ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

الذهاب إلى القناة على Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

إظهار المزيد

📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

تُعد قناة Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 16 041 مشتركاً، محتلاً المرتبة 5 280 في فئة الدين والقيم الروحية والمرتبة 2 239 في منطقة Ethiopia.

📊 مؤشرات الجمهور والحراك

منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 16 041 مشتركاً.

بحسب آخر البيانات بتاريخ 28 أكتوبر, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار 512، وفي آخر 24 ساعة بمقدار -6، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.

  • حالة التحقق: غير موثّقة
  • معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 25.18‎%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 10.37‎% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
  • وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 4 039 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 1 663 مشاهدة.
  • التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 30.

📝 الوصف وسياسة المحتوى

يصف المؤلف القناة بأنها مساحة للتعبير عن الآراء الذاتية:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 29 أكتوبر, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة الدين والقيم الروحية.

16 041
المشتركون
-624 ساعات
+917 أيام
+51230 أيام
أرشيف المشاركات
ወረብ ፭፤ ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ (፪) ዘየኀቱ እምዕንቈ ባሕርይ፤ (በደብራችን መሪጌታ ሄኖክ)

ወረብ ፬፤ ንዒ ኀቤየ ምስለ መላእክት(፪)፤ ዘቀጨኔ ደብረ ሰላም (የቤቱ ቀለም)፤ (በሊቀ ጠበብት ይልማ የደብራችን የአቋቋም መምህርና በኢትዮጵያ ደረጃ የአቋቋም ተጠያቂና መምህር በሆኑት በመምህር ዳዊት)

ወረብ ፫፤ እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ(፪) ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤ (በደብራችን መሪጌታ፤ በ2007 ዓ.ም. የተቀዳ)

የጥቅምት ፴ (የተፈጸመ) ማኅሌተ ጽጌ ወረቦች፤ ወረብ ፩.፩፤ /ዘቀጨኔ ደብረ ሰላም (የቤቱ ቀለም) (በአጋፋሪ ይሁኔ) ኢየኀፍር ቀዊመ ቅድመ ገጸ ስዕልኪወላዲተ አምላክ፤/፪ ጸውዖ ስምኪ ያነሥእ ዘወድቀ(፪)፡፡/፪/

✤✤ #ደብረ_ወገግ_፤ ፠ ‹‹ደብረ ወገግ›› ከ2-5 ዓ.ም. እመቤታችን ከነልጇ ስተሰደድ ለ6 ወር የተቀመጠችበት ሲኾን፤ ደብረ ወገግ የሚለው ስያሜ የተገኘው ከመላእክት ነው፡፡ ድርሳነ ዑራኤል በሰፊው እንደሚያትተው ቅዱስ ዑራኤል በ34ዓ.ም. የጌታችንን ደም በብርሃን ጽዋ ተቀብሎ ዓለምን እየረጨ ሲቀድሳት የያዘውን ጽዋ በደብረ ወገግ ላይ ቆሞ ሳለ ነው ጨልጦ ያንጠፈጠፈው፡፡ ያንጊዜም ደብረ ወገግን የብርሃን ውጋገን ሲያጥለቀልቀው በመታየቱ መላእክትም ቦታውን ‹‹ደብረ ወገግ›› (የብርሃን ተራራ) ብለው ሰይመውታል፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም ‹‹ወደፊት ፈጣሪውን የሚያገለግል ታላቅ ጻድቅ ይወጣባታልና ይህችን ቦታ ባርካት›› ብሎ ቅዱስ ዑራኤልን በነገረው መሠረት ባርኳት አርጓል፡፡ ፠ በደብረ ወገግ ቦታ ላይ ብዙ ጊዜ የብርሃን ምሰሶ ተተክሎ መታየቱን የበቁ ገዳማውያን ብቻ ሳይሆኑ በከተማ ያሉና ለመሳለም ወደ ቦታው የሄዱ ደገኛ ሰዎችም በዐይናቸው ያዩትን ይናገራሉ፡፡ በገዳሙ ዙሪያ እጅግ በጣም ብዙ ስውራን ቅዱሳን እንዳሉ በግልጽ ይታወቃል፡፡ ፠ ገዳሙ በግራኝ ወረራ ወቅት ከጠፋ በኋላ እንደገና መልሶ የቀናው በ1911ዓ.ም. በታላቁ ሊቅና መናኝ በአለቃ ገብረ መድኅን ነው (ለአፄ ኀይለ ሥላሴ በማሳሰብ)፡፡ በ1912 ዓ.ም. የአቡነ ሳሙኤልን ቤተ ክርስቲያንን በሣር ክዳን ሠሩ፤ በዓመቱ በ1918 ዓ.ም. ደግሞ የቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያንን መሥራት ጀምረው ፍጻሜውን ሳያዩ እርሳቸው ቢያርፉም፤ በ1919 ዓ.ም. የሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ ሥራ ተጠናቋል፡፡ በ1929 ዓ.ም. በሶማልያ በኩል በገባው የፋሽስት ኢጣልያ ጦር ገዳሙ ተዘርፏል፥ የቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያንም ፈርሷል፡፡ በወቅቱ በገዳሙ ከነበሩት ከ500 በላይ መነኰሳት መካከል ከፊሉ ታቦቱን ይዘው ወደ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ሲሸሹ ከፊሎቹ ደግሞ ወደ ሞቃዲሾ ተወስደው ታስረዋል፡፡ ከጣሊያን ወረራ በኋላ መነኰሳቱ በ1936 ዓ.ም. ተሰባስበው ወደ አሰቦት መጡ፡፡ ከ22 ዓመት በኋላ ደግሞ የቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን በግርማዊ ቀዳማዊ ንጉሠ ነገሥት ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ትእዛዝ በ1952 ዓ.ም. ተሠራ፡፡ በደርግ ዘመነ መንግሥት ሶማሊያ ኢትጵያን ስትወርር ገዳሙ ላይ አደጋ ለመጣል የመጡ ጠላቶች በተአምራት ያለቁበት ነበር፤ የጃራ ጦር የሚባሉ ገዳሙን ለማጥፋትም መጡ ጠላቶች እንዲሁ በተአምራት አብደው የተመለሱበት ታላቅ ገዳም ነው፡፡ ግንቦት 16 ቀን 1984 ዓ.ም. በአክራሪ ኃይል የገዳሙን መነኰሳትና የአካባቢው ምዕመናን ላይ የከፋ አደጋ ጥሏል፤ ብዙዎችም ሰማዕት ሁነዋል፡፡ በአሰቦት ደብረ ወገግ ገዳም ውስጥ የተሰወሩ እጅግ በርካታ ቅዱሳን ስለመኖራቸው በገድለ አቡነ ሳሙኤል መቅድም ውስጥ በሰፊው ተጠቅሷል፡፡ አሁንም ሆነ ወደፊት በቦታው ላይ የተሰወሩት ቅዱሳን ለገዳማውያኑም ሆነ በዓለም ለሚኖሩ ምግባርን ከሃይማኖት አስተባብረው ለያዙ ሰዎች እየተገለጡላቸው ይታዩዋቸዋል፣ መልእክትም ይነግሯቸዋል፡፡ እንዲሁም ስውራኑ ባሉበት ቦታ የከበሮ ድምጽ ይሰማል፣ ዕጣን ይሸታል፣ ቀንና ሌሊት አራዊት ሲሰግዱበትና ሲጠብቁት ይታያል፡፡ ለአብነትም በ1972ዓ.ም. ሐምሌ 7 ብዙ ሰው እያያቸው አባ መዘምር የተሠወሩበት ታለቅ ገዳም ነው፡፡ /ታሪኩን ለዘገበልን ወንድማችን አምላከ አቡነ ሳሙኤል በረድኤት በበረከት በጤና ይጠብቅልን፡፡/ /የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት/

ታላቁ ገዳማችን አሰቦት ደብረ ወገግንና ደብረ ኪሩብን ለመሠረቱት ለአባታችን ለአቡነ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ በዓለ ዕረፍት (ጥቅምት 29) በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፡፡ ✤✤ #አቡነ_ሳሙኤል-ዘደብረ_ወገግ፡፡ ፠ በታላቁ አባት አቡነ ተክለሃይማኖት ‹እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ፥ ጣዖታትን የሚሰብር፣ የሚያጠፋ፣ አጋንንትን በጸሎቱ የሚያርቅ፣ ሕዝብን ከኀጢአት በሽታ የሚያድን፣ ፈጣሪውን የሚያስደስት ደግ ልጅ› ተብሎ በተነገረለት ትንቢታዊ ብሥራት ከደጋግና ከበቁ አባታቸው እንድርያስና ከእናታቸው አርሶንያ ሐምሌ 10 ቀን 1248 ዓ.ም. በቡልጋ (በኢቲሳ ደብረ ጽላልሽ ገዳም) ተወለዱ፤ ሲወለዱም መልካቸው በአራት ልዩ ልዩ ሕብረ መልክ እየተለዋወጠ አንድ ጊዜ እንደ በረዶ፣ አንድ ጊዜ እንደ እሳት፣ አንድ ጊዜ እንደ ልምላሜና ቢጫ ሆነው ታይተዋል፡፡ ፠ስማቸውን ሳሙኤል ብለው የሰየሟቸውና ክርስትናም ያነሷቸው፤ ኋላም መዓርገ ምንኵስናን በደብረ ሊባኖስ የሰጧቸው አቡነ ተክለሃይማኖት ናቸው፡፡ ፠ ብዙ ጻድቃንን (አቡነ ተክለሃይማኖትን፣ ታዴዎስ ዘደብረ ድኁኃን፣ ሮማኖስ ዘደብረ ዋምን፣ አቡነ አኖሬዎስ ዕንቈ ባሕርይ ዘመረግድ ወመስተጋድል ወምግባር ንጹሕን) በሥጋ የሚዛመዱ ናቸው፡፡ ፠ ሃይማኖቱ የቀና ደግ ጻድቅ ንጉሥ ዳዊት በነገሠ ጊዜ አባታችን ሳሙኤል ዘወገግን አገኘውና አባቱ ዓምደ ጽዮን ለሠራው ክፉ ሥራ ‹‹መማጸኛ እንዲሆነኝ በእንድርያስ መቃብር ላይ ቤተክርስቲያን ሥራልኝ›› ብሎ ለመነውና የሩፋኤልን ቤተ ክርስቲያን ሠራለት፡፡ የእንድርያስንም አጽም ከመቅደሱ ስር አኖረው፡፡ ንጉሡም በዚያ በእንደግብጦን አውራጃ ሁሉ ላይ ፓትርያርክ አድርጎ ሾመው፡፡ ፠፠ አቡነ ተክለሃይማኖት ትንቢት እንደተናገሩላቸው አቡነ ሳሙኤል፤ * በሰዎች፣ በባሕርና በዛፍ ላይ እያደሩ ይመለኩ የነበሩ በጣም ብዙ አጋንንትን አጠፏቸው፡፡ * ጠንቋዮችንም በውስጣቸው ካደረባቸው ሰይጣን እያላቀቁ የእግዚአብሔር አገልጋይ ያደርጓቸውና ያመነኩሷቸው ነበር፡፡ * ወንጌልን ዞረው በማስተማር ሐዋርያትን መሰሉ፥ * ከዓላውያን ጋር ለመዋጋት ሰውነታቸውን ለሞት በመስጠት ሰማዕታትን መሰሉ፥ * በጾም በጸሎት በስግደት በተጋድሎ ቅዱሳን ጻድቃንን መሰሉ፥ * ይህን ኀላፊና ጠፊ ዓለም ንቀው በመተው ባሕታውያንን መሰሉ፥ * በደልንና ኃጢአትን በማስተሠረይ ካህናትን መሰሉ፥ * በጽሕናና በቅድስና መላእክትን መሰሉ፤ * ብዙ አስደናቂ ተአምራትንም በማድረግም ይታወቃሉ፤ ከእነዚህም ጥቂቶቹ በትእምርተ መስቀል አድርገው እንደሙሴ ባሕርን ለሁለት ከፍለዋል፣ እንደ ኢያሱ በጸሎታቸው ፀሐይን አቁመዋል፡፡ አቡነ ሳሙኤል ተጋድሏቸውን ፈጽመው ከጌታችን ታላቅ ቃኪዳን ተቀብለው በዚህች ዕለት (በጥቅምት 29) በኦጋዴን ዘርዘር በተባለ ቦታ በሰላም አርፈዋል፤ ከ7 ወራት በኋላ ሠምረ ክርስቶስ የተባለ ልጃቸው ሥጋቸውን አፍልሶ በደብረ ወገግ በክብር አሳርፎታል፡፡ ፠ አቡነ ሳሙኤል የአሰቦት ደብረ ወገግን (ምስራቅ ሐረርጌ) ና ደብረ ኪሩብ (አፋር) ገዳምን ያቀኑ፥ ለብዙ አእላፍ ቅዱሳን ወላዴ የኾኑና፤ የመሠረቱት ገዳም የምሥጢርና የብዙ ስውራን መኖሪያ የኾነላቸው፥ ምስራቅ ኢትዮጵያን እስከ ሞቃድሾ ድረስ በወንጌል ያረሱ፥ አረማውያንን ያጠመቁ ታላቅ አባት ናቸው፡፡ ፠ ከአቡነ ተክለሃይማኖት በኋላ ከተሾሙት 12ቱ ንቡራነ ዕድ አንዱ ናቸው፤ ሃገረ ስብከታቸውም ሐረርና ሱማሌ ነው፡፡ የአቡነ ሳሙኤል ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡ ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘፍቅዳቲሁ ራብዕ፤ ውእቱ ልኩእ ዲበ ረቀ ሰማይ ሳብዕ፡፡ ሊቀ ካህናት ሳሙኤል ዘደብተራ ሐዲ ምሥዋዕ፤ አስተስሪ ኀጣውእየ በደመ ነቢብ በግዕ፤ ለቤዛ ሙታን ዘሞተ በግፍዕ፡፡ (ሳሙኤል ሆይ ቊጥሩ ዐራት ለኾነ በሰባተኛው የሰማይ ብራና(ወረቀት) ለተጻፈ ስም አጠራርህ ሰላምታ ይገባል፤ የሐዲስ መሠዊያ አገልጋይ፥ የካህናት አለቃ ሳሙኤል ሆይ፤ ለሰዎች ቤዛ ለመኾን በግፍ በሞተ በነባቢ ክርስቶስ ደም ኀጢአቴን አስተሥርይ፡፡) /ታሪኩን ለዘገበልን ወንድማችን አምላከ አቡነ ሳሙኤል በረድኤት ፥ በበረከት ፥ በጤና ይጠብቅልን፡፡/ /የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት/

ሥርዐተ ማኅሌት ዘወርኀ ጽጌ (‹ዘላይ ወዘታች› ቤት) ፪ኛ ዙር ዓመት፤ #፭ኛ ሳምንት፥ #ዘጥቅምት_፴፤ በዓለ ቅዱስ ማርቆሰ ወንጌላዊ፡፡ ✤ #ልዩ_አዋጅ_ዘወርኃ_ጽጌ_ ✤  ማኅሌቱ ሥርዐት የላይ ቤት (የጎንደር መካነ ነገሥት ግምጃ ቤት ማርያም አብነት) እና የታች ቤት (የጎንደር ደብረ ኀይል ዑራኤል ወደብረ ጥበብ በዓታ ለማርያምን አብነት) የሚያደርግ ሲኾን፤ የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም ወደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ የማኅሌት ቁመትም የላይ ቤትን አብነት የተከተለ ሲኾን፤ የዚቁ ወረብ ግን የደብሩን የራሱን(የሸዋን) የተከተለ ነው፤  የላይ ቤት ቁመት የሚቆሙ አድባራት ዘግምጃ ቤት የሚለውን እንዲከተሉ፤ የታች ቤትን ቁመት የሚቆሙ አድባራት ዘበዓታ የሚለውን እንዲከተሉ እያሳሰብን፡፡ የዚቁ ወረብን ግን የቀጨኔ ደብረ ሰላም የቤቱን ቀለም አስቀድመን ቀጥሎ ደግሞ ዓዲ (ወይም) በማለት የጎንደርን ስላስቀመጥነው እንደ ደብራችሁ ይትበሃል መርጣችሁ እንድትጠቀሙበት ኹሉንም አስቀምጠነዋል፡፡ #የጥቅምት_30_የማኅሌተ_ጽጌ_ወረቦች_፤ በደብራችን ሊቃውንትና መምህራን፡፡ ድምፆቹን በሚከተለው የቴሌግራም አድራሻችን ያገኛሉ፤ https://t.me/medihanaelem 5.1. ወረብ ፩.፩፤ ኢየኀፍር ቀዊመ ቅድመ ስዕልኪወላዲተ አምላክ፤/ዘቀጨኔ ደብረ ሰላም (የቤቱ ቀለም) ፤ (በአጋፋሪ ይሁኔ) ወረብ ፩.፪፤ ኢየኀፍር ቀዊመ ቅድመ ስዕልኪ /ዘጎንደር/ (በ…) 5.2. ወረብ ፪፤ እለ ትነብሩ ተንሥኡ፤ (በ…) 5.3. ወረብ ፫፤ እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ(፪) ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤ (በ..) 5.4. ወረብ ፬፤ ንዒ ኀቤየ ምስለ መላእክት(፪)፤ /ዘቀጨኔ ደብረ ሰላም (የቤቱ ቀለም)፤ (በሊቀ ጠበብት ይልማ የደብራችን የአቋቋም መምህርና በኢትዮጵያ ደረጃ የአቋቋም ተጠያቂና መምህር በሆኑት በመምህር ዳዊት) 5.5. ወረብ ፭፤ ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ (፪)ዘየኀቱ እምዕንቈ ባሕርይ፤ (በ…) 5.6. ወረብ ፮፤ ሰአሊ ለነ ማርያም ሰአሊ ለነ ፤ /ዘቀጨኔ ደብረ ሰላም (የቤቱ ቀለም)፤ (በመሪጌታ ተክለ ያሬድ) 5.7. ወረብ ፯.፩፤ ኅብረ ሐመልሚል(፪) አርአያ ኰሰኰስ፤ /ዘቀጨኔ ደብረ ሰላም (የቤቱ ቀለም)፤ (በአጋፋሪ ይሁኔና በአጋፋሪ ዳዊት) 5.8. ወረብ ፰፤ጥቀ አዳም(፪) መላትሕኪ ጥቀ፤ (በ..) 5.9. ወረብ ፱፤ ናዝሬት ሀገሩ አብርሂ/፫/ ናዝሬት፤ (በ…) 5.10. ወረብ ፲፤ ወይቤላ ሶበ ተአምሪ ጽዮን(፪) ወረብ ፲.፪.፩፤ ተመየጢ(፪)ማርያም ሀገረኪ ናዝሬት፤ (በ…) ዓዲ፤ ወረብ ፲.፪.፪፤ ተመየጢ(፪)እግዝእትየ ማርያም ሀገረኪ (በ…) 5.11. ወረብ ፲፩፤ ሃሌ ሉያ ተመየጢ ሰላመ ሰጣዊት፤ (በ…) (ፎቶዎቹ፤ ከ7 ዓመታት በፊት ጥቅምት 30/2007ዓ.ም. በተፈጸመ ማኅሌተ ጽጌ ላይ)

#የሕይወት_ፈተና_ምንጮች_፡፡ Shareee, Like … ለምን እንፈተናለን፤ ፈተናዎች ለምንና እንዴት ይመጣሉ፤ ፈተናዎችን እንዴት አድርገን ድል እናድርጋቸው፤ …. እንዳያመልጣችሁ፤ በሌሎችም ርዕሶች
+1
#የሕይወት_ፈተና_ምንጮች_፡፡ Shareee, Like … ለምን እንፈተናለን፤ ፈተናዎች ለምንና እንዴት ይመጣሉ፤ ፈተናዎችን እንዴት አድርገን ድል እናድርጋቸው፤ …. እንዳያመልጣችሁ፤ በሌሎችም ርዕሶች ዙሪያ በብዙ ጕባኤያት ላይ ያልተዳሰሱ ርዕሶች የሚዳሰሱበት ጕባኤ ስለሆነ እንዳያመልጣችሁ፤ #ደግመን_እንላለን_ይህ_ትምህርት_በፍጹም_እንዳያመልጣችሁ!!!!! ለ፬ ተከታታይ ሳምንታት፤ ትምህርቱ ተከታታይነት ስላለው መቅረትና ማርፈድ አይመከርም!!፡፡ (፻፶ኛ ሳምንት የዐርብ ጕባኤ) ዐርብ ከጥቀምት ፳፰ ጀምሮ ከ፲፪-፪ ሰዓት ከ12-12፡30 በማኅበረ ሥላሴ አባቶቻችን የታዘዘውን የምሕላ ጸሎት በዐውደ ምሕረት ይደርሳል፡፡ ከ12፡30-2፡00 ሰዐት ትምህርቱ ይሰጣል፡፡ አሁንም በድጋሚ እንላለን ለሕይወታችን ወሳኝና በብዙ የትምህርት ጕባኤያት ላይ የማይዳሰሱ ትምህርቶች ስለሆኑ እንዳያመልጣችሁ!!!! የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት፡፡

፨፠መድኀኔዓለም ክርስቶስ ዘኢተአምር በቀለ፤ ተማሕጸንኩ በጻድቃኒከ እስመ ወሀብኮሙ ቃለ፤ ዘጸውዐ ስመክሙ እምሕር ብሂለ፡፡ (መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ ሆይ፤ በቀል የሌለብህ አምላክ እንደመሆንህ በቅዱሳኖ
+1
፨፠መድኀኔዓለም ክርስቶስ ዘኢተአምር በቀለ፤ ተማሕጸንኩ በጻድቃኒከ እስመ ወሀብኮሙ ቃለ፤ ዘጸውዐ ስመክሙ እምሕር ብሂለ፡፡ (መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ ሆይ፤ በቀል የሌለብህ አምላክ እንደመሆንህ በቅዱሳኖች በወዳጆችህ አማላጅነት እማጸንሃለሁ፤ ስማችሁን የጠራ እምርላችኋለሁ ሰትል ቃል ኪዳን ገብተህላቸዋልና፡፡) ፠፠ (ሃሌ ሉያ በአማን በአማን ቃልከ አዳም፤ በእንተ ኀጥኣን ዘተሰቀልከ መድኀኔ ዓለም)፡፡ ፠፨፠ በርካታ አንጋፋ ሊቃውንት በተሰበሰቡበት የጥቅምት 27 የመድኀኔ ዓለም ክብረ በዓል ሥርዐተ ማኅሌት በቀ.ደ.ሰ. መድኀኔ ዓለም በጨረፍታ፡፡ መልአከ ሰላም ስዩም ወልደ ገብርኤል፤ መጋቤ (ሊቀ ካህናት) ኀይለ ሥላሴ ዘማርያም ** ሊቀ ጠበብት ኀይለ መስቀል (ከ1970 ዓ.ም. በፊት የደብራችን አገልጋይ የነበሩና በአሁኑ ሰዐት የእንጦጦ ማርያም ሊቀ ጠበብት የሆኑ)፡፡

፨፨ ሌሎች በሃገራችን የሚገኙ የመድኀኔ ዓለም አብያተ ክርስቲያናት፤ (ፎቶ ያላችሁ ላኩልን፡፡) ✤መቅደላ መድኀኔዓለም ✤ባሕር ዳር ድባንቄ መድኄኔዓለም ✤አዴት መድኃኔዓለም ✤አዲስ አምባ መድኃኔዓለም ከ1600 ዓመት በላይ ዕድሜ ያለው በግብፃዊው ጻድቅ አቡነ ሙሴ የተፈለፈለ የዋሻ ገዳም ✤በቅሎ አግት / ዝንጀሮ አስጨብጭብ/ ጨጨሆ መድኃኔዓለም ገዳም ✤ወንጪት መድኃኔዓለም በአብርሃ ወአጽብሃ ዘመነ መንግስት ተመስርቶ እስካሁን ድረስ ነብር በቤተ መቅደሱ እየኖረ በሚጠብቀው በታላቁ ወይን እንጨት ቅዱስ ሚካኤል ገዳም ውስጥ የተሰራ ✤መቀሌ መድኃኔዓለም ✤አድግራት መድኃኔዓለም ወቅድስት ሥላሴ ወቅዱስ ቂርቆስ ገዳም ብዙ ድንቅ ታሪክ ያለው ✤ደባርቅ መድኃኔዓለም ✤የሽረት መድኃኔዓለም እጅግ ተደንቀውና ተደምመው ምስጋናዎ ኢምንት ሆናብዎት የሚመለሱበት ✤ኮሶ በር መድኃኔዓለም ✤ሐረር መድኃኔዓለም ✤ምስካበ ቅዱሳን ጻድቃኔ ዋሻ መድኃኔዓለም ገዳም ✤እመኪና መድኃኔዓለም ገዳም በመናኔው ጻድቅ ንጉሥ በአጼ ካሌብ ልጅ በጻድቁ ንጉሥ በአጼ ገብረ መስቀል በ6ኛው መ.ክ.ዘ. የተመሰረተ ታሪካዊ ገዳም ✤በሬ አገር መድኃኔዓለም ገዳም 1000 ሜትር ፍልፍል ዋሻ ገዳም ✤ደብረ ታቦር መድኃኔ ዓለም ✤ደብረ ዘይት መድኀኔ ዓለም ቤ.ክ፤ ደብረ ዘይት ከተማ፤ ባቦጋያ አጠገብ ✤ ናዝሬት መድኃኔዓለም ✤ተከዜ መድኃኔዓለም ገዳም በ11ኛው መ.ክ.ዘ. የላስታ ንጉሥ ቅዱስ ገብረ ማርያም /ታላቁ ሐርቤይ/ ደቀመዝሙር እንደነ ነቢዩ ኤልያስና ወንጌላዊው ቅ.ዮሐንስም ሞትን ሳያይ እስከ ምጽዓተ ሐሳዊ መሲህ /ዳግም ምጽአተ ክርስቶስ ዋዜማ/ ድረስ የተሰወረው ጻድቁ አቡነ ሐዋርያ ክርስቶስ ታቦተ ኪዳነ ምሕረትን ከሰማይ ተቀብሎ የመሰረተው ንዑድ ክቡር የሆነ መካነ ጸሎት ወአርምሞ ወትኅርምት ✤ሬማ መድኃኔዓለም አንድነት ገዳም፦ በ1414 በአባ ኖብ የተመሰረተና የብዙ ቅዱሳን መካነ ጸሎት የነበረ በዘመነ ሱስንዮስ ሰማእትነትን የተቀበለቺው ጻድቅት ወሰማእት ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ አጽሟ ያለበትና የከበረና የማይሻር ቃልኪዳኑን ከአምላከ ቅዱሳን የተቀበለችበት እፁብ ድንቅ ሥፍራ ሲሆን የሰማእቷን ጨምሮ በርካታ ቅዱሳን አጽማቸው የሚገኝበት ጥንታዊ ገዳም

በኢትዮጵያና በአሜሪካ የሚገኙ የመድኀኔዓለም ገዳማትና አድባራት፤ የፎቶ ስብስብ 7፤ 1. ✤ላፍቶ ሌንቃ መድኀኔዓለም ቤተክርስቲያን፤ 2. ✤መድኃኔዓለም ቤ.ክ፤ ደብረ ሊባኖስ አጠገብ 3. ✤የቲሊሊ ደብ
+5
በኢትዮጵያና በአሜሪካ የሚገኙ የመድኀኔዓለም ገዳማትና አድባራት፤ የፎቶ ስብስብ 7፤ 1. ✤ላፍቶ ሌንቃ መድኀኔዓለም ቤተክርስቲያን፤ 2. ✤መድኃኔዓለም ቤ.ክ፤ ደብረ ሊባኖስ አጠገብ 3. ✤የቲሊሊ ደብረ ገነት መድኃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን 4. ✤ሚዛን ተፈሪ መድኀኔዓለም ቤተክርስቲያን 5. ✤ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም 6. ✤ኒውዮርክ መድኀኔ ዓለም

በኢትዮጵያ የሚገኙ የመድኀኔዓለም ገዳማትና አድባራት፤ የፎቶ ስብስብ 6፤ 1. ✤ደጀን አበ ብዙኃን አብርሃም ወመድኃኔዓለም፤ ደጀን ጎጃም 2. ✤አርባምንጭ ደብረ መድኃኒት መድኀኔዓለም ቤተክርስቲያን፤
+5
በኢትዮጵያ የሚገኙ የመድኀኔዓለም ገዳማትና አድባራት፤ የፎቶ ስብስብ 6፤ 1. ✤ደጀን አበ ብዙኃን አብርሃም ወመድኃኔዓለም፤ ደጀን ጎጃም 2. ✤አርባምንጭ ደብረ መድኃኒት መድኀኔዓለም ቤተክርስቲያን፤ አርባ ምንጭ ከተማ 3. ✤ቦራራ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን 4. ✤ደብረ ቀራንዮ መድኀኔዓለም ወቅዱስ ላሊበላ ቤ.ክ፤ ጎንደር 5. ✤ጌቴ ሴማኔ ፈረስ ቤት መድኀኔዓለም ቤተክርስቲያን፣ ደብረ ማርቆስ 6. ✤ወልዲያ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም፡፡

በኢትዮጵያ የሚገኙ የመድኀኔዓለም ገዳማትና አድባራት፤ የፎቶ ስብስብ 5፤ 1. ✤ዋሻ መድኃኔ ዓለም አቡነ ሙሴ ቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳም 2. ✤አርብዓሐራ ምስካበ ቅዱሳን መድኀኔዓለም ገዳም(ምስካ
+6
በኢትዮጵያ የሚገኙ የመድኀኔዓለም ገዳማትና አድባራት፤ የፎቶ ስብስብ 5፤ 1. ✤ዋሻ መድኃኔ ዓለም አቡነ ሙሴ ቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳም 2. ✤አርብዓሐራ ምስካበ ቅዱሳን መድኀኔዓለም ገዳም(ምስካበ ቅዱሳን መድኀኔዓለም ገዳም)፦ ደመ ክርስቶስን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ዑራኤል የተቀበለበትን የብርሃን ጽዋ የሚያጥኑና ሌሎችንም ቅዱሳንን አጽም በንሥር አሞራ የተመሰለ የጌታ መልአክ በቀስተ ደመና ተከብቦ በቀን የሚያመጣበት እልፍ ታሪክና ብዙ የብዙም ብዙ ገቢረ ተአምራት የሚፈጸሙበት ለተፈቀደላቸውና እንደሚገባ ሆነው በቦታው ላይ በበጎ ኅሊና ለሚጸልዩ ምዕመናን ሥውራኑ እየተገለጡ ጥያቄያቸውን የሚመልሱበት ግርማ ያለው ክቡር ንዑድ የ40ዎቹ ቅዱሳን ሰማእታት መካነ ጸሎት የአቡነ ሐራ ግብፃዊ የቃልኪዳን ሥፍራ 3. ✤ጨጨሆ መድኀኔዓለም፤ ወሎና ጎንደር ድንበር ላይ 4. ✤በደሌ ደብረ ሣህል መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን፤ ከ100 ዓመት በላይን ያስቈጠረ ጥንታዊ ቤ.ክ. 5. ✤ደሴ መድኃኔዓለም 6. ✤ወዘም ባሕታዊ መድኃኔዓለም፣ ፍቼ አጠገብ ሰሜን ሸዋ