AVT - aviewtainment
الذهاب إلى القناة على Telegram
إظهار المزيد
📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام AVT - aviewtainment
تُعد قناة AVT - aviewtainment (@aviewtainment) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 12 687 مشتركاً، محتلاً المرتبة 4 929 في فئة الرياضة والمرتبة 2 257 في منطقة Ethiopia.
📊 مؤشرات الجمهور والحراك
منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 12 687 مشتركاً.
بحسب آخر البيانات بتاريخ 25 ديسمبر, 2024، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار -237، وفي آخر 24 ساعة بمقدار 0، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.
- حالة التحقق: غير موثّقة
- معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 0%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً N/A% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
- وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 0 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 0 مشاهدة.
- التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 0.
📝 الوصف وسياسة المحتوى
وصف القناة غير متوفر.
بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 26 ديسمبر, 2024) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة الرياضة.
12 687
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-397 أيام
-23730 أيام
أرشيف المشاركات
12 687
+1
አፍሪካውያን የቀድሞ ኮከቦች አዲስ አበባ ገብተዋል
******
ናይጄሪያዊውን የቀድሞ እግርኳስ ኮከብ ንዋንኮ ካኑን ጨምሮ ሄንሪ ካማራ፣ ዳንኤል አሞካቺና ሌሎች በርካታ የቀድሞ የአፍሪካ ኮከብ ተጫዋቾች ማምሻውን አዲስ አበባ ገብተዋል።
በቀጣይ ቀናት በሚካሄደው የሸነን አፍሪካ ፌስቲቫል ላይ ይሳተፋሉም ተብሏል። በፌስቲቫሉ የውጭ ሀገራት የእግር ኳስ ተጫዋቾች፣ ተዋናዮች፣ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች፣ ዲዛይነሮች፣ ሞዴሎች፣ የቴክኖሎጂ ባለሞያዎች፣ ባለ ሃብቶች፣ ዲፕሎማቶችና በሌሎች የሙያ ዘርፎች የተሰማሩ ግለሰቦች እንደሚሳተፉ የቱሪዝም ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
12 687
+3
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቻምፒዮና 10 ሜዳሊያ ወስዳለች
*********
ኢትዮጵያ በ23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ቻምፒዮና 10 ሜዳሊያዎችን በማግኘት ውድድሩን አጠናቅቃለች። ላለፋት ስድስት ቀናት በካሜሩን ዱአላ ከ50 ሺ ሰው በላይ የመያዝ አቅም ባለው የጃፑማ ሁለገብ ስታዲየም ከ27 ሀገራት በላይ የተውጣጡ 2 ሺህ 500 አትሌቶችን በሁሉም የአትሌቲክስ ተግባራት ሲያፎካክር የቆየው ቻምፒዮና ትናንት ምሽት በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ተጠናቋል።
ኢትዮጵያም በ32 ሴት እና በ36 ወንድ አትሌቶች በ19 የአትሌቲክስ የውድድር ተግባራት ተሳትፋ በ5 ወርቅ፣ በ4 ብር እና በ1 ነሐስ በአጠቃላይ በ10 ሜዳሊያዎች ውድድሩን አጠናቅቃለች።
12 687
የቀድሞው የዩናይትድ ኮከብ ወደ ኢትዮጵያ ይመጣል
June 27, 2024
Amen
የመቻል እግር ኳስ ክለብ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ ሙግለጫ የቀድሞ ማንችስተር ዩናይትድ እና ፖርቹጋላዊ ኮከብ ሉዊስ ናኒ ኢትዮጵያ እንደሚመጣ አረጋግጦልናል ብሏል። ከሃምሌ ስድስት ጀምሮ ኢትዮጵያ ይደርሳል የተባለ ሲሆን በአስደናቂ አብዶዎቹ የሚታወቀው የቀድሞ የመስመር አጥቂ ናኒ በቀጥታ ባስተላለፈው የቪዲዮ መልእክት “ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያን ለማየት ጓጉቻለሁ” ብሏል።
👇ሊንክ በመጫን ሙሉውን ያንብቡ
https://aviewtainment.com/?p=64381
ቤተሰብ ለመሆን👇ይጫኑ
https://aviewtainment.com/?page_id=59503
12 687
ህልሙን እውን ያደረገው ጆርጅያዊ
June 27, 2024
Amen
የያኔው የዳይናሞ ቲቢሊሲ አካዳሚ ታዳጊ እንደ ብዙ ታዳጊ ተጫዋቾች ሮናልዶን እያየና እሱን መሆን እየተመኘ ነው ያደገው። ፖርቹጋላዊው የእግር ኳስ ፈርጥ ኳስ ሳያቆም አንድ ቀን አብሬው ብጫወት እያለ ሲመኝና ሲያልምም አድጓል። ይህ ህልምና ምኞቱ ቅዠት ሆኖ አልቀረም።
👇ሊንክ በመጫን ሙሉውን ያንብቡ
https://aviewtainment.com/?p=64376
ቤተሰብ ለመሆን👇ይጫኑ
https://aviewtainment.com/?page_id=59503
12 687
+3
የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ የአመቱ ኮከብ እጩዎች
******
የ2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር የዓመቱ ኮከብ ተጫዋች እጩዎች ይፋ ሆነዋል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር የዓመቱ ኮከብ ተጫዋች፤ ግብ ጠባቂ እና የዓመቱ ወጣት ተስፈኛ ተጫዋች እጩዎች ይፋ ሲደረጉ፣ የዓመቱ ኮከብ ተጫዋች እጩዎች ባሲሩ ኡመር፣ ሽመልስ በቀለ፣ ፈቱዲን ጀማል፣ ቸርነት ጉግሳ፣ አሊ ሱሌይማን፣ ከነዓን ማርክነ እና ቢንያም ፍቅሬ ሆነዋል።
የዓመቱ ኮከብ ግብ ጠባቂ እጩዎች አቡበክር ኑራ፣ ሰዒድ ሀብታሙ እና ፍሬው ጌታሁን ሆነው ተመርጠዋል። የዓመቱ ወጣት ተስፈኛ ተጫዋች እጩዎች ወገኔ ገዛኸኝ፣ ተመስገን ብርሃኑ፣ ዮሐንስ መንግሥቱ፣ በፍቃዱ አለማየሁ እና መድን ተክሉ ሆነዋል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ.ማ ተመልካቾች እስከ ሰኔ 28/2016 ዓ.ም ብቻ በተቋሙ የቴሌግራም ቻናል በመግባት ድምፅ መስጠት እንደሚችሉ አስታውቋል።
12 687
የአቡበከር ናስር ወደ አንጋፋው የጋና ክለብ?
June 26, 2024
Amen
አቡበከር የሙከራ ጊዜውን አጠናቆ ከተሳካለት 88 አመት የሆነውን አንጋፋ የጋና ክለብ ይቀላቀላል። 1935 የተመሰረተው አሳንቴ ኮቶኮ በጋና አሳንቲ ግዛት ኩማሲ መቀመጫውን ያደረገ ክለብ ሲሆን፣ በአማኮም ኩማሲ የሚገኘው ባባያራ ስቴድየምን ይጠቀማል።
👇ሊንክ በመጫን ሙሉውን ያንብቡ
https://aviewtainment.com/?p=64368
ቤተሰብ ለመሆን👇ይጫኑ
https://aviewtainment.com/?page_id=59503
12 687
እድለ ቢሱ ጀርመናዊ!
June 26, 2024
Amen
ባላክ በሁለት የተለያዩ አመታት በትልልቅ ውድድሮች ላይ ስምንት ዋንጫዎችን ለማንሳት አንድ ጨዋታ እየቀረው ሳያነሳ የቀረበት አጋጣሚ አስገራሚ ነው። ይህም በ2002 በባየርሊቨርኩሰንና በብሔራዊ ቡድኑ ሲሆን ሌላው በ2008 ከቼልሲ ጋር ነበር።
👇ሊንክ በመጫን ሙሉውን ያንብቡ
https://aviewtainment.com/?p=64362
ቤተሰብ ለመሆን👇ይጫኑ
https://aviewtainment.com/?page_id=59503
12 687
“አብቅቶልኛል!” – ፖል ፖግባ
June 23, 2024
Amen
ፖግባ ስለቀጣይ የእግር ኳስ ህይወቱ በሰጠው አስተያየት ” ከዚህ በፊት የነበሩኝ ነገሮች ሁሉ አብቅተዋል ፣ አሁን አብቅቶልኛል የቀድሞው ፖግባ በድጋሚ መመለስ አይችልም ” ሲል ተደምጧል።
👇ሊንክ በመጫን ሙሉውን ያንብቡ
https://aviewtainment.com/?p=64356
ቤተሰብ ለመሆን👇ይጫኑ
https://aviewtainment.com/?page_id=59503
12 687
ዩኤፋ ሜዳ የሚገቡ ደጋፊዎች ላይ ጠንካራ ርምጃ ይወስዳል
June 23, 2024
Amen
ፖርቹጋል ትናንት ቱርክን 3ለ0 በረታችበት ጨዋታ ወቅት ከጨዋታው ውጤት ይልቅ በተለያየ ደቂቃ ወደ ሜዳ ዘለው ገብተው ከአል ነስሩ ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ጋር ፎቶ ለመነሳት ጨዋታውን ያወኩ ሰባት ደጋፊዎች ጉዳይ መነጋገሪያ ሆኗል። በዚህም የተነሳ የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር እንደነዚህ አይነት ደጋፊዎችን ለማስቆም ጥበቃውን ለማጠናከር እንደሚገደድ አስታውቋል።
👇ሊንክ በመጫን ሙሉውን ያንብቡ
https://aviewtainment.com/?p=64351
ቤተሰብ ለመሆን👇ይጫኑ
https://aviewtainment.com/?page_id=59503
12 687
በአውሮፓ ዋንጫ የተሸፈነው ኮፓ አሜሪካ
June 22, 2024
Amen
👇ሊንክ በመጫን ሙሉውን ያንብቡ
https://aviewtainment.com/?p=64346
ቤተሰብ ለመሆን👇ይጫኑ
https://aviewtainment.com/?page_id=59503
12 687
ህይወት አድኗ ‘አርም ባንድ’
June 22, 2024
Amen
ሮናልዶ በተለያዩ የሰብአዊ ድጋፎቹና የረድኤት ስራዎቹ የተመሰገነ ስም አለው። የወርቅ ጫማውን ሸጦ ሳይቀር ለተለያዩ ሰብአዊ ድጋፎች ሲያውልም አለም ያውቀዋል። ይህን የሚያደርገውም አውቆና አስቦበበት ነው። በንዴት አውልቆ የወረወረው አርም ባንድ ግን በአንድ ሰው ተነስቶ የሌላ ሰው ህይወትን እታደጋለሁ ብሎ ባላሰበበት መንገድ ሌላ ታሪክ ሰርቷል።
👇ሊንክ በመጫን ሙሉውን ያንብቡ
https://aviewtainment.com/?p=64341
ቤተሰብ ለመሆን👇ይጫኑ
https://aviewtainment.com/?page_id=59503
12 687
ሰርቢያ የአውሮፓ ዋንጫውን ልታቋርጥ ትችላለች
June 20, 2024
Amen
ትናንት ምሽት ክሮሺያና አልባኒያ በምድብ ሁለት 2ለ2 በተለያዩበት ጨዋታ ወቅት የሁለቱ አገራት ደጋፊዎች “ሰርቢያዎችን ግደሏቸው” የሚል ድምፅ ማሰማታቸውን ተከትሎ የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር በነዚህ ደጋፊዎች ላይ እርምጃ ካልወሰደ ሰርቢያ ውድድሩን አቋርጣ እንደምትወጣ አስጠንቅቃለች።
👇ሊንክ በመጫን ሙሉውን ያንብቡ
https://aviewtainment.com/?p=64336
ቤተሰብ ለመሆን👇ይጫኑ
https://aviewtainment.com/?page_id=59503
12 687
ቀበሮዎቹ አዲስ አለቃ አግኝተዋል
....................................
ከአንድ አመት የቻምፒዮንሺፕ ተፋላሚነት በኋላ ወደ ፕሪሚየርሊጉ ያደጉት ሌስተር ሲቲዎች አዲሱን የውድድር አመት በአዲስ አሰልጣኝ ይጀምራሉ። ስቲቭ ኩፐርም የቀበሮዎቹ አዲሱ አለቃ በመሆን ተሹመዋል።
የ44 አመቱ ጎልማሳ አዲስ አዳጊውን ክለብ ለሶስት አመታት ለማሰልጠን መስማማታቸው ይፋ ሆኗል። በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን የታህሳስ ወር ከውጤት መጥፋት ጋር ተያይዞ ከኖቲንሀም ፎረስት ሀላፊነቱ የተሰናበቱት ኩፐር ከ2021-2023 በአሰልጣኝነት መምራት መቻላቸው አይዘነጋም። ኩፐር አዲሱን የኪንግ ፓወር ሀላፊነት በሀምሌ ወር አጋማሽ ከቀበሮዎቹ ጋር በቅድመ ውድድር ዘመን ዝግጅት ጨዋታዎች ይጀምራሉ ተብሏል።
ሌስተር ሲቲ በኢንዞ ማሬስካ እየተመራ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ቢያድግም አሠልጣኙ የቼልሲ አሠልጣኝ ሆነው መሾማቸው ይታወሳል።
12 687
+4
ከደቂቃዎች በኋላ ቱርክ ከ ጆርጂያ የሚያደርጉትን የአውሮፓ ዋንጫ ምድብ ስድስት ጨዋታ የሚያስተናግደው የቦሩሲያ ዶርትሙንድ ስቴድየም ሲግናል ኤዱና ፓርክ ጣሪያዎች እያፈሰሱ ነው:: ይህም ጨዋታው ለተጫዋቾችም ይሁን ለደጋፊዎች ምቹ አይሆንም የሚል ስጋት እንዲፈጥር አድርጓል።
12 687
ጆርጅያ የ30 አመታት ጥረቷን የምታይበት ፍልሚያ
June 18, 2024
Amen
እግር ኳስ ወዳድ ህዝብ ያላት ትንሿ አገር በትልቅ ውድድር ለመሳተፍ ለበርካታ ዓመታት ደጋግማ እድሏን ስትሞክር ቆይታለች። እአአ በ1990 የመጀመሪያው የብሔራዊ ቡድን ጨዋታዋን ያደረገችው ጆርጅያ በትልቅ መድረክ ለመሳተፍ ብዙ ውጣ ውረድ አሳልፋ ዛሬ የመጀመሪያ የአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታዋን ታደርጋለች።
👇ሊንክ በመጫን ሙሉውን ያንብቡ
https://aviewtainment.com/?p=64331
ቤተሰብ ለመሆን👇ይጫኑ
https://aviewtainment.com/?page_id=59503
12 687
ምባፔ እንደ ኦሲምሄን!
June 18, 2024
Amen
ተስፋ የተጣለበት ምባፔ በአውሮፓ ዋንጫው ገና በመጀመሪያው ጨዋታ ቀላል የማይባል የአፍንጫ ጉዳት ገጥሞታል። በዚህም ብብሔራዊ ቡድኑን በአውሮፓ ዋንጫ ቀጣይ ጨዋታዎች እንዲያገለግል ሰባራ አፍንጫውን በማስክ ደግፎ ወደ ሜዳ እንዲገባ የአገሩ እግር ኳስ ባለስልጣናት ሃሳብ አላቸው። ለዚህም ሲባል ወደ ሜዳ ሲገባ አፍንጫውን የሚደግፍበት ማስክ እንደተዘጋጀለት ተጠቁሟል።
👇ሊንክ በመጫን ሙሉውን ያንብቡ
https://aviewtainment.com/?p=64325
ቤተሰብ ለመሆን👇ይጫኑ
https://aviewtainment.com/?page_id=59503
12 687
የተፈራው ፍልሚያ!!
June 16, 2024
Amen
ፖለቲካ ያጠላበት የእንግሊዝና ሰርቢያ ጨዋታ በሁለቱ አገራት ነውጠኛ ደጋፊዎች ሁከት ከቁጥጥር ውጭ ወጥቶ ወደ ለየለት ግጭት እንዳያመራ ጀርመን ከሌሎች ጨዋታዎች በተለየ የፀጥታ ሁኔታውን ጥብቅ አድርጋለች። ያምሆኖ የሰርብ ደጋፊዎች የእንግሊዝ ደጋፊዎችን ባንዲራ ሰርቀው ከወዲሁ ውጥረት ፈጥረዋል።
👇ሊንክ በመጫን ሙሉውን ያንብቡ
https://aviewtainment.com/?p=64318
ቤተሰብ ለመሆን👇ይጫኑ
https://aviewtainment.com/?page_id=59503
12 687
የተፈራው ፍልሚያ!!
June 16, 2024
Amen
ፖለቲካ ያጠላበት የእንግሊዝና ሰርቢያ ጨዋታ በሁለቱ አገራት ነውጠኛ ደጋፊዎች ሁከት ከቁጥጥር ውጭ ወጥቶ ወደ ለየለት ግጭት እንዳያመራ ጀርመን ከሌሎች ጨዋታዎች በተለየ የፀጥታ ሁኔታውን ጥብቅ አድርጋለች። ያምሆኖ የሰርብ ደጋፊዎች የእንግሊዝ ደጋፊዎችን ባንዲራ ሰርቀው ከወዲሁ ውጥረት ፈጥረዋል።
👇ሊንክ በመጫን ሙሉውን ያንብቡ
https://aviewtainment.com/?p=64317
ቤተሰብ ለመሆን👇ይጫኑ
https://aviewtainment.com/?page_id=59503
12 687
በእድሜ ትንሹ የፕሪሚየርሊግ አሰልጣኝ
.................................................
የፕሪሚየርሊጉ ክለብ ብራይተን ፋቢያን ሀርዝለርን አሰልጣኝ አድርጎ ሾሟል። የ31 አመቱ ሀርዝለርም በፕሪሚየርሊጉ ታሪክ በእድሜ ትንሹ አሰልጣኝ ሆኗል። ብራይተን አሰልጣኙን ከጀርመኑ ክለብ ሴንት ፖሊ ለማዘዋወር የውል ማፍረሻውን ለመክፈል የተስማማ ሲሆን፣ ሀርዝለር ሮቤርቶ ዲ ዘርቢን ተክቶ በአሜክስ ስቴድየም ለሦስት አመት የሚያቆየውን ኮንትራት እንደፈረመ ይፋ ተደርጓል።
"የብራይተን አዲሱ አሰልጣኝ በመሆኔ ትልቅ ደስታ ተሰምቶኛል" በማለት ለብራይተን ድረ ገፅ አስተያየቱን የሰጠው ወጣቱ አሰልጣኝ፣ ልዩ ታሪክ ባለው ክለብ የአዲስ ፕሮጀክቱ አካል መሆኑ እንዳስደሰተው ገልጿል። ሀርዝለር በተጠናቀቀው የውድድር አመት ሴንት ፖሊን የቡንደስሊጋ 2 ቻምፒዮን በማድረግ ወደ ዋናው ቡንደስሊጋ ተፎካካሪነት ማሳደጉ ይታወቃል።
12 687
ሮናልዲንሆ ቁጣ !
...................
ጥበበኛው ብራዚላዊው የቀድሞ ኮከብ ሮናልዲንሆ ጎቾ በአገሩ ብሔራዊ ቡድን ደስተኛ አለመሆኑን በቁጣ ገልጿል። በዚህም በቀጣዩ የኮፓ አሜሪካ ውድድር የሀገሩ ብራዚልን ጨዋታዎች መመልከት እንደማይፈልግ በኢንስታግራም ገፁ አሳውቋል። የብራዚል ብሔራዊ ቡድኑ በመጥፎ ሁኔታ ውስጥ መሆኑን የጠቆመዎ ጎቾ " በቀጣዩ ኮፓ አሜሪካ የብራዚልን ጨዋታዎች አልመለከትም በድሎችም አልደሰተም " ሲል ተናግሯል።
"ብሔራዊ ቡድኑ ባለፉት አመታት እስካሁን ካየሁት ሁሉ እጅግ ደካማው ነው በጣም ያሳዝናል" ሲል የገለፀው ጎቾ ለቀድሞ ተጨዋቹ ክብር የሌላቸው ሀላፊዎች እና የማልያ ፍቅር ማጣት መኖሩን በቁጣ ገልጿል።
