ar
Feedback
Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

الذهاب إلى القناة على Telegram

إظهار المزيد
1 474
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-37 أيام
-2130 أيام
أرشيف المشاركات
በትራፊክ አደጋ የአንድ ሰው ህይወት አለፈ የመንገድ ትራፊክ አደጋው የደረሠው መስከረም 7 ቀን 2018 ዓ/ም ከንጋቱ 12:10 ሠዓት በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው አፍንጮ በር አካባቢ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል። እንደ ፖሊስ ዘገባ የጉዞ አቅጣጫውን ከሽሮ ሜዳ ወደ አፍንጮ በር ያደረገው የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 1-12770 አ/አ ሚኒባስ ታክሲ አፍንጮ በር አካባቢ እየተሠራ ከሚገኘው በግምት 30 ሜትር ከሚሆን የወንዝ ዳር ልማት ፕሮጀክት ውስጥ በመግባት ለጊዜው ዕድሜዋ 22 ዓመት አካባቢ የምትሆን ወጣት ህይወት ያለፈ ሲሆን ሌሎች ተጎጂዎች ለህክምና ርዳታ ወደ የካቲት አስራ ሁለትና አቤት ሆስፒታል ተወስደዋል ብሏል። የአደጋው መንስኤ እየተጣራ እንደሆነ የገለፀው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዝርዝር መረጃዎችን በቀጣይ የሚሠጥም መሆኑንም የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ገልጿል። Addis Ababa Police ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

የመደመር መንግሥት" ! የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) 4ኛው መጽሀፍ ዛሬ ተመረቀ። ክቡር ጠቅላይ ሚንስትራችን በጣም እናመሰግናለን!! "Mootummaa Ida'amuu"! Kitaabni 4ffaan kabajamoo Muummicha Ministeeraa Dr.Abiy Ahimad har'a eebbifame. Kabajamoo Muummicha Ministeeraa keenyaa baay'ee isin galateeffanna.

በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ ሚኪሊላንድ ኮንዶሚኒየም ብሎክ 13 አካባቢ ያጋጠመውን የመሬት መሰንጠቅ በተመለከተ ከአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ በቀጣዩ ቪዲዮ ይከታተሉ👉 👉 ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

በትራፊክ አደጋ የአንድ ሰው ህይወት አለፈ የመንገድ ትራፊክ አደጋው የደረሠው መስከረም 7 ቀን 2018 ዓ/ም ከንጋቱ 12:10 ሠዓት በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው አፍንጮ በር አካባቢ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል። እንደ ፖሊስ ዘገባ የጉዞ አቅጣጫውን ከሽሮ ሜዳ ወደ አፍንጮ በር ያደረገው የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 1-12770 አ/አ ሚኒባስ ታክሲ አፍንጮ በር አካባቢ እየተሠራ ከሚገኘው በግምት 30 ሜትር ከሚሆን የወንዝ ዳር ልማት ፕሮጀክት ውስጥ በመግባት ለጊዜው ዕድሜዋ 22 ዓመት አካባቢ የምትሆን ወጣት ህይወት ያለፈ ሲሆን ሌሎች ተጎጂዎች ለህክምና ርዳታ ወደ የካቲት አስራ ሁለትና አቤት ሆስፒታል ተወስደዋል ብሏል። የአደጋው መንስኤ እየተጣራ እንደሆነ የገለፀው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዝርዝር መረጃዎችን በቀጣይ የሚሠጥም መሆኑንም የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ገልጿል። Addis Ababa Police ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

"የመደመር መንግሥት" ! የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) 4ኛው መጽሀፍ ዛሬ ተመረቀ። ክቡር ጠቅላይ ሚንስትራችን በጣም እናመሰግናለን!! "Mootummaa Ida'amuu"! Kitaabni 4ffaan kabajamoo Muummicha Ministeeraa Dr.Abiy Ahimad har'a eebbifame. Kabajamoo Muummicha Ministeeraa keenyaa baay'ee isin galateeffanna.

በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ ሚኪሊላንድ ኮንዶሚኒየም ብሎክ 13 አካባ… See more

አሁን AMN - 24/7 ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!

በአዲስ አበባ ከተማ ልዩ ስሙ ሚኪሊላንድ ኮንደምንየም እና በአካባቢው ያጋጠመ የመሬት መሰንጠቅ ነዋሪዎችን የአደጋ ስጋት ላይ እንዳይጥል የተለያዩ የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎች እየተሰራ መሆኑን በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ገለፁ። ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ይህን የገለፁት በትናንትናው እለት መስከረም 5/ 2018 ዓ.ም በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ሚኪሊላንድ ኮንደምንዬም፣ ሚኪሊላንድ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት እንዲሁም በወረዳ 14 የሚገኝ ቤተ እምነትና አካባቢው ከክረምቱ ማገባደጃ ወራት ጀምሮ ያጋጠመ የመሬት መሰንጠቅ ተባብሶ በነዋሪዎች ላይ ጉዳት እንዳያስከትል የተሰሩ የቅድመ አደጋ ጥንቃቄዎችን ተዘዋውረው በጎበኙበት ወቅት ነው። ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በዚሁ ወቅት ምንም እንኳን የመሬት መሰንጠቅና መሰል የአደጋ ስጋት ከዚህ ቀደም በዚህ ቦታና አካባቢ ተከስቶ ባያውቅም ከአንድ ወር ወዲህ ግን በአካባቢው ይህን መሰል ስጋት መኖሩ መረጃ እንደተገኘ የከተማ አስተዳደሩ በአፋጣኝ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጂኦሎጅ ትምህርት ክፍል ጋር በመተባበር ጥናት እንዲካሄድ ተደርጓል፣የጥናቱን ውጤትም በዛሬው እለት ይፋ ይደረጋል ሲሉ ተናግረዋል። ምንም እንኳን የአደጋ ስጋቱ መኖሩ ከታወቀ አጭር ጊዜ ቢሆንም ባለፉት ቀናት በሚኪላንድ ኮንደምንዬም ብሎክ 13 ነዋሪዎች የሆኑ 29 አባዎራዎች ማለትም150 በላይ የቤተሰብ አባላትን ከአደጋ ስጋት ነፃ ለማድረግ ከነበሩበት ቦታ የማራቅ ስራ መሠራቱንም የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የእሳትና አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ቅርንጫፍ ሃላፊዎችም አመልክተዋል። ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አያይዘውም ከተማ አስተዳደሩ የመሬት መሰንጠቁ ካጋጠመ ጊዜ አንስቶ ነዋሪዎችን ከአደጋ ስጋት የመታደግ ሰፊ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልፀው የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የጂኦሎጂካል ትምህርት ክፍል የጥናቱን ግኝት መሠረት በማድረግ በሚደረሰው መደምደሚያ እና የመፍትሄ ምክረ ሀሳብ መሰረት አፋጣኝ የመፍትሄ እርምጃ እንደሚወሰድም አረጋግጠዋል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

የከተማችን ነዋሪዎች በመስቀል አደባባይ ለህዳሴዉ ግድብ መጠናቀቅ ባደረጉት የደስታ የድጋፍ ሰልፍ ላይ ክቡር ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ ያደረጉት ንግግር፤… See more

ምስጋና ብሔራዊ ድሉን ላከበረዉ ፣ ብሔራዊ ጀግኖቹን ላመሰገነዉ የከተማችን ነዋሪ በሙሉ ! ዛሬ ማለዳ በከፍተኛ የአገር ፍቅር ስሜትና ድል አድራጊነት በነቂስ ወደ አደባባይ በመትመም ደስታዉን ለገለፀዉ ብሔራዊ ጀግኖቹን ላመሰገነዉ መላዉ የአዲስ አበባ ነዋሪ በሙሉ ምስጋናዬን አቀርባለዉ ! ክቡር ፕሬዝዳንት ታዬ አዝቀስላሴ ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እና ሌሎችም ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ፣ የሀይማኖት አባቶች ፣ የአገር ሽማግሌዎች ፣ የዲፕሎማሲዉ ማህበረሰብ በተገኙበት መላዉ የከተማችን ነዋሪዎች ከመቀነቱ ፈቶ ፣ ካለዉ ቆርሶ ፣ የኑዛዜዉ አካል አድርጎ ፣ ህፃናት ተማሪዎች ሳይቀሩ የከረሜላ መግዣቸዉን ለቦንድ መግዣ አዉለዉ፣ ብዙ አለም አቀፍ ጫና ዉስጥ በደምና አጥንት መስዋትነት ገንብተዉ ለፍፃሜ ያበቁትን የህዳሴ ግድብ ድል በታላቅ ድምቀት አክብረዋል ። መላዉ የከተማችን ነዋሪዎች የሌሊት ቁር የዛሬዉ ከባድ ዶፍ ዝናብ ሳይበግራችሁ የዘመናት ፣የትዉልዶች ትግል ዉጤት የሆነዉ ድላችሁን በጋራ አክብራቹሃል ፣ ለዚህ ድል ከነበራችሁ ደጀንነት አንፃር ይገባቹሀል ! ይህ ድል የኢትዮዽያ የመቻል ማሳያ ፣የአይቀሬዉ ብልፅግናችን ማረጋገጫ ብሔራዊ ምልክት ነዉ። በድጋሚ እንኳን ደስ አለን ! ፈጣሪ ኢትዮዽያንና ሕዝቦቿን ይባርክ ! ከንቲባ አዳነች አቤቤ