Addis Ababa City Manager Office
الذهاب إلى القناة على Telegram
إظهار المزيد
1 474
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-37 أيام
-2130 أيام
أرشيف المشاركات
በአጭር ጊዜ ፤ በከፍተኛ ጥራት የተገነቡ ፕሮጀክቶች የብልፅግና ፓርቲን የመፈፀምና ጀምሮ የማጠናቀቅ አቅም ማሳያዎች ናቸዉ!!
የብልፅግና ፓርቲ በህዝብ ቅቡልነት አግኝቶና በዲሞክራሲያዊ ምርጫ አሸንፎ ሀገሪቱን ማስተዳደር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ፓለቲካዊ ዘርፎች በርካታ ውጤቶችን ማስመዝገብ ችሏል።
የብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ በከተማው ከሚገኙ የተለያዩ ክ/ከተሞች የተውጣጡ የፓርቲው አባላትና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተለያዩ ክ/ከተማዎች ዉስጥ ባለፉት 5 የለውጥ ዓመታት የተከናወኑ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶችን ተዟዙረው እየጎበኙ ነው!!
የከተማዋን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ከፍ ለማድረግ የአደጋ መከላከል አቅምን ማሳደግ እንደሚገባ ተገለጸ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የቂርቆስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ያስገነባዉ ሁሉን አቀፍ አገልግሎት የሚሰጥ ዘመናዊ ህንጻ የከተማዉ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም ተመርቋል።
በምርቃት ስነ ስርዓቱ በክብር እንግድነት የተገኙት በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ እንደተናገሩት በለዉጥ ላይ የምትገኘዉ አዲስ አበባ ከተማ ዓለም አቀፍ ተወዳሪነቷን ከፍ ለማድረግ ከተማዋን የሚመጥን የአደጋ መከላከል አቅምን ማሳደግ እንደሚገባ አስታዉሰዉ የከተማ አስተዳደሩም የኮሚሽን መ/ቤቱን አቅም ለማሳደግ የሪፎርም ስራዎች አቅዶ ወደተግባር መግባቱንም አስታዉቀዋል።
ኢንጂነር ወንድሙ አያይዘዉም ዛሬ ለምረቃት የበቃዉ የቂርቆስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤትም የዚሁ ሪፎርም አካል እንደሆነ ገልጸዉ የኮሚሽን መ/ቤቱን የተደራሽነት አቅሙን ከፍ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ እንደሆነም ተናግረዋል።
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍቅሬ ግዛዉ በበኩላቸዉ እንደተናገሩት ዛሬ ለምረቃ የበቃዉ የቂርቆስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ህንጻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለሚሰጠዉ ሁሉን አቀፍ አገልግሎቶች ከፍተኛ አስተዋጾኦ እንደሚያደርግ አብራርተዉ ህንጻዉ ተገንብቶ ለአገልግሎት እንዲበቃ ላደረገዉ የከተማ አስተዳደር ምስጋናቸዉን አቅርበዋል።
በመርሀ ግብሩ ላይ እጩ ዶክተር አዲሱ ሻንቆ የቂርቆስ ክፍለ-ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚና የኮሚሽኑ አመራሮች ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች ተገኝተዋል።
ለእሳትና ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!
የብልጽግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ ዛሬ ማለዳ በከተማ ደረጃ የፅዳት መርሃ ግብር አከናውነናል።
ከተማችንን እና አካባቢያችንን ለመኖር ምቹ እና ጽዱ ለማድረግ የጀመርነው ስራ ፍሬ አፍርቶ አዲስ አበባን ፅዱ ማድረግ የቻልን ሲሆን በቀጣይም የጸዳውን አካባቢ መንከባከብና መጠበቅን እንዲሁም ፅዳትን ባህል በማድረግ በዘላቂነት አካባቢያችንን እንድናጸዳ ጥሪ አቀርባለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ”ህዳር ሲጸዳ” በሚል መሪ ቃል የጽዳት ስራ አከናወነ።
የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ”ህዳር ሲጸዳ” በሚል መሪ ቃል የከተማ፣ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች፣ የጸጥታ አካላትና የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች የተሳተፉበት የማጠቃለያ የጽዳት ስራ አከናውኗል ።
አቶ ማሾ ኦላና በሳምንቱ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የጽዳት ስራ ሲከናወን የቆየበትና የከተማን የጽዳት ገጽታ መቀየር ያስቻለ ልምድ የተገኘበት እንዲሁም የጽዳት ስራ የነዋሪው የእለት ተእለት ተግባር መሆን የቻለበት ሁኔታ ሊፈጠር ችሏል ብለዋል፡፡
አክለውም የዛሬውን የጽዳት ማጠቃለያ ስራ የብልጽግና ፓርቲ 5ኛ አመት የምስረታ በአል እየተከበረ ባለበት ጊዜ መሆኑና በአሉን በስራ እያሳለፍን መሆኑ ለየት ያደርገዋል ብለዋል፡፡
ባለፉት 5 አመታት ውስጥ በ30 አመታት ሊከናወኑ ያልቻሉ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸው የሰው ልጆች የክብር፣ የእኩልነትና የነጻነት ፍላጎትን በዘላቂነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ትሩፋትና ለውጦችን ማምጣት መቻሉን ገልጸዋል፡፡
በ”ህዳር ሲጸዳ” የጽዳት ዘመቻ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአራዳ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጌታሁን አበራ የጽዳት ስራ የኔ ጉዳይ ነው ተብሎ በማሰብ ጽዱ አካባቢና መንደር መፍጠር መለያችን ማድረግን አለብን ብለዋል፡፡
በኮሪደር ልማት እየተሰሩ ላሉ የልማት ስራዎች ትኩረት በመስጠት ንጽህናቸውንና ውበታቸውን እንደጠበቁ ለታለመላቸው አላማ እንዲውሉ ማድረግ እንደሚያስፈልግም አቶ ጌታሁን አክለዋል፡፡
የአራዳ ክ/ከተማ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ማስተባበሪያ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተወዳጅ ኃ/ማርያም በበኩላቸው የብልጽግና ፓርቲን 5ኛ አመት የምስረታ በአል ስናከብር በሀሳብ የጸዳ በተግባርም ጽዳት ያለው ስራ ለህዝብ ማድረስና ማገልገል እንደሚቻል በመረዳት ከማንኛውም ጥላቻና አብሮነትን ከሚሸረሽር አስተሳሰብና ተግባር መራቅ ይኖርብናል ብለዋል፡፡
በፀዳች ከተማ ስንኖር የጸዳ አስተሳሰብ በመያዝ በጋራና በአንድነት መኖር ይገባል ያሉት አቶ ተወዳጅ ፓርቲያችን በገባው ቃል መሰረት ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉና የከተማችንን ገጽታ ወደተሻለ ደረጃ ከፍ ያደረጉ ስራዎች የተሰሩ ሲሆን በሀገር አቀፍ ደረጃም ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እምርታዎች ማስመዝገብ ተችሏል ብለዋል፡፡
የሀሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልፅግና!!!
"ቆሻሻን ማቃጠል ይብቃ፤ ቆሻሻን በማቃጠል አካባቢዬን አልበክልም " በሚል መሪ ቃል ታላቅ የፅዳት ዘመቻ ተካሄደ።
የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ "ቆሻሻን ማቃጠል ይብቃ " በሚል መሪ ቃል ታላቅ የፅዳት ዘመቻ ንቅናቄ ልዩ ቦታዉ ማሰልጠኛ አደባባይ አካባቢ አካሂዷል።
በጽዳት ዘመቻው ላይ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ፍትህ ቢሮ ሀላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ ከለውጡ በፊት ከተማዋ የማይመጥን ሁኔታ ዉስጥ የነበረች ነገር ግን ብልፅግና ፓርቲ በሀገሪቱና በከተማዋ ሁለንተናዊ እድገት ላይ በሰራው ስራ ከተማዋ እንደ ስምዋ ውብና ፅዱ የዲፕሎማሲ መናሀሪያ እየሆነች እንደምትገኝ ጠቅሰው ማህበረሰቡ ቆሻሻን በአግባቡ በመሰብሰብና መልሶ በመጠቀም አካባቢን ንፁህ ማድረግ እንደሚገባው ተናግረዋል ።
የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና ብልፅግና ፓርቲ ባለፉት 5 ዓመታት ሀገሪቱ ገብታበት ከነበረችው የችግር አረንቋ ስቦ በማውጣት በማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ፓለቲካዊ ዘርፎች በርካታ የሚታዩ ስራዎችን በመስራት የህዝቡን ተጠቃሚነት እያረጋገጠና ወደ ብልፅግና ማማ ከፍ እያደረገ እንደሚገኝና ሰው ተኮር ፓርቲ ነው ያሉ ሲሆን በኮሪደር ልማትና ልዩ ልዩ ፕሮጀክቶች ከተማዋን ውብ ፣ ፅዱ ፣ለነዋሪዎችዋ ምቹና ተወዳዳሪ ለማድረግ እያከናወነ በሚገኘው የልማት ስራ ማህበረሰቡ በፅዳት ስራ ላይ ንቁ ተሳታፊ ሊሆን እንደሚገባ ተናግረዋል።
በመጨረሻም በአስተዳደሩ ወረዳ 8 የሚገኘዉ በፅዳትና ዉበት በነዋሪዎች ፅዱና ዉብ የሆነች ጃቴ ሞዴል ብሎክ 1 ተጎብኝቷል።
"የሀሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልፅግና "
የብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት ምስረታን ምክንያት በማድረግ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የፅዳት ዘመቻ ተካሔደ።
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት ምስረታን ምክንያት በማድረግ ለተከታታይ 6 ቀናት ሲያካሔድ የነበረውን የፅዳት ዘመቻ በዛሬው እለት የማጠቃለያ የፅዳት ንቅናቄ አካሔዷል።
በንቅናቄ መርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ ክብርት ወ/ሪት ፋይዛ መሀመድ ከተማችን አዲስ አበባ ፅዱ ውብና ከአፍሪካ ከተሞች አምራና ደምቃ እየታየች ትገኛለች ሲሉ የገለፁ ሲሆን ለዚህም በከተማው እየተሰራ ያለው የኮሪደር ልማት የከተማውን ገፅታ በመቀየር ሚናው ላቅ ያለ እንደሆነ ተናግረዋል።
ክብርት ምክትል አፈጉባዋ አክለውም ብልፅግና ፓርቲ በምርጫ ወቅት ቃል የገባውን በመፈፀም ተጨባጭ ውጤት እያመጣ ይገኛልም ሲሉ ገልፀዋል።
አቶ ንጋቱ ዳኛቸው የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ለውጡን ተከትሎ መሰረታዊ የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄዎችን በመፍታት የተቻለ እንደሆነ ያስገነዘቡ ሲሆን በተለይም በሰው ተኮር ስራዎችና ትላልቅ ፕሮጀክቶችን በመገንባት እምርታዊ ውጤት መታየቱን ጠቁመዋል።
ዋና ስራ አስፈፃሚው አክለው ጤናው የተጠበቀ አካባቢና ፅዱና ውብ ከማድረግ አኳያ በኮሪደር ልማት ፣ በአረንጓዴ አሻራ፣በተለያዩ የመዝናኛ ቦታዎች ግንባታዎች ከተማችን አዲስ አበባ ማራኪና የቱሪስት መዳረሻ እንድትሆን እንዳደረጋት ገልፀዋል።
ህዳር ሲፀዳ" በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት ምስረታን አስመልክቶ የፅዳት ዘመቻ ንቅናቄ ተካሄደ።
በፅዳት ፕሮግራሙ ላይ ንግግር ያደረጉት የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አይዳ አወል ባለፉት አምስት አመታት ከተማችን ውብ፣ ፅዱ እና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል ያሉ ሲሆን ነዋሪው ያለማቋረጥ አካባቢውን ከተማውን በማፅዳት ፅዳት ባህል እንዲያደርግ የተሰራው ስራ አንዱ ነው በዚህም የነዋሪዎቻችን የፅዳት አስተዳደር ሰራተኞችና የባለድርሻ አካላት ድርሻ የላቀ ነበር ሲሉ ገልፀዋል።
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሙስጠፋ ትኪ በበኩላቸው የዛሬው የፅዳት ዘመቻ የፓርቲያችንን 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል እያከበርን ባለበት ወቅት መሆኑ ለየት ያደርገዋል ብለው ውብና ፅዱ የሆነች አዲስ አበባ ለመገንባት እየሰራን እንገኛለን ሲሉ ተናግረዋል::
በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በወረዳ 11 ፊሊፖስ ቤተክርስትያን አካባቢ በተካሄደው የፅዳት ዘመቻ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህብረት ስራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ፣ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።
በመጨረሻም በፅዳት ዘመቻው የተሳተፉ በሙሉ ሞዴል ብሎኮችን ጎብኝተዋል::
በጋራ አካባቢያችንን በማፅዳት ውብ፣ ፅዱ እና ለመኖሪያ ምቹ አዲስ አበባን ለመፍጠር እንሰራለን! አቶ ጃንጥራር አባይ
የብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን አስመልክቶ “ህዳር ሲፀዳ” በሚል መሪ ቃል በየካ ክፍለ ከተማ የፅዳት ዘመቻ ተካሂዷል።
በመርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢዱስትሪ ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ እንደገለፁት በጋራ አካባቢያችን በማፅዳት ውብ፣ ፅዱ፤ ምቹ አዲስ አበባን ለመፍጠር ሁሉም ነዋሪ አካባቢውን ከማፅዳት በሻገር ቆሻሻን በአግባቡ በመለየት የድርሻችን እንወጣ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የነዋሪዎቻችን ጤና ለመጠበቅ ፅዳትን ባህል በማድረግ እና ውብና ማራኪ አካባቢን መፍጠር እንደሚገባ አቶ ጃንጥራር አባይ አሳስበዋል።
የየካ ክፍለ ከተማ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ መገርሳ ገላና በበኩላቸው ፅዳት የከተሜነት መገለጫ በመሆኑ ሁሉም ሰው አካባቢውን ማፅዳት እንደሚገባ ተናግረዋል።
የፅዳት ዘመቻው የብልጽግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ በየካ ወረዳ 11 የተካሄደ ሲሆን የከተማ፣የክፍለ ከተማ፣ የወረዳ አመራሮች እና ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
ከተማችንን እና አካባቢያችንን ለመኖር ምቹ እና ጽዱ ለማድረግ ፅዳትን ባህል ማድረግ እንደሚገባ መልዕክት ተላልፏል።
ህዳር ሲታጠን" አመለካከትን ወደ "ህዳር ሲጸዳ " በመቀየር ጽዳት ባህል የሚያደርግ ህብረተሰብ መገንባት እንደሚገባ ተገለጸ።
በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በማስመልከት ለተከታታይ 10 ቀናት በ10ሩም ወረዳ በሚገኙ ብሎኮች ሲካሄድ የነበረው የፅዳት ንቅናቄ ተጠናቋል።
በጽዳት ንቅናቄው ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ጀማሉ ጀምበር እንደተናገሩት የከተማው አስተዳደር አዲስ አበባን እንደ ስሟ አዲስ እና ውብ ለማድረግ ከሌሎች የአለም ከተሞች ተወዳዳሪ እንድትሆን ነዋሪዎቿ አካባቢያቸውንና ጤንነታቸው የተጠበቀ በአስተሳሰብ የበለፀጉ በኢኮኖሚ ያደጉ እንዲሆኑ በትኩረት እየሰራ ይገኛል በመሆኑም በፅዳት ዙሪያ ላይ የሚከሰት ህገወጥነትን ለመከላከል የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ ተሳትፎ የሚጠይቅ ተግባር በመሆኑ ሁሉም አካል በጋራ ለአካባቢ ፅዳት መቆም እንደሚገባ ገልጸዋል።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ በበኩላቸው ህዳር ሲታጠን በሚል በባህላዊ መንገድ ቆሻሻ ተሰብስቦ ይቃጠል ነበር አሁን ማጠኑን በማስቀረት ወደ ማጽዳት ዘመቻ እየሔድን ነው፤ ምክንያቱም ቆሻሻን ማቃጠል ለአካባቢ አየር ብክለት ፣ ለመተንፈሻ አካል በሽታና ለኦዞን መሳሳት ያጋልጣል በመሆኑም በዋናነት መልሶ መጠቀምን በማበረታት ቆሻሻን ጥቅም ላይ እንዲውል አበክሮ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።
በክፍለ ከተማችን የጽዳትና ውበት ተምሳሌት ለማድረግ የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ቅንጅት የሚጠይቅ ነው በመሆኑም ህብረተሰቡ ላይ የግንዛቤ መፍጠር ስራዎችን በማጠናከር የጽዳት ንቅናቄ ስራዎችን በማጠናከር ጉለሌን የጽዳት ተምሳሌት እንድትሆን በትጋት እንሰራለን ብለዋል።
በንቅናቄው የተሻለ አፈፃፀም ለነበራቸው ወረዳዎች ተቋማትና ግለሰቦች የዋንጫ እውቅና ተበርክቶላቸዋል ።
