ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

الذهاب إلى القناة على Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

إظهار المزيد

📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

تُعد قناة Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 16 042 مشتركاً، محتلاً المرتبة 5 281 في فئة الدين والقيم الروحية والمرتبة 2 239 في منطقة Ethiopia.

📊 مؤشرات الجمهور والحراك

منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 16 042 مشتركاً.

بحسب آخر البيانات بتاريخ 28 أكتوبر, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار 512، وفي آخر 24 ساعة بمقدار -6، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.

  • حالة التحقق: غير موثّقة
  • معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 25.18‎%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 10.37‎% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
  • وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 4 039 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 1 663 مشاهدة.
  • التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 30.

📝 الوصف وسياسة المحتوى

يصف المؤلف القناة بأنها مساحة للتعبير عن الآراء الذاتية:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 29 أكتوبر, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة الدين والقيم الروحية.

16 042
المشتركون
-624 ساعات
+917 أيام
+51230 أيام
أرشيف المشاركات
ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያንችንን ጉዳይ በተመለከተ በየካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል መልአከ ሰላም ሰ/ት/ቤት ጥቅምት 9 ከቀኑ 9፡30 ጀምሮ በሰ/ትቤቱ አዳራሽ እንወያይ፤ በርኩሳን መናፍስት የሚመሩ ቤተ
+1
ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያንችንን ጉዳይ በተመለከተ በየካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል መልአከ ሰላም ሰ/ት/ቤት ጥቅምት 9 ከቀኑ 9፡30 ጀምሮ በሰ/ትቤቱ አዳራሽ እንወያይ፤ በርኩሳን መናፍስት የሚመሩ ቤተ ክርስቲያንን ለማዳከም ቀን ከሌት የሚደክሙበት ወቅት በመሆኑ ከመቼውም በላይ በየሰ/ት/ቤቶቻችን ቅድሚያ በመስጠት ልንወያይና ልንመካከር ይገባልና፡፡ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል በማስተዋል መንገድ ይምራን፡፡

፠፠ #አቡነ_በጸሎተ_ሚካኤል_ አንጦንስ መቃርስን፤ መቃርስ ጳኩሚስን፤ ጳኩሚስ ቴዎድሮስን፤ ቴዎድሮስ አረጋዊን፤ አረጋዊ ማትያስን፤ ማትያስ መድኃኒነ እግዚእን፤ መድኃኒነ እግዚእ ዮሐኒን፤ ዮሐኒ ኢየሱስ
+2
፠፠ #አቡነ_በጸሎተ_ሚካኤል_ አንጦንስ መቃርስን፤ መቃርስ ጳኩሚስን፤ ጳኩሚስ ቴዎድሮስን፤ ቴዎድሮስ አረጋዊን፤ አረጋዊ ማትያስን፤ ማትያስ መድኃኒነ እግዚእን፤ መድኃኒነ እግዚእ ዮሐኒን፤ ዮሐኒ ኢየሱስ ሞዐን፤ ኢየሱስ ሞዐም ትምህርትን ከምግባር ጋር ያስተማራቸውን 800 የሚኾኑ ንቡራነ እድ መነኰሳትን ወልዷል፤ በመላ ሃገሪቱም አሰማርቷል፤ ከእነዚህም ውስጥ አንዱና ዋነኛው አቡነ በጸሎተ ሚካኤል (የደብረ ጎል ገዳምን ያስፋፉ) ናቸው አቡነ በጸሎተ ሚካኤልም ከአባታቸው ማርቆስና ከእናታቸው እግዚእ ክብራ ዛሬ መስከረም 6 ተፀነሱ፡፡ በተወለዱም ጊዜ በቤታቸው ውስጥ ቀስተ ደመና ተተክሎ የታየ ሲሆን አስቀድሞ መልአኩ ስሙን እንዳወጣለት ‹‹በጸሎተ ሚካኤል›› ተብለው ተሠየሙ፡፡ እርሳቸውም በርካታ ቅዱሳንን የወለዱ ወላዴ አእላፍ ሲሆኑ፤ ከወለዷቸው ልጆች መካከል አንዱና ዋነኛው ከልጅነት ጀምሮ በአርድዕትነት (በተላላኪነት) ያገለገሏቸውና ትምህርትን ያስቀሰሟቸው አቡነ ተክለ ሃይማኖት ናቸው፡፡

ወተቀበልዎ መላእክት በስብሐት ወበማኅሌት፤ ወአብዕዎ ኢየሩሳሌም ሰማያዊተ አብዕዎ ገብረ ሕይወት፡፡ እንኳን #ለአቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ_በዓለ_ዕረፍት_በሰላምና_በጤና_አደረሳችሁ፡፡ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (አቦ፥ አቡዬ)፤ * እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ብርሃነ ዓለም የኾኑ፤ * እንደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ጸጋንና ክብርን የተሞሉ፤ * ኰከበ ገዳም፥ መናኔ ዓለም፥ ምድራዊ መልአክ፤ * ስማቸውን ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ያወጣላቸው፤ * በአክናፈ መባርቅት ተጭነው የሚጓዙ፤ * 60 አናብስትና 60አናብርት ይታዘዙላቸው የነበሩ፤ የእግራቸው ትቢያ ለአራዊቶቹ ምግብ የኾነላቸው፤ * ለብዙ አእላፍ ቅዱሳን ወላዴ የኾኑና በረከትን የሰጡ ታላቅ አባት (ለአብነትም፤ ለቅዱስ ላሊበላ፥ ለአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ፥ ለአባ አንበስ ዘደብረ ሐዘሎ፥ ለአባ ብንያም ዘግብፅ) ፠፠፠ #ምድረ_ከብድ_፤ /ዝ_ምድር_ክቡድ_ውእቱ_/ ፤ #ዝቋላ (#ዝ_ቆላ)  ምድረ ከብድ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ለመጀመሪያ ጊዜ ያረፉባት ቦታ ናት፤ ቀጥሎ ወደ ደብር ቅዱስ #ዝቋላ (#ዝ_ቆላ) ለጸሎት ሂደው ለሃገራችን ኢትዮጵያና ለዓለማችን ምሕረትና በረከትን ከአምላካችን ለ100 ዓመታት በባሕር ውስጥ ሆነው ለምነዋል፤ *ወደ ምድረ ከብድ ተመልሰው ለ7 ዓመታት ጸልየዋል፤ ቊራም በሰይጣን ተመስሎ መጥቶ ዓይናቸውም ቢያጠፋውም ከ7 ሱባዔያት በኋላ ሊቀ መላእክት ሚካኤልና ገብርኤል ዓይናቸውን መልሰውላቸዋል፡፡ *ወደ ዝቋላ በመመለስም አጋንንትም ከምድረ ዝቋላ አጥፍተዋል፤ ፠ እንደገና ወደ ምድረ ከብድ ተመልሰው በነበሩበት ጊዜ ታላላቆቹና በአንበሳ ዘባን ላይ የሚሄዱት #አቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ ፣ #አባ_አንበስ_ዘደብረ_ሐዘሎ_አፋር)፣ #አባ_ብንያም_ዘግብፅ ከአባታችን ቡራኬ ለመቀበል መጡ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ተሰውረው ነበርና፤ የአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ አናብስት የ3ቱን አባቶች አናብስት በሉባቸው፤ በ7ኛው ቀን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ተገልጠው የኾነውን ነገር በማየት የተበሉትን አናብስት እንዲመልሱ የራሳቸውን አናብስት አዘዟቸው መልሰውም እንደነበሩ በተዓምራት አስነስተው ሰጧቸው፤ በደመና ጠቅሰው ቅዱስ ፋኑኤል 3ት ሰማያዊ ኅብስትና 3ት ጽዋዕ ይዞ ለእንግዶቻቸው ይዘው ሠረገላ በሚባለው ዋሻ አመጡላቸውና ሰጥተው ሸኟቸው፤ እነዚህን ቅዱሳን በሸኙ በ7ኛው ቀን ወደ ተለያዩ ሃገራት ሄደው አስተምረዋል፡፡ ፠ እድሜያቸው ረዥም እንደመሆኑ፤ ቅዱሱ ንጉሥ አፄ ላሊበላን ጨምሮ ሌሎችም ቅዱሳን ወደ ርሳቸው እየመጡ በረከትን ተቀብለዋል፡፡ ፠#በግብፅ_300_ዓመታት_፥ #በኢትዮጵያ_ምድር_ላይ_262_ዓመታት (በዋነኛነት #በምድረ_ከብድና_በዝቋላ_ ቢኖሩም ሌሎችም የመሠረቷቸውና የኖሩባቸው ገዳማት አሉ፤ ለአብነትም ደቡብ ወሎ የሚገኘውን #ገዘዛ_አቦን_ መጥቀስ ይቻላል) ፠ በድምሩ 562 ዓመታት ከኖሩ በኋላ በንጉሥ ሕዝብናኝ(እንድርያስ) ዘመነ መንግሥት፤ መጋቢት 5 ቀን ቅዳሜ ለእሑድ አጥቢያ ብዙ ቃል ኪዳንን ጌታችን ሰጣቸው፥ 12 አክሊላትንም አቀዳጃቸው፤ የነበሩባት ምድረ ከብድ ገዳም ግን ራደች፥ ተንቀጠቀጠች፥ በብርሃንም ተጥለቀለች፤ ዝቅ እያለችም መንሸራተት ጀመረች፤ ጌታችንም አንቺ መሬት ሆይ ጽኚ ይህንን ኹሉ ስለቻልሽ ምድር ክቡድ /ኋላ ምድረ ከብድ/ ተብለሽ ተጠሪ አላት፤ የጻድቁም ነፍስ ከሥጋቸው ከሌሊቱ 6 ሰዓት ተለየች፡፡ ፠ ይህችውም ምድረ ከብድ ጻድቁ የኖሩባትና የቀደሱባት፥ የመሠረቷትና ያነፅዋት፣ ሠራዊተ መላአክት የከተሙባት፣ ታላላቅ አበው መጥተው በረከት ከአባታችን የተቀበሉባት፣ አርምሞና ጸጥታ የማይለያት፤ አጸዷና ቅጥሯ ልቡናን የሚመስጥ፤ ከአ.አ 125 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ናት፡፡ አምላከ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ረድኤት፥ በረከትን ይክፈለን፡፡ (ሥርዐተ ማኅሌቱን የኢንተርኔት አቅርቦት በሌለባቸው ቦታዎች አድርሱልን፤ በተለይም ወደ ምድረ ከብድ፥ ዝቋላ፥ ገዛዛ አቦና ሌሎች የአባታችን ክብረ በዓል በሚከበርባቸው አድባራትና ገዳማት ያላችሁ አድርሱልን፡፡) /የቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት/

#አብርሃ_ወአጽብሃና_4ቱ ቅዱሳን ነገሥታት እስከ አሁን ድረስ በኢትዮጵያ ከነገሡ ነገሥታት የሚለዩበት ነገር አለ ይኸውም፤ ክህነትን ከንግሥና፥ ቅድስናን ከንጽሕና ጋር አንድ አድርገው በመያዝ (እንደ
+1
#አብርሃ_ወአጽብሃና_4ቱ ቅዱሳን ነገሥታት እስከ አሁን ድረስ በኢትዮጵያ ከነገሡ ነገሥታት የሚለዩበት ነገር አለ ይኸውም፤ ክህነትን ከንግሥና፥ ቅድስናን ከንጽሕና ጋር አንድ አድርገው በመያዝ (እንደ ካህኑ መልከጼዴቅ፣ አፄ ገብረመስቀል፣ አፄ ቴዎድሮስ ቀዳማዊ፣ …) እግዚአብሔርንም ሰውንም ያገለገሉ ናቸው፤ ከዚህም በተጨማሪ ቅድስናን ከሐናፄ ቤተመቅደስነት ጋር ደርበው የያዙም ጭምር ናቸው፡፡ በዚህም በንግሥናቸው ሀገርን በመልካም ሥራና በቅድስና ከማስተዳደራቸው በተጨማሪ ቅዱሳን ጻድቃን ሆነው እግዚአብሔርን በብዙ ድካም በመልካም ተጋድሏቸው ያገለገሉና አገልግሎታቸውም ሆነ ቅድስናቸው በእግዚአብሔር ዘንድ የተመሰከረላቸው፤ ጽላት የተቀረጸላቸው፥ ገድል የተጻፈላቸው፤ (ገድላቸውና ትሩፋታቸው፣ ምግባር ሃይማኖታቸው እጅግ ድንቅ የኾኑ) ቅዱሳን ናቸው፡፡ ዛሬ ጥቅምት 4 ቀን 364 ዓ/ም አጽብሐ ጥቅምት 4 ቀን 379 ዓ/ም በሞተ ሥጋ አርፈዋል፡፡ ክብረ በዓላቸው በትግራይ ባለ ውቅር ገዳማቸው፤ በአዲስ አበባ ደግሞ፤ * * በደብረ ከዋክብት አቡነ አረጋዊ **በየካ ተራራ ዋሻ ተክለ ሐይማኖት **በአያት ቅዱስ ፋኑኤል ቤተክርስቲያን፡፡

#አቡነ_በርተሎሜዎስ_ዘደብረ_ዘመዳ፤ ፠ተወልደው ያደጉት በ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በሸዋ ቡልጋ፤ በጥራ መረዋ አካባቢ ነው፡፡ ለአቅመ አዳም ሲደርስ ሚስት አጭተው ቢያጋቡትም፤ እንደ ድሜጥሮስ ንጽሕናውን ጠብቆ ለጥቂት ጊዜያት ከቆየ በኋላ ወግር ወደሚባል ተራራ ሂዶ 40 ቀን ሱባዔ ገባ፡፡ ሱባዔውን እንደጨረሰም ወደ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ገባ፡፡ ፠ በደብረ ሊባኖስ ገዳምም ከታላቁ ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የምናኔ ሕይወትን ተማሩ፡፡ ፠ምንኵስናን ከጓደኛቸው ከኤዎስጣቴዎስ ጋር አበአንድነት የተቀበሉትም ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት ሲሆን፤ ከትግራይ ወሰን እስከ አንገት ያለውን እንዲያስተምሩም በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ተልከዋል፡፡ ፠ ወደ እንፍራንዝ (ጣና) ከጌርሎስ ከአኖሬዎስ ልጅ ዘንድ ሄደው ሰነበቱና ወደ ሃገራቸው ተመለሱ፡፡ ፠ ክርስትናን ለማስፋት ተመርጠው ከተሾሙ ዓበይት ንቡራነ ዕድ አንዱ ሲሆኑ፤ የተሾሙበት ሃገረ ስብከታቸውም በቆባ፣ የጠጠርና የኮረም ኤጲስ ቆጶስ ሆነው ነው፡፡ በተለይም በወሎና በአፋር ድንበር አካባቢ ወንጌልን በትጋት አስተምረዋል፡፡ ፠ 12ቱ ንቡራነ ዕድ ከያሉበት ሃገር ወደ ደብረ ሊባኖስ በመምጣጥ ወር ወር የአቡነ ተክለ ሃይማኖትን አጽም ያጥኑ ነበር፤ የጻድቁ ዘቡነ በርተሎሜዎስ የማዕጠንት ተራቸውም በወርኃ ጳጕሜን ነበር፡፡ ፠ አፄ ዐምደ ጽዮን የአባቱን ሚስት በማግባቱ ቅዱሳኑና ግብጻዊው ጳጳስ አቡነ ያዕቆብ በመቃወማቸው፤ በአፄ ዐምደ ጽዮንና በልጁ በአፄ ሰይፈ አርዕድ መሰደድ ደረሰባቸው፤ አቡነ በርተሎሜዎስም ከጳጳሰ ጋር ወደ ግብጽ መሰደድ ጀመሩ ነገር ግን፤ አቡነ ያዕቆብ ለአቡነ በርተሎሜዎስ ጽላተ ማርያምን ሰጥተው እንዲመለሱ አደረጓቸው፤ አቡነ በርተሎሜዎስም ጽላተ ማርያምን በደብረ ዘመዳ በክብር አስቀመጣት፡፡ ፠ በ14ኛው መቶ ክ/ዘ ጥቅምት አርፈው በደብረ ዘመዳ ገዳም ዐጽማቸው በክብር አርፏል፡፡ #ደብረ_ዘመዳ_ማርያም_አቡነ_በርተሎሜዎስ_ገዳም (#ደብረ_ዠመዳ) ገዳሙ የሚገኘው ወሎ ላስታ ውስጥ ሲሆን የመሠረቷት አቡነ በርተሎሜዎስ ናቸው፡፡ በዚህ ገዳም እንደ አኵሱምና ደብረ ሊባኖስ ሰዐታትና ማኅሌት ሁልጊዜም ይቆምባታል፡፡ በዚህ ገዳም በርካታ ጥንታውያንና ድንቅ የሆነ ቅርሶች አሉ፤ ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ የሳላት የእመቤታችን ስዕል የምትገኘውም በዚሁ ገዳም ሲሆን፤ መልኳ የሚቀያየርና ቅዱስ ዮሐንስ የሚባል ደግ ሰው ነው ወደዚህ ገዳም ያመጣት፡፡ ** ገዳሙ የሚጠበቀው በዋነኛነት እንደ ነብር ባሉ የዱር አራዊት ነው፡፡ ፠፠፠የደብረ ዘመዳ ዓመታዊ ክብረ በዓል የሚከበረው በጥቅምት 4 በአቡነ በርተሎሜዎስ በዓለ ዕረፍታቸው ቀን ነው፡፡ ፠፠፠ ታላቁ ገዳም ደብረ ዘመዳ የሚገኘው፤ ሰሜን ወሎ ዋጃ ከተማ ከተደረሰ በኋላ የተወሰኑ ሰዓታት የእግር ጕዞ በመጓዝ ነወ፡፡ ከጻድቁ ከአቡነ በርተሎሜዎስ ረድኤት በረከት ይክፈለን፤ አሜን፡፡ /ምንጭ፤ ገድለ አቡነ በርተሎሜዎስ የብራና፤ የአማርኛ የቤ/ክ መዝገበ ቃላት፣ ዶ.ር ሥርግው ሐብለ ሥላሴ፣ ዝክረ ቅዱሳንና ከገድላት አንደበት የፊት ገጾች፡፡) /የቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት/

#ጥቅምት_3_የቤተ_ክርስቲያን_ማኅቶት ፥ #አፈ_በረከት_ሊቁ_አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋሥጫ፤#_ፅንሰቱ_ነው፡፡ ፠ይህ አባት ከ40 በላይ መጻሕፍትን የደረሰና ብዙ መጻሕፍትን እያጻፈ ለመላው ገዳማት ያዳረሰ፤ ጸሓፊ፥ ቅዱስና ጻድቅ፥ ፈላስፋና ደራሲ፥ መናኝና ባሕታዊ፥ ሊቅና ተመራማሪ፥ ገጣሚና በለቅኔ፥ የመጻሕፍት ተርጓሚና የዘመን አቈጣጠር (የአቡሻህር) ሊቅና ተንታኝ፥ አርክቴክትና መሐንዲስ ነው፤ በዚህም ምክንያት በተለያዩ ስያሜዎች ይጠራል፤ ፠ዳግማዊ ቄርሎስ (ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ)፥ ፠ ዐምደ ሃይማኖት ፠ ዳግማይ ቅዱስ ያሬድ፤ ፠ የወርቃማ ዘመን ወርቃማ ደራሲ፤ ፠ የቤተ ክርስቲያን ማኅቶት፥ ፠ አፈ በረከት ፠ የከሃድያን ዘላፊ፥ የቅዱሳን ፀሐይ …….ተብሏል፡፡ እንዲሁም፤ + እንደ ቅዱስ ላሊበላ ቤተ መቅደሱን ራሱ ፈልፍሎ ያነፀ #የሕንፃ_ባለሙያ ነው። + ከጓደኛው ከአባ ጽጌ ድንግል ጋር ሁኖ የወለቃ ወንዝ ድልድይን የሠራ መሐንዲስ፤ እስከ ዛሬም ድረስ ድልድዩን ሕዝቡ ይጠቀምበታል፡፡ + እንደ ቅዱስ አትናቴዎስ መናፍቃንን የረታ #ብርቱ_የቤተ_ክርስቲያን_ጠበቃ ነው። + እንደ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ በርካታ መጻሕፍትን የጻፈ (የደረሰ) #ደራሲ ነው፡፡ + እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ወንጌልን ዙሮ ያስተማረ #ሐዋርያ ነው፡፡ + እንደ ፍጹማን መነኰሳት በጾም በጸሎትና በስግደት ተወስኖ በተጋድሎ ጸንቶ የኖረ #መናኝ_ጻድቅ ነው፡፡ + እንደ ቅዱስ ያሬድ በሰማያዊ ዜማ አምላኩን ያመሰገነ #የዜማ_ሊቅ #የዜማ_ደራሲ ነው። + እንደ ዕዝራ ሱቱኤል ሰማያዊ መጠጥ ጠጥቶ ምስጢራት የተገለጹለት #ድንቅ_ተመራማሪ #የጥበብ_አባት ነው:: (ለምሳሌ፤ በሰዓታት ድርሰቱ ውስጥ ዑደተ ማይን፣ በሌሎች ድርሰቶቹም ስለ አእባንና እጽዋት ቀድሞ ነግሮናል፣ እንዲሁም የውኃ ማቆር ቴክኖሎጂን በዘመኑ ተግባራዊ አድርጓል። + እንደ ሰማዕታት ከነገሥታቱ ስለ ሃይማኖት ብዙ ጸዋትወ መከራ የተቀበለ #ሰማዕት ነው፡፡ + አቡነ አረጋዊ ደብረ ዳሞን፤ አቡነ ኢየሱስ ሞ ሐይቅ እስጢፋኖስን፤ አቡነ ተከለ ሃይማኖት ደብረ ሊባኖስን፤ አቡነ ሳሙኤል ዋልድባን፤ አቡነ ዐምደ ሥላሴ ማኅበረ ሥላሴ ገዳምን እንደመሠረቱና የተመሠረተውንም እንዳስፋፉ፤ እርሱም ደብረ ባሕርይ ጋሥጫን የመሠረተ ቅዱስ ነው፡፡ + በሰዓታት ድርሰቱ ቤተክርስቲያን አምላኳን ፳፬ ሰዓት ያለማቋረጥ እንድታመሰግን ያስቻለ ምድራዊ #መልአክ ነው፡፡ + "አኀዝ እግዚኦ መዋግደ ጸጋከ" እስከሚል ድረስ ጸጋ የበዛለት አባት ነውና ስንቱን እንናገረው? አይቻለንምና!!!፡፡ (በፎቶ ላይ የምታዩት ገዳም፤ በዓለም ብቸኛው የአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ገዳም የኾነው ደብረ ባሕርይ ነው፡፡ የቦታው አቀማመጥ እጅግ በጣም ማራኪና እንደ ደብረ ዳሞ ሲሆን የሚወጣው በመሰላል ነው፡፡)፤ ገዳሙ የሚገኘው በደቡብ ወሎ በቦረና አውራጃ ነው፡፡ (አስተጋባኢ /ይህንን ጽሑፍ ከአባቶች በመጠየቅ ፥ መጻሕፍትን በማንበብ ፥ ከታላቁ ገዳም ደብረ ባሕርይ ጋሥጫ ድረስ ሂዶ ያዘጋጀው የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ሰሌዳ መጽሔት ዝግጅት ክፍል ነው/፡፡) አምላከ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ የሀበነ በረከተ ወረድኤተ፡፡

#የጥቀምት_2_የማኅሌተ_ጽጌ_ወረቦች_፤ በሊቀ ጕባኤ ደምፀ አንበርብር፣ በሊቀ ጠበብት ኤርምያስና በደብራችን ሊቃውንት፡፡ 1) 1 ጽጌ አስተርአየ 2) 2 ናሁ አስተርአየ 3) 3 እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ወረብ 4) 4) ንዒ ርግብየ ሐዋርያት (የቀጨኔ ደብረ ሰላም የቤቱ ቀለም) 5) 5 ክበበ ጌራ ወርቅ ወረብ 6) 6 ውድስት አንቲ በአፈ ነቢያት 7) 7 አርአዮሙ ለመምህራን 8) 8 ከማሃ ኃዘን ወተሰዶ ኃዘን ወረብ በሚከተለው የቴሌግራም አድራሻችን ያገኛሉ፤ https://t.me/medihanaelem (በእኛ ደብር ብቻ ያሉ ቀረጻዎችን ብቻ እንዳይሆኑብን፤ በየደብራችሁ ያሉትን በድምፅ የተቀዱ ሥርዐተ ማኅሌቶችን በውስጥ መስመር ብትልኩልን ደስ ይለናል፡፡)