ar
Feedback
መንፈሳዊ ግጥም ብቻ

መንፈሳዊ ግጥም ብቻ

الذهاب إلى القناة على Telegram

በዚህ ቻናል ላይ በየቀኑ ኦርቶዶክሳዊ ግጥሞችን ያገኛሉ ለአስተያየትና ግጥም እንዲፖሰትላችሁ የምትፈልጉ ለመላክ @Solasc12 @Solasc13 @Mgetem_group ኦርቶዶክሳዊ ጥቅሶች ብቻ @Ortho_quotes

إظهار المزيد

📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام መንፈሳዊ ግጥም ብቻ

تُعد قناة መንፈሳዊ ግጥም ብቻ (@mgetem) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 27 411 مشتركاً، محتلاً المرتبة 2 663 في فئة الدين والقيم الروحية والمرتبة 1 235 في منطقة Ethiopia.

📊 مؤشرات الجمهور والحراك

منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 27 411 مشتركاً.

بحسب آخر البيانات بتاريخ 02 أغسطس, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار 107، وفي آخر 24 ساعة بمقدار 18، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.

  • حالة التحقق: غير موثّقة
  • معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 11.35‎%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 5.89‎% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
  • وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 3 110 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 1 614 مشاهدة.
  • التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 26.

📝 الوصف وسياسة المحتوى

يصف المؤلف القناة بأنها مساحة للتعبير عن الآراء الذاتية:
በዚህ ቻናል ላይ በየቀኑ ኦርቶዶክሳዊ ግጥሞችን ያገኛሉ ለአስተያየትና ግጥም እንዲፖሰትላችሁ የምትፈልጉ ለመላክ @Solasc12 @Solasc13 @Mgetem_group ኦርቶዶክሳዊ ጥቅሶች ብቻ @Ortho_quotes

بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 03 أغسطس, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة الدين والقيم الروحية.

27 411
المشتركون
+1824 ساعات
+497 أيام
+10730 أيام
أرشيف المشاركات
ለተልእኮ ምሥጢር የሚፋጠኑ እግሮች ተሳሰሩ። ቀድሰው የሚያቆርቡ እጆች ተያዙ! ተንሥኡ ጸልዩ የሚል አንደበት ለዘለዓለም ከንግግር ሳይሰናበት፥ በምንችለው እንድረስለት ፣ ለምንችለው እናድርስለት፥ ዲያቆ
+4
ለተልእኮ ምሥጢር የሚፋጠኑ እግሮች ተሳሰሩ። ቀድሰው የሚያቆርቡ እጆች ተያዙ! ተንሥኡ ጸልዩ የሚል አንደበት ለዘለዓለም ከንግግር ሳይሰናበት፥ በምንችለው እንድረስለት ፣ ለምንችለው እናድርስለት፥ ዲያቆን በግሪክ አገልጋይ ማለት ነው። አገልጋይን ማዳን ደግሞ አገልግሎትን ማዳን ነው። ሁለቱም ኩላሊቶቹን በንቅለ ተከላ መተካት ሕይወቱን ማቆያ ብቸኛ አማራጭ ለሆነው የአሰላ ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይና ብርቱ የሥራ ወጣት ዲ/ን ዘካርያስ ሸዋረጋ ከረቡዕ ግንቦት 5 እስከ ዓርብ ግንቦት ሰባት አንጋፋና ተተኪ መዘምራንና መዘምራት የሚሳተፉበት የዝማሬ ምሽትና የገቢ ማሰባሰቢያ መርኃ ግብር ተዘጋጅቷል። እርሶም በዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በtiktok live በመሳተፍ የበኩልዎን ሰብአዊና ክርስቲያናዊ ድርሻ ይወጡ! እስከዚያው ድጋፍ ለማድረግ ካሰቡ CBE: 1000375284603 | Zekarias Shewarega Telebirr: 0913071985 | Zekarias Shewarega Awash: 013201754987100 | Zekarias Shewarega BOA: 114747726 | Zekarias Shewarega Dashen: 5532308128011 | Zekarias Shewarega #Please_Share_This

ጠላት ለምን ከፋው @Mgetem እኔው ጎንበስ ብዬ እኔው ቀና ላልኩት እኔው አመስግኜ እኔው ለሰገድኩት ጠላት ምን ተነካ የሚያረው በቅናት እመቤቴ ብዬ እኔው ለወደድኳት ያንድዬ እናት ብዬ እኔው ላወደስኳት ብወድቅ ብነሳ እኔው ካልደከመኝ ሳወድሳት ባድር እኔን ካልሰለቼኝ ስማፀናት ብውል እኔው ካልታከተኝ ጠላት ምን አገባው አትስገድ የሚለኝ ፃድቃንን አይቼ እኔ ብማፀናት ገብርኤልን አይቼ እኔ ባወድሳት ሰማዕታትን አይቼ እኔ ብሞትላት አምላክን አይቼ እኔ እርሷን ብመርጣት ልጄ ስላለችኝ እናቴ ስላልኳት ጠላት ለምን ከፋው እኔ እርሷን ብወዳት። ከክብሪት ተፈራ   http://t.me/Mgetem http://t.me/Mgetem http://t.me/Mgetem

አባ ገብረኪዳን https://vt.tiktok.com/ZS9vtBHa5/

እርዳኝ ጌታዬ @Mgetem በሚያልፈው ፈተና የማታልፈውን በታናሽ ነገር አንተ ታላቁን ምስጋንን ትተው ከንፈሮቼ እንዳላማርር በአፌ ስቼ  እርዳኝ ጌታዬ የሆነብኝ ነገር ሁሉ ሊያበረታኝ ለኔ ሆነ አምናለሁ ወድቆ አይወድቅም ክርስቶስ አንተን ያመነ በውድቀቴ በሀዘኔ ይታየኝ ጌታ ማዳንህ ብርታት ስጠኝ የኔ ጌታ በእሳት መሃል ላመስግንህ ትዕግስት የለው ሰውነቴ ይቸኩላል  እስኪፈጸም የፈለገው ካልሆነለት ማመስገንን አልለመደም ምክንያት አለህ የኔ ጌታ ሥሕተት አይደል ስትከለክል በደስታዬ ብቻ ሳይሆን በሀዘኔም  ነህ ትክክል ለዘላቂ ድህነቴ ለጊዜው ነው ስትቀጣኝ እንዳልጠፋ አሰበህ ነው ወደኸኝ ነው ስትቆጣኝ ከቅድስናህ እንድካፈል ከክብርህ እንዳልጎድል አሳምመኽ ልታድነኝ ሠጠተኸኝ ነው በጎ እድል  እርዳኝ ጌታዬ ለክፉ አይሁን ልመናዬ አቅም ስጠኝ ልጠብቅህ መልስ  እስኪያገኝ  ጥያቄዬ ✍️ እሸቱ አበባው http://t.me/Mgetem http://t.me/Mgetem http://t.me/Mgetem

እርዳኝ ጌታዬ በሚያልፈው ፈተና የማታልፈውን በታናሽ ነገር አንተ ታላቁን ምስጋንን ትተው ከንፈሮቼ እንዳላማርር በአፌ ስቼ  እርዳኝ ጌታዬ የሆነብኝ ነገር ሁሉ ሊያበረታኝ ለኔ ሆነ አምናለሁ ወድቆ አይወድቅም ክርስቶስ አንተን ያመነ በውድቀቴ በሀዘኔ ይታየኝ ጌታ ማዳንህ ብርታት ስጠኝ የኔ ጌታ በእሳት መሃል ላመስግንህ ትዕግስት የለው ሰውነቴ ይቸኩላል  እስኪፈጸም የፈለገው ካልሆነለት ማመስገንን አልለመደም ምክንያት አለህ የኔ ጌታ ሥሕተት አይደል ስትከለክል በደስታዬ ብቻ ሳይሆን በሀዘኔም  ነህ ትክክል ለዘላቂ ድህነቴ ለጊዜው ነው ስትቀጣኝ እንዳልጠፋ አሰበህ ነው ወደኸኝ ነው ስትቆጣኝ ከቅድስናህ እንድካፈል ከክብርህ እንዳልጎድል አሳምመኽ ልታድነኝ ሠጠተኸኝ ነው በጎ እድል  እርዳኝ ጌታዬ ለክፉ አይሁን ልመናዬ አቅም ስጠኝ ልጠብቅህ መልስ  እስኪያገኝ  ጥያቄዬ ✍️ እሸቱ አበባው

🖥"የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ " በመምህር ዲያቆን ዘላለም ታዬ  👇👇 https://youtu.be/tzerWs__Kgg

🖥 እጅግ ድንቅ ስብከት ዲያቆን ዘላለም ታዬ  "የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ " 👇👇 https://youtu.be/tzerWs__Kgg https://youtu.be/tzerWs__Kgg https://youtu.be/tzerWs__Kgg

ወልድ እናቱን ላከ መዳን ላልወደዱት፥ ባይዋጥላቸው፤ ለእኛ ለም'ናምን፥ ይህ ቀን ግን ልዩ ነው። የአብራካቸው ክፋይ፥ የእያቄም ወሐና፤ ታስደምም ነበረ፥ በውበት ቁንጅና። ፃህፍት እንደሚሉት፥ በሾለ ብዕራቸው፤ ሁለንተናሽ ውብ ነው፥ ሰሎሞን እንዳለው፤ እንደ ቅዱስ አፍሬም፣ እንደ ህርያቆስ፤ ፅፎ እንደማይደክመው፥ እንደአባ ጊዮርጊስ፤ እሷን የነገሩን፥ ሙሽራ ብለው ነው።              ~~~ የታደለች እናት፥ ንፅህት የተባለች፤ በአምላክ ህሊና፥ ታስባ የኖረች፤ አለም ሁሉ እንዲድን፥ ግንቦት 1መጣች፤ እሰይ ደስ ይበለን፥ ማርያም ተወለደች።              ~~~ ግንቦት 1 ልዩ ነው፥ የተወደደ ቀን፤ ወልድ እናቱን ላከ፥ እኛን ሊታረቀን። ልጇ ነው አምላኳ፥ እሷ የምታዘው፤ አምላክ ሁኖ ልጅ ነው፥ አቤት የሚል ምነው። ውሃን የሚቀይር፥ በደልን የሚሸር፤ ሞትን ድል የነሳ፥ ያልያዘው መቃብር፤ የፍጥረትን ጌታ፥ ያቀፈች በክብር፤ የያዕቆብ መሰላል፥ ናት የሙሴ በትር፤ ስሟ የሚጣፍጥ፥ የሁለት ቃል ጥምር፤ ያም ከሰማይ ሲሆን፥ ማር ደግሞ ከምድር፤ ወልዳ ድንግል የሆነች፥ ያረገች በክብር፤ ማርያም ልደቷ ነው፥ ደስታችን እናብስር። ድንግል ልደቷ ነው፤ ደስ ብሎን እናክብር።              ~~~ መላኩ ከሰማይ፥ ደስ ይበልሽ ያላት ፅንስ ከማህፀን፥ በደስታ የዘለለላት ከድንግል ማርያም ውጭ፥ እስኪ ሌላ ማናት? እንዳለች ንገሩኝ፥እስኪ እኔም ልወቃት፤ ግን በፍፁም የለም፥ ከዚህ ሁሉ ፍጥረት።              ~~~ በ3አመት ወጥታ፥ ከእናት ከአባቷ ቤት፤ ቤተመቅደስ ኖረች፥ ለ12 ዓመት። ከቤተ መቅደሱ፥ ከትህትና ጋር፤ መሶብወርቅ ሰራች፥ በወርቅና በሐር። የሚያስፈልገውን፥ ለቤተ መቅደሱ፤ ስታዘጋጅ ኖረች፥ እስከሚመጣ እሱ። ቀርቦ ለለመናት..... ስሟ መድኃኒት ነው፥ ረሀብን ያጠፋል፤ ስለእመብርሃን ሲል፥ ተሜ ያውቅበታል፤ በድንግል ስም ብሎ፥ አኩፋዳው ይሞላል።              ~~~ አይሁድ አህዛቡ፥ ብሎም መናፍቁ.... ስለድንግል ምስጢር፥ ያልተዋጠላቸው፤ ዛሬም ሳይድኑ አሉ፥ ልቦና ይስጣቸው። ገብርኤል ተገልጦ፥ ምስጢር እስኪነግራት፤ ብትሰጣቸው ድንግል፥ ማርያም ንፅህት፤ መቅደሳችን አሉ፥ የአይሁድ ሞኝነት። የአይሁድኮ ድካም፥ የእነሱ ቂልነት፤ ስሞን እስኪፈራ፥ አጣመዋል ትንቢት። ስምኦን ተጨንቆ፥ ድንግል በድንግልና፤ ወንድ ልጅን ወልዳ፥ አለም ይድንና። ብዬ እናገራለሁ፥ በጨካኞቹ ፊት፤ ከዚህ ተሳስቷል፥ የኢሳያስ ትንቢት። ኢሳያስ ቢሳሳት፥ እኔ አልሳሳትም፤ ሴት ብዬ ልቀይ፥ የድንግልን እትም። ብሎ ቢልም ቅሉ፥ ስምኦን በድፍረት፤ መልአኩ ተላከ፥ የእግዜርን አሰራር እንዳይበክልብት።              ~~~ መቼም ከሳጥናኤል፥ መልካም ነገር የለም፤ ሲያስወቅሳት ኖረ፥ ሔዋንን ዘላለም። ከይሴኮ ተንኮሉ፥ የከይሴኮ ክፋት፤ አፉን አለስልሶ፥ አስወጣቸው ገነት፤ እግዜር ተቀይሞ፥ በጥንዶቹ ስህተት፤ የሚያማልድ ጠፍቶ፥ ገነትን የሚከፍት፤ እነ አዳም ኑረዋል፥ ሽህ ዘመን በግዞት።              ~~~ ሰፊው ቤት ቢዘጋ፥ በመጀመሪያዋ እናት፤ ሔዋን ስትወቀስ፥ ለብዙ ሽ ዓመታት፤ ድንግል ተወለደች፥ ማልዳ ምታስከፍት። ዳግማዊቷ ሔዋን፥ አምላኳን ወለደች፤ ዳግም ወደሲኦል፥ ልጆቿ እንዳይገቡ... በቀኙ ቆማለች፥ ማርልኝ እያለች። እንኳንም ተወለድሽ፥ ጠላት ደስ አይበለው፤ መርገም የተፋቀው፥ በደል የተሻረው፤ በድንግል ማርያም ልጅ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ነው።              ~~~ ብላቴናዋ እናት እግረ ተከል፥ ልጇን ክፋ እንዳይነካባት ወደግብፅ ወረደች፥ ገብርኤል እየመራት ። ስንጠይቅ ሰሎሜን፥ መልስ እንደሰጠችን፤ አረጋዊው ስሞን፥ ደግሞ እንደነገረን፤ የበረሀው ጉዞ፥ ከባድ ነበር አሉን።              ~~~ ስለአንድያ ልጇ፥ ብዙ ግፍን ያየች፤ ከ3 ዓመት በላይ፥ በረሃ ያደረች፤ ያች ብላቴና ድንግል፥ ማርያም ነች። ዳዊት በመዝሙሩ፥ እንደዘመረልሽ፤ ፅዮን እልሻለሁ፥ የንጉሱ እናት ነሽ። አንችን ለማወደስ..... ቃላት ባፈላልግ ፈፅሞ ባጣልሽ፤ ከመላእክት ቋንቋ፥ አንድ ተዋስኩልሽ፤ ደስ ይበልሽ አልኩሽ፥ እንኳንም ተወለድሽ።  (2)              ~~~ እኔ እምልሽ ድንግል፥ አንዴ ልጠይቅሽ፤ ያየሁት በመፅሐፍ፥ ዶኪማስ ቤት ሂደሽ፤ ወይኑ ሲያልቅባቸው፥ ከልጅሽ ጠይቀሽ፤ ጋኑን ወይን አስሞላሽ። በላየ ሰብእ እንኳን፥ ብዙ ነፍስን በልቶ፤ በአንቺ ስም ሲለምን.... ለአንዱ የእኔ ቢጤ፥ ጥርኝ ውሃ ሰጥቶ፤ ገነት እንደገባ፥ አንብበናል ጎልቶ።     እና አንዲህ ከሆነ.... ልጅሽን ስትጠይቂው፥ አለ አምቢ የሚልሽ? በበረሃው እንኳን፥ ኖሯል ሲታዘዝሽ፤ አንቺ የወለድሽው፥ ጌታሽ ካከበረሽ፤ ልደትሽን ልናከብር፥ መጥተናል ከደጅሽ፤ እስከ መጨረሻው፥ አማለጃችን ነሽ እኛ እኖድሻለን፥ እንኳንም ተወለድሽ። እንወድሻለን!!! እንኳን  አደረሰን አደረሳችሁ https://youtube.com/@awdemihretzetewahdo?si=ssYLKSzRnD3AOtzx https://youtube.com/@awdemihretzetewahdo?si=ssYLKSzRnD3AOtzx

እንኳን ደስታን ወደ ዓለም ይዞ ለመጣ ተናፋቂው ለድንግል ማርያም ልደት አደረሳችሁ!!! 👇👇👇👇👇👇 https://youtube.com/@awdemihretzetewahdo?si=ssYLKSzRnD3AOtzx

እንኳን አደረሳችሁ @Mgetem በሐኪ ማርያም ማርያም ዘገነት ኮል። ዕፀ ጳጦስ ዕፀ ጳጦስ መዝገቡ ለቃል። ድንግል ማርያም የሱፍ አበባ ትባላለች። የሱፍ ተክሉ እሾሃም ሲሆን አበባው እሾህ የለውም። ድንግል ማርያምም መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ ከነበረባቸው የሰው ልጆች የተገኘች መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ የሌለባት ንጽሕት ናት። ድንግል ማርያም ሶምሶን ከሞተ አንበሳ ያገኛትን የማር ወለላ ትመስላለች። በመርገም ከነበሩ የተገኘች መርገም የሌለባት ንጽሕት ናትና። ድንግል ማርያም ሙሴ ባያት ዕፀ ጳጦስ ትመሰላለች። እሳተ መለኮትን በሥጋ ስትፀንስ እሳተ መለኮት አላቃጠላትም። ለጨለማው ዓለም የሚያበራ ብርሃንን የያዘችልን መቅረዝ ናት። ለተራበው ዓለም ዘለዓለማዊ ሕይወትን የሚሰጥ ምግብን ይዛልን የመጣች መሶበ ወርቅ ናት። የሕይወት ፍሬን የወለደችልን የሕይወት ዛፍ ናት። በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ። © በትረ ማርያም አበባው  🔤🔤🔤🔤🔤🔤🔤🔤🔤 👇👇👇👇👇👇 https://youtube.com/@awdemihretzetewahdo?si=ssYLKSzRnD3AOtzx

ልደታ ለማርያም 📎❤ @Mgetem በግንቦት አንድ ቀን አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደች። እርሷም ለሰው ሁሉ ወገን ድኅነት የሆነባት ናት፡፡ ከወንዶች ወገን የከበረ አባቷም ስሙ ኢያቄም ከሴቶች ወገን የከበረች ሚስቱ ሐና ይባላሉ፡፡ ሁለቱም ልጅ በማጣት ሲያዝኑ ኖሩ። በዚያ ወራት የመካኖች መብዓ ካህናቱ አይቀበሉም ነበርና፡፡ እነርሱም ከሰው የሚደርስባቸውን ሽሙጥና ኅዘናቸውን ያርቅላቸው ዘንድ በቀንና በሌሊት ወደ እግዚአብሔር ፈጽሞ ይማልዱ ነበር፡፡ ሰውን የሚወድ እግዚአብሔርም ከዘራቸው ለዓለሙ ሁሉ መድኃኒት ይሆን ዘንድ መልካም የሆነ ሐሳባቸውን ተመለከተ፡፡ ክቡር ኢያቄምም አርባ ቀን እስኪፈጸም በተራራ ውስጥ ቁሞ ሲጸልይ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ተገለጸለትና ለዓለሙ ሁሉ ድኅነት የሚደረግባት ዘር እንደሚሰጠው አበሠረው፡፡ በፍጹም ልብ አምኖ ከተራራው ወረደ፤ ለተመሰገነች ሚስቱ ለሐናም ከእግዚአብሔር መልአክ የሰማውን ያንን ራእይ ነገራት። ቃሉ እውነት እንደሆነ እርሷም አመነች። ልዑል እግዚአብሔርንም አመሰገነች። የተመሰገነች ቅድስት ሐናም ከእርሷ የሚወለደውን በዘመኑ ሁሉ ለቤተ እግዚአብሔር አገልጋይ ታደርገው ዘንድ ለእግዚአብሔር ስለትን ተሳለች፡፡ ከዚህም በኋላ ይህችን የከበረች ሕፃን ፀንሳ ወለደች። ስሟንም ‹ማርያም› ብላ ሰየመቻት። ትርጓሜውም ‹እመቤት› ነው። ‹ደግሞም ሀብታና ስጦታ› ማለት ነው፡፡ በእውነት የዓለሙ ሁሉ እመቤት ሁላችን በእርሷ ሰማያዊ ሀብት ልጅነትን ያገኘንባት ናትና። የሥጋና የነፍስ መድኃኒት የሆነች እርሷን እናቱን ለሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፤ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በረከቷም ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ለዘለዓለሙ ይኑር፤ አሜን፡፡ ከመጽሐፈ ስንክሳር ዘወርኃ ግንቦት t.me/Mgetem t.me/Mgetem t.me/Mgetem

የቆሎ ተማሪ @Mgetem ........................ ግዕዙን ለማወቅ ቅኔ ማህሌቱን ታሪክ ወግ ባህሉን  ሊያስቀጥል ያባቱን ቁምጣውን አጥልቆ  ኩታውን ደርቦ ደግሞም ይለምናል እንዲሠጠው ዳቦ ስለ እመብርሃን ስለ አዛኝቷ ይኸው መጥቻለሁ አለሁ ከዛች ቦታ እማዬ  እናቴ  እንዳስለመድሽኝ ቁራሺቷን ዳቦ በጠላ ስጪኝ እያለ ቢለምን ከበራፍ ላይ ሁኖ አያፍርም ነበረ በእርሷ ተማፅኖ ጠላውን በጣሳ ቂጣውን በሰፌድ ተብሎ ይሠጣል ቢሆንህ ለመንገድ ሲሄድ ሲገሰግስ ሲሄድ በየዋርካው ደግሞም ይለምናል ቢሆን ለማደሪያው የቆሎ ተማሪው ተርቦ ቢጠይቅ የቆሎ ተማሪው ተጠምቶ ሲጠይቅ ተስፋው ቅኔ ሁኖ አያቅም ዘር ብሔር ይጣደፋል እንጂ ሠጪውን ለማክበር። http://t.me/Mgetem http://t.me/Mgetem ተጨማሪ ግጥም እንለቃለን 👇👇👇👇👇 https://youtu.be/W9Tl9i4vdgE https://youtu.be/W9Tl9i4vdgE

ልደታ ለማርያም 📎❤ @Mgetem በግንቦት አንድ ቀን አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደች። እርሷም ለሰው ሁሉ ወገን ድኅነት የሆነባት ናት፡፡ ከወንዶች ወገን የከበረ አባቷም ስሙ ኢያቄም ከሴቶች ወገን የከበረች ሚስቱ ሐና ይባላሉ፡፡ ሁለቱም ልጅ በማጣት ሲያዝኑ ኖሩ። በዚያ ወራት የመካኖች መብዓ ካህናቱ አይቀበሉም ነበርና፡፡ እነርሱም ከሰው የሚደርስባቸውን ሽሙጥና ኅዘናቸውን ያርቅላቸው ዘንድ በቀንና በሌሊት ወደ እግዚአብሔር ፈጽሞ ይማልዱ ነበር፡፡ ሰውን የሚወድ እግዚአብሔርም ከዘራቸው ለዓለሙ ሁሉ መድኃኒት ይሆን ዘንድ መልካም የሆነ ሐሳባቸውን ተመለከተ፡፡ ክቡር ኢያቄምም አርባ ቀን እስኪፈጸም በተራራ ውስጥ ቁሞ ሲጸልይ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ተገለጸለትና ለዓለሙ ሁሉ ድኅነት የሚደረግባት ዘር እንደሚሰጠው አበሠረው፡፡ በፍጹም ልብ አምኖ ከተራራው ወረደ፤ ለተመሰገነች ሚስቱ ለሐናም ከእግዚአብሔር መልአክ የሰማውን ያንን ራእይ ነገራት። ቃሉ እውነት እንደሆነ እርሷም አመነች። ልዑል እግዚአብሔርንም አመሰገነች። የተመሰገነች ቅድስት ሐናም ከእርሷ የሚወለደውን በዘመኑ ሁሉ ለቤተ እግዚአብሔር አገልጋይ ታደርገው ዘንድ ለእግዚአብሔር ስለትን ተሳለች፡፡ ከዚህም በኋላ ይህችን የከበረች ሕፃን ፀንሳ ወለደች። ስሟንም ‹ማርያም› ብላ ሰየመቻት። ትርጓሜውም ‹እመቤት› ነው። ‹ደግሞም ሀብታና ስጦታ› ማለት ነው፡፡ በእውነት የዓለሙ ሁሉ እመቤት ሁላችን በእርሷ ሰማያዊ ሀብት ልጅነትን ያገኘንባት ናትና። የሥጋና የነፍስ መድኃኒት የሆነች እርሷን እናቱን ለሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፤ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በረከቷም ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ለዘለዓለሙ ይኑር፤ አሜን፡፡ ከመጽሐፈ ስንክሳር ዘወርኃ ግንቦት t.me/Mgetem t.me/Mgetem t.me/Mgetem

እናቱ እናቴ - ልደትሽ ልደቴ ! (በመላኩ አላምረው) @Mgetem + + + ለእናትነት ክብር - እርሱ ከመረጠሽ በዮሐንስ በኩል - ለእኔ ከተሰጠሽ እኔም እርሱን ጌታ - ብዬ ከተቀበልሁ ማዳኑን አምኜ - በሕጉ ስር ከዋልሁ እናቱን እናቴ - ብየ ለመቀበል... ጥያቄ ልደርድር? ለምን? እንዴት? ልበል? + + + ልጅሽ በምድር ላይ - ሥጋሽን በመልበስ አዳምን ሊያድነው - ለእኛም ጽድቅን ሊያወርስ የረገጠው መሬት - የቆመበት ቦታ ከቤተልሄም ዋሻ - እስከ ጎለጎታ ቅዱስ ከተባለ - ውሎ ያደረበት ልዩ ክብር ካለው - የተሰቀለበት... አንችማ እናቱ - ማህፀን ዓለሙ የሰውነት ልኩ - ሥጋውና ደሙ እንዴት አትከብሪ!? እንዴት አትቀደሽ!? እንዴት አትወደጅ!? እንዴት አትወደሽ!? + + + እንኳንስ ለእኔና... ለእርሱም ለጌታችን - ፈጣሪ ለሆነ እናቱ መባልሽ - ይህ እውነት ከሆነ እናቴ መሆንሽ - እንዴት አልታመነ??? + + + በሥጋ ያይደለ - በረቀቀ መንፈስ እናቴ ሆነሽኝ - ያንችን ክብር ብወርስ ይሄንን መታደል - እንዴት እገፋለሁ? እናቱ እናቴ ነሽ! - ተቀብየሻለሁ!!! + + + ፈጣሪን ልትወልጅው - አምላክን ልታ’ዥው ሰማይና ምድር የማይወስኑትን - በእቅፍሽ ልትይዥው ከድንግልና ጡት - ወተት ልታጠቢው የዓለሙን መጋቢ... ከደኃ ማጀትሽ - ሲራብ ልትመግቢው እናት አባትሽን - ከእስር ልታስፈቺ የክፋትን አባት - በፍቅር ልትረቺ ከሀና ከኢያቄም - የተወለድሽ አንቺ እናትና ድንግል - ንግሥትና አገልጋይ ሰማየ ሰማያት - ጽርሐ አርያም ሆይ! የአንቺ ግሩም ልደት - ለእኔም ነው ልደቴ የጥምቀት መሥራቹ - ልጅሽ ነው አባቴ ዳግም የተወለድሁ - ከውኃና መንፈስ ባንቺ መወለድ ነው - የአዳም ተስፋው ሲደርስ ሕይወት የሆነልን - የልጅሽ ሥጋና ደም ከአንቺው ነው የነሳው - ከላይ አልወረደም ዝም ማለት ያልቻልኩት - ለዚህ ነው ድፍረቴ ልጅሽ ሕይወቴ ነው ! እናቱ እና ነሽ - ልደትሽ ልደቴ + + + + ቅድስተ ቅዱሳን - ንጽሒተ ንጹሐን ማሕጸኑ ለጽድቅ - እናቱ ለብርሃን ሰማየ ሰማያት - ታናሽ ብላቴና ከእያቄም ወሀና - ተወለደሻልና ዓለም ብርሃን አየ - ውስጥሽ ባለው ፀሐይ አዳም ቀና አለ - ተስፋ ብርሃኑን ሊያይ ፍጥረታት በሙሉ - ከሰማይ ከምድር በደስታ ተመሉ - ልደትሽ ሲነገር ተወለደሻልና - የፀሐይ እናቱ ጽርሃሐ-አርያም ሆንሽ - ብላቴናይቱ ! + + + + (፡›አበው ስለክብርሽ - ቃላት አጠራቸው ስለ ደም ግባትሽ - ምሳሌ ጠፋቸው እኔ ግን ደፋሩ - እዘባርቃለሁ ባልበሰለ ብዕር - ቃላት እመርጣለሁ በተንሸዋረረ ዓይን - ክብርሽን አያለሁ ምልጃሽን እያሰብሁ - በተስፋ እኖራለሁ‹፡) + + + የብርሃን እናቱ - የፀሐይ ምሥራቁ የአዳም ሙሉ ተስፋ - የሰይጣን መብረቁ ስለ አንቺ መወለድ - ዓለም ተፈጠረ ስለ አንቺ መወለድ - የሰው ልጅ ከበረ አዳምና ዘሩ - በኃጢአት ቢረክሱ በአንቺ መወለድ - ግን በክብር ነገሡ በአንቺ ልዩ ልደት - አዳም አምላክ ሆነ በአንቺ ልዩ ልደት - ክብራችን ገነነ በአንቺ ልዩ ልደት - ዲያብሎስ ታሰረ በአንቺ ልዩ ልደት - ባሪያ መሆን ቀረ እኔም ደፋር ሆንኩኝ - ፍርሃት ተሰወረ ባዶው አዕምሮዬ - ክብርሽን ነገረ፡፡ + + + ሰማይና ምድር - ልደትሽን ሲያከብሩ ሊቃውንት ሲቀኙ - መላእክት ሲዘምሩ ክብርሽን ተማምነው - በምልጃሽ ያደሩ በምህረት ቃል ኪዳን - ለክብር ሲጠሩ እንደልጅነቴ ለእኔም - እንዲደርሰኝ እንባሽን አስታውሶ - ልጅሽ እንዲምረኝ ዝም ማለት ያልቻልኩት - ለዚህ ነው ድፍረቴ የአንቺ መወለድ ነው - የጽድቅ መሠረቴ ልጅሽ ሕይወቴ ነው ! እናቱ እናቴ ነሽ - ልደትሽ ልደቴ፡፡ + + + http://t.me/Mgetem http://t.me/Mgetem ተጨማሪ ግጥም እንለቃለን 👇👇👇👇👇 https://youtu.be/W9Tl9i4vdgE https://youtu.be/W9Tl9i4vdgE

የልደታን ግጥሞች በድምፅ/በቪዲዮ  እንለቃለን ❤️ ሰብስክራይብ እያደረጋችሁ ጠብቁን 🥰 👇👇👇👇👇👇👇 https://youtu.be/W9Tl9i4vdgE https://youtu.be/W9Tl9i4vdgE

#የአምላክ_እንባ (በላይ በቀለ ወያ) @Mgetem . . ከላይ ከሰማያት... በሰው ተበድሎ ፤ ፈጣሪ ያለቅሳል ከታች ያለ ፍጥረት... "ዝናብ ጣለ" ብሎ ፤ ምድሪቱን ያርሳል። ወራትን ጠብቆ፤ ርሀቡን አስታግሶ የሀገሬ ገበሬ... በፈጣሪ እንባ ነው ፤ የሚበላው አርሶ። እንዲያው በተለምዶ፤ ዝናብ የምንለው ትእግስት አጠራቅሞት... ለወራት የቆየ ፤ የአምላክ እንባ ነው። ።።። ከማንባቱ በፊት... ማዘኑን ሊያረዳ፤ ሰማይ ጠቁሮ ሳለ፤ ፈጣሪ ሲቆጣ... ትውልድ ያማትባል፤ "መብረቅ" ነው እያለ። የሀገሬ ገበሬ..... ሰማዩን እያየ፤ ምድሪቱን ያርሳል የገበሬው በሬ... ሳር ሳሩን እያየ፤ ከገደል ይደርሳል በፈጣሪ እንባ በሰው ልጆች ደባ የታረሰ መሬት... ስንዴና እንክርዳዱን፤ባንድ ላይ ያበቅላል ከላይ ከሰማያት... ስንዴን ከእንክርዳዱ ፤ሊለይ ይታገላል ከታች ያለ ፍጥረት ርሀቡን ሊያስታግስ ስንዴና እንክርዳድን፤ ደባልቆ ይበላል። ።።። ለእንደገና ክረምት ለእንደገና በደል ፣ ለእንደገና ለቅሶ የሀገሬ ገበሬ…… ሰማይ ሰማይ ያያል፤ ደረቅ መሬት አርሶ። ።፣ ከላይ ከሰማያት. የፈጣሪ እናት ልጇን ለማባበል ፤ ፈገግ ትላለች ከታች ያለች እናት... "ፀሐይ ወጣ"ብላ ፤ ብቅል ታሰጣለች። እንዲያው በተለምዶ፤ ፀሀይ የምንላት ልጇን ለማባበል…. ብርሀን የሰጠች፤ የአምላክ እናት ናት። t.me/Mgetem t.me/Mgetem t.me/Mgetem

Powered by @Manybot

የልደታን ግጥሞች በድምፅ/በቪዲዮ እንለቃለን ❤️ ሰብስክራይብ እያደረጋችሁ ጠብቁን 🥰 🫴🫴🫴🫴🫴🫴🫴🫴 https://youtube.com/@awdemihretzetewahdo?si=ssYLKSzRnD3AOtzx