Addis Ababa City Manager Office
الذهاب إلى القناة على Telegram
إظهار المزيد
1 474
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-37 أيام
-2130 أيام
أرشيف المشاركات
"የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ" በሚል መሪ ቃል የልደታ ክ/ከተማ ስራ አስኪያጅ ፑል ተጠሪ ተቋማት የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄዱ
"የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ" በሚል መሪ ቃል የልደታ ክ/ከተማ ስራ አስኪያጅ ፑል ተጠሪ ተቋማት አስተባባሪነት በወረዳ 2 ውስጥ በሚገኘው የኢፌድሪ መከላከያ መረጃ ዋና መምሪያ የኤሌክትሮኒክስ ዋርፌር መረጃ መምሪያ ቅጥር ግቢ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሂደዋል።
በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ላይ የኤሌክትሮኒክስ ዋርፌር መረጃ መምሪያ ሃላፊ ኮ/ል አሸናፊ ኦሊ፣የልደታ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ስንታየሁ ደስታ፣ የልደታ ክ/ከተማ የዋና ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ስንታየሁ ተረፈ ፣የወረዳ 2 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዘይኑ ኽሊል ጨምሮ ሌሎች አመራሮችና ሰራተኞች ፤የድንገተኛ የእሳት አደጋ ሰራተኞች እና የመብራት ሃይል ሰራተኞች እና የወረዳው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የልደት ክ/ከተማ የስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ አቶ ስንታየሁ ተረፈ እንደገለፁት በዛሬዉ እለት ለምግብነት የሚዉሉና ለጥላ የሚሆኑ ችግኞ መተከላቸውን ተናግረዋል ።
የልደት ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ስንታየሁ ደስታ በበኩላቸው የምንተክለዉ ችግኝ ለትዉልድ የሚተላለፍ መሆኑን ጠቅሰዉ ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን መንከባከብ ይገባል ብለዋል ።
Lideta sub-city communication office
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
+5
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በ2ኛው ምእራፍ 2ኛ ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር “ የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ” በሚል መሪ ቃል በነፋስ ስልክ/ላፍቶ ክፍለከተማ ወረዳ 9 አዲሱ ሰፈር ደን ክልል ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በመገኘት ለሁለተኛ ጊዜ የችግኝ ተከላ አካሄደ።
ነሐሴ 13 ቀን 2016
በችግኝ ተከላ መርሀ-ግብሩ ላይ በቢሮ ሃላፊ ማእረግ የከተማው ም/ዋ/ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላን ጨምሮ የጽ/ቤቱ አመራሮች እና ሠራተኞች፣ የነፋስ ስልክ/ላፍቶ ክ/ከተማ ስራ አስኪያጅ መዋቅር እና የክ/ከተማው የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ቅርንጫፍ አመራሮች እና ሠራተኞች በጋራ አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።
በመርሐግብሩ 8 ሺህ ያህል የጥላ ዛፍ ችግኞች የተተከሉ ሲሆን በተመሳሳይ የጽ/ቤቱ አመራሮችና ሠራተኞች የችግኝ ተከላው መርሐግብርን በተከታታይ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ በዚሁ ወቅት ተመልክቷል።
በስራ ላይ ያለውን የከተማውን ሲስተም በአዲስ ለመተካት የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት ስራ ውይይት ተደረገ
የአዲስ አበባ ከተማ አገልግሎት እየሰጠችበት ያለውን የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ሲስተም የሚተካ አዲስ የCRVS, e-ID and Mobile ID የተባለ ሲስተም አልምቶ ወደ ስራ ለማስገባት የጋራ ውይይት መድረክ መደረጉ ተገለጸ።
የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን በቶፓን ግራቪቲ ኢትዬጵያ አማካኝነት አልምቶ ለመተግበር ስራ የተጀመረውን አዲስ ሲስተም በተመለከተ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ሰለሞን አማረ ፣ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ፣ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ግሩፕ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ መለከት ሳህሉ ፣ የቶፓን ግራቪቲ ኢትዮጵያ ኩባንያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ቃልኪዳን አረጋ እንዲሁም ሌሎች ሃላፊዎች እና ከፍተኛ ሙያተኞች ተሳትፈውበታል።
ይህ አዲስ ፕሮጀክት ነባሩን ሲስተም በመተካት የተቋሙን አገልግሎት ወደ ኦንላይን የሚያሻግር፣ በከተማዋ ጤና ተቋማት ላይ ስርዓት በመዘርጋት ልደት እና ሞትን በየዕለቱ በመመዝገብ የሲቪል ምዝገባ ሽፋን እና መረጃን የተሟላ ማድረግ የሚያስችል፣ ስማርት ኤሌክትሮኒክ መታወቂያን እንዲሁም ሞባይልን እንደ መታወቂያ መጠቀምያ መተግበርያን ያካተተ ሲሆን አዲስ አበባን ወደ ስማርት ሲቲነት ለመቀየር ከፍተኛ ሚና ያለው ከመሆኑም ባሻገር ተቋም እየሰጠ ያለውን አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ የሚያዘምን እንደሆነ ተነግሯል።
ቶፓን ግራቪቲ ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ መንግስት የሼር ባለቤትነት በሃገር ውስጥ የተቋቋመ የልማት ድርጅት ሲሆን በአሁኑ ወቅት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎትን አዲስ ሲስተም የማልማት እና ተያያዥ የፖስፖርት እንዲሁም ልዩ ልዩ መታወቂያ ፕሮጀክት ስራዎችን ተረክቦ እየሰራ ያለ ኩባንያ ነው። ኩባንያው በኢትዮጵያ ውስጥ ፓስፖርት እና መሰል የምስጢራዊ ህትመቶችን መስራት የሚችል ፋብሪካ ግንባታ መጀመሩ ይታወሳል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
ነሐሴ 17፣ 2016 ዓ.ም በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ዓሻራችንን እናኑር::
በአንድ መንፈስ በመላው ኢትዮጵያ ዓሻራችንን እናኑር፡፡ አንድ ከሆን ከዚህም በላይ እንችላለን!
አዋቂዎች ከ20 በላይ፣ ታዳጊወች ከ10 በላይ በመትከል ለሀገር ያለንን ፍቅር፣ ለትውልድ ያለንን ስጦታ በተገቢው ስፍራ እንግለጥ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) ኤፍኤም 97.1 ሬድዮ ጋር በመተባበር የሚቀርበው ሳምንታዊ የሬድዮ ፕሮግራም ሁለተኛ ምእራፍ የመጀመሪያው ክፍል ፕሮግራም ስርጭቱን በዚህ ሳምንት ጀምሯል።እንድትከታተሉት ተጋብዛችሁዋል።
See less
ለአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት ተጠሪ በሆኑ ተቋማት የሚሰጡ የከተማችን ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ያሉበትን ደረጃ እና ሌሎች ተያያዥ አንኳር ጉዳዮች ላይ በቢሮ ሃላፊ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ ዋ/ ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ ከኢሳት ቴሌቪዥን ጋር ያካሄዱትን ቃለ ምልልስ እነሆ ብለናል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
+5
ከስራ ውጭ ህልማችንን የምንፈታበት ሌላ መንገድ ስለሌለ ያለን የፖለቲካ ዕሳቤ ስራ ብቻ ነው። በዚህ መንገድ የመዲናችንን የነገ መልክ የሚያሳየውን የ’አዲስ ቱሞሮ’ የኢኮኖሚ ዞን ግንባታን ዛሬ አስጀምረናል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
+8
የአዲስ ቱመሮ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ግንባታን ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ዛሬ አስጀምረናል።
በ35 ሄክታር መሬት ላይ ከቻይናው CCCC ጋር በአጋርነት የሚገነባው የአዲስ ቱሞሮ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በከተማ ውስጥ አዲስ ከተማን የመገንባት ያህል ግዙፍ ፕሮጀክት ሲሆን በውስጡ ትላልቅ ሞሎችን፣ የመኖሪያ አፓርትመንቶችን፣ ቢሮዎችን፣ የትምህርት ተቋማትን፣ የጤና ተቋማትን እንዲሁም ሰፋፊ የመዝናኛና የውሃ አካላትን፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ማዕከላትን ያካተተ ነው።
ይህ የአዲስ ቱሞሮ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ለከተማችን አዲስ ገፅታ የሚያላብስ፣ ዓለምአቀፍ ተወዳዳሪነቷን የሚያጎላ፣ ተጨማሪ የውበት ምንጭ የሚሆን፣ ለነዋሪዎች ሰፊ የስራ እድል የሚፈጥር፣ ንግድን የሚያሳልጥ፣ ትልቅ ዓለም አቀፍ የግብይት ማዕከል የሚሆን እንዲሁም ማህበራዊ አገልግሎቶች የሚሰጡ መሰረተ ልማቶችን ያካተተ ሲሆን በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቅቆ ወደ ስራ የሚገባ ይሆናል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ባለስልጣኑ በከተማው የልማት ኮሊሪደር ሆን ብለው በቸልተኝነት የደንብ መተላለፍ በፈጸመ ግለሰብ ላይ እርምጃ ወሰደ::
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በሠሌዳ ቁጥር ኮድ 2 C 28053 አ.አ የቤት መኪና አሽከርካሪ ግለሰብ በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 2 በተለምዶ መጠሪያው ቦሌ ማተሚያ አካባቢ የልማት ኮርደር ላይ በተሽከርካሪ ውስጥ በመሆን ባልተፈቀደ ቦታ ላይ የሲጋራ ቁራጭ ሆን ብሎ በቸልተኝነት በመጣል በህብረተሰቡ እንዲያነሳ ቢጠየቅም ፈቃደኛ ባለመሆን አምልጦ ለግዜው ቢሠወርም በአዲስ አበባ ትራፊክ ፖሊስ ብስለት በተሞላበት ብርቱ ክትትል ከነተሽከርካሪው በዛሬው ዕለት በቁጥጥር ሥር ውሏዋል።
ግለሰቡ የአዲስ አበባ ከተማ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በደንብ ቁጥር 150/2015 በተሻሻለው የቅጣት ሰንጠረዥ 2 ደንብ ቁጥር 167/2016 መሰረት 2000/ሁለት ሺህ ብር/ ተቀጥቷል ።
የተሰራው ልማት አዲስ አበባን ውብ ጽዱ በማድረግ የከተማዉ ህዝብ እንዲጠቀምበት ፣የቱርስት መስህብና ሌሎች በአለማችን የሚገኙ ከተሞች የደረሱበትን ዕድገት ደረጃ ለማድረስ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሌት ተቀን በመሥራት ለህዝብ ጥቅም በማዋል ህብረተሰቡ ተጠቃሚ ማድረጉ ይታወቃል።
ባለስልጣኑ አንዳንድ ግድ የሌሽ ግለሠቦች የተሠራውን ልማት ላይ ሆን ብለዉ በመኪና ሲገጩ ስያበላሹ፣ ያልተፈለገ ደረቅ ቆሻሻ ማለትም ሶፍት ፣የውሃ ፕላስቲክ ፣የሲጋራ ቁራጭ ፣የመሳሰሉትን በሚጥሉ ግለሰቦች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ ይቀጥላል።
የአዲስ አበባ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በደንብ ተላላፊዎች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን በዛሬው ዕለት በተወሰደዉ ቅጣት መረጃውን የሰጡንን የከተማዉን ነዋሪዎች ከልብ እያመሠገንን አሁንም ልማት ወዳዱ የከተማችን ነዋሪዎች አጥፊዎችን መረጃ በመስጠት የጀመረውን ጥቆማ አጠናክሮ እንዲቀጥል በአክብሮት እንጠይቃለን።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
+8
በ#አረንጓዴዓሻራ ልማት ንቅናቄ የፍራፍሬ ተክሎች የማልማት ሥራ ከፍተኛ ለውጥ እና ውጤት እያስመዘገበ ይገኛል። በዚህ ስኬታማ ሥራ ላይ ተመርኩዘን የበለጠ ውጤት ለማግኘት አሠራራችንን ማጎልበት፣ ዘዴዎቻችንን በሚያዘምኑ ፈጠራዎች ላይ መስራት ብሎም የአካባቢ ጥበቃ እና የግብርና ሥራዎቻችንን ለማላቅ ማኅበረሰባችንን ማሳተፍ መቀጠል ይኖርብናል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
