Addis Ababa City Manager Office
الذهاب إلى القناة على Telegram
إظهار المزيد
1 474
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-37 أيام
-2130 أيام
أرشيف المشاركات
+5
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር በ2016ዓ.ም ከዋና መስርያ ቤት እስከ ወረዳ በተሰጡ አገልግሎቶች ላይ መደበኛ የዓመቱ የኦዲት ስራ እንዲጀመር ስምሪት ሰጡ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ እያክናወነ ባለው የተቋም ግንባታ ስራ የተቋሙ አገልግሎቶች ጤናማ ስለመሆናቸው መከታተያ የቁጥጥር እና የተጠያቂነት ስርዓት አሰራርን የዘረጋ መሆኑ ይታወሳል።
ኤጀንሲው ላለፉት ሁለት ዓመታት ያሰራጫቸውን የሰርተፍኬት እና መሰል ህትመቶች ለታለመላቸው ዓላማ ስለ መዋላቸው እና የዲጂታል ምዝገባ ስርዓቱ ጤናማ መሆኑን ኦዲት ሲያደርግ የነበረና ይህንንም መነሻ በማድረግ ተጠያቂነት እያሰፈነ ሲሄድ የቆየ ሲሆን የ2016ዓ.ም የኦዲት ስራ የሚመመራበት እቅድ ላይ መግባባት በመፍጠር የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር የ2016ዓ.ም መደበኛ የአገልግሎት ኦዲት ስራ እንዲከናወን ስምሪት ሰጥተዋል።
የኦዲት ስራው ዋና መስርያ ቤት፣ 11 ክ/ከተሞችን እንዲሁም የተመረጡ 26 ወረዳዎችን የሚያካልል ሲሆን የህትመት ውጤቶች እንዲሁም የዲጂታል አገልግሎቶች ጤናማናት ይፍተሻል። ኦዲቱ በአንድ ወር ግዜ ተጠናቆ የተገኙ ግኝቶች በአሰራሩ መሰረት ለህዝብ ይፋ እንደሚሆን ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
ኤጀንሲው በ2015ዓ.ም የተሰጡ አገልግሎቶች ላይ በተደረገ ኦዲት የተገኙ ግኝቶችን መነሻ በማድረግ ግኝት የተገኘባቸው ሙያተኞች እና አመራሮች በአስተዳደራዊ እንዲሁም በወንጀል ተጠያቂ እንዲሆኑ ማድረጉ ይታወሳል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
👇👇👇👇
+5
ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ የሄቨን እናትን በማግኘት አጽናንተዋል::
ልጇን በግፍ ተነጥቃ ባለፈው አንድ ዓመት ፍትህ ሳታገኝ ለቆየችው እህታችን የፍትህ ሂደቱን ለመከታተል ፣ ያለችበት ሁኔታ የተሻለ እንዲሆንላት እና ተጋላጭነቷን ለመቀነስ እንዲመች የከተማ አስተዳደሩ አንድ የመንግስት የመኖሪያ ቤት እንዲሁም በሙያዋ እዚሁ አዲስ አበባ ውስጥ እንድትሰራ መመቻቸቱን ከንቲባ አዳነች ተናግረዋል::
የህፃን ሄቨን ጉዳይ የሁላችንም ጉዳይ በመሆኑ ድርጊቱ ተገቢውን ፍትህ ማግኘቱ የሌሎች ህፃናት ተጋላጭነትን ለመቀነስ አስተዋፅዖ ያለው ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች የዚህ አይነት ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት እንዳይፈፀም የማህበረሰቡ የአመለካከት ለውጥ እንዲመጣ እና ችግሩ የጋራ ጉዳይ በመሆኑ ሁላችንም ኃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባልም ብለዋል::
2 ቀን ብቻ ቀረን!
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኞች
2 ቀን ቀረን - ነሐሴ 17፣ 2016 ዓ.ም በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን በጋራ ለመትከል።…
+2
ባለስልጣኑ የአካባቢን ፅዳት በበማበላሸት በደንብ በሚተላለፉ ግለሰቦች ላይ የሚወስደው የቅጣት እርምጃ አጠናክሮ መቀጠሉን ገለፀ
ነሐሴ 15/2016 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ያመነጨውን ደረቅ ቆሻሻ በአግባቡ ባለመያዝ አብነት ክሊኒክ የተባለ የግል ድርጅት በደንብ ቁጥር 150/2015 በተሻሻለው የቅጣት ሰንጠረዥ 2 ደንብ ቁጥር 167/2016 ባጠፉት ጥፋት መሰረት 50,000/ሃምሳ ሺህ ብር/ ብር መቅጣቱን ገልጿል ።
በተጨማሪም በዛው ወረዳ በአካባቢ ፅዳት ዘመቻ አልሳተፍም ያለውን ግለሰቡ እና በመንገድ ዳር ሽንቱን የሸናው ግለሰብ እያንዳንዳቸው 2,000/ሁለት ሺህ/ ብር መቅጣቱን አሳውቋል ።
ባለስልጣኑ በደንብ ተላላፊዎች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን የከተማችን ነዋሪዎች ልማቱን የመጠበቅ አጥፊዎችን እያጋለጠ እንዲሄድ በአክብሮት ይጠይቃል።
A.A City Administration Code Enforcement Authority
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
ዲስትሪክቱ የኃይል ስርጭቱን የተሻለ ለማድረግ የሚያስችሉ የመልሶ ግንባታ ሥራዎችን እያከናወነ ነው
**********************
የደቡብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት የኃይል ስርጭቱን የተሻለ ለማድረግ የሚያስችሉ የመልሶ ግንባታ ፕሮጀክቶችና የቅድመ ጥገና ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡
በዲስትሪክቱ የክረምቱን ወቅት ታሳቢ በማድረግ 30 የሚሆኑ መጋቢ መስመሮች ላይ የኃይል አስተላላፊ ኮንዳክተሮችና ኢንሱሌተሮች ቅየራ፣ መስመሮቹ ላይ ያረፉ ዛፎችን የማስተካከል እንዲሁም ያዘመሙ አና ያረጁ ምሰሶዎችን በአዲስ የመቀየር ስራ ተከናውኗል፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የወንዝ ተፋሰስ መልሶ ማልማት ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት እና ህዝቡ አደጋው ከመድረሱ በፊት መውጣት እንደሚኖርበት ተገለፀ
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 በትላትናው ምሽት በተከሰተው የጎርፍ አደጋ በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን እና በንብረት ላይ ቀላል ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አደጋና ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍቅሬ ግዛዉ ገለፁ ፡፡
ኮሚሽነሩ እንደገለፁት መሰል አደጋዎችን ለመከላከል የከተማ አስተዳደሩ ከዚህ ቀደም ሲያከናውን የነበረውን የወንዞችን መልሶ ማልማት ፕሮጀክት አጠናክሮ በማስቀጠል በነዋሪዎች ላይ የሚደርሰውን የአደጋ ስጋት መቀነስ እንደሚቻል አብራርተዋል፡፡
ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካለት ጋር በጋራ በመሆን ለነዋሪዎቹ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተዘጋጅቶ ስፍራውን ለቀው በጊዜአዊነት በተዘጋጀላቸው ማረፊያ እንዲሄዱ በመደረጉ የጉዳት መጠኑ ሊቀንስ መቻሉን ተናግረዋል ፡፡
ኮሚሽነሩ አክለውም ህዝቡ ከወንዝ ዳርቻ አደጋው ችግሩ ከመከሰቱ በፊት መውጣት እንዳለበት እና ወደፊትም በፈር ዞን ቤቶች ሲገነቡ የወንዝ ዳርቻ በፈር ዞን ታሳቢ ያደረገ መሆን እንዳለበት ገልፀዋል::
በመጨረሻም በወንዝ ዳርቻ ጉዳት ለደረሰባቸው ነዋሪዎች የቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉን ገልፀዋል፡፡
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
በቀጣዮቹ 11 ቀናት የሚኖረው ተደጋጋሚነት ያለው ከባድ ዝናብ ጎርፍና የመሬት መንሸራተት የማስከተል አቅም ስለሚኖረው የሚመለከታቸው አካላት አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲትዩቱ አሳሰበ፡፡
ከመደበኛ በላይ የሆነ የዝናብ መጠን ይኖራቸዋል ከተባሉ ከተሞች መካከል አዲስ አበባ አንዷ እንደሆነች የኢንስቲትዩቱ መረጃ አመላክቷል፡፡
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
ማህበረሰቡ ብልሹ አሰራርና ሌብነትን ለመከላከል ከተቋማት ጋር በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ ተገለፀ ።
የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ፣ የፅዳት አስተዳደር ጽ/ቤት እና የሲቪል ምዝገባ የነዋሪዎች አገልግሎት ጽ/ቤት በጋራ በመሆን የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ፣ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ውይይትና የእውቅና ፕሮግራም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የተካሄደ ሲሆን በመድረኩ የሁሉም ጽ/ቤቶች ሪፓርት በጋራ ቀርቦ የቀረበውን ሪፓርት መነሻ በማድረግ ውይይት ተካሂዷል።
በውይይቱ ተሳታፊዎቹ የታቀደው ዕቅድ የሚያሰራ መሆኑ ፣ ስራዎችን በቅንጅትና በቴክኖሎጂ ዘምነው እየተሰሩ መሆኑ ፣ ብልሹ አሰራሮችን ከመከላከል አንፃር በርካታ መሻሻሎች መኖራቸውን ጠቅሰው ለማህበረሰቡ የግንዛቤ ፈጠራ ስራ ሊሰራ እንደሚገባ ፣ አደጋ ሊፈጥሩ የሚችሉ ክፍት ትቦዎችንና የኤሌክትሪክ ፖሎችን ማንሳት እንደሚገባ ፣ በቆሻሻዎች የተደፈኑ የውሀ ማስተላለፊያዎችን መክፈት እንደሚገባ ፣ በውሀ መስመሮች ላይ የሚደርሱ ጉዳቶች ላይ በአፋጣኝ መፍትሔዎች ቢሰጡ የሚሉ አስተያየቶች ተሰጥተዋል።
የክ/ከተማው የሲቪል ምዝገባ የነዋሪዎች አገልግሎት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ቤዛ ከፍያለው በበጀት ዓመቱ የተቋም ግንባታ ስራዎችን ማከናወን፣ በቅንጅት መስራት፣ በወረዳዎች የሚሰጡ አገልግሎቶችን በዲጂታል ሲስተም ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ጠቅሰው በቀጣይ ለተገልጋይ ምቹ ሁኔታዎች መፍጠር፣ የተቋም ግንባታ ስራዎች፣ የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን መፍታት ፣ ሌብነትና ብልሹ አሰራር መከላከል ላይ በትኩረት የሚሰራ መሆኑንና ለተግባሩ መሳካት ህብረተሰቡ ከጽ/ቤቱ ጋር በጋራ በቅንጅት ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የክ/ከተማው የፅዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ በየነ ቱሉ በውይይቱ የተነሱ ገንቢ አስተያየቶች ተወስደው የዕቅዱ አንድ አካል እንደሚደረጉ ጠቅሰው በቀጣይ የግንዛቤ ስራዎች ፣ የተጠያቂነትን ስርዓትን ማስፈን ፣ በሰፊው የሚሰሩ መሆናቸውንና ስራዎች ከባለድርሻ አካላት ጋር በየግዜው እየተገመገሙ እንደሚሄዱ ገልፀዋል ።
የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ማናዬ ጫኔ በበጀት ዓመቱ በርካታ ስኬታማ ስራዎች መሰራታቸውን ነገር ግን የሚቀሩ ስራዎች መኖራቸውን አንስተው በቀጣይ ክፍተቶችን በማረም የተሻለ አፈፃፀም ለማምጣት በልዩ ትኩረት መስራት እንደሚገባ ጠቅሰው ማህበረሰቡ ብልሹ አሰራርና ሌብነትን ለመከላከል ከተቋማት ጋር በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ ገልፀዋል ።
በመጨረሻም በበጀት ዓመቱ የተሻለ አፈፃፀም ላመጡ ተቋማት ፣ ወረዳዎችና ባለሙያዎች የዕውቅና እና የሽልማት ፕሮግራም ተካሄዷል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የቅድመ ሆስፒታልና የአንቡላንስ አገልግሎቶች በአንድ ማዕከል እንዲሰጡ ለማስቻል በትኩረት እየተሰራ እንደሆነ ተገለጸ።
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ከሚሰጣቸዉ አገልግሎት አንዱ በሆነዉ የቅድመ ሆስፒታልና አምቡላንስ አገልግሎትን አስመልክቶ ከፌደራል ጤና ጥበቃና ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ስራ ኃላፊዎች ጋር ዛሬ ነሀሴ 14 ቀን 2016 ዓ.ም ዉይይት ተካሂዷል።
በኮሚሽን መ/ቤቱ በተካሄደዉ የዉይይት መድረክ ላይ በኮሚሽኑ እየተሰጠ ያለዉን የቅድመ ሆስፒታልና አምቡላንስ አገልግሎት አሰጣጥና አሁን ያለዉን አቅም እንዲሁም እያጋጠሙ ያለዉን የአቅም ዉስንነቶች አስመልክቶ ገለጻ ተደርጓል።
የምክክር መድረኩን የመሩት በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ዋ/ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ቆንጅት ደበላ እንደተናገሩት በኮሚሽኑ ለህብረተሰቡ በነጻ እየተሰጡ ያሉ የቅድመ ሆስፒታልና የአንቡላንስ አገልግሎቶችን ለማሻሻል በአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ ስር ከሚገኙ ሆስፒታሎች ጋር በተለያዩ መስኮች በትብብር ለመስራት የሚያስችል ስምምነት መፈረሙን ጠቅሰዉ ከፌደራል ጤና ቢሮ ጋርም ተመሳሳይ ስምምነቶች በማድረግ በደተግባር መግባት እንደሚገባ አብራርተዋል።
ዶ/ር ኢሉባቡር ቡኖ በጤና ሚኒስቴር የሜዲካል አገልግሎት መሪ ስራ አስፈጻሚ በበኩላቸዉ እንደተናገሩት የቅድመ ሆስፒታልና የአንቡላንስ አገልግሎቶችን ማጠናከር ወሳኝ አጀንዳ መሆኑን ጠቅሰዉ በዚህ ረገድ በአዲስ አበባም ሆነ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተሰጠ ያለዉ አገልግሎት መሻሻሎች ቢኖሩም ካለዉ የአገልግሎት ፍላጎትና ጥራት አንጻር ውስንነት ያለበት እንደሆነ ጠቅሰዋል።
ዶ/ር ኢሉባቡር አያይዘዉ ይኸንኑ አገልግሎት ለማሻሻል በተበታተነ ሁኔታ እየተሰጠ ያለዉን አገልግሎት በአንድ ማዕከል እንዲሰጥ ለማስቻል በትኩረት እየተሰራ እንደሆነ ተናግረዋል።
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍቅሬ ግዛዉ እንደተናገሩት በኮሚሽኑ እየተሰጡ ካሉ አገልግሎቶች አንዱ የሆነዉን የአምቡላንስ አገልግሎት ለማሻሻል በሚደረገዉ ጥረት ባለድርሻ አካላት አስፈላጊዉን ድጋፍ እንዲያደርጉም ጠይቀዋል።
በኮሚሽኑ እየተሰጡ ያሉ አገልግሎቶችን ለማሳደግ የአምቡላንሶች እጥረት የባለምያ የአቅም ግንባታ ስልጠናና በተያያዥ ጉዳዮች ላይ ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል ዝርዝር መረጃዎች እንዲጠናከሩ አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን ለዚህም ከጤና ሚኒስቴር ፣ ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ፣ ከስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ፣ ከእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የተዉጣጡ አባላት የተሰየሙ ሲሆን አባላቱ በአጭር ጊዜ መረጃዎችንና መፍትሄዎችንም አመላክተዉ እንዲያቀርቡ ተገልጿል።
በዉይይት መድረኩ ላይ የተሳተፉት ፌደራል ጤና ጥበቃና የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ከፍተኛ አመራሮች በኮሚሽኑ በቅድመ ሆስፒታልና አንቡላንስ አገልግሎቶች እንዲሁም በሰራተኞች ክሊኒክ እየተሰጠ ስላለዉ አገልግሎቶች ጉብኝትና ገለጻ ተደርጎላቸዋል።
ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
+7
ለተደረገልን ደማቅ አቀባበል የሲዳማ ብሔራዊ ክልልን እናመሰግናለን። ዛሬ የሌማት ትሩፋት ያለውን ምርታማነት በሐዋሳ ገምግመን ከመጪው ሀገር አቀፍ የ #አረንጓዴዓሻራ የችግኝ ተከላ ቀን አስቀድሞ ዓሻራችንንም አሳርፈናል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
+7
ዛሬ የከተማችንን አዲስ የከተማ ልማት ስትራቴጂ ዝግጅት በይፋ አስጀምረናል።
ይህም የከተማችንን እምቅ አቅሞችን በመለየት፣ እድሎችን በማንጠር፣ አዳጊ ፍላጎቶችን በማካተት እና ተግዳሮቶችን በመቀነስ የረጅም ጊዜ ርዕይ በመተለም ከተማችንን በዘላቂነት ወደፊት ለማስፈንጠር የሚያግዛትን የተቀናጀ፣ የተደራጀ እና አዳዲስ የከተማ ልማት እሳቤዎችን ያካተተ የልማት ፍኖት እንዲኖራት የሚያስችል ነው።
ይህንን በማሰናዳታችን በጅምር ላይ የሚገኙ እና ሳይንሳዊ ቅቡልነት ያገኙ፣ በተግባር የተፈተኑ የልማት ስራዎቻችንን ለማቀናጀት እና ለማስፋት እንዲሁም በሚቀጥሉት ዓመታት ከተማዋ የምትመራበትን የመዋቅራዊ ፕላናችንን ክለሳ ለመምራት የሚያስችሉንን አዳዲስ እሳቤዎች ለማካተት ያስችለናል።
በተጨማሪም የከተማችንን አዳጊ ፍላጎቶች ለማሟላት የሚያስፈልገንን ሀብት ለማሰባሰብ እንዲቻል እና ሁሉንም የልማት አቅሞች ለማቀናጀት የሚያስችል ግልጽ ራዕያችንን ለማጋራት ይጠቅመናል።
የከተማ ልማት ስትራቴጂ ዝግጅቱን በቴክኒክ የሚደገፈንን World Resources Institute / WRI እጅጉን አመሰግናለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
