cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

Ethiopian Broadcasting Corporation (EBC)

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
123 571
المشتركون
+13324 ساعات
+3387 أيام
+1 66730 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

አፍሪካ እና አውሮፓ በባቡር ትራንስፖርት ሊገናኙ ነው *********************** ለ2030ው የዓለም ዋንጫ አፍሪካ እና አውሮፓ በባቡር ትራንስፖርት ሊገናኙ መሆኑ ተገለጸ። በስፔን ፖርቹጋል እና ሞሮኮ አስተናጋጅነት እንደሚካሄድ በሚጠበቀው የ2030ው ዓለም ዋንጫ አፍሪካ እና አውሮፓ በባቡር ትራንስፖርት ለማገናኘት ታቅዷል ተብሏል። ሞሮኮ እና ስፔን በጋራ የባቡር ትራንስፖርት መስመሩን ለመገንባት ጥረት መጀመራቸው ተገልጿል።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02VZjmZwMtgvQ63PE94kQ2osY6bijbeac2EcEh4FoAbWFnHU4scpy9C6h6cuaLwCm7l
إظهار الكل...
Ethiopian Broadcasting Corporation

አፍሪካ እና አውሮፓ በባቡር ትራንስፖርት ሊገናኙ ነው *********************** ለ2030ው የዓለም ዋንጫ አፍሪካ እና አውሮፓ በባቡር ትራንስፖርት ሊገናኙ መሆኑ ተገለጸ። በስፔን ፖርቹጋል እና ሞሮኮ አስተናጋጅነት እንደሚካሄድ በሚጠበቀው የ2030ው ዓለም ዋንጫ አፍሪካ እና አውሮፓ በባቡር ትራንስፖርት...

👍 23 2👏 2
የትግራይ ክልል ክለቦች ከ2017 ጀምሮ ከጦርነቱ በፊት ወደነበሩበት ሊግ ተመልሰው እንዲወዳደሩ ውሳኔ ተላለፈ ******************** የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ባደረገው መደበኛ ስብሰባ፥ የትግራይ ክልል ክለቦች ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ ከጦርነቱ በፊት ሲወዳደሩበት ወደነበረው ሊግ ተመልሰው እንዲወዳደሩ ውሳኔ አሳልፏል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ውሳኔውን ተግባራዊ እንዲያደርጉ ለሚመለከታቸው አካላት በደብዳቤ ያሳወቀ ሲሆን፤ ለኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ/ማ በተላከው ደብዳቤም ሊጉ በ2017 የወድድር ዘመን በ19 ቡድኖች መካከል ተደርጎ 5 ቡድኖች ወደ ከፍተኛ ሊግ እንዲወርዱ በማድረግ በ2018 ከዚህ ቀደም ወደነበነረበት 16 ክለቦች እንዲመለስ አቅጣጫ መቀመጡን ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። https://www.facebook.com/EBCSPORT/posts/pfbid02anFTwKycGrc3J2U321yvXynymXDvW95D52mgPdTbMS8mabEMydbhAKR5DsKYFPwLl
إظهار الكل...
👍 46👏 9 4
የትግራይ ክልል ክለቦች ከ2017 ጀምሮ ከጦርነቱ በፊት ወደነበሩበት ሊግ ተመልሰው እንዲወዳደሩ ውሳኔ ተላለፈ ******************** የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ባደረገው መደበኛ ስብሰባ፥ የትግራይ ክልል ክለቦች ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ ከጦርነቱ በፊት ሲወዳደሩበት ወደነበረው ሊግ ተመልሰው እንዲወዳደሩ ውሳኔ አሳልፏል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ውሳኔውን ተግባራዊ እንዲያደርጉ ለሚመለከታቸው አካላት በደብዳቤ ያሳወቀ ሲሆን፤ ለኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ/ማ በተላከው ደብዳቤም ሊጉ በ2017 የወድድር ዘመን በ19 ቡድኖች መካከል ተደርጎ 5 ቡድኖች ወደ ከፍተኛ ሊግ እንዲወርዱ በማድረግ በ2018 ከዚህ ቀደም ወደነበነረበት 16 ክለቦች እንዲመለስ አቅጣጫ መቀመጡን ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። https://www.facebook.com/EBCSPORT/posts/pfbid02anFTwKycGrc3J2U321yvXynymXDvW95D52mgPdTbMS8mabEMydbhAKR5DsKYFPwLl
إظهار الكل...
EBC SPORT

የትግራይ ክልል ክለቦች ከ2017 ጀምሮ ከጦርነቱ በፊት ወደነበሩበት ሊግ ተመልሰው እንዲወዳደሩ ውሳኔ ተላለፈ ******************** የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ባደረገው መደበኛ ስብሰባ፥ የትግራይ ክልል ክለቦች ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ ከጦርነቱ በፊት ሲወዳደሩበት...

የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር አዋጅ በአከራይም ሆነ በተከራይ ላይ ጫና በማይፈጥር መልኩ ወደ መሬት እንዲወርድ እንሰራለን፡- ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ****************** በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት መጋቢት 24 ቀን የጸደቀው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር አዋጅ መጽደቁን ተከትሎ ለተግባራዊነቱ እየተሰራ መሆኑን የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ገለጸ። የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ ከኢቲቪ 57 ጋር በነበራቸው ቆይታ፥ የዜጎችን መሰረታዊ የመኖሪያ ቤት ችግር ዘላቂ በሆነ መልኩ ለመፍታት በተጠናከረ መልኩ እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል። ነገር ግን ዜጎች ከገጠር ወደ ከተማ የሚያደርጉት ፍልሰት ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ የመኖሪያ ቤት ፍላጎትም ጨምሯል ብለዋል። https://ebc.et/newsdetails.aspx?newsid=6588
إظهار الكل...
የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር አዋጅ በአከራይም ሆነ በተከራይ ላይ ጫና በማይፈጥር መልኩ ወደ መሬት እንዲወርድ እንሰራለን፡- ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ

በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት መጋቢት 24 ቀን የጸደቀው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር አዋጅ መጽደቁን ተከትሎ ለተግባራዊነቱ እየተሰራ መሆኑን የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ገለጸ።  የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ ከኢቲቪ 57 ጋር በነበራቸው ቆይታ፥ የዜጎችን መሰረታዊ የመኖሪያ ቤት ችግር ዘላቂ በሆነ መልኩ ለመፍታት በተጠናከረ መልኩ እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።  ነገር ግን ዜጎች ከገጠር ወደ ከተማ የሚያደርጉት ፍልሰት ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ  እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ የመኖሪያ ቤት ፍላጎትም ጨምሯል ብለዋል።  የመኖሪያ ቤት አቅርቦት ችግርን በዘላቂነት ለመፍታት 80 በመቶውን የግሉ ዘርፍ፣ 20 በመቶውን ደግሞ መንግሥት እንዲያለማ ስትራቴጂ ተቀምጦ እየተሰራ ይገኛል ነው ያሉት።  የመኖሪያ ቤት ግንባታ ክፍተቱን ለመድፈን በመንግሥትና በግል አጋርነት በቅንጅት እየተከናወነ ያለው ስራም ውጤታማ እየሆነ ነው ብለዋል።  በየትኛውም ሃብታም አገር ሁሉንም ሰው የመኖሪያ ቤት ባለቤት ማድረግ አይቻልም የሚሉት ሚኒስትሯ፤ ዜጎች በአቅማቸው የተረጋጋ ኑሮ እንዲኖሩ ለማስቻል የኪራይ ቤቶችን በአማራጭነት ለማቅረብ መስራት እንደሚገባም ተናግረዋል።  በአደጉ አገራት ሰራተኞች ከደመወዛቸው ከ20 እስካ 30 በመቶ ለቤት ኪራይ ወጪ የሚያደርጉበት ልምድ ተወስዷል ያሉት ወ/ሮ ጫልቱ፤ እንደኛ ባሉ አገራት ደግሞ ሰራተኛው ሙሉ ደመወዙን ለቤት ኪራይ ወጪ ሊያደርግ እንደሚችል አንስተዋል።  ይህ ችግር በሰራተኛው ህይወት ላይ ማህበራዊ ቀውስ እየፈጠረ በመሆኑ የመንግስት ጣልቃ ገብነት አስፈላጊ ሆኗል ነው ያሉት ሚኒስትሯ።  የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር አዋጁ በአከራይም ሆነ በተከራይ ላይ ጫና አይፈጥርም ያሉት ሚኒስትሯ፤ ትክክለኛና ሚዛናዊ በሆነ መልኩ ወደ መሬት…

👍 25 3
የኢትዮጵያ አየር ኃይል ለመላው ኢትዮጵያውያን የኩራት ምንጭ የሆነ ታላቅ ተቋም ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ **************** በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተመራ የአስተዳደሩ የስራ ኃላፊዎች ቡድን በኢፌዴሪ አየር ኃይል ጉብኝት አድርጓል። በጉብኝቱ ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ አየር ኃይል በላቀ የስራ ትጋትና ጥራት እንደ ሀገር ያለንን ሀብት ተጠቅሞ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል አንዱ ማሳያ የሆነ ተቋም ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡ በተለይም ከተጣለበት ሀገራዊ ተልዕኮ ባሻገር በግብርናው ልማት በኩል ቀድሞ አላግባብ ጥቅም አልባ ተደርጎ የነበረውን የተቋሙን መሬት ወደ ልማት በመቀየር ያስመዘገበው ታላቅ ስኬት በሀገር ደረጃም አርዓያነት ያለው አኩሪ ስራ መሆኑን ተናግረዋል። በሰላም ወጥቶ ለመግባትም ብቻ ሳይሆን እንደ ሀገር ለተያዘው የልማት ጉዞ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ያፀናው ሰላም ወሳኝ መሆኑን ያነሱት ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ለመላው ኢትዮጵያውያን የኩራት ምንጭ የሆነ ታላቅ ተቋም ነው ብለዋል። https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0WkygJR84sG8g9meW4pH2SJkmQF9fWrTVtq95ScQECGqUT73LrUQnJp96qtyMHWf6l
إظهار الكل...
የሠራተኛው ትግል ከኢንዱስትሪ አብዮት እስከ ሰው ሠራሽ አስተውሎት ስጋት ************* ኢንዱስትሪ እየተስፋፋ የነበረበት 19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሠራተኛው በርካታ የመብት ጥያቄዎችን ያነሳ የነበረበት ጊዜ ነበር፡፡ ከነዚህ ጥያቄዎች መካከልም የተመጣጣኝ ከፍያ፣ የሥራ ሰዓት፣ የመደራጀት እና ሌሎች ይገኛሉ፡፡ በሥራ ላይ በሚደርስ አደጋ ሕይወትን ማጣት፣ አካል መጉደል፣ ለዘላቂ የጤና ችግር መዳረግ እና ሌሎች ለሰው ልጆች ምቹ ያልሆኑ ሁኔታዎች ጥያቄው መሰረታዊ እንዲሆን ማድረጋቸውን የሠራተኛውን ትግል የሚያወሱ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ሠራተኞች ትግላቸውን ቀጥለው ምቹ ባልሆነ የሥራ አካባቢ ከ10 እስከ 16 ሰዓታት የነበረው የሥራ ሰዓት 8 ሰዓት ብቻ ሆኖ የሙሉ ቀን ደመወዝ እንዲከፈላቸው መጠየቅ ቢጀምሩም፣ የዘመኑ አሠሪዎቻቸው ግን ለጥያቄው ምላሽ መስጠት አልፈለጉም ነበር፡፡ ይህ የከበርቴዎች ለሠራተኛው ጥያቄ ጆሮ ዳባ ልበስ ማለት ግን ሠራተኞች የበለጠ ተደራጅተው ጥያቄያቸውን እንዲገፉበት አደረጋቸው:: ነገር ግን ቀጣሪዎቹ በማይመች አካባቢ እና የአየር ሁኔታ ውስጥ በቀን ለረዥም ሰዓታት በማሠራት ከፍተኛ ትርፍ ማጋበስ የለመዱ በመሆናቸው በቀላሉ ጥያቄዎቹን ለመመለስ ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡ በሠራተኛው እንቅስቃሴ የተበሳጩት እና መጪው ሁኔታ ያሳሰባቸው አሠሪዎች “አድማ ቀስቅሳችኋል፤ ምርታማ መሆን አልቻላችሁም፤ እኛ በምንፈልጋችሁ ሁኔታ እየሠራችሁ ስላልሆነ አንፈልጋችሁም” በማለት በርካታ ሠራተኞችን ከሥራ ማሰናበት ጀመሩ:: https://ebc.et/newsdetails.aspx?newsid=6587
إظهار الكل...
ሰሙነ ሕማማት
إظهار الكل...
43👍 8
ክልሉ ከአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ተጠቃሚነቱን ለማሳደግ በመስራት ላይ ይገኛል - አቶ ጥላሁን ከበደ ************* በኢትዮጵያ በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ የገቢ ምርትን 85 በመቶ በአገር ውስጥ ምርት ለመተካት ጥረት በመደረግ ላይ መሆኑ ይታወቀል። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥትም በክልሉ ፈጣን ዕድገት በማስመዘገብ ህዝቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ትኩረት ከሰጣቸው የልማት ዘርፎች አንዱ የኢንዱስትሪው ዘርፍ ነው። ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ክልሉ ለአምራች ኢንዱስትሪ ልማት እምቅ አቅም ያለው መሆኑን ጠቅሰው፤ በክልሉ ያለውን የመልማት ፀጋ በመለየትና አሟጦ በመጠቀም ከዘርፉ የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ማሳደግ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል። https://ebc.et/newsdetails.aspx?newsid=6586
إظهار الكل...
ክልሉ ከአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ተጠቃሚነቱን ለማሳደግ በመስራት ላይ ይገኛል - አቶ ጥላሁን ከበደ

በኢትዮጵያ በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ የገቢ ምርትን 85 በመቶ በአገር ውስጥ ምርት ለመተካት ጥረት በመደረግ ላይ መሆኑ ይታወቀል። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥትም በክልሉ ፈጣን ዕድገት በማስመዘገብ ህዝቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ትኩረት ከሰጣቸው የልማት ዘርፎች አንዱ የኢንዱስትሪው ዘርፍ ነው። ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ክልሉ ለአምራች ኢንዱስትሪ ልማት እምቅ አቅም ያለው መሆኑን ጠቅሰው፤ በክልሉ ያለውን የመልማት ፀጋ በመለየትና አሟጦ በመጠቀም ከዘርፉ የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ማሳደግ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል። ለዚህም ክልሉ ያለውን አቅም በመጠቀም እና የግል ዘርፉን በስፋት በማሳተፍ የአምራች ኢንዱስትሪ ልማትን ለማሳደግ እና ለማስፋፋት ትኩረት ተሰጥቶ በመሰራት ላይ መሆኑን ገልጸዋል። በተለይ የኢንዱስትሪ ተቋማትን በክላስተር በማቋቋም ሰፊ የስራ ዕድል መፍጠር የሚችሉ እና ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ማጠናከርና ማስፋፋት የክልሉ ዋነኛ ትኩረት መሆኑን ተናግረዋል። በክልሉ ሀብት ያፈሩ አርሶና አርብቶ አደሮችን በኢንዱስትሪው ዘርፍ በማሳተፍ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማስቻልም ትኩረት የተሰጠው መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል። የክልሉ መንግሥት በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ የሚያበረታታ መሆኑን ጠቁመው ባለሀብቶች በክልሉ ኢንቨስት በማድረግ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ ማቅረባቸውን ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

👍 14 4👏 1
ለ2016/17 የምርት ዘመን ከ12 ሚሊየን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ከውጭ መጓጓዙ ተገለፀ *************** ለ2016/17 የምርት ዘመን ከተገዛው የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ እስከአሁን ከ12 ሚሊየን ኩንታል በላይ ከውጭ ተጓጉዞ ጂቡቲ ወደብ መድረሱን የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢግሥኮ) አስታወቀ። ወደብ ከደረሰው ማዳበሪያ 11 ሚሊየን 79 ሺህ 21 ኩንታል ወደ ሀገር ውስጥ ተጓጉዞ በመሠረታዊ የኅብረት ሥራ ማኅበራት አማካኝነት ለአርሶ አደሮች እየቀረበ መሆኑም ተጠቁሟል። ትላንት ሚያዝያ 22 ቀን 2016 ዓ.ም 636 ሺህ 600 ኩንታል ኤን ፒ ኤስ ቦሮን የጫነች መርከብ ጂቡቲ ወደብ መድረሷ ተጠቅሷል፡፡ በተመሳሳይ ከ11 ቀናት በኋላ 543 ሺህ ኩንታል ተጨማሪ ኤን ፒ ኤስ ቦሮን የአፈር ማዳበሪያ ወደብ ይደርሳል ተብሎ እንደሚጠበቅም ከኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
إظهار الكل...
የኦሮሚያ ሕብረት ስራ ባንክ "ማስተር ካርድ" እና "ኮሚኒቲ ፓስ" የተሰኙ የዲጂታል አገልግሎቶችን በስራ ላይ አዋለ ********************* የኦሮሚያ ሕብረት ስራ ባንክ "ማስተር ካርድ" እና "ኮሚኒቲ ፓስ" የተሰኙ የዲጂታል አገልግሎቶችን በዛሬው ዕለት በስራ ላይ አውሏል። ባንኩ አገልግሎቶቹን ከማስተር ካርድ ጋር በመተባበር ነው በስራ ላይ እንዲውሉ ያደረገው። "ማስተር ካርድ" ለውጭ ሀገር ተጓዦች የታለመ የቅድመ ክፍያ አገልግሎት ሲሆን፤ ተጓዦቹ በሚሄዱበት ሀገር የሚያስፈልጋቸውን ገንዘብ በብር በመክፈል በውጭ ሀገር ተሰልቶ የሚሞላላቸው ይሆናል። ከዚህም ባሻገር አገልግሎቱ ተጓዦቹ በሄዱበት ሀገር ሁሉ መጠቀም የሚያስችል ነው ተብሏል። በተጨማሪም ባንኩ በ"ኮሚኒቲ ፓስ" የቀረበ "ኮፕ ፋርም ፓስ" የተሰኘ የዲጂታል አገልግሎት በስራ ላይ አውሏል። "ፋርም ፓስ" የግብርና ምርት ሂደትን የማሳለጥ እና የአርብቶ አደሮች እና ሕብረት ስራ ማህበራትን ትስስር ያጠናክራል ተብሏል። በአሚር ጌቱ
إظهار الكل...