ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

الذهاب إلى القناة على Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

إظهار المزيد

📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

تُعد قناة Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 15 790 مشتركاً، محتلاً المرتبة 5 384 في فئة الدين والقيم الروحية والمرتبة 2 253 في منطقة Ethiopia.

📊 مؤشرات الجمهور والحراك

منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 15 790 مشتركاً.

بحسب آخر البيانات بتاريخ 14 أكتوبر, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار 236، وفي آخر 24 ساعة بمقدار 0، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.

  • حالة التحقق: غير موثّقة
  • معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 9.49‎%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 9.51‎% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
  • وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 1 498 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 1 501 مشاهدة.
  • التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 13.

📝 الوصف وسياسة المحتوى

يصف المؤلف القناة بأنها مساحة للتعبير عن الآراء الذاتية:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 15 أكتوبر, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة الدين والقيم الروحية.

15 790
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+1837 أيام
+23630 أيام
أرشيف المشاركات
፫. መሎጥ አምባ ጊዮርጊስ (አንድ መግቢያ እና መውጫ ያለው፤ ዐፄ ይኵኖ አምላክ ከመንገሡ በፊት በአያቱ መሐሪዉ አምላክ በግዞት የታሰረበት፤) አድራሻ፤ ደቡብ ወሎ ሃገረ ስብከት፥ ዋድላ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደሴ → ዋድላ፡፡ ፬. ደብረ ድማኅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም፤ አድራሻ፤ ምሥራቅ ጎጃም ሃገረ ስብከት፥ ደብረ ድማኅ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ባሕር ዳር መንገድ (በሞጣ መስመር) → ደብረ ድማኅ፡፡ ፭. ሞጣ ጊዮርጊስ፤ አድራሻ፤ ምሥራቅ ጎጃም ሃገረ ስብከት፥ ሞጣ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ባሕር ዳር መንገድ (በሞጣ መስመር) → ሞጣ፡፡ ፮. መሐል ዘጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ፤ አድራሻ፤ ምዕራብ ጎጃም (ባህር ዳር) ሃገረ ስብከት፥ ባሕር ዳር ከተማ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ባሕር ዳር፡፡ ፯. ባሕር ዳር ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ፤ አድራሻ፤ ምዕራብ ጎጃም (ባሕር ዳር) ሃገረ ስብከት፥ ባሕር ዳር ከተማ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ባሕር ዳር፡፡ ፰. ዋሻ ነጎድጓድ ጊዮርጊስ ገዳም፤ (በ16ኛው ክ/ዘመን በዐፄ ልብነ ድንግል ዘመን የተመሠረተ፤ ፈዋሽ ጠበል ያለበት) አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሃገረ ስብከት፥ መንዝ ላሎ ምድር፤ (ከአ.አ. 293 ኪ.ሜ.) ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → መንዝ ላሎ → ወገሬ ከተማ → ዝንዝ (ጦጥ) (ዘብር)፡፡ ፱. ጎንደር እልፍኝ ጊዮርጊስ፤ (ከ44ቱ ታቦታተ ጎንደር አንዱ) አድራሻ፤ ማዕከላዊ ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ ጎንደር ከተማ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር፤ ፋሲለደስ ቤተ መንግሥት፡፡ ፲. ጎንደር ቀዳሜ አድባራት አበራ ጊዮርጊስ፤ (ከ44ቱ ታቦታተ ጎንደር አንዱ) (በጎንደር ከተማ ታቦቱ ወደ ጥምቀተ ባሕር ወርዶ የሚከበርበት) አድራሻ፤ ማዕከላዊ ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ ጎንደር ከተማ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር፥ ኮሌጅ፡፡ ፲፩. ደሴ ጊዮርጊስ፤ አድራሻ፤ ደቡብ ወሎ ሃገረ ስብከት፥ ደሴ ከተማ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደሴ፡፡ ፲፪. ወራኢሉ ጊዮርጊስ፤ አድራሻ፤ ደቡብ ወሎ ሃገረ ስብከት፥ ወራኢሉ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደሴ → ወራኢሉ፡፡ ፲፫. ግሸን ጊዮርጊስ፤ አድራሻ፤ ደቡብ ወሎ ሃገረ ስብከት፥ አምባሰል ወረዳ፥ ግሸን፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደሴ → ግሸን፡፡ ፲፬. ጋሞ ጎፋ ካምባ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ን፤ አድራሻ፤ ጋሞ ጎፋ ሃገረ ስብከት፥ ካምቦ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. አየር ጤና አውቶቡስ ተራ → ጋሞ ጎፋ (አርባ ምንጭ) → ካምቦ፡፡ ፲፭. ቆላድባ ኳሬና ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ን፤ አድራሻ፤ ማዕከላዊ ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ ደምቢያ ወረዳ (ማሩ ቀመስ)፥ ቆላ ድባ ከተማ ፤ (ከጎንደር ከተማ 35 ኪ.ሜ.) ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር አዘዞ አውቶቡስ ተራ → ቆላድባ፡፡ ፲፮. ደብረ ታቦር ጊዮርጊስ ቤ/ን፤ አድራሻ፤ ደቡብ ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ ደብረ ታቦር ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደብረ ታቦር፡፡ ወይም፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ባሕር ዳር → ወረታ → ደብረ ታቦር፡፡ ፲፯. አገው ምድር ሳሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ን፤ አድራሻ፤ አዊ ዞን ሃገረ ስብከት፥ አገው ምድር (አዊ) (ምዕራብ ጎጃም) ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → አዊ (በቡሬ፥ ባሕር ዳር መስመር)፡፡ ፲፰. ድሬደዋ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ን፤ አድራሻ፤ ድሬደዋ ሃገረ ስብከት፥ ድሬደዋ ከተማ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቃሊቲ አውቶቡስ ተራ → ድሬደዋ፡፡ ፲፱. ደብረ ሲና ጉርጅ ጊዮርጊስ ቤ/ን፤ አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሃገረ ስብከት፥ ሲያ ደብር፥ ዋዩ ወረዳ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. አስኮ አውቶቡስ ተራ → ሆለታ/ኢንጪኒ/፡፡ ፳. ኢንጭኒ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ን፤ አድራሻ፤ ምዕራብ ሸዋ ሃገረ ስብከት፥ ኢንጪኒ፤ (ከአ.አ. በሆለታ 65 ኪ.ሜ.) ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደብረ ብርሃን → ደነባ → ሲያ ደብር → በእግር፡፡ ፳፩. ኢንጭኒ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ን፤ አድራሻ፤ ምዕራብ ሸዋ ሃገረ ስብከት፥ ኢንጪኒ፤ (ከአ.አ. በሆለታ 65 ኪ.ሜ.) ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደብረ ብርሃን → ደነባ → ሲያ ደብር → በእግር፡፡ ፳፪. ቆሪቻ ኮቲቻ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ን፤ አድራሻ፤ ምዕራብ ሸዋ ሃገረ ስብከት፥ ጮቢ ወረዳ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. አስኮ አውቶቡስ ተራ → በአምቦ መስመር (ጊንጪ) → ጮቢ → ቆሪቻ ኮቲቻ፡፡ ፳፫. ጊዶሌ የጋርዱላው (የዐድዋው) ጊዮርጊስ ቤ/ን፤ ፳፬. ያበደማን ጊዮርጊስ ቤ/ን፤ ፳፭. ደንደገብ ጊዮርጊስ ቤ/ን፤ ፳፮. አትርፎ ጊዮርጊስ ቤ/ን፤ የአድራሻ ምንጭ /ገዳማትና አድባራት ገጽ/ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #ቅዱሳን #Saints #ክብረ_በዓላት #Feasts https://youtu.be/3o4wj7Qqcaw...

እንኳን ለቅድሱ ጊዮርጊስ ስባረ ዓፅሙ (ዝርወተ አጽሙ ) በሰላም አደረሳቹሁ ፠ ዐላውያን ነገሥታት በደብረ ይድራስ ተራራ ላይ የሊቀ ሰማዕቱን ሥጋውንና አጥንቱ በመንኰራኵር ፈጭተው በነፋስ ለበተኑበት፤ ነገር ግን ለአምላካችን የታመነ ሰማዕት በመሆኑ ያረፈበት መሬትና ዕፅዋት ጊዮርጊስ ቅዱስ ለእግዚአብሔር እያሉ ያመሰገኑበት ነው፡፡ ------------ ....ነገሥታቱም ጊዮርጊስን ሙታኖችን ብታስነሳ በአምላክህ እናምናለን አሉ ፤በጸሎቱ ሙታኖችም አስነሳላቸው በጌታቸንም ስም አምነው በእርሱ ስም አስተማሩ ጥምቀትንም ተቀበሉ ፡፡የቀሩት ነገሥታት ግን ሰይጣናትን ነው ያሳየኸን ብለው ተከራከሩ ፡፡ ※ ከአንዲት እምበለት ቤት ተቀምጦ ምግብ ልትፈልግለት ሄዳ በተመለሰች ጊዜ ቤቷ ላይ ተአምር አየች ፤ የክርስቲያኖች አምላክ በሰው ተመስሎ እኔ ጋር መጣ ብትል ቅዱስ ጊየርጊስም #_እኔ_አምላክ_አይደለሁም_የአምላክ_ባርያ_ነኝ እነጂ አላት፡፡ የአምላክ አገልጋይ ከሆንክ ቸርነትህ እንድትደርሰኝ እለምናለሁ አለችው ልጇንም በመስቀል ምልክት አማትቦበት ከዕውርነት አድኖታል ፡ ※ ንጉሡም ተአምር ማድረጉን በሰማ ጊዜ በመንኰራኵርም ፈጨው ከከተማ ውጪ ወስደው ጣሉት ከሞትም ተነሣ ተመለሶም ወደ ነገሥታቱ ሄደ ፡፡ንጉሡም አድንቆ ይለምንው ጀመር በመንግሥቱ ላይ ሁለተኛ ያደርገው ዘንድ ቃል ገባለት ቅዱስ ጊዮርጊስ እየዘበት ነገ ጠዋት ለአማልክቶች እሰዋለሁ ብሎት አደረ ፡፡ በሚጸልይበትም ጊዜ የንጉሡ ሚስት ሰምታ ጠየቀችው እርሱም ስለ ጌታችን አስተምራት አመነች ፡፡ በማግሥቱም ንጉሡ ሰውን ሰብስቦ እንደሚጠብቀውና እውነት መስሎ በታያት ጊዜ አዘነች ፡፡እርሱም ልጅሽን በምድር ላይ አኑሪው አላት ከዚያም ወደ አጵሎን (ጣዖቱ) ሂድ ወደ እኔም እንዲመጣ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እዘዘው አለው ፡፡ ልጁም ድኖ ቅዱሱ እንዳለው ሄዶ አዘዘው ፡፡ በጣዖቱም የነበረው እርኩስ መንፈስ ወጥቶ እኔ ሰውን የማስት እንጅ አምላክ አይደለሁም አለው ፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስም ምድር ትውጠው ዘንድ አዘዛት ወዲያውኑ ዋጠችው ጣዖቱንም ከአገልጋዮቻቸው ጋር አጠፋቸውን ንጉሡም ከወገኖቹ ጋር አፈረ፡፡ ሙሉውን ታሪክ እዚህ ያንብቡ ----> https://t.me/medihanaelem/6273 ፠ እንደ ጎንደር አበራ ጊዮርጊስ ባሉት ክብረ በዓሉ ወደ ባሕረ ጥምቀቱ ወርዶና አድሮ ነው በዓሉ የሚከበረው፡፡ በጎንደር በጥር ወር የሚከበሩ በዓላት ወደ ጥምቀተ ባሕር በመውጣት የሚከበሩ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ጥር 18 አበራ ጊዮርጊስ፤ ጥር 21 ሎዛ ማርያም፣ ጥር 22 ቅዱስ ዑራኤል (በዓታ ያለው)፤ ጥር 25 ቅዱስ መርቆሬዎስ (በተለይ በገጠሩ አካባቢ፡፡) እርሱ እንደ ንብ አውራ ፈረሱ እንደ አሞራ፤ ጊዮርጊስ፥ ጊዮርጊስ፥ ጊዮርጊስ ኢትዮጵያን አደራ፡፡ ሰአል ለነ ጊዮርጊስ፤ ሰማዕተ ኢየሱስ ክርስቶስ፡፡ ዘሐረፀከ ዱድያኖስ፤ ወወገረከ ደብረ ይድራስ፤ ዘዘረወከ በነፋስ፡፡ ጥር ፲፰፤ በአዲስ አበባ የሚከበርባቸው #፲፯ #ገዳማትና አድባራት፡፡ ፩. ሣሎ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ክ፤ (ከ186 ዓመታት በላይ ታሪክ ያለው) አድራሻው፤ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ፥ ሣሎ፥ በቶታል ገባ ብሎ፤ ታክሲ፤ ከመገናኛ(ከፒያሳ) → ሳሪስ /ቃሊቲ/ → ሣሎ፤ ፪. መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ክ፤ አድራሻው፤ አራዳ ክፍለ ከተማ፥ ፒያሳ፥ ዳግማዊ ምኒልክ አደባባይ፤ ታክሲ፤ ከማንኛውም አዲስ አበባ አቅጣጫ → ፒያሳ /ጊዮርጊስ/፤ ፫. (ቤተል) ደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ ቤተል፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ ሸዋ ዳቦ ቤት (ጦር ኀይሎች) → ቤቴል፡ ፬. ፈረንሳይ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ ብረት ድልድይ፤ ታክሲ፤ ከአራዳ ጊዮርጊስ (ከ4 ኪሎ) (ከ6 ኪሎ) → ፈረንሳይ→ ብረት ድልድይ፡፡ ፭. ኮተቤ ሃገረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ፥ ቅድስት ማርያምና ቅድስት መግደላዊት ማርያም ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ አንቆርጫ፤ ታክሲ፤ ከአራዳ ጊዮርጊስ (ከ4 ኪሎ) (ከ6 ኪሎ) → ፈረንሳይ→ አንቆርጫ፡፡ ፮. ኮተቤ ደብረ ልዳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቅድስት ኪዳነ ምሕረትና አቡነ ሀብተ ማርያም ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ አባዶ፥ ካራ፤ ታክሲ፤ ከመገናኛ → ኮተቤ/አባዶ/ካራ፡፡ ፯. ቦሌ ገርጂ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስና ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ፤ (በ2012ዓ.ም. የ24ት ሰፈር ወጣቶች ሰማዕት ኾኑት በክብር ያረፉበት ደብር) አድራሻ፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ፥ ገርጂ፤ ታክሲ፤ ከመገናኛ → ገርጂ፡፡ ፰. ቦሌ አየር ማረፊያ መንበረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ፥ አየር ማረፊያ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ(መገናኛ) → ቦሌ አየር ማረፊያ፡፡ ፱. ቦሌ ሰሚት ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስና ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ፥ ሰሚት ኮንዶሚኒየም፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ → መገናኛ → ሰሚት ኮንዶሚኒየም፡፡ ፲. ቦሌ አራብሳ ዋሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ፥ አራብሳ፥ ዐደባባዩ ጋራ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ → መገናኛ → አራብሳ (ኮንዶሚንየም /ዐደባባዩ ጋራ/)፡፡ ፲፩. ቱሉ ዲምቱ ደብረ ሰላም ቅዱስ ጊዮርጊስና ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ አቃቂ/ቃሊቲ ክፍለ ከተማ፥ ኬላ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ(መገናኛ) → ቃሊቲ → ቱሉ ዲምቱ፡፡ ወይም፤ ከመገናኛ → ቱሉ ዲምቱ (በ… መንገድ)፡፡ ፲፪. አያት 49 ጀልዱ ቅዱስ ጊዮርጊስና ኪዳነ ምሕረት ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ፥ አያት ጠበል (አያት 49)፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ → መገናኛ → አያት ጠበል → አያት 49፡፡ ፲፫. ደብረ መዊዕ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፥ ሐና፥ ማንጎ ሰፈር፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ → ሜክሲኮ → ሐና /ማንጎ ሰፈር/፡፡ ፲፬. አስኮ ደብረ መንክራት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ አስኮ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ(ዊንጌት) → አስኮ፡፡ ፲፭. ለቡ ደብረ ታቦር በዓለ ወልድና አበ ብዙኃን አብርሃም ገዳም፤ (በድርብነት ይከብራል) አድራሻ፤ ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ፥ ለቡ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ → ሜክሲኮ → ለቡ፡፡ ፲፮. አስኮ ደብረ መድኀኒት መድኀኔ ዓለምና ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ክ፤ (በድርብነት ይከብራል) አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ አስኮ አዲስ ሰፈር፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ(ዊንጌት) → አስኮ አዲስ ሰፈር፡፡ ፲፯. ብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ ወቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ፤ (በድርብነት ይከብራል) አድራሻ፤ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ፥ ጄነራል ዊንጌት ት/ቤት፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ(ከመርካቶ) → አስኮ/ዊንጌት/፡፡ #በኢትዮጵያና_በዓለም_አቀፍ_ደረጃ_የሚከበርባቸው_ #፳፮ #ጥንታውያን #ገዳማትና_አድባራት፡፡ (በዘመነ አስተርእዮ የሚወጡ ታቦታት በአንዳንድ የሃገራችን ክፍሎች እንደ ጥምቀት በዓል ታቦታቱ ወደ ትምቀተ ባሕር በመውረድ ነው የሚያከብሩት) ፩. ብልባላ ጊዮርጊስ፤ (ከ1500 ዓመታት በላይ ዕድሜ ያለው/ላሊበላ ከማነጹ 600 ዓመታት በፊት የታነጸ፥ ከ485 ዓ.ም እስከ 536 ዓ.ም. በንጉሥ አፄ ካሌብ ከአንድ ቋጥኝ ተፈልፍሎ የታነጸ)፡፡ አድራሻ፤ ላስታ ላሊበላ ሃገረ ስብከት፥ ብልባላ ወረዳ፥ ብልባላ ከተማ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ላሊበላ → ብልባላ (በሰቆጣ መስመር) (ከላሊበላ 30 ኪ.ሜ.)፡፡ ፪. ደብረ ሮሐ ቅዱስ ላሊበላ ቤተ ጊዮርጊስ፤ አድራሻ፤ ላስታ ላሊበላ ሃገረ ስብከት፥ ላሊበላ ከተማ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ላሊበላ፡፡

የእርዳታ ጥሪ በቀ/ደ/ሰ መድኀኔዓለም ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት አገልጋይ የሆነችው እኀታችን ርግበ ወልደ ጊዮርጊስበደረሰባት የኩላሊት ህመም ምክንያት በአስቸኳይ የሕክምና እርዳታ ማግኝት እንዳለ
የእርዳታ ጥሪ በቀ/ደ/ሰ መድኀኔዓለም ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት አገልጋይ የሆነችው እኀታችን ርግበ ወልደ ጊዮርጊስበደረሰባት የኩላሊት ህመም ምክንያት በአስቸኳይ የሕክምና እርዳታ ማግኝት እንዳለባት የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል አስታውቋል፡፡ በዚህ ሰዓትም የዲያሊስስ (dialysis) ሕክምና እያረገች ትገኛለች፡፡ የንቀለ ተከላ ሕክምና አስክትጀምር ድረስም በሳምንት ከ 6000 ብር በላይ እያወጣች ትገኛለች፡፡ ለሕክምናውም አቅም ስለሌላት የተቻላቹሁን ያክል እንድትረዷት በመድኀኔዓለም ስም እንጠይቃለን፡፡ 1000450996727 | አስኳል አረጋዊ ፣ መስታወት ይጥና ፣ ቢልልኝ ታከለ 0910299573 | 0934984689 | 09 11864443

የእርዳታ ጥሪ በቀ/ደ/ሰ መድኀኔዓለም ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት አገልጋይ የሆነችው እኀታችን ርግበ ወልደ ጊዮርጊስበደረሰባት የኩላሊት ህመም ምክንያት በአስቸኳይ የሕክምና እርዳታ ማግኝት እንዳለባት የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል አስታውቋል፡፡ በዚህ ሰዓትም የዲያሊስስ (dialysis) ሕክምና እያረገች ትገኛለች፡፡ ለሕክምናውም አቅም ስለሌላት የተቻላቹሁን ያክል እንድትረዷት በመድኀኔዓለም ስም እንጠይቃለን፡፡ 1000450996727 | አስኳል አረጋዊ ፣ መስታወት ይጥና ፣ ቢልልኝ ታከለ 0910299573 | 0934984689 | 09 11864443

#ጥር_15_በ2ት_ዓመት_ከ9ኝ #ወሩ_ሰማዕትነትን_የተቀበለው_ቅዱስ_ቂርቆስ_በ3_ዓመት_ከ1_ወር_ከ3#ቀኑ_አንገቱን_በሰይፍ_ተቆርጦ_ሰማዕትነትን_የተቀበለበት_በዓለ_ዕረፍቱ_ነው፡፡ #በነገታው_በጥር_16ም #እናቱ_ቅድስት_ኢየሉጣ_በክብር_ያረፈችበት_ነው #ስምህ_በተጠራበት_ቤተ_መቅደስህ_በታነጸበት_ስዕልህ_ባለበት_ቦታ_ሁሉ_የሕፃናት_እልቂት_የከብት_በሽታ_የእህል_እጦት_ረሀብ_ቸነፈር_አይደርስም የሚል ቃልኪዳንም ጌታችን ገብቶለታል፡፡ #በገባለት ቃል ኪዳንም መሠረት በመዲናችን #በአዲስ_አበባ በዳግማዊ አፄ ምኒልክ ዘመን የሰው እልቂት የከበት በሽታ ገብቶ በነበረበት ወቅት የቂርቆስ ደብር #መካነ_ሰማዕት ሲተከል የሰውም በሽታ ርቋል፥ የከብት እልቂትም አቁሟል፡፡ #በጎንደር_ደብረ_መንክራት_ቅዱስ_ቂርቆስ_ቤክ_ደግሞ_#ጽዋ_ማስደፋት_ የሚል ሥርዐት አለ በዚህ ሥርዐትም የሰረቀውን ሰው ቅዱስ ቂርቆስ የሚያጋልጥበትና አሁንም ድረስ የሚታይ አስደናቂ ተዓምር ነው፡፡ ፠ የሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ አባቱ ቆዝሞስ (ስምዖን) እናቱ ኢየሉጣ ሲባሉ፤ የተወለደው በዘመነ ሰማዕታት በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን በኅዳር 15 ቀን ነው፡፡ የትውልድ ሀገሩ በታችኛው እስያ ልዩ ስሙ አንጌቤን ይባላል፡፡ ፠ አንጌቤናይት ብጽዕት ኢየሉጣም ባሏ በሕይወት ባለ መኖሩ በመበለትነት ትኖር ነበር፤ በዘመኑ የነበረው መምለኬ ጣዖት የሆነው ንጉሥ እስክንድሮስ ቅድስት ኢየሉጣን ‹‹ለጣዖቴ ስገጂ›› ብሎ አስገደዳት፡፡ እርሷም ‹‹ሕፃኑ ልጄ መጥቶ ይመስክር›› ብላ ስትናገር ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ተጠራና ተጠየቀ፡፡ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስም ‹‹ለጣዖት አንሰግድም፣ ዘላለማዊ የሆነ የማይሻር አምላክ ስላለ ለእርሱ ነው የምንሰግደው›› ብሎ የአምላኩን ክብር በሕፃን አንደበቱ መሰከረ፡፡ ሕፃኑም ይህንን በመሰከረ ጊዜ ዕድሜው ገና ሁለት ዓመት ከዘጠኝ ወሩ ነበር፡፡ ፠ ንጉሡም እጅግ ተቆጥቶ 40 ጋን ውኃ የሚይዝ በርሜል አስጥዶ 40 ቀን ሙሉ እሳት አስነድዶ ቅንጭብ፣ ዘይት፣ ዝፍጥና ሌላም በእጅጉ የሚጎዱ ነገሮችን (ሰም፣ ጨው፣ ባሩድ፣ ሙጫ፣ እርሳስ፣ ብረት፣ ቅንጭብ፣ ቁልቋል) በውስጡ አስጨመረ፤ የእሳቱ ድምፅ እንደ ነጎድጓድ እስኪሰማ፥ ወላፈኑም እንደ ፀሐይ እስኪያንጸባርቅ ድረስ ሆነ፡፡ የፍላቱም ኃይል 14 ክንድ ያህል እየዘለለ ወጣ፡፡ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱን ቅድስት ኢየሉጣን ወደዚያ እቶኑ እሳት እንዲከቷቸው አዘዘ፡፡ በዚያን ጊዜም 11,004 እስረኞች ከእስር ወጥተው እንዲያዩ ሹሙ አዘዘ፡፡ ቅድስት ኢየሉጣም የፍላቱን ግርማ ባየች ጊዜ ተሸበረች፡፡ ተጠብቆላት ያለውንም ዋጋ ትታ ልትክድ ፈለገች፡፡ ቅዱስ ቂርቆስም ይህን ባወቀ ጊዜ "እናቴ ሆይ ከብረት ጋን ግርማ የተነሳ አትፍሪ፤ ድንጋፄም አይደርብሽ" እያለ ከብሉይና ከሐዲስ እየጠቀሰ እንድትጸና አስተማራት፡፡ ፠ እናቴ ሆይ አናንያ አዛርያንና ሚሳኤልን ያዳናቸው እግዚአብሔር እኛንም ከዚህ ከብረት ጋን ውስጥ ሊያድነን ይችላል፡፡ እናት ሆይ ከሚያልፈው ከዚህ ዓለም ጭንቅ ልታመልጭ በሚያልፈው በዘለዓለም እሳት ልትቀጭ ትሻለች፡፡ እናት ሆይ ይህን አትፈልጊ፤ ይቅርብሽ አሁን እግዚአብሔር በመካከላችን አለና ይረዳናል፡፡... እያለ አብዝቶ መከራት፡፡ ነገርግን በዚህም ምክር እናቱን መመለስና ለሰማዕትነት ማዘጋjት አልቻለም፡፡ ከዚህ በኋላ ቂርቆስ ዓይኖቹን ወደሰማይ አቅንቶ መጸለይ ጀመረ፡፡ ‹‹እግዚአብሔር ሆይ ይህች ባርያህ ከምትክድ ከሕይወት መጽሐፍ እኔን ፋቀኝ...›› ብሎ ጸለየ፡፡ በዚያን ጊዜ ዲያብሎስ ከእርሷ ሸሽቶ ሄደ፡፡ ከዚህ በኋላ ቅድስት እናቱ እንዲህ አለች፤ በመንግሥተ ሰማያት አባት የሆንከኝ ልጄ ሆይ ጌታህ ኃይል ሰጠኝ፡፡ የሚጠብቀንን ገድላችንን እንፈጽምና ድል እንነሣ›› አለችው፡፡ የብረት ጋኑን ሲነድ ሳየው በምንጭ ላይ በዝቶ እንደሚወርድ ጠል ሁኖ አየዋለሁና፡፡ እያለች እየነገረችው ሳለ አንሠተው ከብረት ጋኑ ውስጥ ጨመሯቸው፡፡ በውስጡም አንገትን የሚቆለምም ልብን የሚያጣምም ሆድን የሚሰነጥቅ ሥርንም የሚበጥስ መሣሪያ ነበረበት፡፡ ወዲያውም የራማው ልዑል ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል እንደ ዐይን ጥቅሻ ፈጥኖ ከሰማይ ወረደና የብረት ጋኑን እሳት ፈጽሞ አበረደው፡፡ ከቅዱሳንም አንዱን እንኳን ሳይነካው የብረት ጋን ማቃጠሉና መፍላቱ ፀጥ አለ፡፡ እንደ ውኃም ሆነ፡፡ ፠ ንጉሡም እሳቱ እንዳልጎዳቸው ሲያውቅ ከዚያ አውጥቶ፤ * በአፍና አፍንጫቸው መርዝ ከተተበት፣ ነገር ግን መርዙ ምንም አልጎዳቸውም እንዳውም ምግብ ሆነላቸው፡፡ * ጨውና በርበሬ በዐይናቸው አነደደበት፡፡ አሁንም ምንም አልነካቸውም፡፡ * ዐሥራ አራት የተሳሉና የጋሉ ብረቶች፤ ሰባቱን በእናቱ በኢየሉጣ አካል፥ ሰባቱን በቂርቆስ አካል ውስጥ (ከነዚሁም ሁለቱን በጆሮዎቹ፥ ሁለቱን በዓይኖቹ፥ ሁለቱን በአፍንጫዎቹ፥ አንዱን በልቡ) ተከሉ፤ አሁንም ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ፈወሳቸው፡፡ * በ4 ችንካሮች ላይ አስቀመጧቸው፤ መልአኩ ፈወሳቸው * የራስ ጠጕራቸውን ከቆዳቸው ጋር ገፈው በእሳት ውስጥ ጨመሩት፤ ቅዱስ ገብርኤል እንደ ዐይን ጥቅሻ ፈጥኖ መጥቶ ፈወሳቸው፡፡ * በመቃን ውስጥ ጨመረው በገመድ ሰቀሏቸው፤ መልአኩ አዳናቸው፡፡ (ሐምሌ 19 ቀን የምናከብረው ክብረ በዓል ከላይ ያሉትን ሁሉ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ለቅዱስ ቂርቆስና ኢየሉጣ የተራዳበትን በማሰብ ነው፡፡) ፠ ንጉሡም በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ በብዙ ጭንቅና ሥቃይ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣን ለ3 ዓመታት አሠቃያቸው፡፡ እነርሱም መከራን እየተቀበሉ በከሀዲው ንጉሥ ፊት የአምላካቸውን ስም እየጠሩ መሰከሩ፡፡ ፠ በመጨረሻም ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ተጋድሎውን ፈጽሞ ጥር 15 ቀን በ3 ዓመት ከ1 ወር ከ3 ቀኑ አንገቱን በሰይፍ ተቆርጦ ሰማዕትነትን ተቀበለ፡፡ ሲሰየፍም ከአንገቱም ደም፣ ውኃና ወተት የወጣ ሲሆን ሦስት አክሊላትም ወርደውለታል፡፡ ፠ ሕፃኑም በምድር ላይ አልተቀበረም ይልቁንም ጌታችን በኤልያስ ሰረገላ ሥጋውን አሳርጎለታል፤ ሄሮድስ ላስፈጃቸው 144,000 የቤቴልሔም ሕፃናትም አለቃቸው ነው፡፡ እናቱ ቅድስት ኢየሉጣም በጥር 16 ቀን ሰማዕትቷን በክብር ፈጽማለች፡፡ በዚሁ ዕለት የቅዱስ ቂርቆስ ማኅበርተኞች የሆኑ 11,004 ሰዎች የጌታችንን ክብር እየመሰከሩ በሰማዕትነት ዐርፈዋል፡፡ ፠ #በነገታው_በጥር_16ም #እናቱ_ቅድስት_ኢየሉጣ_በክብር_ያረፈችበት_ነው (ምንጭ፤ የቀ.ደ.ሰ መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ፍኖተ ሕይወት ሰሌዳ መጽሔት፣ ከገድላት አንደበትና ዝክረ ቅዱሳን) ሥርዐተ ማኅለሌቱን ከዋይዜማው ጀምሮ አዘጋጅተንላችኋል፡፡ ወረቦቹን፣ እስመ ለዓለም፣ አቡንና ሰላሙን በድምፅ ከፈለጋችሁ በቴሌግራም ገጻችን ያገኛሉ፡፡ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #ቅዱሳን #Saints #ክብረ_በዓላት #Feasts https://youtu.be/3o4wj7Qqcaw...

‹‹ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦትን ሌዋውያን ካህናት ተሸክመውት ባያችሁ ጊዜ ከሰፈራችሁ ተነሥታችሁ ተከተሉት፡፡ ›› ኢያሱ ፫፥፫ የ2014 ዓ.ም የ #በዓለ_ጥምቀት ማስታወሻዎች ፎቶ ስብስብ 1

‹‹ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦትን ሌዋውያን ካህናት ተሸክመውት ባያችሁ ጊዜ ከሰፈራችሁ ተነሥታችሁ ተከተሉት፡፡ ›› ኢያሱ ፫፥፫ የ2014 ዓ.ም የ #በዓለ_ጥምቀት ማስታወሻዎች ፎቶ ስብስብ 1