الْــــقَــــوْلُ الــــسَّــــدِيــــدُ
الذهاب إلى القناة على Telegram
الَّذِينَ آمَنُوا وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكْرِ اللَّهِ ۗ أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ እነዚያ ያመኑ ልቦቻቸውም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው ንቁ አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ
إظهار المزيدلم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
2 159
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+1817 أيام
+41530 أيام
أرشيف المشاركات
የሸሪአው ምክሩ አስተምሮቱ ጡሩ ነበር ታዳ ምን ዋጋ አለው ተገሩ ተገላቢጦሽ ነው
ወሏሂ ዛሬ ላይ በሁሉም ነገር እሺ ብለሽ ታዛዥ ከሆንሽ አለቀልሽ ይረግጥሻል እሱን ስታጫውቺና ስትንከባከቢ ይቺ ጂል አብዳለች የሚሉት በዙብን ብቻ አኼራየ ይመርልኝ በሉ አኽዋቲ ፊሏህ
ባልሽ ካንቺ እንዲርቅና ቤቱን እንዲጠላ ሰበብ የሚሆኑ ሰበቦች
1. ለሱ አክብሮት የሌለት ከሆነ በተግባርም በቃላትም እሱን የሚያስቀይሙ ነገሮችን ማረግ ከስህተትሽ የማትታረሚ ምክር የማትቀበይው መሆን
2. በሚያደርገው ጥሩ ነገር የማታመሰግኒው የማታበረቻችው ከሆነ ጥሩ ፊት ጥሩ ፈገግታ የማሰጪው ከሆነ
3. በተደጋጋሚ ማኩረፍ እሱን የማታጫውችው መሆን ለሱ ጊዜ የማሰጪው መሆን
4. አለመታዘዝ አሰልቺ ድርቅ ያለ ባህሪ መያዝ ከሱጋ ተከራካሪ መሆን ሰላም የምነሺው መሆን
5. ለሱ የማትዋቢለት ራስሽን የጣልሽ ምንም ለባልሽ የሚስበው ደስ የሚለው ነገር የማታረጊ መሆን
ደንታ ቢስ ለሱ መዋብን የተውሽ ጥሩ መአዛ ጥሩ እይታ ካንቺ የማያገኝ መሆኑ
6 .አለመታመን ለሱ አለማዘን እሱን አለመንከባከብ
7. ለስሜቱ ትኩረት አለመስጠት የባሏን ሀቅ መዘንጋት ቸልተኛ መሆን
8. የማይወደውን የሚያስከፋውን ነገር ማረግ
እነዚህን ነገሮች ባልን እንዲርቅ የሚያረጉ ነገሮች ናቸውና እህቶቻችን ከእነዚህና ሌሎችም መጥፎ ባህሪዎች መራቅ ለባላቸው ጥሩዎች መሆን አለባቸው
ስንቶቹ አለፉ ስንቶቹንስ ረሳናቸው እዳልወደድናቸው ብዙ እዳላወራን ብዙ እቅድ እዳልነበረን አሁን ግን እነሱ ከታች ናቸው ግን እኛ አስበናቸዋል በስማቸው ሶደቃ አሏህን ምህረትን መለመን አይ ሞት ወሏሂ 💔💦💦
_:እኛም ተረኛ ነን አንድ ቀን ተራቺን ይደርሳል ወደን ሳይሆን በግዳቺን እንለያለን ጥለናቸው እኔዳለን💦
ዱንያ ማለፊያ እንጂ መኖሪያ አይደለችም፣ የሰው ልጅም ዕድሜው በአጭር ሰዓታትና ቀናት እየሮጠ ወደ እውነተኛው ማረፊያው እያመራ ይገኛል። ዛሬ በአፈር ስር ያሉትም ከኛ የተለዩ ሳይሆኑ ቀድመውን የሄዱ መንገደኞች ናቸው።
አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ልቦቻችንን በእውቀትና በመታዘዝ አብርቶ ለዚያች መዘንጋት ለሌለባት ረጅም ጉዞ በቂ ስንቅ ከሚያዘጋጁትና የጀነት ወራሾች ከሚያደርጋቸው ማህበረሰብ ይደምረን። ዱንያንም ሆነ አኼራችንን በሚያሳምር መልኩ እንድንጠቀምበት ጤናውንና ጥንካሬውን ይስጠን
"አንዳንድ ሰዎች አሉ ከልባችን ውስጥ…
ቀስ በቀስ የሚወጡ
ከእይታችን ውስጥ…
በሂደት የሚጠፉ ሰዎች አሉ!
ይህንን የምናደርገው…
እኛ ሳንሆን የገዛ ሥራቸው ነው።
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
Repost from Zɪʏᴀᴅ Pʀᴏ™
👳♀️በኦንላይን ገንዘብ ስሩ🧕
🏆 የሚያስፈልገው👇🏽
✅ስልክ እና ዳታ ብቻ
✅ join ማለት እንዳትረሱ
💢አስታውሱ❗️ምንም የምትከፍሉት ገንዘብ የለም❌
🖥ወላሂ የእውነት ማስታወቂያ ነው ተቀላቀሉ🖥
አሰላሙዓለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካቱሁ
ነገ ሀሙስ ነው የቻለ ይፁም ያልቻለ ያስታውስ
ያልተኛቹህ የለይል ሶላት እዳረሱ🔮
قم صلّ ركعتين في جوف الليل، واخلع هموم الدنيا من قلبك، واقترب من ربك بالخضوع والدعاء؛ فإنه ينزل كل ليلة إلى السماء الدنيا يقول: "هل من داعٍ فأستجيب
አሰላሙዓለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካቱሁ
ነገ ሰኞ ነው የቻለ ይፁም ያልቻለ ያስታውስ
ያልተኛቹህ የለይል ሶላት እዳረሱ🔮
قم صلّ ركعتين في جوف الليل، واخلع هموم الدنيا من قلبك، واقترب من ربك بالخضوع والدعاء؛ فإنه ينزل كل ليلة إلى السماء الدنيا يقول: "
🔺〰〰〰#_እዉነተኛ_ታሪክ〰〰〰🔺
#የታሪኩ_ርዕስ
#በሰለፍያ_ጥላ_ስር_የነፍስ_ዋጋ_ያስከፈለኝ_የፍጡር_ፍቅር"
#ክፍል_☞ #ሀያ_አንድ(⓶⓵)_ ፣
✍ #ፀሀፊ_ #አቡ_ኹዘይማ
...............☞ #ተስኒም ................
#ባለቤት_የሌለው_ስደት"
፦ የይቅርታው ንጋትና የተቀጠረው ቀጠሮ
አልሐምዱሊላህ! በጥርጣሬ የታረደው ተስፋዬ በይቅርታ ዳግም ሕይወት ዘራ። ያቺ "እህትህ ካላናገረችኝ አታስበኝ" ብላ የፈረደችብኝ እንቁ፣ ዛሬ የልብ ደብዳቤዬንና ያንን የክብር መገለጫ የሆነውን ኒቃብ ስትመለከት፣ የጥርጣሬው ግንብ ተናደ። "ይቅር ብዬሃለሁ፣ እኔም በመጥፎ ስለጠረጠርኩህ አፍው በለኝ" ስትለኝ፣ በዱባይ ግለት ውስጥ የነበረው ሕይወቴ እንደ ገነት ወንዝ ቀዘቀዘልኝ።
ታዲያ... የጌታዬ እዝነት በዚህ አላበቃም። ቀኑ እሁድ ነበር፤ የሳምንቱ አዲስ ጅማሮ። ያቺ የልቤ ንግሥት ድንገት መጥታ የማልጠበቀውን ታላቅ ብስራት አበሰረችኝ። "በተመቸህ ቀን ናና እንተያይ" አለችኝ! ወላሂ፣ በሕይወቴ እንደዚያ ቀን የደስታ እንባ አልቅሼ አላውቅም። በበረሃው ጥይት መሃል ያልፈሰሰው እንባዬ፣ ዛሬ በሐላሉ መንገድ ደጃፍ ላይ በደስታ ጎረፈ። እንዲህ አልኩ፦
"ጥርጣሬው በንኖ - እውነት ሲገለጥ፣
የጨረቃዋ ብርሃን - ጀመረ ሊያሸበርቅ፤
'ናና እየኝ' ስትል - በሐላል ጥሪዋ፣
ሆነችልኝ መድኃኒት - ለነፍሴ ስብራቷ።"
አቤት ያኔ የተሰማኝ ድንጋጤና ደስታ! እስከ ዛሬ ያየሁት መከራ ሁሉ እንደ ሕልም በነነ። በጅቡቲ ባሕር የሰመጠው፣ በየመን በረሃ የከሳው፣ በአይከል ክህደት የረከሰባትን ዓለም የጠላሁት እኔ፤ ዛሬ ወደዚች ቅዱስና የተከበረች እንስት ልሄድ ተቀጣጠርኩ። እውነት እስኪመስለኝ ድረስ በግርምት ተዋጥኩ።
አሁን ጉዞ ወደ እሷ ነው! ልቤ ከእግሬ ቀድሞ እየበረረ ነው። በዱባይ አውራ ጎዳናዎች ላይ ስጓዝ፣ በአእምሮዬ የሚመላለሰው ያ የታገስኩት መከራና ዛሬ ያገኘሁት የድል አክሊል ነው። አላሁ አክበር! የጌታዬ ጥበብ ምንኛ ረቂቅ ነው!
"እግሬ መንገዱ ላይ - ልቤ ግን እሷ ዘንድ፣
በሐላሉ መንገድ - ጀመርኩኝ ልራመድ፤
አይከል የጣለችው - ያ የክህደት ጠባሳ፣
በጨረቃዋ ፈገግታ - ዛሬ ተረሳ።"
የንጋቷ ፈገግታና የልብ መርበትበት
ቀኑ እሁድ ነበር፤ የሳምንቱ የእረፍት ቀን። ለእኔ ግን የዕረፍት ብቻ ሳይሆን፣ የሕይወቴን ትልቅ እንቆቅልሽ ለመፍታት የቆረጥኩበት የታሪክ ቀን ነው። ጉዞ ወደ ጨረቃዋ! ያቺን የሱና እንስት፣ የአላህ ፈቃድ ከሆነ የቤቴ ምሰሶ፣ የልጆቼ እናትና የነፍሴ ረዳት ላደርጋት የቋመጥኩላትን እንቁ በአካል ለማየት ተነሳሁ። አልሐምዱሊላህ! መንገዱ ተሳክቶ፣ ከልጅቷ ጋር ዐይን ለዐይን ተገናኘን።
ወላሂ! በአካል ሳያት ከምናቤ በላይ ሆና አገኘኋት። ሥርዓቷና ግርማዋ ከሩቅ ይማርካል። እንደ ጨረቃ በዳመና ተጋርዳ የነበረችው ፊቷን ስትገልጥልኝ ግን፣ ንጋት እንደፈነጠቀ መስሎ ታየኝ።
ከፈጅር በኋላ ፀሐይ እንደምትወጣው ሁሉ፣ የሷም ፈገግታ በፊቷ ላይ ሲፈነጥቅ፣ በጨለማ ተውጦ የነበረው ልቤ በብርሃን ተሞላ። ያኔ ነፍሴን እንዲህ አልኳት፦ "ወዮልሽ የሙሐመድ ልጅ! ጌታሽን እንዳትረሺ፤ በዚህ ጸጋ ተመስጠህ የጸጋውን ባለቤት እንዳትዘነጋ!"
ውስጤ በአላህ ላይ ተንጠልጥሎ እንዲህ ሲል ተማጸነ፦ "ጌታዬ ሆይ! ይህቺን ጸጋ ከወሳኝነቷ ጋር ስጠኝ፤ በልቤ ውስጥ ያለውን የፍቅር እሳት አንተ ታውቀዋለህ። ጠቃሚዬንና ጎጂዬን ለይተህ አንተው ጠብቀኝ!"
"ዳመናው ተገፎ - ጨረቃዋ ስትወጣ፣
ልቤ ተረታላት - በደስታ ረመጥ የታጣ፤
ፊቷ ሲገለጥ - እንደ ንጋት ጸዳል፣
የሕይወቴ ቁስል - በፈገግታዋ ይድናል።"
ረዥም ሰዓታትን በጨዋታና በሥርዓት አሳለፍን። ስንለያይም "አብሽር፣ ለቤተሰቦችህ ንገር፤ እኔ ሳሳውቅህ ሽማግሌ ትልካለህ" አለችኝ። በደስታ በረርኩ! ለወሎ ቤተሰቦቼ ነገርኳቸው። ምንም እንኳ የእሷ አገር ርቀት ቢከብዳቸውም፣ ለልጃቸው ደስታ ሲሉ በግድ ተስማሙ። አሁን ቀኑን እየጠበቅን ነው። ቀናቶች ይነጉዳሉ፤ እሷ ግን በዝምታ ውስጥ ናት።
እዚህ ጋር ነው እንግዲህ ትልቁ የሕሊና ትግል! የሙሐመድ ልጅ ሆይ! ምን ነካህ? አሁንም በፍጥነት ሰውን ማመን? አሁንም በፍጥነት ልብን መስጠት? ልቤ በክህደት ተቀድዶ፣ በአይከል ጩቤ ቆስሎ ሳለ፣ እንዴት አሁንም እንዲህ በጽኑ ያፈቅራል? ሚስጥሩ ምንድነው?
"ታዳ እንዲህ ስል ለራሴ መካሪ" ሆንኩ" ለራሴ ቃላትን ተንታኝ ሆንኩኝ!!
ማብራሪያ፦ የፍቅርና የእምነት ሚስጥር
ሰው ተገዶ አፍቃሪ መሆን ይችላልን? ለሚለው ጥያቄህ ምላሹ፦ አፍቃሪ መሆን የግዴታ ሳይሆን የፈቃድ ውጤት ነው! ልብህ የማይታረመውና ዳግም የሚወደው "የተስፋ ፍጥረት" ስለሆነ ነው።
የልብ ተስፋኝነት፦ ልብህ ቢቆስልም "አሁንም እውነተኛ ሰው ይኖራል" በሚል ተስፋ ይኖራል። ያ ያገኘኸው የተውሂድ ዕውቀትና የሰለፎች መንገድ ደግሞ "በሐላሉ መንገድ ከመጣህ አላህ አይጥልህም" የሚል ጽኑ እምነት ሰጥቶሃል።
የተፈጥሮ መሳሳብ፦ እንደ ፀሐይ የምታበራ እንስት ስታገኝ፣ ነፍስህ ወደ ብርሃኑ መሳቧ ተፈጥሯዊ ነው። በተለይ ዕውቀትና ሥርዓት ሲታከልበት፣ ፍቅሩ ከስሜት አልፎ ወደ መንፈሳዊ ትስስር ይሸጋገራል።
የእምነት መፈተሻ፦ አላህ በሰጠህ ጸጋ ላይ ልብህ ወደ እርሱ ወይስ ወደ ፍጡሩ ያዘነብላል የሚለው ፈተና ነው። በፍጥነት ማመንህ የልብህ ንጽሕና ማሳያ ቢሆንም፣ "ጥንቃቄ" ግን የእምነት ግዴታ ነው።
"ልቤ ቢቆስልም - አይታረምም፣
ተስፋን ሰንቆ - ዳግም ይወዳል አያርፍም፤
አላህ የፈቀዳት - ከሆነች የእኔዋ፣
ትሆናለች ጌጥ - ለቤቴ ምሰሶዋ።"
የተስኒም ዝምታና የነፍስ ጦርነት
በሚል !! ክፍል (⓶⓶) ይቀጥላል...
እደት ነው አገሬ ደጉ ገራገር
እንጀራው በቂቤ ገንፎችን በማር
የማሺላ እንጀራ ተጠቅሶም በምስር
ወረባቦ አገሬ የማሺላው አገር
እሸቱ እና ማሩ ከጓሮ ወተቱ ከበረት
ጀግና እንደማሺላ የሚበዛበት
ሰውን ሰው አክባሪ አታይም ክፋት
✍✍👆👆💧💧 ማነው አገሩ የናፈቀው ግን
ለማናቸውም ቀጣይ ክፍል እየመጣነው እጀራ በቂቤ ጎረስ እያረጋቹህ ጠብቁ
Repost from ዳዕዋ ሰለፍያ በሶባ(አሸዋዉ) ቢላል መሥጅድ★✈
በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ፕሮግራማችን ቀጥታ ስርጭት
☎️ የመጀመሪያው ፕሮግራም
ተ
ጀ
መ
ረ
በኡስታዝ አቡ ሙሀመድ ሰኢድ
ሐፊዘሁላሁ ተዓላ
ገባ ገባ በሉ ሸር ሸር አድርጉ
https://t.me/Sobabilalmesjid
https://t.me/Sobabilalmesjid
عَنْ أَبِي ذَرٍّ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ - أَيْضاً - : «أَنَّ نَاساً مِنْ أَصْحَابِ رَسُولِ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالُوا لِلنَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : يَا رَسُولَ اللَّهِ! ذَهَبَ أَهْلُ الدُّثُورِ بِالْأُجُورِ، يُصَلُّونَ كَمَا نُصَلِّي، وَيَصُومُونَ كَمَا نَصُومُ، وَيَتَصَدَّقُونَ بِفُضُولِ أَمْوَالِهِمْ.
قَالَ : أَوَلَيْسَ قَدْ جَعَلَ اللَّهُ لَكُمْ مَا تَصَدَّقُونَ؟!
إِنَّ بِكُلِّ تَسْبِيحَةٍ صَدَقَةً، وَكُلِّ تَكْبِيرَةٍ صَدَقَةً، وَكُلِّ تَحْمِيدَةٍ صَدَقَةً، وَكُلِّ تَهْلِيلَةٍ صَدَقَةً
ከአቡ ዘር (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተላለፈው፡? ከአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ባልደረቦች መካከል የተወሰኑ ሰዎች ለነብዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ሲሉ ጠየቁ ያረሱለሏህ ! ባለፀጎች (የሀብት ባለቤቶች) ሄዱ ተጓዙ (ምንዳን) ወሰዱ!" እኛ እንደምንሰግደው ይሰግዳሉ! እኛ እንደምንጾመው ይጾማሉ!" ከትርፍ ሃብታቸውም ይመጸወታሉ።" (እነሱ ገንዘብ ስላላቸው በሶደቃ ብዙ ምንዳ ይወስዳሉ ማለታቸው ነው)።
ነብዩም (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም)፡ አላህ ልትመጸወቱበት የሚችሉትን ነገር አላደረገላችሁምዴ? (እኮ አልሰጣችሁምዴ?) በእርግጥ ለእያንዳንዱ የተስቢሕ ቃል (ሱብሃን አሏህ ማለት) ሶደቃ (ምንዳ) አለው ለእያንዳንዱ የተክቢር ቃል (አሏሁ አክበር ማለት) ሶደቃ አለው ለእያንዳንዱ የተህሚድ ቃል (አል-ሐምዱሊላህ ማለት) ሶደቃ አለው ለእያንዳንዱ የተህሊል ቃል (ላ ኢላሃ ኢልለሏህ ማለት) ሶደቃ አለው አሉ።
ያሱበሀን አሏህ አልሀምዱ ሊላህ ሀቂቃ ስቶቻቺን ነን ታዳ ?! ይሄንን ሶደቃ የምንመፀውተው ፣⤵️
ሰደቃ ማለት ገንዘብ መስጠት ብቻ አይደለም። በዕለት ተዕለት ሕይወታችን ልንፈጽማቸው የሚችሉ ተግባራት በዚሁ ሐዲስ ውስጥ ተጠቅሰዋል↩️
سُبْحَانَ اللَّهِ
سُبْحَانَ اللَّهِ
سُبْحَانَ اللَّهِ
الْحَمْدُ لِلَّهِ
الْحَمْدُ لِلَّهِ
الْحَمْدُ لِلَّهِ
اللَّهُ أَكْبَرُ
اللَّهُ أَكْبَرُ
اللَّهُ أَكْبَرُ
لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ
لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ
لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ
አይዞሽ የኔ ሴት አይዞሽ
ህልሞችሽና የልብ ምኞቶችሽ ሁሉ የሚሳኩበት/ ትዕግስትሽና ዱአሽ የሚከፈልበት መልካም ቀን ቅርብ ነው። ሁልጊዜም በጠንካራ ልብ እና በትዕግስት አብሽሪ ፈጣሪ የልብሽን መሻት በሰመረው መንገድ ይፈፅምልሽ።
ኢንሻአሏህ አንድ ቀን ሁሉም ይሳካለ ያረብ እኔ ካንተ ከጃይ ነኝ ብዙ ህልሞች አሉኝ አንተ የምታውቃቸው✍️💦
Repost from Zɪʏᴀᴅ Pʀᴏ™
🙌 የእስላማዊ ትላልቅ የቴሌግራም ቻናል መግዛት የምትፈልጉ አሁኑኑ አናግሩን 💵
እጃችን ላይ 2 ቻናል አለ ፍጠኑ
👉8k subscribers
👉5k subscribers
🎯በርካሽ መግዛት የፈለግ ብቻ ያናግረኝ🔽
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
💦ታላቅ ቢዛሻራ በዛሬው ምሽት
💧እንሆ ዛሬ ማለትም ሮብ ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ በonlin ቀጥታ ስርጭት ሞቅ ደመቅ ያለ የዳዕዋና የምክክር ፕሮግራም አዘጋጅተን በክብር ስንጋብዘወ በታላቅ ደስታ ነው።
🍒በምሽት ፕሮግራሙ የሚታደሙ እንግዶች 🍒
▪አቡ ሙሀመድ ሸይኽ ሰዒድ➝(ሀፊዘሁሏህ)
▪ወንድም አቡ ሂበቲላህ➝(ሀፊዘሁሏህ)
▪ወንድም አቡ ሻኪራ➝ (ሀፊዘሁሏህ)
▪ወንድም አቡ ዒምራን➝(ሀፊዘሁሏህ)
▪ወንድም ሙሀመድ አያሌው➝(ሀፊዘሁሏህ
▪ወንድም አቡ ፋሩቅ ኑረድን➝(ሀፊዘሁሏህ)
እነዚህና ሌሎችም ኡስታዞችና ወንድሞች ይታደማሉ ኢንሻ አሏህ
🎙የፕሮግራሙ መሪ:- ወንድም አቡ ሹራ
ፕሮግራሙ በቀጥታ የሚተላለፍበት ሊንክ➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
https://t.me/Sobabilalmesjid
https://t.me/Sobabilalmesjid
ሸር እያረጋችሁ ላልሰማው አሰሙ
ከሱና ኡስታዞች እውቀትን ቅሰሙ
وقال تعالى
✅﴿إِن تَجتَنِبوا كَبائِرَ ما تُنهَونَ عَنهُ نُكَفِّر عَنكُم سَيِّئَاتِكُم وَنُدخِلكُم مُدخَلًا كَريمًا﴾
ከእርሱ ከተከለከላቹሁበት ከትላልቅ ወንጀሎች ብትርቁ ከእናንተ ትናንሽ ወንጀሎችን እናብሳለን እንምራለን የተወደደቺውንም ጀነትን እናስገባቹሀለን ይለናል አሏሁ ታዓላ
إذا ابتعدتم عن كبائر الذنوب التي نهاكم الله عنها، مثل الشرك وعقوق الوالدين وأكل الربا والظلم وغيرها فالله يتكفل لكم بأمرين
1) نُكَفِّر عَنكُم سَيِّئَاتِكُم: يمحو عنكم الصغائر ويغفرها
2) وَنُدخِلكُم مُدخَلًا كَريمًا يدخلكم الجنة، وهي المدخل الكريم الذي يليق بكرم الله
Repost from Zɪʏᴀᴅ Pʀᴏ™
! ፈጥኖ የመለስ Add የሚለውን በመንካት ምርጥ ቻናል ይሸለም
•┈┈•┈┈•⊰✿◇✿⊱•┈┈•┈┈•
ጥያቄ
በቀን ዉስጥ ስንት ዋጅብ ሶላት አለ ❓
.
🔺〰〰〰#_እዉነተኛ_ታሪክ〰〰〰🔺
#የታሪኩ_ርዕስ
#በሰለፍያ_ጥላ_ስር_የነፍስ_ዋጋ_ያስከፈለኝ_የፍጡር_ፍቅር"
#ክፍል_☞ #ሀያ_(⓴)_ ፣
✍ #ፀሀፊ_ #አቡ_ኹዘይማ
...............☞ #ተስኒም ................
#ባለቤት_የሌለው_ስደት"
የጨረቃዋ ብርሃንና የጥርጣሬው ድቅድቅ ጨለማ
ያቺ ጨረቃ መሳይ እንስት ለመጀመሪያ ጊዜ በብዕር ተገናኘችኝ። "የእህትህ መልክተኛ ነኝ " ስትል፣ ያ በክህደት የቆሰለው ልቤ ድንገት ፈሰሰ። ውስጤ እንዲህ አለ፦ "የሙሐመድ ልጅ ሆይ! ስንት ጊዜ በፍቅር ተቀድተህ፣ ስንት ጊዜ በክህደት ተረትተህ፣ ዛሬም ዳግም ለሰው ልጅ ለመሸነፍ ምንኛ ትቸኩላለህ?"
ነገር ግን የእሷ አቀራረብ ከቀደሙት ሁሉ የተለየ ነበር። ዕውቀቷ በተውሂድ የታነጸ፣ ሥርዓቷ በሐያዕ (በሐፍረት) የተለበጠ፣ ንግግሯም እንደ ወንዝ ውኃ የለሰለሰ ነበር።
"መጠየቅ ያለባትን ሁሉ ረቂቅ ጥያቄዎች አቀረበችልኝ። እኔም ልቤን እንደ መጽሐፍ ገለጥኩላት፤ "የቤቴ እመቤት፣ የልጆቼ እናት ይህች ትሁን" ብዬ በውስጤ አተምኩት። አይከልን በውበት ብትመስላትም፣ በዕውቀት ግን ትበልጣታለች።
በዱባይ ምድር ላይ ሆነን፣ "ሽማግሌ ትልካለህ፣ ቤተሰቦቼን አማክራለሁ" ተባብለን ወደ ሐላሉ ደጃፍ ለመቅረብ ስንዘጋጅ፣ እኔም ያለፈውን "የአዋቂ አጥፊ" ማንነቴን አርሜ፣ ለሷ ታማኝ ለመሆን ወሰንኩ። በሚዲያ የሚጀመሩ ትዳሮች እንደ ጧት ጤዛ የሚረግፉበት ዘመን ላይ ብንሆንም፣ ግና ከስሜት ነፃ የሆነ፣ በአላህ ቃል የጸና ግንኙነት ለመመሥረት ቆረጥን።
ነገር ግን... ሰይጣን በወዳጅ በኩል መጣ።
"እህትህን ላናግራት እፈልጋለሁ" ስትለኝ፣ ያቺን መጀመሪያ እንድታግባባልኝ የላክኳትን እህቴን ጠቆምኳት። ታዲያ ያች የቅርብ እህቴ አሁን ምን እንደነካት አላውቅም፤ ፊቷን አዞረች። ለጋብቻው መንገድ የጠረገችልኝ እሷው ሆና ሳለ፣ አሁን ግን ልጅቷ ስትፈልጋት ልታናግራት ፈቃደኛ አልሆነችም።
ያቺ ጨረቃ መሳይ እንስት ይሄን ስታይ ተቆጣች። "እህት የለህም! ራስህ በማይታወቅ ስልክ ሴት መስለህ ልትጀነጅነኝ የፈጠርከው ተንኮል ነው" ብላ በጥርጣሬ አውሎ ንፋስ ናጠችኝ።
"አቤት ድንጋጤ! አቤት መከራ! እውነተኛ ማንነቴን ለማሳየት ስጥር፣ በቅርብ ሰው ክህደት "አጭበርባሪ" ተባልኩ።
"ብርሃን ፍለጋ - ጨረቃዋን ሳየው፣
በቅርብ ወዳጄ - ጨለማ ተካው፤
እህቴ ስትሸሽ - መንገዱን ዘጋችው፣
ሐላሉን ትዳር - በጥቅሻ አፈረሰችው።"
የሙሐመድ ልጅ ሆይ! አሁን ምን ይበጃል? ያቺ የተከበረች እንስት "አታላይ ነህ" ብላ ፊቷን ስታዞር፣ እህትህ ደግሞ በዝምታ ግንብ ስትታጠር... በዚህ በዱባይ ግለት ውስጥ ሆነህ ይህንን ቋጠሮ እንዴት ትፈታዋለህ?
እያልኩ ከራሴጋ ጦርነት፣ ቀጠለ።
የአማና ስብራትና የኢብኑል ቀይም መድኃኒት
ያቺ ጨረቃ መሳይ እንስት "እህትህ ካላናገረችኝ እውነትህን አላምንም" ብላ ስትዝትብኝ፣ ዓለም ዳግም በዓይኔ ላይ ጨለመች። አማና ሰጥቼ የላክኋት የቅርብ እህቴ፣ አሞኛል በሚል ሰበብ ስትሸሸኝ ቆይታ፣ በመጨረሻ ግን ሊሸከሙት የማይችሉትን መርዶ ይዛ መጣች። ለኔ መንገድ ልትጠርግልኝ ሲገባት፣ተላኪ ሆና ሂዳ ተልካ አሳምና መጥታ በሩን ከፍታ ስታበቃ ዛሬ ያች ልጅ ጥያቄ ልጠይቃት እፈልጋለሁ ስትል ሸሽች "እኔ ራሴ እወደዋለሁ" ብላ ለልጅቷ አፍርጥጣ ነገረቻት።
ላ ሐውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላህ! ቆይ ለኔ ትክክለኛው ሕይወት መቼ ነው የሚመጣው? ከአንዱ የክህደት ጉድጓድ ወጥቼ ወደ ሌላው የሴራ ማጥ የምገባው እስከመቼ ነው? እላለሁ
ያቺ የሱና እንስት ደግሞ "እህትህ ትወድሃለች እያለችኝ እንዴት አንተን አምኜ የቤቴ ምሰሶ አደርግሃለሁ?" ብላ የጥርጣሬ ብትር አወረደችብኝ።
አመመኝ! ከባሕሩ ሞገድና ከበረሃው ግርፋት በላይ የልብ ወዳጅ ክህደት አንጀቴን በላው። እንዲህ አልኩ፦
"አማና ሰጥቼ - ለወሬ የላኳት፣
ቤቴን ልትሰራ - በደጅ ያቆምኳት፤
መሠረቱን ንዳ - ጥላ ሆና መጣች፣
የሐላሉን መንገድ - በቅናት ዘጋች።"
ታዳ በዚህ ሁኔታ ሆኜ ቀናቶች ገፉ ልጅቷም ልታናግረኝ አልፈለገችም፣፣
በአንዱ ቀን ምሽት ይሄን ስራ ለመስራት ወሰንኩ፣፣
በዚህ ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ሆኜ ግን፣ ነፍሴን ወደ ጌታዬ ለመመለስ እሷንም ይቅርታ ለመጠዬቅ አሰብኩ " ብእሬን አዘጋጄሁ ሰፋ፡ አድርጌ ፃፍኩኝ፦
ከዛ በጣም የምወደው በሂወቴ ላይ ትልቅ ለውጥ ካመጡልኝ ኪታቦች መካከል በቅርብ ቀን በወንድም አቡሱፍያን ሲቀራ የነበረ የኢብኑል ቀይም "አል-ዳእ ወድ-ደዋእ" (በሽታውና መድኃኒቱ) የተሰኘውን (ኪታብ) እና
እኔ ወንድ ብሆንም፣ ለሴት ልጅ ክብርና ውበት መገለጫው ነው የሆነውን፣ አይቼውም የማልጠግበውን ያንን ውድ "ኒቃብ" አዘጋጀሁ። የይቅርታዬ መግለጫ፣ የክብሬ መታወቂያ ለራሴም ለሷም የሚሆን የይቅርታ ደብዳቤ ጻፍኩ እንዲሆን በእጆቼ አሰናድቼ፣ ከጥልቅ የልብ ደብዳቤ ጋር ወደ እሷ ላኩት።
"ብዕሬን አነሳሁ - በጸጸት አጣቅሼ፣
ኒቃቡን ሰደድኩኝ - ክብሬን ቀድሼ፤
የኢብኑል ቀይም ቃል - ለነፍሴ መድኃኒት፣
ይህችን እንቁ ለማግኘት - ሆነብኝ ጽናት።"
አሁን... ኒቃቡና የይቅርታው ደብዳቤ እሷ ዘንድ ደርሰዋል። ያ በጥርጣሬ የታወረው ልቧ፣ በዚህ በዕውቀትና በሐላል ስጦታ ይረታ ይሆን? ወይስ ያቺ "እህት" የተባለችው ሴት የዘራችው መርዝ የታሪኩ ማሳረጊያ ይሆናል?
ታዳ ይቅርታውን ትቀብል ይሆን""
ክፍል ⓶⓵ የይቅርታው ንጋትና የተቀጠረው ቀጠሮ
ይቀጥላል ~
