cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜

📚📚እንኳን በደህና መጡ📖📗🧾 ➥ እዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ የ አማርኛ እና እንጊሊዘኛ ..... መፅሀፍትን በ 📙 Pdf እና ትረካዎችን እና ሌሎችም ጠቃሚ ነገሮችን ያገኛሉ። 📖 ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል‼️ B-) :-መረዳዳት ቢኖር ሁሉም ቢተባበር 100K ይደርስ ነበር ። For any comment @Meki3

إظهار المزيد
Advertising posts
1 858المشتركون
-124 hour
لا توجد بيانات7 يوم
-730 يوم

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

የባከኑ ቀናት ክፍል አንድ (ሂባ ሁዳ) . . "ማሂር" ስሙን ባነሣሁት ቁጥር ፈገግታው ይታወሰኛል። ያኔ ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር ትምህርት ቤት የቀየርኩት፤ ሌሎች ሁለቱ ጓደኞቼ ቀድመውኝ እዛ ትምህርት ቤት ስለገቡ የቀረነው እኔና ኢክራም ስምንተኛ ክፍል እዛው እነሱ ጋር ተመዘገብን። ትምህርት በተጀመረ በሣምንቱ ሰኞ ለመማር ሄድን፤ ግን ደግሞ ሶስታችን አንድ ክፍል ሆነን ኢክራም ግን ሌላ ክፍል ደረሣት። በዚህም ከፍቶን ነበር፤ ምክንያቱም ከመዋለ ህፃናት እስከ ሰባተኛ ክፍል አብረን ነበር የተማርነው። ለመጀመሪያ ጊዜ ስምንተኛ ክፍል ላይ ተለያየን። * የትምህርት የመጀመሪያው ቀን፤ ኢክራምን ወደ ክፍሏ አድርሠናት እኛም ገብተን መማር ጀመርን፤ ረፍት ሰዐት ላይ ኢክሩ መጣች.. <<እንዴት ነው ተመቸሽ ክላሱ? ተዋወቅሻቸው?>> የኔን ያህል የከፋት አትመስልም። <<አይ ኢክሩ ያላንቺ ሁሉም ነገር ደባሪ ነው ባክሽ። የምን መተዋወቅ.. ከማንም ጋር አልተነጋገርኩም። ዩስራ ና ራቢ ሲቀሩ....ያው ቀስ በቀስ እንለምዳቸዋለን።>> መለስኩላት። . ኢክሩ አንድ ቦታ መቆም አትወድም፤ ጊቢውን ዞር ዞር እያልን ማየት ጀመርን። ከመቼው እንደተደወለ ባይገባንም እረፍቱ ሲያልቅ ወደ ክፍል ለመግባት ዞረን ለመመለስ መንገዳችንን ተያያዝን። ኢክሩን ክፍሏ ለማድረስ እየሄድን ዩሲ ና ራቢን ብንፈልጋቸው ልናገኛቸው አልቻልንም። እኔ ላደርሣት ተስማምተን ሶስተኛ ፎቅ ላይ ወደ ሚገኘው ክፍሏ ለመሄድ ደረጃ መውጣት እንደጀመርን ከፊታችን ደረጃ በመውጣት ላይ ያለ ልጅ አየን። ከኢክሩ ጋር ዞር ብለን ተያየን በዛው ቅፅበት <እንዴ ማሂር> እኩል ነበር የጠራነው። ሁለት ድምፅ በአንዴ ሲያደምጥ ወዲያው ዞረ ፤ አየን.. ግራ ተጋብቶ ባለበት ቆመ። እኛ እንደማፈር ብለን እርስ በእርስ ተያይተን ቶሎ አጎነበስን.... * ከልጁ ጋር ሳንነጋገር ኢክሩን ሸኝቻት ለብቻዬ ወደ ክፍሌ ገባሁ። አስተማሪው ግን አልገባም፤ ተማሪዎች ክፍሉን ቅውጥ አድርገውታል። ብዙዎቹ ሰባተኛ ክፍል አንድ ላይ ስለነበሩ ለመግባባቱ ጊዜ አልፈጀባቸውም። እስካሁን ዩስራ ና ራቢያ አልተመለሱም፤ እኔም ብቻዬን ቁጭ ብያለው። በዚህ ጊዜ ከኃላዬ ያለችውን ልጅ አዲስ ስለሆነች ይመስለኛል አንድ ልጅ ይዝጋታል፤ ደግሞም ያሾፍባታል.. ሌሎች ሁለት ልጆች ደግሞ ይስቃሉ። እሷ ጋር ሲጨርስ እኔም ጋር አፉን ሊከፍት ወደኔ መጣ <<ስሚ እናቱ ማለቴ ሰሚራ..>>ዝም አልኩት። ከሁለቱ አንዱ <<ባቢ ዱዳም እኛ ክፍል አለ ማለት ነው?>> ተደረበለት። <<ሃሃሃ>> ሶስቱም ሣቁ አላናደዱኝም፤ ጅል ነው የመሰሉኝ። እንደናኳቸው ሲገባቸው... <<ቆይ ማን ነኝ ብለሽ ነው እያናገርንሽ ዝም የምትዪው?>> ባቢ ያሉት ልጅ ነው የሚያወራው። አሁን አላስቻለኝም። <<ማን ስለሆንክ ማወራህ ይመስልሃል? ቦታህን እወቅ!>> ሣልዞር ነበር የመለስኩለት። <<አረ ባቢ በፍሬሽ ተማሪ ልሰደብ!>> ብሎ ሲነሳ ዞር ብዬ አየሁት። ወደኔ እየቀረበ ነው.. ሊደባደብ መሆኑ አልጠፋኝም። <<እንዴ! ባ..ቢ ና ና!>> ይህን ሲሠማ ዞረ፤ እኔም ተከትዬው ዞርኩ። አብረውት ከነበረው ልጅ እስካሁን ዝም ያለው ነበር። ልክ ሣየው ቶሎ ዞር አልኩኝ። <እንዴ ማሂርን የሚመስለው ልጅ ደግሞ ምን ይሰራል እዚህ?> ከራሴ ጋር ነበር... <<ምንሼ ሎጋው?>> በጥያቄ አስተያየት ማሂርን የሚመስለውን ልጅ ተመልክቶት ግራ እየተጋባ መልስ ይጠብቃል፤ ባቢ። <አሃ ሎጋው ነው እንዴ ስሙ? ማሂር ስንል ምን አዞረው ታዲያ?> ለራሴ አንሸኳሸኩ... <<በቃ ና አልኩሃ>> ብሎ ተነስቶ ወደ በሩ አመራ፤ "ሎጋው"። <<አቤላ ምንሼ ነው የሚለው እእ?>> ባቢ አልዋጥልህ እያለው ቢሆንም "ሎጋው"ን ተከትለው ወደ በሩ አከታትለው ሄዱ። ብቻዬን ቀረሁ ባቢ ፣አቤላ ፣ሎጋው፣ አሃ የክፍሉ ጉልቤ እናንተ ናችሁ ማለት ነዋ!.... * የመጀመሪያው አስተማሪ ሣይገባ ቀጣዩ አስተማሪ መጣ። ከፊት ካሉት ጋር ትንሽ አወራና <<እሽሽሽ ዝምታ!>> ብሎ ዴስኩን መታ መታ አደረገ። ቀጥሎም እሱ ለትምህርት ቤቱ አዲስ እንደሆነና ስማችንን እንድናስተዋውቅ ጠየቀን። ከፊት ጀምሮ እያስተዋወቁ እነ ባቢ ጋር ሲደርስ <<እኔ ባቢ እሱ..>> ብሎ ጓደኛው ጋር ሲደርስ በሩ ተንኳኳ <<ቆየኝ..>> መምህሩ ለመክፈት ወደ በሩ ተራመደ። <<አረ ቲቸር እኔ ባጣ ቆየኝ ነኝ እንዴ?>> <ሃሃሃሃ...> ተማሪው በሳቅ አደመቀው፤ ግማሹ ምን እንደተባለ ሣይሰማ ከተሣቀማ እናድምቀው ይመስል ሳቁን ተቀባበሉት። <<ኢብቲላ?>> አስተማሪው ነበር፤ በሩን ከፍቶ ወደኛ መለስ እያለ... ከውጪ ዩስራን አየሁዋት። <<የለችም?>> አለ ዝም ሲባል። <<ኧረ አለች እዛ ጋር...>> ዩስራ ወደኔ እየጠቆመች ታሳየዋለች። <<አንቺ ስጣራ ለምን ዝም አልሽ?>> አፈጠጠብኝ ። <<መቼ ጠራኸኝ?>> <<ኢብቲላ ስል አልሰማሽም?>> ቆጣ አለ። <<ኧረ የሌላ ሰው መስሎኝ ነው...>> ተማሪው እየቀለድኩበት ስለመሰለው ክፍሉን በሳቅ አናጉት <ሃሃሃሃ..>። መምህሩ ጭራሽ ይበልጥ ተናደደ። <<ነይ ውጪ እንዳገቢ!>> <<ለምን?>> <<ስርዐት የለሽማ!>> <<ማለት?>> ተማሪው ፀጥ አለ፤ <<አትወጪም!?>> በጣም ጮኸብኝ። ተማሪው ዝም ብሎ የሚሆነውን ይከታተላል፤ ባቢ <<ኧረ እንዳትወጪ.. እንዳሠሚው>> አንሾካሸከ። አስተማሪው ፈጠን ፈጠን እያለ በሩን ብርግድ አድርጎ ከፈተው። በዛው እርምጃው ወደኔ እየመጣ ነው፤ ከመቼው እንደ ደረሠ ባላውቅም አጠገቤ ቆመ። ሲፈጥረኝ ሰውን ንቄ መተው ያስደስተኛል። <<አንቺ ጎትቼ ሣላወጣሽ ውጪ!!>> እጁን ሲያነሣ ተማሪው በአንድ ድምፅ <ኧረረረረ....> ሊመታኝ መሠላቸው፤ ተንጫጩ። <<እንዳትነካኝ!!>> ለካ ጮክ ብዬ ነው ያልኩት፤ በአንዴ ጫጫተው በዝምታ ተዋጠ። ከቦታዬ ተነስቼ ቆምኩኝ በዚህ መሃል አንድ አስተማሪ ወደ ክፍላችን ገባ፤ ተቆጣጣሪ ነው። ድምጽ ሰምቶ ነበር የመጣው። <<ምንድነው?>> ሁላችንንም እያፈራረቀ አየን። <<በጣም አስቸገረች ክፍሉን እያስረበሸች ነው።>> <<ኧረረረረ.. እንዴዴዴ...>> አስተማሪው ወደኔ እየጠቆመ ሲያወራ ተማሪው በአንድነት ከቅድሙ በባሰ መልኩ ተጯጯኸ። <<ዝም በሉ! ነይ አንቺ !>> ተቆጣጣሪው ነበር። እንደለመደብኝ ጅንንን ብዬ ስሄድ <<ይኸው ንቀቷን እየው>> አስተማሪው፤ እልህ እንደያዘው ያስታውቃል። ሁሉንም አንድ በአንድ ነገረው። <<ታዲያ ጥፋቱ ያንቺ ነዋ>> ተቆጣጣሪው ኮስተር አለ። <<አይ አይደለም...>> ረጋ ብዬ መለስኩ። <<እንዴት?>> <<ስሜ ኢብቲላ አይደለማ!>> <<እና ማን ነው?>> ተቆጣጣሪው በመገረም ይመለከተኛል። የኔ ስም ሁሉንም ስለማያውቁት ለመስማት እንደ ፈለጉ ገባኝ። <<ኢብቲሣም ነው ስሜ>> በጣም ዝቅ ባለ ድምጽ። ተማሪው እእ ቢሉም ምላሽ ግን አላገኙም። ተቆጣጣሪው ከአስተማሪው ጋር ሲነጋገር ወደ ቦታዬ ተመልሼ ተቀመጥኩ። ግን ሁሉም እያዩኝ ነው፤ ምናልባትም <ምኗ ደረቅ ናት> እያሉም ይሆናል። . #ክፍል_2 ይቀጥላል...
إظهار الكل...
👍 3 1
"ማርፈድ ከትምህርት ቤት ይልቅ ህይወት ላይ ዋጋ ያስከፍላል" #የባከኑ_ቀናት #አዲስ_ተከታታይ_ልቦለድ ✍ ፀሀፊ፡ ሂባ_ሁዳ #ኢትዮ_ልቦለድ . . ማታ 1:00 ላይ ይጠብቁን🥰
إظهار الكل...
👍 2
إظهار الكل...
👍 5🏆 1
ተራው የሶስተኛው ሚዜ ነው። እሱም ከሁለተኛው ሚዜ ተቀብሎ ለሙሽራው መልዕክት ይሰጥ ጀመር። " አህመድ ነብዬ አህመድ ነብዬ ሙሽራው ሙሽራው ሁልጊዜ ውደዳት ሚስቴም ብቻ ሳይሆን እመቤቴ በላት ኢማኔ ነሽ በላት ደስታዬም ነሽ በላት ሁልጊዜ ንገራት እንደምትሳሳላት ጊዜህን አካፍላት ወቅትህን አካፍላት ውደዳት ውደዳት ደስተኛ አድርጋት እንደምትሳሳላት እንደምታስባት በተግባር አሳያት ሀዲያ ስጦታ ለሚስትህ ደስታ እንዳትረሳት ላፍታ ስታያት ጠዋት ማታ ዝንጥ አርጋት ፈታ ( ×2 ) " ወንዶቹ በጭብጨባ ሴቶቹም በእልልታ አድምቀውታል። የተለማመዱትን ባመረ ሁኔታ ከጨረሱ በኋላ በገጣሚ አብዱልማሊክ ላሊ ( ጎራው ) ተፅፎ በማዲህ አሚር ሁሴን የተዜመውን ምርጥ የሰርግ መንዙማ ተለቆ እሱን እየተከተሉ አብረው ማዜም ጀመሩ። " አርሂቡ ነብዬ አርሂቡ ነብዬ በይ መሬት ሁኚለት ሰማይ ይሆንሻል ፍራሽ ከሆንሽለት ምሰሶ ይሆንሻል ባርያ ከሆንሽለት ባርያ ይሆንሻል ክፍተት አትፍጠሪ ሰው ይገባብሻል ሁኚ ለሱ ቆንጆ ደምቀሽ ተዋቢለት አይኑም ወደሌላ እንዳይመለከት ከአንደበት ከላምሽ ክፉ ከቶ አይውጣ በረድ በዪለት እሱ እንኳን ቢቆጣ " ረያን አምሪያ ቅርቡ ስለነበረች ነካ አድጓት " ላንቺ ነው በደንብ ስሚ " አላት በአፉ ። ያለውን ተረድታዋለች ፈገግ አለች... " እጅግ ያምራል ትዳር በሱና ከሄዱ ከጀነት ያደርሳል ፅኑ ነው መንገዱ እንደናንተ ሁሉ ይቀጥል በሌላው ለወንድሙ ሁላ ይድረስ እና እጣው የተቃና ጎጆ ያማረ የደመቀ እስከመጨረሻው ይሁን የፀደቀ በልጅም አጊጡ በልጅ ልጆቻችሁ ድጋሚ እንደገና ይጀድድ ስማችሁ ሰላማችሁ ይብዛ እጅጉን በረካ ያድላችሁ ፀጋ የበረካ ታንኳ በሸሪዓ ቁሙ በነብዬ ሱና በአንድነት አብሩ ክንዳችሁም ይፅና በናንተም ይሰማ የኸይራቶች ዜና ሁሌም የሚጀድድ ዳግም እንደገና! ( ×2 ) " ትምህርት ወስደውበትና ብዙ ተመርቀውበት ሲያሽቁ ቆዩ። ከታሰበው በላይ ሆኖ የሰርጋቸው ቀን በማይረሱ ብዙ ትዝታዎች ተከቦ አለፈ። * " ከ 4 አመት በኋላ " አምሪያ በፋርማሲስት ተመርቃ ስራ ይዛለች። ረያን ህክምና ስለሆነ እያጠና ያለው ገና ነው። በላፕቶፑ ሲሰራ የነበረውን ስራ እንደጨረሰ አጠገቡ ያለውን ዲያሪ ከፍቶ መፃፍ ጀመረ። " አልሀምዱሊላህ! ሁሌም ቢሆን ምስጋናዬን ለአላህ ባደርስም አልጠግብም! ደጋግሜ አልሀምዱሊላህ እላለው! ዛሬ ላይ ሆኜ የበፊቱን ነገር ሳስታውሰው ይገርመኛል። እኔና አምሪ እዚ ከመድረሳችን በፊት ያለፉትን ነገሮች... ብዙ ጊዜ የፍቅር ግኑኝነተችም ሆነ ትዳር የሚፈርሰው አንድ ላይ ከሚያደርገን እልፍ ምክንያቶች ይልቅ ልታለያየን የፈለገችውን አንድ ምክንያት አግዝፈን ስለምናይ ነው! በኔና አምሪ መሀል ብዙ ነገር ቢፈጠርም ፤ አንድ ላይ እንድንሆን አልተፃፈም ብለን እንድናስብ ያደረጉን ብዙ ፈተናዎች ቢገጥሙንም ችግሮችን ማለፍ ግን አንዱ የህይወት አካል ነው። << ኢነመዓል ዑስሪ ዩስራ ( በእርግጥም ከችግር በኋላ ምቾት አለ! ) >> አይደል አላህም ያለን? አምሪዬ ቃል የተገባልኝ ምቾቴ ናት! እስከጀነት ላፈቅራት፣ አብሬያት ልሆን ቃል የገባውላት ንግስቴ! " ፅሁፉን ፅፎ ሳይጨርስ አምሪያ ከኋላው መጥታ አቀፈችው። " እኔኮ እያጠናህ መስሎኝ...ምን እየሰራህ ነው? " ዲያሪውን ልትወስደው ስትል በእጁ ያዘባት። " ሚስጥር ነው እንዴ? ምንድን ነው የፃፍከው? " ከፍ አድርጎ የያዘባትን ልትነጥቀው ትታገላለች። " ስላንቺ ነው የፃፍኩት! " " እና አስነብበኛ..." " አይ ሌላ ጊዜ አሁን እየታገልሺኝ ልጁን አታስጨንቂው " ዲያሪውን ጠረንጴዛው ላይ ካስቀመጠ በኋላ አቅፏት እጁን ሆዷ ላይ አደረገው። " ይኸውልሽ ከረገጠሽ ንገሪኝ እሺ..." " ኧረ ባክህ ምን ልታደርግልኝ ከዛ? " አለች እየሳቀች። " ይመከራላ..." " ወረኛ...በል ባይሆን ገንፎ ፣ ሙቁ ምናምን እንዴት እንደሚሰራ ከአሁኑ ተለማመድ! " " ታዛዥ ነኝ የተከበሩ። " ግንባሯን ስሞ ደረቱ ላይ ለጠፋት። ኢማን ፣ ፍቅር ፣ ትዕግስት ፣ ደስታ ፣ ስኬት! #ስላንቺ 🥰 ታሪኩ እንዴት ነበር እስኪ አስተያየታችሁን ኮሜንት ላይ ጻፉልን 🌸🌺🌸🌹✿❯────ተፈፀመ! ────❮✿ 🌷🌸🌺🌹
إظهار الكل...
👍 5 1🎉 1
. " ስላንቺ " [ ✍ ፀሀፊ፡ ሶፊያ አህመድ ] ╚─━━━━░★░━━━━─╝ #ክፍል_አስራስድስት ( ⓰ ) የመጨረሻ ክፍል ✿❯────「✿」────❮✿ ስልኩ የተገኘው አምሪያ ሎከር ውስጥ አለመሆኑን ስታረጋግጥ ተቆጣጣሪዋን አስፈቅዳ እየሮጠች ወጣች። ስለነገሩ ለማወቅም ጊዜ አልነበራትም ወደባሏ ፣ ወደናፍቆቷ በረረች። ልክ የዩንቨርስቲው በር ጋር እንደደረሰች አይኗን እያንከራተተች ረያንን ፈለገችው ፤ ግን አልነበረም።ልትደውልለት ስልኳን ከቦርሳዋ ስታወጣ ረያን ከኋላ በኩል ወገቧን አቅፎ አሽከረከራት። ፊቱን ባታየውም በጠረኑ በደንብ ለይታዋለች። " አንተ አውርደኝ እንዴ? " በደስታ ትፍለቀለቃለች። ረያንም ለቀቃትና ወደራሱ አዙሮ አቀፋት። ከብዙ አመታት በኋላ ተጠፋፍተው እንደተገናኙ ሰዎች ለረጅም ሰዓት ተቃቅፈው ቆዩ። " እ ባልየው የት ነው ያረፍከው ታድያ? " ጆሮው ስር እንደሆነች ጠየቀችው። " እዛው መነኸሪያው አከባቢ ነው የያዝኩት...ምሳ በልተሻል? " ከእቅፉ አውጥቶ አይኗን ትኩር ብሎ ማየት ጀመረ። " እመጣለሁ ብለህ ልቤን ሰቅለኸው ብበላስ ይወርድልኛል ብለህ ነው? ምንም አይሰማህም ሆዴ ራሱ እንደዚ እየጮኸ? " " እኔን እናቴ...በቃ እንሂድ ቆንጀ ምሳ ነው የምገብዝሽ። " ኮንትራት ታክሲ ይዘው እሱ ወዳረፈበት ሆቴል ሄዱ። እዛው አሪፍ ምሳ በሉ። 11 ሰአት ሲሆን ሁለቱም ጅማን ስለማያውቋት ለመጎብኘት እዛው አከባቢ ወክ ለማድረግ ወጡ። የአመሻሹ ድባብ በጣም ደስ ይላል። አየሩም በደንብ ተስማምቷቸዋል። እጅ ለእጅ ተያይዘው የሆድ የሆዳቸው እያወሩ እስከ ምሽቱ 1 ሰአት ድረስ ሰፈሯን ዞሯት።በጣም ውብ ከተማ ነች! እዛው ሆቴል እራታቸውን በልተው ረያን ቀድሞ ወደያዘው ክፍላቸው ገብተዋል። " አይንሽን ጨፍኚ። " አላት አልጋው ላይ ከተቀመጡ በኋላ... " እኔ አልወድም መጨፈን..." " አትከራከሪኝ...ብዙ አይቆይም። ቶሎ በይ ጨፍኚ። " ምን ሊያደርግ እንደሆነ ግራ ቢገባትም ደስ እንዲለው ብላ ጨፈነችለት። ረያን ከኪሱ ውስጥ አንድ ስጦታ አወጣ። እቃውን ከከፈተ በኋላ ውስጥ ያለውን የአንገት ሀብል አደረገላት። " አሁን መግለጥ ትችያለሽ። " አምሪያ ያደረገላትን ሀብል አየችው። የስሟ የመጀመሪያ ፊደል ያለበት የብር ሀብል ነው። "ወደድሽው? " አላት? መልሷን ጥበቃ ከንፈሯ ላይ እንዳፈጠጠ። አምሪያ ፈገግ እያለች አየችውና እጆቿን አንገቱ ስር ከታ አይኗን እንዲያይ ቀና አደረገችው። " ምነው አልወደድሽውም እንዴ? " አላት ለደቂቃዎች ምንም መልስ ሳትሰጠው ስትቀር...አምሪያ ሳትለቀው ጠጋ ብላ በስሱ ከንፈሩን ሳመችው። " በጣም ወድጄዋለሁ! አመሰግናለሁ የኔ ባል! " አይን አይኑን ትመለከታለች። የረያን ስልክ ሲጠራ ሁለቱም ከገቡበት ሀሳብ ባነኑ። " እ አንተ የፍቅር መቀስ..." አለው ረያን ስልኩን እንዳነሳ። ፋሩቅ ነበር የደወለለት። " ውይ የማይሆን ሰአት ደወልኩ መሰለኝ..." " አሰላም አለይኩም ፈሩ...ኧረ ዝም ብለው ሲቀልድ ነው።" አምሪያ ወደረያን ጠጋ ብላ ተቀመጠች። በ Video call ነበር የሚያወሩት። " እነሰብሪን ናቸው እኮ አንድ ላይ ካላዋራናቸው ብለው..." ሰብሪን እና ጄሪም ተቀላቀሉ። እነሱን ለማዋራት ካፌ ተሰብስበው ነበር። ሁሉም በደምብ ሰላም ሲባባሉ ቆዩ። " እ ነገርካት ስለአዲሱ ነገር? " አለ ፋሩቅ ሰላምታቸውን እንደጨረሱ። " ኧረ ባክህ አይደለም ስለናንተ ለማውራት እራሳችን እንኳን ናፍቆታችንን መች በቅጡ ተወጣን? " " እንዴ ምንድን ነው የሚነገረኝ? " አለች አምሪያ ወደረያን ፊቷን መልሳ። " ሰብሪንና ፋሩቅ በቅርቡ ለመጋባት አቅደዋል! " አላት። " ኦ ማሻአላህ...መብሩክ ብለናል። እና ኒካው መች ነው? " በጣም ደስ ብሏታል። " ኒካህ አይኖርም ውዴ ማለት ሰርግ ብቻ ነው። እመቤቲቷ ሁለት ድግስ አልፈልግም ብላለች። " አለ ፋሩቅ። ፋሩቅ የራሱ ስራ ስላለው ተጋብተው አብረው ለመኖር ነው ሀሳባቸው። " እኔ ምላችሁ ግን ለምን አምሪና ረዩም ከነሱ ጋር በአንድ ቀን አትሞሸሩም? " አለች ጄሪ መሀል ገብታ። " ምን ያደርጋል ዞሮ ዞሮ አምሪ ተመልሳ ወደአዲስ እስከምትመጣ ድረስ አብረው አይኖሩም። " ሰብሪን ሀሳቧን አልደገፈችም። " ታድያ ምን ችግር አለው? እስከዛ ቤታቸው ፣ እዚ ያለውን ነገር በሙሉ እያስተካከሉ ይቆያሉ። እስኪ አስቡት የረጅም አመት ምርጥ ጓደኛሞች በአንድ ቀን ሲጋቡ...እንዴት ደስ እንደሚል አስባችሁታል? " ጄሪ ብዙ ነገር ብላ በመጨረሻም አሳመነቻቸው። * የመጀመሪያው አመት እንዳለቀ አምሪያ ወደአዲስ አበባ ተመለሰች። ሚኪም እሷ ከመጣች ከሁለት ቀን በኋላ ወደአዲስ መጣ። የቆረጡት የሰርግ ቀን ሊደርስ ቀናቶች ስለቀሩት ቤተሰቦቿ ሽር ጉዱን ጀምረው ነበር።ቀኑን ስታስበው ከአሁኑ ደስታ ይወራት ጀመር። አይደርስ የለ የጓጉለት ፤ የናፈቁት ቀን ሁሉት ሙሽሮችን ይዞ ከተፍ አለ። ጄሪ በአጋጣሚ ያመጣችው ሀሳብ ሁሉም ጋር የህይወታቸው ምርጥና የማይረሳ ቀን ሆነ። ሰብሪንና አምሪያ ባሎቻቸው እስከሚደነግጡ ድረስ አምሮባቸው ነበር። በእርግጥ ረያንና ፋሩቅም እስከዛሬ እንደዚ የማረባቸውን ቀን ማንም አያስታውስም ፤ ጄሪና ሚኪ አንደኛ ሚዜዎች ሆነው ሙሽሮቹን ከማስደሰት አልፈው እራሳቸውም ተመቻችተዋል። ጄሪ በለበሰችው ቀሚስና ሂጃብ ምክንያት ከጓደኞቿ ውጪ ማንም አለያትም ነበር። ምሳ በልተ ከጨረሱ በኋላ ሚኪ ለአንድ ሳምንት ሲለማመድ የነበረውን የማዲህ ማህፉዝ አብዱና የማዲህ ሷሊህ ሙሀመድን የሰርግ መንዙማ ተነስቶ ማለት ጀመረ። " አህመድ አህመድ አህመድ ነብዬ ሚዜዎቹና አጃቢዎቹ እሱ ያለውን በማለት ይቀበሉታል ወለላው ነብዬ...አህመድ ነብዬ አዛኙ ነብዬ...አህመድ ነብዬ ቆንጆ ነብዬ...አህመድ ነብዬ " የሴቶቹ ሚዜዎችና አጃቢዎች ሁለቱን ንግስቶች ሲከቡ ወንዶች ሚዜዎችና አጃቢዎች ደሞ ንጉሶቹን ከበዋቸውል። ሚኪ የተለማመደው ግጥም እንዳይጠፋበት በውስጡ እየፀለየ ቀጠለ... " ሙሽራው ሙሽራው ሙሽሪት ሙሽሪት ሙሽሮች ሙሽሮች ሙሀባችሁ ይስባ በኑሮም በሀያት ንግግር ልመዱ መሹራ ውደዱ ሀጃ አታሳድሩ እንድትፋቀሩ ስትነጋገሩ የጠናው በገሩ ይከፈታል በሩ ይከፈታል ኸይሩ በአላህ በጀባሩ! ( ×2 ) " ሁለተኛው ሚዜ ተቀብሎ ለሙሽሪቷ መልዕክቱን ማስተላለፍ ጀመረ። " አህመድ ነብዬ አህመድ ነብዬ ሙሽሪት ሙሽሪት የባልሽ እመቤት የደስታው መነሻ የሀዘኑ መርሻ የፍቅር መሸሻ የአባወራ ጋሻ አድርጊው መከታ ውደጂው በደስታ በየሁሉም ቦታ ለስራው መካሪ ለሀጃው ተጠሪ በባልሽ ማታፍሪ ሁልጊዜ ምትኮሪ ቤቱን እንዲናፍቅ እየሰጠሽ ፍቅር ሙያሽን 'ሚያከብር ደስተኛ አድርጊው ዘንጠሽ ጠብቂው ለቤተሰቦቹውም ለእናት አባቶቹ ለእህት ወንድሞቹ ለዘመድ ጓዶቹ የሚስትነት ሀድ አሳዪው መውደድ ( ×2 ) "
إظهار الكل...
👍 1
➖➖➖➖➖❤️➖➖➖➖➖ ጥሩ እድል ሊሆንም ላይሆንም ይችላል”   ጣፋጭ ታሪክ        በአንድ መንደር ውስጥ የሚኖር አንድ ገበሬ ነበር። ከእለታት አንድ ቀን የዚህ ገበሬ ፈረስ ይጠፋል። የመንደሩ ሰው ሁሉ ተሰብስቦ ወደ ገበሬው ቤት በመሄድ ሃዘናቸውን ይገልጹለታል።እንዲህ ሲሉ ” ፈረስህ በመጥፋቱ አዝነናል፤ እንደው ምን አይነት መጥፎ እድል ነው?” ሲሉት። ገበሬው መልሶ “መጥፎ እድል ሊሆንም ላይሆንም ይችላል” ብሎ መለሰላቸው።በበነጋታው የጠፋው ፈረስ ሌሎች ሰባት ፈረሶችን አስከትሎ መጣ። ይህንን የተመለከቱ የሰፈሩ ሰዎች ወሬውን ይሰሙና ወደ ገበሬው ቤት በመሄድ እንዲህ ይሉታል።” የሚገርም እኮ ነው፤ አንድ ፈረስ ነበረህ አሁን ስምንት ፈረሶች ሆኑልህ። እንደው ምን አይነት ጥሩ እድል ነው?” ገበሬውም ” ጥሩ እድል ሊሆንም ላይሆንም ይችላል” ሲል መለሰላቸው።ሲነጋ የገበሬው ልጅ ከስምንቱ ፈረሶች አንዱን ሰርቆ ሊጋልብ ሲሞክር ፈረሱ አሽቀንጥሮ ይጥለውና ልጁ እግሩን ይሰበራል።ወሬውም በሰፈሩ ሁሉ ተሰማ። እንደ ልማዳቸው የሰፈሩ ሰዎች ተሰባስበው ” ውይ የልጅህ መሰበር እንዴት ያሳዝናል ባክህ? እንደው ምን አይነት መጥፎ እድል ነው?” አሉት። ገበሬውም መልሶ ” መጥፎ እድል ሊሆንም ላይሆንም ይችላል” ሲል እንደልማዱ በእርጋታ መለሰላቸው። በቀጣዩ ቀን የመንደሩ የጦር ተቆጣጣሪ፤ ወጣቶችን ለጦር ሜዳ ሊመለምል ወደ መንደሩ ይዘልቃል። የሁሉንም ቤት ወጣት ወንዶች ለጦርነት ሲመለምል ከፈረስ ላይ የወደቀውን የገበሬውን ልጅ ግን እግሩ ስለተሰበረ ሳይወስዱት ቀሩ።ይሄኔ የመንደሩ ሰዎች ተሰባስበው ወደ ገበሬው በመሄድ እንዲህ አሉት “አየህ ልጅህ እግሩን በመሰበሩ ወደጦር ሜዳ ሳይወሰድ ቀረ፤ እንደው ምን አይነት ጥሩ እድል ነው?” ገበሬው ግን አሁንም እንዲህ አላቸው ” ጥሩ እድል ሊሆንም ላይሆንም ይችላል” እናም ..................................................... ብዙን ጊዜ በኑሮዋችን ውስጥ አንድ ነገር ሲከሰት በችኮላ “መጥፎ” ወይም “ጥሩ” እድል በማለት እንፈርጃለን። መልካም ያልነው ነገር መጥፎ ነገር ይዞ ሲመጣ፤ መጥፎ ያልነው ነገር ደግሞ መልካም ነገር ይዞ ብቅ ሲል፤ ዳኝነታችን መሰረት የሌለው እንደሆነ እንረዳለን። ወደ ኋላ መለስ ብለን የመጣንበትን ብንቃኝ፤ በእርግጠኝነት በአንድ ወቅት መጥፎ እድል ናቸው ብለን የፈረጅናቸው በኋላ ላይ ግን መልካም ነገር ይዘውልን የመጡ የህይወት አጋጣሚዎችን እናገኛለን። እኛ ግን ቀድመን “መጥፎ” እና “ጥሩ” እድል እያልን ነገሮችን ስንከፋፍል፤ አይምሮዋችን አስቀድሞ ነገሮችን ስለሚዳኝ ጭንቀት በጊዜው ከሚሆነው ነገር ጋር እንዳንስማማ ያደርገናል። የገበሬው አመለካከት ግን እጅግ የሚደንቅ ነው። የሚገጥሙት ነገሮች ምን ይዘው እንደሚመጡ ስለማያውቅ “መልካም” እና “መጥፎ” እድል እያለ እራሱን ላልተጠበቀ ሃዘን አያዘጋጅም።የፈረሱ መጥፋት መጥፎ እድል ነው ብሎ ለማለት አልደፈረም። ምክንያቱም የሆነው ነገር ምን ይዞ እንደሚመጣ ስላላወቀ። ፈረሱ ሌሎች ፈረሶችን ይዞ ሲመጣም “መልካም እድል” ብሎ ሊደመድም አልወደደም፤ እንደሰወኛ ብናስብ እነዛ ፈረሶች ባይኖሩ ልጁ አይሰበርም ነበር። የልጁን መሰበርም እንደ መጥፎ እድል ሊወስደው አልፈለገም፤ እንደሰወኛ ግን ልጁ እግሩ ባይሰበር ኖሮ፤ እንደሌሎቹ የሰፈር ወጣቶች ከአባቱ ተነጥሎ ወደ ጦር ሜዳ በተወሰደ ነበር። እንዲህ አይነት አመለካከት ከአልታሰበ የስሜት መናወጥ ያድናል፤ እርግጥ ነው ቀላል አይደለም። ነገር ግን በህይወት መንገድ ላይ ስንጓዝ የሚገጥሙን ሁኔታዎች ጊዜ ብቻ የሚፈታው ሚስጥር በውስጣቸው አለ። ነገሮች ሁሉ ወደ በጎ እየተቀየሩልን እግዚአብሔርን ባማረርንበት አፋችን እንድናመሰግነው ያደረገን አጋጣሚ በሁላችንም ህይወት ውስጥ አለ። በአንጻሩ በስንት ልመና ያገኘነውን ነገር ምነው ባትሰጠኝ ኖሮ ብለን ያማረርንበትም ጊዜ ይኖራል። በዚህ አለም ላይ ያለምክንያት የሚሆን ምንም ነገር የለም። ምናልባት አሁን እያለፍነበት ያለው ፈተና እና የኑሮ ጦርነት እድላችንንን እንድንማረር እያረገን ይሆናል፤ ነገ የሚመጣውን ግን አናውቅም። የእኛ ድርሻ መሆን ያለበት ሁሉንም እንደአመጣጡ መቀበልና ነገር ሁሉ ለበጎ ነው ብለን ለእግዚአብሔር መተው ነው።መጽሐፍ ቅዱስም እንዲህ ይላል “ሁሉም ነገር ለበጎ ነው”ዛሬ ሁሉም ነገር ቢጨልምብህ ለበጎ ነው ብሎ ማለፍ ተረት ብቻ አይደለም፡፡ ጨለማ በጎ ነገሮችን ይዞ ለመምጣቱ ህይወት እራሷ ታስተምረናለችና  ። 🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀                ┉┉✽‌»‌✨❣✨»‌✽‌┉┉     ✍ሴኔሳ ነበርኩ (ሴና )                  ነበርኩ😘     ▫️COMMENT💌 @Meki3 🦋🙏ከወደዱት ሼር🙏🦋       ‌‌‌‌‌‌‌  ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! ➢ ሼር  @ethioleboled 🥀 .    ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
إظهار الكل...
👍 4 1
. " ስላንቺ " [ ✍ ፀሀፊ፡ ሶፊያ አህመድ ] ╚─━━━━░★░━━━━─╝ #ክፍል_አስራአምስት (⓯) ✿❯────「✿」────❮✿ ሁለቱም እኩል ስልካቸውን ተጫኑት። ረያን አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ሲደርሰው አምሪያ ደሞ ጅማ ዩንቨርስቲ ነበር የደረሳት።አምሪያ ስልኳን አስቀምጣ ጠረንጴዛው ላይ ተኛች። " የኔ ውድ... ከተማ ነው እንጂ ሀገር እኮ አልተለያየንም! ደሞ እየመጣው አይሻለው! " እሱ እራሱ ቢያዝንም የራሱን ደብቆ እሷን ለማፅናናት ይሞክራል። አምሪያ ፊቷን እንደጣለችው ተነስታ ተጠመጠመችበት። ለጓደኞቻቸው ደውለው የት እንደረሳቸው ተጠያየቁ። ጄሪ ከረያን ጋር አዲስአበባ ዩንቨርስቲ ነው የደረሳት። ሰብሪን ደሞ ደንቢዶሎ ዩንቨርስቲ ሲደርሳት ሚኪ ወልቂጤ ተመደበ። ሁሉም ቦንብ እንደረገጡ ነገር ነበር የተበታተኑት። ወደዩንቨርስቲ ከመሄዳቸው በፊት አንድ ቀን የመሰናበቻ ፕሮግራም ለማዘጋጀት ተስማሙ። * አምሪያ ክፍሏ ቁጭ ብላ በቅርቡ ስለምትሄድበት ጅማ ዩንቨርስቲ የተለያዩ ነገሮችን እያየች ነው። በመሀል የቤታቸው በር ተንኳኳ። ከሷ ውጪ ቤት ውስጥ ማንም ስለሌለ ሄዳ ከፈተች። በሩ ጋር ግን ማንም አልነበረም።ወደቀኝና ወደግራ እያየች ሰው ብትፈልግም ምንም ማየት አልቻለችም። በሩን ዘግታ ልትገባ ስትል እግሯ ጋር አንድ ፖስታ ተመለከተች። ከማን ሊሆን እንደሚችል ግራ እየተጋባች ፖስታውን ይዛ ወደክፍሏ ገባች። ክፍሏ እንደገባች ወድያው ፖስታውን ከፍታ አየችው።ውስጡ ደብዳቤና ፎቶዎች አሉበት። ቀድማ ፎቶዎቹን አውጥታ ማየት ጀመረች። የሷና የሳሊም የልጅነት ፎቶዎች ናቸው። ፎቶዎቹን ስታይ ብዙ ትዝታዎች ወደጭንቅላቷ መጡ። ከሁሉም የማትረሳው ወደትምህርት ቤት ልትሄድ ስትል ወንዶች መንገድ ላይ ሲያስቸግሯት እሷን አስመልጦ እሱ የተደበደበላት ትዝ አላት። በዛ ምክንያት 3 ቀን ትምህርት ቤት አልገባም ነበር። ሁለተኛውን ፎቶ አንስታ አየችው። ትምህርት የጨረሱ ጊዜ የሚከበረው የወላጆች ቀን ላይ ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜ የደረጃ ተማሪ ሆና ሽልማት ስትቀበል ነበር ያነሳት። ሳታስበው ፈገግ አለች...ሁሉንም ፎቶዎች ተራ በተራ እያየች ትዝታዎቿን ታስባለች። እነዚ ፎቶዎች አብዛኛዎቹ እሷ ጋር ራሱ የሉም። እስካሁን እሱ ጋር በመኖራቸው ተገረመች። ፎቶዎቹን አይታ ስትጨርስ ደብዳቤውን ከፍታ ማንበብ ጀመረ። " አምሪ ከየት እንደምጀምርልሽ አላውቅም...አውቃለው በጣም ትልቅ ጥፋት እንዳጠፋው። ኒካህ ማሰርሽን ስሰማ የታመምኩትን ህመም እኔና አላህ ነን የምናውቀው። አንቺ ባታውቂውም በጣም አፈቅርሽ ነበር። ወደአዲስ አበባ ከመጣሽ በኋላ አድራሻሽን ለማግኘት ብዙ ጣርኩ ግን ላገኝሽ አልቻልኩም። እዛ ሆኜ በእያንዳንዷ ቀን አስብሽ ነበር። በደንብ ሰርቼ ወደአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ለመምጣትና አንቺን ለማግኘት ሁሌም እጓጓ ነበር። ግን ሁሉም ከረፈደ ሆነ። ፈርቼ ስሜቴን እንኳን ሳልነግርሽ የሌላ ሆንሽ። አምሪ አንቺ ብትሆኚ ምን ታደርጊ ነበር? የምታፈቅሪው፣ ብዙ አመት የጠበቅሽው ሰው ሌላ ቢያገባ ምን ታደርጊ ነበር? በዛ ሰአት እናንተን አጣልቼ አንቺን የራሴ ለማድረግ ፈለኩ። አውቃለው የሞኝ ስራ እንደሆነ ግን የዛኔ እሱን ማሰብ አልቻልኩም ነበር። ከእንግዲህ ሄደሻል ልመልስሽ እንደማልችል አውቃለሁ። ቢያንስ ግን ጓደኝነታችንን እንድናጣው አልፈልግም! እስከመጨረሻው ተቀይመሽኝ እንድትቀሪ አልፈልግም። የአንድ ጊዜ ጥፋቴን ሳይሆን ከዚ በፊት ስለነበረን መልካም ጊዜ ስትይ ይቅርታ አድርጊልኝ! አንቺን በማጣት የተቀጣውት ይበቃኛል ልብሽ ውስጥ ለኔ ያለሽን ቦታ በጥላቻ ቀይረሽ ድጋሚ አትቅጪኝ! እዚ የመምጣቴ ዋናው ምክንያቴ አንቺ ነበርሽ! አንቺ የሌላ ሆነሽ የምትኖሪበት ከተማ ላይ መኖር ለኔ ይከብደኛል። ወደሀገሬ ልመለስ ወስኛለው። ይቅርታዬን ከተቀበልሽኝ ከመሄዴ በፊት አንዴ እንኳን አግኚኝ። በተረፈ ለአዲሱ ህይወትሽ መልካሙን ሁሉ እመኝልሻለሁ! ሁሌም ደስተኛ ሆነሽ ኑሪልኝ! " ከአይኗ እየወረዱ ደብዳቤው ላይ ሲንጠባጠቡ የነበሩትን እንባዎች በእጇ እየጠረገች ደብዳቤውን ወርውራ እየሮጠች ከክፍሏ ወጣች። ደብዳቤውን አስቀምጦ ከሄደ ብዙ ደቂቃዎች ስለማያልፉት እዚው አከባቢ አገኘዋለው ብላ አስባ እየደወለችለት ነበር የወጣችው። በተደጋጋሚ ስልክ ብትደውልለትም አያነሳም ነበር። በድንጋጤ እግሯ ወደመራት አቅጣጫ ትሮጣለች። ከሰፈራቸው ወደታክሲ ተራ የሚወስደው መታጠፊያ አንድ ጥግ ጋር ቁጭ ብሏል። እሮጣ ሄዳ አጠገቡ ቆመች። " ስልክህን ለምን አታነሳም? " ሳሊም ቀና ብሎ ተመለከታት። ፊቱ በጣም ተለዋውጦ ነበር። እንደታመመ በደንብ ያስታውቃል። " እዚ ምን ትሰሪያለሽ? " አላት ህመሙን አይታ እንዳታውቅበት ፊቱን ወደመሬት አቀረቀረ። " ለረጅም ጊዜ እውነተኛ ጓደኛዬ ስለሆንክ አመሰግናለሁ! " አለችው ፊቷ ላይ በሙሉ ደስታ ነበር። ከልቧ ነው ያለችው። " ማድረግ የምችለው እሱን ብቻ ነው! " አላት በፀፀት ስሜት... ከተቀመጠበት ሊነሳ ሲል ተንገዳገደ አምሪያ ቶሎ ደገፈችው። " እያመመህ ነው እንዴ? " በጣም ደነገጠች። ደግፋ መልሳ አስቀመጠችው። " ደና ነኝ! ስለኔ መጨነቅ አይጠበቅብሽም..." ተመልሶ ሊነሳ ሲል መልሳ አስቀመጠችው። ወድያው ስልኳን አውጥታ መኪና ጠራች። ብዙም አልቆየም ከደቂቃዎች በኋላ የተጠራው መኪና መጣ። ወደመኪናው ከገቡ በኋላ ለሹፌሩ ቅርብ ወዳለ ሆስፒታል እንዲወስዳት ነገረችው። ሳሊም ላብ በላብ እየሆነ ነበር። ሰውነቱ በጣም ያቃጥላል። ሆስፒታል እንደደረሱ ከሹፌሩ ጋር ወደውስጥ ይዘውት ገቡ። አምሪያ ሹፌሩን ካሰናበተችው በኋላ ሳሊምን ቁጭ ብላ ትጠብቀው ጀመር። ከቤት ተጣድፋ ስለወጣች ኪሷ ውስጥ ከነበረው የተወሰነ ብር ውጪ ሌላ ስላልያዘች ረያንን ደውላ እንዲያመጣላት ጠየቀችው። ከትንሽ ደቂቃ በኋላ ዶክተሮቹ ከሳሊም ክፍል ስለወጡ አምሪያ ወደውስጥ ገባች። " ይቅርታ! እንደዚ እስከምትታመም አብሬህ ስላልነበርኩ ይቅርታ! " አለችው አጠገቡ ሄዳ ከተቀመጠች በኋላ። " ይቅርታ መጠየቅ ያለብኝ እኔ ነኝ! ይቅርታዬን እንደተቀበልሽኝ ልትነግሪኝ ነው አይደል የመጣሽው? " አላት በስስት እየተመለከታት። " የእውነት ከልቤ ይቅርታ እንዳደርግልህ ከፈለክ ትምህርትህን አታቋርጥ! እንደዛ ካደረክ እንዳልከው ጓደኝነታችንን እንመልሳለን! ግን ትምህርትህን ትተህ እንደማትመለስ ቃል ግባልኝ! " በሷ ምክንያት ህልሙን ከገደለው ፀፀቱን አትችለውም። ሳሊምም እንደማያቋርጥ ቃል ገባላት። ረያን ሆስፒታል ደርሶ ስልክ ደወለላት። ያሉበትን ክፍል ነገረችው እና እንደደረሰ ሲነግራት ከክፍሉ ወጣች። ስትወጣ በጣም እያለቀሰች ነበር። ሄዳ ረያን ላይ ተጠመጠመችበት። ረያንም ምንም ሳይጠይቃት አቅፎ አባበላት። የህክምናውን ክፍያ ከከፈሉ በኋላ ሳሊምን ይዘው ወደቤት ሄዱ። ሳሊምና ረያን ከድሮም ጀምሮ አይዋደዱም ነበር። ዛሬ ግን ሳሊም ተሸንፎ ይቅርታ ጠየቀው። ረያንም ከልቡ ይቅርታ አደረገለት። ሳሊምን ቤት ካስገቡት በኋላ አምሪ ደብሯት ስለነበር ምግብ ሊጋብዛት ይዟት ሄደ።
إظهار الكل...
👍 1 1
* ዩንቨርስቲዎች ተማሪዎቻቸውን የሚጠሩበት ጊዜ ደርሶ አምሪያም ወደጅማ ለመሄድ ተዘገጃጅታ ጨርሳለች። ዛሬ ወደ11 ሰአት ላይ ነው በረራዋ። ቀኑን ሙሉ የሚያስፈልጋትን እቃዎች ከሰብሪን ጋር ሲገዛዙ ነበር የዋሉት። በነገራችን ላይ ሰብሪን መሄድ ስላልፈለገች እዚው የግል ኮሌጅ ተመዝግባለች። ከግሩፓቸው ከአዲስ አበባ የሚወጡት አምሪያና ሚኪ ብቻ ናቸው። " እ ምንም የረሳሽው ነገር የለም አይደል? " ረያን ሻንጣዋን ይዞ እየወጣ ነው።ወደ አየር ማረፊያ የሚወስዳቸው መኪና ስለመጣ የሱንም የሷንም ቤተሰቦች ተሰናብታ ወጣች። ረያን ነው የሚያደርሳት። መኪና ውስጥ ከኋላ ቁጭ ብለው እንዳቀፋት ነድ ቦታው ጋር የደረሱት። " ከዚ በኋላ መች ነው የምንገናኘው? " ለበረራዋ የተወሰኑ ደቂቃዎች ስለቀሩት ባሏን ለመሰናበት ውስጥ ቆማለች። አንገቷን ቀና አድርጎ አይኑን እንድታየው አደረጋት " እራስሽን ጠብቂልኝ እሺ! ሁሌም ደስተኛ ሁኚልኝ! በቃ ሰአትሽ እየደረሰ ነው። ሂጂ..." " ትንሽ ደቂቃ መቆየት እፈልጋለው..." እንባ ባቀረሩ አይኖቿ ትመለከተዋለች። " ለመሳናበት እያከበድሽብኝ ነው። " ወገቧን ጭምቅ አድርጎ አቀፋት። " በቃ ሂጂ አምሪ...ናፍቆት አላስቀምጥ ሲለኝ እመጣልሻለሁ..." አላት እንባውን ደብቆ ፈገግ እያለ። በመከራ ተላቀው ተሰነባበቱ። * ጊዜው እንደጉድ ይበራል። አምሪ ወደጅማ ከሄደች ሶስት ወር አለፉ። ከባሏ ጋር በቀን በቀን ስልክ ይደዋወላሉ አንዳንዴም በ Video call እያወሩ ናፍቆታቸውን ለማስታገስ ይሞክራሉ። ዛሬም video call እያወሩ ነው " እና ባልየው ምን አዲስ ነገር አለ? " " ይኸውልሽ ዋነኛው አዲሱ ነገር..." ስልኩን ወደጎን አድርጎ ጄሪን አስገባት። ስልክ እያወራች ነበር። አምሪያን ስታያት እጇን እያወዛወዘች ሰላም አለቻት። ረያን ስልኩን ወዳራሱ ጋር መለሰው " ይኸውልሽ ቀንም ለሊትም ከሚኪ ጋር ማውራት ሆኗል ስራዋ። በዚ ሁኔታዋ ከቀጠለች ትምህርቱንም ማን እንደሚማርላት እንጃ ብቻ።.." አላት እየሳቀ። ጄሪ ስልኳ ላይ ተጥዳ የሚያወሩትንም ብዙ አልሰማችም። " ኦ..ኦ ይሄማ ትልቅ ነገር ነው...ሰርግ ልንበላ ነው በለኛ..." " በሰርግማስ የሚቀድሟቸው ሌላ የሉም ብለሽ ነው? " እነፋሩቅን ማለቱ እንደሆነ ገብቷታል። "ምንም ቢሆን ግን እኛን አይቀድሙንም! ግን እነሱስ እንዴት ናቸው? " " እነሱማ እኔን ለማስቀናት የማያደርጉት ነገር የለም። ጭቅጭቃቸውን አሁንም አልተውትም። ብቻ ግን ደና ናቸው በጣም። ባለፈው እንደነገርኩሽ ፋሩቅ ፍቅሩን ገልፆላታል። ለመጋባትም ወስነዋል! " " ወይኔ ያ ቀን ይለፈኝ? " አለች በንዴት " እንግዲ የላኩልሽን ቪድዮ እያየሽ መፅናናት ነው። ባይሆን ለሰርጋቸው አንደኛ ሚዜ ስለምትሆኚ በደንብ ተዘጋጂ..." ጄሪ ስልኳን ስትጨርስ መታ ተቀላቀለቻቸው። ብዙ ነገሮችን ሲያወሩ ከቆዩ በኋላ በቅርቡ እንደሚመጣ ነግሯት ተሰነባብተው ስልኩ ተዘጋ። * ረያን ቃል በገባው መሰረት ከ 3 ቀን በኋላ ወደጅማ...ወደፍቅሩ ፣ ወደናፍቆቱ ጋር በረረ። አምሪያ መምጣቱን ስትሰማ በጣም ነበር ደስ ያላት። ቅዳሜ ከሰአት ላይ ተገናኝተው እሁድንም አብረው ውለው ማታ ላይ ለመለያየት ተስማሙ። ረያን ወደነሱ ዩንቨርስቲ እየደረሰ እንደሆነ ደውሎ ስለነገራት ልብሷን መቀያየር ጀመረች። ለመጀመሪያ ጊዜ ታገኘው ይመስል የምትለብሰው ልብስ ከዶርሟ ልጆች ቤዛና አሲያ ጋር ሲመራርጡ ቆዩ። በመጨረሻም ውብ የሚያደርጋትን ከመረጡ በኋላ ለመውጣት ስትዘጋጅ ዶርሚተሪዋ ( የአንድ ህንፃ ተቆጣጣሪ) ከአንዲት ተማሪ ጋር የዶርማቸውን በር ከፍታ ገባች። " የዚች ልጅ ስልክ ስለተሰረቀ ሙሉ ኮሪደሩን እየፈተሽን ነው። እናም እናንተም ሎከራችሁን ክፈቱልኝ! " ብላ ትዕዛዝ ሰጠች። አምሪያ ከዚ በፊት የነሚኪ ዩንቨርስቲ አንድ ልጅ ቦርሳው ውስጥ ፈተና የያዘ ሪደር አስቀምጠውበት ምንም በማያውቀው ነገር እንደተባረረ የነገራት ትዝ አላት። ሳታውቀው ልቧ መፍራት ጀመረ። የዶርማቸው አራተኛዎ ልጅ ብሩክታዊት ስላልነበረች ተጠርታ እንድትመጣ ከተደረገ በኋላ ፍተሻ ጀመረች። ሁለቱን ሎከሮች አልፋ ሶስተኛው ውስጥ ነበር ስልኩ የተገኘው። እነአምሪያ በድንጋጤ ውስጥ ሆነው የሚፈጠረውን ከማየት ውጪ ምንም መልስ አልሰጡም ነበር። #ክፍል_አስራስድስት ( ⓰ ) ይቀጥላል... ✿❯────「✿」────❮✿
إظهار الكل...
👍 2
➖➖➖➖➖❤️➖➖➖➖➖ ጥሩ እድል ሊሆንም ላይሆንም ይችላል”   ጣፋጭ ታሪክ        በአንድ መንደር ውስጥ የሚኖር አንድ ገበሬ ነበር። ከእለታት አንድ ቀን የዚህ ገበሬ ፈረስ ይጠፋል። የመንደሩ ሰው ሁሉ ተሰብስቦ ወደ ገበሬው ቤት በመሄድ ሃዘናቸውን ይገልጹለታል።እንዲህ ሲሉ ” ፈረስህ በመጥፋቱ አዝነናል፤ እንደው ምን አይነት መጥፎ እድል ነው?” ሲሉት። ገበሬው መልሶ “መጥፎ እድል ሊሆንም ላይሆንም ይችላል” ብሎ መለሰላቸው።በበነጋታው የጠፋው ፈረስ ሌሎች ሰባት ፈረሶችን አስከትሎ መጣ። ይህንን የተመለከቱ የሰፈሩ ሰዎች ወሬውን ይሰሙና ወደ ገበሬው ቤት በመሄድ እንዲህ ይሉታል።” የሚገርም እኮ ነው፤ አንድ ፈረስ ነበረህ አሁን ስምንት ፈረሶች ሆኑልህ። እንደው ምን አይነት ጥሩ እድል ነው?” ገበሬውም ” ጥሩ እድል ሊሆንም ላይሆንም ይችላል” ሲል መለሰላቸው።ሲነጋ የገበሬው ልጅ ከስምንቱ ፈረሶች አንዱን ሰርቆ ሊጋልብ ሲሞክር ፈረሱ አሽቀንጥሮ ይጥለውና ልጁ እግሩን ይሰበራል።ወሬውም በሰፈሩ ሁሉ ተሰማ። እንደ ልማዳቸው የሰፈሩ ሰዎች ተሰባስበው ” ውይ የልጅህ መሰበር እንዴት ያሳዝናል ባክህ? እንደው ምን አይነት መጥፎ እድል ነው?” አሉት። ገበሬውም መልሶ ” መጥፎ እድል ሊሆንም ላይሆንም ይችላል” ሲል እንደልማዱ በእርጋታ መለሰላቸው። በቀጣዩ ቀን የመንደሩ የጦር ተቆጣጣሪ፤ ወጣቶችን ለጦር ሜዳ ሊመለምል ወደ መንደሩ ይዘልቃል። የሁሉንም ቤት ወጣት ወንዶች ለጦርነት ሲመለምል ከፈረስ ላይ የወደቀውን የገበሬውን ልጅ ግን እግሩ ስለተሰበረ ሳይወስዱት ቀሩ።ይሄኔ የመንደሩ ሰዎች ተሰባስበው ወደ ገበሬው በመሄድ እንዲህ አሉት “አየህ ልጅህ እግሩን በመሰበሩ ወደጦር ሜዳ ሳይወሰድ ቀረ፤ እንደው ምን አይነት ጥሩ እድል ነው?” ገበሬው ግን አሁንም እንዲህ አላቸው ” ጥሩ እድል ሊሆንም ላይሆንም ይችላል” እናም ..................................................... ብዙን ጊዜ በኑሮዋችን ውስጥ አንድ ነገር ሲከሰት በችኮላ “መጥፎ” ወይም “ጥሩ” እድል በማለት እንፈርጃለን። መልካም ያልነው ነገር መጥፎ ነገር ይዞ ሲመጣ፤ መጥፎ ያልነው ነገር ደግሞ መልካም ነገር ይዞ ብቅ ሲል፤ ዳኝነታችን መሰረት የሌለው እንደሆነ እንረዳለን። ወደ ኋላ መለስ ብለን የመጣንበትን ብንቃኝ፤ በእርግጠኝነት በአንድ ወቅት መጥፎ እድል ናቸው ብለን የፈረጅናቸው በኋላ ላይ ግን መልካም ነገር ይዘውልን የመጡ የህይወት አጋጣሚዎችን እናገኛለን። እኛ ግን ቀድመን “መጥፎ” እና “ጥሩ” እድል እያልን ነገሮችን ስንከፋፍል፤ አይምሮዋችን አስቀድሞ ነገሮችን ስለሚዳኝ ጭንቀት በጊዜው ከሚሆነው ነገር ጋር እንዳንስማማ ያደርገናል። የገበሬው አመለካከት ግን እጅግ የሚደንቅ ነው። የሚገጥሙት ነገሮች ምን ይዘው እንደሚመጡ ስለማያውቅ “መልካም” እና “መጥፎ” እድል እያለ እራሱን ላልተጠበቀ ሃዘን አያዘጋጅም።የፈረሱ መጥፋት መጥፎ እድል ነው ብሎ ለማለት አልደፈረም። ምክንያቱም የሆነው ነገር ምን ይዞ እንደሚመጣ ስላላወቀ። ፈረሱ ሌሎች ፈረሶችን ይዞ ሲመጣም “መልካም እድል” ብሎ ሊደመድም አልወደደም፤ እንደሰወኛ ብናስብ እነዛ ፈረሶች ባይኖሩ ልጁ አይሰበርም ነበር። የልጁን መሰበርም እንደ መጥፎ እድል ሊወስደው አልፈለገም፤ እንደሰወኛ ግን ልጁ እግሩ ባይሰበር ኖሮ፤ እንደሌሎቹ የሰፈር ወጣቶች ከአባቱ ተነጥሎ ወደ ጦር ሜዳ በተወሰደ ነበር። እንዲህ አይነት አመለካከት ከአልታሰበ የስሜት መናወጥ ያድናል፤ እርግጥ ነው ቀላል አይደለም። ነገር ግን በህይወት መንገድ ላይ ስንጓዝ የሚገጥሙን ሁኔታዎች ጊዜ ብቻ የሚፈታው ሚስጥር በውስጣቸው አለ። ነገሮች ሁሉ ወደ በጎ እየተቀየሩልን እግዚአብሔርን ባማረርንበት አፋችን እንድናመሰግነው ያደረገን አጋጣሚ በሁላችንም ህይወት ውስጥ አለ። በአንጻሩ በስንት ልመና ያገኘነውን ነገር ምነው ባትሰጠኝ ኖሮ ብለን ያማረርንበትም ጊዜ ይኖራል። በዚህ አለም ላይ ያለምክንያት የሚሆን ምንም ነገር የለም። ምናልባት አሁን እያለፍነበት ያለው ፈተና እና የኑሮ ጦርነት እድላችንንን እንድንማረር እያረገን ይሆናል፤ ነገ የሚመጣውን ግን አናውቅም። የእኛ ድርሻ መሆን ያለበት ሁሉንም እንደአመጣጡ መቀበልና ነገር ሁሉ ለበጎ ነው ብለን ለእግዚአብሔር መተው ነው።መጽሐፍ ቅዱስም እንዲህ ይላል “ሁሉም ነገር ለበጎ ነው”ዛሬ ሁሉም ነገር ቢጨልምብህ ለበጎ ነው ብሎ ማለፍ ተረት ብቻ አይደለም፡፡ ጨለማ በጎ ነገሮችን ይዞ ለመምጣቱ ህይወት እራሷ ታስተምረናለችና  ። 🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀                ┉┉✽‌»‌✨❣✨»‌✽‌┉┉     ✍ሴኔሳ ነበርኩ (ሴና )                  ነበርኩ😘     ▫️COMMENT💌 @SeNesSAS 🦋🙏ከወደዱት ሼር🙏🦋       ‌‌‌‌‌‌‌  ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! ➢ ሼር  @sweet_love3212 🥀 . @sweet_love3212 🥀    ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀  💔 @sweet_love3212 💔 💔  @sweet_love3212 💔
إظهار الكل...
* የኢንትራንስ ፈተናቸው እስከሚደርስ ድረስ ቀን በቀን ላይብረሪ ወይም የአንድ ሰው ቤት ሁሉም እየተሰበሰቡ ለማጥናት ወስነዋል። " በለው ችከላውን ወጥረሻል..." አላት በእጁ የያዘውን አንድ ደብተር ጠረንጴዛው ላይ እያስቀመጠ...ጄሪ ቀና ብላ አየችው። ሚኪ ነው። " ምን ላድርግ እነሱ ሲቆይብኝኮ የተወሰነ ጥያቄ እየሰራው ልጠብቃቸው ብዬ ነው። " " ምነው እነሱ አልሽ እኛ አንጠበቅም እንዴ? " " የሚያጠኑትን ነው የሚመለከተው..." ከነሱ ጋር ጊዜ ለማሳለፍ እንጂ ለማጥናት እንደማይመጣ እራሱም ያውቀዋል። ሰፈራቸው ያለ የህዝብ ላይብረሪ አንድ ጥግ ጋር ነበር ቁጭ ያሉት። አንድ በአንድ እየቆዩም ቢሆን ሁሉም መጥተዋል። ሁሉም የራሳቸውን እያጠኑ ነው። ሚኪና ፋሩቅ ስልክ እየነካኩ ሲያስቸግሩ በረያን ስለተቀሙ ሳይወዱ በግዳቸው የተወሰነ ለማጥናት ሲታገሉ ነበር።በመሀል የከበዳቸውን ደሞ ለሚያውቀው እየጠየቁ እስከምሳ ሰአት ድረስ እዛው ቆዩ። ምሳ ዛሬ ፋሩቅ ቤት ነበር ተረኛ። ያሉበት ቦታ ይበልጥ ለሱ ቤት ስለሚቀርብ ነው እዛ ለመብላት የወሰኑት።ፋሩቅ ጓደኞቹ ቤት እንደሚመጡ ስለነገራቸው የቤት ሰራተኛቸው ቀድማ አዘገጃጅታ ነበር የጠበቀቻቸው። ወንዶቹ ሲበሉ እየተሻሙ ስለሆነ ሴቶቹ የራሳቸውን ይዘው ተቀመጡ። " እ አልጨረሳችሁም እንዴ እስካሁን? " ፋሩቅ የታጠበውን እጁን ላማድረቅ እያራገፈ ወደሶፋው ጋር ሄደ። ምግቡ ከቀረበላቸው 5 ደቂቃ እንኳን አልሞላም እነሱ ግን ጨርሰው ቁጭ ብለው ነበር። ሴቶቹ እስከሚጨርሱ ድረስ ጠበቋቸው። እነሱም ወንዶቹን ለማናደድ ይመስል በጣም እየተሟዘዙ ነበር የበሉት። እንደምንም በልተው ከጨረሱ በኋላ ወደላይብረሪው ስለሚመለሱ ረያን የሱንና የአምሪያን እቃ መሰብሰብ ጀመረ። " ኧረ ደስ አይልም...እዛው እንመለስ ልትል ባልሆነ? " ለፋሩቅ ላይብረሪ መቀመጥ ማለት እንደመሞት ነው። " ኧረ አዎ ቢያንስ ዛሬን ብቻ እንረፍ..." ሚኪም የሀሳቡ ደጋፊ ነው። " እረፍቱ አሪፍ ሀሳብ ነው ግን እዚ ሆነን ታድያ ምን እናደርጋለን? " አለች ሰብሪን እሷም የደከማት ትመስላለች። " ለምን ጌም አንጫወትም? " ፋሩቅ እንደምንም አሳምኗቸው Truth or Dare ለመጫወት ተሰበሰቡ። የመጀመሪያው ዙር የደረሰው ለረያን ነበር። አምሪያን አዝሏት ክፍሉን እንዲዞር አደረጉት። ለነሱ አሪፍ ትዕዛዝ ነበር። ሁለተኛው ዙር ሰብሪን ጋር ደረሰ። " እ Truth or Dare? " ፋሩቅ ሊያዛት የቸኮለ ይመስላል። " Truth " ከትእዛዝ ይሻለኛል ብላ ነው። " ብዙ ጊዜ መናገር እየፈለግሽ ያልተናገርሽው ወይም የሆነ ሰው ቢያውቅልኝ ብለሽ የምትመኚው ነገር አለ? " ረያን ነበር የጠየቃት። ትንሽ ካሰበች በኋላ ቀና ብላ ፋሩቅን ተመለከተችውና መልሳ አቀረቀረች። " ሁሌም አብሮኝ የሆነ..በደስታዬም በሀዘኔም ጊዜ ያልተለየኝ...ሰው በሚያስፈልገኝም ሰአት ከሁሉም ቀድሞ እኔ ጋር የሚገኝ...እውነተኛ የልብ ወዳጄ የሆነ...ምን ያህል እንደምወደው ቢያውቅ ደስ ይለኛል " አለች። ሁሉም ወደፋሩቅ እያዩ አጨበጨቡላት። " ሁለተኛ ሰርግ ልንበላ ነው መሰለኝ..." አለች ጄሪ። አላወሩትም እንጂ ሁለቱም ጋር የፍቅር ስሜት እንዳለ ሁሉም ያውቁታል። የፋሩቅ እናት ስትመጣባቸው ጨዋታውን አቋርጠው ተመልሰው ወደላይብረሪያቸው ሄዱ። * የውጥረቱ ሁለት ሳምንት አልቆ የኢንትራንስ ፈተናቸውን ተፈትነው ጨረሱ። ውጤቱ ከ3 ሳምንት በኋላ ይፋ ተደረገ። ረያን ከግሩፑ ትልቁን ውጤት ይዞ ጄሪ ደሞ በትንሽ ነጥብ ልዩነት ሁለተኛውን ቦታ ይዛ ፈተናውን አለፉ። የአምሪያ ውጤትም አሪፍ ነበር። ሰብሪንና ሚኪ እንደፈሩት ሳይሆን ቀርቶ አለፉ። ፋሩቅ ብቻ ነበር ውጤት ያልመጣለት። እሱ ቀድሞውኑ ከ12 በኋላ የመቀጠል ሀሳብ ስላልነበረው የአባቱ ድርጅት ውስጥ መስራት ጀምሮ ነበር። አለማለፉ ምንም አላስከፋውም።የአብዛኛዎቹ ልፋት ፍሬ ስላገኘ ሁሌም እንደሚያደርጉት ተሰብስበው ደስታቸውን አከበሩ። ቀጣዩ ትልቁ ጭንቀት የዩንቨርስቲ ምደባ ነው። በተለይ ለአምሪያና ለረያን ከባድ ነበር። አንድ ቦታ ካልደረሳቸው የሚቀጥሉትን 4 ወይም ከዛ በላይ አመታትን ተለያይተው ማሳለፋቸው ነው። ይሄንን ሲያስቡት ከአሁኑ ሀሳብ ይዟቸዋል። ብዙም አልቆየም ከተጨማሪ የ2 ሳምንት እረፍት በኋላ የዩንቨርስቲ ምደባው ይፋ እንደሆነ ሰሙ። አምሪያና ረያን ጉዳቸውን ለማየት አብረው ተቀምጠዋል። በእጃቸው የያዙት ስልክ ላይ አፍጠው ለደቂቃዎች ቆዩ። በመጨረሻም የምደባ ቦታቸውን የሚገልፅላቸውን ስልክ እኩል ተጫኑት። ቁርጣቸውን ለማወቅ... #ክፍል_አስራአምስት (⓯) ይቀጥላል... ✿❯────「✿」────❮✿
إظهار الكل...
👍 3 1