cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

Ethiopian Broadcasting Corporation (EBC)

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
124 407
المشتركون
+4124 ساعات
+3037 أيام
+1 30530 أيام
توزيع وقت النشر

جاري تحميل البيانات...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
تحليل النشر
المشاركاتالمشاهدات
الأسهم
ديناميات المشاهدات
01
የኢትዮጵያን የዲጂታል ሽግግር ለማሳካት የግሉ ዘርፍ የመሪነት ሚና መወጣት እንዳለበት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ተናገሩ ***************** ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ሚኒስትሮች እና የቴክኖሎጂ ዘርፍ ባለድርሻዎች በተገኙበት የኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚ ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት በሳይንስ ሙዚየም ተካሂዷል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፤ ዲጂታላይዜሽን አይቀሬ በመሆኑ፣ ኢትዮጵያ ወሳኝ ኢኒሼቲቮችን ቀርፃ መተግበር ጀምራለች ብለዋል። ለኢትዮጵያ ዲጂታላይዜሽንን ማፋጠን የግድ የሆነባቸው ምክንያቶች አሉ ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ አንደኛው፥ ዲጂታላይዜሽን ዕድገትን የሚያፋጥን በመሆኑ ነው ብለዋል። ሁለተኛው፥ መንግሥታዊ አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻልና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን እንደሚያግዝ ታምኖ መሆኑን ገልፀዋል።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02BJCBnEqHA4JPZAvatSgtSuYM5Lpd1dSefoDZufYqZr2B2wP4MP5zr3EtQsaW6fYwl
1 0610Loading...
02
በክልሎች እና በከተማ አስተዳደሮች በሚከናወን አጀንዳዎችን የማሰባሰብ ሂደት ተሳታፊ እንዲሆኑ የተለዩ ባለድርሻ አካላት *********** የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በክልሎች እና በከተማ አስተዳደሮች ለሚያከናውነው አጀንዳዎችን የማሰባሰብ ስራ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን ለይቷል፡፡ በኮሚሽኑ የተዘረዘሩት ባለድርሻ አካላት በሚቀርብላቸው ይፋዊ ጥሪ መሰረት በክልሎች እና በከተማ አስተዳደሮች በሚከናወነው አጀንዳዎችን የማሰባሰብ ስራ ተሳታፊ በመሆን፤ በሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ላይ እንዲንፀባረቅላቸው የሚፈልጓቸውን አጀንዳዎች እንደሚያቀርቡ ይጠበቃል ሲል ኮሚሽኑ በማሕበራዊ ትስስር ገፁ ባወጣው መረጃ ገልጿል፡፡
9070Loading...
03
ከችግሮች ነፃ የሆነች ኢትዮጵያን እውን ሆና ለማየት ምክክሩ ሊያመልጠን አይገባም ፡-አቶ እውነቱ አለነ **************** ከችግሮች ነፃ የሆነች ኢትዮጵያን እውን ሆና ለማየት ምክክሩ ሊያመልጠን አይገባም ሲሉ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰላምና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ እውነቱ አለነ ገለጹ። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን "የኢትዮጵያ ሚዲያ ለኢትዮጵያውያን ውጤታማ ሀገራዊ ምክክር" በሚል መሪ ሃሳብ ከፌዴራል፣ ከክልል፣ ከግል የሚዲያ አመራሮችና ከፍተኛ ባለሙያዎች ጋር እየመከረ ነው። አቶ እውነቱ፤ የምክክር ኮሚሽኑን በተመለከተ ከገለልተኝነት ጋር ተያይዞ የሚቀርብበት ወቀሳ በሕግ የተፈታ ነው ሲሉም ተናግረዋል። ኮሚሽኑ ተጠሪነቱ ለምክር ቤቱ ቢሆንም፤ ምክር ቤቱ ስራውን ከማገዝ ያለፈ ጣልቃ አይገባበትም ነው ያሉት። መገናኛ ብዙኀንም የተሳካ ምክክር እንዲደረግና ልዩነቶች በሰለጠነ መንገድ እንዲፈቱ አቅም ሊሆኑ እንደሚገባም ገልጸዋል።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid04hxbS8AFHy8nHr5gMtGK3NaiJXkXZP9yDSbacoPfHRbmRgWx22GSabBmg5kkJduRl
1 1180Loading...
04
ፓስፖርት በሀገር ውስጥ እንዲታተም የሚያስችል ሥራ እየተከናወነ ነው - የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ********************** በተያዘው ዓመት ፓስፖርት ጠይቀው ይጠባበቁ ከነበሩ ዜጎች መካከል ከ600 ሺህ በላይ ለሚሆኑት መስጠት መቻሉን የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ገልጿል። የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል የፓስፖርት አገልግሎት አንዱ እና ዋንኛው ነው። ይሁን እንጂ የፓስፖርት አሰጣጥን በተመለከተ የሚነሱ ቅሬታዎችን በተደጋጋሚ ይስተዋላል። ኢቢሲም ይህን ጉዳይ በተመለከተ ተደጋጋሚ ዜናዎች መስራቱ ይታወሳል። በኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ከሚነሱ ቅሬታዎች አንዱ መጉላላት ነው የሚለው የአዲስ አበባ ነዋሪው አቶ ያሬድ መንግሥቱ፤ እርሱ ራሱም ላላገኘው አገልግሎት ሁለት ቀን በሰልፍ መጉላላቱን ለኢቢሲ ሳይበር ተናግሯል። https://www.ebc.et/newsdetails.aspx?newsid=6743
1 3673Loading...
05
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ስትራይድ ኢትዮጵያ ኤክስፖን ጎበኙ ***************** ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እና ሚኒስትሮች ስትራይድ ኢትዮጵያ ኤክስፖን መጎብኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል። ስትራይድ ኢትዮጵያ 2024 ኤክስፖ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ግንቦት 10 ቀን 2016 ዓ.ም በይፋ መከፈቱ ይታወቃል። ዓመታዊው ኤክስፖ "ሳይንስ በር ይከፍታል፤ ቴክኖሎጂ ያስተሳስራል፤ ፈጠራ ወደ ፊት ያራምዳል" በሚል መሪ ሀሳብ በሳይንስ ሙዚየም እስከ ግንቦት 18 ቀን 2016 ዓ.ም ለሕዝብ ዕይታ ክፍት ሆኖ ይቆያል። ትኩረቱን ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራና ዲጂታላይዜሽን ላይ ያደረገው ስትራይድ ኢትዮጵያ ኤክስፖ በርካታ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ተቋማትን በማሳተፍ ላይ ይገኛል። በኤክስፖው ላይ የመንግሥትና የግል ተቋማት እንዲሁም ስታርት አፖች የቴክኖሎጂ ፈጠራ ሥራዎችን ለዕይታ አቅርበዋል።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid024mftynvRRd4Mjn2SqrC9jEohuxaPFLoguaxAHxpnpatNtCkYpErJJyHkys23SwFjl
1 7880Loading...
06
የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ቀጣይነት ባለው አግባብ በተደራጀ ህዝባዊ ንቅናቄ ሊተገበሩ ይገባል:- ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ************* የአካባቢ ጥበቃ እና የአረንጓዴ ልማት ስራዎች ቀጣይነት ባለው አግባብ በተደራጀ ህዝባዊ ንቅናቄ ሊተገበሩ ይገባል ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ገለጹ። ርዕሰ መስተዳድሩ፤ በክልሉ በልግ አብቃይ አካባቢዎች እየጣለ ካለው መደበኛና ከመደበኛ በላይ ከፍ ያለ ዝናብ ስርጭትና መጠን ጋር ተያይዞ የተወሰነ የጎርፍና መሰል የተፈጥሮ አደጋ በአንዳንድ አካባቢዎች መስተዋሉ የተፈጥሮ ሐብት ጥበቃ ስራዎችን ይበልጥ ማጠናከር እንደሚገባ ጠቋሚ መሆኑን ተናግረዋል። በክልሉ የሚሰሩ የቅድመ የመከላከልና ጥንቃቄ ስራዎች እንደተጠበቁ ሆነው፤ በየአካባቢው የተፈጥሮ አደጋ ተጋላጭነትን በዘላቂነት ለመከላከል የአካባቢ ጥበቃ ስራን ማጠናከር ይገባል ብለዋል። የክልሉ መንግስት ለአካባቢ ጥበቃና ለአረንጓዴ ልማት ስራዎች ከፍተኛ ትኩረት መስጠቱን ገልጸው፤ በተለይ ለተፈጥሮ ሐብት ልማት፣ ለአፈርና ውኃ ጥበቃ፣ ለተራራ ልማት እና ለአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ልዩ ትኩረት መደረጉን ነው የጠቀሱት።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0UrUB5uExs9yVLFbdpriH9ubXeBoeXwJsKysgdmoY255Szoq1hexQbRxJzkDSEg39l
2 9003Loading...
07
የሰላም ሚኒስቴር በሰሜን አሜሪካ ከሚገኘው የስተርሊንግ ፋውንዴሽን አመራሮች ጋር በሰላም ግንባታ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሄደ ************************ የሰላም ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች ቡድን በሰሜን አሜሪካ ዩታሀ ግዛት ከሚገኘው የስተርሊንግ ፋውንዴሽን መሪዎች ጋር በሰላም ግንባታ ዙሪያ በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል። በኢትዮጵያ በተለያዩ የሰላም ግንባታ ተግባራት ድጋፍ እያደረገ ከሚገኘው ስተርሊንግ ፋውንዴሽን አመራሮች ጋር ድጋፉ ተጠናክሮ በሚቀጥልበት መንገዶች ዙሪያ ለመወያየት በሰላም ሚኒስትሩ አቶ ብናልፍ አንዷለም የሚመራው ቡድን በግዛቷ መዲና ሳልት ሌክ ከተማ ጉብኝት በማካሄድ ላይ ይገኛል። ቡድኑ በግዛቲቱ የሰብዓዊ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት፣ የተለያዩ ሀይማኖቶች በመከባበርና በሰላም አብረው በአካባቢው ሰላም፣ አብሮነትና መከባበር ለማምጣት የሚያከናውኑት ተግባርና የተገኘውን ውጤት ተዟዙረው ጎብኝተዋል።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02jwneEJBYA5vqiu3qzjjvVNNNYjaZ37D7kPFsmyK1p3L5Eg6M81xNvY1NajVcbxbZl
2 7212Loading...
08
የዕለቱ የውጭ ምንዛሬ ዋጋ
2 5451Loading...
09
የኢቢሲን አዳዲስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን በዋትስአፕ አማራጭ Follow EBC on our new WhatsApp channel https://whatsapp.com/channel/0029VaVefI79xVJoMGtunX2T
8 6124Loading...
10
ባለፉት ጥቂት አመታት ዋናውን የዝናብ ወቅት ምርት ሳናስተጓጉል የበጋ ስንዴ ልማት ጥረታችንን ለማስፋፋት ችለናል። የዛሬው ምልከታ የስራዎችን ቀጣይነት የተመለከትንበት ነበር። ግብርና ጠንካራ ኢንቨስትመንት ይፈልጋል። በሰብል የምንሸፍነው የመሬታችን ይዞታም ቀስ በቀስ በመጨመር ላይ ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02waGXZW9S5uzfBsB9bVnZ2jmf2YfHTCnKRLki48aCCzmxDiKuHP1rP4vJdcYW11isl
9 1343Loading...
11
ለመጀመሪያው ዙር የሐጅ ተጓዦች በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሽኝት ተደረገ *************** ለዘንድሮው ለ1 ሺህ 445ኛው የሐጅ ሥነ-ሥርዓት የመጀመሪያ ዙር ተጓዦች በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሽኝት ተደረገ። የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የኢትዮጵያ አየር መንገድ አመራርና ሰራተኞች በተገኙበት ሽኝቱ መደረጉ ታውቋል። የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ጸሃፊ ሸኽ ሃሚድ ሙሳ፤ በሂደቱ የምዝገባ፣ የቪዛ፣ የምክርና ተያያዥ አገልግሎቶች በተቀላጠፈ መልኩ መሰጠታቸውን ገልጸዋል። ለሐጅ ሥነ-ሥርዓቱ ከጉዞ እስከ መመለሻ ድረስ በቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑንም ጠቅሰዋል። በባለፈው ዓመት 11 ሺህ ሑጃጆች መጓዛቸውን አስታውሰው ዘንድሮ ደግሞ ከ12 ሺህ በላይ ተጓዦች ወደ ስፍራው የሚያቀኑ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም መሰረት በዛሬው እለት የመጀመሪያው ዙር የሑጃጆች የሽኝት ሥነ-ሥርዓት መደረጉን ተናግረዋል።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0SoktYNCqtamPpThxFMcJ7TsJKct81qZNPfCzy9qPigBBU8Srns1qxUNMvhZWsVzdl
9 4001Loading...
12
የግንቦት 13 ቀን 2016 የውጭ ምንዛሬ ዋጋ
7 6372Loading...
13
ሽንታችን ስለጤናችን ምን ይነግረናል? ************* ሽንት በምንመገበው ምግብ፣ በምንወሰደው መድኃኒት እንዲሁም በምንጠጣው የውኃ መጠን ምክንያት ቀለሙ፣ ጠረኑ እንዲሁም ዓይነቱ ይቀያየራል። ሽንት ሰውነታችን በፈሳሽ መልክ ቆሻሻን የሚያስወግድበት አንዱ መንገድ ሲሆን በዋናነት ውኃ፣ ጨው፣ ኤሌክትሮላይቶች እንደ ፖታሺየም እና ፎስፈረስ፣ ዩሪያ እና ዩሪክ አሲድ የሚባሉ ኬሚካሎች በውስጡ ይዞ ይገኛል። እነዚህም ኩላሊት መርዛማ ንጥረ ነገሮችን እና ሌሎች መጥፎ ነገሮችን ከደም ውስጥ ሲያጣራ የሚከሰቱ ሲሆኑ፤ መድኃኒት፣ የተለያዩ ዓይነት ምግቦች እና ሕመሞች የሚወገደው የሽንት ዓይነት ላይ ለውጥ እንዲኖረው ያደርጋሉ። ጤናችን ያለበትን ሁኔታ የሚነግሩን የቀለም ዓይነቶች እንዳሉ ስንቶቻችን እናውቃለን? ጤናማ የሽንት ቀለም ምን ዓይነት ነው? ሽንት ፈዛዛ ቢጫ ወይንም ወርቃማ ቀለም ሲኖረው ሰውነት በቂ ውኃ አግኝቷል፤ ጤናማ ነው እንላለን። ሽንት ምንም ዓይነት ቀለም ከሌለው (ውኃ ቀለም) ከሆነ ደግሞ ሰውነታችን በብዛት ውኃ እንዳገኘ እና እንዳበዛን ያመላክታል። ከልክ በላይ ውኃ ማብዛት በሰውነታችን ወስጥ የኤሌክትሮላይት መዛባት ያስከትላል፤ በመሆኑም የምንወስደውን የውኃ መጠን በመቀነስ በቀን ውስጥ ከ6 እስከ 8 ብርጭቆ ውኃ እንድንጠጣ ይመከራል። ቀላ ያለ ሮዝ ቀለም ለኩላሊት እና ለተለያዩ በሽታዎች መጋለጥን ሊያመላክት ይችላል።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02u2BPuvN94L3mR5QgzsH2onD5wwzJvsGMEBQbxBHJMgw26QLHHPo6JRJvhqJuZrfsl
7 75744Loading...
14
1 ሺህ 175 ኢትዮጵያውያን ከሳውዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመልሱ **************** በዛሬው ዕለት በ3 ዙር በረራ በተከናወነ በሳውዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ ዜጎችን የመመለስ ስራ፣ 1 ሺህ 175 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ ተችሏል። ወደ ሀገር የተመለሱት 1 ሺህ 175 ዜጎች ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ፤ ከተመላሾች መካከል 18 ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊ ህጻናት ይገኙበታል። ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ መሆኑን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ፣ እስካሁን ከ27 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉ ተገልጿል።
9 3535Loading...
15
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ንግግሮችና መልዕክቶችን የያዘ መጽሐፍ ለንባብ በቃ *********************** የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ንግግሮችና መልዕክቶችን የያዘና "ከመስከረም እስከ መስከረም" የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ በቃ። በመጽሐፉ ላይ የዳሰሳ ውይይት በወዳጅነት ፓርክ ተካሂዷል። በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሪታሪያት የተዘጋጀው ይህ መጽሐፍ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከመስከረም 24 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ መስከረም 24 ቀን 2016 ዓ.ም በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎችና ዓለም አቀፍ ጉባኤዎች ላይ ያደረጓቸው 91 ንግግሮችና መልዕክቶችን ያያዘ ነው። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሪታሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም በውይይት መድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር፥ መጽሐፉ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንግግሮችና መልዕክቶች የያዘ 6ኛው መድብል መሆኑን ገልጸዋል። የመሪ ታሪክ የሀገር ታሪክ አካል መሆኑን ጠቅሰው፤ ከዚህ አኳያ መጽሐፉ ለታሪክ አጥኚዎች፣ ለፖሊሲ አውጭዎችና ለፖለቲካ ተመራማሪዎች ግብዓት እንደሚሆን ተናግረዋል። በመድረኩ ተማሪዎች ከመጽሐፉ የተመረጡ ገጾችን እንደ ውይይት መነሻ ሃሳብ በንባብ አቅርበዋል። "ከመስከረም እስከ መስከረም" መጽሐፍ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞ በእንግሊዝኛ እና በአረቢኛ ቋንቋዎች ያስተላላፏቸውን ንግግሮችና መልዕክቶች ይዟል። በሮዛ መኮንን
10 4158Loading...
16
ጣሊያን ከኢትዮጵያ ጋር በተለያዩ ወታደራዊ ጉዳዮች ያላትን ትብብር ማጠናከር እንደምትገልግ ገለጸች *********************** በጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የተመራው የኢትዮጵያ መከላከያ የልዑካን ቡድን በጣሊያን ወገን በተደረገለት ግብዣ መሠረት ይፋዊ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛል። የልዑካን ቡድኑ ጣሊያን ሲገባ በሀገሪቱ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም አድሚራል ጁሴፔ ካቮ ድራጎን እና በሌሎች ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣናት ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል። ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በዛሬው ዕለት ከጣሊያኑ አቻቸው አድሚራል ጁሴፔ ካቮ ድራጎን ጋር በወታደራዊ ትብብሮች ዙሪያ ውጤታማ ውይይት አድርገዋል። ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በውይይቱ ወቅት በሁለቱ ሀገራት መካከል እያደገ የመጣውን ግንኙነት አውስተው፣ ለዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጣሊያን ያደረጉት ይፋዊ የስራ ጉብኝት እና ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ በኢትዮጵያ ያደረጉት ጉብኝት የሀገራቱን ግንኙነት መጠናከር አመላካች መሆኑን አንስተዋል። አክለውም፥ አድሚራል ጁሴፔ ካቮ ድራጎን በቅርቡ በኢትዮጵያ ያደረጉት ጉብኝት በዘርፉ ያለውን ትብብር ለማጠናከር ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳበረከተም ገልጸዋል። አድሚራል ጁሴፔ ካቮ ድራጎን በበኩላቸው በሁለቱ ሀገራት መካከል በተለያዩ ወታደራዊ ጉዳዮች ያለውን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ጣሊያን ያላትን ፍላጎት ገልጸዋል። አያይዘውም፥ በዘርፉ በተለያዩ ደረጃዎች ያለውን ግንኙነት ማስቀጠል እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተው መናገራቸውን በሮም የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።
8 8072Loading...
17
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. መንግሥት ለኢራን ሪፐብሊክ መንግሥትና ህዝብ የኀዘን መልዕክት አስተላለፈ ********** የኢራን ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራኢሲ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሁሴን አሚር አብዱላሂያንን ጨምሮ የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት በሄሊኮፕተር አደጋ ሕይወታቸው ማለፉን ተከትሎ፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. መንግሥት ለኢራን ሪፐብሊክ መንግሥትና ህዝብ የኀዘን መልዕክት አስተላልፏል። ከፍተኛ ባለስልጣናቱን ያሳፈረች ሄሊኮፕተር ላይ ትናንት አመሻሹን አደጋ መድረሱ ይታወቃል። አደጋውን ተከትሎም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ የኀዘን መግለጫቸውን ለኢራን ሪፐብሊክ መንግሥትና ህዝብ አስተላልፈዋል። በኀዘን በመግለጫው ሕይወታቸው ላለፈው ባለሥልጣናት ቤተሰቦችና ወዳጆች መፅናናትን መመኘታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
7 5594Loading...
18
በሕግ እና በሕግ የበላይነት መከበር የሚያምን ትውልድ ሊኖረን ይገባል - የአማራ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ *************** የአማራ ክልል ከነበረው የፀጥታ ችግር በመሻሻል አንፃራዊ ሰላም ላይ እንደሚገኝ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ደሳለኝ ጣሰው ገለጹ። ክልሉ በቀደሙት ጊዜያት ባልተጠበቀ ያለመረጋጋት ውስጥ ማለፉን አስታውሰው፤ ይህን ለመቅረፍ መንግሥታዊ ተልዕኮውን የሚወጣ አደረጃጀት የማዋቀር ስራ እየተሰራ እንደሚገኝም ነው የተናገሩት። ለተገኘው ሰላም የመከላከያ ሠራዊት ሚና ላቅ ያለ ነው ብለዋል ኃላፊው። የአመለካከት እና የአስተሳሰብ አንድነት በመፍጠር የተገኘውን ሰላም ለማስቀጠል የክልሉ የፀጥታ መዋቅር የአቅም ግንባታ ስልጠና እየሰጠ መሆኑን ገልጸዋል። https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02Hy1oNPBhvRbPtoj9oSJqzKQDUux3rDEhzp4wXgX3Ft7fHowSRKNREHuJG5QdC1wul
8 8584Loading...
19
ኢትዮጵያና ሞሮኮ ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ ******************* የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በሞሮኮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሁለትዮሽ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ፉዓድ ያዙሁር የተመራ የልዑካን ቡድን ተቀብለው አነጋግረዋል። ሁለቱ ወገኖች ኢትዮጵያና ሞሮኮ ያላቸውን የሁለትዮሽ ግንኙነት አጠናክሮ ማስቀጠል በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ምክክር አድርገዋል። በተለይም ሁለቱ አገራት ቀደም ሲል አብረው ለመስራት ስምምነት የደረሱባቸውን የንግድ፣ የኢንቬስትመንት፣ የፋይናንስ፣ የአየር አገልግሎት እና የትምህርት ዘርፍ የትብብር ስምምነቶች መልሶ በመቃኘት ለማጠናከር ተስማምተዋል። አገራቱ ከሁለትዮሽ ግንኙነት ባለፈ በአህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮችም በትብብር መስራት በሚችሉባቸው መስኮች ላይ መክረዋል። ውይይቱን ተከትሎም በሞሮኮ እና በኢትዮጵያ መካከል የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባ በቅርቡ ለማካሄድ ከስምምነት መደረሱን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
9 1254Loading...
የኢትዮጵያን የዲጂታል ሽግግር ለማሳካት የግሉ ዘርፍ የመሪነት ሚና መወጣት እንዳለበት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ተናገሩ ***************** ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ሚኒስትሮች እና የቴክኖሎጂ ዘርፍ ባለድርሻዎች በተገኙበት የኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚ ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት በሳይንስ ሙዚየም ተካሂዷል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፤ ዲጂታላይዜሽን አይቀሬ በመሆኑ፣ ኢትዮጵያ ወሳኝ ኢኒሼቲቮችን ቀርፃ መተግበር ጀምራለች ብለዋል። ለኢትዮጵያ ዲጂታላይዜሽንን ማፋጠን የግድ የሆነባቸው ምክንያቶች አሉ ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ አንደኛው፥ ዲጂታላይዜሽን ዕድገትን የሚያፋጥን በመሆኑ ነው ብለዋል። ሁለተኛው፥ መንግሥታዊ አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻልና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን እንደሚያግዝ ታምኖ መሆኑን ገልፀዋል።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02BJCBnEqHA4JPZAvatSgtSuYM5Lpd1dSefoDZufYqZr2B2wP4MP5zr3EtQsaW6fYwl
إظهار الكل...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
በክልሎች እና በከተማ አስተዳደሮች በሚከናወን አጀንዳዎችን የማሰባሰብ ሂደት ተሳታፊ እንዲሆኑ የተለዩ ባለድርሻ አካላት *********** የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በክልሎች እና በከተማ አስተዳደሮች ለሚያከናውነው አጀንዳዎችን የማሰባሰብ ስራ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን ለይቷል፡፡ በኮሚሽኑ የተዘረዘሩት ባለድርሻ አካላት በሚቀርብላቸው ይፋዊ ጥሪ መሰረት በክልሎች እና በከተማ አስተዳደሮች በሚከናወነው አጀንዳዎችን የማሰባሰብ ስራ ተሳታፊ በመሆን፤ በሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ላይ እንዲንፀባረቅላቸው የሚፈልጓቸውን አጀንዳዎች እንደሚያቀርቡ ይጠበቃል ሲል ኮሚሽኑ በማሕበራዊ ትስስር ገፁ ባወጣው መረጃ ገልጿል፡፡
إظهار الكل...
ከችግሮች ነፃ የሆነች ኢትዮጵያን እውን ሆና ለማየት ምክክሩ ሊያመልጠን አይገባም ፡-አቶ እውነቱ አለነ **************** ከችግሮች ነፃ የሆነች ኢትዮጵያን እውን ሆና ለማየት ምክክሩ ሊያመልጠን አይገባም ሲሉ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰላምና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ እውነቱ አለነ ገለጹ። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን "የኢትዮጵያ ሚዲያ ለኢትዮጵያውያን ውጤታማ ሀገራዊ ምክክር" በሚል መሪ ሃሳብ ከፌዴራል፣ ከክልል፣ ከግል የሚዲያ አመራሮችና ከፍተኛ ባለሙያዎች ጋር እየመከረ ነው። አቶ እውነቱ፤ የምክክር ኮሚሽኑን በተመለከተ ከገለልተኝነት ጋር ተያይዞ የሚቀርብበት ወቀሳ በሕግ የተፈታ ነው ሲሉም ተናግረዋል። ኮሚሽኑ ተጠሪነቱ ለምክር ቤቱ ቢሆንም፤ ምክር ቤቱ ስራውን ከማገዝ ያለፈ ጣልቃ አይገባበትም ነው ያሉት። መገናኛ ብዙኀንም የተሳካ ምክክር እንዲደረግና ልዩነቶች በሰለጠነ መንገድ እንዲፈቱ አቅም ሊሆኑ እንደሚገባም ገልጸዋል።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid04hxbS8AFHy8nHr5gMtGK3NaiJXkXZP9yDSbacoPfHRbmRgWx22GSabBmg5kkJduRl
إظهار الكل...
👍 2
ፓስፖርት በሀገር ውስጥ እንዲታተም የሚያስችል ሥራ እየተከናወነ ነው - የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ********************** በተያዘው ዓመት ፓስፖርት ጠይቀው ይጠባበቁ ከነበሩ ዜጎች መካከል ከ600 ሺህ በላይ ለሚሆኑት መስጠት መቻሉን የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ገልጿል። የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል የፓስፖርት አገልግሎት አንዱ እና ዋንኛው ነው። ይሁን እንጂ የፓስፖርት አሰጣጥን በተመለከተ የሚነሱ ቅሬታዎችን በተደጋጋሚ ይስተዋላል። ኢቢሲም ይህን ጉዳይ በተመለከተ ተደጋጋሚ ዜናዎች መስራቱ ይታወሳል። በኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ከሚነሱ ቅሬታዎች አንዱ መጉላላት ነው የሚለው የአዲስ አበባ ነዋሪው አቶ ያሬድ መንግሥቱ፤ እርሱ ራሱም ላላገኘው አገልግሎት ሁለት ቀን በሰልፍ መጉላላቱን ለኢቢሲ ሳይበር ተናግሯል። https://www.ebc.et/newsdetails.aspx?newsid=6743
إظهار الكل...
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ስትራይድ ኢትዮጵያ ኤክስፖን ጎበኙ ***************** ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እና ሚኒስትሮች ስትራይድ ኢትዮጵያ ኤክስፖን መጎብኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል። ስትራይድ ኢትዮጵያ 2024 ኤክስፖ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ግንቦት 10 ቀን 2016 ዓ.ም በይፋ መከፈቱ ይታወቃል። ዓመታዊው ኤክስፖ "ሳይንስ በር ይከፍታል፤ ቴክኖሎጂ ያስተሳስራል፤ ፈጠራ ወደ ፊት ያራምዳል" በሚል መሪ ሀሳብ በሳይንስ ሙዚየም እስከ ግንቦት 18 ቀን 2016 ዓ.ም ለሕዝብ ዕይታ ክፍት ሆኖ ይቆያል። ትኩረቱን ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራና ዲጂታላይዜሽን ላይ ያደረገው ስትራይድ ኢትዮጵያ ኤክስፖ በርካታ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ተቋማትን በማሳተፍ ላይ ይገኛል። በኤክስፖው ላይ የመንግሥትና የግል ተቋማት እንዲሁም ስታርት አፖች የቴክኖሎጂ ፈጠራ ሥራዎችን ለዕይታ አቅርበዋል።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid024mftynvRRd4Mjn2SqrC9jEohuxaPFLoguaxAHxpnpatNtCkYpErJJyHkys23SwFjl
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ቀጣይነት ባለው አግባብ በተደራጀ ህዝባዊ ንቅናቄ ሊተገበሩ ይገባል:- ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ************* የአካባቢ ጥበቃ እና የአረንጓዴ ልማት ስራዎች ቀጣይነት ባለው አግባብ በተደራጀ ህዝባዊ ንቅናቄ ሊተገበሩ ይገባል ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ገለጹ። ርዕሰ መስተዳድሩ፤ በክልሉ በልግ አብቃይ አካባቢዎች እየጣለ ካለው መደበኛና ከመደበኛ በላይ ከፍ ያለ ዝናብ ስርጭትና መጠን ጋር ተያይዞ የተወሰነ የጎርፍና መሰል የተፈጥሮ አደጋ በአንዳንድ አካባቢዎች መስተዋሉ የተፈጥሮ ሐብት ጥበቃ ስራዎችን ይበልጥ ማጠናከር እንደሚገባ ጠቋሚ መሆኑን ተናግረዋል። በክልሉ የሚሰሩ የቅድመ የመከላከልና ጥንቃቄ ስራዎች እንደተጠበቁ ሆነው፤ በየአካባቢው የተፈጥሮ አደጋ ተጋላጭነትን በዘላቂነት ለመከላከል የአካባቢ ጥበቃ ስራን ማጠናከር ይገባል ብለዋል። የክልሉ መንግስት ለአካባቢ ጥበቃና ለአረንጓዴ ልማት ስራዎች ከፍተኛ ትኩረት መስጠቱን ገልጸው፤ በተለይ ለተፈጥሮ ሐብት ልማት፣ ለአፈርና ውኃ ጥበቃ፣ ለተራራ ልማት እና ለአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ልዩ ትኩረት መደረጉን ነው የጠቀሱት።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0UrUB5uExs9yVLFbdpriH9ubXeBoeXwJsKysgdmoY255Szoq1hexQbRxJzkDSEg39l
إظهار الكل...
15👍 6👏 2
የሰላም ሚኒስቴር በሰሜን አሜሪካ ከሚገኘው የስተርሊንግ ፋውንዴሽን አመራሮች ጋር በሰላም ግንባታ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሄደ ************************ የሰላም ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች ቡድን በሰሜን አሜሪካ ዩታሀ ግዛት ከሚገኘው የስተርሊንግ ፋውንዴሽን መሪዎች ጋር በሰላም ግንባታ ዙሪያ በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል። በኢትዮጵያ በተለያዩ የሰላም ግንባታ ተግባራት ድጋፍ እያደረገ ከሚገኘው ስተርሊንግ ፋውንዴሽን አመራሮች ጋር ድጋፉ ተጠናክሮ በሚቀጥልበት መንገዶች ዙሪያ ለመወያየት በሰላም ሚኒስትሩ አቶ ብናልፍ አንዷለም የሚመራው ቡድን በግዛቷ መዲና ሳልት ሌክ ከተማ ጉብኝት በማካሄድ ላይ ይገኛል። ቡድኑ በግዛቲቱ የሰብዓዊ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት፣ የተለያዩ ሀይማኖቶች በመከባበርና በሰላም አብረው በአካባቢው ሰላም፣ አብሮነትና መከባበር ለማምጣት የሚያከናውኑት ተግባርና የተገኘውን ውጤት ተዟዙረው ጎብኝተዋል።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02jwneEJBYA5vqiu3qzjjvVNNNYjaZ37D7kPFsmyK1p3L5Eg6M81xNvY1NajVcbxbZl
إظهار الكل...
👍 7👏 3
Photo unavailableShow in Telegram
የዕለቱ የውጭ ምንዛሬ ዋጋ
إظهار الكل...
👍 6 1
Photo unavailableShow in Telegram
የኢቢሲን አዳዲስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን በዋትስአፕ አማራጭ Follow EBC on our new WhatsApp channel https://whatsapp.com/channel/0029VaVefI79xVJoMGtunX2T
إظهار الكل...
👍 23 7👏 7
ባለፉት ጥቂት አመታት ዋናውን የዝናብ ወቅት ምርት ሳናስተጓጉል የበጋ ስንዴ ልማት ጥረታችንን ለማስፋፋት ችለናል። የዛሬው ምልከታ የስራዎችን ቀጣይነት የተመለከትንበት ነበር። ግብርና ጠንካራ ኢንቨስትመንት ይፈልጋል። በሰብል የምንሸፍነው የመሬታችን ይዞታም ቀስ በቀስ በመጨመር ላይ ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02waGXZW9S5uzfBsB9bVnZ2jmf2YfHTCnKRLki48aCCzmxDiKuHP1rP4vJdcYW11isl
إظهار الكل...
Ethiopian Broadcasting Corporation

ባለፉት ጥቂት አመታት ዋናውን የዝናብ ወቅት ምርት ሳናስተጓጉል የበጋ ስንዴ ልማት ጥረታችንን ለማስፋፋት ችለናል። የዛሬው ምልከታ የስራዎችን ቀጣይነት የተመለከትንበት ነበር። ግብርና ጠንካራ ኢንቨስትመንት ይፈልጋል። በሰብል የምንሸፍነው የመሬታችን ይዞታም ቀስ በቀስ በመጨመር ላይ ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ...

👍 22👏 5 4👎 2