2 359
المشتركون
-124 ساعات
-347 أيام
-17230 أيام
أرشيف المشاركات
2 359
የግንኙነት አለመጣጣም ምልክቶች
አብዛኛዎቹ የጾታ ፍላጎት ልዩነቶች በግልጽ መግባባትና ችግሩን ለመፍታት በሁለቱም ፈቃደኝነት ሊስተካከሉ ይችላሉ።
ምልክቶቹ በተለይ ግንኙነቱ መጀመሪያ ላይ ሁልጊዜ ግልጽ ላይሆኑ ይችላሉ። ስለዚህ በትክክል ሊታዩ የሚገባቸው ነገሮች እነሆ፦ 👇
1. ማን ይጀምር በሚለው ላይ ፉክክር አለ — ወይም ሁልጊዜ እርስዎ ብቻ ትጀምራላችሁ፣ ግንኙነት ለመጀመር ሆነ ለመፈጸም እርሶ ብቻ ነው ሚያነሳሱት
2. ጾታዊ ግንኙነት እንደ ድርድር ሲሆንባችሁ፣ መነጋገር እያለ ድርድር ሊመስል ይችላል ይህም እንደ መስጠት እና መቀበል ይሆናል
3. አብራችሁ የጾታ ግንኙነት ሚያሳዩ ፊልም ሆነ ትዕይንቶችን ከመመልከት ትርቃላችሁ ይህም ያለውን መቀራረብ ያሰፋል
4. ከእናንተ አንዱ ያለማቋረጥ እርካታ አያገኝም፣ ከሁለት አንዳቸው ሁሌም እንዳተደሰቱ ይቆያሉ
6. ስለ ጉዳዩ ሙሉ በሙሉ ማውራት አቁመዋል
@addisposts ነን! መልካም ቀን 🙏 Share & like
2 359
የመስቀል በዓልን ለምታከብሩ መላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሀነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ!
መልካም በዓል ይሁንላችሁ❤️
2 359
1. ቡና እና አረንጓዴ ሻይ ☕🍵
ጤናማ መጠጦች ጤናማ የጉበት ጤናን ሊደግፉ ይችላሉ።
የሚመርጧቸው፦
• ቡና
• አረንጓዴ ሻይ
• ማቻ (Matcha)
ማቻ የአረንጓዴ ሻይ በተጠናከረ መልኩ የተዘጋጀ አይነት ነው።
2. በቫይታሚን C የበለፀጉ ምግቦች 🍊
እንደነዚህ ያሉ ፍራፍሬዎችን በመመገብ ተጨማሪ ቫይታሚን C በማግኘት
• ኪዊ
• ብርቱካን
• ግሬፕፍሩት
እነዚህ ምግቦች ለሰውነትዎ በርካታ ጠቃሚ ንጥረ-ምግቦችን ይሰጣሉ።
3. በኦሜጋ-3 የበለፀጉ ምግቦች 🐟
ኦሜጋ-3 የያዙ ምግቦች በመደበኛነት በምግብዎ ውስጥ መካተት ይገባቸዋል።
ይመገቡ፦
• ሳልሞን
• የቺያ ዘር
• የተልባ ዘር
4. በጤናማ ቅባት የበለፀጉ ምግቦች 🥑
• የወይራ ዘይት
• ለውዝ
• አቮካዶ
@addisposts ነን! መልካም ቀን 🙏 Share & like
2 359
🚨 በ30 ዓመት ዕድሜ ላይ ግዴታ
ስለ ስራ ፣ ገንዘብ እና ጤናን ስለመጠበቅ የሚያወሩ የጓደኞች ስብስብ ሊኖርዎት ይገባል፤ ኑሯችን ውሏችን ሁሉ ከነዚ ሰዎች ጋር ከሆነ የተሻለ ነገ ይጠብቀናል። ስለ ፖለቲካ እና ቲክታከሮች ምናምን እያወራን ጊዚያችንን ምናጠፋበት እድሜ አደለም።
@addisposts ነን! መልካም ቀን 🙏 Share & like
2 359
ውጥረት ለረጅም ጊዜ ከቀጠለ፣ የጾታ ፍላጎትዎን፣ መነቃቃትን፣ የብልት መቆምን እና አጠቃላይ የጾታዎ ግንኙነት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ሊያሳድር ይችላል።
ውጥረት በወንድ ላይ የሚያሳድራቸው 4 ተፅዕኖዎች እና ምን ማድረግ እንደሚቻል በጥቂቱ እንመልከት
1. አጠቃላይ የጾታ ግንኙነት ፍላጎትዎን ሊቀንስ ይችላል
በተከታታይ ጫና ውስጥ ሲሆኑ፣ ለአእምሮዎ የጾታ ግንኙነት ከሌሎች ጉዳዮች ያነሰ ቅድሚያ ሊኖረው ይችላል።
መፍትሄ ፦ በቂ እረፍት ማድረግ ከአልኮል መራቅ
2. የብልት መቆምን ለማቆየት አስቸጋሪ ሊያደርገው ይችላል
ውጥረት የሰውነትን የጭንቀት የመደንገጥ ምላሽ ያነቃቃል፤ ይህም ለጾታዊ መነቃቃት ተስማሚ ሁኔታ አይደለም እንደውም ይቃረነዋል።
መፍትሄ ፦ ከጾታዊ ግንኙነት በፊት ሙሉ በሙሉ ለመረጋጋት ራስዎን ለማከም ጊዜ ይስጡ።
3. እንቅልፍዎን ሊያውክ ይችላል
ረጅም ጊዜ የሚቆይ ውጥረት እንቅልፍን ሊያውክ ይችላል፤ ደካማ እንቅልፍም በተጨማሪ ኃይልን፣ ስሜትን እና የጾታ ተግባርን ሊያሳድር ይችላል።
መፍትሄ ፦ ቋሚ የመኝታ ሰዓት ይኑርዎት እና ከመተኛት በፊት የ30 ደቂቃ የመረጋጋት ጊዜ ያዘጋጁ።
4. ግንኙነትዎን ሊያውክ እና ሊበጠብጥ ይችላል
በቀላሉ መበሳጨት፣ የስሜት ድካም እና በተከታታይ መጨነቅ ቅርበትን እና የጾታ ፍላጎትን ሊቀንስ ይችላል።
መፍትሄ፦ ራስዎን ከመዝጋት ይልቅ ከፍቅር አጋር ወይም ጓደኛ ጋር በግልጽ መነጋገር
@addisposts ነን! መልካም ቀን 🙏 Share & like
2 359
ሞቅ ያለ የሎሚና ዝንጅብል ሻይ 🍋🫚
ዝንጅብልን በሙቅ ውሃ ውስጥ አድርገው ከዚያ ጥቂት የሎሚ ጭማቂ ይጨምሩ።
ሙቀቱ የምሽት ጊዜዎን የተረጋጋና የሚያድስ ስሜት እንዲሰጥ ሊያግዝ ይችላል።
@addisposts ነን! መልካም ቀን 🙏
2 359
የስብ መቀነስን የሚደግፉ 5 ምግቦች
የስብ መቀነስ ግብዎን ለመደገፍ ውስብስብ ምግቦችን መመገብ አያስፈልግም።
በእነዚህ 5 ምግቦች ይጀምሩ።
1. እንቁላል 🥚
እንቁላል በኮሊን (Choline) የበለፀገ ነው።
ኮሊን የይዛወር (bile) መመንጨትን ይደግፋል፤ ይህም ሰውነትዎ በጉበት ውስጥ ያለውን ስብ ለማቀነባበር ይረዳል።
ስለዚህ እንቁላልን በምግብዎ ውስጥ ማከል ለሰውነት ጠቃሚ ንጥረ-ምግቦችን በቀላሉ ለማግኘት እና የስብ አሠራርን ለመደገፍ ይረዳል።
2. ብሮኮሊ 🥦
ከምግብዎ ጋር 1 ኩባያ የተቀቀለ ወይም በትንሽ ዘይት የተጠበሰ ብሮኮሊ ይመገቡ።
አንድ ኩባያ ብሮኮሊ ክሮሚየም (Chromium) የተባለ ንጥረ-ማዕድን ይዟል፤ ይህም የደም ስኳር ቁጥጥርን ይደግፋል።
የተሻለ የደም ስኳር ቁጥጥር የክብደት መቀነስን ሊደግፍ ይችላል።
3. ቃሪያ 🌶️
ቃሪያ ለሚያቃጥለው ጣዕሙ ምክንያት የሆነ ካፕሳይሲን (Capsaicin) የተባለ ንጥረ ነገር ይዟል።
ይህ ንጥረ ነገር ሰውነት ሙቀት እንዲያመነጭ የሚያደርግ thermogenic effect ሊፈጥር ይችላል።
ይህም የሜታቦሊዝምን እንቅስቃሴ በመጠኑ ሊጨምር እና የስብ መጠቀምን ሊደግፍ ይችላል።
ስለዚህ በምግብዎ ላይ ትንሽ ቅመም ይጨምሩ።
@addisposts ነን! መልካም ቀን 🙏
2 359
በድንገት እኩል ለሊት ወይም ሊነጋ ሲል ከእንቅልፋችን ምንነቃበት 3 ምክንያቶች?
"ነጋ ወይስ አልነጋም" ብለን ስልካችንን በተደጋጋሚ ቼክ ምናረድ ሰዎች ጥቂት አደለንም፣ ግን ለምን ብላችሁ እራሳችሁን ጠይቃችሁ ታውቃላችሁ? ምክንያቱን ካወቅክን ለመፍትሄው አንቸገርም።
1. ከመጠን ያላፈ ጭንቀት: ምናልናት ነገ ጠዋት ሚጠብቀን ሚያጓጓ ወይም ሁሉ ነገራችንን ሚፈትን ስራ ይጠብቀን ይሆናል፡ ጭንቀት መነሻው ብዙ ቢሆንም፣ ፍርሃትን ያቀፈ የስሜት ስብስብም ነው። አብዛኛው የስነ-ልቦና አማካሪዎች እንደሚሉት፡ ጭንቀት የአብዛኛው ሰው እንቅልፍ አለመተኛት ምክንያትም ነው። ስለዚህ የመንቃት ከዛም በትግል የመተኛት ድግግሞሽ ውስጥ እንገባለን። ጭንቀታችን ሰው እንደሞናችን ሚጠበቅ ቢሆንም፣ ጭንቀትን ለመቀነስ ደሞ ህይወት እድል ሰታናለች። የሁላችንም ችግር ይለያያል።
2. የተፋረሰ የእቅልፍ ሰዓት: እራሳችንን ማስለመድ ያለበት ነገር፣ ምንተኛበትን እና ምንነቃበትን ሰዓት ተመሳሳይ ማድረግ ነው። ስንፈልግ ቀን፣ ስንፈልግ ማታ መተኛታችን፣ ለሊት ላይ እንቅልፍ ጨርሰን እንድድነቃ ያደርገናል።
3. የጤና ችግሮች: የስኳር መጠን መውረድ፡ ቶሎ ቶሎ መሽናት.....ድብርት ምናምን...ተያያዥ ህመሞች እንቅልፋችንን በሰላም እንዳንተኛ ያደርጋሉ።
@addisposts ነን! መልካም ሰኞ!
2 359
ትምህርቱን አቋርጦ ትልቅ ህልም ሰንቆ፣ አስደናቂ ሄሊኮፕተር በመስራት የራሱን ህይወት የቀጠፈው ወጣት......
ይህ ወጣት ከ3 አመታት በፊት የ7ኛ ተማሪ ነበር።
ት/ቤት ገብቶ ብዙም ደስተኛ ስላልነበር በአነስተኛ ብረታ ብረቶች ስራ ይሰራ ነበር። ብዙም ሳይቆይ ወዲያው በፈጠራ ስራ ተጠመደ።
በአነስተኛ ጉልበት ረጅም ርቀት ምትሄድ ባለ 1 መቀመጫ ሄሊክፕተር መስራት ጀመረ። ወደ 1600 ሰዓታትም በፈጀው ሙከራ እና ስራ የሚደንቅ ውጤት ሲያይ ነበር።
ለ3-4 አመታት በዚህ ሙከራ ተሰማርቶ፣ በአከባቢው እንደ እብድ ሲታይ፣ ግን ደሞ ማይታመን ውጤት በቅጽበት እያሳየ ነበር።
ለመጨረሻ ሙከራ ያደረገበትን ምሽት እየቀረጸውም ነበር፣ ድንገት ግን ፊልም ሚመስል አሳዛኝ ክስተት ሆነ። የሄሊኮፕተሩ ተሽከርካሪ ብረት ወልቆ ወደ ውስጥ በመሹለክ ጭንቅላቱን አገኘው። ሼይክህ እስማኤል ወዲያው ሆስፒታል ቢወሰድም፣ ህይወቱን ማትረፍ አልተቻለም። በወቅቱ አለም መነጋገሪያ አድርጎትም ነበር።
ብሩክ ቀን እየተጠነቀቃችሁ! እኛ @addisposts ነን። ሼር ያድርጉ!
2 359
ኢራን በባለፈው በሶሪያ በሚገኘው ቢሮዬ እስራኤል ለከፈተችብኝ ጥቃት ምላሽ ሰጥቻለሁ ስትል አስታወቀች።
300 ድሮኖችን በእስራኤል ሰማይ ላይ አዝንባለች። እስራኤል በበኩሏ 99% የሚሆነውን መክቻለው አክሽፌያለሁ ብላለች።
"የቃል ኦፕሬሽን" ብላ ኢራን የሰየመችው አዲሱ ጥቃት፣ ወደ ጎረቤት ሀገራት ግጭት እንዳይስፋፋ የተሰጋ ሲሆን፣ የባይደን መንግስት ኦፕሬሽኑን "የሽብር ጥቃት" ብሎ ጠርቶታል። የባይደን መንግስት በዚህ ጉዳይ ከእስራኤል ጎን መቆሙን ቢያሳውቅም፣ የእስራኤልን የስለላ ድርጅት ሞሳድን የሚገዳደር እንቅስቃሴ አሁንም ቀጥሏል።
ኢራን አሁንም ቢሆን እስራኤልን ማስፈራራቷ አይሏል። "አሁንም በድጋሜ" ጥቃት ከከፈተችብኝ ቅጣቴንም ከበድ አረገዋለሁ ብላለች። አሜሪካንም በግልጽ "አይመለከትሽም" የሚል ብላሽ ሰታታለች።
አለም የእስራኤልን የበቀል ጥቃት ምን ሊሆን እንደሚችል እየጠበቀ ነው።
@addisposts ነን የትም ሽፋን ያላገኙ ምርጥ መረጃዎችን ያግኙ
2 359
ኢራን ምሽቱን እስራኤል ላይ የድሮን ዝናብ ስታዘንብ ማምሸቷን ተገለጸ። ይህን ተከትሎ እስራኤል በግዛቷ ድንገተኛ ደውል ደውላለች።
እስራኤል በዘመኗ እንደዚህ አይነት ውርጅብኝ እና ጥቃት ወርዶባት እንደማያቅ አሳውቃለች።
አሁን ላይ ቀጥታ በምሽት የእስራኤል ሰማይ ላይ የኢራን ድሮኖች እንደ እሳት ሲወነጨፉ ታይቷል። ኢራን ከድሮን በተጨማሪ ሮኬቶችን ቀላቅላ ተኩሳለች።
የእስራኤል እና ኢራን ፍጥቻ ወዴት ያመራ ይሆን?
ከራሺያ ጋር ትግል የቀጠለው የዩክሬኑ ዘነለስኪ፣ አሜሪካ እሱን ረስታ ትኩረቷ ሁሉ እስራኤል ላይ ሆኗል።
@addisposts ነን አዳዲስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ።
2 359
የገንዘብ የመግዛት አቅም አሁን ካለበት የባሰ ከቀነሰ ኑሯችን ወዴት ያመራ ይሆን?
ኢትዮጵያ ጫና ላይ ነች፣ በዚህ ውጥንቅጥ ውስጥ ሌላ ራስ ምታት እና ትኩሳት ወደ ህዝባችን እየመጣ ነው።
ኢትዮጵያ ምን አይነት አጣብቂኝ ውስጥ ነች?
ኢትዮጵያ እምቢ ወይም እሺ ብትል፣ በሁለቱም አማራጭ መጥፎ ውጤቶች አሉበት። ብድር ልውሰድ ብትል ዛሬ ሱቅ ገብተን በ100 ብር ምንገዛው እቃ 180-250 ብር ይንራል። አይ ብድር አንፈልግም ካልንም ደሞ የአጠቃላይ ብድራችን 28 ቢሊዮን ዶላር ሽግሽግ ሳይኖረው፣ ብድር መክፈል እንደማንችል ተቆጥሮ፣ አለም አቀፍ ኢንቨስተሮች የቢዝነስ ሰዎች ሁሉ መንገዳቸውን ዘግተው፣ ኢኮኖሚውን ዜሮ ያረጉታል።
አሁን አሁን ከእስር በእስር ግጭት በተጨማሪ በአለም መድረክ የታወቅንበት ጉዳይ፣ የኢኮኒሚያችን መቆርቆዝ ነው።
2 359
ኢራን የእስራኤልን ግዙፍ ጀልባ በቁጥጥር ስር አውላ ወሰደች።
የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ጠባቂ ሄሊኮፕተር የእስራኤል ንብረትነት ያለውን ግዙፍ ጀልባ ሲቆጣጠር የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ተለቋል።
እስራኤል ምን አለች? የእስራሌል ባለ ስልጣናት ኢራን ዋጋ ትከፍልበታለች በማለት መልዕክት ልከዋል።
ጀልባው እንዴት ሊወሰድ ቻለ? ጀልባው ከአረብ ኢሜሬትስ ተነስቶ በህንድ ውቂያኖስ በኩል በማለፍ በንግድ ስራ ላይ ያተኮረ ቢሆንም፣ ኢራን ግን እስራኤልን ማመን ማቆሟን ተገልጿል። የኢራን መንግስት ለእገታው እውቅና የሰጠ ሲሆን፣ እስራኤል በበኩሏ ይህ የለየለት የውንብድና ስራ በመሆኑ በአለም አቀፍ ህግ ያስከስስሳል ብላለች።
ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ ታጣቂዎችን እንደምትደግፍ እንዲሁም እስራኤልን ለማጥፋት ከፍተኛ ፖለቲካዊ ፍላጎት ያላቸውን ሀይሎች ተገን አድርጋ ልትወጋት ደፋ ቀና እያለች መሆኑን ባለ ስልጣናቱ ጨምረው ገልጸዋል።
ኢራን በባለፈው እስራኤል በሶርያ ዲፕሎማቲክ ቢሮ በወሰደችው የአየር ጥቃት በተፈጠረው ጥፋት እና የንጽሁሃን እልቂት፣ እስራኤል ከኢራን ከባድ አጸፋ ይወሰድብኛል ብላ እየፈራች መሆኑን ተናግራለች። እስራኤል ከኢራን መልሶ ጥቃት እንደሚደርስባትም በማወቅ ከአሜሪካ እና መሰል ሀገሮች ብዙ ድጋፍን እየተቀበለች ዝግጅቷን ቀጥላለች።
@addisposts ነን
2 359
አሜሪካ እና ቻይና ሰማዩን ለመያዝ የገቡበት ትንቅንቅ።
አስተውለን ከሆነ ወፎች፥ አሳዎች እንዲሁም በርካታ ህይወት ያላቸው ፍጥረታት ተሰብስበው ይንቀሳቀሳሉ፡ ይህም ሊያጠቃቸው የሚፈልግን ግራ ያጋባል።
አሜሪካ ከ10 አመታት በፊት ያበለጸገችው ቴክኖሎጂ እንደ አንዳንድ ተመራማሪዎች ከሆነ ከኑውክለር የባሰ አደገኛ ነው። በመቶ እና በሺህ የሚቆጠሩ ጥቃቅን ድሮኖች እንደ ንብ ሲጓዙ፡ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ወይም AI ታግዘው እንደፈለጉ ቦታ ሲቀይሩ፡ የጠላትህ ድሮን መጥለፊያ ግራ አጋብቶ እንዲጠቃ ያረገዋል።
ከሰሞኑ ስለዚህ ቴክኖሎጂ ምን አዲስ ነገር አለ?
ቻይና ይህንን ዘርፍ ተቀላቅላ ከፍተኛ የምርምር ውጤት እያገኘች ሲሆን፡ አሜሪካ በበኩሏ ላለመቀደም ብዙ እየሰራችበት ነው።
ይህ ቴንክኖሎጂ ከክላስተር ቦምብ ጋር ቢመሳሰልም፡ ግን በሰው ሰራሽ አስተውሎቱ እና ውስብስብ ቀመሩ ድንቅ አድርጎታል።
ለመጀመሪያ ጊዜ ይህንን ስራ ላይ አውላ አመርቂ ውጤት ያሳየችው ያስመሰከረችው እስራኤል ነች።
ንቦች በብዛት ሆነው ሲሄዱ ሚያሰሙትን አስፈሪ ድምጽ፡ ይህ የድሮን ውጤት ምድር ላይ የከተመ ጠላ በማስፈራራት ስነ ልቦና የማዳከም ብቃት አለው።
@addisposts ነን 🙏🙏🙏
2 359
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው በቁጥጥር ስር ዋለ።
ከጥቂት ወራት በፊት ታስሮ ከእስር የተፈታው የቀድሞ የአውሎ ሚዲያ ባልደረባ አሁን ላይ " አልፋ ቲቪ " የተሰኘ የማህበራዊ ሚዲያ መስራች እና አዘጋጅ ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው በፀጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር መዋሉን ጠበቃ ታደለ ገብረመድህንን ዋቢ አድርጎ አዲስ ስታንዳር አስነብቧል።
የጋዜጠኛውን መታሰር ባለቤቱ ሄለን አባተ አረጋግጠዋል።
በሌላ በኩል ፤ ትላንት የፊንፊኔ ኢንተግሬትድ ብሮድካስቲንግ የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋዜጠኛ ሰቦንቱ አህመድ በአዲስ አበባ ፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለች ሲሆን (በለቡ ፖሊስ ጣቢያ ነበረች) ዛሬ ወደ ቢሾፍቱ መወሰዷን የጣቢያው ዋና ዳይሬክተር ለሚ ታዬ መናገራቸውን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረገፅ አስነብቧል።
ሰቦንቱ ትላንት በፖሊስ የተያዘችው አመሻሽ ላይ ከስራ ቦታዋ ስትወጣ ሲሆን በቁጥጥር ስር ያዋሏት ፖሊሶች የፍርድ ቤት ትዕዛዝ አለመያዛቸውንም ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።
አክለውም፤ ትላንት ለቡ ፖሊስ ጣቢያ እያለች አነጋግረዋት እንደነባርና የተያዘችበት ምክንያት ምን እንደሆነ እንዳልተገለጸላት ፍርድ ቤትም እንዳልቀረበች ለ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረገፅ " አስታውቀዋል።
ጋዜጠኛዋ ዛሬ ወደ ቢሾፍቱ ከተማ እንድትወሰድ ተደርጓል።
@tikvahethiopia
