ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

الذهاب إلى القناة على Telegram

إظهار المزيد
1 474
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-37 أيام
-2130 أيام
أرشيف المشاركات
photo content
+7

ከንቲባ አዳነች አቤቤ "Liveable and Sustainable Cities: Rejuvenate, Reinvent, Reimagine" በሚል መሪ ቃል በሲንጋፖር ከተማ እየተካሄደ በሚገኘዉ በርካታ የአለም ከተሞች በተሳተፉበት ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ:: ጉባኤው ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹና አረንጏዴ በማድረግ ፣ የአየር ብክለትን መከላከል እና የፈጣን ለውጥ ማዕከል በማድረግ ለትውልድ የሚተላለፍ አሻራ ስለማኖር በሰፊው እየመከረ የሚገኝ ሲሆን ልምድ ልውውጥ እና መማማርን ማዕከል ያደረገ ጉባኤ ነው:: ከንቲባ አዳነች አቤቤ በC40 አባል ከተሞች አማካይነት በተዘጋጀዉ የፓናል ዉይይት ላይ በመሳተፍ በከተማችን ቀጣይነት ያለው እድገት በማረጋገጥ ለኑሮ ምቹ ለማድረግ እየተሰሩ ባሉ ስራዎች ፣ ዕድሎች እና ተግዳሮቶች ዙሪያ ልምድ ያካፈሉ ሲሆን በተለይ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን በመቋቋም የተሻለ ከተማን ለመገንባት እየተከናወኑ ባሉ የወንዝ ዳርቻ ስራዎች፣ የህዝብ መዝናኛ ፓርኮች በመገንባት፣ የአረንጓዴ ልማት ኢንሼቲቭን በማከናወን ላይ ስለሚገኙት የኮሪደር ልማት ስራዎች እንዲሁም የሚሰራው ልማት ሁሉ ለሰው ልጆች ተስፋ እና የኑሮ ጫናን የሚያቃልል ይሆኑ ዘንድ ሰው ተኮር ተግባራት በተመለከተ በዝርዝር አስረድተዋል:: ከጉባኤው ተሳትፎ ጎን ለጎን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከሲንጋፖር ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴስሞንድ ሊ ፣ ከተለያዩ ከንቲባዎች ፣ ከተማ አስተዳዳሪዎች እንዲሁም በከተሞች ዙሪያ ከሚሰሩ የድርጅት ተወካዮች ጋር በመገናኘት በቀጣይ የትብብር መስኮች ላይ ውይይት ለማድረግ ችለዋል:: ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager?is_from_webapp=1&sender_device=pc Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

photo content
+7

የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት ከአራት ኪሎ እስከ ራስ መኮንን ድልድይ ያለው አሁናዊ ገጽታ፦ ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager?is_from_webapp=1&sender_device=pc Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

photo content
+3

ይህን ያውቁ ኖሯል?...... “በካይ ቅጣቱን ይከፍላል!” ዙሪክ እና የዙሪ ከረጢቶች የስዊዘርላንድ ከተማ በሆነችው የዙሪክ ከተማ ያለው የቆሻሻ አያያዝ “በካይ ቅጣቱን ይከፍላል!” በሚለው መርህ ላይ የተመሰረተ ነው። የዙሪክ የቆሻሻ አስተዳደር ተቋም እ.ኤ.አ ከ1985 ጀምሮ የተለያዩ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ከረጢቶችን (ዙሪ-ከረጢቶችን) በማምረት የከተማው ነዋሪ ለቆሻሻ አወጋገድ እንዲጠቀም አድርጓል። "በጣልከው ቆሻሻ ልክ ክፈል!" የሚለውን ፅንሰ-ሀሳብ ተከትሎ የዙሪ ከረጢትን መጠቀማቸው በከተማው የቆሻሻ አስተዳደሩን ቀላል አድርጎታል፡፡ ምክንያቱም ዜጎች ቆሻሻን ከከረጢት ውጭ ጥለው ቢገኙ አሊያም ሌላ አካባቢን ለብክለት የሚዳርጉ ማጠራቀሚያዎችን ለመጣል ቢጠቀሙ ቅጣት ይደርስባቸዋል። ስለዚህም ሁሉም ዜጋ ቆሻሻን ለማጠራቀም የዙሪ ከረጢት የሚጠቀም ሲሆን ከዚህ ውጪ ቆሻሻን አግባብ ባልሆነ መንገድ የአካባቢና የስነ ምህዳር ብክለት በሚያስከትል መልኩ ቆሻሻን ማዝረክረክና መጣል ከባድ ቅጣት ያስከትላል። በዚህ መልኩ የከተማቸው የጽዳት ጉዳይ የሁሉም ዜጋ ሃላፊነት መሆኑን አረጋግጠዋል። Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager?is_from_webapp=1&sender_device=pc Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

photo content
+9

photo content

"ብክለት ይብቃ ውበት ይንቃ" በሚል መሪ ቃል የፅዳት ዘመቻ ተካሄደ ። በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 አስተዳደር ፅዳት አስተዳደር ፅ/ቤት "ብክለት ይብቃ ውበት ይንቃ" በሚል መሪ ቃል ቤንይሸር ሆቴል አካባቢ የጽዳት ዘመቻ ተካሄደዋል ። በፅዳት ዘመቻው የክ/ከተማ እና የወረዳ አመራሮች፣የደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች፣የሽርክና ማህበራት ፣የፅዳት አስተዳደር ሰረተኞች እና ነዋሪዎች ተገኝተዋል ። አካባቢያችንን መፅዳት የእለት ተእለት ተግባራችን መሆን እንዳለበት ብሎም አሁን ለይ የወረዳው ማህበረሰብ የተሸለ ግንዛቤ እንደለው እና ቆሻሻን በመጠየፍ የአካባቢያችንን ንፅህና መጠበቅ ይኖርብናል ሲሉ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ዘላለም ብርሃኑ ተነግረዋል ። የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሰለሞን ፈንቴ በበኩላቸው ነዋሪዎች የአካባቢ ፅዳትን ባህል ለማድረግ የአመለካከት ለውጥ መፍጠር እና የከተማዋን ውበት መጠበቅ ሁሉም ማህበረሰብ ሀላፊነት እንዳለበት ገልፀዋል ። Lafto Communication- ላፍቶ ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ ለመከተል እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager?is_from_webapp=1&sender_device=pc Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

photo content
+2

photo content
+9

በአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት የጎርፍ የአደጋ ሰጋት ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎች ካሉባቸው ቦታዎች በ5 ክፍለ ከተሞች የቅድመ ጎርፍ መከላከሉ ተግባር ያለበትን ደረጃ ለማወቅ የሚያስችል የመስክ ምልከታ ተካሂዷል ። የመስክ ምልከታው አላማ በየክፍለ ከተሞች የተለዩት የአደጋ ስጋት ቦታዎች ላይ በተቋማት ቅንጅት እየተከናወኑ ያሉ የቅድመ ጎርፍ አደጋ መከላከል ተግባር አፈፃፀሞች ከሪፖርት ባሻገር በመስክ ምልከታ በትክክለኛ መረጀ በማረጋገጥ ባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ ጥረታቸውን ይበልጥ እንዲያጎለብቱ ለማድረግ ያለመ ነው። በዚህም መጪው ክረምት ከመግባቱ በፊት ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችን ከወዲሁ ለመቀነስ የሚያስችሉ ስራዎች በፍጥነት እንዲጠናቀቁ ለማድረግ የሚያስችል መረጃ ለመስጠትም የሚያግዝ ነው። በጽ/ቤቱ የኮሙዩኒኬሽን ዘርፍ ባለሙያዎች በጉለሌ እና በለሚኩራ ክፍለ ከተሞች ባሉ 8 ወረዳዎች በአደጋ ሰጋት የተለዩ ቦታዎችላይ የመስክ ምልከታው ተካሂዷል። በጉለሌ ወረዳ 6 በተለምዶ "መቀጠያ ግንብ" እየተባለ የሚጠራ አካባቢ ከ400 በላይ ለሆኑ ሴቶች የሸክላ ማምረቻ ሼዶች የተገነቡበት እና በመሬት መንሸራተት እና በጎርፍ አደጋ ከፍተኛ ሰጋት ያለበት ሲሆን በአሁኑ ወቅት 50% የሚሆነው ችግር ሼዶችን በሰተግራ በሚያዋስነው በኩል በተሰራ ስራ የተፈታ መሆኑ ተመልክቷል።ሆኖም ግን ቀሪው ስራዎች በአፋጣኝ ተጠናቀው ችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ሊያገኝ እንደሚገባ በአካባቢው ያሉ ነዋሪዎች ተናግረዋል። በጉለሌ ወረዳ 5 በተለምዶ "ሳንሱሴ ታቦት" ማደሪያ እየተባለ የሚጠራ አካባቢ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ሸገር ከተማ አስተዳደር አዋሳኝ ቦታ ላይ የሚገኝ ከፍተኛ ደለል እና የቆሻሻ ክምችት የውሀ ማፋሰሻ ቱቦዎችን በመድፈን ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ ሊያስከትል ስለሚችል የፍሳሽ መውረጃ መስመሮች ጽዳት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። በለሚኩራ ወረዳ 14 በተለምዶ "አዳማ አንድ" የተባለ የኮንደሚኒየም ሳይት ከፍተኛ የደለል እና የጎርፍ አደጋ የሚያስከትል የውሀ ማፋሰሻ ቱቦ በማሽን ሊፀዳ የሚችል በመሆኑ የሚመለከታቸው አካላት በአስቸኳይ ችግሩን እንዲፈቱ ነዋሪዎቹ ጠይቀዋል። ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager?is_from_webapp=1&sender_device=pc Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

photo content
+9

photo content

የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ተጨማሪ 2ኛውን ቅርንጫፍ ቢሮ ዛሬ በይፋ ከፈተ የሲቪል ምዝገባ እና የ የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ 2ኛውን የሰነድ ማመሳከር እና የማረጋገጥ አገልግሎት በመገናኛ አከባቢ በሚገኘው አማረ አብርሃም እና ቤተሰቦቹ ህንፃ ላይ ያስጀመረ ሲሆን በአገልግሎቱ የሚሸፈኑት ክፍለ ከተሞች ቦሌ፣ የካ እና ለሚ ኩራ ክ/ከተማ መሆናቸው ታውቋል። ቅርንጫፍ ቢሮው ዛሬ በምክትል ከንቱባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ-አስኪያጅ ክብርት ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን መርቀው ስራ ያስጀመሩ ሲሆን ቀልጣፋ እና የተገልጋይ የአገልግሎት እርካታው ከፍ ያለ አገልግሎት በመስጠት የቅርንጫፉን ግብ ማሳካት እንደሚገባ አሳስበዋል። ከወረቀት ንክኪ ነፃ በመሆነ መልኩ የዲጂታል አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን ከዋና መስርያ ቤት ጋር ተናባቢ የሆነ ሲስተም ፣ የካሜራ መስመር እንዲሁም የዲጂታን ክፍያ አማራጮች ያሉት መሆኑን የCRVS ዳይሬክተር ወ/ሮ ቤተልሄም ታደሰ ገልፃ አድርገዋል። በየግዜው እየጨመረ ያለውን የአገልግሎት ፍላጎት ከግምት በማስገባት በዋና መስርያ ቤት እየተሰጠ ያለውን አገልግሎት ለተገልጋዩ ነዋሪ በአማካይ ስፍራ ተደራሽ ማድረግ የተቋም ግንባታ አንዱ ፕሮግራም መሆኑን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ የገለፁ ሲሆን ይቻል ዘንድ ኤጀንሲው ከወራት በፊት በዶ/ር አበበች ጎበና የሰየመውን ቅርንጫፍ መክፈቱን አስተዋል። ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager?is_from_webapp=1&sender_device=pc Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

photo content

የአዲስ አበባ ከተማ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በነገው እለት ማክሰኞ ግንቦት 20/2016 ዓ ም በዋና መስሪያ ቤት፣ በቅርንጫፍ የማስረጃ ማረጋገጫ፣ የክ/ከተማ እና የወረዳ ጽ/ቤቶቹ ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸውን አስታውቋል። በዚህም መሠረት በነገው እለት አገልግሎት ማግኘት የሚሹ የኤጀንሲው ተገልጋዮች በተጠቀሱት ማእከላት በመገኘት አገልግሎት ማግኘት የሚችሉ መሆኑን ኤጀንሲው አመልክቷል። ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager?is_from_webapp=1&sender_device=pc Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

photo content
+4

photo content
+9

የረዳን ፈጣሪ ክብርና ምስጋና ይሁንለት! "በጎነት"ብለን በሰየምነው የመኖሪያ መንደር የተገነቡ ሁለት ባለ 9 ወለል ዘመናዊ ሕንጻዎችን እና የስራ ዕድል መፍጠሪያ ማዕከላትን መርቀን ለ140 አቅመ ደካሞች እና አካል ጉዳተኛ ነዋሪዎች አስተላልፈናል። በልደታ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ቆርቆሮ ሰፈር በሚባለው የተጎሳቆለ የመኖሪያ መንደር ይኖሩ ለነበሩ አቅመ ደካሞች፣ አካል ጉዳተኞች፣ ማየት ለተሳናቸው፣ ለተለያየ ማህበራዊ ችግር ለተጋለጡ እና በልማት ለተነሱ ነዋሪዎች ያስተላለፍናቸው ምቹ የመኖሪያ ቤቶች ሳሎን፣ መኝታ ቤት፣ የማብሰያ እና የመጸዳጃ እንዲሁም የመኝታ ክፍሎች ያላቸው ዘመናዊ ቤቶች ናቸው። በዚህ የበጎነት መንደር ካስተላለፍናቸው የመኖሪያ ቤቶች ጋር በማቀናጀት የእናቶችን ጫና የሚያቀል የህጻናት ማቆያ፣ ለአካባቢው እናቶች የስራ ዕድል የሚፈጥር ዘመናዊ የእንጀራ መጋገሪያ፣ የሚሰሩ እጆችን ከስራ የሚያገናኙ የወንዶችና የሴቶች የውበት ሳሎኖችን እንዲሁም የልብስ ስፌት ማሽኖችን አዘጋጅተን ለነዋሪዎቹ የስራ እድል ፈጥረናል። በመኖሪያ መንደሩ ቤት ለሰጠናቸው ማየት የተሳናቸው ነዋሪዎች እንቅስቃሴ እጅግ አስፈላጊ የሆኑ ኬኖች፣ ለአካል ጉዳተኛ ነዋሪዎች ደግሞ ክራንችና ዊልቸሮችን አዳርሰናል። ሰርቶ ካገኘው ላይ ለወገን በጎ ለመስራት ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመተባበር ቤቶቹን የገነባውን ሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በራሴና በነዋሪዎቹ ስም እያመሰገንኩ፣ በጎነት አያጎድልምና ፈጣሪ ጨምሮ እንዲሰጠው እመኛለሁ። የሚሰሩ ልማቶች ሁሉ ለሰው ልጆች ተስፋ የሚሰጡ እና የኑሮ ጫናን የሚያቃልሉ ይሆኑ ዘንድ ሰው ተኮርነታችን በተግባር የሚገለጽ ነው። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ