ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

الذهاب إلى القناة على Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

إظهار المزيد

📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

تُعد قناة Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 16 042 مشتركاً، محتلاً المرتبة 5 281 في فئة الدين والقيم الروحية والمرتبة 2 239 في منطقة Ethiopia.

📊 مؤشرات الجمهور والحراك

منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 16 042 مشتركاً.

بحسب آخر البيانات بتاريخ 28 أكتوبر, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار 512، وفي آخر 24 ساعة بمقدار -6، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.

  • حالة التحقق: غير موثّقة
  • معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 25.18‎%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 10.37‎% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
  • وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 4 039 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 1 663 مشاهدة.
  • التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 30.

📝 الوصف وسياسة المحتوى

يصف المؤلف القناة بأنها مساحة للتعبير عن الآراء الذاتية:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 29 أكتوبر, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة الدين والقيم الروحية.

16 042
المشتركون
-624 ساعات
+917 أيام
+51230 أيام
أرشيف المشاركات
እንኳን ደስ ያለን፤ ሥርዐተ ማኅሌት መጻፍ ከጀመርን እነሆ ሰባት ዓመት ዛሬ ሆነን፡፡ ይህንንም በማስመልከት በጽሑፍና በፎቶ ስንዘግብላችሁ የነበረውን እንደ አምላከ አበው መድኀኔ ዓለም ፈቃድ በድምፅ፣ በድምፅና በምስል እንዲሁም በመጽሐፍ ለማቅረብ እንተጋለን፡፡ እነሆ ብለናል፡፡ #የጥቀምት_2_የማኅሌተ_ጽጌ_ዚቅ_፤ በደብራችን ርዕሰ ደብር ጥሩነህ፡፡ 1) 1) መሥ- ለአፉክሙ… አሰርጎካ ለምድር-1 2) 2) ማኅ - ጽጌ አስተ… ናሁ አስተርአየ ጽጌ-1 3) 3) ማኅ- እንዘ ተሐቅ… ንዒ ርግብየ-1 4) 4) ማኅ - ክበበ ጌራ ወርቅ… ውድስት አንቲ-1 5) 5) ማኅ - ቅዳሴኪ ማርያም… አስተምሕር ለነ-1 6) 6) ሰቆ. በስመ እግዚ… እወ አማን-1 በሚከተለው የቴሌግራም አድራሻችን ያገኛሉ፤ https://t.me/medihanaelem (በእኛ ደብር ብቻ ያሉ ቀረጻዎችን ብቻ እንዳይሆኑብን፤ በየደብራችሁ ያሉትን በድምፅ የተቀዱ ሥርዐተ ማኅሌቶችን በውስጥ መስመር ብትልኩልን ደስ ይለናል፡፡)

ሥርዐተ ማኅሌት ዘወርኀ ጽጌ (‹ዘላይ ወዘታች› ቤት) (፪ኛ ዙር ዓመት፤ ፩ኛ ሳምንት፥ጥቅምት ፪) በዓለ አባ ሕርያቆስ፡፡ የቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/
+6
ሥርዐተ ማኅሌት ዘወርኀ ጽጌ (‹ዘላይ ወዘታች› ቤት) (፪ኛ ዙር ዓመት፤ ፩ኛ ሳምንት፥ጥቅምት ፪) በዓለ አባ ሕርያቆስ፡፡ የቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት

#ማኅሌተ_ጽጌ_ዘይሰመይ_ስሙ_፡፡ ማኅሌተ ጽጌ ከሁለት የግዕዝ ቃላት ጥምረት የተገኘ ነው፡፡ ማኅሌት ማለት ምስጋና፣ ማወደስ ማለት ሲኾን፤ ጽጌ ማለት ደግሞ አበባ፣ የፍሬ ምልክት፤ ውበት፣ ደም ግባት ያለው ማለት ነው፡፡ ማኅሌተ ጽጌ ተብሎ በአንድነት ሲነገር እና ሲተረጎም ደግሞ የአበባ ምስጋና ማለት ነው፡፡ ይህም ድንግል ማርያም እና የማሕፀኗ ፍሬ ኢየሱስ ክርስቶስ በጎ በጎ መዓዛ ባላቸው አበባዎችና ፍሬዎች እየተመሰሉ በዳዊት መዝሙር መጠን በ150 እንዲሁም እንደ መልክዕ በባለ 5ት መስመር ግጥም ተደርጎ የሚመሰገኑበት ምስጋና ማለት ነው፡፡ ጽጌ የዘመን (የወራት) ስምም ይኾናል፤ ዘመነ (ወርኃ) ጽጌ 40 ቀን ነው ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 5 ነው፡፡ በዚህ ወራት የሚጾመው ጾም ጾመ ጽጌ ሲባል ጾሙም የፈቃድ ጾም ነው፡፡ በሀገራችን ዘመነ ክረምት አልፎ መስከረም 26 ቀን ዘመነ ጽጌ ይጀመራል፡፡ ዘመኑ አበቦች የሚያብቡበት እና ሜዳዎችን እና ተራሮችን የሚስጌጡበት ዘመን ነው፡፡ ፍሬ ከአበባ አበባም ከፍሬ እንደሚገኝ ኹሉ በማኅሌተ ጽጌ እመቤታችንን በአበባ፥ ጌታችን በፍሬ፤ ወይም እመቤታችንን በፍሬ፥ ጌታችንን በአበባ እየተመሰሉ በምሥጢራዊ ግጥም ቀርበዋል፡፡ የማኅሌተ ጽጌ ደራሲ ሊቁ አባ ጽጌ ድንግልም የአበቦችን ነገር ከእመቤታችን ስደት ጋር እያደረገ፣ እጅግ አስደናቂ የሆኑ ታሪኮችን እያጣቀሰ ማኅሌተ ጽጌ (የአበባ ማኅሌት) የተባለውን ጸሎት ደርሷል፡፡ በዘመነ ጽጌ ወቅት ቅዳሜ ለእሑድ አጥቢያ ማኅሌት ይቆማል፤ የሚቆመው ቁመትም አባ ጽጌ ድንግል የደረሱት ማኅሌተ ጽጌና ሰቈቃወ ድንግል ነው፡፡ አባ ጽጌ ድንግል ጓደኛቸው አባ ገብረማርያም የጀመሩትን ማኅሌተ ጽጌ አብነት በማድረግ በተለይም በጎንደር ዘመነ መንግሥት በእቴጌ ምንትዋብ ዘመን በጎንደር ደብረ ፀሐይ ቊስቊም ማርያም የማኅሌተ ጽጌ ቁመት መቆም ተጀምሯል፤ ቆይቶ ግን ይህ ማኅሌት ወደ ዘንሥር ዮሐንስ ማእከላ ለጎንደር ተዛውሮ እስከ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ድረስ ሲቆም ቆይቶ በመምህር ተክሌ ጊዜ ወደ መካነ ነገሥት ግምጃ ቤት ማርያም ተዛውሮ በጎንደር አብያተ ክርስቲያናት በብቸኝነት በዚህችው ደብር የጎንደር አድባራት ሊቃውንት በመሰባሰብ ሲቆም ቆይቷል፤ በሌሎች የሃገራችን ክፍሎች አዲስ አበባን ጨምሮ ባሊ አብያተ ክርስቲያናትም የጽጌ ቁመት ተስፋፍቷል፡፡ ከ1999(2000)ዓ.ም. ጀምሮ በጎንደር ደብረ ፀሐይ ቊስቋምና የተወሰኑ የጎንደር አብያተ ክርስቲያናት የማኅሌተ ጽጌ ቁመት ጀምረዋል፤ ነገር ግን ቢጀምሩም ቅሉ አሁንም ግን የጎንደር አድባራት ሊቃውን በዋነኛነት በመካነ ነገሥት ግምጃቤት እየተሰባሰቡ የሚቆሙት የማኅሌተ ጽጌ ቁመት እጅግ በጣም ልብን የሚማርክና ኅሊናን የሚመስጥ በሃገራችን በኢትዮጵያ ደረጃም ተወዳዳሪ የሌለው ነው፡፡ በሌሎች የሃገራችን ክፍሎችና በመዲናችን በአዲስ አበባ ባሉ አብያተ ክርስቲያናት ደግሞ የአገልጋይ ካህናት እጥረት በሌለባቸው ኹሉ ይቆማል፡፡ #ሰቈቃወ_ድንግል፤ ማለት እመቤታችን ከልጇ ከመድኀኔዓለም፥ ከአረጋዊ ዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር በስደቷ ወቅት ያየችውን መከራ፥ ልቅሶ፥ ዋይታ የሚዘከርበት የማኅሌተ ጽጌ አርኬ ነው፡፡ የሰቈቃወ ድንግልን ደራሲ በተመለከተ አባ ጽጌ ድንግል ደረሱት የሚሉ አሉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ አባ ገብረ ኢየሱስ ዘገዳመ መጕና ወይም /አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ/ ወይም /አባ አርከ ሥሉስ/ ነው የደረሱት የሚሉም አሉ፡፡ ፎቶዎቹ፤ #ቤተ_ክርስቲያኖች_ *ደብረ ጽጌ ገዳም፤ የአባ ጽጌ ደንግል ገዳም፤ ማኅሌተ ጽጌ የተደረሰበት፤ ወሎ ወግዲ አጠገብ፤ ኅዳር 6 ይከብራል፡፡ *ጎንደር ደብረ ፀሐይ ማርያም፤ ለበርካታ ዘመናት ማኅሌተ ጽጌ ይቆምባት የነበረች ታላቋ ደብር፡፡ *ጎንደር ዘንሥር ዮሐንስ፤ እስከ አፄ ኀይለ ሥላሴ ዘመን የጎንደር የ44ቱ ታቦታት ሊቃውንት አየተሰበሰቡ ማኅሌተ ጽጌ ይቆሙበት የነበረ ደብር፡፡ *ጎንደር መካነ ነገሥት ግምጃ ቤት ማርያም፤ ከአፄ ኃይለ ሥላሴ እስከ አሁን ድረስ የጎንደር የ44ቱ ታቦታት ሊቃውንት አየተሰበሰቡ ማኅሌተ ጽጌ የሚቆሙባት ታላቂቷ ደብር፡፡ #መምህራን_ ✤ #መምህር_ተክለማርያም_፤ የታለቁ ገዳም የማኅበረ ሥላሴ አበምኔት፤ የግምጃ ቤት ማርያም የሐዲሳት መምምህር፤ የድጓና የአቋቋምም መምህር፤ የጎንደር አድባራት በጋራ በመኾን የማኅሌተ ጽጌን ቁመት በአንድ ላይ ይቆሙበት ከነበረው ዘንሥር ማዕከላ ለጎንደር ዮሐንስ ወደ መካነ ነገሥት ግምጃ ቤት ያመጡ ታላቁና ይህ ቀረሽ የሚይባሉ ሊቅ ✤፠ #መምህር_ክፍለ_ማርያም_ይመር_፤ የመጻሕፍት ትርጓሜ ብርሃን፤ የየቀኑን ምሥጢር ከድጓ፣ ከጾመ ድጓ፣ ከዝማሬ መዋሥዕት፣ ከቅዳሴ፣ ከሰዐታት እየተመለከቱና እያውጣጡ ዚቁን ያዘጋጁ፤ ይህ ቀረሽ የማይባሉ የሊቆች ሊቅ፡፡ ✤፠ #ሊቀ_ማዕምራን_ወመጋቤ_ሐዲስ_ወሰንበት_ባይነሳኝ_፤ የጽጌ ዚቅን (የላይ ቤትን) አቀናብረው ያቀረቡ፤ የመጻሕፍተ ሐዲሳት ዋና ምስክርና የመካነ ነገሥት ግምጃ ቤት ማርያም ዋና አስተዳዳሪ፤ የሚያስተምሩት የሚኖሩ፤ ሊቅነትና ከትሕትና የያዙ፤ ከቀደምት ዐበይት ሊቃውንት መካታቻ የሆኑ፤ በቅርቡ ያረፉ፤ ጕባኤ እያሄዱ (እያስተማሩ) የሚያሳይ ፎቶ ✤፠ ሊቀ ማዕምራን ሐዋዝ ጥሩነህ፤ የግምጃ ቤት ማርያም አለቃ፤ ከላይ የተጠቀሱ ሊቃውንት የደረሱትን ዚቅ በእጅ ጽሑፍ ለትውልድ ያቆዩ ብልህ አስተዳዳሪ፡፡ ✤፠ #መምህር_ክፍሌ_ወለደ_ጻድቅ፤ የጽጌ ዚቅን (ዚቅን) (የታች ቤትን) አቀናብረው ያቀረቡ፤ የደብረ ኃይል ወደብረ ጥበብ በዓታ የአቋቋም ዋና ምስክር የነበሩ፡፡ የአሁንን ዝክረ ቃልን በቀድሞ ስሙ አባጃሌ የተባለውን መጽሐፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሕትመት ያበቁ፡፡ ✤ #መምህር_ላዕከ_ጊዮርጊስ_ደምሴ፤ የግምጃ ቤት ማርያም የሐዲሳት ምክትል መምህር የነበሩና ዜማ አዋቂ ምሁር፤ በወርኃ ጽጌ የዕለቱን ምሥጢር በተመለከተ ዚቅ እያዘጋጁ ለሊቃውንቱ ያቀርቡ የነበሩ ✣✤✣ #መካነ_ነገሥት_ግምጃ_ቤት_ማርያም፤ ለሃገራችን ኢትዮጵያና ለኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ ባለውለታ የኾነች ጥንታዊት ቤ.ክ.፤ በደርቡሽ ወረራ ጊዜ መመህራን ጕባኤያችንን (ማስተማራችንን የታሪክ መዘክርነታችንን) ለቅቀን አንሔድም በማለት ሰማዕት የኾኑባት፡፡ **የብዙ ሊቃውንተ መፍለቂያ፤ እስከ ዐፄ ኀይለሥላሴ ዘመን ድረስ (ከሠለስቱ ምዕትና ከልደታ አብያተ ክርስቲያናት ጕባኤ ቤት በመቀጠል) በሃገራችን ኢትዮጵያ ብቸኛዋ የታች ቤት የመጻሕፍት /አንድምታ ትርጓሜ/ (የ4ቱ ጕባኤያት) ብቸኛ ማስመስከሪያ፡፡ /በአሁኑ ሰዓት በዋነኛነት በኢትጵያ ደረጃ የመጻሕፍተ ሐዲሳት የታች ቤት ትርጓሜ ዋና ማስመስከሪያ መካነ አእምሮ (university)/፡፡ እዲሁም የላይ ቤት የአቋቋም የዜማ የድርሰት ማዕከልና ዋና አብነት ነች፡፡ በውስጧ ተዓምረኛ የኾነች የእምቤታችን ሥዕል ይገኝባተል፡፡ /ፎቶ፤ HYPERLINK "https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/" የቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት/

እንደ መድኀኔ ዓለም ፈቃድ፤ ልዩ መርሐ ግብር ስለሚኖር እንዳያመልጥዎ፤ የጽጌ ሥርዐተ ማኅሌት እንደተለመደው በጕባኤው ላይ ይታደላል፡፡ #የዐርብ_ጕባኤ_፻፵፯ኛ_ሳምንት #መስከረም_፴/፳፻፲፪ዓ.ም. ከ፲
እንደ መድኀኔ ዓለም ፈቃድ፤ ልዩ መርሐ ግብር ስለሚኖር እንዳያመልጥዎ፤ የጽጌ ሥርዐተ ማኅሌት እንደተለመደው በጕባኤው ላይ ይታደላል፡፡ #የዐርብ_ጕባኤ_፻፵፯ኛ_ሳምንት #መስከረም_፴/፳፻፲፪ዓ.ም. ከ፲፪-፪ ሰዓት፤ #በሰዐቱ_ይገኙ!!!!!!!! እንዳያመልጥዎ!! በታላላቅ ገዳማት የሚጸለየው #የመሐረነ_አብ ጸሎት ይደርሳል፡፡ ላልሰሙት ያሰሙ፤ <<Like, Share>> በማድረግ ይተባበሩ /የቀ.ደ.ሰ መድኀኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት፡፡/

#ነግሥ_ነግሥ_ነግሥ እንኳን ለወርኃ ጽጌ በሰላምና በጤና አደረሰን፥ አደረሳችሁ፡፡ በማንኛውም ወርኀዊና ዓመታዊ ክብረ በዓላት ላይ ማኅሌተ ጽጌን ጨምሮ ማኅሌት ሲቆም፤ መጀመሪያ የሚባለውን ነግሥንና የ
+6
#ነግሥ_ነግሥ_ነግሥ እንኳን ለወርኃ ጽጌ በሰላምና በጤና አደረሰን፥ አደረሳችሁ፡፡ በማንኛውም ወርኀዊና ዓመታዊ ክብረ በዓላት ላይ ማኅሌተ ጽጌን ጨምሮ ማኅሌት ሲቆም፤ መጀመሪያ የሚባለውን ነግሥንና የነግሥ መቅድምን እነሆ፡፡ *ነግሥ ምን ማለት ነው *ዚቅ ምን ማለት ነው *የነግሥ መቅድምና ነግሥ ቀመረ መረግድ፤ (ማንኛውም ማኅሌት ሲቆም ባለ 5 መስመር ግጥም ሲሆን እያንዳንዱ መስመር 28ት ጊዜ በከበሮና በጸናጽል ይመረገዳል ፤ የአመረጋገዱን ቅደም ተከተል እንዲቀላችሁ በማሰብ በቀመር (በቊጥር አስቀምጠንላችኋል፡፡) ….. ከጽሑፉ ያገኟቸዋል፡፡ ይህን ነግሥ በሁሉም ማኅሌት መጀመሪያ የሚባል እንደመሆኑ መጠን በቃላችሁ አጥኑት፡፡ /ፎቶ፤ HYPERLINK "https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/" የቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት/

እንኳን ለቅድስት አርሴማ ዓመታዊ ክብረ በዓል (በዓለ ዕረፈት) አደረሰን፥ አደረሳችሁ፡፡ በዚህች በመስከረም 29 ቀን አርሴማ ቅድስት ወሰማዕት እና የእርሷ ማኅበርተኞች ድል አድራጊዎች 27 ሰማዕታት በሰማዕትነት ያረፉባት ዕለት ነች፡፡ እግዚአብሔር ከእነዚህ ቅዱሳን ሰማዕታት ረድኤት በረከታቸውን ይክፈለን፡፡ እነዚህም ቅዱሳን፤ 1ኛ. #አርሴማ፤ #ቅድስት_ወሰማዕት_ኃያል_ተጋዳሊት_ 2ኛ. ኢያሚኖስ፤ ጸሎትን የሚያሳርግ ካህን 3ኛ. አፍጢኖስ፤ ከብዙዎች የተመረጠ 4ኛ. በርቲኖስ፤ ጻድቅና ቸር 5ኛ. ጢሞና፤ በመላላክ ሥራ አገልጋይ የኾነ 6ኛ. ጢሞዓና፤ ተአጋሽና ጸዋሚ 7ኛ. ዘኬዎስ፤ ከከበሩ የከበረ 8ኛ. እስጢፋኑ፤ ተጋዳይና የበደሉትን ይቅር ባይ 9ኛ. አርሞና፤ ከጎልማሶች ይልቅ ደም ግባቱና መልኩ ያማረ 10ኛ. ኪርያኮስ፤ ሥጋውን ያላረከሰ ንጹሕ 11ኛ. አንጥያኮስ፤ ቡሩክ የኾነ የአቡሪ ልጅ 12ኛ. ያዕቆብ፤ የእግዚአብሔር ታማኝ የኾነ 13ኛ. ቡራኬሌስ፤ በሰው ዘንድ ተወዳጅ የኾነ 14ኛ. አስቂርያቆስ፤ ክርስቶስን የሚወደው 15ኛ. አስኪርያኖስ፤ ባለሟል የኾነና ግርማው የሚያስፈራ 16ኛ. ሚርያኖስ፤ ፊቱና መልኩ ደስተኛ የኾነ 17ኛ. ትትግርጦስ፤ ወደ ንስሐ የተመለሰ 18ኛ. ያስቲኖስ፤ የሚፈርድና የሚበይን 19ኛ. ጥልያኖስ፤ ያላመኑ ሰዎችን የሚገስጽ 20ኛ. ዑልያኖስ፤ የዚህ ዓለም ጥበብ መምህር የኾነ 21ኛ. ጴርቅላስ፤ በስም አጠራርና በሽምግልና መልካም የኾነ 22ኛ. ኬብያኖስ፤ ተጋዳይ የኾነ 23ኛ. ጴጥሮስ፤ የጠራ የባሕርይ ዕንቊ 24ኛ. ጰኵንዮስ፤ የሮምያ ሹም 25ኛ. ሐናንያ፤ የዋህና ሽንገላ የሌለው 26ኛ. ሐሊባኖስ፤ ጾምና ጸሎትን የሚወድ 27ኛ. ኤስያኖስ፤ በመንፈስ ቅዱስ ጎልማሳ የኾነ 28ኛ. ኤልያብ፤ በረኛና የሰማዕት መጀመሪያ፡፡ ሰላም ለፀዐተ ነፍስኪ በጊዜ ኃለፈ ሰይፍ፤ መንገለ ክሣድኪ ድኑን ለአምሳለ መሥዋዕት ውኩፍ፡፡ እስእለኪ አርሴማ በከናፍር ወአፍ፤ ረድኤትኪ ትሩፍ በላዕሌየ ያንጸፈጽፍ፤ እስመ አርአየኒ ዘንተ ሞትኪ ትሩፍ፡፡ ሰላም ለዘአዕረፉ ምስሌኪ ፳ወ፯ቱ ሰማዕታት፤ ረድኤቶሙ ትረድ ላዕሌየ ዘምስለ ብዙኅ ምሕረት፡፡ ወኀበ ሀለወ ስሞሙ ምስለ ስምኪ ቅድስት፤ ዓዲ ኢይቅረብ አርሴማ ሕማመ ብድብድ ወሞት፤ በኵሉ አዝማን ወበኵሉ ዓመታት፡፡ /ፎቶ፤ HYPERLINK "https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/" የቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት/

መድኀኔዓለም ተወከፍ እንተ አቅረብኩ ንስቲተ፤ ዘሰተይከ በእንቲአየ ከርቤ ወሐሞተ፤ በሞተ ዚአከ ከመ ትቅትል ሞተ፡፡ ትርጕም፤ ፈጣሪዬ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ ሆይ ፤ በሞትህ ሞትን ታጠፋው ዘንድ ከርቤ
+3
መድኀኔዓለም ተወከፍ እንተ አቅረብኩ ንስቲተ፤ ዘሰተይከ በእንቲአየ ከርቤ ወሐሞተ፤ በሞተ ዚአከ ከመ ትቅትል ሞተ፡፡ ትርጕም፤ ፈጣሪዬ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ ሆይ ፤ በሞትህ ሞትን ታጠፋው ዘንድ ከርቤ የተቀላቀለበትን መራራ ሐሞትን ስለኔ ሕይወት የጠጣህ የአቀረብኳትን አነስተኛ የምስጋና መባ በቸርነትህ ተቀበል፡፡ (መልክአ መድኀኔ ዓለም ለዝክረ ስምከ) ፎቶዎቹ፤ ፩ኛ) መ.መ.መ. (መንበረ መንግሥት መድኀኔ ዓለም /ጎንደር/) ፪ኛ) ደ.ቀ.መ. (ደብረ ቀራንዮ መድኀኔ ዓለም) ፫ኛ) ቀ.ደ.ሰ. (ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም) /የቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት/

✤✣✤#ገዳመ_ጽጌ_ድግል_፤ የአቡነ ጽጌ ድንግል ገዳም በ14ኛው ክፍለ ዘመን የተመሠረተው በታላቁ አባት በአቡነ ጽጌ ድንግል ሲኾን፤ እኝህ ታላቅ አባት እጅግ ሰፊ ኾኖ የሚያምረውንና ዕጹብ ድንቅ የሚያሰኘውን ባለሦስት ክፍል (ቅኔ ማሕሌት፣ ቅድስትና መቅደስ) ያለውን የገዳመ ጽጌን ውቅር ዋሻ ቤተክርስቲያን ያነጹ፣ ከሰባቱ ቅዱሳን ዘጋሥጫ (አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ዘደብረ ጎል፥ አቡነ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ፥ አቡነ ያዕቆብ ዘቀዳሚት ግሸን ደብረ ከርቤ፥ አቡነ ገብረ እንድርያስ ዘደብረ ቆዘት፥ አቡነ ዘካርያስ ዘወለቃ፥ አቡነ ዮሴፍ ዘወለቃ፥ የዝቋላው አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዘምስካበ ቅዱሳን ገዘዛ) አንዱ የኾኑና የወርቃማ ዘመን ወርቃማ ደራሲ የኾኑ በዚህም በቤተክርስቲያናችን ከመስከረም ፳፮ እስከ ኅዳር ፮ የምንጸልይበትንና የምናመሰግንበትን ማሕሌተ ጽጌን ባለ ፭ት አርኬና እንደ መዝሙረ ዳዊት በ፻፶ መዝሙር ልክ አድርገው የደረሱና ጸሐፊያቸው በኾኑ ጓደኛቸው አቡነ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታ አጽፈው ለትውልድ ያስተላለፉ፤ እንዲሁም ሰቈቃወ ድንግልን ከጓደኛቸው አቡነ ገብረ ኢየሱስ ዘገዳመ መጕና ጋር አብረው የደረሱ ቅዱስ አባት ናቸው፤ እንዲሁም በዘመናቸው ከነበሩት ከጓደኛቸው ከታላቁ አባት አቡነ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ጋር ብዙ ገቢረ ተዓምራትን የሠሩ (የወለቃ ወንዝ ድልድይን ጨምሮ ያነጹ)፥ አሁንም ብዙ ገቢረ ተዓምራትን የሚሠሩ አባት ናቸው፡፡ ገዳሙ የሚገኘው በደቡብ ወሎ ሃገረ ስብከት፥ በወግዲ ወረዳ ልዩ ስሙ ደብረ (ገዳመ) ጽጌ ጫቀታ በሚባል ቦታ፤ ለዐባይ ወንዝ ገባሮች ከኾኑትና በበረሀ ውስጥ ከሚጓዙት አንዱ በኾነው በወለቃ ወንዝ አቅራቢያ ነው፡፡ ገዳሙ ለታላቁ አባት በተሰጠው ቃል ኪዳን መሠረትም አኹንም ድረስ ፈውሰ ሥጋ፥ ፈውሰ ነፍስ እየሰጠ ይገኛል፤ የገዳሙ ፍየሎችና ከብቶችም በአካባቢው ከሚገኙት ነብሮች ጋር አብረው ያለምንም አደጋ ይኖራሉ፡፡ ገዳሙ በግራኝ መሐመድ ወረራ ወቅት 500 መነኰሳት በሰማዕትነት የተሰየፉበት ሲኾን ከዚህ ጀምሮ እስከ 20ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ተዘግቶ ቆይቶ በልዑል ራስ ካሣ ኀይሉ አማካይነት ተከፍቶ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል፤ በድጋሚ በጣሊያን ወረራ ወቅት አደጋ ደርሶበታል፤ በደርግ ዘመንም የገዳሙ 84 ጋሻ መሬት ስለተወሰደበት እንደገና እስከ ከ1995ዓ.ም. ገዳሙ ዘግቷል፤ ነገር ግን በ1995ዓ.ም. በበጎ አድራጊ ምዕመናን ድጋሚ ሊከፈት ችሏል፡፡ ማሕሌተ ጽጌ የተደረሰበት ይህ ገዳም እስከ 2008ዓ.ም. ማሕሌቱ ሳይቆምበት ቆይቶ ከ2009 ዓ.ም. ጀምሮ ማሕሌቱ እየተቆመ ይገኛል፡፡ ለበርካታ ዓመታት የሊቁ የአባ ጽጌ ድንግል በዓለ ዕረፍት መስከረም 27 መከበር አቁሞም ነበር፤ እንደ አምላከ አበው ፈቃድ ከ2011 ዓ.ም. ጀምሮ ክብረ በዓሉ በገዳም ሥርዐት እየተከበረ ይገኛል፡፡ ወደ ገዳሙ ለመሄድ ለሚፈለጉ ምዕመናን፤ (በተለይ ወደ ግሸን ደብረ ከርቤ የተጓዛችሁ በዛው ለመሄድ ቅርብ ነው፡፡) 1ኛ) ከደሴ ከተማ ለምትነሱ ወግዲ በሚል መኪና ከተሳፈሩ በኋላ ከተወሰኑ የእግር ጕዞ በኋላ ይገኛል፤ 2ኛ) ከጎጃም በመካነ ሰላም ለምትነሱ ወግዲ በሚል መኪና ከተሳፈሩ በኋላ ከተወሰኑ የእግር ጕዞ በኋላ ይገኛል፤ 3ኛ) በመርሐ ቤቴ በሚዳ ለምትነሱ ወግዲ በሚል መኪና ከተሳፈሩ በኋላ ከተወሰኑ የእግር ጕዞ በኋላ ይገኛል፡፡ † በዚሁ አጋጣሚ የታለቁ ሊቅ የአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በዓለ ጽንሰታቸውም ጥቅምት 3 ስለሚከበር አብሮ ማክበር ይቻላል፡፡ /ከዋልድባ ዋሊ ገጽ የተወሰደ/ (የገዳሙን ኹኔታ የዘገበልንን ወንድማችንን አምላከ አባ ጽጌ ድንግል ወጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ይስጥልን፤ በረድኤት በበረከት ቅዱሳን ሊቃውንቱ ይጎብኙልን፡፡)

✤✤#መስከረም_27_ሊቁ_አባ_ጽጌ_ድንግል (#ጽጌ_ብርሃን)፤ #የማኅሌተ_ጽጌ_ደራሲ¬ ✤✤ የተወለደው በ14ኛው መ.ክ.ዘ. በሰሜን ሸዋ በይፋት(ዊፋት) አውራጃ ውስጥ ሲሆን፤ ነገዱ ታቦተ ጽዮንን ይዘው ከመጡት ከ318 ሌዋውያን ነው፡፡ የቀድሞ እምነቱ አይሁዳዊ ሲኾን ስሙም ዮሐኒ ይባል ነበር፡፡ በወጣትነት ዕድሜው አውሬ ለማደን በይፋት አውራጃ በምትገኝ ልዩ ስሟ ገዳመ ደነስ ወደሚባል ዱር (ጫካ) ሄደ፤ በጫካዋ ውስጥም ፊቷ በጽጌረዳ አበባ የተከበበና ያጌጠ፣ እጅግም ደስ የምታሰኝ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ሥዕል አይቶ በሥዕሏ ውበት እየተደነቀ ሲመለከት እንደ እርሱ ያልተጠመቀ አይሁዳዊ ጓደኛው መጥቶ፣ ‹‹ምን እየፈለግህ ነው? የክርስቲያኖችን ሥዕል ነውን?›› ብሎ ለድንግል ማርያም ምስጋና ይግባትና በያዘው በትር ሥዕሏን ሲመታት ወዲያው ተቀሥፎ ሞተ፣ ከዚህ በኋላ ቅዱስ ሩፋኤል በነጭ ወፍ ተመስሎ አንድ መነኵሴ እሰኪመጣ ድረስ፣ ይህችን ሥዕል ጠብቃት ብሎ በሰው አነጋገር ነግሮት ተሠወረ፣ አቡነ ዜና ማርቆስ ደብረ ብስራት ከሚባለው ገዳሙ ወደ ይፋት መጥቶ ከነቢዩ ኢሳይያስ ትንቢት በምዕ. 11፥1 ‹‹ትወጽእ በትር እምሥርወ እሴይ ወየዐርግ ጽጌ እምኔሃ (ከዕሤይ ግንድ በትር ትወጣለች /ትገኛለች/ ከሥሩም ቁጥቋጦ ያፈራል››) እያለ ሲያነብ አባ ጽጌ ድንግል በሰማ ጊዜ አባቶቼ አይሁድ የነቢያትን ትንቢት ንባቡን አስተምረውኛል አውቀዋለሁ፤ ትርጕሙን ግን አላውቀውምና ተርጕምልኝ አለው፡፡ አቡነ ዜና ማርቆስም ሲተረጕምለት እንዲህ አለ፤ ፠ትወጽእ በትር እምሥርወ እሴይ፣ የሚለው ከእሴይ ነገድ የሕይወት በትር የኾነች ድንግል ማርያም ትወለዳለች፡፡ ፠ ወየዐርግ ጽጌ እምኔሃ የሚለው ንባብ ደግሞ፤ ከእመቤታችን ጌታችን በድንግልና ይወለዳል፤ ጌታችንም ተወልዶ ትንቢቱ ተፈጽሟል ብሎ ተረጐመለት፡፡ ኢሳ. 7፥14፣ ማቴ. 18፥24፡፡ ይህ ሰውም (አባ ጽጌ ድንግልም) በዚህ ትርጕም ደስ ተሰኝቶ አባት ሆይ በመልካም ሁኔታ ተረጐምከው አለውና፣ ሥዕሏ ወዳለችበት ቦታ ወስዶ ታሪኩ ከላይ የተገለጸውን ሁሉ ነገረው፣ አቡነ ዜና ማርቆስም ከሥዕሏ የተደረገውን ተአምር ሰምቶ፣ እጅግ ደስ አለውና አስተምሮ አጥምቆ #ጽጌ_ብርሃን_ ብሎ ሰየመው፡፡ ከዚህ በኋላ ሥዕሏን ከገዳመ ደንስ ደብረ ብሥራት ወደሚባል ገዳሙ ወስዶ በዘመነ ጽጌ ጥቅምት አንድ ቀን በክብር አስቀመጣት የምትከብርትንም ቀን ጥቅምት 3 እና ሰኔ 8 ቀን አደረገ፡፡ አቡነ ዜና ማርቆስም ጽጌ ብርሃንን ለመዓርገ ምንኵስና አበቃው፤ አባ ጽጌ ድንግል ምንም እንኳን አስቀድሞ ብሉያትን ቢማርም ከአቡነ ዜና ማርቆስ ዘንድ ብሉያትንና ሐዲሳትን ንባባቸውን ከነትርጓሜያቸው ተማረ፡፡ አባ ጽጌ ድንግል ከሰባቱ ቅዱሳን ዘጋሥጫ (አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ዘደብረ ጎል፥ አቡነ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ፥ አቡነ ያዕቆብ ዘቀዳሚት ግሸን ደብረ ከርቤ፥ አቡነ ገብረ እንድርያስ ዘደብረ ቆዘት፥ አቡነ ዘካርያስ ዘወለቃ፥ አቡነ ዮሴፍ ዘወለቃ) አንዱ የኾኑና ገባሬ ተዓምራት ወመንክራት የኾኑ የወርቃማ ዘመን ወርቃማ ደራሲ ናቸው፡፡ በወርቃማ ደራሲነታቸው ማኅሌተ ጽጌንና ሰቈቃወ ድንግልን ደርሰዋል፡፡ ሊቁ ሲደርሱም ዋርማ (ሽክና) ሙሉ እንባን እያነቡ ባነቡት እንባ ቀለም እየበጠበጡ እርሳቸው እየደረሱ፤ ጸሓፊያቸውና ጓደኛቸው የኾኑት አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታ ደግሞ እየጻፉ ነው፡፡ #ማኅሌተ_ጽጌ_ እመቤታችንንና ፈጣሪ ልጇን በጎ፥ በጎ መዓዛ ባላቸው አበባዎችና ፍሬዎች እየመሰለ የሚያመሰግን ሲኾን፣ በአባቷ በዳዊት መዝሙር መጠን 150 አድርጎ ደረሶታል፤ ፍሬ ከአበባ አበባም ከፍሬ እንደሚገኝ ኹሉ በማኅሌተ ጽጌ እመቤታችንን በአበባ፥ ጌታችን በፍሬ፤ ወይም እመቤታችንን በፍሬ፥ ጌታችንን በአበባ እየመሰለ እጅግ አስደናቂ የሆኑ ታሪኮችን እያጣቀሰ ደርሶታል፡፡ ዘመነ ጽጌ ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 5 ድረስ 40 ቀናት ሲኾን በዚህ ወቅት የሚጾመው ጾም ጾመ ጽጌ ሲባል ጾሙ የፈቃድ ነው፡፡ #ሰቈቃወ_ድንግል፤ ማለት እመቤታችን ከልጇ ከመድኀኔዓለም፥ ከአረጋዊ ዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር በስደቷ ወቅት ያየችውን መከራ፥ ልቅሶ፥ ዋይታ የሚዘከርበት የማኅሌተ ጽጌ አርኬ ነው፡፡ የሰቈቃወ ድንግልን ደራሲ በተመለከተ አባ ጽጌ ድንግል ደረሱት የሚሉ አሉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ አባ ገብረ ኢየሱስ ዘገዳመ መጕና ወይም /አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ/ ወይም /አባ አርከ ሥሉስ/ ነው የደረሱት የሚሉም አሉ፡፡ በገቢረ ተዓምራት አድራጊነታቸውም እንደ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በአየር ላይ የሚጓጓዙት በክነፈ ነፋስ፥ በሠረገላ እሳት፥ በደመናት፥ በመባርቅትና በነጐድጓድ ሲኾን በምድር ላይ ደግሞ በአንበሳና በነብር ተጭነው እንዲሄዱ ጸጋው ተሰጥቷቸው ነበር፡፡ በዘመናቸው ከነበሩት ከጓደኛቸው ከታላቁ አባት አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ጋር ብዙ ገቢረ ተዓምራትን የሠሩ ሲኾን የእግዜር ድልድይ (የወለቃ ወንዝ ድልድይን) ያነጹ፥ ብዙ ድውያንና ሙታንን አብረው ያስነሱ ናቸው፤ አሁንም ብዙ ገቢረ ተዓምራትን የሚሠሩ አባትም ናቸው፡፡ ገዳሙ የተመሠረተው በአባ ጽጌ ድንግል ሲኾን፤ እጅግ ሰፊ ኾኖ የሚያምረና ዕጹብ ድንቅ የሚያሰኝ ባለአራት ክፍል (ቅኔ ማኅሌት፣ ቅድስትና መቅደስ፣ አጽመ ቅዱሳን ማረፊያ) ያለው ነው፡፡ የሚገኘውም በደቡብ ወሎ ወግዲ ወረዳ ነው፡፡ /ምንጭ ገዳሙ ካሳተመው ታሪክና ከቀ.ደ.ሰ. መድኀኔ ዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሰሌዳ መጽሔት፡፡/ /የቀ.ደ.ሰ. መድኀኔ ዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት፡፡/

#ዘመኑን_የዋጀ_ተከታታይ_መንፈሳዊ_ትምህርት_ (Course)፤ ለወጣቶች (በቀንና በማታ) እና ለሕፃናት (በቀን)፤ ለምትፈልጉ ምዕመናን በሙሉ፤ ሰ/ት/ቤታችን የቀ.ደ.ሰ መድኀኔ ዓለም ወደ/ት/ቅ/ገብር
+2
#ዘመኑን_የዋጀ_ተከታታይ_መንፈሳዊ_ትምህርት_ (Course)፤ ለወጣቶች (በቀንና በማታ) እና ለሕፃናት (በቀን)፤ ለምትፈልጉ ምዕመናን በሙሉ፤ ሰ/ት/ቤታችን የቀ.ደ.ሰ መድኀኔ ዓለም ወደ/ት/ቅ/ገብርኤል ፍኖተ ሕይወት ለወጣቶችና ሕፃናት ምዕመናን በ2012ዓ.ም. ልዩ ተከታታይ ትምህርቶችን አዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል፡፡ የትምህርቶቹ ዓይነቶች፤ በወጣት ክፍል የሚሰጡ፤ ✤ #በቀዳማይ፤ * ትምህርተ ሃይማኖት (መግቢያ ሥነ ፍጥረትና አእማድ) * የቤተ ክርስቲያን ታሪክ መግቢያና በዓለም መድረክ * የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መግቢያና አዋልድ ቅዱሳት መጻሕፍት * ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ✤ #በካልዓይ፤ * ነገረ ማርያም ወነገረ ቅዱሳን * የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ (የቤ.ክ ታሪክ በኢትዮጵያ) * ብሉይ ኪዳን * ተግባራዊ ክርስትና (ክርስቲያናዊ ሕይወት) ✤ #በሣልሳይ * ነገረ ክርስቶስ ወነገረ ድኅነት * ልሳነ ግእዝ * ሐዲስ ኪዳን * ሥርዐት ወምሥጢራተ ቤ.ክ እንዲሁም በሕፃናት ክፍል የአብነት ትምህርትን ጨምሮ የተለያዩ ትምርቶች ይሰጣሉ፡፡ ትምህርቱ የሚሰጠው፤ * ለወጣቶች በቀን (ቅዳሜ ከ9-11 ና እሑድ ከ4፡30-6፡30) * ለወጣቶች በማታ (ሰኞ፣ ረቡዕና ዐርብ ከ12-2)፤ ለ6 ወራት * ለሕፃናት በቀን (ቅዳሜ ከ6፡30-8፡30 ና እሑድ ከ6፡30-8፡30) ✣✣ መመዝገቢያ፤ በሰ/ት/ቤቱ ጽሕፈት ቤትና ትምህርት ክፍል ✣ ከአኀት ሰንብት ትምህርት ቤቶችና ከግቢ ጕባኤ ለመማር የምትመጡ የተማራችኋቸውን ትምህርቶች የሚገልጽ ደብዳቤ (ምስክር ወረቀት /ካርድ (Certeficet)/ ማምጣት ይጠበቅባችኋል፡፡ ✤✤ ትምህርቱ ጥቅምት 1 ይጀመራል፡፡ ‹‹የነፍስ ምግቧ የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡›› ለበለጠ መረጃ፤ 0922 85 13 74 /0921 05 60 56/

እንኳን ለዘመነ ጽጌ (ከመስከረም ፳፮ - ኅዳር ፭) በሰላምና በጤና አደረሰን ፥ አደረሳችሁ፡፡ ኀለፈ ክረምት ቆመ በረከት፣ ተሠርገወት ምድር በሥነ ጽጌያት፡፡ ትርጕም፤ የክረምት ዘመን (ከሰኔ 26 -
+3
እንኳን ለዘመነ ጽጌ (ከመስከረም ፳፮ - ኅዳር ፭) በሰላምና በጤና አደረሰን ፥ አደረሳችሁ፡፡ ኀለፈ ክረምት ቆመ በረከት፣ ተሠርገወት ምድር በሥነ ጽጌያት፡፡ ትርጕም፤ የክረምት ዘመን (ከሰኔ 26 - መስከረም 25) አለፈ፥ ሄደ /መኃ.2 11/፡፡ የጽጌ ዘመን (ከመስከረም 26 - ኅዳር 5) ተተካ፡፡ /የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ. ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት፡፡/

#የዐርብ_ጕባኤ_፻፵፮ኛ_ሳምንት #መስከረም_፳፫/፳፻፲፪ዓ.ም. ከ፲፪-፪ ሰዓት፤ #በሰዐቱ_ይገኙ!!!!!!!! እንዳያመልጥዎ!! በታላላቅ ገዳማት የሚጸለየው #የመሐረነ_አብ ጸሎት ይደርሳል፡፡ ላልሰሙት
+1
#የዐርብ_ጕባኤ_፻፵፮ኛ_ሳምንት #መስከረም_፳፫/፳፻፲፪ዓ.ም. ከ፲፪-፪ ሰዓት፤ #በሰዐቱ_ይገኙ!!!!!!!! እንዳያመልጥዎ!! በታላላቅ ገዳማት የሚጸለየው #የመሐረነ_አብ ጸሎት ይደርሳል፡፡ ላልሰሙት ያሰሙ፤ <<Like, Share>> በማድረግ ይተባበሩ /የቀ.ደ.ሰ መድኀኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት፡፡/