሌተ ጽጌ) በደብረ ምጥማቅ ከተሰበሰቡት ሕዝብ መካከል እናትና አባታቸው፣ ዘመዶቻቸው እንዲሁም ባልንጀሮቻቸው የሞቱባቸው ሰዎች ቅድስት ድንግል ማርያም እንድታሳያቸው በለመኗት ጊዜ እንደ ቀደመ መልካቸው አድርጋ ታሳያቸው ነበር፡፡ አንዳንዶች ደግሞ መሀረባቸውን ወደ ላይ በሚወረውሩት ጊዜ እርሷ የወደደቻቸው እንደሆነ በእጅዋ ተቀብላ መልሳ ትጥልላቸዋለች፤ ሁሉም ለበረከት ይካፈሉታል፡፡ እነርሱም ወደ ቤታቸውም ለመሄድ በሚፈልጉ ሰዓት ተሰናብተውና በተባርከውም ይሄዳሉ፡፡ (መጽሐፈ ስንክሳር ግንቦት ፳፩ ገጽ. ፫፻፲፱) የደብረ ምጥማቅና የአካባቢዋ ሰዎች እመቤታችን ድንግል ማርያምን ያዩባቸው ቀናት አረማውያኑ ያመኑበት፣ የበደሉት በምልጃዋ ቸርነትን ምሕረትን ያገኙበት፣ ያመኑት ደግሞ የተባረኩበት ዕለታት ነበሩ፡፡ ሕዝቡ እርሷን ተመኝተው ያጡት ወይንም ጠይቀው ያልተፈጸመላቸው ምንም ነገር አልነበረም:: ነቢያት፣ ሐዋርያት፣ ጻድቃን፣ ሰማዕታት፣ ደናግል፣ መነኮሳት መላእክትና ሊቃነ መላእክትም ለድንግል ማርያም ሲሰግዱ ይታዩ ነበር:: ከዚህ በኋላ በዘመናት ይኖሩ የነበሩ ቅዱሳን የአምላክን እናት ለማየት ብዙዎች ተመኝተዋል፤ የመልክአ ማርያም ደራሲ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ የአምላኩን እናት ቅድስት ድንግል ማርያምን ፊቷን ለማየት ሽቶ ‹‹ሰላም ለመልክእኪ ዘተሠርገወ አሜረ ዘያበርህ ወትረ ፍቅርትየ አንቲ እንተ ታበድሪ ፍቅረ አርእዪኒ ገጸ ዚኣኪ ማርያም ምዕረ ዘኢይሰምዖ ካልእ እንግርኪ ነገረ፤” ዘወትር የሚያበራ ፀሐይን ጌጥ ላደረገ መልክሽ ሰላምታ ይገባል፤ ፍቅርን የምትመርጪ (የምታስቀድሚ) አንቺ የምወድሽ ማርያም ሌላ የማይሰማው ነገርን እነግርሽ ዘንድ አንድ ጊዜ ያንቺን ፊት ግለጪልኝ (አሳይኝ)›› በማለት ተማፅኗታል፡፡ (መልክአ ማርያም) ነቢዩ ዳዊት ‹‹ወለገጽኪ ይትመሐለሉ ኲሎሙ አሕዛብ ብዑላነ ምድር፤ የምድር ባለጠጎች አሕዛብ ሁሉ በፊትሽ ይማለላሉ›› በማለት ትንቢትን እንደተናገረላት በርካት ቅዱሳን ሰዎች ቅድስት ድንግል ማርያምን ተገልጻላቸው ለማየት ተመኝተዋል፤ ልመናቸው ተሰምቶላቸው የአምላክ እናት ተገልጻላቸው ፊቷን ለማየትን ክብሯን ለመግለጥ ቅዱሳን አባቶች፣ ጻድቃን ሰማዕታት በቅተዋል፡፡ ይህም የሆነው በፍጹም ልቡናቸው በመማፀናቸውና በፍጹም ትጋት የጌታቸውን እናት ሲያገለግሉ በመኖራቸው እንደሆነ የጻድቃኑ ገድል ምስክር ነው፡፡ እነርሱም ሌት ከቀን ምኞታቸው ይሳካላቸው ዘንድ በጸሎት ይማፀኑ ነበር፡፡ (መዝ. ፵፬፥፲፪) እመቤታችን ድንግል ማርያምም ጸሎታቸውን ሰምታ ያሰቡትን ትፈጽምላቸው ነበር፤ ምኞታቸው ከተሳካላቸው ቅዱሳን አባቶች መካከል አባ ይስሐቅ አንዱ ነው፤ ይህ ቅዱስ አባትም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን በፍጹም ልቡናው ይወዳት ስለነበር ለሰባት ዓመታት አምላኩን ክብርት እናቱን ያሳየው ዘንድ በጸሎቱ ተማጸነ፡፡ ዘወትር ከሠርክ ጸሎት በኋላ ሌሎች መነኮሳት ለመኝታ ወደ የበዓታቸው ሲሄዱ አባ ይስሐቅ ወደ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ በቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕሏ ፊት ቆሞ ሦስት መቶ ስግደትን እየሰገደ ይማፀን ነበር፡፡ ከስግደቱም ጋር ‹‹ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ አርእየኒ እመከ አሐተ ሰዓተ፤ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ለአንዲት ሰዓት እናትህን አሳየኝ›› እያለ ይጸልይ ነበር፡፡ በእንደዚህም ሁኔታ ለሰባት ዓመት ከቈየ በኋላ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በታላቅ ግርማ ተገለጸችለት፤ የልቡም መሻት ምን እንደሆነ ጠየቀችው፤ አባ ይስሐቅም የርሷን ገጽ ያዩ ዐይኖቹ ሌላ ነገርን ማየት እንደማይሹ ነገራት፤ ከተወደደ ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ እንድታማልደውም ተማጸናት፡፡ ቅድስት ድንግል ማርያምም ልመናውን ተቀበለች፤ ከዚያም በኋላ የዕረፍቱ ቀን ከሦስት ቀን በኋላ መሆኑን አሳወቀችው፤ ባርካውም ወደ ሰማይም በክብር ዐረገች፤ ይህ ቅዱስ አባት ይስሐቅም እርሷን ካየ በሦስተኛው ቀን ዐረፈ፡፡ (መጽሐፈ ስንክሳር ታኀሣሥ ፳፩ ገጽ.፬፻፺፪) እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በደብረ ምጥማቅ ተገልጣ የሕዝቡን ምኞት እንደፈጸመችላቸው የእኛንም በጎ መሻት ትፈጽምልን፤ አሜን፡፡
2680Loading...
13
በተጨማሪም፡- 👉የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የፕትርክና መንበሩ ከግብፅ ወደ ኢትዮጵያ ከመጣበት ከሰኔ 21/1951 ዓ/ም ጀምሮ  አስቸኳይ ጉባዔያትን ሳይጨምር 128 መደበኛ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔያት መካሔዳቸውን ታሪክ ያስረዳል። 👉ከእነዚህ መደበኛ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔያት መካከል በቅዱሳን ፓትርያርኮች ርእሰ መንበርነት የተመሩ ሲሆን  በሁለት የተለያዩ ዓመታት ግን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ፓትርያርክ ባለመኖሩ ምክንያት በአቃብያነ መንበር በብፁዓን አባቶች ተመርተዋል። 👉አንደኛው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ፓትርያርክ በወቅቱ በነበረው አገዛዝ ምክንያት  በግፍ ለግዞት ስለተዳረጉ ግንቦት 11 ቀን 1968 ዓ/ም የዋለውን ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አቃቤ መንበር በነበሩት በብፁዕ አቡነ ዮሐንስ የመላ ትግራይ  ሊቀ ጳጳስ ርእሰ መንበርነት ተመርቷል። 👉ሁለተኛው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ 5ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ  ነሐሴ 10/2004 ዓ/ም ከዚህ ዓለም ድካም በማረፋቸው ምክንያት የጥቅምቱ 12/2005 ዓ/ም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔን የወቅቱ አቃቤ መንበር የነበሩት ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ  በርእሰ መንበርነት መርተዋል።   📌የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ  በቤተ ክርስቲያን ታላላቅ ጉዳዮች ውሳኔ የሚሰጥበት ሲሆን እምነት የማጽናት ሥርዓትን  ማስጠበቅ አስፈላጊ ከሆነም መሻሻል ያለባቸውን ጉዳዮች  የማሻሻል ሥልጣን ያለው የቤተ ክርስቲያን የበላይ አካል ነው። “በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።”   ሐዋርያት ፳፥፳፰ ©️ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ
2701Loading...
14
ርክበ ካህናት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓትና ትውፊት መሠረት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ በዓመት ሁለት ጊዜ ይካሔዳል። በየዓመቱ የሚካሔዱት ሁለቱ ጉባዔያት አንደኛ ቋሚ በሆነ ቀን በጥቅምት 12 ሲጀምር ሁለተኛው ግን የአጽዋማቱን አዋጅ ተከትሎ በሚወጣው የባሕረ ሐሳብ ቀመር መሠረት በዓለ ትንሣኤ በዋለ 25ኛ ቀን ይከናወናል። ዘንድሮ ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ ነገ ግንቦት 21/2016 ዓ/ም የሚጀምር ዛሬ ከሰዓት በኋላ በቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት ሥርዓተ ጸሎቱ ተከናውኗል።
3141Loading...
15
Media files
10Loading...
16
አስቸኳይ መልእክት የሰንበት ትምህርት ቤታችን ልጅ እናት በጠና ስለታመሙብን ሕክምና ሄደው ኦፕሬሽን (Operation ) ማድረግ አለባችሁ ስለተባሉ ። ለሕክምና የሚሆን ገንዘብ ደግሞ የተጠየቁት ከአቅማቸው በላይ 50000 ሺህ ብር ስለሆነ ፤ ለእናታችን መታከሚያ ቀን ደግሞ የቀረን አራት ቀናት ብቻ ስለሆኑ ማድረግ የምትችሉትን ነገር በማድረግ ፣ የምታውቁትንም ሰው በማስተባበር ፣ ለቤተሰብም ችግሩን አስረድታችሁ በመተጋገዝ ከፊታችን በቀሩን ጥቂት ቀናት በ አቅማችሁ ጸሎትም እያደረጋችሁ ቆዩ ! ከበጎ አድራጎት ክፍል ለበለጠ መረጃ 0953409521 0964881188 0967877206
3247Loading...
17
🌾🍇በጥንተ አድባራት ወገዳማት ደብረ ፀሀይ ቅዱስ ጊዮርጊስና ደብረ አድህኖ ቅዱስ ገብርኤል አብያተ ክርስቲያናት ፍሬ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት አዳጊና ህፃናት ክፍል የተዘጋጀ የነዳያን ምገባ መርሀ ግብር በቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ተከናውኗል ።😍 በሀሳብ በገንዘብ የደገፋችሁ እግዚአብሄር አምላክ ብድራችሁን ይክፈላችሁ።❤🙏 መታዘዝ፣ ማገልገል የማይደክማችሁ የሰንበት ትምህርት ቤት ፍሬዎች መድሀኒያለም አብዝቶ ይባርካችሁ።ከቤቱ አይለያችሁ❤❤🙏🙏🙏🙏
3381Loading...
የፍጥረት እንጀራ ብዙ ስሞች ሲገኑ አይታችሁ ሊሆን ይችላል ፣ ግን ሲያድኑ አላያችሁም ፣ ስሙን በመጥራት አጋንንት አንገታቸውን ደፍተው አልቅሰው ተዋርደው ወደ ቤታቸው ገብተዋል ። ይገርማችኃል የእርሱን ስም በመጥራት ነፍሳችን ትረካ ነበረ ። ሰዎች ብቻ የሚያውቁት ስም አይደለም አጋንንት ራሱ ስሙን ያውቁታል ደንግጠውም ይሄዳሉ ። በሽተኞችም የእርሱን ስም ሰምተው ድነዋል ። ይህ ስም ግን የማን ይመስላችኃል ? ታሪካችን ብቻ ሳይሆን ሕይወታችንም ሠላምን አገኝ ። ለዚህ አምላክ ታዲያ እኛ ብቻ አይደለንም ሠላሳ ስምንት ዓመታትን በአንዲት አልጋ ላይ ያስቆጠረው መፃጉዕም ይመሰክራል ፤ ምክንያቱም መፃጉዕ የተፈወሰው በእርሱ ነውና ። አሁን ሁላችሁም ለዚህ ስም መዘመር ጀምሩ ፤ ምክንይቱም ነገ መድኃኔዓለም ነውና ። ማለታቸው አይቀርም ቅዱሳን ሐዋርያት ስለ መድኃኔዓለም ተናገሩ ብንላቸው ። እንኳን ለመድኃኔዓለም ወርሃዊ በዓል አደረሳችሁ ። ጸሐፊ ፥ ናሆም መስፍን ግንቦት 2016
إظهار الكل...
3👍 2
🌾🍇ውድ የፍሬ-ሃይማኖት ቤተሰብ ፨፨፨ የምህላ ጸሎት መርሐ ግብር ነገ ማለትም በ27 እና በ28 እለት ። በህመም ውስጥ ለሚገኙት እናታችን ሲባል ባዘጋጀነው የ ጸሎት መርሐ ግብር ላይ ከጠዋቱ 12 ሰዓት እስከ 1:00ድረስ ብቻ የሚቆይ የምህላ ጸሎት ስለተዘጋጀ ከነገ ጠዋት ጀምሮ እንድንገናኝ ። በጠዋት ጸሎት ማድረግ አጋንንትን ያስደነግጣል ፤ እና ጠላትን መጣል ከፈለጋችሁ በጠዋት ጸሎት አድርሱ ፤ ደስ ብሏችሁ እንድትውሉ ቀናችሁን በምሕላ ጸሎት ስትጀምሩት ሁሉ መልካም ይሆናል ። ብቻችንን ቆመን ከምናደርገው ጸሎት ይልቅ የማኅበር ጸሎት እጅግ ኃይል አላት ።
إظهار الكل...
👍 2
🌾🍇ሰላም እንደምን አመሻችሁ ውድ የፍሬ-ሃይማኖት ቤተሰብ ፨፨፨ ነገ 25/2016 ወርሃዊ የሰማዕቱ ቅ/መርቆሬዎስ ዝክር ቀን ስለሆነ የሰ/ት/ቤት መ/ግብራችን 8:30 ተጀምሮ 10:40 ይጠናቀቃል። መ/ግብር እንዳለቀ አንድ ላይ ወደ መንበረ ጵጵስና ጌቴሴማኒ ቅ/ኪዳነምህረት ገዳም በሰ/ት/ቤቶች አንድነት ኅብረት የተሰናዳውን ዝክር ለመሳተፍ እንሄዳለን። ፨፨፨ የሰማዕቱ ምልጃ እና በረከት አይለየን🙏
إظهار الكل...
5👍 2
👋 ውድ የፍሬ-ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት አባላት የዛሬው የጸሎት መርሐ ግብራችን የሚሆነው ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ-ክርስቲያን ስለሆነ ። በጊዜ ልክ 10:30 ላይ የጸሎት መርሐ ግብራችንን ስለምንጀምር በተባባልንበት ሰዓት እንገናኝ ። ጊዜው የጠላታችን ቢሆንም ፤ በጸሎት ሁሉን ማድረግ ስለሚቻል እንዳትቀሩ ! ይህንንም እያሰባችሁ ራሳችሁን ለጸሎት አዘጋጁ ይለን ነበረ ። የአትሮኖሱ ንጉሥ ( ዩሐንስ አፈወርቅ ) ጸሎት ማድረግ ጠንካራ ክርስቲያን እንደሚያደርገን እየመከረን ፤ ይቆይ ነበረ ጸሎት ሲደርስ ሌላ ሥራ መሥራት ለሚያምረን እየነገረን ።
إظهار الكل...
👍 3
👋ሰላም እንደምን አረፈዳችሁ ውድ የፍሬ-ሃይማኖት ቤተሰብ እንኳን ለሊቀ ሰማዕታት ቅ/ጊዮርጊስ ወርሀዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን🙏 📌 ዛሬ በቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሰርክ መርሃ ግብር ላይ አገልግሎት ስላለን ሁላችንም በጊዜ በመገኘት እንድናገለግልና የበረከቱ ተካፋይ እንድንሆን አምላካችን ይርዳን 🙏🙏🙏 አሜን 📌የሚቀርቡ ዝማሬዎች   1. ህያውን ከሙታን 2. ማዕዶቴ ነሽ 3. እርሱ እንደ ንብ አውራ ዝማሬዎቹን ተዘጋጅተን እንምጣ መልካም ቀን ሰላም ዋሉ 🙏🙏🙏
إظهار الكل...
👋ሰላም እንደምን አረፈዳችሁ ውድ የፍሬ-ሃይማኖት ቤተሰብ እንኳን ለሊቀ ሰማዕታት ቅ/ጊዮርጊስ ወርሀዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን🙏
إظهار الكل...
🌾🍇 ውድ የፍሬሃይማኖት ቤተሰብ 👋 ከዚህ በታች ስማችሁ የተጠቀሰ የመርኃ ግብር መሪዎች ናችሁ ቅዳሜ ===== 📌ቅዱስ ጊዮርጊስ ሕፃናት ናትናኤል ስንታየሁ 📌ቅዱስ ጊዮርጊስ አዳጊ አብርሃም ላሜሮ 📌ቅዱስ ገብርኤል ሕፃናት ሄኖክ አሸናፊ 📌ቅዱስ ገብርኤል አዳጊ አማኑኤል አይተንፍሱ 📌ቅዱስ ገብርኤል ወጣት ዲ/ን አቤኔዘር አጥላባቸው እሁድ ===== 📌ቅዱስ ጊዮርጊስ ሕፃናት አራርሶ ተስፋዬ 📌ቅዱስ ጊዮርጊስ አዳጊ ናሆም መስፍን 📌ቅዱስ ገብርኤል ሕፃናት ፍጹም ጌታቸው 📌ቅዱስ ገብርኤል አዳጊ ወንድሜነህ ማሩ 📌ቅዱስ ገብርኤል ወጣት ዲ/ን አብርሃም ፨፨፨፨፨፨፨ ጥያቄ ወይም ሀሳብ ለማቅረብ ☎️ +251953409521 ☎️ +251923462089 ፨፨፨፨፨፨፨ "ማንም ሲያገለግል ፤ የአገልጋዩ ማንነት ይገለጥ ዘንድ ሳይሆን የእግዚአብሔር ክብር ይገለጥ ዘንድ ነውና ፤ ሁሉን በትህትና እና በፍቅር እናድርግ"
إظهار الكل...
👍 4
👋 ሰላም እንደምን ዋላችሁ ውድ የፍሬ-ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት አባላት 📌📌📌 የዛሬው የረቡዕ መዝሙር ጥናት መርሃ-ግብር አይኖረንም ላልሰሙት በመንገር እንተባበር። መልካም ጊዜ🙏🙏
إظهار الكل...
😢 2💔 1

7🥰 1