Addis Ababa City Manager Office
الذهاب إلى القناة على Telegram
إظهار المزيد
1 474
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-37 أيام
-2130 أيام
أرشيف المشاركات
ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያለውን ግንኙነት በተመለከተ
ኢትዮጵያ ከጎረቤቶቿ ውጭ ህልውና የላትም። ከኢትዮጵያ ውጭ ጎረቤቶቻችን ህልውና የላቸውም። ያልተፈቱ ችግሮች ስለነበሩ በዚያ ምክንያት ወጣ ገባ የሚሉ ጉዳዮች አሉ። እኛ መልካም ዘር መዝራት ነው ፍላጎታችን። የባህር በር ፍላጎታችን በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ማግኘት እንጂ በኃይል አንፈልግም። በሰላማዊ መንገድ ነው ሁሉንም ማሳካት የምንፈልገው። ሉዓላዊነታቸውን እናከብራለን። ኢትዮጵያ ሉዓላዊ ሀገር ናት፤ ይህ ሙሉ እንዲሆን ደግሞ የባህር በር እንድታገኝ ጎረቤቶቻችን በጎ ምላሽ መስጠት አለባቸው። ኢትዮጵያ በትናንሽ ጠጠር አትታወክም፤ ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር ትልቅ ባህር ናት። ኢትዮጵያ የሚያውካትን ተከላክላ መልማት ትችላለች። ይህንን በደንብ ተገንዝቦ ሰብሰብ ማለት ያስፈልጋል። ኢትዮጵያ ከፍተኛ ኢኮኖሚ፣ የህዝብ ቁጥር፣ የዘመነ ሰራዊት ያላት ሀገር ናት። ከኤርትራ ጋር የጦርነት ስጋት ለሚያነሱ አካላት በእኛ በኩል ምንም ዓይነት ውጊያ እንደማንፈልግ ማወቅ ይገባል፤ ይህንን በእነሱም በኩል ማድረግ አለባቸው። ባለፉት ሰባት ዓመታት አንድም ግጭት ከጎረቤት ሀገራት ጋር አላደረግንም። ትብብር አብሮ ማደግ ነው ፍላጎታችን። የማንሰራራት ጉዟችን እንዳይስተጓጎል ከሁሉም ጎረቤቶቻችን ጋር በሰላም መኖር እንፈልጋለን። ሰላማችንን የሚያሰጋ ነገር ካለ ግን ኢትዮጵያ ራሷን ለመከላከል በቂ አቅም አላት። ትበለፅጋለች። ኢትዮጵያ ትበለፅጋለች፤ ኢትዮጵያ ትጸናለች፤ ለማጽናት የሚያበቃ በቂ አቅም አላት፤ ኢትዮጵያ በታሪክ ጠላቶች ነበሯት አሏት፤ አይናቸው እያየ ግን እናንሰራራለን።
#የጠሚሩምላሾች
#PMOEthiopia
የመሃሉ ዘመን ወጥመድን በተመለከተ
የመሃል ዘመን ማለት በሽግግሩ ማጠናቀቂያና በጸናው ስርዓት መጀመሪያ ላይ ማለት ነው። ስድስት ዓመታት የፖለቲካ ሪፎርም አደረግን የሰፈር ፓርቲ አጥፍተን ብልጽግናን ፈጠርን፡ በየሰፈሩ የነበረን ፓርቲ አምጥተን ብልጽግናን መፍጠር በራሱ ትልቅ እምርታ ነው። እኛ ያደረግነውን እኮ ብዙዎቹ አልቻሉም ገና በማህበራዊ ድረ ገጽ ውስጥ ነው ያሉት። ከተቋማት ሪፎርም ጀምሮ የተሟላ ኢኮኖሚ ሪፎርም ስላደረግን ነው መሃል ያልነው። ይሄ ማለት ሽግግሩም መቶ በመቶ አልጠፋም የጸናውም መቶ በመቶ አልጀመረም። መሃል ላይ ነው ያለነው። ያኛው እያለቀ ይህኛው እየጀመረ ማለት ነው። በዚህ ጊዜ ብዙ ድካሞች አሉ። የለውጥ ድካም የሚጀምረው መሃል ላይ ነው። መጀመሪያ ሁሉም ጉልበት አለው በኋላ ያለው ነገር የሚጨበጥ የሚነካ ይሆናል። ለምንድን ነው የመሃሉ ዘመን የሚያመጣብንን ፈተና እንጠንቀቅ ያልነው ብዙ ፈተና አይተናል። ብዙ ድል አግኝተናል፤ እኛ ባለፉት ዓመታት ኢትዮጵያ ውስጥ የሰራናቸው ስራዎች ላለፉት ሀምሳ እና ስልሳ ዓመታት አልተሰሩም ተጨባጭ ለውጥ አለ ኢትዮጵያ ውስጥ። ይህ ግን እንዳያኩራራን መድረስ የሚገባን ቦታ ሳንደርስ አንቆ እንዳያስቀረን አልቀን እንድንሰራ ፈተናን እንዳንለማመድ ድልን ደግሞ ማቀብና መጠበቅ እንድንችል ነው። መሃል ወደ ፊትም መስፈንጠር ያስችላል፤ ወደኋላም እንደገና ሊያንሸራትተን ይችላል ። ለዚህ ነው ነቅተን የመሃሉ እስረኛ እንዳንሆን ያልነው። ከዘመን ጋር የምንዘምን፣ ዘመንን የምንዋጅ፣ አብረን እንድናድግ፣ ባለንበት እንዳንቆም ካስፈለገ የመሃሉ ዘመን ፈተናን መገንዘብ ያስፈልጋል።
#የጠሚሩምላሾች
#PMOEthiopia
የኢትዮጵያ ማንሰራራት የለውጥ መትከል፣ የለውጥ ማጽናት፣ የለውጥ መሰረት ማስያዝ ስራ ተጠናቆ፣ የሪፎርሙንም ውጤት ወደ ማግኘት መሸጋገራችንን የሚያመላክት ነው።
ዘንድሮ ለኢትዮጵያ የማንስራራት ዘመን ነው፤ አመርቂ ድሎች የተመዘገቡበትና ታይተው የማይታወቁ ድሎችን የተጎናጸፍንበት ነው። ለተገኘው ድልና ለነበራችሁ አስተዋፅኦ የየኢትዮጵያ ህዝብ እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን አባላትን ከልብ አመሰግናለሁ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ2017 ዓመተ ምህረት የእቅድ አፈፃፀም ከማቀረብ ባሻገር በፓርላማ ምድረ ግቢ በ #አረንጓዴዐሻራ መርሃ ግብር ችግኝ በመትከል ሁሉም ለዚህ አመት የተያዘውን ግብ ለማሳካት እንዲረባረብ ጥሪ አቅርበዋል።
6ኛው የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፤ 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 42ኛ መደበኛ ስብሰባ… See more
ከሾላ መብራት - ሃያ አራት ያለውን የመንገድ መብራት በመጠገን አገልግሎት እንዲሰጥ ተደረገ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን ከሾላ መብራት - በተሸጋጋሪ ድልድይ ላይ አድርጎ ሃያ አራት ድረስ ባለው የመንገድ ግራና ቀኝ የመብራት ምሰሶዎች ላይ አስፈላጊውን ጥገና በማድረግ አገልግሎት እንዲሰጥ አደረገ፡፡
ባለስልጣኑ ችግሩን ለመፍታት የብልሽቱን መንስኤ በማጥናት ወደ ስራ የገባ መሆኑን በባለስልጣኑ ኦፕሬሽንና ጥገና ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ እንከንየለሽ አለሙ ገልጸዋል፡፡ በተደረገው ዳሰሳ ምክንያት ሆነው የተገኙት የተተከሉ የመብራት ምሰሶዎች ላይ የተፈፀመ ኬብል ስርቆት በተለይም በተሻጋሪ ድልድዩ ላይ በሚገኙ የመብራት ምሰሶዎች ላይና በመንገዱ ወደ 792 ሜትር ርዝመት ያለው ኬብል ተስቦ መሰረቁን አስታውቀዋል፡፡ ሌሎቹ በመንገዱ ላይ ያሉ የመብራት ቆጣሪዎች መነሳት፣ በምሰሶዎች ላይ የሚደርስ የተሽከርሽካሪ ግጭትና ኬብሉ በሌቦች ሲጎተት በሚፈጠር የኃይል መስመር ንክኪ ኤል.ኢ.ዲ መብራቶች እንዲቃጠሉ ማድረጉን ወ/ሮ እንከንየለሽ አስታውቀዋል፡፡
ይህን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ባለስልጣኑ ከቦሌና ከየካ ክፍለ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ፣ ከስራ አስኪያጅ ጽ/ቤትና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በአካል ምልከታ ተደርጎ ወደ ስራ መገባቱን ተናግረዋል፡፡ በተለይም የሚፈፀምን ስርቆት በመከላከልና በምሰሶ ላይ የተሽከርካሪ ግጭት ደርሶ ሲገኝ ተገቢውን ክትትል በማድረግ አጥፊው የጉዳት ካሳ ግምት እንዲከፍል የማድረግ ስራ በመሰራት ላይ ይገኛል፡፡
በተጨማሪም ባለስልጣኑ ችግሮቹን ለይቶ ወደ ጥገና በሚገባበት ወቅትና ከጥገና በኋላም የመብራት መሰረተ-ልማቱ ለህብረተሰቡ ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጥ ለማስቻል ለክፍለ ከተማና ለወረዳ አካላት የማስረከብ ስራ አከናውኗል፡፡
በመጨረሻም ባለስልጣኑ የህብረተሰቡ የረጅም ጊዜ ጥያቄ የነበሩ መንገዶችን በማብራት ባከናወነው ከፍተኛ ስራ የጥገና ሽፋኑን ተደራሽ ማድረግ ከማስቻሉ በተጨማሪ አዲስ አበባ የቀን ብቻ ሳትሆን የምሽትም በማድረግ ያለውን የእግረኛና የትራፊክ እንቅስቃሴ ጤናማ፣ ምቹና ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን ስራውን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
አይበለውና በኤሌክትሪክ አደጋ የተያዘ ሰው ቢያጋጥምዎ ምን ማድረግ እንደሚኖርብዎት ያውቃሉ? ⚠️
ኤሌክትሪክ ጠቀሜታው የላቀ ቢሆንም በጥንቃቄ ጉድለት በአካልና በንብረት ላይ ጉዳት ያስከትላል፤ ለሞትም ይዳርጋል፡፡ ታዲያ ሁሌም እራስዎን ከኤሌክትሪክ አደጋ መጠበቅ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ሊሆን ይገባል፡፡ ነገር ግን አንድ ሰው በኤሌክትሪክ ቢያዝ ወዲያውኑ አስፈላጊውን እርምጃ በመውሰድ ህይወቱን ሊያድን የሚችልበት አግባብ አለ።
⛔️ አይበለውና በኤሌክትሪክ አደጋ የተያዘ ሰው ቢያጋጥምዎ ምን ማድረግ እንደሚኖርብዎት ያውቃሉ?
✅ የኤሌክትሪክ ምንጭን ማጥፋት ወይም ቆጣሪ ብሬከር መመለስ
ይህ የመጀመሪያውና ዋነኛው እርምጃ ሲሆን፤ የቆጣሪ ብሬከሩ የት እንዳለ ካወቁ በፍጥነት ማጥፋት እና የኤሌክትሪክ ፍሰት መቆሙን ሲያረጋግጡ ብቻ ወደ ተጎጂው መቅረብ፤
✅ ኤሌክትሪክን ወዲያውኑ ማጥፋት ካልቻሉ ተጎጂውን ከኤሌክትሪክ ምንጭ ለማራቅ ደረቅ እና ኤሌክትሪክ የማያስተላልፍ (non-conductive) ነገር ይጠቀሙ፤
✅ በፍፁም ባዶ እጅዎን ወይም እርጥብ ነገርን አይጠቀሙ!
ለምሳሌ:- ደረቅ የእንጨት ዘንግ፣ የፕላስቲክ መጥረጊያ እጀታ፣ ወፍራም ጋዜጣ ወይም መጽሐፍ፣ ወይም የጎማ ምንጣፍ መጠቀም ይችላሉ።
✅ ተጎጂውን አይንኩ! በኤሌክትሪክ የተያዘ ሰው ሰውነታቸው ሊያስተላልፍ ይችላል፤
✅ የኤሌክትሪክ ንዝረት የቆዳ ላይ እና ውስጣዊ ቃጠሎ ሊያስከትል ስለሚችል የተቃጠለውን ወይም የተጎዳውን የሰውነት ክፍል በቀዝቃዛ (በረዶ ባልሆነ) ውሃ በማቀዝቀዝ ንጹህና ደረቅ በሆነ ጨርቅ ይሸፍኑት።
✅ የህክምና እርዳታ እንዲያገኝ ወደ ህክምና ተቋም ይደውሉ፤
ያስታውሱ‼️
የኤሌክትሪክ አደጋ የሚያስከትል ሁኔታ ሲመለከቱም አደጋው ከመድረሱ በፊት በአቅራቢያዎ ካለ የተቋማችን የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት በአካል ወይም በጥሪ ማዕከሉ 905 እና 904 በመደወል አልያም በማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻችን ያሳውቁ!
የእርስዎ ደህንነት ቀዳሚ መሆኑን አይርሱ❗️
እራስዎን ከአደጋ ይጠብቁ❗️
ኤሌክትሪክን በቁም ነገር ይዩት🚫
#Safety_First_Always - #ሁልጊዜም_ቅድሚያ_ለጥንቃቄ⚠️
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ነገ ሰኔ 26 ቀን፣ 2017 ዓ.ም በምክር ቤቱ ተገኝተው ማብራሪያ ይሰጣሉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምክር ቤቱ የሚገኙት የመንግሥታቸውን የ2017 የዕቅድ አፈፃፃም አስመልክቶ የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለሚያነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ለመስጠት ነው፡፡
በኢፌዴሪ ህገ መንግስቱ አንቀፅ 55 ንዑስ አንቀፅ (17) እና በምክር ቤቱ የአሰራርና የአባላት የሥነ-ምግባር ደንብ ቁጥር 6/2008 አንቀፅ 81 ንዑስ አንቀፅ ( 1 እና 3) መሰረት የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትሩን እና ሌሎች የፌዴራሉ መንግሥት ባለስልጣናትን ለጥያቄ የመጥራትና የሕግ አስፈፃሚውን አካል አሰራር የመመርመር፤ የመከታተልና የመቆጣጠር ሥልጣን አለው፡፡
በዚሁ ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌና በምክር ቤቱ የአሰራር ደንብ መሰረት 6ኛው የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ4ኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ ነገ ሐሙስ ሰኔ 26 ቀን 2017 ዓ.ም በሚያካሂደው 42ኛ መደበኛ ስብሰባው ክቡር የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በምክር ቤቱ ተገኝተው የመንግሥታቸውን የ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፃም አስመልክቶ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ የሚሰጡ ሲሆን የፌዴራል መንግሥት የ2018 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት ምክር ቤቱ እንደሚያፀድቅም ይጠበቃል ፡፡
በጉባኤው ላይ ጥሪ የተደረገላቸው ተጋባዥ እንግዶች፤ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሐይማኖት አባቶች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች የሚገኙ ሲሆን የጉባኤው ሙሉ ሂደትም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በቀጥታ ሥርጭት የሚተላለፍ ይሆናል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
የአዲስ አበባ ከተማ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከትናንት ሰኞ ሰኔ 24 ጠዋት ጀምሮ ከሲስተም ጋር በተያያዘ መጠነኛ ችግር ስላጋጠመ የሲስተም መዘግየት በወረዳ ጽ/ቤቶች ላይ እንዳጋጠመው ገልጿል።
በመሆኑም ችግሩን ለመፍታት ከአዲስ አበባ ከተማ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ጋር በጋራ እየሰራ እንደሚገኝ በመግለፅ ለገጠመው የአገልግሎት መስተጓጎል ተገልጋዮችን ከልብ ይቅርታ እንጠይቃለን ብሏል።
ኤጀንሲው አገልግሎቱ ችግር የገጠመው ቀደሞ የዲጂታል ምዝገባ ያደረጉ ፣ እድሚያቸው ከ12 በታች የሆኑ ህፃናትን እንዲሁም በውክልና የሚስተናገዱ ተገልጋዮችን የማያካትት መሆኑን በማወቅ ሌሎች አገልግሎቶችን ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን ሲልም አስታውቋል።
ለበለጠ መረጃ በነፃ መስመር 7533 ይደውሉ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
