Addis Ababa City Manager Office
الذهاب إلى القناة على Telegram
إظهار المزيد
1 474
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-37 أيام
-2130 أيام
أرشيف المشاركات
"ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ፥
ለዘመናዊ የከተማ አስተዳደር "
በቀጣዩ ቪዲዮ ይከታተሉ 👉👉
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
See less
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የ90 ቀናት የንቅናቄ ስራዎች ያሉበትን ደረጃ በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫዎችን ሰጥተዋል።
ከንቲባዋ ከ15 ቀናት በፊት ከመላው አመራር ጋር በመወያየት ዝርዝር አቅጣጫ የተሰጠባቸው 18ቱም ከተማ አቀፍ የክረምት ንቅናቄ አጀንዳዎች ዙሪያ አበረታች ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ለአብነትም በገበያ ማረጋጋት፣ ስራ ዕድል ፈጠራ፣ ከተማ ግብርናና ሌማት ትሩፋት፣ ገቢ አሰባሰብ፣ የክረምት በጎ ፍቃድ ስራዎች፣ የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር፣ የሁለተኛ ዙር ኮሪደር ልማት ቀሪ ስራዎችን ቆጥሮ ማጠናቀቅ እና ሌሎች ትላልቅ ፕሮጄክቶች አፈጻጸም ዙሪያ አበረታች ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆናቸውን በተደረገው ግምገማ ተረጋግጧል።
በተለይም ደግሞ የህዝባችንን የኑሮ ጫናዎችን ለማቃለል በተሰራው የተቀናጀ ስራ የከተማችን የገበያ ማዕከላት፣ የእሁድ ገበያዎች፣ የከተማ ግብርናና የሌማት ትሩፋት ስራዎች፣ አምራች ኢንዱስትሪዎች እና መሰል ዘርፎች የምርት አቅርቦት ሰንሰለትን በማሳለጥ ከፍተኛ አበርክቶ እንዲኖራቸው መደረጉም ተገልጿል።
ቀሪ ስራዎችን በተሟላ መልኩ ለማሳካት በየደረጃው ያለው አመራር ለላቀ ውጤት በትብብር እንዲረባረብ አቅጣጫ ተሰጥቷል።
መዲናችን አዲስ አበባ ከሰባት አመት (የለውጡ አመታት) በፊት ቆሻሻን ተረማምደን የምናልፍበት አይነት ከተማ ነበረች ። በአሁኑ ወቅት ከለውጡ ወዲህ በተሰሩ አስደማሚ ስራዎች አዲስ አበባን ልጆቻችን በሰላም የሚጫወቱባት፣ ሰፈራችን የሚደምቅባት፣ ጽዳት፣ ውበትና የህዝባችን የደኅንነት መብት እንጂ አጀንዳ የማይሆንባት ከተማ እየፈጠርን እንገኛለን።የጽዳት ጉዳይ የመርሐግብር ጉዳይ አይደለም.።እንደ ከተማም ሆነ እንደማህበረሰብ ማን እንደሆንን ማንነታችንን የምንገልጽበት፣ ክብራችንን የምናስጠብቅበት ጉዳይ ነው፣ የመዲናችን የፅዳት አጠባበቅ ጉዳይ አብረን ስንተጋ ምን አይነት ተአምር መስራት እንደምንችል ያሳየንበት ትልቅ ተአምራዊ ለውጥ ያመጣንበት እና ስኬታማ ተግባር የፈፀምንበት ነው።"
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በምክትል ከንቲባ ማእረግ
የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ
የ90 ቀናት የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችን በተቀናጀ የህብረተሰብ ተሳትፎ ማስተግበሪያ እና የ"ፅዱ ኢትዮጵያን" በመዲናችን ይፋዊ የማስጀመሪያ የንቅናቄ መድረክ ላይ ከተናገሩት የተወሰደ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ቃል በተግባር !!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኮሪደር ልማት እና በእርጅና ምክንያት በፈረሰዉ ህንፃ ምትክ ያስገነባውን ሁለገብ ህንጻ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በተገኙበት የምርቃት ስነስርአት ላይ ለቤተክርስቲያኗ አስረክበናል።
ሁለገብ ህንፃዉ በአራዳ ክፍለ ከተማ ፒያሳ አካባቢ በተለምዶ መሐሙድ ሙዚቃ ቤት በመባል በሚታወቀዉ የቤተክርስቲያኗ ይዞታ ላይ የተገነባ ነዉ።
በአስተዳደሩ በጀት ደረጃዉን በጠበቀ መልኩ በዛሬዉ ዕለት የተመረቀዉ ህንፃ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተገንብቶ የተጠናቀቀ ነዉ፡፡
ፈጣሪ ኢትዮዽያንና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
"ዛሬ ጠዋት በሬይስ ኦፍ ሆፕ ጉባኤ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ከመጡት የአለምአቀፍ የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ(IAEA) ዋና ዳይሬክተር ማሪያኖ ግሮሲ ጋር ተገናኝተናል።
የአለም አቀፉ አቶሚክ ኃይል በኢትዮጵያ የሚያደርገው ድጋፍ በካንሰር ሕክምና ክብካቤ፣ የእንስሳት ጤና፣ የፀፀ ፍላይ ዝንብ ማጥፊያ፣ በኒኩለር ኢንጂነሪንግ እና የቁጥጥር ማዕቀፎች ላይ ያተኮረ ነው። ውይይታችን በመካሄድ ላይ ባሉ ድጋፎች እና የወደፊት የትብብር እድሎች ላይ ያተኮረ ነበር"።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
AQMGCj6uYGgjKrubbxZ1JBv9uW3BlVRz1hsMHkHROqn7SnBj_9ArZJ80s4_ooPM25.13 MB
እንኳን ለ2017 ዓ. ም የጋራ አሻራ ማኖር አደረሳችሁ !!
ሀገራችን ዘመን የማይሽረው ታሪክ አስቀምጣለች።
ባለፉ ስድስት ዓመታት ሁሉም ኢትዮጵያዊ 40 ቢሊዮን ችግኝ በመትከል ታሪክ አኑሯል።
በከተማችንም ባለፋት ስድስት ዓመታት 6 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል የአረንጓዴ ሽፋናችንን ከ 2 ነጥብ 8 ወደ 22 በመቶ ማድረስ ችለናል። የፅድቀት መጠኑም ከ85 በመቶ በላይ መድረሱን አረጋግጠናል። ይህ ለሁላችንም ኩራት ነዉ።
በአረንጓዴ አሻራ መረሀ ግብራችን የተራቆቱ አካባቢዎች አረንጓዴ ለብሰዋል፤ የነጠፉ ወንዞች እና አካባቢዎች ማንሰራራት ችለዋል። አዲስ አበባችንም ንፁህ ውብ እና የቱሪስት ገቢ ማግኛ መሆን ችላለች።
በከተማ ደረጃ ዛሬ ያስጀመርነው የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መረሀ ግብር ከሸገር ወንዝ በእንጦጦ ፓርክ አስከ ፒኮክ ወንዝ ዳርቻ የሚደርስ 21 ኪ. ሜ ሲሆን፤ 860 ሄክታር መሬት ይሸፍናል ።
በአጠቃላይ ከተማችን ለዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 916 ሄክታር ቦታ አዘጋጅታለች። ውድ የከተማችን ነዋሪዎች በወንዝ ዳርቻዎች፣ በጤና ተቋማት ፣ በሃይማኖት ተቋማት ፣ በግል ሴክተሮች እና በጎዳናዎች ለምግብነት የሚውሉ አትክልት እና ፍራፍሬዎችን በመትከል ኢኮኖሚያችንን እንገንባ ።
እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ ህፃን አዋቂ፣ የተማረ ያልተማረ ሳንል ሁሉም ዜጋ በጋራ በመሆን እንትከል ስል ጥሪዬን አስተላልፋለሁ።
አዲስ አበባን ለመኖር ምቹ ለማድረግ መስራታችንን እንቀጥላለን።
በመጨረሻም ለዚህ መርሃ ግብር ያለመታከት የሰራችሁ፣ የደገፋችሁ እና ተንከባክባችሁ ያሳደጋችሁ ታሪክ ያመሰግናቹሃል፤ ኢትዮጵያም ታመሰግናችኋለች።
ፈጣሪ አምላክ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
AQMovkCVonlvXfoDhi8NmaCgt_5Ust_j3hamVrsmKz_eusPlJf8z1Gcq_u6MdZEhvp9y91y61.60 MB
ዛሬ ከሁሉም የከተማችን የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ተክለናል!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን አና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የ90 ቀን ልዩ የንቅናቄ አጀንዳ አካል የሆነ ጽዱ ውብ እና ደህንነቷ የተጠበቀች አዲስ አበባ በሚል መሪ ሃሳብ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችን ማስተግበሪያ የመክፈቻ መርሃ ግብር አካሂዷል ፡፡
AMN-Addis Media Network
See less
