cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

GRAZMACH-HIGH-SCHOOL-E-LIBRARY/BONGA/

-ተማሪዎች የትምህርት መረጃዎችን, ኖቶችን, መማሪያ መጽሀፍትን በቀላሉ እንዲያገኙ ታስቦ የተዘጋጀ ቻናል ነው:: -ከተለያዩ ት/ቤቶች ተዘጋጅተው በቴለግራም የተለቀቁ model_exam,handout እና ሌሎች ተያያዥ መረጃዎች በማቅረብ ተማሪዎች ለብሄራዊ ፈተና(National exam) ዉጤታማ እንድሆኑ የሚረዳቸው የትምህርት ቻናል ነው። -ቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች የሚቀርብበት ምርጥ ቻናል ነው::

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
279
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+27 أيام
+930 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

የሚኒስትሪ መልስ መስጫ ወረቀት አጠቃቀም መመሪያ ለተማሪዎች ➊ የተማሪዎች መለያ ቁጥር እና የትምህርት ዓይነት መለያ ቁጥር ለእያንዳንዳቸው በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ከላይ ወደ ታች መፃፍ አለበት፡፡ ❷ በተፃፈው መለያ ቁጥር ፊት ለፊት የተፃፈውን ቁጥር የያዘውን ክብ ብቻ መጠቆር አለበት፡፡ ➌ ተማሪዎች የመረጡትን መልስ ትይዩ በተሰጠው ክብ ላይ በትክክል ማጥቆር አለባቸው፡፡ ❹ ተማሪዎች ያጠቆሩትን መልስ መቀየር ቢፈልጉ መጀመሪያ ያጠቆሩትን ክብ በደንብ ማጥፋት አለባቸው፡፡ ❺ በአንድ ረድፍ ከአንድ በላይ ክብ ማጥቆር የተከለከለ ነው፡፡ ❻ ለመፃፍ እና ለማጥቆር ከተፈቀደው ቦታ ውጭ ምንም አይነት ፅሁፍም ሆነ ጭረት ማድረግ የተከለከለ ነው፡፡ ❼ ለመፃፍ ከተፈቀደው ቦታ ውጭ ተፅፎ ወይም ትንሽ ጭረት እና ነጥብ ከተገኘ የመልስ መስጫ ወረቀቱ ሙሉ  በሙሉ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ ❽ መልስ በሚጠቆርበት ጊዜ እርሳሱ ከተሰጠው የክብ ሳጥን መውጣት የለበትም። ከወጣም በማጥፊያ (Eraser/Rubber) ማጥፋት ይጠበቅባችኋል። ❾ መልስ መስጫ ኮርነር ላይ ያሉትን አራት ጠርዞች መንካትም ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡ ➓ ተፈታኞች የመልስ መስጫ ወረቀታቸውን በንፅህና መያዝ አለባቸው ማለትም እንዳይቆሽሽ፣ እርጥበት  እንዳይነካው፤ እንዳይቀደድ እና እንዳይታጠፍ መጠንቀቅና ሙሉ ኃላፊነት መውሰድ አለባቸው፡፡ 11. በእስኪብርቶ መፃፍ አይፈቀድም። ስለዚህ እርሳስ፣ ላጲስ እና መቅረጫ አይለያችሁ 12. ፈተና ጨረስኩ ብሎ አላስፈላጊ ነገር ስዕል ወይም ሌላ ከጀርባም ይሁን ከፊት አይፃፍበትም 13. በጣም የተቀረፀ ሹል እርሳስ በምንጠቀም ወቅት ወረቀቱ እንዳይቀደድ መጠንቀቅ አለብን። ትምህርት ሚኒስቴር https://t.me/Tmhrt_Minister https://t.me/Tmhrt_Minister
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
ትልቅ ደረጃ መድረስ ከፈለጋችሁ! በእድሜ ቆጠራ ብቻ፣ በገንዘብ ብዛት ብቻ፣ በአእምሮ እውቀትም ብቻ . . . ትልቅ ደረጃ መድረስ አይቻልም፡፡ እነዚህንና ሌሎችም ነገሮች ኖሯቸው በሕብረተሰቡ መካከል ትልቅ ደረጃ የደረሱ ሰዎች የመኖራቸውን ያህል፣ እነዚህ ነገሮች እያሏቸው ለአናሳ ነገር ሰክነውና አናሳ ሕይወት ኖረው የሚያልፉ ጥቂቶች አይደሉም፡፡ ትልቅ ደረጃ መድረስ ከፈለጋችሁ፡- 1. ከትንሽነት አመለካከት መውጣት አስፈላጊ ነው፡፡ አመለካከታችን ዛሬ ካለንበት ደረጃችን ወደላቀ ከፍታ የሚያወጣንን ራእይና አላማ ካላካተተ ይህ የአመለካከታችን ትንሽነት የማንነት አናሳነት መፍጠሩ አይቀርም፡፡ 2. ከትንንሽ ንግግሮች መላቀቅ የግድ ነው፡፡ የምናወራቸው ነገሮች በእለቱ ከሚናፈሰውና የሰውን ነገር ከመብላት አልፎ ካልሄደ የንግግራችን አናሳነት የማንነት ትንሽነት መፍጠሩ አይቀርም፡፡ 3. ከትንንሽ ገጠመኞች በላይ መኖር ወሳኝ ነው፡፡ በየቀኑ የሚገጥሙንን ጥቃቅን አስቸጋሪ ገጠመኞች አልፈን በመሄድ ትኩረታችንን ዋናውና ዘላቂው የሕይወታችን አላማ ላይ ካላደረግን ሁኔታው የማንነት አናሳነት መፍጠሩ አይቀርም፡፡፡፡ 4. ከትንንሽ ዘሮች ዘልቆ መሄድ ጠቃሚ ነው፡፡ ትንሽ ዘር፣ ትንሽ ፍሬ … ትንሽ ሙከራ፣ ትንሽ ስኬት … ትንሽ መስዋእትነት ትንሽ ዋጋ … ትንሽ እቅድ፣ ትንሽ ውጤት ስሌቱ ይኸው ነው፡፡ ከዚህ አዙሪት ወጥተን በትልቁ መዝራት ካልጀመረን ሁታው የማንነት አናሳነት መፍጠሩ አይቀርም፡፡
إظهار الكل...
ለተማሪዎች የሚጥቅሙ የAI ቱሎች 🌟Academic Help https://academichelp.net/ = Assists students and writers in creating high-quality essays 🌟Wisdolia https://www.wisdolia.com/ = Generate flashcards and multiple choice questions in seconds. 🌟Grammarly https://www.grammarly.com/ Real-time grammar, tone, and plagiarism checker 🌟Smodin https://smodin.io/ Elevate writing, research, and homework with AI, multilingual 🌟POE https://poe.com/ Enhance user interactions with adaptable, intelligentShare for Others ══════════════ ይ🀄️ላ🀄️ሉን👇👇👇 share👇 https://t.me/GrazmachPaulosElibrar
إظهار الكل...
Academic Help: Number 1 Place For Your Educational Tools & Learning Hub

Quickly complete your homework, find out how to write any assignment, and check your tasks for mistakes with a selection of tools and guides from Academic Help.

ለተማሪዎች የሚጥቅሙ የAI ቱሎች 🌟Academic Help https://academichelp.net/ = Assists students and writers in creating high-quality essays 🌟Wisdolia https://www.wisdolia.com/ = Generate flashcards and multiple choice questions in seconds. 🌟Grammarly https://www.grammarly.com/ Real-time grammar, tone, and plagiarism checker 🌟Smodin https://smodin.io/ Elevate writing, research, and homework with AI, multilingual 🌟POE https://poe.com/ Enhance user interactions with adaptable, intelligent 🌐 ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ 💻ይ🀄️ላ🀄️ሉን👇👇👇 share👇 https://t.me/GrazmachPaulosElibrary
إظهار الكل...
Academic Help: Number 1 Place For Your Educational Tools & Learning Hub

Quickly complete your homework, find out how to write any assignment, and check your tasks for mistakes with a selection of tools and guides from Academic Help.

ምርጥ 9 ድረገፆች 📲 Unscreen.com የአንድን video back ground ለማጥፋት እና video quality ለመጨመር። 📲 math.he.net ማንኛውንም የmaths ጥያቄ መስራት የምትችሉቀት website ነው ጅ። 📲 ALLPCWORLD.COM በጣም ብዙ እና አዳዲስ software ታገኙበታላችሁ። 📲 IFIXIT.COM ማንኛውንም ነገር ሲበላሽባችሁ የትም ሳትሄዱ እራሱ GUIDE እያረገ እንድትሰሩት ያስችላችኋል ለምሳሌ ስልክ፣ ላፕቶፕ፣ TV፣ REDIO፣ ሳይክል የመሳሰሉትን። 📲 Accountingcouch.com Accounting የምትማሩ ከሆነ በጣም ይጠቅማችኋል። 📲 bit.ly/learn-eh2 በነፃ ethical hacking (hacking) የምትማሩበት web site ነው ሰርተፍኬትም አለው። 📲 durable.ai በ 5 ደቂቃ ብቻ ገራሚ AI WEB SITE የምትሰሩበት WEB SITE ነው ከናንተ የሚጠበቀው ስለምትፈልጉት website መፃፍ ነው እራሱ ይጨርስላችኋል። 📲 Podcast.adobe.com video record ያደረጋችሁትን Video አላስፈላጊ ድምፅ ያጠፋላችኋል እንዲሁም የvoice quality ይጨምርላችኋል። 📲 https://www.logoai.com/ የተለያዩ logo በነፃ ይሰራላችኋል ከናንተ የሚጠበቀው ስም ማስገባት ብቻ ነው። 🌐 ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ 💻ይ🀄️ላ🀄️ሉን👇👇👇 share👇 https://t.me/GrazmachPaulosElibrary
إظهار الكل...
Become an Ethical Hacker in easy steps with this free online course

Learn about reconnaissance, protocols, Windows hacking and pentesting wireless networks to attack web technologies as an ethical hacker or cybersecurity expert.

ላፕቶፓችን ያለኛ ፍቃድ ፍላሽ ዲስክ እንዳይቀበል ማድረግ እንዴት እንደ ሚቻል ላሳያችሁ። ⚡️ፍላሽ ዲስክ ፋይሎችን የምናስቀምጥበትና በቀላሉ ይዘነው የምንቀሳቀሰው ማሽን ነው፡፡ በስራ ምክንያትም ይሁን በሌላ ፋይሎችን ለማስተላለፍና ኮፒ ለማድረግ ሰዎች የሚጠቀሙበት ፍላሽ ዲሰኮች ላፕቶፓችን ላይ እንሰካል፡፡ ⚡️ላፕቶፓችን ላይ ያገኘነውን ፍላሽ ዲስክ የምንሰካ ከሆነ ደሞ ላፕቶፓችን አደጋ ውስጥ ይገባል፡፡ ምክንያቱም ፍለሽ ዲሰክ ፋይሎችን ብቻ ሳይሆን ቫይረሶችንም ስለሚያስቀምጥ ያገኘነውን ፍላሽ ላፕቶፓችን ላይ የምንሰካ ከሆነ በፍላሽ ዲሰኮች አማካኝነት ቫይረሶች ወደ ኮፒውተራችን በመግባት ላፕቶፓችን ላይ አደጋ ሊያደርሱ ይችላል፡፡ ⚡️ከኛ ፍቃድም  ውጪ ሳናውቀው አንድ ሰው ተደብቆ ላፕቶፓችን ላይ ፍለሽ ዲሰክ በመሰካት ላፕቶፓችንን ክጥቅም ውጪ ሊያደርገው ይችላል፡፡ ⚡️ስለዚህ በተለይ ያለኛ ፍቃድና እውቀት ላፕቶፓችን ፍላሽ ዲሰክ እንዳይቀበል ለማድረግ የሚከተሉትን ስቴፖች መከተል ነው፡፡ 1ኛ፡-መጀመሪያ Start በተንን ክሊክ እናደርግና gpedit.msc ብለን እንፅፍና ኢንተር እንጫናል፣ 2ኘ፡- የተለያዩ አማራጮች የያዘ ሊስት ይመጣል፤ ሊስቱ ውስጥ “Local Group Policy Editor” የሚለውን ምረጡ፣ 3ኛ፡-ከዚያ የሚከተለውን መንግድ ተከተሉ ፤ computer configuration>administrative templates>system>Removable storage access 4ኛ፡-አሁን በቀኝ በኩል ከሚመጡ አማራጮች ውስጥ “All Removable Storage Classes: Deny all access” የሚለውን ክሊክ ማድረግ፣ 5ኛ፡- “Enable” የሚል አለ እሱን መምረጥ፣ 6ኛ፡- “Apply”> “Ok” ሁለቱንም ተራ በተራ ክሊክ ማድረግ፡፡ ⚡️አለቀ፡፡ ካሁን በኋላ ማንም ሰው ፍላሽ ዲስኩን ላፕቶፓችሁ ላይ መሰካት አይችልም፡፡ ⚡️ምናልባት ይህንን የከለከላችሁትን አክሰስ መመለስ ስትፈልግ ከላይ ከ1 እስከ 4 ስቴፖችን እንዳሉ ተከተሉ እና፣ 5ኛ፡- “Not Configure” የሚል አለ እሱን መምረጥ፣ 6ኛ፡- “Apply”> “Ok” ሁለቱንም ተራ በተራ ክሊክ በማድረግ ወደ ነበረበት መመለስ እንችላለን፡፡ ▬▬ ▬ Share ▬▬▬▬ ይ🀄️ላ🀄️ሉን👇👇👇 share👇 https://t.me/GrazmachPaulosElibrary
إظهار الكل...
GRAZMACH-HIGH-SCHOOL-E-LIBRARY/BONGA/

-ተማሪዎች የትምህርት መረጃዎችን, ኖቶችን, መማሪያ መጽሀፍትን በቀላሉ እንዲያገኙ ታስቦ የተዘጋጀ ቻናል ነው:: -ከተለያዩ ት/ቤቶች ተዘጋጅተው በቴለግራም የተለቀቁ model_exam,handout እና ሌሎች ተያያዥ መረጃዎች በማቅረብ ተማሪዎች ለብሄራዊ ፈተና(National exam) ዉጤታማ እንድሆኑ የሚረዳቸው የትምህርት ቻናል ነው። -ቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች የሚቀርብበት ምርጥ ቻናል ነው::

Photo unavailableShow in Telegram
ተማሪዎች በበይነ መረብ መፈተናቸው ስህተትን መቀነስን ጨምሮ በርካታ ጠቀሜታዎች እንዳሉት ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ። የበይነ መረብ ፈተና ለስህተት በር አይከፍትም የበይነ መረብ ፈተና አንድ ጥያቄ ሳይመልሱ ወደ ፈለጉት ጥያቄ በአንድ Click የመሔድ እንዲሁም ተመልሰው መስራት የሚፈልጉትን ጥያቄ Flag በማድረግ ተመልሶ የመስራት ዕድልን ይሰጣል። ጊዜ ቆጣቢ ነው በአንድ Click የፈተና ጥያቄን መልስ ለመስጠት ያስችላል። እንዲሁም ምን ያህል ደቂቃ እንደተጠቀሙ ከመፈተኛ ስክሪን ላይ ማየት ስለሚቻል ጊዜን በአግባቡ ለመጠቀም ያስችላል። የተሻሻለ የመረጃ ቋት አለው የበይነ መረብ ፈተናዎች በቂ የፈተና መረጃዎችን ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ በማከማቸት ለተፈታኞች አመጣጥኖ ያቀርባል፡፡ የተሰሩ ጥያቄዎችን መልስ በፍጥነት በራሱ ይልካል በፈተና ወቅት ጥያቄዎቹን ሰርተው ሳያጠናቀቁ የተሰጠው ደቂቃ ካለቀ የሰሩትን በጠቅላላ በራሱ በፍጥነት ይልካል። ፈጣን ግብረ መልስ ይሰጣል በበይነ መረብ ፈተናዎች ሲሰጡ ውጤታቸው ከሌላው ጊዜ በተለየ ፈጥኖ የመታወቅ ዕድል ይሰጣል። ተማሪዎች በቤታቸው እያደሩ እንዲፈተኑ ዕድል ይሰጣል ትምህርት ቤቶች የተደራጀ የኮምፒውተር ቤተሙከራ ካላቸውና የመፈተኛ ክላስተር ለመሆን አስፈላጊውን መስፈርቶች ማሟላታቸው ከተረጋገጠ ተማሪዎች በተማሩበት ትምህርት ቤት ሆነው እንዲፈተኑ ዕድል ይፈጥራል። #MoE @minster_of_education
إظهار الكل...
የማስታወስ ችሎታዎን ለማሻሻል 11 ዘዴዎች የሚከተሉት 11 በጥናት የተረጋገጡ ስልቶች የማስታወስ ችሎታን በብቃት ሊያሻሽሉ፣ ማስታወስን ሊያሳድጉ እና መረጃን ማቆየት ሊጨምሩ ይችላሉ። 1. ትኩረትዎን ይስጡ ➤ ትኩረት ከማስታወስ ዋና ዋና ክፍሎች አንዱ ነው. መረጃ ከአጭር ጊዜ ማህደረ ትውስታ ወደ የረጅም ጊዜ ማህደረ ትውስታዎ እንዲሸጋገር ፣ ይህንን መረጃ በንቃት መከታተል ያስፈልግዎታል። እንደ ቴሌቪዥን፣ ሙዚቃ እና ሌሎች ትኩረትን የሚከፋፍሉ ነገሮች በሌሉበት ቦታ ያጥኑ:: 2. መጨናነቅን ያስወግዱ ➤ ቁሳቁሶችን በበርካታ ክፍለ ጊዜዎች ማጥናት መረጃን በበቂ ሁኔታ ለማስኬድ የሚያስፈልግዎትን ጊዜ ይሰጥዎታል። ጥናቶች በተከታታይ እንደሚያሳዩት በመደበኛነት የሚያጠኑ ተማሪዎች በአንድ የማራቶን ክፍለ ጊዜ ትምህርታቸውን ከሚከታተሉት በተሻለ ሁኔታ ትምህርቱን ያስታውሳሉ። 3. መዋቅር እና ማደራጀት ➤ ተመራማሪዎች መረጃ በማህደረ ትውስታ ውስጥ በተዛማጅ ስብስቦች ውስጥ የተደራጁ መሆናቸውን ደርሰውበታል::ተመሳሳይ ጽንሰ-ሀሳቦችን እና ቃላትን አንድ ላይ ለመቧደን ይሞክሩ:: 4. ምኒሞኒክ መሳሪያዎችን ይጠቀሙ ➤ የማስታወሻ መሳሪያዎች ብዙውን ጊዜ ተማሪዎች ለማስታወስ የሚረዱ ዘዴዎች ናቸው። ምኒሞኒክ በቀላሉ መረጃን ለማስታወስ መንገድ ነው። ለምሳሌ፣ ማስታወስ ያለብዎትን ቃል እርስዎ ከሚያውቁት የተለመደ ነገር ጋር ሊያያይዙት ይችላሉ። 5. ይግለጹ እና ይለማመዱ በጣም ውጤታማ ከሆኑ የኢኮዲንግ ቴክኒኮች አንዱ ገላጭ ልምምድ በመባል ይታወቃል።የዚህ ዘዴ ምሳሌ የአንድ ቁልፍ ቃል ፍቺን ማንበብ, የቃሉን ፍቺ ማጥናት እና ከዚያም ይህ ቃል ምን ማለት እንደሆነ የበለጠ ዝርዝር መግለጫ ማንበብ ነው. 6. ጽንሰ-ሐሳቦችን በዓይነ ሕሊናህ ተመልከት ➤ ብዙ ሰዎች የሚያጠኑትን መረጃ በዓይነ ሕሊናቸው በማየት በእጅጉ ይጠቀማሉ። በመማሪያ መጽሐፍትዎ ውስጥ ላሉ ፎቶግራፎች፣እና ሌሎች ግራፊክሶች ትኩረት ይስጡ። በማስታወሻዎችዎ ጠርዝ ላይ ገበታዎችን ወይም ምስሎችን ይሳሉ ወይም ተዛማጅ ሀሳቦችን በጽሑፍ የጥናት ማቴሪያሎችዎ ውስጥ ለመቧደን በተለያየ ቀለም ያጌጡ ወይም እስክሪብቶችን ይጠቀሙ። 7. አዲስ መረጃን አስቀድመው ከሚያውቋቸው ነገሮች ጋር ያገናኙ ➤ የማታውቀውን ነገር በምታጠናበት ጊዜ ይህ መረጃ ከምታውቀው ነገር ጋር እንዴት እንደሚዛመድ ለማሰብ ጊዜ ወስደህ አስብ። 8. ጮክ ብለህ አንብብ ➤ ጮክ ብለው ማንበብ የማስታወስ ችሎታዎን በእጅጉ ያሻሽላል። አስተማሪዎች እና የሥነ ልቦና ባለሙያዎች ተማሪዎች በእውነቱ አዲስ ጽንሰ-ሀሳቦችን ለሌሎች እንዲያስተምሩ ማድረጉ ግንዛቤን እና ትውስታን እንደሚያሳድግ ደርሰውበታል። 9. ለአስቸጋሪ መረጃ ተጨማሪ ትኩረት ይስጡ ➤ ከመካከለኛ መረጃን ማስታወስ አስቸጋሪ ቢሆንም፣ ይህንን መረጃ በመለማመድ ተጨማሪ ጊዜ በማጥፋት ይህንን ችግር ማሸነፍ ይችላሉ። በተለይ አስቸጋሪ የሆነ ፅንሰ-ሀሳብ ሲያጋጥሙ፣ መረጃውን ለማስታወስ የተወሰነ ተጨማሪ ጊዜ ይውሰዱ። 10. የጥናት መደበኛ ስራዎን ይቀይሩ የማስታወስ ችሎታዎን ለመጨመር ሌላው ጥሩ መንገድ የጥናትዎን መደበኛነት መለወጥ ነው። በአንድ የተወሰነ ቦታ ማጥናት ከለመዱ በሚቀጥለው የጥናት ክፍለ ጊዜ ወደ ሌላ ቦታ ለመሄድ ይሞክሩ። 11. እንቅልፍ ያግኙ አዲስ ነገር ከተማሩ በኋላ ትንሽ መተኛት በፍጥነት እንዲማሩ እና በደንብ እንዲያስታውሱ እንደሚያግዝ ጥናቶች አረጋግጠዋል። ስለዚህ ካጠኑ በኋላ ጥሩ እንቅልፍ ለመተኛት ያስቡበት። Share for Others ══════════════ ይ🀄️ላ🀄️ሉን👇👇👇 share👇 https://t.me/GrazmachPaulosElibrary
إظهار الكل...
GRAZMACH-HIGH-SCHOOL-E-LIBRARY/BONGA/

-ተማሪዎች የትምህርት መረጃዎችን, ኖቶችን, መማሪያ መጽሀፍትን በቀላሉ እንዲያገኙ ታስቦ የተዘጋጀ ቻናል ነው:: -ከተለያዩ ት/ቤቶች ተዘጋጅተው በቴለግራም የተለቀቁ model_exam,handout እና ሌሎች ተያያዥ መረጃዎች በማቅረብ ተማሪዎች ለብሄራዊ ፈተና(National exam) ዉጤታማ እንድሆኑ የሚረዳቸው የትምህርት ቻናል ነው። -ቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች የሚቀርብበት ምርጥ ቻናል ነው::

Photo unavailableShow in Telegram
ጭንቅላት ስለጠፋ ዓለማችን ላይ ያሉ ሀገሮች ሁለት አይነት ሀብት አላቸው! የጭንቅላትና የመሬት አፍሪካውያን የመሬቱ ተባርኮላቸዉ ጭንቅላት ላይ ግን ችግር አለ ። እነ ጃፓን ደግሞ መሬቱ በየአመቱ በሱናሚ የሚናወጥ ሀገር ነው ። ነገር ግን ሱናሚ የጃፓንን ህንፃዎች እንጂ የጃፓንን ጭንቅላት ማፍረስ አይችልም ። ጃፓን ለኮንጎ ዛዬር እርዳታ ትልካለች የሁለቱን ሀገር የተፈጥሮ ሀብት ልዩነት ካዬነዉ ልዩነቱ የተአምር ያህል ነው ። ዛዬር ነበረች እርዳታ መላክ የነበረባት ግን መሬቱ ተባርኮ ጭንቅላት ስለጠፋ አስር ኩንታል ጤፍ እቤት ዉስጥ ቢኖር አስፈጭቶ ካልተበላ ከርሃብ ማምለጥ አይቻልም ። 💎ስለዚህ አስተሳሰብ ላይ ትልቅ ስራ መስራት ይገባናል ። ለዚህም ደግሞ ትልቁ መንገድ ማንበብ ነው ። ያላነበበ ጭንቅላት ጥሩ ሀሳብና ጠቃሚ ነገር ማመንጨት አይችልም! የዘወትር ስራው አሲድ ማመንጨት ነው ስለዚህ እናንብብ! 📖እናንብብ! እናንብብ!📖 መጋቢ  ሀዲስ እሸቱ
إظهار الكل...
Repost from Exam cafe ☕
Photo unavailableShow in Telegram
የመንግስትም ሆነ የግል ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ተፈታኝ ተማሪዎቹን በት/ቤታቸው ለማስፈተን ምን ማሟላት አለባቸው? በዚህ አመት በኦንላይን የተዘጋጅውን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ አገር አቀፍ ፈተናን ተማሪዎች በተማሩበት ትምህርት ቤት ለማስፈተን ፍላጎት ያለው ማንኛዉም የመንግስትም ሆነ የግል ትምህርት ቤት የተደራጀ የኮምፒዉተር ላብራቶሪ ሊኖረው ግድ ይለዋል። ይሄውም 1. ዴስክቶፕ ወይም ላፕቶፕ ኮምፒዉተሮች 2. የዉስጥ ኔትዎርክ ያለዉ (የገመድ) ኔትዎርክ/Local Area Network / 3. የኢንተርኔት መስመር ከበቂ ባንድዊድዝ ጋር እንደ የመፈተኛ ኮምፒዉተር ብዛት 4. የባክ አፕ ፓዎር (ጄኔሬተር) ጋር አሟልተው መገኘትና ለትምህርት ቢሮዎች በማሳወቅ በቢሮዎች በኩል መሟላቱ ሲረጋግጥ የፈተና ማእከል በመሆን ተማሪዎቹን ማስፈተን እንደሚችሉ እያሳውቅን ለፈተና የሚዘጋጁት ዴስክቶፕ እና ላፕቶፕ ኮምፒዉተሮች ማሟላት ያለበቸዉ ትንሹ ስፔስፊኬሽን እንደሚከተለው ቀርቧል። 1. RAM --------------- 4GB or higher 2. Storage --------------250GB or higher 3. Processor Speed -------- 2.5GHZ or higher 4. Processors ---------- Intel Core i3 or higher 5. OS --------------- Windows 10 6. Browsers ---------------Safe Exam Browser and other 7. Accessories ---------- Keyboards and Mouse for desktop computers. 📌Join and share 👇👇👇              ✳️  @Ethio600   🎯              ✳️  @Ethio600   🎯
إظهار الكل...