cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት - ዘብሔረ ጎንደር (ዲ/ዮርዳኖስ አበበ)

በዚህ ቻናል ዲ/ዮርዳኖስ የሚያስተምራቸው ወቅታዊ እና የነገረ ቅዱሳን (ዝክረ ቅዱሳን ትምህርቶችን ከእርሱ በመቀበል እናስተላልፋለን):: "ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
40 926
المشتركون
+1224 ساعات
+2247 أيام
+88330 أيام
توزيع وقت النشر

جاري تحميل البيانات...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
تحليل النشر
المشاركاتالمشاهدات
الأسهم
ديناميات المشاهدات
01
Media files
1 1005Loading...
02
✝✝✝ እንኩዋን ለዳግሚያ ትንሳኤ በሰላም አደረሳችሁ ✝✝✝ =>ለስም አጠራሩ ጌትነት ይድረሰውና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅድስት ትንሳኤው በሁዋላ ለደቀ መዛሙርቱ በጉባኤ 3 ጊዜ ተገልጦላቸዋል:- 1.በዕለተ ትንሳኤ ምሽት በፍርሃት ሳሉ 2.ያላመነ ቶማስን ለማሳመን በተነሳ በ8ኛው ቀን (ማለትም ዛሬ) 3.ከተነሳ ከ23 ቀናት በሁዋላ በጥብርያዶስ ባሕር ዳርቻ ላይ ነው:: +ጌታ አርባውን ቀን ለአንዱም: ለሁለቱም በግል ይገለጥላቸው ነበር:: እመቤታችንን ግን ፈጽሞ አይለያትም ነበር:: +ጌታችን ከተነሳ በሁዋላ ለሳምንት ተለይቷቸው ስለ ነበር በቤተ ክርስቲያን ውዳሴ ማርያም እንጂ መልክዐ ኢየሱስ በማሕበር አይደገምም:: +በዚሕች ዕለት ደቀ መዛሙርቱ በጽርሐ ጽዮን ሳሉ ጌታችን "ሰላም ለእናንተ ይሁን" ብሏቸዋል:: ቶማስንም "ና ዳስሰኝ" ብሎታል:: ሐዋርያው እጁን ከተወጋ ጐኑ ላይ ቢያሳርፍ በመቃጠሉ "ጌታየ አምላኬም" ሲል ጮሆ ምስጢረ ተዋሕዶውን መስክሯል:: +ጌታም ቶማስን "እስመ ርኢከኒሁ አመንከኒ" (ማለትም ስላየኸኝ አመንከኝ)! "ብጹዐንሰ እለ እንዘ ኢይሬእዩኒ የአምኑኒ" (ሳያዩ የሚያምኑ ግን ብጹዐን (ማለትም ንዑዳን ክቡራን) ናቸው ብሎታል:: (ዮሐ. 20:24) =>ከጌታችን ከትንሳኤው: ከቅዱሱም ሐዋርያ በረከት አይለየን:: =>+"+ ደጆች ተዘግተው ሳሉ ኢየሱስ መጣ:: በመካከላቸውም ቆሞ 'ሰላም ለእናንተ ይሁን' አላቸው:: ከዚያም በሁዋላ ቶማስን 'ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ:: እጅህንም አምጣና በጐኔ አግባው:: ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን' አለው:: ቶማስም 'ጌታዬ አምላኬም' ብሎ መለሰለት:: ኢየሱስም 'ስላየኸኝ አምነሃል:: ሳያዩ የሚያምኑ ብጹዓን ናቸው' አለው:: +"+ (ዮሐ. 20:26-29)    <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
8325Loading...
03
💠"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"💠    /(ማቴ ፫:፫/) ✝እንኳን አደረሰን! 🛑 ዝክረ ቅዱሳንን ላልደረሳቸው  እናድርስ እናስፋ ስለ ሀገራችን እንጸልይ ንስሐ እንግባ!!🛑 ✝ 5 ነገሮችን በደንብ ያዙ።     1, 🛑አላማ     2 ,🛑እምነት     3,🛑ጥረት     4 🛑ጥንቃቄ      5🛑ጽናት =>እነዚህን ያዟቸው ተጠቀሙባቸዉ ኑሯቸው። ❇️9ኙ የቅድስና መንገዶች❇️ ፩👉ሃይማኖት ፪👉ጾም ፫👉ጸሎት ፬👉ስግደት ፭👉ምጽዋት ፮👉ፍቅር ፯👉ትህትና ፰👉ትዕግስት ፱👉የዋህነት ✝ንስሐ የተጣመመውን ያቀናል።በኃጥያት የቆሸሸውን ያነጻል፤ንስሐ ለሚገቡ ሁሉ የመላዕክት ንጹሕ ልብስ ይሰጣችኃል።         (ቅዱስ መቃርስ )   ንስሐ ግቡ።✝ ዝክረቅዱሳን (ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት) " ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::        አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/ 🛑በዩቲብለመከታተል👉https://www.youtube.com/@ZikereKedusan 🛑በቴሌግራም👉https://t.me/zikirekdusn 👉 ግእዝ መማር የምትሹ https://t.me/lisanegeez5
4932Loading...
04
Media files
4232Loading...
05
#Feasts of #Ginbot_4 ✞✞✞On this day we commemorate the departure of Abune Melchizedek the Righteous✞✞✞ ✞✞✞In the name of the Father, the Son and the Holy Spirit, one God. Amen!✞✞✞ ✞✞✞Abune Melchizedek✞✞✞ =>The Ethiopian Saint Abune Melchizedek is known by many for his wondrous monastery which is found in Shewa (Mida). In addition to the monastery being endowed with age old trees, anyone that is buried there, his/her body does not decay (will not corrupt) and that is because of the covenant the Saint has [which he received from God]. If asked the life accounts of the Saint, it was as follows. ✞Abune Melchizedek lived during the reigns of the Shewa Kings, and was a close relative of Emperor Amda Seyon. The Saint’s parents were called Fre Seyon, and Amete Maryam. Abune Melchizedek studied administration while he was still a kid. ✞And later on, after he studied the Old and New Testaments from a teacher, he shunned this world, escaped from the palace, went to Abune Aron Thaumaturgus and became a monk. ✞And when the news was heard around the citadel, his parents wept. And Abune Aron was accused. However, as it was [a call] from God, an angel led Abune Melchizedek to where his monastery is now located, Shewa (Mida). ✞There, he built a small cell and fought the spiritual battle for many years. And the cave, his cell, was named Debre Medhanit (A Place of Salvation). The Saint, in addition to his prayer and fasting, used to whip himself 300 times every Friday remembering the passion of our Lord Jesus Christ. And he used to ask his disciples to lash him as well. At one time, because he had nailed his hands and legs, he was found with his blood dripping. ✞And in the end, Abune Melchizedek asked the Lord to forgive Ethiopians. And the Lord answered, “I will forgive those who believe in your name, those who beseech through the covenant I gave you and those who come to your monastery.” ✞And on this day, the Saint, after making many miracles, passed away. And Abune Amha Iyesus shrouded him honorably and buried him in his cell. ✞✞✞May our God not detach us from the Saint’s reward, and blessing. ✞✞✞Annual feasts celebrated on the 4th of Ginbot 1. Abune Melchizedek, Priest (Ethiopian Saint) 2. Abba John (Youhanna) Archbishop (29th Pope of Alexandria) 3. Sts. Sosima and Noda (Noba), Martyrs (Followers of the Great St. Victor) ✞✞✞ Monthly Feasts 1. St. John the Evangelist 2. St. Andrew Apostle 3. St. Sophia Martyr 4. St. John of Herakleia/ Arakli (Martyr) ✞✞✞“Is any sick among you? let him call for the elders of the church; and let them pray over him, anointing him with oil in the name of the Lord: And the prayer of faith shall save the sick, and the Lord shall raise him up; and if he have committed sins, they shall be forgiven him. Confess your faults one to another, and pray one for another, that ye may be healed. The effectual fervent prayer of a righteous man availeth much.”✞✞✞ Jas. 5:14-16 ✞✞✞ Salutations to God ✞✞✞ (Translated by Mhr. Esuendale Shemeles with the permission of Dn. Yordanos Abebe) https://t.me/zikirekdusn
4230Loading...
06
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† እንኩዋን ለጻድቁ አቡነ መልከ ጼዴቅ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ††† +"+ አቡነ መልከ ጼዴቅ +"+ =>ኢትዮዽያዊው ጻድቅ አቡነ መልከ ጼዴቅን ብዙ ሰው ሽዋ (ሚዳ) ውስጥ በሚገኘው አስደናቂ ገዳማቸው ያውቃቸዋል:: ገዳሙ በእድሜ ጠገብ ዛፎች ያጌጠ ከመሆኑ ባሻገር በጻድቁ ቃል ኪዳን ምክንያት በቦታው የሚቀበር ሁሉ አካሉ አይፈርስም:: የጻድቁስ ዜና ሕይወታቸው እንደምን ነው ቢሉ:- +አቡነ መልከ ጼዴቅ በሸዋ ነገሥታት ዘመን የነበሩ: የንጉሱ ዓምደ ጽዮን የቅርብ ዘመድ ነበሩ:: የጻድቁ ወላጆች ፍሬ ጽዮንና ዐመተ ማርያም ይባላሉ:: አቡነ መልከ ጼዴቅ ገና በሕጻንነታቸው ሥርዓተ መንግስትን አጥንተዋል:: +በሁዋላ ከመምሕር ዘንድ ገብተው ብሉይ ከሐዲስ ተምረው ሲያጠናቅቁ ይሕንን ዓለም ናቁና ከቤተ መንግስቱ አካባቢ ጠፍተው ወደ አቡነ አሮን መንክራዊ ዘንድ ሔደው መንኩሰዋል:: +ነገሩ በቤተ መንግስት አካባቢ ሲሰማ ወላጆች አለቀሱ:: አቡነ አሮንም ተከሰው ነበር:: ነገሩ ግን ከእግዚአብሔር ነበርና አቡነ መልከ ጼዴቅን መልዐክ እየመራ አምጥቶ አሁን ገዳማቸው ያለበት ሸዋ (ሚዳ) አደረሳቸው:: +በዚያ ትንሽ በዓት ሰርተው ለዘመናት ተጋድለዋል:: ዋሻዋም ደብረ መድኃኒት ትባላለች:: ጻድቁ ከጾምና ጸሎታቸው በተረፈ ዓርብ ዓርብ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሕማማት በማሰብ ጀርባቸውን 300 ጊዜ ይገርፉ: ደቀ መዛሙርቱንም ግረፉኝ ይሉ ነበር:: አንድ ጊዜም እጃቸውንና እግራቸውን በትልልቅ ችንካሮች ቸንክረውት ደማቸው ሲፈስ ተገኝቷል:: +በመጨረሻ አቡነ መልከ ጼዴቅ ጌታን ኢትዮዽያውያንን ማርልኝ አሉት:: ጌታችንም መለሰ:- "በስምህ ያመኑትን: በቃል ኪዳንህ የተማጸኑትን: ገዳምሕን የተሳለሙትን እምርልሃለሁ::" +ጻድቁም ብዙ ተአምራትን ሰርተው በዚሕች ቀን አርፈዋል:: አቡነ አምሃ ኢየሱስም በክብር ገንዘው በበዓታቸው ውስጥ ቀብሯቸዋል:: =>አምላካችን እግዚአብሔር ከጻድቁ ዋጋና በረከት አይለየን:: =>ግንቦት 4 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.አቡነ መልከ ጼዴቅ ካህን (ኢትዮዽያዊ ጻድቅ) 2.አባ ዮሐንስ ሊቀ ዻዻሳት 3.ቅዱሳን ሶሲማና ኖዳ ሰማዕታት (የታላቁ ፊቅጦር ተከታዮች የነበሩ) =>ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጉዋድ (ወንጌላዊው) 2.ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ 3.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት 4.ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ (ሰማዕት) =>+"+ ከእናንተ የታመመ ማንም ቢኖር የቤተ ክርስቲያን ቀሳውስትን ወደ እርሱ ይጥራ:: በጌታም ስም እርሱን ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት:: የእምነትም ጸሎት ድውዩን ያድናል:: ጌታም ያስነሳዋል:: ኃጢአትም ሠርቶ እንደ ሆነ ይሠረይለታል:: እርስ በርሳችሁ በኃጢአታችሁ ተናዘዙ:: ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ:: የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች:: +"+ (ያዕ. 5:14) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር ††† https://t.me/zikirekdusn
7105Loading...
07
Media files
3823Loading...
08
✝✞✝ እንኩዋን ለእናቶቻችን "ቅዱሳት አንስት" ዓመታዊ የመታሠቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ +"+ +*" ቅዱሳት አንስት "*+ =>ከትንሳኤ ሳምንት ይህች ዕለት "ቅዱሳት አንስት" (የተቀደሱ ሴቶች) ተብላ ትጠራለች:: +በወቅቱ በኢየሩሳሌምና ዙሪያዋ ከተከተሉት ሴቶች ጌታችን 36ቱን መርጧል:: እነዚህ እናቶች ከዋለበት ውለው : ካደረበት አድረው : የቃሉን ትምሕርት ሰምተዋል:: የእጁንም ተአምራት አይተዋል:: ፈጽመውም አገልግለውታል:: +መጽሐፍ "አንስተ ገሊላ ኩሎን:: አዋልዲሃ ለጽዮን:: አስቆቀዋሁ ለመድኅን:: ከመ ዖፈ መንጢጥ እንዘ ይሤጽራ ገጾን::" ይላልና በዕለተ ዐርብ ፊታቸወውን እየነጩ : ደረታቸውን እየደቁ : እንባቸውም እንደ ጐርፍ እየፈሰሰ አብረውት ውለዋል:: +ጌታም ፍጹም ፍቅራቸውን ተመልክቷልና ከሁሉ አስቀድሞ ትንሳኤውን ለእነሱ ገለጠላቸው:: እነርሱም ትንሳኤውን በመፋጠን አብሥረዋል:: "ሰበካ ትንሳኤ፡ አዋልዲሃ ለጽዮን" እንዳለ ማኅሌታይ ቅዱስ ያሬድ፡፡ በዚህም ምክንያት ይህች ዕለት "ቅዱሳት አንስት" ተብላ ትከበራለች:: =>አምላካችን በፍቅርና በቅድስና ጌጥ ካጌጡ እናቶቻችን በረከትን ያድለን:: =>+"+ መልአኩም መልሶ ሴቶቹን አላቸው:- 'እናንተስ አትፍሩ:: የተሰቀለውን ኢየሱስን እንድትሹ አውቃለሁና:: እንደተናገረ ተነስቷልና በዚሕ የለም:: የተኛበትን ሥፍራ ኑና እዩ:: ፈጥናችሁም ሒዱና ከሙታን ተነሣ: እነሆም ወደ ገሊላ ይቀድማቹሃል:: በዚያም ታዩታላችሁ ብላችሁ ለደቀ መዛሙርቱ ንገሯቸው' . . . እነሆም ኢየሱስ አገኛቸውና ደስ ይበላችሁ አላቸው:: እነርሱም ቀርበው እግሩን ይዘው ሰገዱለት:: +"+ (ማቴ. 28:5-10)    <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> https://t.me/zikirekdusn
4 10439Loading...
09
Media files
4 07729Loading...
10
https://youtu.be/qvkIAJU74Dc?si=Bxh4cH1FGZW4lF36
3 69615Loading...
11
https://youtu.be/59iDern_vZ0?si=fXEEDeiPdqUk4duc
3 84326Loading...
12
Media files
3 46919Loading...
13
🛑<<< በስመ አብ : ወወልድ : ወመንፈስ ቅዱስ : አሐዱ አምላክ . . . አሜን:: >>> << 🛑በበዓለ ሃምሳ ንስሃ ለምን ተከለከለ? 🛑>> =>በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ያለ ምክንያት የሚደረግ : ያለ ምሥጢርም የሚከወን ምንም ነገር የለም:: የሃይማኖትን ትምህርት አብዝተን በተማርን ቁጥር የምናውቀው አለማወቃችን ነውና ምንም ያህል ብንማር : የአዋቂነት መንፈስም ቢሰማን ከመጠየቅ ወደ ጐን አንበል:: መጠየቅ ለበጐ እስከሆነ ድረስ ሁሌም ሸጋ ነው:: ግን ልብን እያጣመሙ ቢያደርጉት ደግሞ ገደል ይከታል:: +ወደ ጉዳዬ ልመለስና ሁሌ የሚገርመኝ የትውልዱ አመለካከት ነው:: ጾም ሲመጣ "ለምን? . . . አልበዛም? . . ." ዓይነት ቅሬታዎች ይበዛሉ:: በዓለ ሃምሳ ሲመጣ ደግሞ "እንዴት ይህን ያህል ቀን ይበላል? . . ." ባዩ ይከተላል:: +ቤተ ክርስቲያን ግን ሁሉን የምትለን ለጉዳይ : ለምክንያትና ለእኛ ጥቅም ነው:: ለምሳሌ:- በዓለ ሃምሳ ድንገት እንደ እንግዳ ደርሶ : እንደ ውሃ ፈሶ የመጣ ሥርዓት አይደለም:: ይልቁኑ ምሳሌ ተመስሎለት በብሉይ ኪዳንም ሲከወን የነበረ እንጂ:: +እንደሚታወቀው እስራኤል ከግብጽ ባርነት በ9 መቅሰፍት : በ10ኛ ሞተ በኩር ወጥተው : በ11ኛ ስጥመት ጠላት ጠፍቶላቸው ወደ ምድረ ርስት ተጉዘዋል:: ቅዱስና የእግዚአብሔር ሰው ሙሴም ከእግዚአብሔር እየተቀበለ ብዙ ሥርዓቶችን ለቤተ እስራኤል አስተምሯል:: +እነዚህ ሥርዓቶች ሁሉ ለሐዲስ ኪዳን ምሥጢረ ድኅነት ጥላና ምሳሌዎችም ነበሩ:: በኦሪት ዘሌዋውያን ላይ ጌታ እንዲህ ይላል:- ". . . ከሰንበት ማግስት ፍጹም ሰባት ጊዜ ሰባት ቀን ቁጠሩ:: እስከ ሰባተኛ ሰንበት ማግስት ድረስ አምሳ ቀን ቁጠሩ:: አዲሱንም የእህል ቁርባን ወደ እግዚአብሔር አቅርቡ::" (ዘሌ. 23:15) +ይህም "በዓለ ሰዊት (የእሸት በዓል)" የሚባል ሲሆን ከፋሲካ 7 ሱባኤ (49 ቀን) ተቆጥሮ : በሰንበት (ቅዳሜ) ማግስት (እሑድ ቀን) በዓለ ሃምሳ ይውላል:: በዓሉ በግሪክኛው "ዸንጠቆስቴ (Pentecost)" ይባላል:: "በዓለ ሃምሳ" እንደ ማለት ነው:: +ለዚያም ነው ቅዱስ መጽሐፍ የመንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያት በዚህ ቀን መሰጠትን ሊነግረን ሲጀምር "ወአመ ተፈጸመ መዋዕለ ዸንጠኮስቴ . . ." የሚለው:: (ሐዋ. 2:1) በዓለ ሃምሳ (50ው ቀናት) በብሉይ "የእሸት በዓል" ቢባሉም ለሐዲስ ኪዳን ግን "የሰዊት (እሸት) መንፈሳዊ" ዕለታት ናቸው:: +ጌታ መድኃኔ ዓለም ስለ እኛ መከራ ተቀብሎ : ሙቶ ከተነሳ በሁዋላ 50 ያሉት ቀናት የዕረፍት : የተድላ : የመንፈሳዊ ሐሴት ቀናት ናቸው:: በእነዚህ ዕለታት ማዘን : ማልቀስ : ሙሾ ማውረድ : ንስሃ መግባት ወዘተ. አይፈቀድም:: =>ለምን? 1.ለእኛ ካሣ በጌታችን መፈጸሙን የምሰናስብባቸው ቀናት ናቸውና:: በእነዚህ ዕለታት ብናዝን "አልተካሰልንም" ያሰኛልና:: 2.በዚህ ጊዜ መስገድ : መጾም "ክርስቶስ በከፈለልን ዋጋ ሳይሆን በራሴ ድካም (ተጋድሎ) ብቻ እድናለሁ" ከማለት ይቆጠራልና:: 3."ፍስሐ ወሰላም ለእለ አመነ - ላመን ሁሉ ደስታና ሰላም ተደረገልን" ተብሎ በነግህ በሠርክ በሚዘመርበት ጊዜ ማዘን . . . ሲጀመር ካለማመን : ሲቀጥል ደግሞ "ደስታው አይመለከተኝም" ከማለት ይቆጠራልና:: 4.50ውም ቀናት እንደ ዕለተ ሰንበት ይቆጠራሉና:: መጾምና መስገድ በዓል ያስሽራልና:: 5.ዋናው ምሥጢር ግን እነዚህ 50 ዕለታት የአዝማነ መንግስተ ሰማያት (የሰማያዊው ዕረፍት) ምሳሌዎች ናቸው:: ስለዚህ በእነዚህ ቀናት መጾም : መስገድ "መንግስተ ሰማያት ውስጥ ከገቡ በሁዋላ ድካም : መውጣት መውረድ አለ" ያሰኛልና ነው:: +በዚያውም ላይ "ኢታጹርዎሙ ጾረ ክቡደ (ከባድ ሸክም አታሸክሙ)" የተባለ ትዕዛዝ አለና ቅዱሳን አበው በጾም የተጐዳ ሰውነት ካልጠገነ ወጥቶ ወርዶ : ሠርቶ መብላት ይቸግረዋልና ሰውነታችን እንዲጠገን : ይህንን በፈሊጥ ሠርተዋል:: +ስለዚህም:- "ሐጋጌ አጽዋም እምስቴ:: ወሠራዔ መብልዕ በዸንጠኮስቴ::" እያልን አበውን እናከብራለን:: (አርኬ) +ስለዚህ በበዓለ ሃምሳ ጾም : ስግደት : ንስሃ : ሐዘን : ልቅሶ . . . የለም:: አይፈቀድምም:: <<ግን ይህንን ተከትሎ 50ውን ቀን ሙሉ ሆድ እስኪተረተር ከበላን ጉዳቱ ሥጋዊም : መንፈሳዊም ይሆናል!!>> +አበው እንደነገሩን "እንደ ልባችሁ ብሉ" ሳይሆን የተባለው "ጦም አትዋሉ" ነው:: ለምሳሌ:- 1.በልቶ ጠጥቶ ከሚመጣ ኃጢአት : ክፋትና ፈተና ለመጠበቅ 50ውን ቀናት ጥሬ የሚበሉ አሉ:: 2.ጠዋት ተመግበው ከ24 ሰዓት በሁዋላ ጠዋት የሚመገቡ አሉ:: 3.መጥነው ጥቂት በልተው አምላካቸውን የሚያመሰግኑ አሉ:: 4.ነዳያንን አጥግበው እነርሱ ከነዳያን ትራፊ የሚቀምሱ አሉ:: +እኛም ከእነዚህ መካከል የሚስማማንን መርጠን ልንከውን : በተለይ ደግሞ በጸሎት ልንተጋ ይገባል:: አልያ ብሉ ተብሏል ብለን ያለ ቅጥ ብንበላ : ብንጠጣ እኛው ራሳችን የሰይጣን ራት መሆናችን ነውና ልብ እንበል:: ማስተዋልንም ገንዘብ እናድርግ:: "እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ የሥጋን ነገር ያስባሉና:: እንደ መንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን የመንፈስን ነገር ያስባሉ:: ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና:: ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው:: ስለ ሥጋ ማሰብ በእግዚአብሔር ዘንድ ጥል ነውና:: ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛምና:: መገዛትም ተስኖታል:: በሥጋ ያሉትም እግዚአብሔርን ደስ ሊያሰኙት አይችሉም::" (ሮሜ. 8:5) =>አምላከ ቅዱሳን ማስተዋሉን ያድለን:: << ወስብሐት ለእግዚአብሔር >> Dn Yordanos Abebe https://t.me/zikirekdusn
3 37374Loading...
14
💠"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"💠    /(ማቴ ፫:፫/) ✝እንኳን አደረሰን! 🛑 ዝክረ ቅዱሳንን ላልደረሳቸው  እናድርስ እናስፋ ስለ ሀገራችን እንጸልይ ንስሐ እንግባ!!🛑 ✝ 5 ነገሮችን በደንብ ያዙ።     1, 🛑አላማ     2 ,🛑እምነት     3,🛑ጥረት     4 🛑ጥንቃቄ      5🛑ጽናት =>እነዚህን ያዟቸው ተጠቀሙባቸዉ ኑሯቸው። ❇️9ኙ የቅድስና መንገዶች❇️ ፩👉ሃይማኖት ፪👉ጾም ፫👉ጸሎት ፬👉ስግደት ፭👉ምጽዋት ፮👉ፍቅር ፯👉ትህትና ፰👉ትዕግስት ፱👉የዋህነት ✝ንስሐ የተጣመመውን ያቀናል።በኃጥያት የቆሸሸውን ያነጻል፤ንስሐ ለሚገቡ ሁሉ የመላዕክት ንጹሕ ልብስ ይሰጣችኃል።         (ቅዱስ መቃርስ )   ንስሐ ግቡ።✝ ዝክረቅዱሳን (ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት) " ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::        አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/ 🛑በዩቲብለመከታተል👉https://www.youtube.com/@ZikereKedusan 🛑በቴሌግራም👉https://t.me/zikirekdusn 👉 ግእዝ መማር የምትሹ https://t.me/lisanegeez5
2 68821Loading...
15
Media files
2 30020Loading...
16
#Feasts of #Ginbot_3 ✞✞✞On this day we commemorate the departure of Saint Jason, one of the 72 Disciples, and Empress Welete Maryam of Ethiopia✞✞✞ ✞✞✞In the name of the Father, the Son and the Holy Spirit, one God. Amen!✞✞✞ ✞✞✞Saint Jason the Apostle✞✞✞ =>The forgetfulness of commemorating the names of the saints and their deeds is one of the sad things of our day and age. As if their blood was not shed and their bones were not crushed for the Church, we see today no one remembering them or most failing to recall even their names.  ✞On top of that, some heretics accuse us, the Orthodox Tewahedo believers, as if we only are preaching about the saints and not about Christ. ✞Overlooking the Holy Apostles (the 120) is one of the major dismaying aspects [of today].  And because the names of many of the 120 Disciples have been forgotten and as the scholars have also chosen to stay silent, when we call on the names of the 72 Disciples saying, “Jason, Erastus, Epaphroditus, Phorus (Fournous) . . .” a generation that is bewildered has came up.  ✞Let us at least remember the Apostles and the major saints! And that is because by commemorating them, we and not they are benefited. =>Saint Jason, whom we commemorate today, was one of the 72 Disciples. He followed our Lord after His baptism and had learned under Him for 3 years. Then, after the ascension of our Lord, he went out to evangelize after receiving the gifts of the Holy Spirit. ✞The Saint has preached with St. Paul by going back and forth [to many places]. He also suffered with him. And after the great Apostles received martyrdom, he passed on what he had heard word for word from our Lord Jesus Christ to the then new Christian generation which arose.   ✞Because he preached the Gospel, gentiles imprisoned, beat, and tried him many times. And at time, they even burned him. However, his Creator used to miraculously save him as He had not departed from him. ✞The Saint captured many souls to Christianity including bandits by going outside the city [where he preached in], from the wilderness and from prisons as well. St. Jason preached for many years and departed [on this day] in a good old age. ✞✞✞Empress Welete Maryam of Ethiopia✞✞✞ =>Also on this day, Blessed Welete Maryam the Ethiopian, our Mother, is commemorated. ✞Welete Maryam was the wife of Emperor Naod, and the mother of Emperor Lebna Dengel and Saint Romane Work. During the years she was Empress (from 1487-1500E.C), as it was a time of famine, many people perished. ✞Nonetheless, Blessed Welete Maryam, in addition to prayer and fasting, saved many of the starved by providing them with food.  She was also praised for leading the royal family to a good Christian life. And on this day, after her passing, she was entombed. ✞✞✞May our God not detach us from the blessings of the Saints. ✞✞✞ Annual feasts celebrated on the 3rd of Ginbot 1. Saint Jason the Apostle (One of the 72 Disciples) 2. Abba Besoy (Bishoy) the Martyr 3. Saint Eusebius the Priest 4. Blessed Welete Maryam, Empress (Mother of Emperor Lebna Dengel) ✞✞✞Monthly Feasts 1. The Entrance of our Lady the Virgin Saint Mary the God-bearer into the Temple 2. Sts. Joachim and Anna 3. Sts. The Arch-Priests (Zacharias and Simeon) 4. Abba Libanos of Mata 5. Abune Zena Markos 6. Abune Medhanine Egzi of Debre Benkol ✞✞✞ “And the seventy returned again with joy, saying, Lord, even the devils are subject unto us through thy name. And he said unto them . . . Behold, I give unto you power to tread on serpents and scorpions, and over all the power of the enemy: and nothing shall by any means hurt you. Notwithstanding in this rejoice not, that the spirits are subject unto you; but rather rejoice, because your names are written in heaven.”✞✞✞ Luke 10:17 ✞✞✞ Salutations to God ✞✞✞ (Translated by Mhr. Esuendale Shemeles with the permission of Dn. Yordanos Abebe) https://t.me/zikirekdusn
2 6148Loading...
17
Media files
2 79937Loading...
18
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ❖ ግንቦት 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት +"+ ቅዱስ ያሶን ሐዋርያ +"+ +ባለንበት ዘመን አሳዛኝ ከሆኑ ነገሮች አንዱ የቅዱሳኑ ስማቸው ከነሥራቸው መዘንጋቱ ነው:: ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ደማቸው እንዳልፈሰሰ: አጥንታቸውም እንዳልተከሰከሰ ይሔው አስታዋሽ አጥተው ስማቸውም ተዘንግቶ ይኖራል:: +አንዳንድ ንፉቃን ደግሞ ከዚሁ ብሶ ጭራሹኑ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ስለ ክርስቶስ ትታ ስለ ቅዱሳኑ ብቻ ትሰብካለች ይሉናል:: +በእጅጉ ከሚያሳዝኑኝ ነገሮች አንዱ የቅዱሳን ሐዋርያት (የ120ው ቤተሰብ) መዘንጋት ነው:: ከ120ው ቤተሰብ የአብዛኞቹ ስም በመዘንጋቱ: ሊቃውንቱም ዝምታን በመምረጣቸው "ያሶን: አርስጦስ: አፍሮዲጡ: ቆሮስ . . . እያልን የ72ቱን አርድእት ስም ስንጠራ ግር የሚለው ዓይነት ትውልድ ተፈጥሯል:: +እስኪ እንዲያው ቢያንስ ሐዋርያትንና ዐበይት ቅዱሳንን እናስባቸው:: አስበናቸው የሚጨመረልን እንጂ የሚጨመርላቸው የለምና:: +ዛሬ የምናስበው ቅዱስ ያሶን ሐዋርያ ከ72ቱ አርድእት አንዱ ነው:: ጌታችንን ከጥምቀቱ በኋላ ተከትሎ ለ3 ዓመታት ከእግሩ ሥር ቁጭ ብሎ ተምሯል:: ከጌታችን ዕርገት በኋላ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ ለስብከተ ወንጌል ወጥቷል:: +ለብዙ ጊዜ ከቅዱስ ዻውሎስ ጋር ተመላልሶ ሰብኳል:: በመከራውም ተካፍሎታል:: ታላላቆቹ ሐዋርያት ሰማዕትነትን ከተቀበሉ በኋላ ለመጣው አዲስ ክርስቲያን ትውልድ ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቃል በቃል የሰማውን አስተላልፏል:: +ወንጌልን ስለ ሰበከላቸው አሕዛብ ብዙ ጊዜ አስረው ይደበድቡት: ያንገላቱት ነበር:: አንዳንድ ጊዜም እሳት እያነደዱ ያቃጥሉት ነበር:: ፈጣሪው ግን በተአምራት እያዳነው ከርሱ ጋር አልተለየም:: +ከከተማ ወጥቶ በዱርና በእስር ቤቶች ብዙ ነፍሳትን: ሽፍቶችንም ሳይቀር ወደ ክርስትና ማርኳል:: ቅዱስ ያሶን ለረዥም ዓመታት ሰብኮ በመልካም ሽምግልና አርፏል:: ❖ ንግሥት ወለተ ማርያም ❖ +ዳግመኛ በዚህ ቀን ኢትዮዽያዊቷ እናታችን ቡርክት ወለተ ማርያም ትታሰባለች:: +ወለተ ማርያም ማለት የደጉ አፄ ናኦድ ሚስት: የአፄ ልብነ ድንግልና የቅድስት ሮማነ ወርቅ እናት ናት:: በንግስትነት በቆየችባቸው ዘመናት (ከ1487-1500 ዓ/ም) የረሃብ ጊዜ በመሆኑ ብዙ ሕዝብ አልቆ ነበር:: +ቡርክት ወለተ ማርያም ከጾምና ከጸሎት ባሻገር የተራቡትን በማብላት ብዙዎችን ታድጋለች:: የንጉሡን ቤተሰብ ወደ መልካም ክርስትና በመምራትም የተመሰገነች ነበረች:: በዚህ ቀንም አርፋ ተቀብራለች:: ❖አምላካችን ከቅዱሳኑ በረከት አይለየን:: ❖ግንቦት 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ ያሶን ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት አንዱ) 2.አባ ብሶይ ሰማዕት 3.ቅዱስ አውሳብዮስ ቀሲስ 4.ቡርክት ወለተ ማርያም ንግሥት (የዐፄ ልብነ ድንግል እናት) ❖ወርኃዊ በዓላት 1፡ በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም 2፡ ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና 3፡ ካህናት ዘካርያስ ወስምዖን 4፡ አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ 5፡ አባ ዜና ማርቆስ 6፡ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ 7፡ ቅዱስ ቄርሎስ ዓምደ ሃይማኖት 8፡ ቅዱስ ስምዖን ዘዓምድ ++"+ ሰብዓውም በደስታ ተመልሰው ጌታ ሆይ! አጋንንት ስንኳ በስምህ ተገዝተውልናል አሉት:: እንዲህም አላቸው . . . እነሆ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችሁአለሁ:: የሚጐዳችሁም ምንም የለም:: ነገር ግን መናፍስት ስለ ተገዙላችሁ በዚህ ደስ አይበላችሁ:: ስማችሁ ግን በሰማያት ስለ ተጻፈ ደስ ይበላችሁ:: +"+ (ሉቃ.10:17) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> https://t.me/zikirekdusn
4 24556Loading...
19
https://youtu.be/INYw4R8sLoU?si=wo1ndv6Gks5ThhU1
4 87825Loading...
20
https://youtu.be/INYw4R8sLoU?si=1Til0BGYs9O2Ryp5
5882Loading...
21
=>የሰላም አምላክ የእርሱን ሰላም (ዮሐ. 14:27) : የድንግል እናቱን ሰላም (ሉቃ. 1:41) : የቅዱሳኑን ሰላም (ማቴ. 10:13) በእኛ ላይ ያሳድርብን:: <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር:: አሜን:: >>> Re. Dn Yordanos Abebe ✝ ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር። " ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/ https://t.me/zikirekdusn
4 83336Loading...
22
✝✞✝ በስመ አብ : ወወልድ : ወመንፈስ ቅዱስ : አሐዱ አምላክ . . . አሜን:: ✝✞✝ ✝ ግብረ-ሰላም ✝ (ከአንድ ወንድም በደረሰኝ ጥያቄ መሠረት ለጊዜው እነዚህን ጉዳዮች ብቻ እንመልከት) "ገብረ ሰላመ በመስቀሉ:: ትንሳኤሁ አግሃደ::" 1." ትርጉም " =>"ግብረ-ሰላም" ማለት "የሰላም : የፍቅር : የአንድነት ተግባር" እንደ ማለት በጥሬው ሊተረጐም ይችላል:: 2." ምንነት " =>ግብረ-ሰላም የጌታን ትንሳኤ ተከትለው በሚመጡ 50 ቀናት የሚከናወን ተግባር ሲሆን መንፈሳዊና ሥጋዊ ድግሶች የሞሉበት ትውፊታዊ ክዋኔ ነው:: 3." መነሻ " =>ቤተ ክርስቲያናችን የሁሉ ነገሯ መሠረት መድኃኔ ዓለምና ትዕዛዛቱ ናቸው:: የግብረ ሰላምም መሠረቱ ቅዱስ መጽሐፍ ነው:: በብሉይ ኪዳን አገልጋይ ካህናትና ነቢያትን መመገብ በጐና የተለመደ ተግባር ነበር:: +ኦሪት ላይ እንደተጻፈው ቅዱስ ኢያሱ ርስትን ሲያካፍል ለካህናት አልሰጣቸውም:: ምክንያቱም የካህናቱ ርስት ሕዝቡ ነበርና:: (ኢያ. 21) በመጽሐፈ ነገሥት 2ኛ ያቺ ደግ ሱነማይት ሴት ለቅዱስ ኤልሳዕን ትመግበው : ታሳድረውም እንደ ነበርም ተጽፏል:: እንዲያውም ቤት ሁሉ ሠርታለታለች:: (2ነገ. 4:8) +በሐዲስ ኪዳን ደግሞ የክብር ባለቤት : አማናዊው ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሰዎች ቤት ገብቶ ግብር ሲያገቡለት (ሲጋበዝ) እንደ ነበር ቅዱስ ወንጌል ይናገራል:: እንደ ማሳያም ቤተ ማርታን (ሉቃ. 10:38) : ቤተ ስምዖን ዘለምጽን (ማቴ. 26:6) : ቤተ አልዓዛር ወኒቆዲሞስን (ዮሐ. 12:1) መጥቀስ እንችላለን:: << ስለዚህ ካህናትን ወደ ቤት ጠርቶ መጋበዙ (ግብረ ሰላም ማድረጉ) መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው:: >> +በተአምረ ኢየሱስ ላይ እንደተጠቀሰው ደግሞ በበዓለ ሃምሳ ካህናትን እንደ አቅሙ (ከ1 ጀምሮ) ያበላ በፍርድ ቀን ከመከራ እንደሚያመልጥ ጌታ መናገሩ ተዘግቧል:: +በተለይ ግን አበው ሐዋርያትን ጌታ እንዲህ ብሏቸዋል ሲል ቅዱስ ማቴዎስ ነግሮናል:: "በምትገቡባትም በማናቸውም ከተማ ወይም መንደር : በዚያ የሚገባው ማን እንደሆነ በጥንቃቄ መርምሩ:: እስክትወጡም ድረስ በዚያ ተቀመጡ:: ወደ ቤትም ስትገቡ ሰላምታ ስጡ:: ቤቱም የሚገባው ቢሆን ሰላማችሁ ይድረስለት:: (ይደርበት) ባይገባው ግን ሰላማችሁ ይመለስላችሁ:: ከማይቀበላችሁም : ቃላችሁንም ከማይሰሙ ሁሉ ከዚያ ቤት ወይም ከዚያች ከተማ ስትወጡ የእግራችሁን ትቢያ አራግፉ:: እውነት እላቹሃለሁ:: በፍርድ ቀን ከዚያች ከተማ ይልቅ ለሰዶምና ለገሞራ አገር ፍርድ ይቀልላቸዋል::" (ማቴ. 10:11) +በተጨማሪም "የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሠር" ያለውን የኦሪት ትዕዛዝ "ይደልዎ አስቦ ለዘይትቀነይ-ለሠራተኛ ደሞዙ ይገባዋል" ሲል ጌታ ተናግሮታል:: የአነጋገሩ ምሥጢር ብዙ ቢሆንም በጥሬው ግን የካህናት ደሞዝ ከምዕመናን መሆኑን ያሳያል:: (ዘዳ.25:4, 1ቆሮ.9:9, ማቴ.10:10 4." አፈጻጸም " =>ግብረ-ሰላም በቤተ ክርስቲያን ዙሪያ (በቤተ ምርፋቅ) ሊከወን ቢችልም ብዙ ጊዜ የሚፈጸመው በምዕመናን ቤት ነው:: ለምን? . . . ቤታቸው በአበው ካህናት ይባረክ ዘንድ ይገባልና:: +ከትንሳኤ ማግስት ጀምሮ ምዕመናን እንደ አቅማቸው:- 1.መምህረ ንስሃ (የነፍስ አባታቸውን) 2.ከደብሩ ካህናት በቁጥር 3.የደብሩን ሁሉ አገልጋዮች 4.የአድባራትን ሊቃውንት . . . ሊጠሩ ይችላሉ:: ባለጠጐች ከሆኑ ብዙ ሊጠሩ ይችላሉ:: የኔ ብጤ የሆነ ደግሞ እንደ አቅሙ ማለት ነው:: +የተጠሩ ካህናት (ሊቃውንት) ወደ ቤት ሲደርሱ የቤቱ አባወራ አደግድጐ : እማወራዋ አገልድመው ከበር ላይ ይጠብቃሉ:: "እንኩዋን ደህና መጣችሁ" እያሉ አስገብተው በየማዕረጋቸው እንዲቀመጡ ይደረጋል:: +ከሁሉ የሚቀድም ጸሎት ነውና ማዕዱ ቀርቦ ጸሎት በርዕሰ ደብሩ ወይም በመምህሩ ይደረጋል:: ሲበላም በመስሪያ (6 ሆነው) ሲሆን ይህም ከ6ቱ ቃላተ ወንጌል ብዙዎቹ የሚከወኑበት መሆኑን ያጠይቃል:: በየመሥሪያው አበው እየቆረሱ "በእንተ ማርያም" ሰጥተው በሥርዓት ይበላል:: +መጠጥም (ወይን : ጠላ : ጠጅ ወይም ሌላ ሊሆን ይችላል) ጐን ለጐን ይቀርባል:: አጥንት ካለ እንደየ ማዕርጋቸው ለመምህራንና ለአበው ፍሪምባ : ቅልጥም ለምክትል መምህራን ወዘተ. ተሰጥቶ በቃለ ማኅዘኒ "ስብሐት ለአብ" ተብሎ እግዚአብሔር ይመሰገናል:: +መምህሩ አፉን አጥርቶ ትምህርት ከሰጠ በሁዋላ አበው እየተነሱ ይመርቃሉ:: የዜማ መምህራን በበኩላቸው የክርስቶስን ትንሳኤና የማዳን ሥራ የሚያዘክሩ ወረቦችን እየቃኙ ይወርባሉ:: ይቸበችባሉ:: በመጨረሻም ኑዛዜ ተሰጥቶ ስንብት ይሆናል:: +አበውና ካህናት "ስብሐት" ብለው ያተረፉትንም የቤቱ ባለቤቶች : ሕጻናትና ጐረቤት ሁሉ በደስታ ተካፍሎ ይበላዋል:: እጅግ ታላቅ በረከት ነውና:: 5." ግብረ-ሰላም በትውፊት " =>ይህ መንፈሳዊ ተግባር ምንም እንኩዋ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቢሆንም በቤተ ክርስቲያንና በሃገራችን ታሪክም ተዘግቦ የሚገኝ : ለባለጠጐች : ለመሣፍንቱና ለነገሥታቱ ከነ ስሙም "ግብር ማግባት" የሚባል ነበር:: +በዘመነ ሐዋርያትና ሰማዕታት አገልጋይ ካህናትን ሰብስቦ መጋበዙ የሚታሰብ አልነበረም:: ምክንያቱም ጊዜው የመከራና ክርስቲያኖች መብታቸው የተነፈገበት ነበርና:: +ከዘመነ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ወዲህ ግን ተመሳሳይ ግብር የማግባት (የግብረ ሰላም) ተግባራት እንደ ነበሩ ይታመናል:: እንደ ምሳሌም በ4ኛውና 5ኛው መቶ ክ/ዘ የነበሩ ደጋግ ነገሥታት (እነ ቴዎዶስዮስ 1ኛና 2ኛ : አርቃድዮስ : አኖሬዎስ : ዘይኑን እና አንስጣስዮስ) እንዲሁ ያደርጉ እንደ ነበር ገድላተ ቅዱሳን ያሳያሉ:: +በሃገራችን ኢትዮዽያም ከብሉይ ኪዳን ሲያያዝ የመጣው ተግባር በክርስትና ጸንቶ መቀጠሉን በነገሥታቱ ዜና መዋዕሎች ላይ መመልከት ይቻላል:: ሁሉም ነገሥታት ይህንን ያደርጉ ነበር ብሎ መናገር የሚቻልም ይመስለኛል:: በሕዝቡ ደረጃም አበው እና እማት ይህንን ሲከውኑ እዚህ ደርሰናል:: 6." ዛሬስ " =>ግብረ-ሰላም ዛሬም በትውፊታዊ ሥርዓቱ ቀጥሎ በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች ይከወናል:: በተለይ ደግሞ በሰሜኑ አካባቢ:: ነገር ግን አፈጻጸሙ ላይ ከሚታዩ ስሕተቶች የተነሳ ለጊዜውም ቢሆን እያስነቀፈን ይገኛል:: 1.የተግባሩን መንፈሳዊነት ያልተረዱ አንዳንድ ምዕመናን . . . ሲጀመር "እንካ ብላ : አፈር ብላ" ዓይነት ግብዣ እያደረጉ አበው ካህናትን ሲያቀሉ ተመልክተናል:: 2.በአንድ ጊዜ ጠጅ : ጠላ : አረቄ እና ውስኪን ቀላቅለው የሚጋብዙ እንዳሉም ሰምቻለሁ:: 3.በአንዳንድ ቦታዎች ደግሞ "ማኅሌተ ገንቦ" በሚል ኃጢአት የሆነውን ዘፈን የሚሞክሩም አይጠፉምና "ቢታሰብበት!" ባይ ነኝ:: ☞ዘንድሮ (በ2012) ደግሞ ባብዛኛው በኮሮና ቫይረስ ሰበብ ቀርቷል ብሎ ለመናገር በሚያስደፍር ደረጃ ላይ መድረሱን ታዝቤአለሁ፡፡ አንዳንድ ደጋግ ሰዎች ለበረከት ቢያደርጉትም፡፡ +ይህንን የመሰለ መጽሐፋዊ : ትውፊታዊና ታሪካዊ የበረከት ሃብታችንን በሥርዓቱ ማስቀጠል ብንችል . . . ወዲህ እንጠቀማለን:: ወዲያ ደግሞ ለትውልድ እናስተላልፋለን:: ‹‹የእግዚአብሔር ሙላቱ በእርሱ እንዲኖር በእርሱ በኩል በመስቀሉ ደም ሰላም አድርጎ በምድር ያሉት ሁሉ ለራሱ እንዲያስታርቅ ፈቅዷልና ›› (ቆላ. 1:19-20)
4 00875Loading...
23
Media files
5 30621Loading...
24
Media files
3 28322Loading...
25
🛑ዕለተ ዐርብ🛑። ✝በእውነት አብያተክርስቲያናትን ቸሩ ይጠብቅልን በቸርነቱ ይማረን።✝ ✞✝ እንኩዋን ለዕለተ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንና ለነፍሳተ ብሉይ ዓመታዊ የመታሠቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✝✞✝ =>ከትንሳኤ ሳምንት ቀናት ይህች ዕለት ቤተ ክርስቲያን አንድም ነፍሳት በመባል ትታወቃለች:: ✝ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ✝ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዓለም ሳይፈጠር በአምላክ ልቡና ታስባ : በዓለመ መላእክት ከታየች በኋላ:- ¤አበው ተስፋ ሲያደርጓት ¤ነቢያት ትንቢት ሲናገሩላት ¤ሱባኤ ሲቆጥሩላት ¤ምሳሌም ሲመስሉላት ኑረዋል:: ††† ዘመኑ በደረሰ ጊዜ በአምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ :- ¤በመጸነሱ ተጸንሳ ¤በመወለዱ ተወልዳ ¤በጥበብና በሞገስ አብራው አድጋ ¤በጥምቀቱ ተጠምቃ ¤በትምሕርቱ ጸንታ ¤በደሙ ተቀድሳ ¤በትንሣኤው ከብራ ¤በዕርገቱ ሰማያዊነቷን አጽንታ ¤በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስ ወርዶላት በይፋ ለልጆቿ ተሰጥታለች:: ድንገት የተመሠረተች ሳትሆን ቅድመ ዓለም በአምላክ ልቡና የታሠበች: በዓለመ መላእክት የተወጠነች ናት:: በአማን ጐልታ: ግዘፍ ነስታ የተመሠረተችው ግን በደመ ክርስቶስ ተቀድሳ: በትንሳኤው ከብራ: ንጽሕትና ጽሪት ባደረጋት ጊዜ ነው:: መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ባይነሳ ኖሮ ቤተ ክርስቲያን ሕልውና አይኖራትም ነበርና ይህች ዕለት ቤተ ክርስቲያን ተብላ ትከበራለች:: ✝ ነፍሳት ✝ =>በብሉይ ኪዳን የነበሩና ለ5,500 ዓመታት በሲዖል የተጋዙ ሰዎችን ያመለክታል:: እነርሱም ከአባታችን አዳም ጀምሮ በዓመተ ኩነኔ የነበሩ ሰዋች ሲሆኑ ደመ ክርስቶስ ቀድሷቸው: የትንሳኤው ብርሃን ደርሷቸው ወደ ገነት ስለ ገቡ በዚሁ ቀን ይታሠባሉ:: =>እግዚአብሔር ከአባቶች ነፍስና ከቅድስት ቤቱ በረከት አይለየን:: =>+" መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ: ተቀበረም:: መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነስቷል...  ከዚያም በሁዋላ ለያዕቆብ: ሁዋላም ለሐዋርያት ሁሉ ታየ:: ከሁሉም በሁዋላ እንደ ጭንጋፍ ለምሆን ለእኔ ደግሞ ታየኝ:: እኔ ከሐዋርያት ሁሉ የማንስ ነኝና:: የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ስላሳደድሁ ሐዋርያ ተብየ ልጠራ የማይገባኝ: ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ የሆንሁ እኔ ነኝ:: "+ (1ቆሮ. 15:3-10)    <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
4 33845Loading...
26
የቅዱስ ኢዮብ ቤተክርስቲያን ሊባኖስ ።
4 39024Loading...
27
💠"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"💠    /(ማቴ ፫:፫/) ✝እንኳን አደረሰን! 🛑 ዝክረ ቅዱሳንን ላልደረሳቸው  እናድርስ እናስፋ ስለ ሀገራችን እንጸልይ ንስሐ እንግባ!!🛑 ✝ 5 ነገሮችን በደንብ ያዙ።     1, 🛑አላማ     2 ,🛑እምነት     3,🛑ጥረት     4 🛑ጥንቃቄ      5🛑ጽናት =>እነዚህን ያዟቸው ተጠቀሙባቸዉ ኑሯቸው። ❇️9ኙ የቅድስና መንገዶች❇️ ፩👉ሃይማኖት ፪👉ጾም ፫👉ጸሎት ፬👉ስግደት ፭👉ምጽዋት ፮👉ፍቅር ፯👉ትህትና ፰👉ትዕግስት ፱👉የዋህነት ✝ንስሐ የተጣመመውን ያቀናል።በኃጥያት የቆሸሸውን ያነጻል፤ንስሐ ለሚገቡ ሁሉ የመላዕክት ንጹሕ ልብስ ይሰጣችኃል።         (ቅዱስ መቃርስ )   ንስሐ ግቡ።✝ ዝክረቅዱሳን (ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት) " ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::        አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/ 🛑በዩቲብለመከታተል👉https://www.youtube.com/@ZikereKedusan 🛑በቴሌግራም👉https://t.me/zikirekdusn 👉 ግእዝ መማር የምትሹ https://t.me/lisanegeez5
4 35223Loading...
28
Media files
3 95028Loading...
29
Media files
10Loading...
30
የቅዱስ ኢዮብ ቤተክርስቲያን ሊባኖስ ።
10Loading...
31
#Feasts of #Ginbot_2 ✞✞✞On this day we commemorate the departure of Saint Job the Man of Patience✞✞✞ ✞✞✞In the name of the Father, the Son and the Holy Spirit, one God. Amen!✞✞✞ ✞✞✞Saint Job✞✞✞ =>There was nothing as we see in the Bible that St. Job, the father of patience, was not tested by. The Saint’s genealogy is drawn from Abraham [as follows]. *Abraham begot Isaac *Isaac begot Esau *Esau begot Reuel *Reuel begot Zerah *And Zerah begot Job. ✞St. Job lived while Israelites were in bondage in Egypt. He was very wealthy – lacking nothing, kind, and a worshipper of God. The kindness of Job was not attested by the words of mere men (mortals). Rather, it was attested to by the Creator Himself. ✞Nevertheless, the Devil, who was jealous of this, asked permission from God to try Job. And as the Lord had wanted to reveal the Saint’s forbearance, Satan destroyed Job’s wealth. And in one day, he became poor. However, he blessed his Creator. ✞And Satan continued, he took away (killed) the fruits of his loins (his children). Still, Job expressed gratitude [to God]. ✞The third time, the Devil smote his body with boils. And the lesions were not as those that you see today. But they were severe, beyond the abilities of a man. And the Saint, while suffering for an age that amounts to a young man’s life, used to scrape his body with an ostracon (a potsherd). Nonetheless, he did not stop thanking God. ✞Finally, Satan came through his wife. And she said, “Curse God”. But he answered saying, “The Lord gave, and the Lord hath taken away; blessed be the name of the Lord.” ✞After all these things, God removed Satan from the Saint’s path. He then gave him back his health, wealth and children. And added 140 years to his age. The righteous and long-suffering man, St. Job, at the age of 248, passed away on this day. =>May God, our Lord, not detach us from the Saint’s persistence and blessing. ✞✞✞ Annual feasts celebrated on the 2nd of Ginbot 1. Saint Job the Righteous (The Father of Patience) 2. Abba Tadros (Theodore) the Abbot 3. The 22 Martyrs (The Followers of Abba Esi) ✞✞✞ Monthly Feasts 1. St. John the Baptist 2. St. Thaddeus the Apostle 3. St. Abel the Righteous 4. St. Abba Paul the Hermit (The Great) 5. St. Severus of Antioch 6. Abba Heryakos of Behensa ✞✞✞ “Take, my brethren, the prophets, who have spoken in the name of the Lord, for an example of suffering affliction, and of patience. Behold, we count them happy which endure. Ye have heard of the patience of Job, and have seen the end of the Lord; that the Lord is very pitiful, and of tender mercy.”✞✞✞ Jas. 5:10-11 ✞✞✞ Salutations to God ✞✞✞ (Translated by Mhr. Esuendale Shemeles with the permission of Dn. Yordanos Abebe) https://t.me/zikirekdusn
3 6918Loading...
✝✝✝ እንኩዋን ለዳግሚያ ትንሳኤ በሰላም አደረሳችሁ ✝✝✝ =>ለስም አጠራሩ ጌትነት ይድረሰውና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅድስት ትንሳኤው በሁዋላ ለደቀ መዛሙርቱ በጉባኤ 3 ጊዜ ተገልጦላቸዋል:- 1.በዕለተ ትንሳኤ ምሽት በፍርሃት ሳሉ 2.ያላመነ ቶማስን ለማሳመን በተነሳ በ8ኛው ቀን (ማለትም ዛሬ) 3.ከተነሳ ከ23 ቀናት በሁዋላ በጥብርያዶስ ባሕር ዳርቻ ላይ ነው:: +ጌታ አርባውን ቀን ለአንዱም: ለሁለቱም በግል ይገለጥላቸው ነበር:: እመቤታችንን ግን ፈጽሞ አይለያትም ነበር:: +ጌታችን ከተነሳ በሁዋላ ለሳምንት ተለይቷቸው ስለ ነበር በቤተ ክርስቲያን ውዳሴ ማርያም እንጂ መልክዐ ኢየሱስ በማሕበር አይደገምም:: +በዚሕች ዕለት ደቀ መዛሙርቱ በጽርሐ ጽዮን ሳሉ ጌታችን "ሰላም ለእናንተ ይሁን" ብሏቸዋል:: ቶማስንም "ና ዳስሰኝ" ብሎታል:: ሐዋርያው እጁን ከተወጋ ጐኑ ላይ ቢያሳርፍ በመቃጠሉ "ጌታየ አምላኬም" ሲል ጮሆ ምስጢረ ተዋሕዶውን መስክሯል:: +ጌታም ቶማስን "እስመ ርኢከኒሁ አመንከኒ" (ማለትም ስላየኸኝ አመንከኝ)! "ብጹዐንሰ እለ እንዘ ኢይሬእዩኒ የአምኑኒ" (ሳያዩ የሚያምኑ ግን ብጹዐን (ማለትም ንዑዳን ክቡራን) ናቸው ብሎታል:: (ዮሐ. 20:24) =>ከጌታችን ከትንሳኤው: ከቅዱሱም ሐዋርያ በረከት አይለየን:: =>+"+ ደጆች ተዘግተው ሳሉ ኢየሱስ መጣ:: በመካከላቸውም ቆሞ 'ሰላም ለእናንተ ይሁን' አላቸው:: ከዚያም በሁዋላ ቶማስን 'ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ:: እጅህንም አምጣና በጐኔ አግባው:: ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን' አለው:: ቶማስም 'ጌታዬ አምላኬም' ብሎ መለሰለት:: ኢየሱስም 'ስላየኸኝ አምነሃል:: ሳያዩ የሚያምኑ ብጹዓን ናቸው' አለው:: +"+ (ዮሐ. 20:26-29)    <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
إظهار الكل...
ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት - ዘብሔረ ጎንደር (ዲ/ዮርዳኖስ አበበ)

በዚህ ቻናል ዲ/ዮርዳኖስ የሚያስተምራቸው ወቅታዊ እና የነገረ ቅዱሳን (ዝክረ ቅዱሳን ትምህርቶችን ከእርሱ በመቀበል እናስተላልፋለን):: "ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/

Photo unavailableShow in Telegram