Defence Construction Enterprise
الذهاب إلى القناة على Telegram
Defence Construction Enterprise (DCE) is a leading construction company in Ethiopia, distinguished by its ability to operate in the country's most remote and challenging regions. We are deeply committed to building the nation.
إظهار المزيد1 723
المشتركون
+124 ساعات
-27 أيام
-130 أيام
أرشيف المشاركات
የድል ሠራዊት፦ 119ኛው የሠራዊት ቀን
119ኛው የሠራዊት ቀን*"የድል ሠራዊት" በሚል መሪ ቃል በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ ይገኛል።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት "በፈተናዎች ሁሉ እየተገነባ የመጣ" የሀገራችን ህልውና፣ የነጻነት እና የአንድነት የማይናወጥ ምሰሶ ነው።
ይህ አኩሪ ሠራዊት ተራራና ሸለቆዎችን፣ ከባድ ዝናብና የፀሐይ ሐሩርን ተቋቁሞ፤ የሚገጥሙትን ማንኛውንም የተፈጥሮም ሆነ ሰው ሰራሽ ፈተናዎች በብቃት ሰብሮ በማለፍ ታሪካዊ እና ሃገራዊ ግዴታውን በመወጣት ላይ ይገኛል። ለሀገር ክብርና ለህዝብ ደህንነት ሲል ሌሊትና ቀን የሚተጋ የቁርጥ ቀን አርበኛ በመሆኑ፣ ደመወዙ የሀገር ሰላም እና የህዝብ ጽኑ ደህንነት ነው።
የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ ሲል የከበረ ህይወቱን ጭምር አሳልፎ በመስጠት፣ ኢትዮጵያን በጽናት አቆይቶ የቆመ ዛሬም ወደኋላ የማይመለስ ታማኝ የክብር ኃይል ነው።
ይህ የቁርጥ ቀን ሠራዊት የኢትዮጵያ የረጅም ዘመን ታሪክ፣ የነጻነት እና የክብር መገለጫ አርማ ነው። ከሀገር አልፎ በአህጉርና በዓለም አቀፍ ደረጃ በተሰማራባቸው የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች የላቀ ጀግንነት፣ አንጸባራቂ ወታደራዊ ዲስፕሊን እና ሰብአዊነት በማሳየት የኢትዮጵያን ስም በዓለም መድረክ በድምቀት ያስጠራ ብሔራዊ ኩራታችን ነው። በየዘመናቱ የሚገጥሙትን ፈተናዎች አሸንፎ፣ የአባቶቹን አደራ በታማኝነት በመወጣት ላይ ይገኛል።
ታሪኩ የድል ማህደር የሆነው መከላከያችን፤ ለሀገር ህልውና ቀጣይነት የዘብነት ሚናውን በብቃት እያከናወነ ይገኛል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ኢትዮጵያ ዛሬም ሆነ ነገ በነጻነቷና በሉዓላዊነቷ ኮርታ እንድትቀጥል ያስቻለ የጀግኖች ስብስብ ነው።
ለሰላምና ለክብር የምታደርጉት መስዋዕትነት የሉዓላዊነታችን ዋስትና እና የኩራታችን አርማ በመሆኑ ሁልጊዜም በታላቅ ክብር ይታወሳል!
እንኳን ለ119ኛው የመከላከያ ሠራዊት ቀን አደረሰን አደረሳችሁ!
የድል ሠራዊት፦ 119ኛው የሠራዊት ቀን
119ኛው የሠራዊት ቀን*"የድል ሠራዊት" በሚል መሪ ቃል በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ ይገኛል።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት "በፈተናዎች ሁሉ እየተገነባ የመጣ" የሀገራችን ህልውና፣ የነጻነት እና የአንድነት የማይናወጥ ምሰሶ ነው።
ይህ አኩሪ ሠራዊት ተራራና ሸለቆዎችን፣ ከባድ ዝናብና የፀሐይ ሐሩርን ተቋቁሞ፤ የሚገጥሙትን ማንኛውንም የተፈጥሮም ሆነ ሰው ሰራሽ ፈተናዎች በብቃት ሰብሮ በማለፍ ታሪካዊ እና ሃገራዊ ግዴታውን በመወጣት ላይ ይገኛል። ለሀገር ክብርና ለህዝብ ደህንነት ሲል ሌሊትና ቀን የሚተጋ የቁርጥ ቀን አርበኛ በመሆኑ፣ ደመወዙ የሀገር ሰላም እና የህዝብ ጽኑ ደህንነት ነው።
የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ ሲል የከበረ ህይወቱን ጭምር አሳልፎ በመስጠት፣ ኢትዮጵያን በጽናት አቆይቶ የቆመ ዛሬም ወደኋላ የማይመለስ ታማኝ የክብር ኃይል ነው።
ይህ የቁርጥ ቀን ሠራዊት የኢትዮጵያ የረጅም ዘመን ታሪክ፣ የነጻነት እና የክብር መገለጫ አርማ ነው። ከሀገር አልፎ በአህጉርና በዓለም አቀፍ ደረጃ በተሰማራባቸው የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች የላቀ ጀግንነት፣ አንጸባራቂ ወታደራዊ ዲስፕሊን እና ሰብአዊነት በማሳየት የኢትዮጵያን ስም በዓለም መድረክ በድምቀት ያስጠራ ብሔራዊ ኩራታችን ነው። በየዘመናቱ የሚገጥሙትን ፈተናዎች አሸንፎ፣ የአባቶቹን አደራ በታማኝነት በመወጣት ላይ ይገኛል።
ታሪኩ የድል ማህደር የሆነው መከላከያችን፤ ለሀገር ህልውና ቀጣይነት የዘብነት ሚናውን በብቃት እያከናወነ ይገኛል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ኢትዮጵያ ዛሬም ሆነ ነገ በነጻነቷና በሉዓላዊነቷ ኮርታ እንድትቀጥል ያስቻለ የጀግኖች ስብስብ ነው።
ለሰላምና ለክብር የምታደርጉት መስዋዕትነት የሉዓላዊነታችን ዋስትና እና የኩራታችን አርማ በመሆኑ ሁልጊዜም በታላቅ ክብር ይታወሳል!
እንኳን ለ119ኛው የመከላከያ ሠራዊት ቀን አደረሰን አደረሳችሁ!
Repost from FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ መሃመድ ኢድሪስ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝን ጎበኙ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጥቅምት 09 ቀን 2019 ዓ.ም
የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መሃመድ ኢድሪስ እና ሚኒስትር ዴኤታዋ ወይዘሮ ሎሚ በዶ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝን ጎብኝተዋል፡፡
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብርጋዲየር ጄኔራል ኢንጂነር ሰጠኝ ሊኪሳ፤ ተቋሙ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ያከናወናቸውን የኮንስትራክሽን ሥራዎች፣ የሰው ኃይልን የማብቃት፣ በቴክኖሎጂ የታገዙ ሥራዎችን በመስራት የተመዘገቡ ውጤቶችን በተመለከተ ገለፃ አድርገዋል፡፡
በገለጻውም የተቋሙ ቀጣይ ልማት አቅጣጫዎችና ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች የተመላከቱ ሲሆን፣ በተለይም ተቋሙ አትራፊነቱን ጠብቆ ለመሄድና ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቀጠል ሰፊ ስራዎች እንደሚሠራ ተገልጿል።
የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ መሃመድ ኢድሪስ በኢንተርፕራይዙ በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ እና ተቋሙም አገራዊ ኃላፊነቱ እየተወጣ መሆኑን መገንዘባቸውን ገልጸው፤ አትራፊነቱን ጠብቆ ለመሄድ ከያዘው ተልዕኮ አንጻር የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ፣ በቀጣይም አቅሙን አጠናክሮ መስራት እንዲችል ስትራቴጂያዊ አቅጣጫዎችን መከተል እንዳለበት አሳስበዋል።
የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሎሚ በዶ በበኩላቸው፤ ተቋሙ ከተልዕኮው በመነሳት ያስመዘገባቸውን ውጤቶች ይበልጥ አስጠብቆ እንዲጓዝ ከፍተኛ አመራሩ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡
ዘጋቢ ማርታ ተፈሪ
ፎቶግራፍ ጥላሁን ደስታ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
https://www.facebook.com/fdredefense.official
+3
19ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በድምቀት ተከበረ
ጥቅምት 2 ቀን 2019 ዓ.ም
“ሠንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን” በሚል መሪ ሀሳብ 19ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የሥራ መሪዎች፣ የሰራዊት አባላትና ሲቪል ሠራተኞች በተገኙበት በኢንተርፕራይዙ ዋና መሥሪያ ቤት በድምቀት ተከበረ።
በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የኮርፖሬት ሰርቪስ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሽፈራው በቀለ ሰንደቅ ዓላማውን በወታደራዊ ሥነ-ሥርዓት ታጅቦ የመስቀል ሥነ-ሥርዓት አከናውነዋል።
ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን ታሪካችንን የምናስታውስበት ብቻ ሳይሆን፣ የወደፊቷን ኢትዮጵያ በጋራ ጥረት ለመገንባት ቃላችንን የምናድስበት ታላቅ ዕለት ነው።
ከፍ ብሎ በሰማያችን ሥር የሚውለበለበው የሦስቱ ቀለማት ሕብረት ተራ ጨርቅ ሳይሆን የትውልዶች መስዋዕትነት፣ የነፃነት አየር እና የብሔራዊ ኩራታችን ሕያው ምስክር ነው።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ኮሌጅ ዘመናዊ የተማሪዎች ማደሪያ ህንፃዎች ግንባታው ተጠናቆ ጊዜያዊ ርክክብ ተደረገ
መስከረም 18 ቀን 2018 ዓ.ም
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ እየተገነባ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ኮሌጅ ግንባታ ፕሮጀክት፣ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ሁለት ዘመናዊ የተማሪዎች ማደሪያ ህንፃዎች አጠናቆ የመጀመሪያውን ርክክብ አከናውኗል። የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ዮሃንስ ኃይሉ እንደገለጹት፤ በኮሌጁ ግቢ ውስጥ ሁለት (G+5) የተማሪዎች ማደሪያ ህንፃዎች፣ የመመገቢያ ህንፃ፣ የቢሮ አስተዳደር እና የመማሪያ ህንፃዎች ግንባታ እየተከናወኑ የሚገኙ ሲሆን፣ ከነዚህ መካከል ሁለቱ የተማሪዎች ማደሪያ ህንፃዎች ሙሉ በሙሉ ተጠናቀው ለባለቤቱ ርክክብ ተፈፅሟል።
እንደ ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጁ ገለጻ፣ አዲሶቹ ህንፃዎች ለሰልጣኞች ምቹና የተሟላ አገልግሎት የሚሰጡ ሲሆን፤ በአንዱ ህንፃ ብቻ 44 ሰልጣኞችን በየራሳቸው ክፍል በበቂ ሁኔታ ማስተናገድ የሚችሉ ሰፊ መኝታ ቤቶችን ይዘዋል። በተጨማሪም ህንፃዎቹ ጥራታቸውን የጠበቁ ሳሎን፣ ላውንደሪ ክፍል፣ የፊትለፊት የምግብ ማብሰያ እና የሻወር ክፍሎች አሏቸው። እያንዳንዱ ፎቅ ላይ የጽዳት ዕቃዎች ማከማቻ፣ ተጨማሪ ስቶሮች እና የቡድን ስራዎችን ማከናወኛ አነስተኛ ክፍሎች የተካተቱ ሲሆን፣ የቆሸሹ ልብሶችን በቀጥታ ከክፍል ወደ ላውንደሪ ክፍል በቀላሉ ለመላክ የሚያስችል ዘመናዊ ቴክኖሎጂም ተገጥሞላቸዋል።
የፕሮጀክት ባለቤት በመከላከያ ሚኒስቴር የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ ሲሆን፣አማካሪ ድርጅቱ ደግሞ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ነው። የግንባታ ቁጥጥርና አማካሪ መሐንዲስ ኢንጂነር ደረጄ አባቡ እንደገለጹት፣ የግንባታ ግብዓቶች አገልግሎት ላይ ከመዋላቸው በፊት ጥብቅ ፍተሻና ቁጥጥር ይደረግባቸዋል። አሁን ባለው ሂደቱ መሰረት የህንፃ ግንባታው ለታለመለት ዓላማ እንዲውልና በተቀመጠለት ዲዛይን እና ጥራት ግንባታው ተከናውኗል።
ቀሪዎቹ የቢሮ አስተዳደር፣ የመመገቢያ አዳራሽ እና የመማሪያ ህንፃዎች ግንባታም በሚፈለገው ከፍተኛ ጥራት በመከናወን ላይ ይገኛል።
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብ/ጄኔራል ሰጠኝ ሊኪሳ የአዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት
ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ እንዲሁም ለመከላከያ ሠራዊት አባላት እና ለኢንተርፕራይዙ ሲቪል ሠራተኞች በሙሉ፤ እንኳን ለ2019 አዲስ ዓመት በሰላም በጤና አደረሳችሁ፣ አደረሰን።
ባለፈው ዓመት የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የተቋሙን እና የሀገርን ዕድገት የሚያረጋግጡ መሠረታዊ የሆኑ ታላላቅ ሀገራዊ የግንባታ ፕሮጀክቶችን በጥራትና በፍጥነት በመገንባት፣ የባለቤቱን ፍላጎት መሠረት ባደረገ ሁኔታ ገንብተን ማስረከባችን ይታወቃል።
ያሳለፍነው ዓመት የየዕለት ትጋታችንን፣ ድካማችንን እና ቁርጠኝነታችንን የጠየቀ፤ በዚያው ልክ ደግሞ ትልልቅ የግንባታ ፕሮጀክቶችን አጠናቀን በማስረከብ ፍሬ ያየንበት ነበር። አዳዲስ ተስፋዎችን ሰንቀን ወደ ተሻለ የማንሰራራት ምዕራፍ እየተሸጋገርን ስለሆነ፣ ይህ አዲስ ዓመት በሁሉም መስኮች እጅ ለእጅ ተያይዘን የምንሠራበትና ይበልጥ የምንጎለብትበት እንደሚሆን ሙሉ እምነት አለኝ።
ያለፈው የበጀት ዓመት ለድርጅታችን ቀላል የማይባሉ ፈተናዎች የታዩበት ቢሆንም፣ አመራሩና ሠራተኛው በጋራ ባደረግነው ርብርብ አስደናቂ ስኬቶችን ማስመዝገብ ችለናል። በየደረጃው የምትገኙ ውድ የሥራ ባልደረቦቼ! ከምንም በላይ ለድርጅታችን ግቦች መሳካት በየግንባታ ፕሮጀክቶቻችን ያሳያችሁት ቁርጠኝነት ከልብ የሚያስመሰግናችሁ ነው። የዛሬው አቅማችን መሠረት የሆነው ይኸው የጋራ ጥንካሬያችን ነው።
አዲሱ የ2019 ዓ.ም ለኢንተርፕራይዛችን የዕድገት፣ የአዳዲስ ጅማሮዎች እና የሰፋፊ ዕድሎች በር የተከፈተበት ዘመን ነው። በመሆኑም የደንበኞቻችንን እርካታ ይበልጥ ለማሳደግ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግራችንን ለማፋጠን እና የሥራ አፈጻጸማችንን በአዲስ መንፈስ ለማደስ በብርቱ ትጋት ላይ እንገኛለን። ለዚህ ስኬት ደግሞ የእያንዳንዳችሁ የባለቤትነት ስሜት፣ የፈጠራ አቅም እና ያላሰለሰ ጥረት እጅግ ወሳኝ ነው።
በመጪው ዓመት ልዩነቶቻችንን በምክክር አቻችለን፣ በአንድ ልብ በመሥራት ለድርጅታችን ላቅ ያለ ውጤት እንድንተጋና ለሀገራችን የኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማት የበኩላችንን አሻራ እንድናሳርፍ አደራ እላለሁ። አዲሱ ዓመት በአዲስ ጉልበትና በታደሰ መንፈስ ወደ ሥራ ገበታችን የምንመለስበት እና ለድርጅታችን አዲስና ብሩህ ታሪክ የምንጽፍበት እንዲሆን ከልብ እመኛለሁ።
መልካም አዲስ ዓመት
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት
የነገው ቀን
"ሀገራዊ የቴክኖሎጂ ሽግግር
ከወረቀት ወደ ዲጂታል፤ ከተጠቃሚነት ወደ ፈጣሪነት! ትናንትን በመማርና በማረም ዛሬን በላቀ ትጋት በመገንባት ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የዕለት ተዕለት ባህላችን እየሆነ ነው። ንግድና አገልግሎትን ያቀላጥፋል፣ መረጃዎችን ተደራሽ ያደርጋል፣ ዘርፎችንም ያዘምናል! የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያ ኮደሮች ንቅናቄ ወጣቶችን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ፈጣሪ በማድረግ ወደ 7 ሚሊዮን ግባችን እያመራ ሲሆን የዲጂታል አገልግሎት ተደራሽነትና ጥራትን አረጋግጧል። በሀገር በቀል አቅም የበለጸገው የሳይበር ሉዓላዊነታችን ደግሞ የማንቆጣጠራቸው ቴክኖሎጂዎችን ጥገኝነት አላቆ በዲጂታል ኢኮኖሚ በራስ አቅሟ የምትቆም አዲሷ ኢትዮጵያ በታላቅ ምዕራፍ ላይ መሆኗን በኩራት ያበስራል!"
#DigitalEthiopia2030
+1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጳጉሜን 4 - የኅብር ቀንን በማስመልከት ያስተላለፉት መልዕክት
**************************
የኅብር ቀን
ኢትዮጵያችን በሀገር በቀል እሴቶቿ፤ የነገውን ብሩህ ተስፋዋን በገዛ እጆቿ እየቀረጸች ትገኛለች!
በትውልድ ቅብብሎሽ ያገኘናቸውን ድንቅ የሀገር በቀል እሴቶቻችንን በማጎልበት እና በመደመር ፍልስፍና በመመራት፣ ለጽኑ ኅብረብሔራዊ አንድነታችን የማይናወጥ መሠረት ጥለናል።
ታሪካዊውን ሀገራዊ ምክክር የመጀመር የታሪክ እጥፋት ተነስተን፣ የሁሉም ዜጎቻችንን ሕይወት ከሚለውጡ ሰው-ተኮር የኮሪደር ልማታችን፣ የበጎ ፈቃድ ስራዎቻችን እንዲሁም የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃግብርን በተግባር እውን እስከማድረግ ድረስ፤ ሁላችንም በአንድነት ስንቆም የጋራ ትርክቶቻችን ወደ ጋራ ስኬት እንደሚያሻግሩን በተግባር አሳይተናል።
እኛ የምንገነባው አካታች የሆነች፣ በኢኮኖሚ ራሷን የቻለች፣ የአብሮነትና መረዳዳት ባህል የጎለበተባት ጠንካራ ሀገር ብቻ ሳይሆን የሁሉንም ኢትዮጵያውያን የጋራ ታላቅነትና እምቅ አቅም በተግባር እያረጋገጥን እንገኛለን። በአንድነት ወደ ብልጽግና ጉዟችን እንቀጥላለን።
አንድ ህዝብ፣ ታላቅ ሀገር ኢትዮጵያ!
የኅብር ቀን
ኢትዮጵያችን በሀገር በቀል እሴቶቿ፤ የነገውን ብሩህ ተስፋዋን በገዛ እጆቿ እየቀረጸች ትገኛለች!
በትውልድ ቅብብሎሽ ያገኘናቸውን ድንቅ የሀገር በቀል እሴቶቻችንን በማጎልበት እና በመደመር ፍልስፍና በመመራት፣ ለጽኑ ኅብረብሔራዊ አንድነታችን የማይናወጥ መሠረት ጥለናል። ታሪካዊውን ሀገራዊ ምክክር የመጀመር የታሪክ እጥፋት ተነስተን፣ የሁሉም ዜጎቻችንን ሕይወት ከሚለውጡ ሰው-ተኮር የኮሪደር ልማታችን፣ የበጎ ፈቃድ ስራዎቻችን እንዲሁም የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃግብርን በተግባር እውን እስከማድረግ ድረስ፤ ሁላችንም በአንድነት ስንቆም የጋራ ትርክቶቻችን ወደ ጋራ ስኬት እንደሚያሻግሩን በተግባር አሳይተናል።
እኛ የምንገነባው አካታች የሆነች፣ በኢኮኖሚ ራሷን የቻለች፣ የአብሮነትና መረዳዳት ባህል የጎለበተባት ጠንካራ ሀገር ብቻ ሳይሆን የሁሉንም ኢትዮጵያውያን የጋራ ታላቅነትና እምቅ አቅም በተግባር እያረጋገጥን እንገኛለን። በአንድነት ወደ ብልጽግና ጉዟችን እንቀጥላለን።
አንድ ህዝብ፣ ታላቅ ሀገር ኢትዮጵያ!
#EthiopiaPrevails
