الْــــقَــــوْلُ الــــسَّــــدِيــــدُ
الذهاب إلى القناة على Telegram
الَّذِينَ آمَنُوا وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكْرِ اللَّهِ ۗ أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ እነዚያ ያመኑ ልቦቻቸውም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው ንቁ አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ
إظهار المزيدلم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
2 186
المشتركون
+2824 ساعات
+447 أيام
+45130 أيام
أرشيف المشاركات
+1
👉ቁምነገር?
"ጊዜ ልክ እንደ ወንዝ ፈሳሽ ነው አንዴ ካለፈ አይመለስም
የቀኑ ውብ እና ምርታማው ሰዓት ላይ እንገኛለን። ነገር ግን ይህንን ውድ ጊዜ በምን ላይ እያሳለፍነው ነው? በባዶ ወሬ በማይጠቅም የሶሻል ሚዲያ መርበብ ወይስ ነገ ለእኛ በሚጠቅም ቁምነገር?
እያንዳንዱ የሰዓት እቅስቃሴ ወደ መጨረሻችን መስመር እያቀረበን እንጂ እያራቀን አይደለም። ዛሬን ካልሰራንበት ነገ የፀፀት እንባ ከማፍሰስ ውጪ ሌላ ምንም ትርፍ የለንም።
በምኞት ብቻ መኖር ይብቃን
ነገ እቀየራለሁ ነገ እሰራለሁ ነገ አነባለሁ…" የሚለው የተስፋ ማታለያ የሰነፎች መደበቂያ ነው። ካልጀመርነው 'ነገ' መቼም አይመጣም።
ማሳሰቢያ
ውድ ወንድሜ/እህቴ! ከንቱ ውጫዊ ነገሮችና የዚህች ዓለም ጊዜያዊ ውበት አይጠልፉህ። አሁን ካለህበት የቸልተኝነት እንቅልፍ ንቃ! ይህ ሰዓት ተመልሶ አይመጣምና ወደ ስራ ወደ እውቀት እና ወደ መልካም ስነ-ምግባር ተመለስ
Repost from Zɪʏᴀᴅ Pʀᴏ™
⚜️መልካም ዜና
⚜️የተጅዊድ ትምህርት በነፃ መማር ይፈልጋሉ
እንግዳዉስ ይቀላቀሉን ያለምንም ክፍያ እናስተምራለን
👉 ማካርጅ
👉አህካም
👉ምድ
👉 ሲፋ የፈለጉትን ይማሩ 🫴🫴🫴🫴
💧የደውራችን ጣፋጭ ትዝታና የመለያየት መራራ ስሜት!💧
🥀አልሐምዱሊላህ! በአላህ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَى ቸርነትና ስኬት በጉጉት ስንጠብቀው የነበረው የታላቁ የዒልም ዑደት (የኮርስ/ደውራ) ፕሮግራማችን በድል ተጠናቋል። ያ አላህ! በእንዲህ ያለ የተቀደሰ ስብስብ ውስጥ የሚገኝን ደስታ በምን ቃላት ልግለጸው? ይህ እኮ እንዲሁ ተራ ስብሰባ ሳይሆን፣ መላእክት ክንፋቸውን የሚዘረጉበት፣ የአላህ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَى ራህመት የሚዘንብበትና ነፍስ እውነተኛ እረፍቷን የምታገኝበት የጀነት ጨፌ ነበር።
🌹በእነዚህ ቀናት ውስጥ የታላቁ ነቢይ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ እውነተኛ ወራሾች የሆኑትን፣ የምድር ከዋክብትና የእውቀት ተራራዎችን፣ ታላላቅ መሻይኾቻችንንና ብርቅዬ ኡስታዞቻችንን ፊት ለፊት ማየት መታደል ብቻ ሳይሆን ትልቅ የልብ ሕክምና ነበር። ከማር የሚጣፍጥ፣ ልብን የሚያርስና ከመንገድ የወጣችን ነፍስ ቀጥ የሚያደርግ ያንን ጣፋጭ ምክራቸውን ስንሰማ ሰዓቱ እንዴት እንደረፈደ አናውቅም ነበር። ያልገባንን ነገር በጠየቅናቸው ቁጥር፣ በዚያ በአማረና በረጋ ፊታቸው፣ በለሰለሰ አንደበታቸውና በፈገግታ የታጀበ ማብራሪያቸው ልባችንን ሲያረኩት ማየት... ሀቂቃ ዱንያ ላይ ከዚህ የሚበልጥ ምንስ
ደስታ አለ?
💦 በዛ ላይ ደግሞ የሰለፊይ ወንድሞቻችን በሱና ኑር (ብርሃን) የሚያበራ ፊት ማየት ሌላው ድምቀት ነበር። ከተለያየ አቅጣጫ መጥተን፣ በቋንቋ ባንግባባ እንኳ በዐቂዳና በመንሐጅ ተሳስረን፣ እርስ በርስ ተቃቅፈን ስንዘያየር፣ አብረን ስንበላና ስንጠጣ፣ በአንድ ምንጣፍ ላይ ቁጭ ብለን የዒልም ማዕድ ስንካፈል የተሰማን መከባበርና መዋደድ በቃላት የማይገለጽ ታላቅ ሀብታችን ነው። ይህ ነው እውነተኛው ወንድማማችነት! ለአላህ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَى
ተብሎ የሚመሰረት ፍቅር መጨረሻው እንዲህ ያማረ ነው።
⚠️ነገር ግን... ዛሬ ኮርሳችንን ስንጨርስና መለያያችን ሲደርስ፣ ያ ሁሉ ደስታ በናፍቆትና በሐዘን ደመና ተሸፈነ። ከነዚያ ብርቅዬ መሻይኾችና ከነዚያ ልብ ከሚያክሙ ኡስታዞችና ወንድሞች መለየት በእውነት አንጀትን የሚበላ መራራ ስሜት ነው። ያንን ልብ ሰንጥቆ የሚገባውን
የመሻይኾቻችንን ፈገግታና የወንድሞቻችንን ፍቅር ትቶ መሄድ እንባን መቆጣጠር የማይቻልበት ከባድ ወቅት ነበር።
🥀 "እረ እነዚህን የምድር ኮኮቦች እንዴት ልለያቸው? መቼ ይሆን ድጋሚ እንዲህ በደስታ የምንገናኘው?" እያልኩ ልቤ በዝምታ ሲያለቅስ ተሰማኝ።
በዚያ የመለያየት ሰዓት፣ በልቤ ውስጥ ለነዚህ እንደ ራሴ ለምሳሳላቸው መሻይኾቼ፣ ኡስታዞቼና የሱና ወንድሞቼ ወደ ጌታዬ እጆቼን ዘርግቼ እንዲህ አልኩኝ፦
🌹"ያ አላህ! እነዚህን የዲንህን አርበኞች አንተ በያሉበት በራህመትህ ጥበቃ ስር አድርግልን። በሕይወታቸው ላይ በረካን፣ በዒልማቸው ላይ ጥንካሬን ስጣቸው።
ያ አላህ! እኛንም እነሱንም እስከ እስትንፋሳችን መጨረሻ ድረስ በትክክለኛው የመንሐጅ ሰለፊያ ጎዳና ላይ አጽናን። ይህንን ልብ የሚመስጥ ፈገግታቸውን ከፊታቸው ላይ አታጥፋባቸው፤በዱንያም ላይ ደጋግመን የምንገናኝ አድርገን ለሙወሒዶች ባዘጋጀሀት ጀነትህም ላይ ሰብሰበን ብዬ ኢላሒን ከለመንኩ ቡሀላ ማንንም አቀፌ መሰናበት ሲያቅተኝ ውዱን ኡስታዜን ኢብኑ ሙነወርን እቅፍ አድርገጌ እጁን ስሜ ከታላቁ የየመን ሙሐድስ ወደ ደሴ ከ2 ወንድሞቼና ከዶ/ር ሰኢድ ሙሳ ጋር አቀናን በደሴ አረብገንዳ መስጅድ ላይም ለዛለች ነፍስ መድሀኒት የሚሆን የታላቁን ሸይኽ አሊዩ አራዚህን ጣፋች ምክሮችን ሰምተን ተለያየን።"
ከሁሉም በላይ ደግሞ... ልክ ዛሬ በዚህች ምድራዊ ስብስብ ላይ እንዳገናኘኸን ሁሉ፣ ነገ በጀነተል ፊርደውስ ከነቢያትና ከሷሊሆች ጋር አብረን የምንቀመጥና የምንሳሳቅ የጀነት ጎረቤቶች አድርገን። መለያየታችን ለናፍቆት እንጂ ለጥል አይሁን።
አላህ ሆይ! በሰማነውና በተማርነው የምንሰራ፣ ሱናን በተግባር የምናደምቅና ለዲንህ ታማኝ የሆንን ባሮችህ አድርገን።
በመጨረሻ የምኮምቦልቻ ጠንካራ ሰለፊይ ጀመዓዎች ሆይ! ላደርጋችሁልን ያማር የጣፈጠ መስተንግዶ አላህ ጀዛችሁን በዱኒያም በአኼራም ይክፈላችሁ አላህ ያስደስታችሁ የዒልማችንን አዝመራ አላህ ይባርክላችሁ! ሁላችሁንም ለአላህ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَى ስል እወዳችኋለሁ።
📝ለአላህ ብሎ የሚወዳችሁ ትንሹ ወንድማችሁ አቡ ሒበቲላህ ሁሰይን ኢስማኢል
🌹t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
🌹t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
የዝሙት መዘዙ አስከፊነቱ እጅግ የላቀ ነው አሏህ ይጠብቀን እና
لا تقربوا الزنى إنه كان فاحشة وساء سبيلا
ወደ ዝሙትም አትቅረቡ እርሱ በእርግጥ አስከፊ (ወንጀል) ነው መጥፎ መንገድም ነው(ሱረቱል ኢስራዕ 32")
የኢማን መውጣት💧 አንድ ሰው ዝሙት ላይ በሚሆንበት ጊዜ ኢማኑ ከላዩ ላይ እንደሚገፈፍ በሐዲሥ ተነግሯል።
የፊት ብርሃንን (ኑርን) ማጣት💧 ዝሙት የሰውን ልጅ ክብርና በፊቱ ላይ የሚኖረውን የቅንነትና የሰላም ብርሃን ያጠፋል
ለበሽታ መጋለጥ 👈በሕክምናው ዓለምም እንደምናየው ለተለያዩ የማይፈወሱና አስከፊ ለሆኑ የአዕምሮና የአካል በሽታዎች (እንደ ኤችአይቪ እና ሌሎች የአባለዘር በሽታዎች) ዋነኛ መንገድ ነው።
2. በማኅበረሰብ ላይ የሚያደርሰው ጥፋት
የትውልድ መበላሸት👈የቤተሰብን ዋጋ ያጠፋል ያለ አባትና ያለ እናት እንክብካቤ የሚወለዱ ልጆችን በማብዛት ለማኅበራዊ ቀውስ ይዳርጋል
የእምነትና የሐያእ (ዕፍረት) መጥፋት በአንድ ማኅበረሰብ ውስጥ ዝሙት ሲስፋፋ ዕፍረትና መከባበር ይጠፋል ይህም የአላህን ቁጣና ቅጣት ያፋጥናል
የደስታና የበረከት መራቅ👈 በዝሙት የሚገኝ ጊዜያዊ ስሜት የውስጥ ሰላምን ይነጥቃል በሪዝቅ (በሲሳይ) ውስጥ የሚኖረውን በረከትም ያጠፋል።
ታላቅ መልዕክት👈 አላህ ሁል ጊዜ መሐሪና አዘኔታው ሰፊ የሆነ ጌታ ነው። የሰው ልጅ ተሳስቶ እንኳ ወደዚህ መንገድ ሄዶ ከሆነ ወዲያውኑ በቅን ልብ ተጸጽቶ (ተውባት አድርጎ) ወደ አላህ መመለስ አለበት። አላህ እውነተኛ ተውባትን ይቀበላል ወንጀልንም ይምራል። ራሳችንን ትውልዳችንን እና ቤተሰባችንን ከዚህ አስከፊ መንገድ ለመጠበቅ አላህን መፍራት እይታን መስበር ከመጥፎ ጓደኞች መራቅና ወደ መልካም ተግባራት መቅረብ ያስፈልጋልhttps://t.me/umu_afifah_ami_chanal
Repost from ስለ ቀልባችን
ከሰሞኑ በውስጥ መስመር ከደረሱኝ እጅግ ልብ የሚነኩ መልእክቶች መካከል፣ ከላይ የምትመለከቱት የወንድማችን መልእክት አንዱ ነው።
ይህ ወንድማችን በዚህ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ በበጎ ተሳትፎው የምናውቀው ሰው ነው። ነገር ግን ዱኒያ ፈታኝ ናትና፣ የልጆች አልባሳት ቡቲክ ስራ ውስጥ ገብቶ በደረሰበት ከባድ ኪሳራ ምክንያት አሁን ላይ እጅግ ከባድ የዕዳ ሸክም ወድቆበታል። በአሁኑ ሰዓት የሰው ዕዳ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴውን አግቶት፣ የቤት ኪራይ መክፈያና የልጆቹን ቀለብ ማቅረቢያ እንኳ አጥቶ በእጅጉ ተጨንቋል።
ዱኒያህ ይህችው ናት...ዛሬ እኛ መርዳት የምንችልበት አቅም ሲኖረን፣ ነገ የእኛ መድረሻ ምን እንደሚሆን አናውቅም።
📌 የባንክ አካውንት
ንግድ ባንክ (CBE)
1000340662583
አቢሲኒያ ባንክ
10686369
አዋሽ ባንክ
014250816807603
የአካውንቱ ስም፦MEHAMMED BEDIRU NASIR
📌 እሱን ቀጥታ አግኝታችሁ ለማነጋገር፦
0900076123
@AbuMeryem
የኔ ሴት ከሰውጋ የሚያኖርሽ መልክሽ ሳይሆን መልካምነትሽ ነው ::ስለዚህ መልካም ስነምግባር ይኑርሽ
መልካም ባህሪ ያላት ሴት መልክዋ ቢለወጥ እንኳ የሰራችው መልካምነትና ትህትናዋ ሁሌም በሰዎች ልብ ውስጥ በክብር ይኖራል። እውነተኛ ክብሯ የሚለካው በሰውነቷ ላይ በምታደርገው ጌጥ ሳይሆን በልቧ ውስጥ ባለው መልካምነት ነው።
ውዷ እህቴ ውጫዊ ገጽታሽን ለመጠበቅ እንደምትለፊው ሁሉ ከሰው ጋር በሰላምና በፍቅር የሚያኖርሽን ውስጣዊ ማንነትሽንና ስነ-ምግባርሽን ለመገንባት ይበልጥ ትኩረት ስጪ። ውበትሽ ባህሪሽ ነው::
https://t.me/htt_Aselefy
https://t.me/htt_Aselefy
Repost from Zɪʏᴀᴅ Pʀᴏ™
👉 የእስላማዊ ትላልቅ ቻናል መግዛት የምትፈልጉ እጃችን ላይ ሁለት ቻናል አሉ በርካሽ ዋጋ 💵
👉5000 subscribers
👉10000 subscribers
🫰መግዛት የሚፈልግ ብቻ ያናግረን ✨
Repost from ዳዕዋ ሰለፍያ በሶባ(አሸዋዉ) ቢላል መሥጅድ★✈
በዚህ ግቡና የሸይኽ አሊዩ ራዚሂን ሙሀዶራ ተከታተሉ
ከደሴ አረብ ገንዳ መስጅድ ቀጥታ ስርጭት
//t.me/AbulBukhariSeid?livestream
🌟 አይዞሽ በትግል ላይ ያለሺው እህቴ
🌸አይዞሽ እራሴ በይ ነፍስሺን አጠናክሪያት👑
አይዞሽ እራሴ ይህ የጀመርሽው መንገድ እንዲሁ ተራ መንገድ አይደለም የአላህን ዲን ይበልጥ ለማወቅና እርሱን በዕውቀት ለመገዛት የሚደረግ ታላቅ የጂሃድ አይነት ነው
ዒልም (ዕውቀት) ብርሃን ነው ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ዕውቀትን መፈለግ በሙስሊም ሁሉ ላይ ግዴታ ነው ብለዋል። ይህን ግዴታ ለመወጣትና የአላህን ውዴታ ለማግኘት የምታደርጊውን ጥረት አላህ ከንቱ አያደርገውም
👉ኢኽላስ (ጥራት) ይኑርሽ የምታጥኚው ለዱንያ ክብር ወይም ለሰው ምስጋና ሳይሆን በውስጥሽ ያለውን ድንቁርና ለማስወገድ አላህን በዕውቀት ለመፍራትና ዲንሽን በተስተካከለ መልኩ ለመተግበር ይሁን
👉ትዕግስትና ጽናት👈ዕውቀት በአንድ ጀምበር አይገኝም። ድካም ሲሰማሽ ሰይጣን ስንፍናን ሊያናውዝሽ ሲሞክር 👉ረቢ ዚይድኒ ዒልማ (ጌታዬ ሆይ! ዕውቀትን ጨምርልኝ) በማለት ዱዓ አድርጊ
አላህ ያግዝሻል ለአላህ ብለሽ የተነሳሽበትን መንገድ እርሱ ያቀልልሻል። ወደ ጀነት የሚወስደውን መንገድም ይመራሻል
+1
🌟 አይዞሽ በትግል ላይ ያለሺው እህቴ
🌸አይዞሽ እራሴ በይ ነፍስሺን አጠናክሪያት👑
አይዞሽ እራሴ ይህ የጀመርሽው መንገድ እንዲሁ ተራ መንገድ አይደለም የአላህን ዲን ይበልጥ ለማወቅና እርሱን በዕውቀት ለመገዛት የሚደረግ ታላቅ የጂሃድ አይነት ነው
ዒልም (ዕውቀት) ብርሃን ነው ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ዕውቀትን መፈለግ በሙስሊም ሁሉ ላይ ግዴታ ነው ብለዋል። ይህን ግዴታ ለመወጣትና የአላህን ውዴታ ለማግኘት የምታደርጊውን ጥረት አላህ ከንቱ አያደርገውም
👉ኢኽላስ (ጥራት) ይኑርሽ የምታጥኚው ለዱንያ ክብር ወይም ለሰው ምስጋና ሳይሆን በውስጥሽ ያለውን ድንቁርና ለማስወገድ አላህን በዕውቀት ለመፍራትና ዲንሽን በተስተካከለ መልኩ ለመተግበር ይሁን
👉ትዕግስትና ጽናት👈ዕውቀት በአንድ ጀምበር አይገኝም። ድካም ሲሰማሽ ሰይጣን ስንፍናን ሊያናውዝሽ ሲሞክር 👉ረቢ ዚይድኒ ዒልማ (ጌታዬ ሆይ! ዕውቀትን ጨምርልኝ) በማለት ዱዓ አድርጊ
አላህ ያግዝሻል ለአላህ ብለሽ የተነሳሽበትን መንገድ እርሱ ያቀልልሻል። ወደ ጀነት የሚወስደውን መንገድም ይመራሻል
Repost from Zɪʏᴀᴅ Pʀᴏ™
❤️🔥❤️🔥❤️🔥❤️🔥❤️🔥❤️🔥
🎧✍መልካም ዕድል ለእውቀት ፈላጊዎች በሙሉ
የተጅዊድ ትምህርት የምትፈልጉ ሙሉ በሙሉ ነፃ የሆነ join ማለት ብቻ
👉 ሙራጃ
👉 ተጅዊድ በነፃ
👉 ለተደቡር
🫴እውነተኛ ማስታወቂያ ነዉ ተቀላቀሉ ተማሩ 🫴🫴
የጠዋት አዝካር
اللهُ لاَ إِلَهَ إِلاَّ هُوَ الْحَيُّ الْقَيُّومُ لاَ تَأْخُذُهُ سِنَةٌ وَلاَ نَوْمٌ لَّهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الأَرْضِ مَن ذَا الَّذِي يَشْفَعُ عِنْدَهُ إِلاَّ بِإِذْنِهِ يَعْلَمُ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُمْ وَلاَ يُحِيطُونَ بِشَىْءٍ مِّنْ عِلْمِهِ إِلاَّ بِمَا شَاء وَسِعَ كُرْسِيُّهُ السَّمَاوَاتِ وَالأَرْضَ وَلاَ يَؤُودُهُ حِفْظُهُمَا وَهُوَ الْعَلِيُّ الْعَظِيمُ
አላህ ከእርሱ በቀር ሌላ በሀቅ የሚመለክ አምላክ የለም፡፡ ሕያው ራሱን ቻይ ነው፡፡ ማንገላጀትም እንቅልፍም አትይዘውም፡፡ በሰማያት ውስጥና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ የርሱ ብቻ ነው፡፡ ያ እርሱ ዘንድ በፈቃዱ ቢኾን እንጅ የሚያማልድ ማነው ከፍጡሮች በፊታቸው ያለውንና ከኋላቸው ያለውን ሁሉ ያውቃል፡፡ በሻውም ነገር እንጂ ከዕውቀቱ በምንም ነገር አያካብቡም አያውቁም፡፡ መንበሩ ሰማያትንና ምድርን ሰፋ፡፡ ጥበቃቸውም አያቅተውም፡፡ እርሱም የሁሉ በላይ ታላቅ ነው።
https://t.me/umu_afifah_ami_chanal
⚠️ ስለ መንሐጅ ምርጥ ነሲሀ ምክር ሁላችንም ልናዳምጠው የሚገባ ጉዳይ ነው።
⚠️ስለ ኢኽዋኖችም ተዳሶበታል ስለሌሎችም ተዳሶበታል
🎙በጀግናው ኡስታዛችን ኢብኑ ሙነወር (ሀፊዘሁሏህ)
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
🔰 ስለ ዑዝር ቢል ጀህል ምርጥ ነሲሀ
⚠️የሙሳ ሠዎች ታሪክ ተጠቅሷል
⚠️አድስ ተክፊሮች አሉ ኢብን ተይሚያን:ኢብን ዑሠይሚንን... የሚያከፍሩ
🎙በጀግናችን ኡስታዝ ኢብን ሙነወር
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
Repost from Ansuar Muhammed {አንሷር ሙሐመድ} Official Channel
አስቸኳይዛሬ ኢን ሻ አላህ ከመ غሪብ እስከ ኢሻ በደሴ ከተማ የደዕዋ ፕሮግራም አለ።
አሬራ ሰላም መስጂድበኡስታዝ አቡ ሒዛም እና
አውራ ጎዳና (የጤሮ አንዋር) መስጂድበኡስታዝ ሁሴን አሊ ደሴዎች ይሄን ታላቅ የሆነ እድል ልንጠቀምበት ይገባል። ሼር አድርጉት
+2
☕️ የቡናዋ መሐንዲስና የመዳም ፈትዋ ክክክክክ
ይቺው የኛዋ የቡና መሐንዲስ አንድ ቀን እንደለመደችው ክፍሏን ዘግታ ቡኩሯን አጥና ኬክና ቡናዋን አቅርባ ቁጭ ብላለች። ልክ የመጀመሪያውን የቡና ኮብ ልታደርግ ሲያምራት... መዳም በሩን “ክፈቺ!” ብላ አንኳኳችው።
መሐንዲሷም በሩን ስትከፍት መዳም በጭሱ ተገርማ ሳሎን ያለውን ስራ ማዘዝ ጀመረች።
የኛዋ መሐንዲስ ግን በውስጧ እንዲህ አለች ይባላል
“ይሄ መዳም ቤት ስራ መብዛት እኮ በሸሪዓ (በህግ) ቢታይ... ኒካህ (ጋብቻ) እንደማውረድ ነው! በቃ አንድ ጊዜ ‘ፈታሁሽ’ ተብሎ የሚገላገሉት ቢሆን ኖሮ ይቺን ቡናዬን ሰላም ለመጠጣት ስል መቶ ጊዜ ‘ፈትቼሻለሁ መዳም’ እላት ነበር
💡 ቁም ነገር የእውነታው ጨዋታ 👌👌
ቀልዱን እንተወውና... በትልልቅ ዑለማኦች (አሊሞች) ዘንድ ትልቅ ቁም ነገር አለ። ሰሃቦችና ታላላቅ ሰዎች ጭንቀትና ስራ ሲበዛባቸው ራሳቸውን ፈገግ የሚያደርግ ጨዋታ ይጫወቱ ነበር
እውነተኛ እረፍት በዱንያ ላይ ሙሉ በሙሉ ከስራና ከድካም ማረፍ አይቻልም። እውነተኛው እረፍት ያለው አእምሮን በሶላት አካልን ደግሞ ለራስ በሚሰጥ ጥቂት የቡና ሰዓት ማደስ ሲቻል ነው።
ትዕግስትና አጅር ሰው አገር ላይ ተቸግሮ ሰርቶ የራስን ሃላል ኑሮ መኖር ትልቅ ጂሃድ እና ሸሪዓዊ ክብር አለው።
ስለዚህ ያቺ የምትጠጫት ቡና እንዲሁ ዝም ብላ መጠጥ ሳትሆን ለነገው ጥንካሬሽ የሚሆን የትዕግስት መሙያ ባትሪሽ ናት!
አላህ ስራሽን ያቅልልሽ የቡና ሰዓትሽን የተባረከ ያድርገው 🤲🌹
Repost from ዳዕዋ ሰለፍያ በሶባ(አሸዋዉ) ቢላል መሥጅድ★✈
ከወሎው ታላቅ ደውራ ኮንቦልቻ ከተማ ከአንሷር መስጅድ ቀጥታ ስርጭት
ኡስታዝ አብዱሮህማን ሹመት ገብቷል
👇👇👇👇👇🌹👇👇👇
t.me/Sobabilalmesjid?livestream=a404eee12a9d181392
