الْــــقَــــوْلُ الــــسَّــــدِيــــدُ
الذهاب إلى القناة على Telegram
الَّذِينَ آمَنُوا وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكْرِ اللَّهِ ۗ أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ እነዚያ ያመኑ ልቦቻቸውም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው ንቁ አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ
إظهار المزيدلم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
2 203
المشتركون
+1824 ساعات
+617 أيام
+46430 أيام
أرشيف المشاركات
🌹 የልብ መረጋጋትና የእምነት ስንቅ ከቁርአንና ከሀዲስ 🌹
በዚህች ፈታኝ ዱንያ ላይ ልባችን እረፍት እንዲያገኝ ህይወታችንም በበረካ እንድትሞላ እነዚህን ሁለት ታላላቅ መመሪያዎች ሁልጊዜም በልባችን እንያዛቸው
አላህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) በቁርአኑ እንዲህ ይላል
الَّذِينَ آمَنُوا وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكْرِ اللَّهِ ۗ أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوب
እነዚያ ያመኑ ልቦቻቸውም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው ንቁ አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ
ዱንያ ስታስጨንቅህ መውጫ ቀዳዳ ያጣህ ሲመስልህ ወደ ዚክር ተመለስ የአላህ ስም የሚጠራበት ልብ መረጋጋትንና ሰላምን ይጎናጸፋል
ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል
احْرِصْ عَلَىٰ مَا يَنْفَعُكَ، وَاسْتَعِنْ بِاللَّهِ وَلَا تَعْجِزْ
(رواه مسلم
ለአንተ የሚጠቅምህን ነገር ላይ ጉጉ (ትጉ ሁን በአላህም ታገዝ አትስነፍ (አትስጠም
በዕለት ተዕለት ህይወትህም ሆነ በዲንህ ላይ የሚጠቅምህን ነገር ለመያዝ በሙሉ አቅምህ ጣር። ነገር ግን በራስህ እውቀትና ጉልበት ብቻ አትመካ ሁልጊዜም ያ አላህ እርዳኝ በማለት እርዳታን ከእሱ ጠይቅ ስንፍናና ተስፋ መቁረጥ በሙእሚን ህይወት ውስጥ ቦታ ሊኖራቸው አይገባም
✨ አላህ በንግግራችንም ሆነ በተግባራችን ቀጥተኞችን (ሳዲቅ) ያድርገን
ሊንኳን ሸር አርጓት ✍🍓
https://t.me/umu_afifah_ami_chanal
اللهم صل على نبينا محمد ﷺ
خَطَوَاتُنَا تَمْشِي إِلَى بَيْتِ الرَّحْمَن،
نَبْغِي الرِّضَا وَالعَفْوَ وَالأَمَان.
يَوْمُ الجُمُعَةِ نُورٌ لِلْقُلُوب،
فِيهِ دُعَاءٌ تُمْحَى بِهِ الذُّنُوب.
صَلُّوا عَلَى خَيْرِ الأَنَامِ مُحَمَّدٍ،
تَسْعَدُوا فِي الدُّنْيَا وَيَوْمِ المَوْعِدِ
እርምጃዎቻችን ወደ ረህማን ቤት (መስጂድ) ያመራሉ እርካታን ምህረትንና ሰላምን እንፈልጋለን የጁሙዓ ቀን ለልቦች ብርሃን ነው ወንጀሎች የሚማሩበት ዱዓ አለው በሰው ዘር ምርጥ በሆኑት በነቢዩ ሙሐመድ ላይ ሰለዋት አውርዱ በዱንያም በአኺራም ትደሰታላችሁ
+8
ሴት ልጅ እደዚህ ናት🌸💧
المرأةُ كِتَابٌ نَادِرٌ،
يَقرَأُهُ مَن يَعرِفُ قِيمَةَ الجَمَال.
هِيَ لَيسَتْ نِصفَ المُجتَمَعِ بَل كُلّهُ،
هِيَ الحُبُّ، والأَمَلُ، ودِفءُ الخَيَال.
إِنَّهَا رَقِيقَةٌ كَالوَرْدِ فِي بَسَاتِينِهِ،
وقَوِيَّةٌ كَالصَّخْرِ فِي وُجْهِ الجِبَال🍃
ሴት ማለት ብርቅዬ መጽሐፍ ናት
የውበትን ዋጋ የሚያውቅ ብቻ የሚያነባት
እሷ የማኅበረሰቡ እኩሌታ ብቻ አይደለችም ሙሉው እንጂ
እሷ ፍቅር ናት ተስፋ ናት የሕልም ሙቀት በደጅ
በአትክልቱ ስፍራ እንዳለች ጽጌረዳ ስስና ለስላሳ ናት
በተራራው ፊት እንደቆመ ዐለት ግን ጠንካራ ናት
የኔ ጠንካራዋ እህቴ አቺኮ ቃላት የማይገልፅሽ እናትነትን መዓረግ የተሰጠሽ ልዩ ፍጡር ነሽ🥇✅
ጫት እና ጫት ቃሚ 👀 👇እየቃመ በሰማይ የሚበረው ክክ
ፊቱን አሳብጦ ጉንጩን እንደ ፊኛ
ቁጭ ብሏል ፎቅ ላይ የቅዠት መጋቢኛ
ቅጠሏን ሲያኝካት(“ሀብታም ነኝ) ይላል
ምርቃናው ሲለቀው ግን አምስት ሳንቲም ያጣል
አትቃሙት ተውት✍👏
በቀን አራት ሰዓት ጉንጩን ሲያደልበው
የፍየል ዘመድ እንጂ፣ ሰው እንዳይመስለው
ሚስቱ እቤት ሆና ድስቱን ስታማስል
እሱ መጅሊስ ሆኖ አሜሪካን ይገነባል
ፀያፍ ነው ድርጊቱ👌
ጥርስን ያጠቁራል ምራቅ ያስተፋል
ያንን ሁሉ ወርቅ ጊዜ በከንቱ ይበላል
ሶላት ሲያልፍ አይታየው ዲኑ ሲፈራርስ
ጭንቅላቱ ዞሯል በቅጠል ማዕበል
ሚሊየነር ሆኖ በሀሳብ ሲበርር
ሚርቃናው ሲወርድ ይጀምራል መክሰር
ሚርቃናዬን ሰበርከኝ”፣ ብሎ ይቆጣል
ለውርደት ስንፍና ራሱን ይሰጣልወዳጄ ሆይ ስማኝ ተውት ያንን ቅጠል
የሰውነትህን ክብር በከንቱ አይቀጥል
ከፍየል መላመድ ይበቃል ይብቃህ
በቁምነገር ኑርና ይውጣ ሰብዕናህ
بسم الله الرحمان الرحيم
እህቶች ሆይ ይቺን ነሲሀ እድታነቧት እፈልጋለሁኝ ሁሉንም በብዛት ከእኛ ከሴቶች ዘንዳ የሚከሰት ክስተት ነው ✅ከዛም ቆም ብለን ልናስብ ይገባናል ባረከሏሁ ፊኩም
በአንድ የጋራ ግሩፕ ውስጥ ተሰባስቦ አብሮ እያደጉና የአላህን ዲን እየተማሩ አለመከባበር በጣም አሳዛኝና ሊታረም የሚገባው ጉዳይ ነው የዲን እውቀት ዋናው ግቡና ፍሬው መልካም ስነ-ምግባር (አኽላቅ) እና መከባበር ነው እውቀት እየቀሰሙ ስነ-ምግባርን አለማሳየት የዱንያም የአኺራም ኪሳራ ነው
አብረው ዲን እየተማሩ ለማይከባበሩ እህቶች የሚከተለው እህታዊይ ምክር ነው ✅
1✍️ የዲን እውቀት ፍሬው መልካም ስነ-ምግባር ነው
ዲን መማር ማለት የቃላት ክምችት ማጀግጀግ ሳይሆን በውስጡ ያለውን እውነት በተግባር ማሳየት ነው እህትሽን ሳታከብሪ ስሜቷን እየጎዳሽና እያጣጣልሻት የምትማሪው የዲን እውቀት ምንም በረካ አይኖረውም እውቀት ትህትናን ሊጨምርልሽ ይገባል እንጂ ኩራትንና ሌሎችን መናቅን ሊያመጣ አይገባም
2 ✍️የዲን ግሩፕ የአምልኮ (ኢባዳ) ቦታ ነው
አንድ ላይ ዲን የምትማሩበት ግሩፕ የመላኢካዎች እዝነት የሚወርድበት አላህ የሚወሳበት የኸይር ቦታ ነው ይህንን የተቀደሰ ቦታ በንትርክ በምቀኝነት በሹክሹክታና አንዷ ሌላዋን በማሳነስ ማርከስ አይገባም እርስ በርስ መከባበር የዲኑ አንዱ አካል ነው
3✍️ የምላስ መጥፎነት ስራን ያበላሻል
የቱንም ያህል ብንሰግድ ብንጾምና ዲን ብንማር... በምላሳችን እህቶቻችንን የምናቆስልና የማናከብር ከሆነ የቂያማ ቀን የሰራነው መልካም ስራ ሁሉ ተወስዶብን (ከሳሪ) እንዳንሆን መጠንቀቅ አለብን
የክብር እና የመከባበር
የእስልምና ዲን ለአማኞች ክብር ፍቅርና መከባበር ትልቅ ቦታ ሰጥቷል በተለይም አብረው የዲን እውቀት የሚቀስሙ እህቶች እርስ በርስ ሊኖራቸው የሚገባውን ስነ-ምግባር በተመለከተ ከቁርአንና ከሀዲስ የመጡ ማስረጃዎች እንደሚከተለው እንመልከት✍️👇
የሌሎችን ክብር አለመንካትና አለማሾፍ አላህ (ሱ.ወ) በሱረቱል ሁጁራት ላይ አማኞችን እርስ በርስ እንዳይናቁና እንዳይሳለቁ ሲያዝ እንዲህ ይላል
﴿يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا يَسْخَرْ قَوْمٌ مِّن قَوْمٍ عَسَىٰ أَن يَكُونُوا خَيْرًا مِّنْهُمْ وَلَا نِسَاءٌ مِّن نِّسَاءٍ عَسَىٰ أَن يَكُنَّ خَيْرًا مِّنْهُنَّ ۖ وَلَا تَلْمِزُوا أَنفُسَكُمْ وَلَا تَنَابَزُوا بِالْأَلْقَابِ﴾ [الحجرات 11]
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ወንዶች ከወንዶች አይሳለቁ ከእነሱ የበለጡ ሊሆኑ ይችላሉና ሴቶችም ከሴቶች አይሳለቁ؛ ከእነሱ የበለጡ ሊሆኑ ይችላሉና ነፍሶቻችሁንም (እርስ በርሳችሁ) አታንኳስሱ በቅጽል ስሞችም አትጠራሩ
የንግግር ውበትና ትህትና
﴿وَقُل لِّعِبَادِي يَقُولُوا الَّتِي هِيَ أَحْسَنُ ۚ إِنَّ الشَّيْطَانَ يَنزَغُ بَيْنَهُمْ﴾ [الإسراء: 53]
ለባሮቼም በላቸው ያችን እሷ መልካም የሆነችውን ቃል ይናገሩ ሰይጣን በመካከላቸው ያበላሻልና (በግሩፕ ውስጥ የምንመርጣቸው ቃላት ሰይጣን በመካከላችን እንዳይገባ በጥንቃቄ መመረጥ አለባቸው
ሙስሊም የእህቱ/የወንድሙ ክብር ጠባቂ ነው የአላህ መልክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል
المُسْلِمُ أخُو المُسْلِمِ، لا يَظْلِمُهُ ولا يَخْذُلُهُ، ولا يَحْقِرُهُ، التَّقْوَى هاهُنا -ويُشِيرُ إلى صَدْرِهِ ثَلاثَ مَرَّاتٍ- بحَسْبِ امْرِئٍ مِنَ الشَّرِّ أنْ يَحْقِرَ أخياهُ المُسْلِمَ، كُلُّ المُسْلِمِ علَى المُسْلِمِ حَرامٌ: دَمُهُ، ومَالُهُ، وعِرْضُهُ [رواه مسلم
ሙስሊም የሙስሊም ወንድም (እህት) ነው አይበድለውም አይጥለውም አይንቀውምም አላህን መፍራት እዚህ ጋ ነው (ወደ ደረታቸው ሶስት ጊዜ እየጠቆሙ) አንድን ሰው ክፉ ለመሆን ሙስሊም ወንድሙን (እህቱን) መናቁ ብቻ በቂው ነው የሙስሊም ደሙ ገንዘቡና ክብሩ በሌላው ሙስሊም ላይ እርም ነው
መልካም ስነ-ምግባር የኢማን ማሟያ ነው ነቢዩ (ﷺ) ለአክብሮትና ለበጎ ስነ-ምግባር ትልቅ ደረጃ ሰጥተዋል
أَكْمَلُ الْمُؤْمِنِينَ إِيمَانًا أَحْسَنُهُمْ خُلُقًا [رواه الترمذي
ከአማኞች መካከለል ኢማኑ ይበልጥ ፍጹም የሆነው ስነ-ምግባሩ ይበልጥ ያመረው ነው
ትህትና ደረጃን ከፍ ያደርጋል በግሩፕ ውስጥ ለአስተማሪም ሆነ ለአብሮ አደግ ጓደኛ ዝቅ ማለት ደረጃን ያሳድጋል
وَمَا تَوَاضَعَ أَحَدٌ لِلَّهِ إِلَّا رَفَعَهُ اللَّه [رواه مسلم
ማንም ሰው ለአላህ ብሎ በትህትና ዝቅ አይልም አላህ ደረጃውን ከፍ ቢያደርገው እንጂ
ማጠቃለያ ምክር ✍️
ዲን የምትማሩ እህቶች ሆይ! ዛሬ የምትማሩት እውቀት ነገ ለአላህ ፊት ስትቆሙ ምስክር ይሆንባችኋል ወይስ ይሟገትላችኋል እርስ በርስ በመከባበር አንዷ ለሌላዋ ሰበብ በመሆን እና የግሩፑን ስነ-ስርዓት በመጠበቅ የእውቀታችሁን በረካ አብዙ አንዷ ብትሳሳት እንኳን በውስጥ መስመር በፍቅርና በክብር ማረም ሲገባ በግሩፕ ፊት ማሸማቀቅና ማሳነስ ከእውቀት ፈላጊዎች የማይጠበቅ ተግባር ነው
https://t.me/umu_afifah_ami_chanal
+2
አንድ ሰው ክፉ ለመሆን ሙስሊም ወድሙን ( እህቱን መናቁ ብቻ በቂው ነው )
አሏህ ይጠብቀን ከዚህ ተግባራት
+1
اللهم إنك عفو تحب العفو فاعف عنا، اللهم أكرمنا وأصلحنا ويسر أمورنا وأحسن خاتمتنا.🍫
( فَقَلْتُ اسْتَغْفِرُوا رَبَّكُمْ إِنّهُ كَانَ غَفَارًا )
استغفر الله
سبحان الله
الحمد لله
لا إله إلا الله
الله أكبر
لا حول ولا قوة إلا بالله
سبحان الله وبحمده
سبحان الله العظيم
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
لا إله إلا أنت سبحانك إني كنت من الظالمين.
اِنْتَبِهُوا وَاحْذَرُوا، وَعَنِ الْكِبْرِ ابْتَعِدُوا
ንቁ ተጠንቀቁ ከኩራትም ራቁ
يُحْشَرُ الْمُتَكَبِّرُونَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ أَمْثَالَ الذَّرِّ فِي صُوَرِ الرِّجَالِ يَغْشَاهُمُ الذُّلُّ مِنْ كُلِّ مَكَانٍ
_ኩሩዎች በቂያማ ቀን በሰው አምሳል ሆነው ነገር ግን እንደ ጥቃቅን ጉንዳን ተደርገው ይቀሰቀሳሉ ውርደት ከየአቅጣጫው ይከባቸውል_
قِيلَ ادْخُلُوا أَبْوَابَ جَهَنَّمَ خَالِدِينَ فِيهَا ۖ فَبِئْسَ مَثْوَى الْمُتَكَبِّرِينَ
_ሱረቱ አዝ-ዙመር 72 በውስጧ ዘላለም ነዋሪዎች ስትሆኑ የጀሀነምን ደጃፎች ግቡ ይባላል የኩሩዎችም መኖሪያ ምንኛ ከፋ_
* እስልምናችን የሚስተምረን መኩ ራራትን ሳይሆን ዝቅ ማለትን መተናነስን ትህትናን ነው የሚያስተምረው ትህትናን (التواضع) ሲሆን ራሱን ዝቅ ያደረገን ሰው አላህ ከፍ እንደሚያደርገው ቃል ገብቷል*
https://t.me/umu_afifah_ami_chanal
+1
✍ትነበብልኝ 🌸👇
በጥቁሯ ጀበና እሳት አንደድሽባት
ዕጣኑ ሲታጠን ይወጣል መዓዛሽ
አንቺ የቤቱ ሞቅታ የነቃሽ ጠቢብ ሴት
በሲኒው ጨዋታ ፍቅር ነው ማዕድሽ
ፈገግታሽ ሲታከል ከቡናው ቃና ጋር
ያነቃል አእምሮን ይከፍታል አዲስ በር
ሀሳብ ታፈልቂያለሽ ከእያንዳንዱ ሲኒ
የባህል ፈርጥ ሆነሽ ቁጭ በዪልን እባክሽ
ቤቱን አድምቂው በነቃው መንፈስሽ
ማናት የሚል አይጠፋም እ🌸👌
ለአላማ የተፈጠረች ማንነትን ማስታወስ
የሰው ልጅ የተፈጠረበት ዋናው ትልቅ ዓላማ አላህን በብቸኝነት ሊያመልከውና እሱን ሊያውቀው ነው እውቀት ደግሞ የኢባዳ ሁሉ መሰረት ነው ራሳችን ባዶ እየሆንን ሌሎችን ለመቀየር መሮጥ የራሱን ቤት ሳያጸዳ የሌሎችን ግቢ ለመጥረግ እንደመቸኮል ነው ስለዚህ
ቅድሚያ ለራስ እውቀት መስጠት ዲንን በሚገባ ማወቅና መተግበር ለአንቺ መዳኛሽ ነው በቁርኣን፣ በተፍሲር እና በኪታብ ትምህርቶች ላይ ጠንክሮ መቀመጥ በዱንያም በአኺራም ትልቅ ደረጃን ያጎናጽፋል
ሚዛናዊ መሆንን መልመድ በሶሻል ሚዲያ ላይ የሚደረጉ የኸይር ስራዎች (ጥያቄና መልስ ማዘጋጀት ሰዎችን ማሳተፍ) የሚደነቁ ቢሆኑም ያንቺን የውስጥ እውቀትና መንፈሳዊ ጥንካሬ በሚያሳጣ መልኩ ሙሉ ጊዜሽን ሊሰርቁሽ አይገባም
📱 የሶሻል ሚዲያ (የቴሌግራም) አጠቃቀምን መገደብ
ቴሌግራም ላይ የሚለጠፉ ፎቶዎች የሚለቀቁ ኦዲዮዎችና ፅሁፎች ሰፊ ጊዜን ከመብላት ባለፈ አንዳንዴ ለልብ መታወክና ለሪያእ (ለእዩልኝ) በር ሊከፍቱ ይችላሉ ለዚህ መፍትሄ የሚሆኑ ነጥቦች
የጊዜ ሰሌዳ ማውጣት በሶሻል ሚዲያ ላይ የሚጠፋውን ጊዜ በግልፅ መወሰን ለምሳሌ በቀን ውስጥ ከ1 ሰዓት በላይ በየግሩፑ ላለመዘዋወር ራስን መገደብ
የእውቀት ሰዓትን ማክበር ለቂርኣን ለዚክር እና ለኪታብ ጥናት የሚሆን ልዩና የማይነካ ሰዓት በቤት ውስጥ መመደብ ያ ሰዓት ሲደርስ ስልክን ሙሉ በሙሉ ማጥፋት ወይም ራቅ አድርጎ ማስቀመጥ
ትርፍ ጊዜን ብቻ መጠቀም ዋናው የቤት ስራሽና የዕለት ተዕለት የኢባዳ ፕሮግራምሽ ከተጠናቀቀ በኋላ በተረፈሽ ትርፍ ጊዜ ብቻ ሌሎችን ለማስታወስና ለመርዳት መሞከር
ብርሃን ለሌሎች ከመስጠቱ በፊት መጀመሪያ ራሱ መብራት አለበትውድ እህቴ ሆይ አንቺ እውቀት ኖሮሽና በዲንሽ ጠንክረሽ ስትገኚ ለቤተሰብሽም ሆነ ለዓላማሽ የምትሰጪው ፍሬ ይበልጥ ያምራል。 ራስን ሳያዘጋጁ በዳዕዋና በፕሮግራሞች መጠመድ መጨረሻው ድካምና ራስን ማሞኘት ብቻ ነው ስለዚህ ዛሬውኑ ውሳኔሽን አስተካክዪ ወደ ቂርኣን ሰሌዳሽና ወደ ኪታብሽ ተመለሺ https://t.me/umu_afifah_ami_chanal
إِنَّ الَّذِينَ قَالُوا رَبُّنَا اللَّهُ ثُمَّ اسْتَقَامُوا تَتَنَزَّلُ عَلَيْهِمُ الْمَلَائِكَةُ أَلَّا تَخَافُوا وَلَا تَحْزَنُوا وَأَبْشِرُوا بِالْجَنَّةِ الَّتِي كُنتُمْ تُوعَدُونَ
እነዚያ ጌታችን አላህ ነው ያሉ ከዚያም ቀጥ ያሉ በእነርሱ ላይ መላእክት ይወርዳሉአትፍሩ አትዘኑም በዚያችም ትገቡባት በነበራችሁት ገነት ተበሰሩ በማለት (ይወርዱላቸዋል
ዓለም በምትጠፋበትና ሁሉም በራሱ ጭንቅ በሚይዝበት ሰዓት መላእክት መጥተው አትፍሩ አትዘኑ የገነት የምስራች ይሁንላችሁ"ሲሉ የሚሰማው ሰላም እጅግ ልብን ያረካል ያረብ እኛንም ከነዚህ እድለኞች አድርገን
+1
اللهم في هذا الصباح افتح لنا أبواب الخير والرزق والطمأنينة، واكتب لنا فيه سعادةً تملأ القلوب، وتوفيقًا يرافق الخطى، ورحمةً تشملنا ومن نحب، واغفر لنا ولوالدينا ولجميع المسلمين. 🍫🍃
+1
መልእክተኛው ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም በሀዲሳቸው አሏሁ ታዓላ በቁረአኑ 👇👇
እህቴ ሆይ በቁርአን እና በሀዲስ ውስጥ ለሴቶች የተላለፉ ጠንከር ያሉ ማስጠንቀቂያዎች (ተግሳጾች) ዓላማቸው ክብርሽን ለመቀነስ ሳይሆን ካልታሰበ ጥፋትና ከአላህ ቅጣት ለመጠበቅ እንዲሁም ወደ ጀነት ጎዳና ለመምራት ነው
ከቁርአን እና ከሐዲስ የተወሰዱ ዋና ዋና የማስጠንቀቂያ መልእክቶች ናቸው ልብ እንበል እህቶች አሏህ ይምራን እና
تَكْفُرْنَ الْعَشِيرَ، وَتَكْفُرْنَ الإِحْسَانَ، لَوْ أَحْسَنْتَ إِلَى إِحْدَاهُنَّ الدَّهْرَ كُلَّهُ ثُمَّ رَأَتْ مِنْكَ شَيْئًا قَالَتْ: مَا رَأَيْتُ مِنْكَ خَيْرًا قَطُّ ባልን ትክዳላችሁ (ውለታውን ታጣጥላላችሁ) መልካም መዋልንም ትክዳላችሁ ከአንዳቸው ጋር እድሜ ልክህን በደግነት ብትኖር ከዚያም ከአንተ አንዲት (የማትወደውን) ነገር ብታይ ከአንተ መቼም ቢሆን መልካም ነገር አላየሁም' ትላለች” (ቡኻሪና ሙስሊምصِنْفَانِ مِنْ أَهْلِ النَّارِ لَمْ أَرَهُمَا... وَنِسَاءٌ كَاسِيَاتٌ عَارِيَاتٌ، مُمِيلَاتٌ مَائِلَاتٌ، رُؤُوسُهُنَّ كَأَسْنِمَةِ الْبُخْتِ الْمَائِلَةِ، لَا يَدْخُلْنَ الْجَنَّةَ وَلَا يَجِدْنَ رِيحَهَا ከእሳት ሰዎች የሆኑ ሁለት ክፍሎችን እኔ እስካሁን አላየኋቸውም (ወደፊት ይመጣሉ (ሁለተኛው ክፍል) የለበሱ ነገር ግን የተራቆቱ ወደ ወንዶች ያዘነበሉና ወንዶችንም ወደራሳቸው የሚያዘነብሉ ራሶቻቸው ልክ እንደ ግመል ሻኛ የሆኑ ሴቶች ናቸው እነሱ ጀነት አይገቡም ሽታዋንም አያገኙም ሙስሊም ዘግበውታል
✍ ጀግናዬ
ካንች አልፎ ለወላጆችሽ ዘዉድ እንድለበሱ ትፈልጊያለሽ ???
እንግዳስ ከቁርአን ጋር ይሁን አላቃሽ
አንዳድ ጊዜ መለስ ብየ ሳስታውሳቸው🎀🦋
መልካም ስነ-ምግባር (አህላቅ) የአንድ ሙስሊም የህይወት መሰረት እና የኢማኑ መገለጫ ነው
እራስን በዕውቀት ማነፅና ወደ አላህ መጠጋት
የአህላቅ መስተካከል የሚጀምረው አላህን በመፍራትና እውቀትን በመፈለግ ነው። እንዲሁም ሁልጊዜ አላህ አህላቃችንን እንዲያሳምርልን መለመን አለብን። ነቢዩ (ﷺ) በዱዓቸው እንዲህ ይሉ ነበር
اللَّهُمَّ اهْدِنِي لأَحْسَنِ الأَخْلاقِ، لا يَهْدِي لأَحْسَنِهَا إِلا أَنْتَ
አላህ ሆይ! ወደ መልካም ስነ-ምግባር ምራኝ ወደ መልካሙ ስነ-ምግባር ከአንተ ውጭ የሚመራ የለም
የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) የተላኩት መልካም ስነ-ምግባርን ሊያሟሉ ነው የእሳቸውን ትዕግስት እውነተኝነት ይቅር ባይነትና ትህትና ማጥናት ትልቅ ትምህርት ይሰጠናል። አላህ በቁርዓኑ እንዲህ ይላ
وَإِنَّكَ لَعَلَىٰ خُلُقٍ عَظِيمٍ
አንተም ሙሐመድ ሆይ በታላቅ ስነ-ምግባር ላይ ነህ
አብዛኛው የአህላቅ መበላሸት የሚመጣው ከምላስ (በሀሜት በውሸት በስድብ እና በቁጣ ጊዜ እራስን አለመቆጣጠር ነው
እራስን መመርመርና ታጋሽ መሆን المحاسبة والصبر
በየቀኑ የምናደርጋቸውን ነገሮች መገምገም ሰዎችን መበደልን መናቅን ወይም በእነሱ ላይ መኩራራትን ማስወገድ ስሜታችንን ለማሸነፍና ሰዎችን ይቅር ለማለት ትዕግስት (ሶብር) ያስፈልገናል
መልካም ጓደኞችን መምረጥ صحبة الأخيار
የምንውልበት ሰው በአህላቃችን ላይ ቀጥተኛ ተፅዕኖ አለው። መልካምና አላህን የሚፈሩ ስንሳሳት የሚያርሙን ጓደኞችን መያዝ አህላቅን ለማስተካከል እጅግ በጣም ይረዳል ነቢዩ ﷺእንዲህ ብለዋል
الرَّجُلُ عَلَى دِينِ خَلِيلِهِ، فَلْيَنْظُرْ أَحَدُكُمْ مَنْ يُخَالِلُ
አንድ ሰው በጓደኛው ዲን (መንገድ) ላይ ነው ስለዚህ አንዳችሁ ማንኛውን እንደሚወዳጅ እንደሚገጥም ይመልከት
ማጠቃለያ ምክር
👇🤌
አህላቅን በአንድ ቀን መቀየር አይቻልም ቀስ በቀስ እራስን በመታገል (ጂሃዱ-ነፍስ) እና አላህን በማገዝ የሚመጣ ነው ሁልጊዜ ለሰዎች መልካም ማሰብ ፈገግታን ማዘውተርና ሰዎችን በምንፈልገው መልኩ ማክበር ትልቁ መፍትሄ ነው አላህ መልካሙን አህላቅ ይወፍቀን
https://t.me/umu_afifah_ami_chanal
+1
አመላቹህ ከልጆ ቹየበዛ ነው 🕶 ይሄው ሆሆ እናታቸውን አውጪና ልጆቹን ብቻ እዳትሉ ክክክ
+2
ይሄው ሁለቱም መጡላቹህ እኔ ግን ሁለቱም ናፍቀውኛል💧💧
يَا بُنَيَّ يَا نُورَ عَيْنِي
يَا جَمَالًا فِي حَيَاتِي
كُنْ شُجَاعًا، كُنْ كَرِيمًا
أَنْتَ أَغْلَى أُمْنِيَاتِي
ልጄ ሆይ የዓይኔ ብርሃን
በሕይወቴ ውስጥ ያለህ ውበት
ጀግና ሁን ቸርም ሁን
አንተ ከምኞቶቼ ሁሉ ውዱ ነህ
يا ابنتي الجميلة
يَا ابْنَتِي يَا زَهْرَةَ الدَّارْ
يَا مَلَاكًا مِنْ سَمَائِي
ضِحْكَتُكِ تُنِيرُ الدَّرْبَ
أَنْتِ حُبِّي وَرَجَائِي
ልጄ ሆይ የቤቱ አበባ
ከሰማይ የወረድሽ መላኬ
ሳቅሽ መንገዱን ያበራል
አንቺ ፍቅሬና ተስፋዬ ነሽ
ደስ አይሉም ግን ልብ ቅልጥ ያደርጋሉ የምር 👑💎 የኔ ትንሽየ ልጅዋ ሴት ልጅ የሚወደው ማነው የኔ ጩጩዬ 🦋🦋
🦋أُمِّي يَا نَبْضًا فِي دَمِي يَجْرِي
يَا شَمْسَ عُمْرِي وَنُورَ صَدْرِي
أَحِنُّ إِلَيْكِ إِذَا اللَّيْلُ دَجَا
وَبِغَيْرِ حِضْنِكِ لَا أَرَى فَرَجَا
تَأَذَّى القَلْبُ يَا أُمِّي لِفِرَاقِكِ
وَجَفَّ الدَّمْعُ شَوْقًا لِعِنَاقِكِ
أَنْتِ الجَنَّةُ فِي الدُّنْيَا وَالآخِرَةِ
فَاغْفِرْ لَهَا يَا رَبِّي كُلَّ آخِرَةِ🎀🦋
የእናት ፍቅር እና ናፍቆት
أُمِّي يَا نَبْضًا فِي دَمِي يَجْرِي
ኡሚይ የልቤ ትርታ በደሜ ውስጥ የምትፈሺ
يَا شَمْسَ عُمْرِي وَنُورَ صَدْرِي
የዘመኔ ፀሐይ ነሽ የደረት እፎይታ የምትለግሺ
أَحِنُّ إِلَيْكِ إِذَا اللَّيْلُ دَجَا
ጨለማው ሲወርሰኝ ናፍቆትሽ ይበረታል
وَبِغَيْرِ حِضْنِكِ لَا أَرَى فَرَجَا
ካንቺ እቅፍ ውጪማ የት መጽናኛ ይገኛል
تَأَذَّى القَلْبُ يَا أُمِّي لِفِرَاقِكِ
ልቤ ተሰበረ እናቴ ካንቺ መለየት
وَجَفَّ الدَّمْعُ شَوْقًا لِعِنَاقِكِ
እቅፍሽን ናፍቆ.. ዐይኔ እምባ ደረቀበት
ናፍቀሽኛል ኡሚዋ ስደት አካላችንን አራርቆታል ልባችን አብሮ ቢሆንም💧💧💧
🌹የባልና የሚስት ፍቅር ከየተኛውም ፍቅር ጋር አይወዳደርም !
🌹በባልና በሚስት መካከል ያለው ፍቅር ከማንኛውም የሰው ልጅ ፍቅር ጋር አይወዳደርም፤ አይለካምም። ይህ ፍቅር እንዲሁ በአጋጣሚ የሚከሰት ስሜት ሳይሆን፣ ዓለማትን በፈጠረው ጌታ አማካኝነት በሁለት ባዕድ ልቦች ውስጥ የሚዘራ መለኮታዊ ሚስጥር ነው።
⚠️ታላቁ ዓሊም ሸይኽ አብዱራህማን አዝ-ሰዕዲ (ረሒመሁላህ) እንዳሚሉት፤ አላህ በትዳር አጋሮች መካከል “መወደድና
እዝነትን” አድርጌያለሁ በማለቱ፣ ይህ ግንኙነት ከጓደኝነትም ሆነ ከሌሎች የዝምድና ትስስሮች ሁሉ የላቀና የተለየ
እንዲሆን አድርጎታል።
🌹 በትዳር ውስጥ ያለው “መወደድ” (መወዳህ) ማለት በመካከላቸው ያለውን ጥልቅ ፍቅር፣ መሳሳብና መልካም መስተጋብርን የሚገልጽ ሲሆን፤ “እዝነት” (ራሕመት) የተባለው ደግሞ ስሜታዊ ፍቅሩ በሂደት ቢቀዘቅዝ እንኳ አንዱ ለሌላው የሚኖረውን ርህራሄ፣ መከባበርና በችግር ጊዜ ደራሽነትን ያጠቃልላል።
🌹ይህ ፍቅር ልዩ የሚያደርገው ትላንት ለማያውቁት ሰው፣ ዛሬ ግን ከገዛ ስጋና ደም
በላይ የሚሳሱለት የሕይወት አካል ሆኖ መገኘቱ ላይ ነው። ሰዎች ከቤተሰቦቻቸው ጋር የሚኖራቸው ፍቅር የተፈጥሮ ትስስር ቢሆንም፣ በትዳር ውስጥ ያለው ግን አላህ በቃሉ ያጸናውና በሁለት ልቦች መካከል የገነባው ታላቅ መለኮታዊ ተዓምር ነው።
⚠️ ስለዚህ በትዳር ውስጥ ለሚገኝ ፍቅር ሌላ ምሳሌ መፈለግ አያስፈልግም፤ ምክንያቱም የዚህ ፍቅር ባለቤትና ሰጪው ራሱ አላህ በመሆኑ ነው።
🌹 ይህ መለኮታዊ ስጦታ በቤታችን ውስጥ እንዲሰፍን ካስፈለገ ደግሞ፣ ወደ ሰጪው ጌታ በመቃረብና እርሱን በመታዘዝ የፍቅሩን መርከብ ከማዕበል መጠበቅ ይኖርብናል። እውነተኛ ደስታ የሚገኘው አላህ የሰጠንን የትዳር አጋር በፈጣሪ እይታ ውስጥ ሆነን ስንወዳቸውና ስናዝንላቸው ብቻ ነው።
አላህ በፍቅር የተሞላ ትዳርን ይወፍቀን!
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
