ሙሓጂሪን መድረሳ مدرسة المهاجرين Muhajirin medresa
الذهاب إلى القناة على Telegram
1 177
المشتركون
+224 ساعات
+477 أيام
+10530 أيام
أرشيف المشاركات
Repost from አቡ ዓኢሻ العلم نور
ከሼይኽ ሐሰን ገላው ሀፊዘሁላህ ወርቃማ ንግግሮች ውስጥ
ዲን በመሰለኝና በደሣለኝ የሚገነባ አይደለም
ምንኛ አማረች ንግግሯ ላስተዋላት ሰው
ዲን ማለት አንተ ደስ ሲልህ ብቻ ምትሰራው ሳይሆን ለእያንዳንዱ ለህይወትህ ጉዞ ስንቅ ነው
ዲን ማለት አንተ ስለመሰለህ ብቻ ትክክል ነው/ ውሸት ነው ብለህ ምታውጀው ሳይሆን ቁርዓኑና ሀዲሱ በሶሀቦች አረዳድ ነው ሚወሰነው
ገባ ገባ በሉ
በአቡ ኢልሓም ሙሀመድ ኑር (وفقه الله)
ተጀመረ
ተጀመረ
ተጀመረ
ተጀመረ
➢ ገባ
➢ ገባ
➢ገባ
➢ገ ባ
➢ በሉ
➢ ገባ ገባ በሉ ጆይን በሉ ሸር አድርጉ ባረከላህ ፊኩም ጀዛኩሙሏሁ ኸይረን👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/sunah123
https://t.me/sunah123
🔖ዘወትር ቅዳሜና እሁድ ከሱብሂ ሰሏት በኋላ የሚቀራው ደርስ በሰዐቱ ይቀጥላል
📒 دعائم منهاج النبوة
🖌للشيخ أبي عبدالله محمد سعيد رسلان حفظه الله📒ደዓኢም ሚንሀጂ አን-ኑቡወህ
🖌ሊሸይኽ ሙሀመድ ሰዒድ ረስላን 🎙 ኡስታዝ አቡ ኢልሐም ሙሐመድ ኑር (وفقه الله) https://t.me/sunah123 🕌በአልሙሐጂሪን መድረሳ https://t.me/sunah123
📌 የሰለፊዮች አንድነት፡ በቡድናዊነት ሳይሆን በተውሂድና በሱና ላይ!
በአሁኑ ዘመን እውነተኛውን እስልምና እና የሰለፎችን (የቀደምት ደጎች) ፈለግ መከተል ማለት ዝም ብሎ ስም መሸከም ወይም በአንድ የተወሰነ ስብስብ ሥር መሰባሰብ አይደለም።
"የሰለፊዮች በተውሂድ ላይ መሰብሰብ ቡድናዊ ሳይሆን ትክክለኛ ወንድማማችነት፣ መተጋገዝ፣ ቁርኣንና ሐዲስን ከመከተል የሚደረግ መሰብሰብ ነው።"1. ሰለፊይነት «ቡድን» (ሒዝቢያ) አይደለም! ብዙዎች ሰለፊይነትን እንደ አንዱ ዝግ የፓርቲ ወይም የቡድን ስብስብ አድርገው ሊያስቡት ይችላሉ። ነገር ግን እውነታው ፍጹም ተቃራኒ ነው። ✅ ቁርኝቱ ከሰዎች ጋር ሳይሆን ከሐቅ ጋር ነው፦ ሰለፊዮች የሚሰበሰቡት ለአንድ ግለሰብ፣ ለአንድ መሪ ወይም ለአንድ የተወሰነ ማኅበር ፍላጎትና ስሜት አይደለም። ☑️ መሠረቱ ተውሂድ ነው፦ ትስስሩ አላህን በብቸኝነት ከማምለክ (ከተውሂድ) እና የአላህን መልእክተኛ ﷺ በቅንነት ከመከተል የሚመነጭ ንጹሕና ትክክለኛ ወንድማማችነት ነው። 2. ከመረጃ ውጭ መሪም ሆነ ቅድሚያ የሚሰጠው የለም፦ ሰለፊዮች ከኪታብና ከሱና ውጭ የራሳቸው የተለየ «መሪና አመራር» የላቸውም።
"መረጃን ከትክክለኛው የቁርኣንና የሐዲስ ምንጭ ይቀዳሉ።"ይህ ማለት አንድ ሰለፊይ የሚመራው በስሜት፣ በወሬ ወይም በጭፍን ተከታይነት (ተቅሊድ) ሳይሆን በማስረጃና በዕውቀት ነው። መረጃ ባለበት ቦታ ሁሉ የሱና ሰው አለ። መረጃ በሌለበት ግን ማንም ይሁን ማን አይከተለውም። 3. ከፈሊጣውያን(ከሙብተድዖች) የሚለዩበት መስመር ✅ ድንበር አይጥሱም፦ እንደ ሙብተድዕና የራሳቸውን ፍልስፍና እንደሚያስቀድሙ ሰዎች፣ ሰለፊዮች በሸሪዓው ላይ በራሳቸው ፍላጎት ድንበር አያልፉም። ✅ ዕውቀትንና ተግባርን ያከብራሉ፦ ከዕውቀትና ከተግባር ባለቤቶች (ከኡለሞች) ጋር ያላቸውን ትስስር ያጠነክራሉ። ሸሪዓዊ ሒክማንና ስነ-ምግባርን (አደብን) ጠብቀው ይጓዛሉ። ✅ ያልተረዱትን ነገር ጠይቀው ይረዱታል፦ መረጃው ግልጽ ካልሆነላቸው ወይም ግራ ካጋባቸው፣ በግምትና በጭፍን ጥላቻ አይፈርዱም፤ ይልቁኑ "ቀርበው ይጠይቃሉ"። 💡 የማጠቃለያ መልእክት በጥቅሉ ይህ መልእክት ዛሬ ላለንበት ተጨባጭ ትልቅ ማስተማሪያ ነው። ሰለፊይነት በተግባር የሚገለጽ እንጂ በይገባኛል ጥያቄ የሚገኝ ስም አይደለም። 🔴 ይህንን ትክክለኛ ሰለፍይነት በተግባር ለመግለፅ ከሚረዱን ነገሮች በጥቂቱ፦ ✅ እምንሰራውን ተግባር ለአላህ ብለን መስራት፤ ✅ ብዙ ተከታይን ለማገኘት ሳይሆን ብዙ የሱና አንበሶችን ለማፍራት መነሳት፤ ✅ እውነተኛ ወንድማማችነትን ማስፈን፤ ✅ ከመላምትና ከቡድናዊ ክፍፍል መራቅ፤ ✅ መረጃንና የኡለሞችን ምክር አጥብቀን መያዝ፤ ✅ ግልጽ ያልሆነልንን ነገር በሰከነና በተረጋጋ መንፈስ ቀርበን መጠየቅ፣ ✅ ታዋቂነትን ሳይሆን አዋቂ መሆንን መምረጥ፣ ✅ ተከታይን (ቲፎዛን ) ሰብስቦ እውነተኛ ነኝ ብሎ አለመንቀሳቀስ እና የመሳሰሉት.... አላህ እውነትን አውቀው ከሚከተሉት፣ ሱናን በተግባር ከሚኖሩት ያድርገን! https://t.me/sunah123
