ar
Feedback
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

الذهاب إلى القناة على Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

إظهار المزيد

📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

تُعد قناة Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 15 399 مشتركاً، محتلاً المرتبة 5 564 في فئة الدين والقيم الروحية والمرتبة 2 183 في منطقة Ethiopia.

📊 مؤشرات الجمهور والحراك

منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 15 399 مشتركاً.

بحسب آخر البيانات بتاريخ 30 يونيو, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار 21، وفي آخر 24 ساعة بمقدار 1، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.

  • حالة التحقق: غير موثّقة
  • معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 21.61‎%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 10.23‎% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
  • وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 3 327 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 1 576 مشاهدة.
  • التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 17.

📝 الوصف وسياسة المحتوى

يصف المؤلف القناة بأنها مساحة للتعبير عن الآراء الذاتية:
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 01 يوليو, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة الدين والقيم الروحية.

15 399
المشتركون
+124 ساعات
+307 أيام
+2130 أيام
أرشيف المشاركات
‹‹ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ ›› ኤፌ 5 ፥ 17 በ መ/ር ቢትወደድ ኅዳር 10 ፤ 2014 ዓ.ም። በድረ ገጻችን ያድምጡ https://finotehiwotsundayschool.com/%e1%8b%93%e1%88%ad%e1%89%a5-%e1%8c%95%e1%89%a3%e1%8a%a4/

#አንኳን_አደረሳቹህ ኅዳር ፲፪፤ ቅዱስ ሚካኤል በእልፍ አእላፍ መላእክት ላይ የተሾመበትና እስራኤልን የመራበት ክብረ በዓል ነው፡፡ በዓለ ሢመቱ_፥ #ወበዓለ_መራኄ_ፍኖቱ_ለቅዱስ_ሚካኤል_ሊቀ_መላእክት_፨ ፨፨፨ #Share ያድርጉ ኅዳር ፲፪ ለሰው ወገን የሚያዝንና የሚራራ፥ በእግዚአብሔር የጌትነት ዙፋን ፊት ሁልጊዜ ለምስጋና የሚቆም፥ ለፍጥረት ሁሉ የሚማልድ፥ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በዓለ ሢመቱና እስራኤላውያንን በባሕረ ኤርትራ ያሸገረበት በዓል ነው፡፡ ፠ #፩ በዓለ ሢመቱ፤ ሚካኤል ማለት ማን እንደ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ከሌሎች መላእክት ጋር በእለተ እሑድ ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ የተፈጠረ ሲሆን፤ እርሱም መጀመሪያ ከ100ው ነገደ መላእክት የ10ሩ ነገደ መላእክት (የኃይላት) አለቃቸው ነበር፤ በተጨማሪም ከሳጥናኤል ውድቀት በኋላ የኃይላት አለቅነቱን እንደያዘ የአጋእዝትን ነገድም (ሳጥናኤል/ሰማልያል/) ይመራቸው የነበሩትን 10 ነገዶችም በአለቅነት ደርቦ አለቃ ኾኗል፤ እንዲሁም በዛሬው ዕለት ለ100ውም(99ኙም) ነገደ መላእክት (ለእልፍ አእላፋት መላእክት) አለቃቸውም ቅዱስ ሚካኤል ኾኖ የተሾመበት ዕለት ነው፡፡ ልዑል ውእቱ ልዑለ መንበር ያሰኘውም ይኸው ነው፡፡ ቅ/ሚካኤል ለሰው ልጆች ምሕረትን ከኅዳር 12 (ከበዓለ ሢመቱ) ጀምሮ እስከ ኅዳር 13 (የአእላፍ መላእክት) በዓል ድረስ ከአምላኩ ለፍጥረታት ሁሉ ምሕረትን የሚለምንበት ዕለታት ናቸው፡፡ ፨፨፨ ፠#፪ እስራኤልን ከግብጽ ባርነት እየመራቸው ማውጣቱን የሚዘከርበት በዓል ነው፡፡ ይህም የሆነው ያዕቆብ በረሃብ 70 ኹኖ ወደ ግብፅ ከወረደ በኋላ ከ215 ዓመታት (አብርሃም ወደ ግብፅ በተሰደደ ከ430 ዓመታት) በኋላ፤ የዮሴፍን ዝና ያልሰማ፥ ዮሴፍን የማያውቅ ፈርዖን በግብፅ ነገሠ፡፡ እስራኤል ከእኛ ይልቅ በዝተዋል ጠላቶቻችን ቢነሱብን ከጣለቶቻችን ጋር ተደርበው ያጠፉናል በማለት አገዛዝ አጸናባቸው፥ ፍርድ አጓደለባቸው፡፡ የእስራኤል ሴቶች ልጅ ሲወልዱ ወንድ ከሆነ እንዲገደል በማድረግ መከራ አጸናባቸው፡፡ ለ215 ዓመታት በግብፅ በባርነት ከቆዩ በኋላ ከዕብራውያን ወገን የሆነችው ራሔል ጭቃ እያቦካች ምጥ በያዛት ጊዜ ከሥራዋ እንዲያሳርፏት ጠየቀች፤ ግብጻውያን ግን የሕፃናቱ ደም ጡቡን ያጠነክራል ርገጭ አሏት፡፡ ከማሕፀኗ የወጡ ሁለት መንትያ ልጆቿን እያየች ከጭቃ ጋር ረገጠች፤ ራሔልም መሪር ልቅሶን አለቀሰች፤ ስለ ልጆቿም መጽናናትን እንቢ አለች፡፡ የእስራኤል ንጉሥ ሆይ የሆነብንን እይ ስትል ራሷን ይዛ ታለቅስ ጀመር ፥ እንባዋንም ወደ ሰማይ ንጉሥ ወደ እግዚአብሔር ረጨች፡፡ የራሔል እንባዋ የሕዝበ እስራኤልን ሁሉ ጩኸት ፥ እሮሮ ይዛ ቅድመ እግዚአብሔር ደረሰች፡፡ “. . . ራሔል ስለ ልጆቿ አለቀሰች የሉምና ስለ ልጆቿ መጽናናት እንቢ አለች” /ኤር 31፥5፤ ማቴ 2፥17/ እንዲል፡፡ ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን አስነሳና፤ በሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል መሪነት፤ 10 ተዓምራትን በምድረ ግብፅ በ11ኛ ተዓምር ደግሞ በኅዳር 12 (ፈርዖንን ከነሠራዊቱ በኤርትራ ባሕር አስጥሞ) ወደ ተስፋይቱ ምድረ መራቸው፡፡ ባሕረ ኤርትራን እስራኤላውያን እንደተሻገሩም የእስራኤል ልጆች የሙሴ የአሮን እኅት ማርያም ከበሮ እየመታች ‹‹ንሴብሖ ለእግዚአብሔር ስቡሐ ዘተሰብሐ ፤ እግዚአብሔር ተዋጊ ነው ስሙም እግዚአብሔር ነው እያሉ፡፡›› ጠላታቸውን የመታላቸውን ፥ እነሱንም በተአምራቱ ያሻገራቸውን ፥ ከጠላታቸው እጅ ያዳናቸውን እግዚአብሔርን አመሰገኑ፡፡ ከዚህ በኋላ መጋቤ ብሉይ ቅዱስ ሚካኤል እየመራቸው ፥ መና ከሰማይ እያወረደላቸው ፥ ውሃ ከጭንጫ እያፈለቀላቸው ፥ ቀኑን በደመና ፥ ሌቱን በብርሃን መርቷቸው አርባ ዘመን ተጕዘው የቃል ኪዳን አገራቸው ምድረ ርስት ከነዓንን (የዛሬዋ ኢየሩሳሌምን) ወርሰዋል፡፡ /ዘጸ. 15/ ከሙሴ በኋላ እስራኤልን የመራው ነቢዩ ኢያሱም እስራኤልን በሚመራበት ጊዜ ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል እስራኤልን ይረዳቸው ነበር፡፡ ከጠላቶቻቸው ጋር ሲዋጉም ሰልፉን ይመራ የነበረው ቅዱስ ሚካኤል ነበር፡፡ ለምሳሌ እስራኤላውያን ከኢያሪኮ አጠገብ በነበሩበት ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል ተገልጦኢያሱን አነጋግሮታል፡፡ ኢያሱ በኢያሪኮ አጠገብ ሳለ ቀና ብሎ ሲመለከት የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ አንድ ሰው ከፊቱ ቆሞ አየ፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ “ከእኛ ወገን ነህ ወይስ ከጠላቶቻችን?” ሲል ጠየቀው፡፡ እርሱም “አይደለሁም ነገር ግን የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ በመሆኔ መጥቻለሁ” ብሎታል /ኢያሱ 5፥13-15/፡፡ ይህ የተመዘዘ ሰይፍ ይዞ ከኢያሱ ፊት ለፊት የቆመው መልአክ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል (እንዲሁም መልአኩ ቅዱስ ራጕኤል) ነው፡፡ ይህን ለአብነት አነሣን እጅ እስራኤል በሚበድሉበት ጊዜ ሁሉ ወደ እግዚአብሔር የሚማልድላቸው ይህ ታላቅ መልአክ መጋቤ ብሉይ ቅ/ሚካኤል ነበር፤ እግዚአብሔር አምላክ በእደ መልአኩ ይጠብቀን፤ ከበዓሉ ረድኤት ፥ በረከት ይክፈለን፤ አሜን፨ ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡ #Share ያድርጉ ሥርዓተ ማኀሌቱ እስመ ለዓለሙን የሰንበትን በማድረግ ተጠቀሙ(ሰርዓ ለነ) በመዲና ከተማችን የሊቀ መልአኩ የቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓል የሚከብርባቸው ገዳማትና አድባራትን እንጠቁማችሁ፡፡ /ፎቷቸውን ያልለጠፍናቸውና ስማቸውን ያልጠቀስናቸውን እንድትልኩልን በሊቀ መልአኩ ስም እንጠይቃለን) 1) *የካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን (ሾላ፤ መገናኛ) 2) *አንቀጸ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል /ጭቁኑ/፤ ፈረንሳይ 3) *ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል (አዲሱ ሚካኤል)፤ አውቶብስ ተራ 4) *ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል፤ /ቦሌ/ 5) *ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ሚካኤል፤ /ላፍቶ/ 6) *ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል፤ (መካኒሣ) 7) *ኮተቤ ደብረ ጽባሕ ቅዱስ ሚካኤል /ሳጠራው/ (ቀድሞ ኮተቤ አሁን ሲምሲ) 8) *ደብረ ምሕረት ሚካኤል (ቀድሞ ወህኒ ቤት ሚካኤል) 9) *መካነ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል 10) *ገነተ አምባ ቅዱስ ሚካኤል 11) *ደብረ ኢዮር ቅዱስ ሚካኤል 12) *ካራ ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ሚካኤልና 24ቱ ካህናተ ሰማይ 13) *ሐያት ጨፌ ኢያሪኮ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን (በ1980ዓ.ም ጽላቱ ከነ ድርሳናቱ ተቀብሮ የተገኘበት) 14) *መንበረ ክብር ቅዱስ ሚካኤል ወአቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም /ኋላ ወቅድስት አርሴማ በሚል እየተጠራ የሚገኝ/፤ (በቀጨኔ በአዲሱ ገበያና በእንጦጦ መሃል ጉብታ ላይ የሚገኝ) እንዲሁም በድርብነት 15) *እንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት 16) *መንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ (ስድስትኪሎ) 17) *ደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ (መስቀል አደባባይ) 18) *ጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ቤ.ክ (ኋላ ጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል በሚል እየተጠራ የሚገኘው)፤ (ኢምግሬሽን አጠገብ) 19) *ደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ (ኋላ ወመካነ ጎልጎታ ቅድስት ድንግል ማርያም በሚል እየተጠራ የሚገኝ ) (ሰሜን ሆቴል አካባቢ) /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/

#አንኳን_አደረሳቹህ ኅዳር ፲፪፤ ቅዱስ ሚካኤል በእልፍ አእላፍ መላእክት ላይ የተሾመበትና እስራኤልን የመራበት ክብረ በዓል ነው፡፡ በዓለ ሢመቱ_፥ #ወበዓለ_መራኄ_ፍኖቱ_ለቅዱስ_ሚካኤል_ሊቀ_መላእክት_፨ ፨፨፨ #Share ያድርጉ ኅዳር ፲፪ ለሰው ወገን የሚያዝንና የሚራራ፥ በእግዚአብሔር የጌትነት ዙፋን ፊት ሁልጊዜ ለምስጋና የሚቆም፥ ለፍጥረት ሁሉ የሚማልድ፥ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በዓለ ሢመቱና እስራኤላውያንን በባሕረ ኤርትራ ያሸገረበት በዓል ነው፡፡ (እንኳን አደረሳችሁ) ፠ #፩ በዓለ ሢመቱ፤ ሚካኤል ማለት ማን እንደ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ከሌሎች መላእክት ጋር በእለተ እሑድ ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ የተፈጠረ ሲሆን፤ እርሱም መጀመሪያ ከ100ው ነገደ መላእክት የ10ሩ ነገደ መላእክት (የኃይላት) አለቃቸው ነበር፤ በተጨማሪም ከሳጥናኤል ውድቀት በኋላ የኃይላት አለቅነቱን እንደያዘ የአጋእዝትን ነገድም (ሳጥናኤል/ሰማልያል/) ይመራቸው የነበሩትን 10 ነገዶችም በአለቅነት ደርቦ አለቃ ኾኗል፤ እንዲሁም በዛሬው ዕለት ለ100ውም(99ኙም) ነገደ መላእክት (ለእልፍ አእላፋት መላእክት) አለቃቸውም ቅዱስ ሚካኤል ኾኖ የተሾመበት ዕለት ነው፡፡ ልዑል ውእቱ ልዑለ መንበር ያሰኘውም ይኸው ነው፡፡ ቅ/ሚካኤል ለሰው ልጆች ምሕረትን ከኅዳር 12 (ከበዓለ ሢመቱ) ጀምሮ እስከ ኅዳር 13 (የአእላፍ መላእክት) በዓል ድረስ ከአምላኩ ለፍጥረታት ሁሉ ምሕረትን የሚለምንበት ዕለታት ናቸው፡፡ ፨፨፨ ፠#፪ እስራኤልን ከግብጽ ባርነት እየመራቸው ማውጣቱን የሚዘከርበት በዓል ነው፡፡ ይህም የሆነው ያዕቆብ በረሃብ 70 ኹኖ ወደ ግብፅ ከወረደ በኋላ ከ215 ዓመታት (አብርሃም ወደ ግብፅ በተሰደደ ከ430 ዓመታት) በኋላ፤ የዮሴፍን ዝና ያልሰማ፥ ዮሴፍን የማያውቅ ፈርዖን በግብፅ ነገሠ፡፡ እስራኤል ከእኛ ይልቅ በዝተዋል ጠላቶቻችን ቢነሱብን ከጣለቶቻችን ጋር ተደርበው ያጠፉናል በማለት አገዛዝ አጸናባቸው፥ ፍርድ አጓደለባቸው፡፡ የእስራኤል ሴቶች ልጅ ሲወልዱ ወንድ ከሆነ እንዲገደል በማድረግ መከራ አጸናባቸው፡፡ ለ215 ዓመታት በግብፅ በባርነት ከቆዩ በኋላ ከዕብራውያን ወገን የሆነችው ራሔል ጭቃ እያቦካች ምጥ በያዛት ጊዜ ከሥራዋ እንዲያሳርፏት ጠየቀች፤ ግብጻውያን ግን የሕፃናቱ ደም ጡቡን ያጠነክራል ርገጭ አሏት፡፡ ከማሕፀኗ የወጡ ሁለት መንትያ ልጆቿን እያየች ከጭቃ ጋር ረገጠች፤ ራሔልም መሪር ልቅሶን አለቀሰች፤ ስለ ልጆቿም መጽናናትን እንቢ አለች፡፡ የእስራኤል ንጉሥ ሆይ የሆነብንን እይ ስትል ራሷን ይዛ ታለቅስ ጀመር ፥ እንባዋንም ወደ ሰማይ ንጉሥ ወደ እግዚአብሔር ረጨች፡፡ የራሔል እንባዋ የሕዝበ እስራኤልን ሁሉ ጩኸት ፥ እሮሮ ይዛ ቅድመ እግዚአብሔር ደረሰች፡፡ “. . . ራሔል ስለ ልጆቿ አለቀሰች የሉምና ስለ ልጆቿ መጽናናት እንቢ አለች” /ኤር 31፥5፤ ማቴ 2፥17/ እንዲል፡፡ ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን አስነሳና፤ በሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል መሪነት፤ 10 ተዓምራትን በምድረ ግብፅ በ11ኛ ተዓምር ደግሞ በኅዳር 12 (ፈርዖንን ከነሠራዊቱ በኤርትራ ባሕር አስጥሞ) ወደ ተስፋይቱ ምድረ መራቸው፡፡ ባሕረ ኤርትራን እስራኤላውያን እንደተሻገሩም የእስራኤል ልጆች የሙሴ የአሮን እኅት ማርያም ከበሮ እየመታች ‹‹ንሴብሖ ለእግዚአብሔር ስቡሐ ዘተሰብሐ ፤ እግዚአብሔር ተዋጊ ነው ስሙም እግዚአብሔር ነው እያሉ፡፡›› ጠላታቸውን የመታላቸውን ፥ እነሱንም በተአምራቱ ያሻገራቸውን ፥ ከጠላታቸው እጅ ያዳናቸውን እግዚአብሔርን አመሰገኑ፡፡ ከዚህ በኋላ መጋቤ ብሉይ ቅዱስ ሚካኤል እየመራቸው ፥ መና ከሰማይ እያወረደላቸው ፥ ውሃ ከጭንጫ እያፈለቀላቸው ፥ ቀኑን በደመና ፥ ሌቱን በብርሃን መርቷቸው አርባ ዘመን ተጕዘው የቃል ኪዳን አገራቸው ምድረ ርስት ከነዓንን (የዛሬዋ ኢየሩሳሌምን) ወርሰዋል፡፡ /ዘጸ. 15/ ከሙሴ በኋላ እስራኤልን የመራው ነቢዩ ኢያሱም እስራኤልን በሚመራበት ጊዜ ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል እስራኤልን ይረዳቸው ነበር፡፡ ከጠላቶቻቸው ጋር ሲዋጉም ሰልፉን ይመራ የነበረው ቅዱስ ሚካኤል ነበር፡፡ ለምሳሌ እስራኤላውያን ከኢያሪኮ አጠገብ በነበሩበት ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል ተገልጦ ኢያሱን አነጋግሮታል፡፡ ኢያሱ በኢያሪኮ አጠገብ ሳለ ቀና ብሎ ሲመለከት የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ አንድ ሰው ከፊቱ ቆሞ አየ፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ “ከእኛ ወገን ነህ ወይስ ከጠላቶቻችን?” ሲል ጠየቀው፡፡ እርሱም “አይደለሁም ነገር ግን የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ በመሆኔ መጥቻለሁ” ብሎታል /ኢያሱ 5፥13-15/፡፡ ይህ የተመዘዘ ሰይፍ ይዞ ከኢያሱ ፊት ለፊት የቆመው መልአክ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል (እንዲሁም መልአኩ ቅዱስ ራጕኤል) ነው፡፡ ይህን ለአብነት አነሣን እጅ እስራኤል በሚበድሉበት ጊዜ ሁሉ ወደ እግዚአብሔር የሚማልድላቸው ይህ ታላቅ መልአክ መጋቤ ብሉይ ቅ/ሚካኤል ነበር፤ እግዚአብሔር አምላክ በእደ መልአኩ ይጠብቀን፤ ከበዓሉ ረድኤት ፥ በረከት ይክፈለን፤ አሜን፨ ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/ #Share #like #Share ያድርጉ በመዲና ከተማችን የሊቀ መልአኩ የቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓል የሚከብርባቸው ገዳማትና አድባራትን እንጠቁማችሁ፡፡ /ፎቷቸውን ያልለጠፍናቸውና ስማቸውን ያልጠቀስናቸውን እንድትልኩልን በሊቀ መልአኩ ስም እንጠይቃለን) 1) *የካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን (ሾላ፤ መገናኛ) 2) *አንቀጸ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል /ጭቁኑ/፤ ፈረንሳይ 3) *ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል (አዲሱ ሚካኤል)፤ አውቶብስ ተራ 4) *ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል፤ /ቦሌ/ 5) *ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ሚካኤል፤ /ላፍቶ/ 6) *ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል፤ (መካኒሣ) 7) *ኮተቤ ደብረ ጽባሕ ቅዱስ ሚካኤል /ሳጠራው/ (ቀድሞ ኮተቤ አሁን ሲምሲ) 8) *ደብረ ምሕረት ሚካኤል (ቀድሞ ወህኒ ቤት ሚካኤል) 9) *መካነ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል 10) *ገነተ አምባ ቅዱስ ሚካኤል 11) *ደብረ ኢዮር ቅዱስ ሚካኤል 12) *ካራ ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ሚካኤልና 24ቱ ካህናተ ሰማይ 13) *ሐያት ጨፌ ኢያሪኮ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን (በ1980ዓ.ም ጽላቱ ከነ ድርሳናቱ ተቀብሮ የተገኘበት) 14) *መንበረ ክብር ቅዱስ ሚካኤል ወአቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም /ኋላ ወቅድስት አርሴማ በሚል እየተጠራ የሚገኝ/፤ (በቀጨኔ በአዲሱ ገበያና በእንጦጦ መሃል ጉብታ ላይ የሚገኝ) እንዲሁም በድርብነት 15) *እንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት 16) *መንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ (ስድስትኪሎ) 17) *ደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ (መስቀል አደባባይ) 18) *ጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ቤ.ክ (ኋላ ጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል በሚል እየተጠራ የሚገኘው)፤ (ኢምግሬሽን አጠገብ) 19) *ደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ (ኋላ ወመካነ ጎልጎታ ቅድስት ድንግል ማርያም በሚል እየተጠራ የሚገኝ ) (ሰሜን ሆቴል አካባቢ) /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/

ያለፈው ሳምንትን የአርብ ጕባኤ ትምሕርተ ወንጌል በ ድረ-ገጻችን ያድምጡ

#የክርስቶስ_አያት ኀዳር 11 በዚህችም ቀን ለጌታችን ለመድኀኒታችን ፣ፀሐይን እና ጨረቃን ለሚገዛ ፣ ሰውን በአርያውን በመልኩ ለፈጠረ ፈጣሪያችን አያት የሆነች ፣ ለእመቤታችን ለቅድስት ቅዱሳን ድንግል ማርያምም እናቷ የሆነች የተመሰገነች እና የከበረች ቅድስተ ሐና ዐረፋቷ ነው፡፡ #share ያድርጉ #ቅድስት_ሐና በኢየሩሳሌም ከሌዊ ነገድ ከካህኑ አሮን ትውልድ የሌዊ የሚልኪ ልጅ ለሆነው የማጣት ልጅ ናት፡፡ ____ #ማጣትም 3 ልጆች አሉት እነርሱም ፤ #የመጀመሪያይቱ ስሟ ማርያም ነው፤ አዋላጅ የነበረች ስትሆን ቅድስት ሰሎሜን ወልዳለች ፤ ሰሎሜም እመቤታችን መድኃኒታችንን ከወለደችው ጀምሮ በስደቷም ወራት ከአረጋዊ ዮሴፍ ጋር እመቤታችንን ያገለገለቻት ናት፡፡ #ሁለተኛይቱ ስሟ ሶፍያ ነዉ ፤ ይህቺ ቅድስተ ለመጥመቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ እናት የሆነችውን ቅድስት ኤልሳቤጥን ወለደች፡፡ #ሦስተኛይቱም ስሟ ሐና ነው፤ ይህች ቅድስት ሐና ከይሁዳ ነገድ ለሆነ ጻድቅ ስሙም ኢያቄም ከሆነ ጋር ተጋብታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ወለደቻት፡፡ ሰሎሜና ቅድስት ኤልሳቤጥ የእመቤታችን እናት ለሆነች ለቅድስት ሐና እኀትማማች ናቸው፡፡ _ ቅድስት ሐና መካነ እያለች አምላክን ልጅ እንዲሰጣት እጅግ አብዝታ ትለምን ነበር፡፡ እግዚአብሔርም በእርሷ ለዓለም ሁሉ ድኀነት የተደረገባትን ይቺን የተባረከችን የከበረች ልጅን ሰጣት እርሷም አምላክን የወለደች እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት፡፡ ጌታ የዘር ሐረግ ውስጥ የተቆጠሩ ሁሉ ክቡራን ናቸው የመጨረሻዎቹ አያቶቹ ደግሞ የመጨረሻው ክብር ይገባቸዋል እነርሱም ሐና እና ኢያቄብ ናቸው:: አምላካችንን የልጅ ልጅቻችን ነው ለማለት ተገብተዋልና፡፡ ቅድስት ሐና ከሴቶች ሁሉ የምትከብርና የምትበልጥ መሆኗን አምላክን ለወለደችልን ለቅድስት እናታችን ድንግል ማርያም እናት ሆና አይተናል፤ ከሴቶች ሁሉ የሚበልጥ ትሩፋትና ተጋድሎ ባይኖራት ይህ ጸጋ ባልተገባት ነበር፡፡ አባቶችም ታጋድሎዋ እጅግ ብዙ እንድሆነ ነግረውናል፡፡ ---ምልጃዋ አይለየን ፡፡ ሃገራችንን ቅድስት ኢትዮጵያን እና ቅድስት ቤተክርስቲያናችንን ትጠብቅልን አሜን! አርኬ ሰላም ለኪ ለጸሎተ ኵሉ ምዕራጋ፡፡ ከመ አስካለ ወይን ዲበ ሐረጋ፡፡ ሐና ብፅዕት ተፈሥሒ እንበለ ንትጋ፡፡ እስመ ረከብኪ ምገሰ ወአድማዕኪ ጸጋ፡፡ እምሔውተ አምላክ ትኵኒ በሥጋ፡፡ በቦታው ሄዳቹ በዓሉን ማክበር ለምትፈልጉ👇🏼 ፎቶዎቹ፤ በአ.አ. እና በሌሎች የሚገኙ የቅድስት ሐና አብያተ ክርስቲያናት ... ፠ ኮተቤ መካነ ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና ቤ/ክ ፡ ፠ ደብረ ንግስት መንዝ ቅድስት ሐና:: ፠ በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት በደብረ መንክራት ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን በደባልነት ትገኛለች ሌሎች በዓሉ የሚከብሩባቸውን ቦታዎች ኮሜንት ላይ ያጋሩን /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #Share #like