cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

አቡ መርየም አዳማ

هدفنا الذب عن السنة..................... ትክክለኛው እስላማዊ አስተምህሮ ከቁርአንና ከሐዲስ ከደጋግ ቀደምቶች አረዳድ ከታማኝ ዑለሞች የሚሰራጭበት ቻናል ነው። በተጨማሪም ተውሂድንና ሽርክን እንዲሁም ሱናንና ቢድአን እንዲሁም የቢድአ ሰዎችን ለሰዎች በፁሁፍና በሙሀደራ መልክ ግልፅ ማድረግ https://telegram.me/abumerymadama

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
746
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+17 أيام
+1430 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱህ የዙልሂጃ ወር በማግባት እና በአረፋ ምክኒያት ተቋርጦ የነበረው የኢብኑ ተይሚያ መስጂድ ደርስ ከነገ ከሰኞ ሰኔ 17 ጀምሮ የሚቀጥል ይሆናል https://t.me/abuabdurahmen
إظهار الكل...
📝Abu abdurahman«አብዱልቃዲር ኢብኑ ሐሰን»

هدفنا الذب عن السنة ይህ ቻናል የአቡ አብዱረህማን አብዱል ቃድር ሀሰን ደርሶች ሙሓደራዎች እና ጠቃሚ የሆኑ ፈዋኢዶች የሚለቀቁበት ቻናል ነው ይቀላቀሉ ➘➘➘➘➘➘➘➘

https://t.me/abuabdurahmen

https://t.me/abuabdurahmen

https://t.me/abuabdurahmen

ከአሉ ተባለ ወሬ ተከልክለናልና እንጠንቀቅ!! ——— አሎባልታ ወሬ ብዙዎችን በተለያየ መንገድ አክስሯል!! አሉ ተባለ ወሬ በማህበረሰቡ ላይ ጉዳቱና መዘዙ የከፋ ስለሆነ ሸሪዓችን አጥብቆ ከልክሏል። ከወርራድ አስሰቀፊይ ተይዞ እንዲህ አለ:- ሙዓዊየህ ወደ ሙጊረህ ቢን ሹዕበህ እንዲህ በማለት ፃፈ፣ ከአላህ መልክተኛ ﷺ ከሰማሀው ምክር የሆነ ነገር ወደኔ ፃፍልኝ አለው፣ ሹዕበህ ኢብኑ ሙጊረህም እኔ ከመልክተኛው ﷺ የሚከተለውን ሲሉ ሰምቻለሁ በማለት ፃፈለት:- “አላህ ሶስት ነገሮችን ጠልቶላችኋል፣ አሉ ተባለን፣ ገንዘብን ማባከንና ጥያቄ ማብዛትን።” [ቡኻሪና ሙስሊም የዘገቡት ሶሂህ ሀዲስ ነው።] በዚህ አሉ ተባለ ወሬ ስንቱ ሱሰኛ ሆነ?! ስንቱ ከቂርኣት (ከደርስ) ርቆ በዚህ ተጠመደ?! ያውም የበለጠ ከማበላሸት ውጭ ሊያስተካክለው በማይችለው ነገር ላይ ገብቶ ስንቱ ተጠመደ?! ስንቱ ነው በእንዲህ ያሉ ወሬዎች ተጠምዶ እውቀት ፈላጊ ምስኪኖችን ከደርስ ያቋረጠው?! ስንቱ ነው በዚህ መልኩ ለቢድዐህ ባለቤቶችና ለአስመሳዮች በር የከፈተው?! ስንቱ ነው በዚህ ተግባር ተዘፍቆ ከድሮ ጀምሮ ወደ ቡድንተኝነት (ተሀዙብ) ያመራው?! እንንቃ!! ጎበዝ ጊዜያችን አናባክን!! ወዳጅነትን አሻክረው በጀመዓ ላይ ክፍተት እንዲፈጠር ሰበብ ከሚሆኑ ተግባሮች እንራቅ!! አሉ ተባለ ወሬን አጥብቀን ተጠይፈን እንራቅ!! ታላቁ ፈቂህ ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሷሊህ አል-ዑሰይሚን (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:- “በአሉ ተባለ ወሬ፣ ጥያቄን በማብዛትና ጊዜን በማባከን መወጠር (ቢዚ busy) መሆን በሰዎች መካከል ከተንሰራፋ በእውነቱ በሽታ ነው!! አላህን ጤነኛነትን እንጠይቀዋለ!!። ይህ ተግባር እንደ ትልቅ አንገብጋቢ ጉዳይ ይሆንበታል፣ በል እንዲያውም አንዳንዴ (በዚህ ተግባር ያልገጠመውን) ጥላትነት ለማይገባው ሁሉ ጥላትነትን ይጠቀማል፣ አለያም ደግሞ (በዚህ ተግባር ስለ ገጠመው ብቻ) ወዳጅነት የማይገባውን ወዳጅ ሊያደርግ ይችላል። ወደዚህ ደረጃ የሚደርሰው፣ ለዚህ እውቀትን ከመፈለግ አርቆ ውጥረት ውስጥ ለከተተው (ለአሉ ባልታ ወሬ) ከሰጠው ትኩረት የተነሳ ነው። እንደ ማስረጃ የሚያቀርበው ደግሞ ሀቅን መርዳት ነው የሚል ነው። እውነታው ግን እንደዛ አይደለም!። ይልቅ እውነታው ነፍስንም ሆነ ሰዎችን በማይመለከታቸው ነገር ውጥረት ውስጥ መክተት ነው!!። የሆነ ወሬ ሳትፈልገው መምጣቱ ግን ውጥረት ውስጥ ሊከትህ አይችልም፣ እንደ ወሬ ማንኛውም ሰው ዘንድ ሳይፈልገውና ለወሬው ቦታ ሰጥቶ ሳይዘጋጅለት ሊመጣው ይችላል ነገር ግን ቦታ አይሰጠውም፣ በሱ ውጥረት ውስጥ አይገባም!!። ትልቅ ትኩረት የሚሰጠውም ጉዳዩ አይሆንም!! ምክንያቱም እውቀት ከመፈለግ ያዘናገዋል፣ ነገሮችንም ያበላሽበታል፣ በማህበረሰቡም ውስጥ የቡድንተኝነትን በር ይከፍታል፣ በዚህ ሰበብም ኡመቱ ለመከፋፈል ይበቃል።” [መጅሙዕ አል-ፈታዋ 26/127] ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሷሊህ አል-ዑሰይሚን (ረሂመሁላህ) በድጋሚ ተፍሲሩ ጁዝእ ዐማ ገፅ 197 ላይ እንዲህ አሉ:- “በእኛ ላይ ግዴታ የሚሆነው ፊትናዎችን ግልፅ የወጡትንም ይሁን በድብቅ የሚሰራጩትን መጠንቀቅ ነው!!፣ ሰዎችንም ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ ከሚያነሳሱ ነገሮች ሁሉ መራቅ ይጠበቅብናል፣ ሁሌም መረጋጋትን መያዝ ይጠበቅብናል፣ ከአሉ ተባለ ወሬ እና ጥያቄን ከማብዛት መራቅ ግዴታ ይሆንብናል፣ ይህ ነቢዩ ﷺ ከከለከሉት ተግባርም ነው። ስንት (በአሉ ተባለ ወሬ የምትሰራጭ) አንዲት ቃል የሰላ ሰይፍ የማይሰራውን ሰርታለች?!፣ በእኛ ላይ ግዴታ የሚሆነው የሚግባባና የሚዋደድ ማህበረሰብ እንዲሆን ከፊትና እና ፊትናን ከሚቀሰቅስ ነገር መራቅ ነው!!።” ✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa) የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa
إظهار الكل...
[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

እራስህን ሁል ጊዜ ለቁርኣንና ለሀዲስ ተጎታች አድርግ! በአንድ ነገር ላይ ከቁርኣንና ከሀዲስ ማስረጃ ሳታገኝ አቋም አትያዝ! ሁሌም ለሰዎች መልካምን ተመኝ! ለሀቅ እንጂ ለሰዎች ወጋኝ አትሁን

ሰለፊዮች ፈተናን ከመካከላቸው እንዴት ሊያርቁ ይችላሉ https://t.me/abuabdurahmen
إظهار الكل...
4_6034860862596977459-mc.mp36.87 KB
ሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ) እንዲህ አሉ:- 🔹“የዚል ሒጀህ ቀናቶች ልክ እንደ መብረቅ በፍጥነት አለፉ፣ አያሙ ተሽሪቅም ተከተለቻትና ልክ እንደ ዓይን እርግብግብታ የተቆጠሩ ደቂቃዎችን በሚመስሉ መልኩ ፈጥነው አለፉ። ልክ እንደዚሁ ነው እድሜያችን በፍጥነት የሚያበቃው፣ ሞት ድንገት ይመጣናል፣ ልክ ህይወትህ በፍጥነት ከማለፏ የተነሳ ጥፍጥናዋንና ፍጥነቷን ሁሉ እንደ ቅዠት እስክትመለከት ድረስ ይሁንብሃል፣ እንደ ዳመና በፍጥነት ታልፋለች። ብልህ የሆነ ሰው ጊዜውን አላህን በመታዘዝ፣ ወደ አላህ በሚያቃርቡ ነገሮች፣ የአላህን ፀጋ በማስታወስና እርሱንም በማመስገን የተጠቀመው ሰው ነው። አምላካችን አላህ እንዲህ ብሏልና:- وَمَا بِكُم مِّن نِّعْمَةٍ فَمِنَ اللَّهِ «ማንኛውም በእናንተ ላይ ያለው ፀጋ ከአላህ ነው፡፡» አን-ነህል 53 ከፀጋዎች ሁሉ ትልቁ ፀጋ የተውሒድና የሱንና ፀጋ ነው!! በዚህ ላይ እስከ እለተ ሞት ድረስ መፅናት ነው!! በእርግጥም በሶሂህ አል-ቡኻሪይ ከዐብደላህ ኢብኑ ዐባስ - ረዲየላሁ ዐንሁ - መርፉዕ የሆነ እንዲህ የሚል ሀዲስ ተዘግቧል:- “በብዙ ሰዎች ላይ ስውር የሆኑባቸው አለያም ሰዎች የዘነጓቸው ሁለት ፀጋዎች አሉ: እነሱም ጤናማነትና ጊዜ ናቸው።” ኢማሙ አህመድ - ረሂመሁላህ - እንዲህ ብለዋል:- “በእስልምና እና በሱና ላይ የሞተ ሰው መልካም በተባለ ነገር ሁሉ ላይ ሆኖ ነው የሞተው።” [አስ-ሰይር] : የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa
إظهار الكل...
[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

እራስህን ሁል ጊዜ ለቁርኣንና ለሀዲስ ተጎታች አድርግ! በአንድ ነገር ላይ ከቁርኣንና ከሀዲስ ማስረጃ ሳታገኝ አቋም አትያዝ! ሁሌም ለሰዎች መልካምን ተመኝ! ለሀቅ እንጂ ለሰዎች ወጋኝ አትሁን

💥 #خطبة_الجمعة 💥 📌بعنوان: دار أهل النعيم لفضيلة الشيخ العلامة: محمد بن صالح العثيمين رحمه الله تعالى ✅[ https://t.me/salafibooks/3909 ]✅
إظهار الكل...
دار اهل النعيم .m4a23.95 MB
Photo unavailableShow in Telegram
أفضل_ #اللحم 🍖 ▪️قال الإمام ابن القيم - رحمه الله تعالى - : لحم العنق جيد لذيذ سريع الهضم خفيف، و لحم الذراع أخف اللحم و ألذه و ألطفه وأبعده من الأذى و أسرع إنهضاماً . ▪️و قال - رحمه الله - : و أفضل [ اللحم ] عَائِذُهُ بالعظم و الأيمن أخف و أجود من الأيسر و المقدم أفضل من المؤخر، و كان أحب الشاة إلى رسول الله صلى الله عليه و سلم مقدمها و كل ما علا منه سوى الرأس كان أخف و أجود مما سفل . 📚 زاد المعاد ٤ / ٣٤٢ . . ▪️وقال - رحمه الله - : كلوا اللحم فإنه يصفي اللون، و يخمص البطن ، و يحسن الخلق . 📚 الطب النبوي صـ ٣٤٠ . . ▪️و قال - رحمه الله - : أكل اللحم يزيد سبعين قوة ، اللحم يزيد في البصر . 📚الطب النبوي صـ ٤٣٠ https://t.me/abuabdurahmen
إظهار الكل...
🔷 የነብዩላሂ ኢብራሂም ታሪክ ክፍል ሰባትና የመጨረሻው ነብዩላሂ ኢስማኢል ከአደን ሲመለሱ የመጣ ሰው ነበር ወይ ብለው ጠየቅዋት ። አው ብላ የሆነውን ነገረቻቸው ። ምን አለሽ አሉዋት ባለቤትሽ ሲመጣ የቤትህን መቃን አጥብቀው ጥሩ መቃን ነው በይው ብሎኛል አለችው ። እሳቸውም እሱ አባቴ ነው መቃኗ አንቺ ነሽ በደንብ ያዛት ማለቱ ነው አሉዋት ።    ነብዩላሂ ኢብራሂም ለሶስተኛ ጊዜ ቤተሰባቸውን ለማየት ወደ መካ መጡ ። ነብዩላሂ ኢስማኢል ቀስት እየሰሩ አገኟቸው ። ሁለቱም ተያዩ አባት በልጁ ላይ ልጅም በአባቱ ላይ እንደሚያደርገው ተቃቅፈው ተሳሳሙ ። ነብዩላሂ ኢብራሂም ካዕባን ከልጃቸው እስማኢል ጋር ሆነው መሰረቱን ከፍ አድርገው እንዲገነቡ አላህ ያዘዛቸው መሆኑን ነገሯቸው ። ነብዩላሂ ኢስማኢልም በጣም ተደሰቱ ። ካዕባንም መገንባት ጀመሩ ። ይህን ክስተትና ከግንባታው ጋር የተገናኙ ሁለቱም ያደረጓቸው ዱዓኦችን አላህ በላሚቷ ምእራፍ ከ25 – 30ኛው አንቀፅ ላይ እንዲህ ብሎ ይነግረናል : – وَإِذْ جَعَلْنَا الْبَيْتَ مَثَابَةً لِّلنَّاسِ وَأَمْنًا وَاتَّخِذُوا مِن مَّقَامِ إِبْرَاهِيمَ مُصَلًّى ۖ وَعَهِدْنَا إِلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ أَن طَهِّرَا بَيْتِيَ لِلطَّائِفِينَ وَالْعَاكِفِينَ وَالرُّكَّعِ السُّجُودِ ቤቱንም ለሰዎች መመለሻና ጸጥተኛ ባደረግን ጊዜ (አስታውስ) ፡፡ ከኢብራሂምም መቆሚያ መስገጃን አድርጉ ፡፡ ወደ ኢብራሂምና ወደ ኢስማዒልም ቤቴን ለዘዋሪዎቹና ለተቀማጮቹም ለአጎንባሾች ሰጋጆቹም አጥሩ ስንል ቃል ኪዳን ያዝን ፡፡ وَإِذْ قَالَ إِبْرَاهِيمُ رَبِّ اجْعَلْ هَٰذَا بَلَدًا آمِنًا وَارْزُقْ أَهْلَهُ مِنَ الثَّمَرَاتِ مَنْ آمَنَ مِنْهُم بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ ۖ قَالَ وَمَن كَفَرَ فَأُمَتِّعُهُ قَلِيلًا ثُمَّ أَضْطَرُّهُ إِلَىٰ عَذَابِ النَّارِ ۖ وَبِئْسَ الْمَصِيرُ ኢብራሂም ባለ ጊዜ (አስታውስ) ፡፡ ጌታዬ ሆይ! ይህንን ጸጥተኛ አገር አድርግ፡፡ ቤተሰቦቹንም ከነሱ በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነውን ሰው ከፍሬዎች ስጠው ፡፡ (አላህም) የካደውንም ሰው፤ (እሰጠዋለሁ) ፡፡ ጥቂትም እጠቅመዋለሁ፤ ከዚያም ወደ እሳት ቅጣት አስጠጋዋለሁ፤ ምን ትከፋም መመለሻ! (አለ) ፡፡ وَإِذْ يَرْفَعُ إِبْرَاهِيمُ الْقَوَاعِدَ مِنَ الْبَيْتِ وَإِسْمَاعِيلُ رَبَّنَا تَقَبَّلْ مِنَّا ۖ إِنَّكَ أَنتَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ ኢብራሂምና ኢስማኢልም «ጌታችን ሆይ! ከእኛ ተቀበል፡፡ አንተ ሰሚውና ዐዋቂው አንተ ነህና» የሚሉ ሲኾኑ ከቤቱ መሠረቶቹን ከፍ ባደረጉ ጊዜ (አስታውስ) ፡፡ رَبَّنَا وَاجْعَلْنَا مُسْلِمَيْنِ لَكَ وَمِن ذُرِّيَّتِنَا أُمَّةً مُّسْلِمَةً لَّكَ وَأَرِنَا مَنَاسِكَنَا وَتُبْ عَلَيْنَا ۖ إِنَّكَ أَنتَ التَّوَّابُ الرَّحِيمُ «ጌታችን ሆይ! ላነተ ታዛዦችም አድርገን ፡፡ ከዘሮቻችንም ላንተ ታዛዦች ሕዝቦችን (አድርግ) ፡፡ ሕግጋታችንንም አሳየን፤ (አሳውቀን) ፡፡ በኛም ላይ ተመለስን፤ አንተ ጸጸትን ተቀባዩ ሩኅሩኅ አንተ ብቻ ነህና ፡፡» رَبَّنَا وَابْعَثْ فِيهِمْ رَسُولًا مِّنْهُمْ يَتْلُو عَلَيْهِمْ آيَاتِكَ وَيُعَلِّمُهُمُ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَيُزَكِّيهِمْ ۚ إِنَّكَ أَنتَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ «ጌታችን ሆይ! በውስጣቸውም ከነሱው የኾነን መልክተኛ በነርሱ ላይ አንቀጾችህን የሚያነብላቸውን መጽሐፍንና ጥበብንም የሚያስተምራቸውን (ከክህደት) የሚያጠራቸውንም ላክ፤ አንተ አሸናፊው ጥበበኛው አንተ ብቻ ነህና» (የሚሉም ሲኾኑ) ፡፡ وَمَن يَرْغَبُ عَن مِّلَّةِ إِبْرَاهِيمَ إِلَّا مَن سَفِهَ نَفْسَهُ ۚ وَلَقَدِ اصْطَفَيْنَاهُ فِي الدُّنْيَا ۖ وَإِنَّهُ فِي الْآخِرَةِ لَمِنَ الصَّالِحِينَ ከኢብራሂምም ሕግጋት ነፍሱን ያቄለ ሰው ካልኾነ በስተቀር የሚያፈገፍግ ማነው? (የለም)፤ በቅርቢቱም ዓለም በእርግጥ መረጥነው ፡፡ በመጨረሻይቱም ዓለም እርሱ ከመልካሞቹ ነው ፡፡ አላህ ለነብዩላሂ ኢብራሂም የካዕባን ቦታ አመላክቷቸው ከገቡ በኋላ ካዕባን ገንብተው ጨረሱ ። አላህም ለሐጅ ጥሪ እንዲያደርጉ አዘዛቸው ። እሳቸውም ጌታዬ ሆይ እንዴት አሰማለሁ አሉ ። አላህ አንተ ተጣራ እኔ አሰማለሁ አላቸው ። ተጣሩም ። አላህ ጥሪው እንዲሰሙ ካደረጋቸው ነፍሶች ውስጥ በዛን ጊዜ የነበሩና የቻሉ እንዲመጡ አደረጋቸው ። ነብዩላሂ ኢብራሂምም የመጡትን የሐጅን ስርኣት አስተማሯቸው ። እነዚያ ስርኣቶች ናቸው ሐጅ ላይ የሚከናወኑት ። ይህ ክስተት በሐጅ ምእራፍ ላይ በሰፊው ተብራርቷል ። ከዛውስጥ 26ኛውና 27ኛውን አንቀፅ ቀጥሎ እንመልከት : – وَإِذْ بَوَّأْنَا لِإِبْرَاهِيمَ مَكَانَ الْبَيْتِ أَن لَّا تُشْرِكْ بِي شَيْئًا وَطَهِّرْ بَيْتِيَ لِلطَّائِفِينَ وَالْقَائِمِينَ وَالرُّكَّعِ السُّجُودِ ለኢብራሂምም የቤቱን (የካዕባን) ስፍራ መመለሻ ባደረግንለት ጊዜ «በእኔ ምንንም አታጋራ፣ ቤቴንም ለሚዞሩትና ለሚቆሙበት ለሚያጎነብሱትና በግንባራቸውም ለሚደፉት ንጹሕ አድርግላቸው» (ባልነው ጊዜ አስታውስ) ፡፡ وَأَذِّن فِي النَّاسِ بِالْحَجِّ يَأْتُوكَ رِجَالًا وَعَلَىٰ كُلِّ ضَامِرٍ يَأْتِينَ مِن كُلِّ فَجٍّ عَمِيقٍ (አልነውም) ፡- በሰዎችም ውስጥ በሐጅ ትዕዛዝ ጥራ ፡፡ እግረኞች ከየሩቅ መንገድ በሚመጡ ከሲታ ግመሎችም ሁሉ ላይ ሆነው ይመጡሃልና ፡፡ ከዚህ በኋላ ነብዩላሂ ኢብራሂም መካ ላይ ተረጋግተው መኖር ጀመሩ ። የኢስሐቅን ልጅ ነብዩላሂ የዕቆብን ካዩ በኋላ ወደ አኼራ ሄዱ ። የነብዩላሂ ኢብራሂም አጭር የህይወት ታሪክ በዚህ ተፈፀመ ። ክፍል አንድን ለማግኘት የሚከተለውን ሊንክ ይጫኑ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/bahruteka/5019 ክፍል ሁለት 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/bahruteka/5022 ክፍል ሶስት 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/bahruteka/5026 ክፍል አራት 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/bahruteka/5033 ክፍል አምስት 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/bahruteka/5034 ክፍል ስድስትን 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/bahruteka/5037 http://t.me/bahruteka
إظهار الكل...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

👉 የነብዩላሂ ኢብራሂም ታሪክ ክፍል አንድ የነብዩላሂ ኢብራሂም ታሪክ ቁርኣን ላይ ቱክረት ከተሰጣቸው የነብያት ታሪክ ውስጥ በግንባር ቀደምትነት ይመደባል ። ታሪካቸው ቁርኣን ውስጥ በ17 ምእራፍ ወደ 69 ጊዜ ተጠቅሷል ። ይህ የሚያሳየው ታሪካቸው ምን ያክል አስፈላጊና ቁም ነገር አዘል መሆኑ ነው ። ነብዩላሂ ኢብራሂም ዒራቅ ውስጥ ባቢል በሚባል ቦታ በጣኦት አምላኪ ማህበረሰብ ውስጥ ተወለዱ ። ከህብረተሰቡ ውስጥ ኮከብ የሚያመልክ ፣ ጨረቃ የሚያመልክና ፀሀይ የሚያመልክ እንዲሁም ከእንጨት የተሰራ ጣኦት የሚያመልክ ነበር ። አባታቸው ኣዘር ከእንጨት ጣኦት እየሰራ ይሸጥ ነበር ። እሳቸው በልጅነታቸው እርሻ ይሰሩ ነበር ። አባታቸው ጣኦት እያዞሩ እንዲሸጡላቸው ሲያዙዋቸው ተቀብለው መሬት ለመሬት እየጎተቱ የማይጠቅምና የማይጎዳ የሚገዛ እያሉ ያዞሩ ነበር ። በዚህም ምክንያት ማንም የሚገዛ ስለማያገኙ ይዘውት ይመለሳሉ ። እድሜያቸው 13 አመት ሲሞላቸው ፈጣሪዬ ማን ነው ብለው ማሰብ ጀመሩ ። ቤተሰቦቻቸውና ማህበረሰቡ በሚያመልኩት ነገር ደስተኛ አልነበሩም ። ለብቻቸው ሲሆኑ ማን ነው የፈጠረኝ እያሉ ይብሰለሰላሉ ። በዚህ ስሜት ውስጥ ሆነው ከቤት ወጥተው ወደ ሰማይ በሚያዩበት ጊዜ የተከሰተውን አላህ ሲነግረን በአል አንዓም ምእራፍ ከ75 – 79 ድረስ እንዲህ ይለናል : – وَكَذَٰلِكَ نُرِي إِبْرَاهِيمَ مَلَكُوتَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَلِيَكُونَ مِنَ الْمُوقِنِينَ እንደዚሁም ኢብራሂምን (እንዲያውቅና) ከአረጋጋጮቹም ይኾን ዘንድ የሰማያትንና የምድርን መለኮት አሳየነው ፡፡ فَلَمَّا جَنَّ عَلَيْهِ اللَّيْلُ رَأَىٰ كَوْكَبًا ۖ قَالَ هَٰذَا رَبِّي…

የጁሙዓ ኹጥባ ርዕስ አሏህን መፍራት 🎙አቡ አብዲረህማን አቡዱልቃዲር ሐሰን 📆 ዙልሂጃ 15/1445 https://t.me/abuabdurahmen
إظهار الكل...
تقوى الله.mp33.55 MB
🚫  እህቶችን መሰረት ያደረገ የሿሿ ጥቃት       ሿሿ ማለት የሚታወቀው በአንድ ሚኒ ባስ ታክሲ ላይ ከስብእና የወጡ ሴቶች የሽማግሌ ቀላሎችና ወሮበላ ወጣቶች ተሰባስበው የሶስት ሰው ቦታ ከፊት ከመሀልና ኋላ ክፍት አድርገው ከተሳፋሪ ውስጥ የሚፈልጉትን ሲያገኙ አንድ ሰው ብቻ ብለው ያስገባሉ ። በክብር ቦታ የተለቀቀለት በማስመሰል የሚፈልጉት ቦታ እንዲቀመጥ ይደረጋል ። ያ ቦታ ማለት የተዋጣለት ፈታሽ የተዘጋጀበት ቦታ ነው ። ፈታሹ ስራውን ሲጀምር ውስጥ ያለው የውርጋጦች ስብስብ ረብሻ ይፈጥራል ። ሹፌሩ መኪናውን የሚገለብጠው ይመስላል ። በዚህ መሀል ግራ በመጋባት ምን እንደተፈጠረ ሳይገባው በፍተሻው የተራቆተው እንግዳ ተሳፋሪ እንዲወርድ ይደረጋል ። ወደራሱ ሳይመለስ ግራ እንደተጋባ ቆሞ ታክሲውን ያያል ። ታክሲው ትቶት ይፈተለካል ።   ወደራሱ ሲመለስና ኪሱን ሲፈትሽ ተራቁቷል ። ለመደወል ስልክ የለም ለመሳፈር ሳንቲም የለም ። የዚህን ጊዜ ነው የድራማው ሚስጢር የሚገባው ። ይህ ነው ከዚህ በፊት በሿሿ የሚታወቀው ።      የአሁኑ ሿሿ የረቀቀና ከውጭ የመጡ ወይም የውጭ ሀገር እድል ያገኙ እህቶችን መሰረት ያደረገ ነው ። በአብዛኛው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አካባቢና እንዲሁም ኤምባሲዎች አካባቢ ነው የወጥመዱ አካባቢዮች ።     ይህን በድራማ መልኩ የሚሰራ ትእይንተ ዘረፋ የሚያካሄዱ ዋልጌዎች በተቀናጀ መልኩ ስፍራ ስፍራቸውን ይይዛሉ ። በቅርብ ርቀት ቦታና የስራ ድርሻ ይመዳደባሉ ። የተንጣለለ ጊቢ ተከራይተው ለእኩይ ተግባራቸው ያዘጋጃሉ ።      በአብዛኛው ሒጃብ የለበሱ ሴቶችና ፂም ያስረዘሙ ሱሪ ያሳጠሩ ኮፍያ ያጠለቁ የሙስሊም ገፀባህሪ ተደርገው የተዘጋጁ የድራማው ተሳታፊ ይሆናሉ ። በዚህም በቀላሉ የሙስሊም እህቶችን ዐይን ይስባሉ ።      ከቀረጥ ነፃ ወረቀት ውክልና ሰጥተው ለማረጋገጥ ወደ ውጪ ጉዳይ የሚሄዱ , የጋብቻ ወይም የልደት አሊያም የትምህርት ማስረጃ ለማረጋገጥም ወደዚያ የሚያመሩ እህቶች በተለይ ከተማውን የማያውቁ ከሆኑ ቶሎ ይታወቃሉ ። ወዲያው በእነዚያ በተዘረጋ ሰንሰለት አቀባበል ይደረግላቸዋል ።       ሙስሊሞች ከሆኑ በባለ ሒጃቧ ወዴት ነው ?  ተብለው ይጠየቃሉ ያለ ምንም መጠራጠር ለምን ጉዳይ ወዴት መሄድ እንደሚፈልጉ ይናገራሉ ። እኔም ወደዛው ነኝ አብረን እንሄዳለን ይባላሉ ።  ጉዞ ይጀመራል ። ከደቂቃ በኋላ መኪና ይዞ የቆመ የሰንሰለቱ ተዋናይ ጋር ይደርሳሉ ።  ባለ ሂጃቧ ውጪ ጉዳይ በየት በኩል ነበር የሚያስገባው ?  ብላ ትጠይቃለች ። ተዋናዩም ግቡ ላድርሳችሁ ይላል ። ወደ ትወናው ቢሮ ጊቢ አድርሶ ያው ብሎ አውርዶ ይሄዳል ። በድራማው የተመለመሉ የወንድና ሴት ጥበቃዎች የት ነበር ብለው ይጠይቃሉ ይነገራቸዋል ።      እዚህ ጋር የሚሰራውን ድራማ ለመረዳት ወደ ተለያዩ በጣም ጥብቅ የሆኑ የመንግስት ተቋማት ሲገባ ያለውን ሁኔታ ላስታውሳችሁ ።      እንደ ሰላም ሚኒስቴር ፣ ደህንነትና መረጃ ፣ ኤር ፖርትና የመሳሰሉ ቦታዎች ሲገባ አንድ ሰው ወንድም ይሁን ሴት ወደ ውስጥ ለማለፍ ፍተሻ አልፎ ነው የሚገባው ። ፍተሻው ጋር ኤክስሬ ማሽን አለ ። ማንም ሰው በእጁም በኪሱም የያዘውን ማንኛውንም ብረት ነክ ነገር እንደ ሰአት ፣ ቁልፍ ጌጣጌጥ ፣ ቀበቶም ጭምር አውጥቶ በማሽኑ እንዲያልፍ አድርጎ ራሱም በሌላ ፈታሽ ማሽን አልፎ ይሄድና ያ በማሽን እንዲያልፍ ያደረገውን ንብረቱን ይወስዳል ። ከዚህ በኋላ ወደ መስሪያ ቤቱ ቢሮ ያመራል ።      ይህ ታዲያ እነዚህ ድራማ ሰሪዮች እንዴት እንደሚጠቀሙበት እንይ : – ይህች ድራማ የሚሰራባት ምስኪን እህት በእነዚህ ተልእኮ በተሰጣቸው ሴት ፈታሾች ምንም ብረት ነክ ነገር ይዞ መግባት አይፈቀድም ስለዚህ ሰአት ፣ ሞባይል ፣ ጌጣ ጌጦችን በሙሉ አውጥተሽ በቦርሳሽ ውስጥ አድርጊ ትባላለች ። ምስኪኗ እህትም የተባሉትን በሙሉ በቦርሳው ውስጥ ያለውን ብርም ጭምር ታስረክባለች ። ምናልባት ፓስፖርትና የሚረጋገጠው ወረቀት ቦርሳው ውስጥ ካለ በፓስፖርቱ ውስጥ መቶ ብር ተደርጎ ይሰጣታል ። ወደ ተባለው ቢሮ ስትገባ ማንም የለም ትንሽ ቆዪ ይመጣሉ ትባላለች ። ይሁን እንጂ የሚመጣ የለም ለመጠየቅ ስትወጣ ዘበኛው ተቀይሮ ሌላ ነው ።  ስትጠይቀው ቢሮ ገና ሰው ያልገባበት ባዶ ነው ። የምን የውጪ ጉዳይ ነው እንዲህ የሚብል ነገር አላቅም ይላል ። ‼      ኤምባሲ ከሆነ ድራማ ሰሪዮቹ በታክሲ ወደ ኤንባሲ የመጡ እህቶችን አዛኝ መስለው ኤምባሲው ከዚህ ለቋል ተብለን ነው ኑ ወደ አዲሱ ቢሮ አብረን እንሄዳለን በማለት የተለመደውን ድራማ ይሰራሉ ። ሴቶችን መሰረት ያደረገው ሿሿ ይህን ይመስላልና እህቶች ራሳችሁን ጠብቁ ።     ወጪ ለመቀነስ ብላችሁ በታክሲ ከመሳፈር በሚታወቁ ታማኝ ራይዶች ሄዳችሁ ጉዳያችሁን ፈፅማችሁ በሰላም ተመልሳችሁ ተመጣጣኝ ዋጋ ብትከፍሉ ከአስደንጋጭ ዘረፋ ትድናላችሁና ለማንኛውም ተጠንቀቁ!!።           http://t.me/bahruteka
إظهار الكل...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

✅ #አዲስ_ሙሐደራ  ✅ #محاضرة_جديدة ↘️ ርዕስ➘➘➘ ↪️ «ከጀነት ሰዎች ከፊል መገለጫዎች» ↙️ عنوان ➘➘➘ ↩️ «من صفات أهل الجنة» 🎙للشيخ أبي طلحة أبي ذر بن حسن الولوي «حَفِظَهُ اللَّهُ» 🎙 በሸይኽ አቡ ዘር ሀሰን አቡ ጦልሃ አላህ ይጠብቃቸው! 🕌 በኮምቦልቻ ሰለፍዮች የመስጂደ-ሰላም ገቢ ማሰባሰቢያ ግሩፕ ላይ በቀጥታ ስርጭት የተደረገ ሙሐደራ። 🗓 ጁምዓ ጥቅምት 02/2016 ወይም በላይቭ (ቀጥታ ስርጭት) የተደረገ። https://t.me/UstazAbuzarhassenAbutolha/8812
إظهار الكل...
❞مِن صِفَاتِ أَهْلِ الجَنَة❝.mp313.04 MB
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.