ar
Feedback
Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

الذهاب إلى القناة على Telegram

إظهار المزيد
1 474
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-37 أيام
-2130 أيام
أرشيف المشاركات
ዛሬ ማለዳ የህዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅን በማስመልከት በመስቀል አደባባይ በተካሄደው የደስታ፣ የድጋፍ እና የምስጋና መግለጫ ሰልፍ ላይ ያደረኩት ንግግር፤… See more

የህዳሴ ግድብ መጠናቀቅን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ በተካሄደው ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ላይ የተካፈሉ ከፍተኛ የፌደራልና ከተማ አስተዳደር የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ዲፕሎማቶች ፣ የሃይማኖት አባቶች ፣ አባገዳዎች ፣ የአገር ሽማግሌዎች እና የመዲናዋ ነዋሪዎች - በምስል በከፊል :- #ኢትዮጵያ ችላለች #GERD #Ethiopia #addisababa

የዛሬዉ የማለዳዉ ከባድ ዝናብ ያልበገረዉ የአዲስ አበባ ህዝብ ለህዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅ ካደረገዉ ድጋፍ ሰልፍ ድባብ በጥቂቱ #ኢትዮጵያ ችላለች #GERD #addisababa

ከባድ ዝናብ ያልበገረዉ የአዲስ አበባ ህዝብ በህዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅ የተሰማውን ደስታ ለመግለጽ ዛሬ ያካሄደው የድጋፍ ሰልፍ ድባብ በከፊል፤… See more

ለኢትዮጵያ የብሩህ ተስፋ ቀንዲል ለሆነው የሕዳሴ ግድብ በድል መጠናቀቅ እንኳን አደረሳችሁ” ከንቲባ አዳነች አቤቤ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናቅቆ መመረቁን አስመልክቶ “ኢትዮጵያ ችላለች!” በሚል መሪ በአዲስ አበባ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል። በድጋፍ ሰልፉ ላይ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ “ለኢትዮጵያ የብሩህ ተስፋ ቀንዲል፣ የታሪካችን እውነተኛ እጥፋት፣ የማንሰራራት ድንቅ መሠረት ለሆነው ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ታሪካዊ እና ሕዝባዊ ድል እንኳን አደረሰን፣ እንኳን አደረሳችሁ! ሲሉ የደስታ መልዕክት አስተላልፈዋል። የአዲስ አበባ ሕዝብ ከሕፃን እስከ አዋቂ፣ ከደሃ እስከ ሀብታም፣ ከተማሪ እስከ ምሁር፣ ከሕዝብ እስከ መሪ በአንድ ድምፅ፣ በአንድ አቋም፣ በኅብረብሔራዊ አንድነት በደማቁ ለተጻፈው እና ለማይደበዝዘው ደማቅ አሻራ መቀነታችንን እና ቀበቶአችንን አጥብቀን ከእለት ጉርሳችን በላባችን፣ በደማችን ጭምር የገነባነው የወል ስኬታችን፣ የድል ብስራታችን ለሆነው ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ በአብሮነት ደስታችንን ለመግለጽ እና ለጀግናው እና ለማይበገረው ሕዝባችን ምስጋና ለማቅረብ በመስቀል አደባባይ ተገናኝተናል ብለዋል። #ኢትዮጵያ ችላለች #GERD #Ethiopia #addisababa ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

ገነባነው! ጨረስነው! አስመረቅነው”!! ከንቲባ አዳነች አቤቤ #Ethiopia #GERD

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናቅቆ መመረቁን አስመልክቶ “ኢትዮጵያ ችላለች!” በሚል መሪ ቃል ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀሥላሴ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ታላቅ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በአዲስ አበባ በመስቀል አደባባይ እየተካሄደ ይገኛል። #GERD #Ethiopia

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅን በማስመልከት በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ያለ ትዕይንተ ህዝብ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅን በማስመልከት በአዲስ አበባ በተካሄደ የድጋፍ ሰልፍ ላይ ያስተላለፉት መልዕክ… See more

ኢትዮዽያ ችላለች ! ኢትዮዽያ የድል አድራጊዎች ፣ የአሸናፊዎች ምድር ! መላዉ አዲስ አበባ ለዳግማዊዉ የአድዋ ታላቅ ድል ክብር ከሌሊት አንስቶ ወደ መስቀል አደባባይ በከፍተኛ የድል አድራጊነት ስሜት በነቂስ እየተመመ ይገኛል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ #ሕዳሴ #GERD #Ethiopia #AddisAbaba.