cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ኢትዮጵያ

ስለ ሀገራችን ታሪክ ፣ ባህል ፣ ጥንታዊ ቅርሶች ፣ ገዳማት ፣ መጎብኘት ስላለባቸው ስፍራዎች መረጃ ለማግኘት ካስፈለገ ይህንን ቻናል ይቀላቀሉ ። ኢሉሚናቲን እናወግዛለን። የዚህ ቻናል አላማ ትውልዱ ሐይማኖቱንና ታሪኩን ያውቅ ዘንድ እና ሙሉ ትውልድ ይሆን ዘንድ ማገዝ ነው ። አንድነታችን ለህልዉናችን @HISCULHEROFETHIOPIA

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
390
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-17 أيام
-1030 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Repost from N/a
ክርስቶስ ከሙታን ተነስቷል። በራሱ ኃይል ስልጣን። የእግዚአብሔር ሰለም ከእናተ ጋር ይሁን። የጌታችን የመደኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሞቱ በራሱ መሥዋዕትነት እንጂ በኃይል ወይም በግዳጅ አለመሆኑ ትንሣኤው አረጋግጧል።የክርስቶስን ትንሣኤ ማመን ማለት በእርሱ ፍቅር በእርሱ ምሥዋዕት ሆኖ መቅረብና በእርሱ የሰው ልጆችን ከሞት ባርነት ነጻ ማውጣት ማመን ነው። ከዚህ ተጨማሪ በእርሱ ኃይል አስቀድሞ ስለራሱ በተናገራቸው ቃላትና ከእግዚአብሔር ጋር አንድ በመሆኑ ማመን ነው። ይህ ኃይል በሥጋው ሞቶ በመለኮቱ ሕያው የሆነው የአንድዬ የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ነው። ይህ ኃይል ለዮሐንስ በራዕዩ እንደሚከተለው የተነገረው የአንድዬ የኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ነው።".....አትፍራ ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ ሞቼም ነበርሁ እንሆም ከዘላለም አስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ የሞተና የሲዖል መክፈቻ አለኝ።"ራእ 1:8። ስለዚህ ኃይል አንድዬ ሐዋርያውን ቅዱስ ጴጥሮስን በሐምሣኛው ቀን መንፈስ ቅዱስ በወረደባቸው ጊዜ ሰክረዋል የሚል ቃል ከአይሁድ በተነገረባቸው ጊዜ እንዲህ ብሎ አናግሮታል"እግዚአብሔር ግን የሞትና ጣር አጥፍቶ አስነሰው ሞት ይይዘው ዘንድ አልቻለምና።" ሐዋ 2:24። ዳዊትንም ትንቢት አናግሮታል"...ነፍሴን በሲዖል አትተዋትምና ቅዱስ መበስበስን ያይ ዘንድ አተሰጠውም። " መዝ 15: 8-11።ቅዱስ ጳውሎስም ፦ "....ክርስቶስ ከሙታን ተነሥቶ ወደ ፊት እንዳይሞት ሞትም ወደ ፊት እንዳይገዛው እናውቃለንና። " ሮሜ 6 :9። ስለዚህ የጌታችን ትንሣኤ የሚያስተምረን ወደፊት የማይምት ሞት የማይገዛው አምላካችን ነው። አለም ያላት አምላክ ግን "የዚህ ዓለም አምላክ የማያምኑትን አሳብ አሳወረ" 2ኛ ቆሮ 4:4 ተብሎ እንደተነገረ አለም ያላት አምላክ ወደውጭ የሚጣል እና የሚፈረድበት ነው። ዮሐ 12:31-32 ራእ 20:10። መልካም ጊዜ።
إظهار الكل...
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ           አሜን ✍"ችግር ለራሳችን እንድንጸልይ ያነቃቃናል፤ ፍቅር ደግሞ ለሌሎች ሰዎች እንድንጸልይ ያስገድደናል" ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን           በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን አሰሮ ለሰይጣን አግዓዞ ለአዳም ሰላም እምይእዜሰ ኮነ ፍስሐ ወሰላም      🛎 ስንክሳር ዘወርኀ ግንቦት ፱       አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ግንቦት ዘጠኝ በዚች ቀን የጻድቅ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ እናት ቅድስት ዕሌኒ አረፈች። ❖ ይቺም ቅድስት በፊት የአንድ ነጋዴ ሰው ሚስት ነበረች እርሱም በነገረ ሠሪ ንጽሕት ሁና ሳለች ወደ ባሕር ጣላት፤ የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ፈቃድም ሮሐ ከሚባል አገር ደርሳ የበራንጥያ ንጉሥ ቊንስጣ አገኛት፤ ውበቷንና ደም ግባቷንም አይቶ አገባት ለክርስቲያን ነገሥታት መጀመሪያቸው የሆነውን ቈስጠንጢኖስን ወለደችው ምግባርንና ሃይማኖትን በማስተማር በመልካም አሳደገችው። ❖ ልጇም በነገሠ ጊዜ ወደ ኢየሩሳሌም ሒደሽ የክብር ባለቤት የሆነ የክርስቶስን መስቀል ግለጪ የከበሩ ቦታዎችንም ሥሪ የሚላትን በሕልሟ አይታ እንዴት እንዳየች ይህን ለልጇ ነገረችው እርሱም ከብዙ ሠራዊት ጋራ ሰደዳት። ❖ በደረሰችም ጊዜ የክብር ባለቤት ስለሆነ ስለ ጌታችን መስቀል መረመረች አዳኝ የሆነ መስቀሉንም ሁለቱ ወንበዴዎች ከተሰቀሉባቸው መስቀሎች ጋራ አገኘችው፤ የክብር ባለቤት የክርስቶስ መስቀል የትኛው እንደሆነ ታውቅ ዘንድ በወደደች ጊዜ ከራሱ በላይ ይህ የናዝሬቱ ኢየሱስ የአይሁድ ንጉሥ ነው የሚል በእንጨት የተቀረጸበት ጽሑፍ ያለው እንደሆነ የኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ ቅዱስ መቃርስ ነገራት። ❖ ከዚህ በኋላ ከእርሱ ምልክት ታይ ዘንድ ፈለገች የሞተ ሰውም አግኝታ መስቀሎችን በበድኑ ላይ አኖረች አልተነሣም፤ ከዚህ በኋላ ሦስተኛውን መስቀል በላዩ አኖረች፤ ያን ጊዜ ምውት ተነሣ ሃይማኖቷም ጸና ደስታዋም በዛ። ❖ ከዚህ በኋላም ዜናቸው በመስከረም ወር በዐሥራ ሰባት የተጻፈ በከበሩ ቦታዎች ውስጥ አብያተ ክርስቲያናትን ትሠራ ዘንድ ጀመረች፤ ለአባ መቃርስም በከበሩ ቦታዎች ሁሉ አብያተ ክርስቲያናትን እንዲሠራ ብዙ ገንዘብ ሰጠችው። ❖ ከዚህ በኋላ ወደ ልጇ ተመልሳ የሆነውን ሁሉ ነገረችው የከበረ መስቀል በመገኘቱ እጅግ ደስ አለው፤ ይቺም ቅድስት በጎ ገድሏን ከፈጸመችና እግዚአብሔርንም ከአገለገለች በኋላ ስለ ካህናትም ልብስና ቀለብ ለአብያተ ክርስቲያናትና ለገዳማት ብዙ ጉልቶችና ርስቶችን ለድኆችና ለምስኪኖችም እንዲሁ ከሠራችና ከተከለች በኋላ በሰላም አረፈች መላ ዕድሜዋም ሰማንያ ሆነ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቷ ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                    አርኬ ✍️ ሰላም ለዕሌኒ ውስተ ምድረ ሕይወት ኤልዳ። ምክረ መንፈስ ቅዱስ አመ ወስዳ። ለሐይወ በድን በለኪፈ መስቀል ቅድመ ዐውዳ። እምአይቴ አንተ ትቤሎ ወእምአይ እንግዳ። ዘተረከብከ ግዱፈ በበዳ። በዚችም ዕለት የበይደርና የስልዋኖስ መታሰቢያቸው ነው በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ለዘላለም ትኑር አሜን።
📌 ግንቦት 9 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1. ቅድስት እሌኒ ንግሥት 2. ቅዱስ ስልዋኖስ 📌 ግንቦት 9 ቀን የሚከበሩ ወርሐዊ በዓላት 1. አባ በርሱማ ሶርያዊ (ለሶርያ መነኮሳት ኁሉ አባት) 2. አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ (ኢትዮዽያዊ) 3. "318ቱ" ቅዱሳን ሊቃውንት (ርቱዐነ ሃይማኖት ዘኒቅያ) 4. የብሔረ ብፁዐን ጻድቃን 5. አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ (ኢትዮዽያዊ) 6. ቅዱስ ዞሲማስ ጻድቅ (ዓለመ ብፁዐንን ያየ አባት)
إظهار الكل...
Repost from N/a
የእግዚአብሒር ሰላም ከእናተ ጋር ይሁን። መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በትንሣኤው ከሞት ይበልጥ ኃያል መሆኑን አረጋግጧል። ይህ በመሆኑም ሞቱና ለፍርድ ሲቀርብ የገለጠው ዝምታ በውስጡ ካለው ፍርሐት አልመሆኑን እንረዳለን። ቢናገር ኖሮ አፈቸውን በማስያዝ አድማጮቺን ማሳመን ይችል ነበር። ይሁን እንጂ የእርሱ ዓለማ ይህ አልነበረም። የእርሱ ዓለማ እኛን ነጻ ማውጣት ነበር። ስለሆንም ከመሰቀል ላይ እንዲወርድ በጠየቁት ጊዜ መውረድ ቢችልም እንኳ ምንም ዓይነት መልስ አልሰጣቸውም። የእርሱ ብቸኛ ዓለማ ስለ እኛ ሕማምን ተቀብሎ በመሞት የኃጢአትን ዋጋ በእኛ በመክፈል ለእኛ ስረየትና ድኅነት ማስገአት ነበር። የክሮስቶስ ዝምታ ድካም አለመሆኑን ትንሣኤው አረጋግጧል። የትንሣኤው ኃይል ክርስቶስን በድካም ለሚወነጅሉት ወይም ስቅለቱ የአቅም የማጣቱ ምልክት እንደ ሆነ አድርገው ለማያስቡ ሰዎች ሁሉ ብርቱ ምላሽ ነው። ትንሣኤው ዝምታ የላቁ ዓለማዎች እንዳሉት አረጋግጧል። እርሱ ዝም ያለው ራሱን ለእኛ ሊሰጠን ስለ ወደደ ነው። ቢናገር ኖሮ ለፍርድ ያቀረብት ጠላቶቹን አፍ በማስያዝ አድማጮቹን ማሳመን ይችል ነበር። ራሱን ቢከላከል ኖሮ የተከሰሰባቸውን ያለ ምንም ጥርጥር ያሸንፍ ነበር። ከዚህ ሌላ ገና የአስራሁለት ዓመት ብላቴና ሳለ ይናገራቸው የነበሩት ቃላት ኃይል እነርሱ ራሳቸው በመደነቅ መስክረውለታል። "ከሦስት ቀንም በኋላ በመምህራን መካከል ተቀምጦ ሲሰማቸውም ሲጢይቃመቸውም በመቅደስ አገኙት የሰሙትም ሁሉ በማስተዋሉና በመልሱ ተገረሙ።" ሉቃ 2:46- 47። አድማጮቹም ቢሆኑ በሥልጣን መናገሩን በአግራሞት መስክረውለታል። "....ሕዝቡ በትምህርቱ ተገረሙ እንደ ጻፎቻቸው ሳይሆን እንደ ባለስልጣን ያስተምራቸው ነበረ። " ማቴ 7:28-29። ከዝህ ከፍል የምንረዳው ጌታችን በአስራሁለት ዓመቱ በአይሁድ መምህራን መካከል ሲነጋገር እንደ ባለስልጣን ያስተምራቸው የነበረ አምላካችን ነው። በትንሣኤው ከሞቱ ይበልጥ ኃያል መሆኑን አረጋግጦልናል። በአንድ ልጅህ በርሱ ያለ ክብርና ጽንዕ ሐአንተ ይገባል ከእርሱ ጋራ ከመንፈስ ቅዱስም ጋራ ዛሬም ዘወትርም ለዘላለም ለዘለአለሙ አሜን። መልካም ጊዜ።
إظهار الكل...
††† እንኳን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጥንተ በዓለ ዕርገት እና ለጻድቁ አባ ዳንኤል ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† ዕርገተ እግዚእ ††† ††† ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዓለ ዕርገትን 2 ጊዜ ታከብራለች:: አንዱ "ጥንተ በዓል" : ሁለተኛው ደግሞ "የቀመር በዓል" ይሠኛል:: ጥንተ በዓል ማለት ጌታችን በትክክል ያረገበትን ቀን ያመለክታል:: የክብር ባለቤት መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ በኪነ ጥበቡ (በሕማሙ : በሞቱ) ዓለምን አድኖ: 40 ቀን ለሐዋርያቱ መጽሐፈ ኪዳንን: ትምሕርተ ኅቡዓትን አስተምሯቸዋል:: በ40ኛው ቀን 120ውን ቤተሰብ ይዟቸው ወደ ቢታንያ ወጣ:: በዚያም እስከ ሊቀ ዽዽስና ድረስ ሾሟቸው : ከኢየሩሳሌም እንዳይወጡም አዟቸው የመንፈስ ቅዱስን ተስፋ ጠብቁ ብሏቸዋል:: እየባረካቸው በተዋሐደው ሥጋ ወደ ሰማያዊ ዙፋኑ አርጓል:: ሰማያት: ምድር: ደመናት: ነፋሳት: መባርቅትና መላእክት: ፍጥረት በሙሉ አመስግኗል:: አይሁድ መናፍቃን ዕርገቱን ምትሐት ነው እንዳይሉ: ጌታችን ትንሳኤውን አማናዊ እንደሆነ ለማስረዳት በ40ኛው ቀን ዐረገ:: አንድም ራስ ባለበት ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ሊኖሩ ይገባልና ጌታችን ዕርገቱን በገሃድ አደረገው:: "ዐርገ እግዚእ ከመ ያለቡ ዕርገተ ጻድቃን ንጹሐን" እንዲል:: ††† ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ:: ወእግዚእነ በቃለ ቀርን:: ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ:: ††† (መዝ. 46:6) ††† ታላቁ አባ ዳንኤል ††† ††† ይህ ቅዱስ አባት ስም አጠራሩ ክቡር ነው:: በሁሉ ነገሩ የተቀደሰ የገዳማውያን መብራትም ነው:: ከተረፈ ንጹሕ ሕይወቱ ጣዕመ መንግስተ ሰማያትን አይቷልና:: አባ ዳንኤል በትውልድ ግብጻዊ ሲሆን ዓለምን ንቆ (መንኖ) ገዳም የገባው ገና በወጣትነቱ ነው:: ጊዜውም ዘመነ ጻድቃን (በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን) ነበር:: በገዳመ አስቄጥስ እና በደብረ ሲሐት ይታወቃል:: ታላቋ መካነ ቅዱሳን ገዳመ ሲሐት ዛሬም ድረስ በስሙ የምትጠራ ሲሆን ለዚህም ምክንያቱ እጅግ ለብዙ ዘመናት በውስጧ ተጋድሎ ፍሬ ስላፈራባት : ደቀ መዛሙርትን በቅድስና ስለ ወለደባት ነው:: ስለዚህም ዛሬም ድረስ "አባ ዳንኤል ዘደብረ ሲሐት" ተብሎ ሲጠራ ይኖራል:: ሌላኛው ስሙ ደግሞ "ዘገዳመ አስቄጥስ" ይሰኛል:: ገዳመ አስቄጥስ የታላቁ ቅዱስ መቃርስ ርስት ሲሆን በዓለም በስፋትም : ብዙ ቅዱሳንን በማፍራትም አንደኛ የሆነ ገዳም ነው:: በዚህ ገዳም ላይ አበ ምኔት ሆኖ የሚሾሙ አበው ሁሌም የብቃት መዓርግ ላይ የደረሱ ሲሆኑ ክብራቸው ከፓትርያርክ በላይ ነው:: አባ ዳንኤልም ከብዙ የቅድስና ዓመታት በኋላ በአስቄጥስ ገዳም አበ ምኔት ሆኖ ተሹሞ እልፍ አእላፍ መነኮሳትን በጽድቅ መንገድ መርቷል:: ቅዱሱ ከትጋቱ የተነሳ ለምግብና ለእንቅልፍ ጊዜ አልነበረውም:: ቀን ቀን መነኮሳቱን ሲናዝዝ : ድውያንን ሲፈውስ : ሥርዓተ ገዳምን ሲቆጣጠር ይውላል:: ልክ ሲመሽ ጭው ወዳለውና ስውራን ወደ ሚገኙበት በርሃ ይወጣል:: +በዚያም ሙሉውን ሌሊት የተሰወሩ አባቶችን ሲፈልግ ያድር ነበር:: በዚህም ምክንያት የብዙ ስውራንን ገድል የጻፈ ሲሆን ባረፉ ጊዜም ገንዞ በመቅበር በረከታቸውን ተሳትፏል:: ታላቅ ሙያንም ፈጽሟል:: እርሱ ገንዞ ቀብሮ : ዜናቸውን ከጻፈላቸው ሥውራን ቅዱሳንም እንደ አብነት እሥራኤላዊቷን ቅድስት ዓመተ ክርስቶስን (ለ38 ዓመት ራቁቷን በሥውር የኖረች) እና ቅድስት በጥሪቃ ንግሥትን (መንግስቷን ትታ በሥውር የኖረች ናት) መጥቀስ እንችላለን:: ከዚህ ባለፈም አባ ዳንኤል በሰው ዘንድ የተናቁትንም ማክበርን ያውቅበታል:: ለምሳሌ በሴቶች ገዳም እብድ ናት ተብላ በበር የተጣለችውን ቅድስት አናሲማን : በእስክንድርያ ከተማ ሊቀ ዻዻሳቱ ሳይቀር "እብድ ነው" ብለው የናቁትን ቅዱስ ምሕርካን: እብድ ሳይሆኑ ራሳቸውን የሠወሩ ቅዱሳን መሆናቸውን ገልጧል:: አባ ዳንኤል ሐዋርያዊም ነበር:: በጊዜው ጦማረ ልዮን የሚባል የኑፋቄ ደብዳቤ ይላክ ነበርና ለዚህ ኬልቄዶናዊ ኑፋቄ በትጋት ምላሽ ይሰጥ ነበር:: አንድ ቀንም በንጉሥ ትዕዛዝ ኑፋቄው በእርሱ ገዳም ሊነበብ ሲል ቅዱሱ ከወታደሩ ቀምቶ ስለ ቀደደው ለሞት እስኪደርስ ደብድበውታል:: ጻድቁ አባ ዳንኤል አንዴ አውሎጊስ የሚባልድሃ ድንጋይ ጠርቦ እንግዳ ሲቀበል ተመልክቶ "ጌታ ሆይ! ይህንን ደግ ሰው ለምን ድሃ አደረከው?" ሲል በፈጣሪ ሥራ ገባ:: ጌታም እንደ ወትሮው በገሃድ ተገልጦ "በነፍስህ ትዋሰዋለህ?" አለው:: "አዎ ጌታየ" ስላለው ጌታችን ለአውሎጊስ ሃብትን ሰጠው:: ግን ወዲያው የጦር አለቃና ጨካኝ ሰው ሆነ:: ጻድቁ ወሬውን ሰምቶ ሊጠይቅ ቢሔድ የአውሎጊስ ወታደሮች ደበደቡት:: ጌታችንም አባ ዳንኤልን ወደ ፍርድ ዙፋኑ አቅርቦ "ወዳጄን መልስልኝ" አለው:: እመ ብርሃን ግን ቀርባ የልጇን እግር ሳመች:: "ልጄ ሆይ ማር!" አለችው:: ጌታም "እሺ" ብሎ ጻድቁን ወደ በአቱ: አውሎጊስን ወደ ቀደመ ግብሩ መለሳቸው:: የአባ ዳንኤል ድንቁ ብዙ ነው:: ሌላው ቢቀር ሽፍታ አባ ዳንኤልን መስሎ ወደ ደናግል ገዳም ሊዘርፍ : በማታለል ገባ:: ደናግሉም ጻድቁ መስሏቸው እግሩን አጥበው ዐይነ ስውሯን ቢቀቧት ዐይኗ በርቷል:: ሽፍታውም ደንግጦ ንስሃ ገብቷል:: አባ ዳንኤል ግን ተጋድሎውን ፈጽሞ በዚህች ቀን ዐርፏል:: ††† በተረፈው ግን ከቅድስና ሕይወቱ ባሻገር:- 1.በገዳመ አስቄጥስ (ግብጽ) አበ ምኔት ሆኖ ተሹሞ ባሳየው ትጋት:: 2.በሃይማኖት ጠበቃነቱ በደረሰበት ድብደባና ስደት:: 3.ብዙ የበርሃ ቅዱሳንን በየበአታቸው እየዞረ በመቅበሩ:: 4.የብዙ ስውራን ቅዱሳንን ዜና ሕይወት በመሰብሰቡ:: 5.በየጊዜው በእግዚአብሔር ኃይል ይፈጽማቸው በነበሩ ተአምራት:: እና 6.ለድንግል እመቤታችን ማርያም በነበረው ልዩ ፍቅር ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታከብረዋለች:: ††† ቸር አምላክ ክርስቶስ ከዕርገቱና ከጻድቁ በረከት አይለየን:: ††† ግንቦት 8 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱሳን የጌታ ቤተሰብ (120ው) 2.ቅዱስ አባ ዳንኤል ጻድቅ 3.ቅዱስ ዮሐንስ ሰማዕት 4.ቅዱስ መክሲሞስ መስተጋድል 5.አቡነ ዮሐኒ ዘደብረ ዳሞ (አቡነ ተክለ ሃይማኖትንና አቡነ ኢየሱስ ሞዐን ለምንኩስና ያበቁ) ††† ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት 2.ኪሩቤል (አርባዕቱ እንስሳ) 3.አባ ብሶይ (ቢሾይ) 4.አቡነ ኪሮስ 5.አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን 6.ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት) ††† "እስከ ቢታንያም አወጣቸው:: እጆቹንም አንስቶ ባረካቸው:: ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ:: ወደ ሰማይም ዐረገ:: እነርሱም ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ:: ዘወትርም እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እየባረኩ በመቅደስ ኖሩ::" ††† (ሉቃ. 24:50-53) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
إظهار الكل...
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ           አሜን ✍"ችግር ለራሳችን እንድንጸልይ ያነቃቃናል፤ ፍቅር ደግሞ ለሌሎች ሰዎች እንድንጸልይ ያስገድደናል"                             ቀናችንን በጸሎት እንጀምር ክርስቶስ ተንሥአ እም ሙታን በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን አሰሮ ለሰይጣን አግዓዞ ለአዳም ሰላም እምይእዜሰ ኮነ ፍስሐ ወሰላም 🛎 ስንክሳር ዘወርኀ ግንቦት ፰ አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ግንቦት ስምንት በዚች ቀን አባ ዳንኤን ተጋድሎውን ፈጽሞ በዚህች ቀን አረፈ።    ❖ ይህ ቅዱስ አባት ስም አጠራሩ ክቡር ነው፤ በሁሉ ነገሩ የተቀደሰ የገዳማውያን መብራትም ነው፤ ከተረፈ ንጹሕ ሕይወቱ ጣዕመ መንግስተ ሰማያትን አይቷልና፤ አባ ዳንኤል በትውልድ ግብጻዊ ሲሆን ዓለምን ንቆ (መንኖ) ገዳም የገባው ገና በወጣትነቱ ነው፤ ጊዜውም ዘመነ ጻድቃን (በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን) ነበር:: በገዳመ አስቄጥስ እና በደብረ ሲሐት ይታወቃል:: ❖ ታላቋ መካነ ቅዱሳን ገዳመ ሲሐት ዛሬም ድረስ በስሙ የምትጠራ ሲሆን ለዚህም ምክንያቱ እጅግ ለብዙ ዘመናት በውስጧ ተጋድሎ ፍሬ ስላፈራባት ደቀ መዛሙርትን በቅድስና ስለ ወለደባት ነው:: ❖ ስለዚህም ዛሬም ድረስ "አባ ዳንኤል ዘደብረ ሲሐት" ተብሎ ሲጠራ ይኖራል፤ ሌላኛው ስሙ ደግሞ "ዘገዳመ አስቄጥስ" ይሰኛል፤ ገዳመ አስቄጥስ የታላቁ ቅዱስ መቃርስ ርስት ሲሆን በዓለም በስፋትም ብዙ ቅዱሳንን በማፍራትም አንደኛ የሆነ ገዳም ነው:: ❖ በዚህ ገዳም ላይ አበ ምኔት ሆኖ የሚሾሙ አበው ሁሌም የብቃት መዓርግ ላይ የደረሱ ሲሆኑ ክብራቸው ከፓትርያርክ በላይ ነው፤ አባ ዳንኤልም ከብዙ የቅድስና ዓመታት በኋላ በአስቄጥስ ገዳም አበ ምኔት ሆኖ ተሹሞ እልፍ አእላፍ መነኮሳትን በጽድቅ መንገድ መርቷል:: ❖ ቅዱሱ ከትጋቱ የተነሳ ለምግብና ለእንቅልፍ ጊዜ አልነበረውም፤ ቀን ቀን መነኮሳቱን ሲናዝዝ ድውያንን ሲፈውስ ሥርዓተ ገዳምን ሲቆጣጠር ይውላል፤ ልክ ሲመሽ ጭው ወዳለውና ስውራን ወደ ሚገኙበት በርሃ ይወጣል:: ❖ በዚያም ሙሉውን ሌሊት የተሰወሩ አባቶችን ሲፈልግ ያድር ነበር፤ በዚህም ምክንያት የብዙ ስውራንን ገድል የጻፈ ሲሆን ባረፉ ጊዜም ገንዞ በመቅበር በረከታቸውን ተሳትፏል፤ ታላቅ ሙያንም ፈጽሟል፤ እርሱ ገንዞ ቀብሮ ዜናቸውን ከጻፈላቸው ሥውራን ቅዱሳንም እንደ አብነት እሥራኤላዊቷን ቅድስት ዓመተ ክርስቶስን (ለ38 ዓመት ራቁቷን በሥውር የኖረች) እና ቅድስት በጥሪቃ ንግሥትን (መንግስቷን ትታ በሥውር የኖረች ናት) መጥቀስ እንችላለን:: ❖ ከዚህ ባለፈም አባ ዳንኤል በሰው ዘንድ የተናቁትንም ማክበርን ያውቅበታል፤ ለምሳሌ በሴቶች ገዳም እብድ ናት ተብላ በበር የተጣለችውን ቅድስት አናሲማን በእስክንድርያ ከተማ ሊቀ ዻዻሳቱ ሳይቀር "እብድ ነው" ብለው የናቁትን ቅዱስ ምሕርካን እብድ ሳይሆኑ ራሳቸውን የሠወሩ ቅዱሳን መሆናቸውን ገልጧል:: ❖ አባ ዳንኤል ሐዋርያዊም ነበር በጊዜው ጦማረ ልዮን የሚባል የኑፋቄ ደብዳቤ ይላክ ነበርና ለዚህ ኬልቄዶናዊ ኑፋቄ በትጋት ምላሽ ይሰጥ ነበር፤ አንድ ቀንም በንጉሥ ትዕዛዝ ኑፋቄው በእርሱ ገዳም ሊነበብ ሲል ቅዱሱ ከወታደሩ ቀምቶ ስለ ቀደደው ለሞት እስኪደርስ ደብድበውታል:: ❖ ጻድቁ አባ ዳንኤል አንዴ አውሎጊስ የሚባልድሃ ድንጋይ ጠርቦ እንግዳ ሲቀበል ተመልክቶ "ጌታ ሆይ! ይህንን ደግ ሰው ለምን ድሃ አደረከው?" ሲል በፈጣሪ ሥራ ገባ፤ ጌታም እንደ ወትሮው በገሃድ ተገልጦ "በነፍስህ ትዋሰዋለህ?" አለው "አዎ ጌታየ" ስላለው ጌታችን ለአውሎጊስ ሃብትን ሰጠው:: ግን ወዲያው የጦር አለቃና ጨካኝ ሰው ሆነ:: ❖ ጻድቁ ወሬውን ሰምቶ ሊጠይቅ ቢሔድ የአውሎጊስ ወታደሮች ደበደቡት፤ ጌታችንም አባ ዳንኤልን ወደ ፍርድ ዙፋኑ አቅርቦ "ወዳጄን መልስልኝ" አለው፤ እመ ብርሃን ግን ቀርባ የልጇን እግር ሳመች "ልጄ ሆይ ማር!" አለችው፤ ጌታም "እሺ" ብሎ ጻድቁን ወደ በአቱ አውሎጊስን ወደ ቀደመ ግብሩ መለሳቸው የአባ ዳንኤል ድንቁ ብዙ ነው፤ ሌላው ቢቀር ሽፍታ አባ ዳንኤልን መስሎ ወደ ደናግል ገዳም ሊዘርፍ በማታለል ገባ ደናግሉም ጻድቁ መስሏቸው እግሩን አጥበው ዐይነ ስውሯን ቢቀቧት ዐይኗ በርቷል፤ ሽፍታውም ደንግጦ ንስሃ ገብቷል:: አባ ዳንኤል ግን ተጋድሎውን ፈጽሞ በዚህች ቀን ዐርፏል:: 📌 በተረፈው ግን ከቅድስና ሕይወቱ ባሻገር 1.በገዳመ አስቄጥስ (ግብጽ) አበ ምኔት ሆኖ ተሹሞ ባሳየው ትጋት:: 2.በሃይማኖት ጠበቃነቱ በደረሰበት ድብደባና ስደት:: 3.ብዙ የበርሃ ቅዱሳንን በየበአታቸው እየዞረ በመቅበሩ:: 4.የብዙ ስውራን ቅዱሳንን ዜና ሕይወት በመሰብሰቡ:: 5.በየጊዜው በእግዚአብሔር ኃይል ይፈጽማቸው በነበሩ ተአምራት እና 6.ለድንግል እመቤታችን ማርያም በነበረው ልዩ ፍቅር ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታከብረዋለች:: ቸር አምላክ ክርስቶስ ከዕርገቱና ከጻድቁ በረከት በረከት አይለየን፤ በጸሎቱም ይማረን
📌 ግንቦት 8 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱሳን የጌታ ቤተሰብ (120ው) 2. ቅዱስ አባ ዳንኤል ጻድቅ 3.ቅዱስ ዮሐንስ ሰማዕት 4.ቅዱስ መክሲሞስ መስተጋድል 5.አቡነ ዮሐኒ ዘደብረ ዳሞ (አቡነ ተክለ ሃይማኖትንና አቡነ ኢየሱስ ሞዐን ለምንኩስና ያበቁ) 📌 ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት 2.ኪሩቤል (አርባዕቱ እንስሳ) 3.አባ ብሶይ (ቢሾይ) 4.አቡነ ኪሮስ 5.አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን 6.ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት)
إظهار الكل...
ቅዱስ ጴጥሮስ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” የሚለውን የትንሣኤውን ጌታ ድምጽ ከሰማ ፣ የተጠራጠረው ቶማስ እጁን በጎኖቹ አግብቶ “ጌታዬ አምላኬ” ብሎ ሲያምን ከተመለከተ በኋላ “ዓሣ ላጠምድ እሄዳለሁ” ብሎ ሲናገር እናገኘዋለን።(ዮሐ 21፥3) ክርስቶስ ተላልፎ በተሰጠበት በሐሙስ ምሽት ከእሳት ዳር ተቀምጦ ያደረገውን ሊረሳውና ራሱን ይቅር ሊል ስላልቻለ፣ ጌታው ቀድሞ የሰጠውን የወንጌል መረብ ተወና የዓሣውን መረብ ጨብጦ ወደ ገሊላ ባሕር ሮጠ።(ማቴ 4፥19) በኃጢአት ምክንያት የተሰማው ኃፍረትና መሸማቀቅ ሐዋርያነቱን ትቶ በድሮ ማንነቱ ውስጥ ራሱን እንዲደብቅ አደረገው። የካደን ማን ለምስክርነት ይፈልገዋል በሚል ዓይነት ስሜት ለወንድሞቹ  “ዓሣ ላጠምድ እሄዳለሁ” አላቸው። ደስ የሚለው ነገር ግን ይህን አስቀድሞ የሚያውቅ ይቅር ባይ አምላኩ ጴጥሮስን “በገሊላ ቀድሞት ነበር”። በበደሉ ተሸማቆ የተወውን ሐዋርያነት ሥልጣን በፍቅሩ መማለጃነት መልሶ ሊሰጠው፣ አይገባኝም ብሎ ያስቀመጠውን የወንጌል መረብ ዳግመኛ ሊያሲዘው በገሊላ ባሕር ዳር ቀደመው። እኛም አንድ ኃጢአት ይኖረናል። መርሳት ያልቻልነው፣ ንስሐ እንኳን ብንገባበት ራሳችንን ይቅር ለማለት የተቸገርንበት፣ “ከዚህ በኋላማ...” እያሰኘ የድሮ መረብ አስይዞ ወደ ገሊላ የሚመልስ አንድ በደል ይኖረናል። ነገር ግን ጌታ ለቅዱስ ጴጥሮስ እንዳደረገው ለእኛም እንዲሁ ያደርጋል። ከባሕሩ ዳር ይጠብቀናል፣ “ትወደኛለህ” ብሎ ይጠይቀናል፣ ከዚያ በማይለወጥ ፍቅሩ ወልውሎ ሰንግሎ አፍረን ወደ ሸሸነው መንፈሳዊነት ይመልሰናል። ጌታችን በገሊላ ይቀድመናል!
إظهار الكل...
ስንክሳር ዘወርኀ ግንቦት ፯ May 7, 2021 by @YeBiruk ዲያቆን ቡሩክ ይርጋ ዘውብ ✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝ ✍"ችግር ለራሳችን እንድንጸልይ ያነቃቃናል፤ ፍቅር ደግሞ ለሌሎች ሰዎች እንድንጸልይ ያስገድደናል"                             ቀናችንን በጸሎት እንጀምር ክርስቶስ ተንሥአ እም ሙታን በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን አሰሮ ለሰይጣን አግዓዞ ለአዳም ሰላም እምይእዜሰ ኮነ ፍስሐ ወሰላም 🛎   ስንክሳር ዘወርኀ ግንቦት ፯        አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ግንቦት ሰባት በዚች ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሃያኛ የሆነ የከበረ አባት የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ሐዋርያዊ አትናቴዎስ አረፈ። ❖ ይህም ቅዱስ ሐናፊ ከሚባል የእስላም ነገድና ከአረማውያን ተወላጅ ነው ይባላል፤ እርሱም ከመምህር ከሚማሩ ሕፃናት ጋራ እያለ እርስ በርሳቸው በመጫወት ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን እየሠሩ ከእነርሱ ውስጥ ዲያቆናትን ኤጲስቆጶሳትንም ሲያደርጉ እሊያን የክርስቲያንን ልጆች አይቶ ጨዋታቸው ደስ ስለአለው ከእሳቸው ጋራ በጨዋታቸው አንድ ይሆን ዘንድ የክርስቲያንን ልጆች ለመናቸው፤ እነርሱም አንተ አረማዊ ነህና ከእኛ ጋራ አትደመርም ብለው ከለከሉት እርሱም ክርስቲያን እሆናለሁ አላቸው እነርሱም ደስ ተሰኙበት። ❖ ያን ጊዜም ወስደው በሊቀ ጳጳሳት አምሳል አደረጉት ከበታቹም ወንበር አድርገው ይሰግዱለት ጀመር፤ በዚያን ጊዜም ሊቀ ጳጳሳት አባ እለእስክንድሮስ በዚያ አለፈ የክርስቲያን ልጆች ሲጫወቱ በአያቸው ጊዜ አብረውት ላሉ ይህ ሕፃን ከፍ ከፍ ያለችና የከበረች ሹመትን ይሾም ዘንድ አለው አላቸው። ❖ አባቱም በሞተ ጊዜ ወደ አባ እለእስክንድሮስ መጣ የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቀው፤ ከዚህም በኋላ የአባቱን ገንዘብ ሁሉ ወስዶ ለድኆችና ለጦም አዳሪዎች ሰጥቶ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርትና ሕግ ሥርዓትንም ከአባ እለእስክንድሮስ ዘንድ እየተማረ ኖረ እርሱም ተወዳጅ ልጅ አደረገው። ❖ ከዚህም በኋላ ዲቁና ሾመው የመንፈስ ቅዱስንም ጸጋ የተመላ ሆነ፤ የከበረ አባት እለእስክንድሮስም በአረፈ ጊዜ ይህን አባት አትናቴዎስን በእስክንድርያ አገር ላይ ሊቀ ጳጳሳት አድርገው ሾሙት። ❖ ከዚህ አስቀድሞ ግን የሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት ኤጲስቆጶሳት ስብሰባ በተደረገ ጊዜ አባ እለእስክንድሮስ ከዚህ ዓለም ሳይለይ ይህም አትናቴዎስ ከእሳቸው ጋራ ተሰብስቧል፤ የጉባኤውም ጸሐፊ አድርገውት በኒቅያ ከተማ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን ከእሳቸው ጋራ ሠራ። ❖ ጻድቁ ቈስጠንጢኖስ በሞተ ጊዜ አርዮሳዊ ልጁ ሁለተኛው ቈስጠንጢኖስ ነገሠ አርዮሳውያንም በዙ ይህንንም አባት አርዮሳዊው ንጉሥ ከመንበረ ሢመቱ አሳደደው በእርሱም ፈንታ ጊዮርጊስ የተባለ ከሀዲ ሰው ሾመ። ❖ ከዚህም በኋላ ብዙ ጊዜ ሲአሳድዱትና ሲመልሱት ኖረ በስደቱም በአንዲት ምዕራባዊት አገር በአለ ጊዜ በዚያ የጣዖት ቤት አለች፤ በዚያችም የጣዖት ቤት ብዙ ሕዝቦች በውስጧ ይሰበሰባሉ፤ ለዚያችም የጣዖት ቤት በውስጧ የሚሠሩ ብዙ የሰይጣን ሥራዎች አሏት፤ እርሱም የክብር ባለቤት የሆነ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመነው ያቺንም የጣዖት ቤት አፍርሶ የአገር ሰዎችን ሁሉ እግዚአብሔርን ወደማወቅ መለሳቸው። ❖ ይህንንም አባት አምስት ጊዜ አሳደዱት የሹመቱም ዘመን አርባ ሰባት ሲሆን ዐሥራ አምስቱን ዓመት በስደትና በእሥራት ነው ያሳለፈው፤ ይህንንም አባት ብዙ መከራና ድካም መሰደድም ስለደረሰበት ሐዋርያዊ ተብሎ ተጠራ፤ በሚሞትበትም ጊዜ በእግዚአብሔር ዘንድ ባለሟልነትን ባገኝ ይህን የጣዖት ቤት ያፈርስ ዘንድ በፊቱ እኔ እየሰገድኩ እለምነዋለሁ፤ ይህም አባት ከአረፈ በኋላ ንጉሥ ልኮ ያንን የጣዖት ቤት አስፈረሰው። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት ጸሎትና ምልጃ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። 🛎 📌 🛎  ዳግመኛም በዚህች ዕለት የባሕታዊያን አለቃ ግብፃዊው አባ ሲኖዳ ልደታቸው ነው፤ እኚኽም ታላቅ ጻድቅ ሀገራቸው ግብፅ ነው፤ የባሕታውያን አለቃ የሆኑ መስተጋድል አቡነ ሲኖዳ ከላዕላይ ግብፅ ከአክሚም አውራጃ የተገኙ ታላቅ አባት ናቸው፡፡ ❖ ገና ሳይወለዱ እናታቸው አንድ ቀን ውኃ ልትቀዳ ስትሄድ አንድ የበቁና ሴት አናግረው የማያውቁ ጻድቅ አባት ‹‹የማኅፀንሽ ፍሬ የተባረከ ነው›› ብለው ለደቀ መዛሙርቶቻቸውም የልጁን ታላቅ ክብር ነግረዋቸዋል፡፡ ❖ ይህ ቅዱስ አባትም ስለ አቡነ ሲኖዳ መወለድ ትንቢት በተናገሩት መሠረት በዛሬዋ ዕለት ግንቦት 7 ቀን ተወለዱ፡፡ ❖ የበግ እረኛም ሆነው ሳለ ስንቃቸውን ለነዳያን እየሰጡ እሳቸው ግን እስከ ማታ ድረስ ይጾሙ ነበር፤ ሌሊት ደግሞ ባሕር ውስጥ እየገቡ ሲጸልዩ ያድሩ ነበር፤ በጉድጓድ ውስጥ ሆነው ሲጸልዩ ዓሥር ጣቶቻቸው እንደፋና ሲያበሩ አንድ ጻድቅ አባት አይተዋቸው የልጁን ክብር ለወላጆቻቸው ቢነግሯቸው እነርሱም ‹‹እንዲህ ከሆነማ ለእግዚአብሔር ይሁን›› ብለው ወስደው ለመምህር ሲሰጧቸው ከሰማይ ‹‹እነሆ የባሕታውያን ራስ ይባላል›› የሚል ድምፅ ከሰማይ ተሰምቷል፡፡ ❖ በገዳምም በታላቅ ተጋድሎ ሲኖሩ መልአክ ለመምህሩ የኤልያስን አስኬማ የዮሐንስን ቅናት እንዲያለብሳቸው ነግሮት አመንኩሰዋቸዋል፡፡ ❖ አቡነ ሲኖዳ ንስጥሮስን ለማውገዝ በ431 ዓ.ም በቁስጥንጥንያ በተካሄደው ጉባኤ ላይ ቅዱስ ቄርሎስን ተከትለው በጉባኤው ተገኝተዋል፡፡ ❖ ንስጥሮስንም አውግዘው ሃይማኖትን አጽንተው ሲመለሱ መርከበኞች ‹‹ሊቀ ጳጳሳቱ በሚሳፈሩበት መርከብ አትሳፈርም›› ብለው ቢከለክሏቸው አቡነ ሲኖዳ ሊቀ ጳጳሳቱን እጅ ከነሱ በኋላ ብሩህ ደመና ጠቅሰው በደመና ተጭነው ሲሄዱ ሊቀ ጳጳሳቱም መርከበኞቹም አይተዋቸው መርከበኞቹ ‹‹ጻድቅ ሰው አስቀየምን›› ብለው አዝነው ንስሓ ገብተዋል፡፡ ❖ አንድ ቀን ሌሊት በጸሎት ላይ ሳሉ ጌታችን ተገልጦላቸው አብሯቸው ተቀመጠ፤ አባታችንም ጌታችንን ‹‹ጌታዬ ፈጣሪዬ ሆይ ልዩ ሦስትነትህንና ጌትነትህን ስለሚነቅፉ ከሃድያን ወደ ጉባዔው እሄድ ዘንድ እንዲጠሩኝ ሊቀ ጳጳሳቱ ወደ እኔ ልኳልና እንደቀድሞው ታጸናኛለህን›› ብለው ጠየቁት፡፡ ❖ ጌታችንም ‹‹ወዳጄ ሲኖዳ ሆይ 120 ዓመት ኖረሃል ገና ሌላ ዕድሜ ትሻለህን በ9 ዓመትህ አስኬማን ለብሰህ እስካሁን አገልግለኸኛልና ይበቃሃል›› አላቸው፤ትልቅ ቃልኪዳንም ከሰጣቸው በኋላ ሐምሌ 7 ቀን ነፍሳቸውን ከሥጋቸው ለይቶ በክብር አሳርጓታል፡፡
📌 ግንቦት 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ 2.የባሕታውያን አለቃ ታላቁ አባ ሲኖዳ (ጽንሰቱ) 3.ቅዱስ ዮሐንስ ጻድቅ (ሃብቱን: ንብረቱን: ልብሱን ሳይቀር መጽውቶ ራቁቱን የተገኘ ደግ ሰው ነው) 4.አባ ሐርስዮስ ገዳማዊ 1. ሥሉስ ቅዱስ (አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ)  2. አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ 3. አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን አለቃ) 4. አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት 5. አባ ባውላ ገዳማዊ 6. ቅዱስ አግናጥዮስ (ለአንበሳ የተሰጠ)
إظهار الكل...
Repost from N/a
ከእግዚአብሔር አብ ከመደኃኒታችንም ኸጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ምህረት ሰላምም ይሁን። በጌታችን በመደኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ የቀረበልን ስጦታ እና በረከት፦ ሁለተኛው፦ዘላለማዊ ሕይወትን መናፈቅ ነው። ሐዋርያው ቅ.ጳውሎስ ይህን አስመልክቶ ሲናገር"....ልሄድ ከክርስቶስም ጋር ልኖር እናፈቃለሁ ከሁሉም የሚበልጥ ነውና.... " ፊልጲ1:23። "...ከሥጋ ተለይተን በስደት መኖር በጌታ ማደር ደስ ይለናል። "2ኛ ቆሮ 5:8።ይህ ሐዋርያ ከሙታን መካከል ተለይቶ ከተነሣው ወደ ሰማይ ካረገውና በአባቱ ቀኝ ከተቀመጠው ከርስቶስ ጋር ለመሆን ይናፍቅ ነበር። ይህ ክርስቶስ"...እኔም ከምድር ከፍ ከፍ ያልሁ እንደ ሆነ ሁሉን ወደ እኔ እስባለሁ። " ዮሐ 12:32 በማለት የተናገረው ክርስቶስ ነው። ይህ አባታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኮ እንዲህ ብሎ ተናግሯል ፦"...ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሔዳለሁና ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንዳትሆኑ ሁለተኛ አመጣለሁ ወደ እኔም አወስዳችኋለሁ። ዮሐ 14 :2-3። የዘላለም ሕይወት ፍቅር በምድር ላይ ካለው ሕይወት የሚለቅ ነገር እንዲናፍቁ ቅዱሳን አባቶቻችን እናእናቶቻችንን አድርጓቸዋል። ይህ ናፍቆት በምድር ላይ ካለው ምኞትና ፍላጎት የሚበልጥ ኃይል ያለው ከመሆኑም በተጨማሪ ከማንኛውም ፍሬ ነገርና መሠረታዊ ጉዳይ ይልቅ የተከበረ ነው። ቅዱስን አባቶች እና እናቶች ይህችን ምድር የሚመለከቷት እንደ ኋላ ቀርና ባዕድ ሐገር አድረገው ነው። ራሳቸውን የሚቆጥሩትም እንደ እንግዶችና እንደ መጻተኞች ነው። "እነዚህ ሁሉ አምነው ሞቱ የተሰጣቸውን የተሰፋ ቃል አላገኙምና ዳሩ ግን ከሩቅ ሆነው አይቱና ተሳለሙት በመድሪቱም እንግዶችና መጻተኞች እንደሆኑ ታመኑ" ዕብ 11 :13 እንደተባለ። እነርሱ የሚናፍቁት ሰማያዊዋን ማደርያ ነው። እነርሱ የሚናፍቁት መንፈሳዊውንና ዘላለማዊውን ሕይወት ለመምራት ነው። ከዚህ በተጨማሪ ቅዱሳን የሚናፍቁት ሐዘን ትካዜ ፣ማቃሰት፣ኃጢአት፣ጥላቻና ዘረኝነት፣ ጠብ የሌሉባትን ሌላ ዓለም ነው። ክፋ ነገር የሌለበት ምልካም ነገሮች ብቻ የሚገለጡበት የፍቅር የደስታ የሰላምና የንጽሕና ዓለም ይመጣል። ስለዚህ በትንሣኤው የተገኘውን በረከት ዘላለማዊ ሕይወትን በመናፈቅ የትንሣኤውን በኣል እየተረዳን እናሳልፍ። መልካም ጌዜ ይሁንላችሁ።
إظهار الكل...
✍"ችግር ለራሳችን እንድንጸልይ ያነቃቃናል፤ ፍቅር ደግሞ ለሌሎች ሰዎች እንድንጸልይ ያስገድደናል"          📚ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ                    ቀናችንን በጸሎት እንጀምር ክርስቶስ ተንሥአ እም ሙታን በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን አሰሮ ለሰይጣን አግዐዞ ለአዳም ሰላም እምይእዜሰ ኮነ ፍስሐ ወሰላም   🛎   ስንክሳር ዘወርኀ ግንቦት ፮       አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ግንቦት ስድስት በዚች ቀን ከግብጽ ደቡብ ዳፍራ ከሚባል አገር የከበረ አባ ይስሐቅ ምስክር ሁኖ አረፈ።     ❖ ለዚህም ቅዱስ በሌሊት ራእይ የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጾለት የሰማዕትነትን አክሊል ትቀበል ዘንድ ጣዋ ወደሚባል አገር ሒድ አለው፤ ከዚያም በነጋ ጊዜ ከመሔዱ በፊት አባትና እናቱን ሊሰናበታቸው ተነሣ፤ ሁለተኛም የእግዚአብሔር መልአክ መጥቶ ከአገሩ እስከ አወጣውና ሀገረ ጣዋ እስካደረሰው ድረስ እነርሱ በላዩ እያለቀሱ አልለቀቁትም፤ በደረሰም ጊዜ መኰንኑን በዚያ ከውሽባ ቤት አገኘው ከዚያም በወጣ ጊዜ በክብር ባለቤት በጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ የማምን እኔ ክርስቲያን ነኝ ብሎ በመኰንኑ ፊት በግልጽ ጮኸ። ❖ ከኒቅዩስ ሀገርም እስኪመለስ ቅዱሱን ወስዶ እንዲጠብቀው ከወታደሮች አንዱን አዘዘው ከዚያ ወታደርም ጋራ ቅዱስ ይስሐቅ አልፎ ሲሔድ በመንገድ ዳር የተቀመጠ አንድ ዕውር የእግዚአብሔር ቅዱስ ሆይ ይቅር በለኝ ዐይኖቼንም አድንልኝ ብሎ ለመነው። ❖ አባ ይስሐቅም የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ስለዚያ ዕውር ለመነው ያን ጊዜም ዐይኖቹ ተገለጡ፤ ይህንንም ድንቅ ተአምር ወታደሩ አይቶ የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ የክርስቲያን ወገን ሆነ፤ መኰንኑም በተመለሰ ጊዜ ያ ወታደር በመኰንኑ ፊት የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ በመታመን ሰማዕት ሁኖ አክሊል ተቀበለ። ❖ ከዚህም በኋላ መኰንኑ ቅዱስ ይስሐቅን ጽኑ ሥቃይን አሠቃይቶ ወደ ሀገረ ብህንሳ ሰደደው በዚያም አሠቃዩት፤ በመርከብም ሲወስዱት የጽዋ ወኃን ለመናቸው ከቀዛፊዎችም አንዱ አንድ ዐይኑ የታወረ ውኃን በጽዋ ሰጠው የከበረ ይስሐቅም ያን ውኃ በላዩ ረጨ ዐይኑም ድና እንደ ሌላዪቱ ሆነች። ❖ ጽኑ ሥቃይን የሚአሠቃዩት የብህንሳ ሀገር ሰዎችም ይህን ድንቅ ሥራ በአዩ ጊዜ ወደ መኰንኑ ወሰዱትና ብትገድለውም ብትተወውም አንተ ታውቃለህ አሉት፤ መኰንኑ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ ወዲያውኑ አዘዘ የከበረች ራሱንም ቆረጡት የምስክርነት አክሊልንም ተቀበለ። ❖ በዚያም ምእመናን ሰዎች ነበሩ የአባ ይስሐቅንም ሥጋ በሠረገላ ጭነው በበሮች እያሳቡ ዳፍራ ወደተባለ አገሩ አደረሱት ያሻግሩትም ዘንድ መርከብ ባላገኙ ጊዜ ተሸክመው አሻግረው ወደ ቤቱ አደረሱት፤ ቤቱንም አፍርሰው በስሙ ቤተ ክርስቲያን አድርገው ሠሩዋት ሥጋውንም በውስጥዋ አኖሩ ከእርሱም የሚያስደንቁ ብዙዎች ተአምራት ተገለጡ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ እውነተኛ ምስክር ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። 🛎  በዚችም ቀን የእስክንድርያ ቄስ የከበረ አባት አባ መቃርስ አረፈ፤ ይህም ቅዱስ በአባቱ በሚቀድመው በታላቁ በክቡር አባ መቃርስ ዘመን ለአስቄጥስ ገዳም አባት ሁኖ ብዙ ትሩፋትን ሠራ። 🛎 በዚችም ቀን ቅድስት ዲላጊ ከአራት ልጆቿ ጋራ ምስክር ሆና አረፈች እነርሱም ሱርስ ኀርማን ያአፋ ናቸው፤ ይችም ቅድስት በክብር ባለቤት ክርስቶስ ሃይማኖት የጸናች ናት። ❖ መኰንኑ አርያኖስም ሀገረ አስና በደረሰ ጊዜ ልጆቿን እየነዳች ተቀበለችው በፊቱም ቁማ አርያኖስ ሆይ ሰማይንና ምድርን በውስጣቸው ያለውን በፈጠረ በክብር ባለቤት ኢየሱስ ክርስቶስ የማምን ክርስቲያን ነኝ አለችው። ልጆቿም እንደርሷ እኛ ክርስቲያን ነን እያሉ በግልጽ ጮኹ። መኰንኑም ሰምቶ ቁጣን ተመላ ራሳቸውንም በሰይፍ ቆረጠ ምስክርነታቸውንም ፈጽመው ነፍሶቻቸውን ወደ ክብር ባለቤት ኢየሱስ ክርስቶስ መላእክት ወሰዱ። በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። 🛎 በዚችም ዕለት ደግሞ ንጽሕናን ቅድስናን ድንግልናን ገንዘብ ያደረገች ተሐራሚት ሰሎሜ አረፈች፤ ይችም ቅድስት ወረብ ከሚባል አገር ናት ወላጆቿም እግዚአብሔርን የሚፈሩ ናቸው በበጎ አስተዳደግም አሳደጉዋት፤ በአደገችም ጊዜ እርሷ ሳትፈቅድ አንድ መኰንን አጭቶ በሠርግ አገባት። ያን ጊዜም አምላካዊ ኃይል ከልክሎት ወደርሷ መቅረብ አልቻለም አባለ ዘሩ ተቀሥፎአልና። ❖ በእንደዚህም እያለች ራሷን ሠውራ በሌሊት ሔደች በእግዚአብሔር ኃይል አመለጠች፤ ቅዱሳን በአሉበት ሁሉ በመዞር በጾም በጸሎት ተወስና ዕውነተኛ መንገድን ጌታ ይመራት ዘንድ በቀንና በሌሊት ስትማልድ ኖረች። ❖ ጌታችንም ልመናዋን ሰምቶ ወደ ደብረ ሊባኖስ ገዳም አደረሳት የመላእክት የሆነ አልባሰ ምንኲስናን በአባ ዮሐንስ ከማ እጅ ለብሳ የሰውን ልብ የሚያስደነግጥ ጽኑ ገድልን ተጋደለች። ❖ በጾም በጸሎት በተመሰገነ ገድል ሁሉ የፍጹማን አባቶችን ጐዳና ተጓዘች፤ በመጽሐፈ ገድሏ እንደ ተጻፈ ብዙዎች ድንቆች ተአምራትንም እስከ ማድረግ ደርሳ ከዚህ በኋላ በሰላም አረፈች። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቷ ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                         🛎 በዚችም ዕለት ገድሉን በሰይፍ የፈጸመ የከበረ አባት አባ ደናስዮስ አረፈ። እግዚአብሔርም በጸሎቱ ይማረን ለዘላለሙ አሜን።                     
📌 ግንቦት 6 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ አባ መቃርስ ገዳማዊ 2.እናታችን ቅድስት ሰሎሜ ኢትዮዽያዊት 3.አባ ይስሐቅ ጻድቅ 4.ቅድስት ዲላጊና 4 ሴት ልጆቿ (ሰማዕታት) 5.ቅዱስ ዳናስዮስ ሰማዕት 6.ቅዱስ በንደላዖስ ሰማዕት (የታላቁ ኤስድሮስ አባት) 7.አባ አሞን ጻድቅ (ዽዽስናን አልፈልግም ብሎ የሸሸ አባት) 📌 ወርኀዊ በዓላት 1.ቅድስት ደብረ ቁስቁዋም 2.አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን 3.አባታችን ኖኅና እናታችን ሐይከል 4.ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ 5.ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ 6.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ 7.ቅድስት ሰሎሜ 8.አባ አርከ ሥሉስ 9.አባ ጽጌ ድንግል 10.ቅድስት አርሴማ ድንግል
إظهار الكل...
«ወደ እግዚአብሔር የምንጸልየው፥ መረጃ ወይም መመሪያ ልንሰጠው ሳይሆን፥ ወደ እርሱ እንድንቀርብና ከእርሱ ጋር ኅብረት ያለን እንድንሆን ነው።» ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
إظهار الكل...