ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

الذهاب إلى القناة على Telegram

إظهار المزيد
1 474
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-37 أيام
-2130 أيام
أرشيف المشاركات
ዓመታዊው የ “ኅዳር ሲጸዳ” እና የብልጽግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት በዓል የጽዳት ንቅናቄ ማጠቃለያ በቦሌ ክፍለ ከተማ ተካሄደ፡፡ በታይዋን ሰፈር በተካሄደው የፅዳት ዘመቻ መርሐ ግብር ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር አቶሜ አበበ ባደረጉት ንግግር ጽዳት የሥልጣኔ መገለጫ በመሆኑ ኅብረተሰቡ የጽዳት ሥራን በባለቤትነት በመያዝ አካባቢውን ጽዱ ማድረግ እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡ “ያደጉ ሀገራት የመሰልጠን አንዱ ምክንያት ለጽዳት የሚሰጡት ትኩረት ነው” ያሉት ዶ/ር አቶሜ፣ በመሆኑም ከለውጥ ማግሥት ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረትና በአዲስ አበባ ከተማ ጽዱ አካባቢዎችን ለመፍጠር በተከናወኑ ተግባራት የቦሌ ክፍለ ከተማ እያከናወነ የሚገኘውን ውጤታማ ሥራ ከንቅናቄ ባሻገር ማጠናከር እንዳለበት አክለው አሳስበዋል፡፡ የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ዓለምጸሐይ ሺፈራው በበኩላቸው በክፍለ ከተማው ከሚገኙ 472 ብሎኮች መካከል በ2016 በጀት ዓመት 233 ብሎኮችን ሞዴል ለማድረግ መቻሉን ገልጸው፣ በብልጽግና ፓርቲ መሪነት ጽዱና ውብ አዲስ አበባን ለመፍጠር እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ ተጨባጭ ውጤቶችን እያስመዘገበና ኅብረተሰቡን ተሳታፊና ተጠቃሚነቱ እያደገ መምጣቱን አመልክተዋል፡፡ የክፍለ ከተማው ነዋሪዎችና የጽዳት ባለድርሻ አካላት ቦሌን ውብ፣ ጽዱና ተመራጭ ለማድረግ እያደረጉ ላለው የነቃ ተሳትፎ ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

photo content
+3

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን በማስመልከት "ህዳር ሲፀዳ" በሚል መሪ ሀሳብ የፅዳት ንቅናቄ ተካሂዷል። በዕለቱም የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ፣ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ካባ መብራቱ ጨምሮ ሌሎች የከተማ፣ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች፣ የፀጥታ አካላትና ነዋሪዎች ተገኝተዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ የብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት ምስረታ በዓልን ስናከብር ፓርቲው ያመጣውን ፅዱ አካባቢ ላይ መስራትና መኖርን የመሳሰሉ የተለወጡ እሳቤዎችን በማውሳት ሊሆን ይገባል ብለዋል:: በዓሉን ስናከብር ቆሻሻን በማፅዳት ብቻ ሳይሆን የውስጥ ጥላቻንም በማስውገድና አገልግሎት አሰጣጡን ከብልሽት በማፅዳትና የበለጠ በማዘመንና በማቀላጠፍ ሊሆን እንደሚገባ ተናግረዋል። አቶ ቢኒያም አክለውም አዲስ አበባ ፅዱና ውብ ለነዋሪዎቿ የምትመችና የብልፅግና ማሳያና ተምሳሌት እንድትሆን እየተሰሩ ካሉ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች ጎንለጎን ፅዳትን ባህሉ ያደረገ ማህበረሰብ መፍጠር እየተቻለ መሆኑን ተናግረዋል። የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ካባ መብራቱ የብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት ምስረታ በዓልን በማስመልከት በህዳር ወር ከብሎክ ጀምሮ በሁሉም ወረዳዎች በየዕለቱ ፅዳት ሲደረግ የነበረ መሆኑን አንስተዋል። ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ጨምረው እንዳሉት ቆሻሻ ሲቃጠል የአየር ብክለትና የጤና እክል ሊፈጥር እንደሚችል ጠቁመው መልሶ መጠቀምና ወደ ሀብትነት መቀየር የጎላ ፋይዳ እንዳለው ገልፀዋል። በመሆኑም ህዳር ሲታጠን የሚለው ትርክት ወደ ህዳር ሲፀዳ ወይም ህዳርን በፅዳት በሚል መተካት አለበት ብለዋል የፅዳት ዘመቻው በክ/ከተማ ባሉ 13ቱም ወረዳዎች ተካሄዷል::

የብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን አስመልክቶ "ህዳር ሲፀዳ " በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የቆየው የፅዳት ዘመቻ ንቅናቄ የማጠቃለያ መርሀ ግብር ተካሄደ።

photo content
+4

የብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን አስመልክቶ "ህዳር ሲፀዳ " በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የቆየው የፅዳት ዘመቻ ንቅናቄ የማጠቃለያ መርሀ ግብር ተካሄደ። የልደታ ክፍለ ከተማ "የሀሳብ ልዕልና ለሁለተናዊ ብልፅግና" በሚል መሪቃል የብልፅግና 5ኛ አመት የምስረታ ክብረ በዓል አስመልክቶ "በህዳር ሲፀዳ" መሪ ቃል ሲካሄድ የነበረው የፅዳት ዘመቻ መርሀ ግብር የማጠቃለያ መርሃ ግብር ተካሄደ። በጽዳት ዘመቻው የከተማ ከፍተኛ አመራሮች የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮ የጽዳት አንባሳደር አርቲስቶች በተገኙበት የፅዳት ዘመቻ ተደርጓል። በጽዳት ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተዉ መልዕክት ያስተላለፉት በም/ ከንቲባ ማዕረግ የአ/አ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ እንደተናገሩት አዲስ አበባን ፅዱና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን በዚህ ላይ ሁሉም ነዋሪ ሀላፊነቱን በመወጣት ከተማችንን በማልማትና ከማንኛውም ቆሻሻ ጽዱ የሆነ አካባቢን መፍጠር ያስፈልጋል በማለት ገልፀዋል ። ኢንጂነር ወንድሙ አክለው ከተማችን ለነዋሪዎቿ ምቹ ጽዱ ለማድረግ እየተጉ ያሉ የፅዳት ሰራተኞች በማመስገን በጋራ የምንሰራው ስራ ሀገር እየገነባን ነው ሲሉ ገልፀዋል የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ እሸቴ በፕሮግራም ማስጀመሪያ እንደተናገሩት በልደታ ክፍለ ከተማ 4 ወረዳዎች ከዚህ በፊት በተሰሩ ስራዎች ሞዴል በማድረግ ለተለያዪ ከተሞች ተሞክሮ በማካፈል የምትገኝ ሲሆን በተያዘው በጀት ዓመት ሁሉም ወረዳዎችን ሞዴልና ፅዱ እናደርጋለን በማለት ገልፀዋል ወ/ሮ አበባ እሸቴ አክለው ሁሉም የክ/ከተማ ነዋሪዎቻችንን በማሳተፍ አካባቢዉን የማጽዳት ተግባር በየጊዜው አየተሰራ የሚገኝና ተጠናክሮ የሚቀጥል ተግባር ነው በማለት ገልፀዋል፡፡ በፅዳት ዘመቻው ላይ የፅዳት አባሳደር አርቲስቶች በመጋበዝ አካባቢያችንን የምናፀዳው ህዳርን ጠብቀን ሳይሆን የእለት ተእለት ተግባራችን መሆን አለበት በማለት ገልፀዋል።

photo content
+6

ከአዲስ አበባ ከተማ ውጪ ደረቅ ቆሻሻ በመኪና ጭነው ያስገቡ ግለሰቦች 300,000 ብር መቀጣታቸው ተገለፀ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ከአዲስ አበባ ከተማ ውጪ ደረቅ ቆሻሻን ወደ ከተማዋ በመኪና ጭነው በማስገባት ባልተፈቀደ ቦታ የጣሉ ግለሰቦች በገንዘብ መቅጣቱ አስታወቀ። ግለሰቦቹ ከነ ተሽከርካሪአቸው በቁጥጥር ስር በማዋል በባለስልጣኑ በተሻሻለዉ የቅጣት ሰንጠረዥ 2 ደንብ ቁጥር 167/2016 ተራ ቁጥር 31.2 መሰረት እያንዳንዳቸው 100,000 /መቶ ሺህ/ ብር በድምሩ 300,000/ሦስት መቶ ሺህ/ ብር መቀጣታቸው የወረዳው ደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ሃላፊ ሻለቃ ዋጋዬ አቶምሳ ገልፀዋል። አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከተማዋ ውብ፣ጽዱ እና ማራኪ ለማድረግ ቀን ከሊሊት እየሰራ ባለበት ሰዓት የአካባቢ ውበቱ ሆን ብለዉ የሚያበላሹ ግድ የለሽ ግለሠቦችን አስተማሪ ቅጣት እየቀጣ መሆኑ ባለስልጣኑ አስታውቋል። ባለስልጣኑ የደንብ መተላለፉን የፈፀሙ ግለሰቦች ተጠያቂ እንዲሆኑ መረጃውን ለሰጡትና እገዛ ላደረጉ የከተማዉን ነዋሪዎች እያመሰገነ በቀጣይም ሁሉም የከተማው ነዋሪዎች ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች በ9995 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲሰጡ ጥሪውን ያቀርባል። መረጃው፦የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው ። ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

photo content
+5

በከያኒት ዓለም ፀሐይ ወዳጆ በመታደስ ላይ የሚገኘውን የቢትወደድ ኃ/ጊዮርጊስ ኃ/ሚካኤል የቀድሞ መኖሪያ ቤት፣ የመጀመሪያው የማዘጋጃ ቤት፣ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት፣ ከ119 ዓመታት በፊት የተገነባውን እና ለእቴጌ ጣይቱ የባህልና ትምህርት ማዕከል ሆኖ የሚያገለግል የቅርስ ቤት እድሳት ጎብኝተናል። ከያኒት ዓለም ፀሐይ እያደረገች ላለችው ተምሳሌታዊ ሥራ እያመሰገንኩ አብዛኛውን እድሳት በጥሩ ሁኔታ በመስራት ላይ የምትገኝ ሲሆን ቀሪ ስራዎችን ደግፈን በተሻለ ሁኔታ ለቱሪስት መስህብነት እና ለታለመለት አላማ እንዲውል እናደርጋለን:: ትናንት ወረት መሆን የሚችሉትን ከዛሬ ጋር በማስማማት ለነገ እንዲተላለፍ በማለት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን በቤተ መንግስት እና በመላዉ ሀገራችን ያሉትን በማልማት እና በሀገራችን ያሉ ቅርሶች በተገቢው መንገድ በማደስ ባስጀመሩን መሰረት እንደ አዲስ አበባ ጥንታዊ ቅርሶችን ከዛሬ ጋር በማስተሳሰር ለነገ ለማሻገር እድሳት የሚፈልጉት እድሳት በማድረግና በማዘመን ለቱሪዝም ስበት በሚያገለግል መልኩ በማስተዋወቅ፣ ሀብት ለማፍራት እንዲሁም ለትውልድ እንዲተላለፍ ተገቢውን ትኩረት ሰጥተን ከአራት ኪሎ እስከ ፒያሳ የሚገኙ ቅርሶችን በአዲስ መንገድ በልዩ ሁኔታ በኮሪደር ልማት ስራችን አድሰናል:: ማደስ፣ ማዘመን፣ ማስተዋወቅ፣ ቱሪዝምን በመጠቀም ሀብት መፍጠር እንዲሁም ትውልድ እንዲማርበት ማቆየት ተገቢ ሲሆን ያረጀ እና አሮጌው ሁሉ ቅርስ ባለመሆኑ ፈርሶ ዘመኑን በሚዋጅ ደረጃ ማልማት አስፈላጊ ነዉ:: ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

photo content
+6

መዲናችን አዲስ አበባ በፈጣን የልማት እድገት ላይ እንደምትገኝ የአፍሪካ ሀገራት ከተሞችን የዕድገት ደረጃ የሚገልጸው ኢኮኖሚስት ኢንተለጀንስ ዩኒት አስታውቋል። የአፍሪካ ሀገራት ከተሞች የዕድገት ደረጃ በ2024 ባወጣው ሪፖርት የኢትዮጵያ ዋና ከተማ የሆነችው አዲስ አበባ በፈጣን ዕድገት ላይ የምትገኘ ከተማ መሆኗን ባወጣው ሪፖርት አመላክቷል ። አዲስ አበባ ባለፊት ዓመታት በከተማዋ የተሰሩ የልማት ስራዎች እና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ከተማዋን በፈጣን እድገት ላይ እንደምትገኝ መረጃዎች ያሳያሉ። በዚህም በከተሞች ዕድገት አዲስ አበባ አሁን ካለችበት ከ12ኛ ደረጃ በ2035 6ተኛ ደረጃን እንደምትይዝ ከወዲሁ ሪፖርቱ አመላክቷል፡፡

የፀጥታ መዋቅራችን በጉለሌ ክፍለ ከተማ የህዳር ሲፀዳ ንቅናቄ ላይ ያደረገው ተሳትፎ :- ቀጣዪን ቪዲዮ ይመልከቱ!…

photo content
+9

የጸጥታ መዋቅሩ "ህዳር ሲታጠንን ወደ ህዳር ሲጸዳ !! " በሚል መሪ ቃል የጽዳት ዘመቻ አካሄደ። በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር "ህዳር ሲታጠንን ወደ ህዳር ሲጸዳ !! " በሚል መሪ ቃል በ10ሩም ወረዳ በሚገኙ ብሎኮች የጽዳት በማድረግ የጸጥታ መዋቅሮች የተሳተፉበት የጽዳት ንቅናቄ ተካሄዷል። በጽዳት ዘመቻው ላይ የተገኙት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ደረጀ እንደተናገሩት የጸጥታ መዋቅሩ ከነዋሪው ጋር በመተባበር የአካባቢውን ሰላምና ጸጥታ ከማስጠበቅ ባሻገር ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በርካታ ተግባራት ያከናውናል በዛሬው ዕለት ህዳር ሲታጠንን ወደ ህዳር ሲጸዳ አስተሳሰብ በመቀየር ቆሻሻ ሃብት መሆኑን ዓላማ ያደረገ የጽዳት ዘመቻ አካሄደናል ብለዋል። የክፍለ ከተማው ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አማን አንዱዓለም በበኩላቸው ህዳር ሲታጠን የሚለውን አስተሳሰብ ወደ ህዳር ሲጸዳ የጽዳት ዘመቻው ለተከታታይ ቀናት የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን እያሳተፈ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ እየፈጠርን እንገኛለን በዛሬው ዕለትም የጸጥታ መዋቅሩ የጽዳት ባለቤት በመሆን የድርሻውን አበርክቷል ብለዋል። የጉለሌ ክፍለ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሰለ ይትባረክ በበኩላቸው የጽዳት ዘመቻው ዋና ዓላማ ህዳር ሲታጠንን ወደ ህዳር ሲጸዳ ማህበረሰቡ አስተሳሰቡን በመቀየር አካባቢውን ከአየር ብክለት በመጠበቅ ቆሻሻ ሀብት መሆኑን እንዲረዳ ማስቻል እንደሆነ ገልጸው በዛሬው የጸጥታ መዋቅሩ ክፍለ ከተማው ውብ ጽዱ እንዲሆን ለሚያከናውነው ተግባር ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በክፍለ ከተማው በ10ሩም ወረዳ በሚገኙ ብሎኮች በተካሄደው ጽዳት ዘመቻው የጀግናው መከላከያ ሰራዊት አባላት ፣ የፌደራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት ፣ የፌደራል ፖሊስ አድማ ብተና ፣ የደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች ፣ የሰላም ሰራዊት አባላት እንዲሁም ነዋሪዎች ተሳትፈውበታል ። Gullele communication-ጉለሌ ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

photo content
+5

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በሚገኙ ወረዳዎች ዉስጣችንን ከጥላቻ አከባቢያችን ከቆሻሻ እናፅዳ!! በሚል መሪ ቃል የፅዳታ ዘመቻ በዛሬው እለት ተካሂዷል፡፡ የብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ በክፍለ ከተማው በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች ዉስጣችንን ከጥላቻ አከባቢያችን ከቆሻሻ እናፅዳ!! በሚል መሪ ቃል የፅዳት ዘመቻ ተደርጓል፡፡ በፅዳት ዘመቻው የፀጥታ ሃይሎችና የደንብ ማስከበር ሰራተኞችን የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡ ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

photo content
+1

photo content
+9