ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

الذهاب إلى القناة على Telegram

إظهار المزيد
1 474
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-37 أيام
-2130 أيام
أرشيف المشاركات
photo content
+3

ከ13 ሚለየን ብር በላይ በአንድ ወር ግዜ ውስጥ በቴሌብር የዲጂታል አማራጭ ገቢ መሰብሰብ መቻሉ ተገለፀ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በተቋም ግንባታ ፕሮግራሙ ከአገልግሎት የሚሰበሰቡ ክፍያዎችን ወደ ዲጂታል የክፍያ ስርዓት ማሸጋገር አንዱ እቅድ አድርጎ ሲሰራ ቆይቷል። በዚሁ መሰረት ከቴሌብር ጋር በጋራ በተጀመረው ስራ በአንድ ወር ግዜ ውስጥ ከዋና መስርያ ቤት እስከ ወረዳ 13,083,547.85 ብር በዲጂታል መሰብሰብ መቻሉ በዛሬው ግመገማ በቀረበው ሪፖርት ተመላክቷል። የኢትዮ ቴሌኮም ምክትል ስራ አስፈፃሚዎች እና የስራ ክፍል ሃላፊዎች በተገኙበት በተደረገው የስራ ግምገማ ከዋና መስርያ ቤት እስከ ወረዳ ድረስ ያለው የአፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጓል። ሃላፊዎቹ ባጠረ ግዜ ተቋሙ የዲጂታል አማራጩን ለመተግበር ያሳየው ቁርጠኝነት ለሌሎች ተቋማት አርዓያ እንደሚሆን ገልፀው በቀጣይ ሙሉ ለሙሉ የሚሰበሰበውን ገቢ ወደ ዲጂታል ማሻገሩ ላይ ትኩረት ተደርጎ አሁንም ሊሰራ እንደሚገባ ጠቁመዋል። በውይይቱ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ እንደገለፁት በቀጣይ ዓመት ተቋሙ ሙሉ ለሙሉ ከገንዘብ ንክኪ ነፃ በመሆን የገቢ አሰባሰብ ስርዓትን በመተግበር የተቋሙን የዲጂታል ተጠቃሚነት በሁሉም ዘርፍ ውጤታማ ለማድረግ እንደሚሰራ ተናግረዋል። በሪፖርቱ የነበሩ ጥንካሬዎች እና ክፍተቶች ተለይተው የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫ የተሰጠበት ሲሆን የዲጂታል አማራጩን በመተግበር አዲስ ከተማ እና ንፋስ ስልክ ላፍቶ የተሻለ አፈፃፀም ማሳየታቸው ተመላክቷል። ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

photo content
+3

"ልመና እና ተረጂነትን ማስቀረት፣ የስራ እድልን በስፋት መፍጠር እና የኑሮ ውድነት ጫናን በዘላቂነት መቀነስ አንዱ ትልቅ ትኩረት የሚሰጠው ስራ በመሆኑ በዚሁ ላይ ከመላው የከተማችን አመራሮች ጋር ተወያይተናል። ይህን ለማሳካት የልማት ሃይላችንን በማስተባበር እና ጸጋዎቻችንን በመጠቀም የጀመርናቸውን ስራዎች አጠናክረን በመቀጠል፣ ግንዛቤዎችን ከፍ በማድረግ እንዲሁም የስራዎቻችንን ውጤታማነት በማስቀጠል የምግብ ዋስትና ሉዓላዊነታችንን በማረጋገጥ ለብልፅግናችን እንተጋለን"። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ እና የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸዉን የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ ። የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ከአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ጋር በአቅም ግንባታ ስልጠና ፣ በአደጋ መንስዔ ምርመራ ፣ በጥናትና ምርምር ፣ በአደጋ ስራ አመራር እና በተያያዥ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸዉን የመግባቢያ ሰነድ ዛሬ ግንቦት 19 ቀን 2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ተፈራርመዋል። በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ ም/ኮሚሽነር ጀነራል መስፍን አበበ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት እንደተናገሩት ሁለቱም ተቋማት ተመሳሳይ ተልዕኮ ያላቸዉ በመሆኑ በጋራ መስራታቸዉ የላቀ ስኬት ማስመዝገብ እንደሚያስችላቸዉ ጠቅሰዉ ዩኒቨርሲቲዉ ለተፈራረመባቸዉ የትኩረት መስኮች ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠዉ አብራርተዋል። አቶ ፍቅሬ ግዛዉ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር በበኩላቸዉ እንደተናገሩት መዲናችን አዲስ አበባን የሚመጥን አገልግሎት ለመስጠት ጊዜዉ የሚጠይቀዉን እዉቀትና ክህሎት መታጠቅ እንደሚያስፈልግ ጠቅሰዉ ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር መስራታችን በምንፈልገዉ ጥራትና ፍጥነት ተልዕኮአችንን መፈጸም ያስችለናል ብለዋል። ዛሬ ፊርማ የተከናወነበት የመግባቢያ ሰነድ ጊዜዉን የዋጀ እንዲሆን በየአምስት አመቱ እንደሚከለስ በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ ተገልጿል። በመርሀ-ግብሩ ማጠናቀቂያ ላይ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ እያከናወናቸዉ ያሉትን የማስፋፋያ ስራዎች፣ የዩኒቨርሲቲዉን ታሪክ የተመለከቱ የመረጃ ማዕከልንና ልዩ ልዩ የስራ ክፍሎችን የኮሚሽኑ አመራሮች እንዲጎበኙ ተደርጓል። ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎት በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ! ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager?is_from_webapp=1&sender_device=pc Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

photo content
+8

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኤሌክትሪክ አገልግሎት ነገ ግንቦት 20 ቀን 2016 ዓ.ም በዋናው ቢሮ፣ በአራቱም ዲስትሪክት ቢሮዎች እና በሁሉም የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት እስከ ቀኑ 11፡00 ድረስ አገልግሎት እንደሚሰጥ አስታውቋል፡፡ በመሆኑም የከተማችን ነዋሪዎች እንደማንኛውም የስራ ቀን በተቋማችን አገልግሎት ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን ሲል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለተገልጋዮች መልእክቱን አስተላልፏል። ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager?is_from_webapp=1&sender_device=pc Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

ለሚ ፎረም በክፍለ ከተማ በድምቀት ተካሄደ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ከወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ጋር በጋራ በመሆን "እኔ የእህቴ የወንድሜ ጠባቂ ነኝ" በሚል መሪ ቃል የለሚ ፎረም ማካሄዱን ገለፀ። በለሚ ፎረም የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ምክትል ወጣት ዘርፍ ሀላፊ፥ የአዲስ አበባ ብልፅግና ፖርቲ ወጣት ሊግ ሀላፊ ፥የሸገር ሲቲ ወጣት ሊግ ተወካዮች ፥የ10ሩም ክፍለ ከተማ የወጣት ሊግ ሀላፊዎችና ተጋባዦች እንዲሁም የለሚ ኩራ ወጣቶች ተሳታፊዎች ነበሩ። በለሚ ፎረም መድረክ ትኩረት ያገኙ ተግባራት 👉በለሚ ውሎ "ፅዱ ኢትዮጵያ "በሚል ርዕስ ላይ ጽሑፍ ቀርቧል 👉የፓናል ውይይት ተካሂዷል 👉በዶ/ር አሸናፊ ኃይሌ በወጣት አመራርና ወንድማማችነት ዙሪያ ስልጠና ተሠቷል። በዚህ የለሚ ፎረም ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን በንግግራቸው ወጣትነት በማስተዋል ብርሃን ደምቆ ችግር የሚፈታ ነው፣ወጣትነት ፍቅር መስበክ በፍቅር መኖር፣ለፍቅር መስዋዕት መሆን ነው ሲሉ ተናግረው ለለውጡ ጉዞ መደራጀትና መፅናት ለኢትዮጵያ ሁለተናዊ ጉዞ የወጣቱ ሚና እጅግ ከፍተኛ ነው ስለዚህ የሀገራችንን ብልፅግና ለማምጣት ትልቅ ሀላፊነት የተጣለው በወጣቱ ነው። በመሆኑም ይህንን ሀላፊነት ለመወጣት ወጣቱ በስነ ልቦና እና በእውቀት መደርጀት አለበት ብለዋል። የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድር አክለው እንዳሉት በሀገራችን ካለው ማህበረሰብ ክፍል ከፍተኛውን ቁጥር የያዘው ወጣቱ ነው። ስለሆነም በሀገራችን ሰፊ ለውጥ ለማጣት በእውቀት የበለፀገ እንዲሁም ዘመኑን የዋጀ ወጣት መፍጠር የሁሉም አካል ሀላፊነት ሊሆን ይገባል ሲሉ ተናግረዋል። በስተመጨረሻም በመድረኩ ተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎች ቀርበው በመድረክ ተወክለው በማወያየት ከፍተኛ ሀላፊነት እየተወጡ ካሉ አካላት የጥያቄ ምላሽ እና አስተያየቶች በበቂ ሁኔታ በመስጠት በክፍለ ከተማው የወጣቶች እና ስፖርት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ዮናስ ጠንክር የማጠቃለያ ንግግር መድረኩ ተጠቃሏል። Lemi Kura Communication ለሚ ኩራ ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager?is_from_webapp=1&sender_device=pc Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

ለሚ ፎረም በክፍለ ከተማ በድምቀት ተካሄደ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ከወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ጋር በጋራ በመሆን "እኔ የእህቴ የወንድሜ ጠባቂ ነኝ" በሚል መሪ ቃል የለሚ ፎረም ማካሄዱን ገለፀ። በለሚ ፎረም የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ምክትል ወጣት ዘርፍ ሀላፊ፥ የአዲስ አበባ ብልፅግና ፖርቲ ወጣት ሊግ ሀላፊ ፥የሸገር ሲቲ ወጣት ሊግ ተወካዮች ፥የ10ሩም ክፍለ ከተማ የወጣት ሊግ ሀላፊዎችና ተጋባዦች እንዲሁም የለሚ ኩራ ወጣቶች ተሳታፊዎች ነበሩ። በለሚ ፎረም መድረክ ትኩረት ያገኙ ተግባራት 👉በለሚ ውሎ "ፅዱ ኢትዮጵያ "በሚል ርዕስ ላይ ጽሑፍ ቀርቧል 👉የፓናል ውይይት ተካሂዷል 👉በዶ/ር አሸናፊ ኃይሌ በወጣት አመራርና ወንድማማችነት ዙሪያ ስልጠና ተሠቷል። በዚህ የለሚ ፎረም ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን በንግግራቸው ወጣትነት በማስተዋል ብርሃን ደምቆ ችግር የሚፈታ ነው፣ወጣትነት ፍቅር መስበክ በፍቅር መኖር፣ለፍቅር መስዋዕት መሆን ነው ሲሉ ተናግረው ለለውጡ ጉዞ መደራጀትና መፅናት ለኢትዮጵያ ሁለተናዊ ጉዞ የወጣቱ ሚና እጅግ ከፍተኛ ነው ስለዚህ የሀገራችንን ብልፅግና ለማምጣት ትልቅ ሀላፊነት የተጣለው በወጣቱ ነው። በመሆኑም ይህንን ሀላፊነት ለመወጣት ወጣቱ በስነ ልቦና እና በእውቀት መደርጀት አለበት ብለዋል። የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድር አክለው እንዳሉት በሀገራችን ካለው ማህበረሰብ ክፍል ከፍተኛውን ቁጥር የያዘው ወጣቱ ነው። ስለሆነም በሀገራችን ሰፊ ለውጥ ለማጣት በእውቀት የበለፀገ እንዲሁም ዘመኑን የዋጀ ወጣት መፍጠር የሁሉም አካል ሀላፊነት ሊሆን ይገባል ሲሉ ተናግረዋል። በስተመጨረሻም በመድረኩ ተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎች ቀርበው በመድረክ ተወክለው በማወያየት ከፍተኛ ሀላፊነት እየተወጡ ካሉ አካላት የጥያቄ ምላሽ እና አስተያየቶች በበቂ ሁኔታ በመስጠት በክፍለ ከተማው የወጣቶች እና ስፖርት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ዮናስ ጠንክር የማጠቃለያ ንግግር መድረኩ ተጠቃሏል። Lemi Kura Communication ለሚ ኩራ ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

የዘንድሮ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራችንን ለአቅመ ደካሞችና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ነዋሪዎች ሶስት ባለ 9 ወለል ህንጻዎችን ልደታ ክፍለ ከተማ ላይ ወደ ግንባታ በማስገባት ጀምረናል። በክረምት
+9
የዘንድሮ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራችንን ለአቅመ ደካሞችና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ነዋሪዎች ሶስት ባለ 9 ወለል ህንጻዎችን ልደታ ክፍለ ከተማ ላይ ወደ ግንባታ በማስገባት ጀምረናል። በክረምት የቤት ግንባታ እና እድሳት ስራችን 3500 ቤቶችን በመገንባት 17 ሺሕ 500 አቅመ ደካሞች እና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የህብረተስብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የምናደርግ ሲሆን፣ በባለፈው የክረምት እና የበጋ የበጎ ፈቃድ ስራችን 6730 ቤቶችን በመገንባት ለነዋሪዎች ማስተላለፍ ችለናል። ካላቸው በማካፈል በዚህ ስራ ላይ የተሳተፉ አካላትን ሁሉ በነዋሪዎቹ ስም በድጋሚ ላመሰግናቸው እወዳለሁ። ዛሬ ያስጀመርናቸውን ሶስት ባለ 9 ወለል ህንጻዎች ከቲኤንቲ ኮንስትራክሽን፣ ኢትዮ ኮቴጅ እና ከአዲስ አበባ ቤቶች ኮርፖሬሽን ጋር በመተባበር የምንገነባ ሲሆን የህብረተሰቡን የኑሮ ጫና ለማቅለል በጀመርነው ስራ ላይ በመሳተፍ ከጎናችን ስለቆሙ በነዋሪዎቻችን ስም አመሰግናቸዋለሁ። በዘንድሮው የክረምት የበጎ ፈቃድ መርሃ ግብራችን 15 ዋና ዋና ፕሮግራሞችን እና 18 መርሃ ግብሮችን በማዘጋጀት ከ1.2 ሚሊዮን በላይ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የምናደርግ ይሆናል። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ኤፍ ኤም 97.1 ጋር በመተባበር የሚያቀርቡላችሁ ሳምንታዊ የሬድዮ ፕሮግራም በክፍል 10 ዝግጅቱ በመዲናችን በጋራ መኖሪያ ቤቶች ለሚኖሩ ነዋሪዎቾ እየተሰጠ ባለ የቅድመ አደጋ መከላከልና መቆጣጠር ግንዛቤና ስልጠና ላይ ትኩረቱን አድርጓል። እንድትከታተሉት ተጋብዛችኋል።

በብልጽግና ፓርቲ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ፖለቲካ ዘርፍ የተዘጋጀ "በነዋሪዎቿ እየፀዳች የምትዋብ ሕብረ ብሔራዊ የነገሰባት አዲስ አበባ!! " በሚል መሪ ቃል ሣምንታዊ የጽዳት
+6
በብልጽግና ፓርቲ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ፖለቲካ ዘርፍ የተዘጋጀ "በነዋሪዎቿ እየፀዳች የምትዋብ ሕብረ ብሔራዊ የነገሰባት አዲስ አበባ!! " በሚል መሪ ቃል ሣምንታዊ የጽዳት ንቅናቄ አካሄዷል ። በጽዳት ዘመቻው ላይ የተገኙት የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በብልጽግና ፓርቲ ምክትል እና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፍራኖል ሞሲሳ በበኩላቸው ህብረተሰቡ ክፍለ ከተማችን ዉብና ጽዱ ለኑሮ አመቺ እንድትሆን የማድረግ ሀላፊነትን መወጣት እንደሚገባ አሳስበው ለመጪው ትውልድ የለመለመች አዲስ አበባን ለማስረከብ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።… See more

photo content
+3

"ኑ በጋራ እናፅዳ አካቢያችንን ውብና ፅዱ እናድርግ" በሚል መልዕክት 5ኛ ወር የበጋ የፅዳት ንቅናቄ መዝጊያ መርሃ-ግብር በወረዳ 10 አስተዳደር ተካሄደ። የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የወረዳ 10 አስተዳደር የ5 ወራት የበጋ ፅዳት ንቅናቄ መዝጊያ መርሃ-ግብር አካሄደ። በንቅናቄ መርሀ-ግብሩ የክ/ከተማው የብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ፋኪያ ሸሪፍ፤ የክ/ከተማው ዋና ስራ አስኪጅ አቶ ማናዬ ጫኔ፤ የወረዳ 10 አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ መኪያ ሁሴን፤ የፅዳት አምባሳደሮችና ነዋሪዎች በተሳተፉበት የ5 ወራት የበጋ የፅዳት ንቅናቄ መዝጊያ መርሃ-ግብር ተካሄዷል። የወረዳ 10 አሰተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ መኪያ ሁሴን በንቅናቄው ተገኝተው እንደተናገሩት ህብረተሰቡ ያለቀስቃሽ በመሳተፍ የአካቢያቸውን ጽዳትና ውበት በመጠበቅ እንደሚገባና ከጽዳት ጉድለት ከሚከሰት የጤና እክል መጠበቅ እንደሚገባ ጠቁመዋል። የክ/ከተማው ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ማናዬ ጫኔ በመርሃ-ግብሩ ንግግር ሲያደርጉ እንደገለጹት ለወረዳው ነዋሪ የቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ዙሪያ በማስገንዘብ በፅዳቱ ንቁ ተሳታፊ ማድረግ እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል። የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ፋኪያ ሸሪፍ በ5 ወር የበጋ የፅዳት ንቅናቄ መዝጊያ መርሃ-ግብር ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ነዋሪው በጽዳት ንቅናቄው በስፋት በመሳተፍ አካባቢውን ብሎም ወረዳውን ሞዴል ማድረግ እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል። Akaki Kality Communication-አቃቂ ቃሊቲ ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

photo content
+6

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 የግንባታ ተረፈ ምርቶችን የማጽዳት ንቅናቄ ተካሄደ። በንቅናቄው ላይ የተገኙት የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አበበ እሸቱ እንደገለጹት አዲስ አበባን ውብና ጽዱ ለማድረግ በሚደረገው እንቅስቃሴ አካባቢን ከቆሻሻ ብቻ ሳይሆን ከተረፈ ምርት ክምችትም ማጽዳት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል። የግንባታ ሥራ በርካታ መጠን ያለው ተረፈ ምርት የሚያመነጭ ዘርፍ መሆኑን ያመለከቱት ኃላፊው፣ በመሆኑም ገንቢዎች ከግንባታ በኋላ ተረፈ ምርትን በአግባቡ በማስወገድ ለአካባቢው ጽዳት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አክለው አስገንዝበዋል። Bole Communication- ቦሌ ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የመስሪያ ቦታዎችን ጽዱህ እንዲሁም ለተገልጋይና ለአገልጋይ ምቹ ለማድረግ የተሰሩት የእድሳት ስራዎችን ጎብኝተናል:: የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን እድሳት ጽዱ፣ ውብ እና
+4
በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የመስሪያ ቦታዎችን ጽዱህ እንዲሁም ለተገልጋይና ለአገልጋይ ምቹ ለማድረግ የተሰሩት የእድሳት ስራዎችን ጎብኝተናል:: የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን እድሳት ጽዱ፣ ውብ እና ለአካባቢው ተጨማሪ ውበትን እንዲሁም ምቹ አካባቢ ለማድረግ የተሰራው ስራ ለሌሎች ሞዴል መሆን የሚችሉ ናቸው:: የተጀመሩ ጥረቶች የሚሳኩት በትብብርና በጋራ ጥረት ስለሆነ የግልም ሆነ የመንግስት መስሪያ ቤቶች በጀመሩት መንገድ አካባቢያቸውን ጽዱህ እና ለኑሮ ምቹ አድርገው ቢሰሩ አዲስ አበባችን ጽዱ፣ ውብ እና እንደ ስሟ አበባ ትሆናለች:: ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት ከአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ኤፍኤም አዲስ 96. 3 ጋር በመተባበር ዘወትር አርብ በመዲናዋ ባሉ ትምህርት ቤቶች በሚከናወነው ጽዳት ዙሪያ የተዘጋጀ የሬድዮ ፕሮግራም እንድትከታተሉት ተጋብዛችሗል። ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

"ትምህርት ቤቴን በፅዳት ተምሳሌት ለማድረግ ቃል እገባለሁ!" በሚል መሪ ቃል የ5 ወር የበጋ የፅዳት ንቅናቄ መርሐግብር ተካሄደ። የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ጽዳት አስተዳደር በደራርቱ ቱሉ ሁለተኛ ደረጃ
+7
"ትምህርት ቤቴን በፅዳት ተምሳሌት ለማድረግ ቃል እገባለሁ!" በሚል መሪ ቃል የ5 ወር የበጋ የፅዳት ንቅናቄ መርሐግብር ተካሄደ። የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ጽዳት አስተዳደር በደራርቱ ቱሉ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት "ትምህርት ቤቴን በፅዳት ተምሳሌት ለማድረግ ቃል እገባለሁ!" በሚል መሪ የ5 ወር የበጋ የፅዳት ንቅናቄ ማጠቃለያ ተካሂዷል። በፅዳት ዘመቻው የክ/ከተማው ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ማናዬ ጫኔ ፣ የክ/ከተማው ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ወንድማገኝ በቀለ ፣ የወረዳ 8 ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ አይናለም ግርማ ፣ መምህራን፣ ተማሪዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል ። የፅዳት መርሀ-ግብሩን ያስጀመሩት የክ/ከማው ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ማናዬ ጫኔ ተማሪዎችና የትምህርት ማህበረሰብ በቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ እንዲሁም በመልሶ መጠቀም ዘዴዎች ላይ የተሻለ ግንዛቤ ይዘው የትምህርት ቤታቸውንና የአካባቢያቸውን ፅዳት በመጠበቅ እና የቆሻሻን ሀብትነት በተግባር በማሳየት ለማህበረሰቡና ለሌሎች ተቋማት አርአያ ሊሆኑ ይገባል ሲሉ ገልፀዋል። ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

photo content