ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

الذهاب إلى القناة على Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

إظهار المزيد

📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

تُعد قناة Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 16 042 مشتركاً، محتلاً المرتبة 5 280 في فئة الدين والقيم الروحية والمرتبة 2 240 في منطقة Ethiopia.

📊 مؤشرات الجمهور والحراك

منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 16 042 مشتركاً.

بحسب آخر البيانات بتاريخ 29 أكتوبر, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار 518، وفي آخر 24 ساعة بمقدار 1، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.

  • حالة التحقق: غير موثّقة
  • معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 25.50‎%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 10.35‎% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
  • وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 4 090 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 1 660 مشاهدة.
  • التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 33.

📝 الوصف وسياسة المحتوى

يصف المؤلف القناة بأنها مساحة للتعبير عن الآراء الذاتية:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 30 أكتوبر, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة الدين والقيم الروحية.

16 042
المشتركون
+124 ساعات
+917 أيام
+51830 أيام
أرشيف المشاركات
ሃሌ ሃሌ ሉያ ለቤተ ክርስቲያን፤ ሐነፃ ላሊበላ ለቤተ ክርስቲያን፡፡ /ወረብ ዘሸዋ፤ በየካ ሚካኤል በሰኔ የሚወረብ የቤቱ የሸዋ ወረብ ቀለም/፤ ዛሬ የሐናፄ መቅዱስ ቅዱስ ላሊበላ(ላልይበላል) ክብረ በዓሉ ነው፡፡

ሰኔ ቅዱስ ሚካኤልና ሥርዐተ ማኅሌት፡፡ #ሰኔ_፲፪ #መከበሩ_ስለምንድን_ነው_ቢሉ_፤ ከጽንፍ እስከ ጽንፍ የሚበር፤ ንሥረ አርያም የሚባል፥ ውዳሴው እንደ ማር የጣፈጠ፥ ንዑድ ክቡር የሆነ ፥ የመላእክት ሁሉ አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ፭ት ነገሮችን የፈጸመበት እለት ስለኾነና የሌሎችም ቅዱሳን መታሰቢያ ቀናቸው ስለኾነ ነው፡፡ እነርሱም፤ ፠፩. በዓለ ሲመቱ ለቅዱስ ሚካኤል፤ ፠፪. ባሕራንን ያዳነበት፤ ፠፫. የአስተራኒቆስ ሚስት ቅድስት አፎምያን ያዳነበት፤ በዓለ እረፍቷም በዚሁ እለት ነው፤ ፠፬. በግብፅ ሃገር ፓትርያርክ እለ እስክንድሮስ ቅዳሴ ቤቱን ያከበረበት፤ ፠፭. ቅዱስ ላሊበላን ወደ ሰማያት ነጥቆ ወስዶ ያሳየበት፤ ፠ሐናፄ መቅደስና በሰማያት ያለ ምሥጢርን የተመለከተ ቅዱስ ላሊበላ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ በዓለ ዕረፍቱ ነው፤ ፠67ኛ ሊቀ ጳጳስ ቄርሎስ ሊቀ ዻዻሳት ዘእስክንድርያ እረፍቱ ነው፤ ፠የእስክንድርያ 6ኛ ሊቃነ ጳጳሳት አባ ዮስጦስ (ወንጌላዊና ሐዋርያው ቅዱስ ማርቆስ የክርስትና ጥምቀትን ያጠመቀው፥ ዲቁናና ቅስናን የሾመው) እረፍቱ ነው፡፡

ሰኔ ቅዱስ ሚካኤልና ሥርዐተ ማኅሌት፡፡ #ሰኔ_፲፪#መከበሩ_ስለምንድን_ነው_ቢሉ_፤ ከጽንፍ እስከ ጽንፍ የሚበር፤ ንሥረ አርያም የሚባል፥ ውዳሴው እንደ ማር የጣፈጠ፥ ንዑድ ክቡር የሆነ ፥ የመላእክት ሁሉ አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ፭ት ነገሮችን የፈጸመበት እለት ስለኾነና የሌሎችም ቅዱሳን መታሰቢያ ቀናቸው ስለኾነ ነው፡፡ እነርሱም፤ ፠፩. በዓለ ሲመቱ ለቅዱስ ሚካኤል፤ ፠፪. ባሕራንን ያዳነበት፤ ፠፫. የአስተራኒቆስ ሚስት ቅድስት አፎምያን ያዳነበት፤ በዓለ እረፍቷም በዚሁ እለት ነው፤ ፠፬. በግብፅ ሃገር ፓትርያርክ እለ እስክንድሮስ ቅዳሴ ቤቱን ያከበረበት፤ ፠፭. ቅዱስ ላሊበላን ወደ ሰማያት ነጥቆ ወስዶ ያሳየበት፤ ፠ሐናፄ መቅደስና በሰማያት ያለ ምሥጢርን የተመለከተ ቅዱስ ላሊበላ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ በዓለ ዕረፍቱ ነው፤ ፠67ኛ ሊቀ ጳጳስ ቄርሎስ ሊቀ ዻዻሳት ዘእስክንድርያ እረፍቱ ነው፤ ፠የእስክንድርያ 6ኛ ሊቃነ ጳጳሳት አባ ዮስጦስ (ወንጌላዊና ሐዋርያው ቅዱስ ማርቆስ የክርስትና ጥምቀትን ያጠመቀው፥ ዲቁናና ቅስናን የሾመው) እረፍቱ ነው፡፡

በመዲና ከተማችን የሊቀ መልአኩ የቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓል የሚከብርባቸው ገዳማትና አድባራትን እንጠቁማችሁ፡፡ /ፎቷቸውን ያልለጠፍናቸውና ስማቸውን ያልጠቀስናቸውን እንድትልኩልን በሊቀ መልአኩ ስም እንጠይቃለን) 1. *የካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን (ሾላ፤ መገናኛ) 2. *አንቀጸ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል /ጭቁኑ/፤ ፈረንሳይ 3. *ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል (አዲሱ ሚካኤል)፤ አውቶብስ ተራ 4. *ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል፤ /ቦሌ/ 5. *ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ሚካኤል፤ /ላፍቶ/ 6. *ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል፤ (መካኒሣ) 7. *ኮተቤ ደብረ ጽባሕ ቅዱስ ሚካኤል /ሳጠራው/ (ቀድሞ ኮተቤ አሁን ሲምሲ) 8. *ደብረ ምሕረት ሚካኤል (ቀድሞ ወህኒ ቤት ሚካኤል) 9. *መካነ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል 10. *ገነተ አምባ ቅዱስ ሚካኤል 11. *ደብረ ኢዮር ቅዱስ ሚካኤል 12. *ካራ ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ሚካኤልና 24ቱ ካህናተ ሰማይ 13. *ሐያት ጨፌ ኢያሪኮ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን (በ1980ዓ.ም ጽላቱ ከነ ድርሳናቱ ተቀብሮ የተገኘበት) 14. *መንበረ ክብር ቅዱስ ሚካኤል ወአቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም /ኋላ ወቅድስት አርሴማ በሚል እየተጠራ የሚገኝ/፤ (በቀጨኔ በአዲሱ ገበያና በእንጦጦ መሃል ጉብታ ላይ የሚገኝ) እንዲሁም በድርብነት 1. *እንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት 2. *መንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ (ስድስትኪሎ) 3. *ደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ (መስቀል አደባባይ) 4. *ጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ቤ.ክ (ኋላ ጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል በሚል እየተጠራ የሚገኘው)፤ (ኢምግሬሽን አጠገብ) 5. *ደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ (ኋላ ወመካነ ጎልጎታ ቅድስት ድንግል ማርያም በሚል እየተጠራ የሚገኝ)

#በዓለ_ጰራቅሊጦስ፤ /ከቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ሰሌዳ መጽሔት የተወሰደ/ ሥርዐተ ማኅሌቱ በዓለ ጳራቅሊጦስ ከ፱ኙ ዐበይት በዓላተ እግዚእ አንዱ እንደመኾኑ በኹሉም ገዳማትና አድባራት ይከበራል፤ ነገር ግን ታቦተ ሕጉ ወጥቶ በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች በሐዋርያትና በመንፈስ ቅዱስ ስም በተሰየሙ አብያ ክርስቲያናት ይከበራል፤ ይልቁንም በአዲስ አበባ ብቸኛ በኾነው #በጽርሐ_ጽዮን_ሐዋርያት_መንፈስ_ቅዱስና_/ኋላ/#ጎላ_ሚካኤል_ (ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል አገብ) ቤተ ክርስቲያን ይከበራል፡፡ ጰራቅሊጦስ ማለት መንጽሒ (የሚያነጻ)፥ መጽንዒ (የሚያጸና)፥ መስተፈሥሒ (ደስታን የሚሰጥ)፣ መስተሥርይ (ኀጢአትን ይቅር የሚል)፣ ናዛዚ (የሚያረጋጋ)፣ ከሣቲ (ምሥጢርን የሚገልጥ) የሚል ትርጕምን ይሰጣል (መጻሕፍተ ሠለስቱ ሐዲሳት፣ ገጽ ፪፻፹፫)፡፡ ይኸውም መንፈስ ቅዱስ በኀጢአት ጭቃ የወደቁትንና የሚወድቁትን እንደሚያነጻቸው፤ በመንፈሳዊ ተጋድሎ ላሉት ኹሉ በፈተናቸውና በመከራቸው ኹሉ እንደሚያበረታቸው (እንደሚያጸናቸው)፤ የሚነዋወፁትን እንደሚያረጋጋቸው፤ ያዘኑትን እንደሚያጽናናቸው፤ የሚደክሙትን እንደሚያበረታቸው፤ የተከዙትንም ሐሴትን እንደሚሰጣቸው የሚያስገነዝብ ነው፡፡ ጻድቃንን ወደ ተጋድሎ፤ ሰማዕታትን ወደ ደም፣ መነኰሳትን ወደ ገዳም፣ ማኅበረ ክርስቶስንም ወደ ቤተ ክርስቲያን ልቡናቸውን የሚያነሣሣና የሚመራ እርሱ መንፈስ ቅዱስ ነው፤ /ዮሐ.፲፮፥፲፪/፡፡ #በዓለ_ሃምሳ_በብሉይ እስራኤል ዘሥጋ በዓለ ኃምሳን የሚያከብሩት ስለ ብዙ ምክንያት ነው፡፡ ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያኽልም፤ ፩ኛ) ከምድረ ግብጽ ከወጡ በኋላ ምድረ ከነዓን ገብተው ለመዠመርያ ጊዜ እሸት የበሉበትን የሚዘክሩበት ነው፡፡ ዳግመኛም በበረኻ ሳሉ እግዚአብሔር ከሰማያት ኅብስተ መናን አውርዶ፥ ከጭንጫ ውኃን አመንጭቶ እንደመገባቸው ይዘክሩበታል፡፡ በመኾኑም በዚኽ በዓል ቀዳምያት፥ ዐሥራትና በኵራት እያወጡ፣ በየዓመቱ ከሚዘሩት እኽል እሸት (በብዛት ስንዴ) እየበሉ እግዚአብሔርን ስለ ምድር ፍሬ የሚያመሰግኑበት በዓል ነው፡፡ ፪ኛ) እግዚአብሔር ከግብጽ ባርነት ካወጣቸው በኋላ በሃምሳኛው ቀን በደብረ ሲና ሕገ ኦሪትን ስለተቀበሉበት ይኽን ያስቡበታል፡፡ ፫ኛ) እግዚአብሔር ከምድረ ግብጽ በታላላቅ ገቢረ ተአምራት ስላወጣቸው ይኽን ያስቡበታል፡፡ ከላይ ለመግለጥ እንደተሞከረው ይኽ በዓል እኽል በሚታጨድበት በመከር ወቅት የሚከበር በዓል ነው፡፡ መከር ሲገባ መጀመርያ ከሚሰበስቡት እኽል ለእግዚአብሔር መሥዋዕት እንዲያቀርቡ ታዝዘው ነበር /ዘጸ. ፳፫፡፲፮/፡፡ በመኾኑም ከበዓለ ፋሲካ ጀምረው ሰባት ሳምንታት (፵፱ ቀናት) በየዕለቱ አንድ መስፈርያ እኽል ይሰጡ ነበር፡፡ በ፶ኛው ቀን ደግሞ ሊቀ ካህኑ ከተሰበሰበው እኽል በትልቅ መስፈርያ አድርጎ ካቀረበ በኋላ መሥዋዕተ በግ ይሠዋ ስለነበር ታላቅ በዓል ኾኖ ይከበር ነበር /ዘሌ. ፳፫፥፲-፲፯፣ ዘዳ. ፲፪፥፭-፯/፡፡ ***አማናዊ ትርጓሜ - በሐዲስ ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ድኅነተ ዓለምን በፈጸመበት ዓመት ግን፥ እስራኤል ዘሥጋ ከላይ በገለጥነው መንገድ ከያሉበት ተሰባስበው በዓሉን በኢየሩሳሌም ሲያከበሩ፤ ለእሥራኤል ዘሥጋና ለእሥራኤል ዘነፍስ ብርሃን እንዲኾኑ የመረጣቸው ሐዋርያትም ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የነገራቸውን ተስፋ እየተጠባበቁ በደብረ ጽዮን በቅዱስ ማርቆስ እናት በማርያም ቤት ተሰባስበው ነበር /ሉቃ. ፳፬፡፵፱/፡፡ በዓለ ሃምሳ የተባለው ቀን በደረሰ ጊዜም ከወደ ሰማይ እንደ ዓውሎ ነፋስ ድምፅ ያለ ድምፅ ነጕዶ ተሰማ፤ መንፈስ ቅዱስ ነበር፡፡ በዚኽም ብሉይና ሐዲስ ተገናኙ፤ ተተካኩ፡፡ የነቢያት ትንቢታቸው፥ የሐዋርያትም ስብከታቸው የኾነው ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነቢያትንና ሐዋርያትን በደብረ ታቦር ተራራ እንዳገናኛቸው፥ በዚያም ክብረ መንግሥቱን፥ ብርሃነ መለኮቱን እንደገለጸላቸው የሚታወስ ነው /ማቴ. ፲፮፡፩-፯/፡፡ በምሴተ ኀሙስም በቤተ አልዓኣዛር የብሉይ ፋሲካን እንዳዘጋጁና እርሱም መሥዋዕተ ብሉይን በመሥዋዕተ ሐዲስ እንደተካው የተጻፈ ነው /ማቴ. ፳፮፡፲፯-፳፱/፡፡ በበዓለ ኃምሳ የኾነውም ልክ እንደዚኹ ነው /ሐዋ. ፪/፡፡ ይኽ ኹሉ በኢየሩሳሌም፣ በመዠመርያዪቱ ቤተ ክርስቲያን በተሰየመች በቤተ ማርያም (የማርቆስ እናት) ተፈጸመ፡፡ ቤተ ክርስቲያን ለፊተኞችም ለኋለኞችም እናታቸው እንደኾነችም ታወቀ፤ ተረዳ፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት በዲድስቅልያ ፴፩ ላይ፡- “ከዕርገቱ ቀን በኋላ ታላቅ በዓል ይደረግ፤ በዚኽች ቀን በሦስተኛው ሰዓት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጰራቅሊጦስን ልኮልናልና እኛም በርሱ ስጦታዎች ተሞላን፤ አዳዲስ ቋንቋም ተናገርን” በማለት በዓሉን በቤተ ክርስቲያን ልናከብረው እንዲገባ ሥርዐት ሐዋርያት የሠሩልንም ስለዚኹ ነው፡፡ በነቢያትና በሐዋርያት መሠረት የታነጸችው ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችንም ይኽንኑ በዓል ከጌታችን ዘጠኝ ዐበይት በዓላት አንዱ በማድረግ በድምቀት ታከብረዋለች፡፡ #ርደተ_መንፈስ_ቅዱስ ጌታችን እንደነገራቸው መቶ ሃያው ቤተ ሰብእ በቤተ ማርያም ኀይልን ከአርያም እስኪለብሱ ድረስ ተሰብስበው ነበር፡፡ በትዕግሥት ከመጠበቅ ውጪ መንፈስ ቅዱስ መቼ እንደሚወርድም አያውቁም ነበር /ሐዋ. ፪፥፪/፡፡ ጌታችን ባረገ በዐሥረኛው ቀን ግን እኔና እናንተ እንደምንሰማው ዓይነት ያይደለ፥ ነገር ግን ከወደ ሰማይ እንደ ዓውሎ ነፋስ ድምፅ ያለ ድምፅ ነጕዶ ተሰማ፡፡ ያሉበትን ቤት ሞላው፡፡ ላንቃ ላንቃ ያለው እሳት ኾኖ ታያቸው፡፡ በበደልን ጊዜ ከእኛ ርቆ ነበርና አኹን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ስለታረቅን በኹሉም አደረባቸው: /ማቴ. ፫፡፲፩/፡፡ ኀይል የሚኾናቸው ሀብትን፣ ሀብት የሚኾናቸው ዕውቀትን ገንዘብ አደረጉ፡፡ #መንፈስ_ቅዱስ መንፈስ ቅዱስ ከሦስቱ አካላተ ሥላሴ አንዱ ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ ከአብና ከወልድ ጋር የሚሠለስ የሚቀደስ የባሕርይ አምላክ ነው፡፡ እንደ አብና ወልድ ፍጹም ገጽ፥ ፍጹም መልክዕ፥ ፍጹም አካል አለው፡፡ መንፈስ ቅዱስ አካላዊ እንጂ ሕጹጽ (ብትን፣ ዝርው) አይደለም፡፡ በተለየ ግብሩም መሥረፅ (መውጣት) ነው፤ መሥረጹም ከአብ ብቻ እንጂ አንዳንዶች (ካቶሊኮችና መካነ ኢየሱሶች) እንደሚሉት ከወልድም ጭምር አይደለም /ዮሐ.፲፭፡፳፮/፡፡ መንፈስ ቅዱስ ቢሠርፅ እንጂ አያሠርጽም፤ አይወልድም፤ አይወለድም፡፡ በባሕርይ፥ በመለኮት፥ በሥልጣን፥ በሕልውና፥ በአገዛዝ፥ ዓለማትን በመፍጠርና በማሳለፍ ከአብና ከወልድ ጋራ የተካከለ ነው /ጸሎተ ሃይማኖት/፡፡ ቀዳሚነትም ኾነ ተቀዳሚነት የሌለው ይልቁንም ከአብና ከወልድ ጋር የተካከለ (ዕሩይ) ነው፡፡ ከአብና ከወልድ ጋር ዓለም ሳይፈጠር ፥ ዘመን ሳይቈጠር ይህ ነው በማይበል ዘመን የነበረ ቀዳማዊ፤ ከአብና ከወልድ ጋር አሁንም ያለ ማዕከላዊ፤ ከአብና ከወልድ ጋር አብሮ ተካክሎ ይህ ነው ለማይባል ዘመን ወደፊት የሚኖር ደኃራዊ ነው፡፡ /የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት/

ጾመ ሐዋርያት (የሰኔ ጾም) ፤ ከባለ 3 ገጹ የፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ሰሌዳ መጽሔት ላይ የተወሰደ፡፡

ጾመ ሐዋርያት (የሰኔ ጾም) ፤ ከባለ 3 ገጹ የፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ሰሌዳ መጽሔት ላይ የተወሰደ፡፡

(ከታች ያሉትን 2ት ፍሬ ነገሮች ለታሪክ ማስታወሻነት እንዲሆኑ፤ በፈለጋችሁት የቅኔ መንገድና የቅኔ ቤት ዝረፏት /አሰናኟት/፡፡) #አቡነ_ኤልሳዕን_ባሰብን_ጊዜ_፤ _ ፩#ነቢዩ ኤልሳዕ በሠረገላ ከተጓዘው ከመምህሩ ከኤልያስ የዮርዳኖስ ባሕርን ተሻግሮ በረከትን እንደተቀበለ፤ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕም በገላውዴዎስ ታቦት ሠረገላ ከሚባርኩት ከመምህሮቹ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት (ቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት) እጅ የዐባይን ወንዝ ተሻግሮ /በበዓለ ዕረፍቱ ቀን/ በረከትን ተቀበለ፤ በዓለ ዕረፍቱን አስባረክ፡፡ ፪#፠ፓትርያርኩና ጳጳሳቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባን አቋርጠው አቡነ ኤልሳዕ ዕድሜ ዘመናቸውን ይወዱት ወደ ነበረውና ወዳሠሩት የቅዱስ ገላውዴዎስ ቤ/ክ በመሄድ በመገረምና በመደነቅ እንዲህ እያሉ በውዳሴና በቅዳሴ፤ በቡራኬና በማኅሌት ሥርዐተ ግብዐተ መሬቱን አከናወኑ፤ * ታላቁ አባታችን ሆይ ተለይህን!? * መምህራችን ሆይ ዝም አልክን!? * መካሪያችን ሆይ ጸጥታን መረጥክን!? ፠ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በጎን እያለቀሱ ፥ በጎን የያሬድን ዜማ እያፈሰሱ ሸኟቸው፤ ፠ ምእመናን ተክዘው ፤ ጉንጫቸው የዕንባ ሸለቆ ሁኖ ተሰናበቷቸው፤ ፠ አንዳንዱም የሆነውን ባለማመን የሚደረጉትን ሁኔታዎች በማየት ደንግጦ የሚደረጉትን ድርጊቶች በማየት ተሰናበታቸው፡፡ ፠፠፠እርሳቸው ለካ ጕዞ ኑሯቸው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባን በሚከተሉት ሁኔታዎች ረስተው ወደ ጕዟቸው አመሩ፤ * በጎንደር ሆስፒታል ሐኪሞች ፍቅር ተስበው፤ * ከጎንደር ከተማ ወደ ደቡብ ጎንደር በሠረገላ (በመኪና) ጕዞ እንቅልፍ አሸልበው፤ * በመካነ ሰማዕት ገባሬ መንክራት ቅዱስ ገላውዴዎስ ታቦተ ሕግ ዑደት ቡራኬ ያሉበትን ረስተው፤ * በፓትርያርኩ ቡራኬና ተባርከው፤ ‹የሰላም አባት› በሚል ማዕረግና ሽልማት ተደስተው፣ * በፓትርያርኩና በጳጳሳቱ ቅዳሴና ዕጣን ተመስጠው፣ * በጕዟቸውም በየከተሞቹ፤ ከጎንደር ከተማ እስከ ደብረ ታቦር፤ ከቆማ ፋሲለደስ እስከ ገላውዴዎስ በቅዱስ ያሬድና በተከታዮቹ ደባትር ካህናት ዜማና ጸሎተ ፍትሐት ተማርከውና ፈዘው፣ (ወተቀበልዎ መላእክት በስብሐት ውስተ ሰማያት /ለብጹዕ ኤልሳዕ/፤ ወአብእዎ ኢየሩላሌም ሰማያዊት በፍሐ ወበሐሴት፡፡ (መላእክት በሰማያት በምሥጋና ብጹዕ ኤልሳን ተቀበሉት፤ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ወደተባለች ለጊዜው ገነት ለመጨረሻው መንግሥተ ሰማያት በደስታና በእልልታ አስገቡት፡፡) በሚለው ፈዘው * በመንግሥት አካላት እጀባ ኮርተው፤ * በምእመናን ዕንባና ሐዘን ተታለው፤ ******** አልተመለሱም፤ ወደ ወዲያኛው ዓለም፤ ይመኙት ወደነበረው፤ ወዳገለገሉት አምላክ አመሩ እንጂ።

የመልስ መርሐ ግብር ጥሪ፡፡ ለ .................................... የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ትቤት፤ ከዚህ በፊት ጋብቻቸውን ለፈጸሙ እኅቶቻችን፣ ወንድሞቻችንና ማኅበረ ካህናት የሚኾን ልዩ የመልስ መርሐ ግብር እሑድ ሰኔ 2/፳፻፲፩ ዓ.ም. ከቀኑ በ7፡30 ላይ አዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል፤ በመኾኑም ከ ባለቤትዎ/ባልተቤትዎ/ ጋር እንዲገኙልን በማክበር ጠርተንዎታል፡፡ ፠፠ለበዓሉ ድምቀት፤ ወደ መርሐ ግብሩ ሲመጡ ሥርዐተ ቤተክርስቲያንን የጠበቀ የሃገር ባህል ልብስ ወይም የተሞሸሩበትን የሃገር ባህል ልብስ ለብሰው እንዲመጡ በትህትና እናሳስባለን፡ ‹‹በእናንተ ዘንድ ሁሉ በፍቅር ይሁን፡፡›› ዕብ. ፲፥፳፭ ሰዓት በማክበር የበኩልዎን አስተዋጽዖ ያድርጉ፡፡ የፍኖተ ሕይወት ሰንበት ት/ቤት፡፡

በእንተ ግብረ ሰዶም፤ እምጥንቱ እስከ ተፍጻሜቱ፡፡ /ክፍል ፩/ በመጪው ነሐሴ በጉብኝት ስም ወደ ኢትዮጵያ እንመጣለን ያሉ ግብረ ሰዶማውያንን #መሬቷና_ሕዝቡ_እንዳይቀበሏቸው_ቅዱስ_ሲኖዶስ_አወገዘ፨ ***የግብረ ሰዶም ድርጊት፤ ፠በሃይማኖት ኀጢአት የሆነ፤ ፠በባህል ነውርና አጸያፊ የሆነ፣ ፠በተፈጥሮ እንስሳት (ቊንጫ እንኳን የማትፈጽመው) አስጸያፊ ነውር የሆነ፤ ፠በኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 629 ወንጀል የሆነ ነው፡፡ ፠በምንም ተኣምር በመጪው ነሐሴ ወር በቶቶ ቱርስ አስተባባሪነት ግብረ ሰዶማውያን በቱሪዝም ሽፋን ቅዱሳት መካናትን እንዳይረግጡ ለመንግሥት ማሳሰቢያ እንዲጻፍ አዘዘ፡፡ **መንግሥትም ይህን ድርጊት እንዲያወግዝ፤ በወንጀል አድራጎቱ የሚያዙ ግለሰቦችን በቀላል ቅጣት መለቀቅ እንደሌለባቸውና የወንጀል ሕጉን በማጥበቅ ቁርጠኝነቱን እንዲያሳይ ጠየቀ፡፡ **ለጋባዡ ፥ ለቪዛ ፈቃጁ ለኢትዮጵያ መንግሥትም ጠበቅ ያለ ማሳሰቢያና ማስጠንቀቂያ እንዲጻፍም ሲኖዶሱ አዟል። **ይህ ወንጀል መሆኑንና የሚያሳስር የሚያስቀጣ መሆኑን እያወቀ የጉብኝቱን ቪዛ የፈቀደው በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሕግ መጠየቅ እንዳለበትም ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ የሕግ ባለሙያዎች እየጠቆሙም ይገኛሉ። **የፌደራል ፖሊስ ልክ ቦሌ ላይ ሀሺሽ፣ ሕገ ወጥ መሣሪያዎችን ሲገቡ ይዞ ወደ ሕግ ጥላ ሥር እንደሚያውለው ሁሉ እነዚህን በግልጽ ግብረ ሶዶማዊያን ነን ብለው እያወጁ ኢትዮጵያ ለመምጣት የወሰኑትን በኢትዮጵያ ወንጀል በመሆኑ እንዲያስርና በሕግ እንዲጠየቁም ያደረግ ዘንድም ብዙዎችም በመጠየቅ ላይ ናቸው፡፡ ከሡራኄ (Surahe) ገጽ የተወሰደ፡፡ https://t.me/Surahe

#የክርስቶስ_ዕርገት_በትምህርተ_ሐዋርያት ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተነጋገረ በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ፡፡ ማር.16፥19 ‹‹እስከ ቢታንያ አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ እነርሱም ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደኢየሩሳሌም ተመለሱ፤ ዘወትርም እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እየባረኩ በመቅደስ ኖሩ፡፡›› ሉቃ.24፥50 ‹‹ይህንም ከተናገረ በኋላ እነርሱ እያዩት ከፍ ከፍ አለ ደመናም ከዐይናቸው ሰውራ ተቀበለችው፤ እርሱም ሲሄድ ወደ ሰማይ ትኩር ብለው ሲመለከቱ ሳሉ እነሆ ነጫጭ ልብስ ለብሰው ሁለት ሰዎች /መላእክት/ በአጠገባቸው ቆሙ ደግሞም ‹‹የገሊላ ሰዎች ሆይ ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ ስለምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት ዳግመኛ ይመጣል፡፡›› አሏቸው›› ሐዋ.1፥9-12 በማለት ሐዋርያት የክርስቶስን ዕርገት ከመላእክት ጋር ሆነው እንደተመለከቱ ደስታውን እንደተካፈሉ ቅዱስ ሉቃስ ጽፎልናል፡፡ በትንሣኤው ነጭ ልብስ ለብሰው የታዩ መላእክት የደስታ ዘመን ነው ሲሉ በእርገቱም ነጭ ልብስ ለብሰው የዕርገቱን የምሥራች ለሐዋርያት አብስረዋል፡፡ /ምንጭ፤ የቃል ትምህርትና በመምህር ምሥጢረ ሥሳሴ ማናየ/ የአምላካችን ቸርነቱ ረድኤቱ አይለየን፡፡፠ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፠

ዕርገተ እግዚእ እንኳን ለጌታችን በዓለ ዕርገት ሐሙስ ግንቦት 29/2011ዓ.ም. አደረሳችሁ፥ አደረሰን፤ በዓሉን የሚመለከት ጽሑፍና ሥርዐተ ማኅሌቱን እንደተለመደው አቅርበንላችኋል፡፡ መልካም ንባብ፤ መልካም የምሥጋና ማኅሌት፡፡ /ከቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ሰሌዳ መጽሔት በማሳጠር የተወሰደ/ ‹‹አልቦ ዘዓርገ ውስተ ሰማይ ዘእንበለ ዘወረደ እምሰማይ ወልደ ዕጓለመሕያው፤ ከሰማይ ከወረደው የሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም፡፡›› ዮሐ.3፥13 ከሰማይ ከወረደው የሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም፡፡ እርሱም በሰማይ የሚኖረው ነው፡፡ ይህ ኃይለ ቃል ክብር ምስጋና ይግባውና ስለጌታችን፣ አምላካችን፣ መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት መውረድ ከድንግል ማርያም መወለድ እና የሰውነቱን ሥራ ጨርሶ በክብር ወደ ሰማይ ማረጉን የሚገልጽ ነው፡፡ እንደሚታወቀው አምላካችን ስለሁለት ዐቢይ ጉዳዮች ሰው ሆኗል፡፡ 1. *ለቤዛነት /ዓለምን ለማዳን/ 2. *ለአርአያነት /ምሳሌነት/ የሰውን ልጅ በመውደዱ ልዑል ባሕርዩን ዝቅ አድርጎ ከሰማይ ወረደ ሥጋ ለበሰ በምድር ላይ ተመላለሰ፤ ምድርን በኪደተ እግሩ ቀደሰ፤ ድውያንን ፈወሰ፤ ፍጹም ሰው እንደ መሆኑ ተራበ ፍጹም አምላክ መሆኑንም ያስረዳ ዘንድ አምስት ገበያ ሕዝብ በአምስት እንጀራ በሁለት ዓሣ አጠገበ ማቴ.14፥19 ለእኛ አርአያና ምሳሌ ለመሆን ዝቅ ብሎ የደቀ መዛሙርቱን እግር አጠበ ዮሐ.13፥14 እኛም ፍለጋውን እንከተል ዘንድ አንትሙኒ ከመዝ ግበሩ ለቢጽክሙ እናንተም ለባልንጀሮቻችሁ እንዲሁ አድርጉ ብሎ አዘዘ፡፡ መምሕረ ትሕትና ነውና በዚህ ዓይነት መልኩ ሠላሳ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር በዚህ ዓለም ኖረ ለሐዋርያት ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ወንጌልን አስተማራቸው ትምህርት በሚገባ ከተረዳለት በኋላ ለድኅነተ ዓለም በማዕከለ ምድር በቀራንዮ ተሰቀለ፡፡ #ወገብረ_መድኀኒተ_በማዕከለ_ምድር_እንዲል_በምድር_መካከል_መድኀኒትን_አደረገ_መዝ.73፥12 ‹‹እስመ ኢይደልዎ ለነቢይ መዊት በአፍአ ዘእንበለ በኢየሩሳሌም፤ ነቢይ በኢየሩሳሌም ነው እንጂ በውጭ ሊሞት አይገባውም፡፡›› ብሎ እንደተናገረ፡፡ ሉቃ.13፥33 በሞቱ ዓለምን አድኖ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት በከርሰ መቃብር አድሮ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ ብርሃነ መለኮቱን ገልጾ ተነሣ፡፡ ነቢያት እንደተናገሩ ‹‹እግዚአብሔር ይነሣል ጠላቶቹም ይበተናሉ›› መዝ.67፥1 ‹‹እኔ ተኛሁ አንቀላፋሁ እግዚአብሔርም አስነሥቶኛልና ተነሣሁ፡፡›› መዝ.3፥5 ‹‹እግዚአብሔር አሁን እነሣለሁ ይላል መድኀኒትንም አደርጋለሁ በዕለቱም እገለጣለሁ›› መዝ.11፥5፡፡ ‹‹ሥጋየ ደግሞ በተስፋ /በትንሣኤ/ ታድራለች ነፍሴን በሲዖል /በመቃብር/ አትተዋትምና/ እነሣለሁ ቅዱስህንም መበስበስን ያይ ዘንድ አትተወውም፡፡›› መዝ.15፥9 ‹‹አቤቱ ንቃ ለምንስ ትተኛለህ ተነሥ ለዘወትርም አትጣለን›› መዝ.43፥23 ‹‹እግዚአብሔር ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ›› መዝ.77፥65 ተብሎ የተተነበየውን ትንቢት ፈጽሞ ተነሣ፡፡ በሞቱ ሞታችንን ሻረልን፤ በመቀበሩም ሙስና መቃብርን አጠፋልን፡፡ ‹‹በሞቱ ሞትን አጠፋው›› እንዲል መጽሐፈ ኪዳን፡፡ ሕንፃ መነኮሳት ‹እርሱ በሁሉ ምሉዕ ሲሆን በመቃብር ለመቀበር ዮሴፍ ኒቆዲሞስ ገንዘውት ታየ፡፡ ከመሬት ውስጥ በመቀበሩም ሙስና መቃብርን አጠፋ፤ ከሥሩም ነቀለው ከተነሣ በኋላ ትንሣኤውን መጀመሪያ ለማርያም መግደላዊት ገለጸ ማር.16፥9፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም ስለ ትንሣኤው ሲመሰክር ‹‹ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፤ ተቀበረም፤ መጽሐፍ እንደሚል፤ በሦስተኛው ቀን ተነሣ፡፡ ለኬፋም ታየ በኋላም ለአሥራ ሁለቱ ከዚያም በኋላ ከአምስት መቶ ለሚበዙ ወንድሞች በአንድ ጊዜ ታየ፡፡ ከዚያም በኋላ ለያዕቆብ ኋላም ለሐዋርያት ሁሉ ታየ›› 1ቆሮ.15፥3-8 ብሎ ክርስቶስ ትንሣኤውን ለተከታዮቹ በሙሉ የገለጠ መሆኑን መስክሯል፡፡ የሚያምኑ ፈሪሳውያንም ‹‹ትንሣኤው ምትሐት ነው›› እንዳይሉ እየታየ እያስተማረ እስከ 40 ቀን ድረስ መቆየቱን ይገልጽልና፡፡ በዚህም የአርባ ቀን ከትንሣኤ በኋላ ቆይታው ሦስት ቀን ጉባኤ አድርጎ ደቀ መዛሙርቱን እንዳስተማረ ቅዱስ ወንጌል ይነግረናል፡፡ ኢየሱስ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ለደቀ መዛሙርቱ ሲገለጥላቸው ይህ ሦስተኛ ጊዜ ነበረ እንዲል ዮሐ.21፥14 ይህንም ሊቃውንት አባቶቻችን፡- 1. *የትንሣኤ 2. *የአግብኦተ ግብር /ዳግም ትንሣኤ/ 3. *የጥብርያዶስ ነው ብለው አስቀምጠውታል በዚህ 40 ቀን ቆይታ መጽሐፈ ኪዳንን ለደቀ መዛሙርቱ አስተምሯል፡፡ ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስም ዕርገቱን ለመናገር ከሰማየ ሰማያት መውረዱን አስቀድሞ ከሰማይ ከወረደው ከሰው ልጅ በቀር ማንም ወደ ሰማይ የወጣ የለም እርሱም በሰማይ የሚኖረው ነው ብሎ ከዕርገቱ በኋላ በየማነ አብ፤ በዘባነ ኪሩብ በአምላክነት ሥልጣን ለመኖር ወደሰማይ የወጣ ከእርሱ በቀር ሌላ እንደሌለ አስረግጦ ነገረን፡፡ ሲጀምር ከሰማይ መውረዱን ማስቀደሙ ወረደ ብሎ ዐረገ ለማለት ይመቻል፡፡ ተጸነሰ ተወለደ ለማለት ጥንቱ ከሰማያት ወረደ ማለት እንደሆነ ሁሉ፤ ‹‹ተሰቀለ፤ ሞተ፤ ተቀበረ፤ ተነሣ'››ለማለት ‹‹ጥንቱ:- ተጸነሰ፤ ተወለደ፤ አደገ ተመላለሰ ሠላሳ ዓመት ኖረ›› የሚለው ነው፡፡ ስለሆነም ቅዱስ ዮሐንስ ጠርዝና ጠርዙን ይዞ ተናገረ፡፡ ‹‹ወረደ ዐረገ›› የሚሉት ሁለት ቃላት የዓለም ድኅነት መነሻና መድረሻ ናቸው፤ እነዚህን ሁለት ቃላት ስናይ በሁለቱ መካከል የተፈጸሙትን የአምላክ ሥራዎች ልብ ማለት ይገባል፡፡ ቤት በመሠረት ይጀመራል በጣሪያ ይፈጸማል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ይህን የቤዛነት ሥራ ሲያስረዳ በዮሐ.1፥14 ‹‹ቃል ሥጋ ኮነ፤ ቃል ሥጋ ሆነ›› ብሎ ጀምሯል ይህንም ቃል ‹‹ከሰማይ ከወረደው የሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም›› በማለት ሰው መሆኑን ብቻ ሳይሆን በአርያም የሚኖር መሆኑን አስተማረን፡፡ እንግዲህ ጌታችን ዕርገት እንዲሁ እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውኃ ፈሳሽ አለመሆኑን ቀድሞ በነቢያት የተነገረ ኋላም በሐዋርያት የተመሰከረ መሆኑን ማወቅ ያስፈለጋል፡፡ #የክርስቶስ_ዕርገት_በትንቢተ_ነቢያት ‹‹ሰማዮችን ዝቅ ዝቅ አደረገ ወረደም ጨለማ /ዲያብሎስ/ ከእግሩ በታች ነበር በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ በነፍሳትም ክንፍ በረረ›› መዝ.17፥9 ‹‹አምላክ በእልልታ እግዚአብሔር በመለከት ድምጽ ዐረገ መዝ.46፥5 ወደላይ ዐረግህ፥ ምርኮን ማረክህ ፥ስጦታንም ለሰዎች ሰጠህ›› መዝ.67፥18፡፡ ‹‹ዘምሩ ለእግዚአብሔር ዘዓርገ ውስተ ሰማይ ዘመንገለ ጽባሕ፤ በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ ለእግዚአብሔር ዘምሩ›› መዝ.67፥33፡፡

እንኳን ለአምላካችንና ፈጣሪያችን ቅዱስ አማኑኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን ፥ አደረሳችሁ፡፡ ክብረ በዓሉ ከሚከበርባቸው ገዳማትና አድባራት ዐበይቶቹ (እናንተም የምታውቋቸውንና በአቅራቢያችሁ ያሉትንከነፎቷቸው ጨምሩበት) ፠ ኦፍና አማኑኤል፤ መርሐ ቤቴ፥ አለም ከተማ፤ በ4ኛው ክፍለ ዘመን የተመሠረተ ጥንታዊ ቤ.ክ. ፠ ኤነር አማኑኤል፤ ምድረ ጕራጌ፤ እጅግ በጣም ጥንታዊ ገዳም ፠ ደብረ መንክራት በጎል ሰከበ ሚጣቅ ቅዱስ አማኑኤል፤ ከደብረ ብርሃንና አንኮበር መሃል ላይ የሚገኝ፤ በንጉሥ ሣህለ ሥላሴ የተመሠረተ፤ እጅጉን በጣም ፈዋሽ የኾነ ጠበል የሚገኝበትና የቅዱሳን መናኸሪያ የኾነ፡፡ ፠ ጫገል ቅዱስ አማኑኤል /በደብረ ሊባኖስ ገዳም ከሚተዳደሩ አብያተ ክርስቲያናት አንዱ/ ፠ ደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል፣ አዲስ አበባ፤ መርካቶ መሳለሚያ ፠ ባሶ ወረዳ ጣፎ ደብረ ሰላም ቅዱስ አማኑኤል ቤተክርስቲያን፤ ከጢያ ከተማ ወደ አጠገብ የሚገኝ፡፡