ar
Feedback
Orthodox mezemur ኦርቶዶክስ መዝሙር

Orthodox mezemur ኦርቶዶክስ መዝሙር

الذهاب إلى القناة على Telegram

እኔ ግን በቸርነትህ ታመንሁ ልቤም በመድኃኒትህ ደስ ይለዋል የረዳኝን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ ለልዑል እግዚአብሔር ስምም እዘምራለሁ ። መዝሙረ ዳዊት 13 : 5 - 6 o⁠:⁠-⁠)- ለማንኛውም ጥያቄ በስር ባስቀመጥነው ሊንክ ሊጠይቁን ይችላሉ 👇👇 - @tan_flf -

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
283
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-17 أيام
+2530 أيام
أرشيف المشاركات
አሜን የኔ ጌታ ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች    •➢ ሼር // SHARE 👇👇👇 @yemezmur_getimoche @yemezmur_getimoche @yemezmur_getimoche ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች    •➢ ሼር // SHARE 👇👇👇 @yemezmur_getimoche @yemezmur_getimoche @yemezmur_getimoche

በእኔ ቢጠቁር በእኔ ቢጠቁርም ሰማይ በእኔ ቢጠልቅም ፀሀይ በነፋሳት የማይጠፋ ፋኖሴ ኢየሱስ ነው የመኖር እስትንፋሴ (፪) እርሱን ታምኜ እወጣለሁ እርሱን ታምኜ እገባለሁ ድብቅ ሰራዊት አለው ለኔ የሚጠብቀኝ በዘመኔ እግዚአብሔር ለኔ ብርሀኔ ነው የሚያስደነግጠኝ የሚያስፈራኝ ማነው ሰው አልባ ሆኜ በስደት ወዳጄ ሆነኝ የኔ አባት ክርስቶስ ለኔ ህይወቴ ነው እርሱን ታምኜ እኖራለሁ የለም የሚያስፈራኝ በዘመኔ ብርሀን ነውና እግዚአብሔር ለኔ መች ይሰጠኛል ለጠላት አይሰለጥንም በኔ ሞት የሚጠብቀኝ ጌታ ነው የትኛው ጠላት ሊደፍረው በቤቴ መካን ላይ ደም ይታያል እኔን ከእግዚአብሔር ከቶ ማን ይለያል ይሄው አቆመኝ በመቅደሱ እየጠበቀ በመንፈሱ እኔን ሊያከብር ራሱን ሰቶ ገዝቶኛል ጌታ ሞቴን ሞቶ ይገዛ ለስሙ ስጋ መንፈሴ በእርሱ ነውና ለዛሬ መድረሴ ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች    •➢ ሼር // SHARE 👇👇👇 @yemezmur_getimoche @yemezmur_getimoche @yemezmur_getimoche

ተናገር አለኝ ተናገር አለኝ መስክር ተናገር አለኝ ዘምር ለቀራንዮ ውለታ አርምሞ የለም ዝምታ ለመድኃኔዓለም ውለታ አርምሞ የለም ዝምታ
አዝ
ሰው አድርጎኝ ሞቶ በደሙ ኑሮዬን ባርኮት ሕመሙ ሰላም አውጥቶ ካስገባ ልያዝ ለክብሩ ዘንባባ ሆሳዕና ልበል መድኃኒት ከፍ በልልኝ የኔ አባት ተጠምተኸ እኔ ረካሁ ስራህ ግሩም ነው ደነቀኝ
አዝ
እጆቹን እዩት በእምነት ቆሰለ ሊሰጠኝ ሕይወት በዚያ ታትሞ ውበቴ እየሱስ ለኔ ብርታቴ ከማንም በላይ ከምንም ለኔ ልዩ ነው ዘላለም ሕይወቴን ለእርሱ አስማርኬ እኔስ በረታሁ በአምላኬ
አዝ
የእሾህ አክሊሉ በራሱ ለእኔ ቤዛ ነው ሞገሱ ሞቴን ገድሎታል አባቴ ሰላሜ እርሱ ነው እረፍቴ ሰው የመሆኔ ምስጢሩ የማይለወጥ ነው ፍቅሩ የገባኝ እውነት በምድር ላይ ፍቅር ነው ጌታ ኤልሻዳይ
አዝ
ክብሩን ለማወጅ ተነሳሁ ሲያድነኝ ከሞት እያየሁ ገመና ሸፋኝ ኪዳኔ ተራበ ውዴ መድኃኔ ይሄ ነው የቆመኝ በፊቱ ወሰን የሌለው ምሕረቱ ለዚህ ደግነት ውለታ ምን ይከፈላል ለጌታ ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች    •➢ ሼር // SHARE 👇👇👇 @yemezmur_getimoche @yemezmur_getimoche @yemezmur_getimoche

ንዒ በሰዓታቱ ንዒ/3/ በሰዓታቱ ዜማ ሁሉም አደግድጎ ምስጋና(አማፅኖ) ሲያሰማ ንዒ/3/ ቅረቢ ሃቤየ ልክ እንደሚወዱሽ ሐዋርያት አበውያን ምንኛ ቢታደል ፍቅርሽ ቢገባው ነው ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ንዒ ንዒ ያለው እኛም እንጮኻለን ሆነን በጉባኤ እንደ ሐዋርያት ገብተናል ሱባኤ       ርግብየ/2/ ሶበ እቤለኪ       ቅረቢ ሃቤየ ድንግል ሰላም ለኪ አዝ ህናቱ በዜማ ዝቡ በተመስጦ ንዒ ይላላል ዘውትር ቢያፈቅርሽ አብልጦ በእንተ ማርያም ነው የፍጥረት ልመና ግሩም ስለሆነ የክብርሽ ልዕልና       ርግብየ/2/ ሶበ እቤለኪ       ቅረቢየ ሃቤየ ድንግል ሰላም ለኪ አዝ በንፁህ ልቦና እንደ ህፃቱ እንፁም እፀልይ እንጩኽ በብርቱ ትንሳኤ እርገትሽን እንዲያሳየን አምላክ በእንባ እንማልዳለን ፊቱ በመምበርከክ        ርግብየ/2/ ሶበ እቤለኪ       ቅረቢየ ሃቤየ ድንግል ሰላም ለኪ አዝ አንስዓት እምነ ብለን ለመዘመር በጤና ጠብቆ እንዲያቆመን ለክብ ደግሞ ለአመ ሱባኤ እንድበቃ ልጅሽ ይለመነን የሠላም አለቃ       ርግብየ/2/ ሶበ እቤለኪ       ቅረቢየ ሃቤየ ድንግል ሰላም ለኪ ዘማሪ አቤል ተስፋዬ የበገና መዝሙር ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች    •➢ ሼር // SHARE 👇👇👇 @yemezmur_getimoche @yemezmur_getimoche @yemezmur_getimoche

​​ተግተን እንጸልይ ተግተን እንጸልይ ወደ ፈተና እንዳንገባ በሕይወታችን በንደራችን እግዚአብሔር ይግባ በአባታችን ፊት በጸሎት ወድቀን ኃይል እንታጠቅ በጸጋ እንድንኖር የሚቃወመን ጠላትም ይድቀቅ         አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸► በጦር ሰፈር ነን ያ ጠላታችን ሌጌዎን ታጥቋል መሳሪያ ሳንይዝ የወጣነውን ስንቶቹን ጥሏል ዘይት አልቆብን የመቅረዛችን መብራት ደብዝዟል ብርሃኑን ጥለን የጠላት ምሽግ በምን ይታያል    ተንስኡ ለጸሎት         አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸► ያዘነብላል ጆሮውን ወደኛ ጠላት ይመታል ወጥመዱን ሰብሮ ያመንንበትን ያሻግረናል ያሰማራናል በለምለሙ መስክ በተስፋ ሞልቶ ማን አፍሮ ያውቃል የእግዚአብሔርን ስሙንስ ጠርቶ    ተንስኡ ለጸሎት         አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸► የክብር ዘይት በቆሰለው ሰው ቀድተው ቢያፈሱት መድኃኒት ነው ለዓለም ኹሉ ዲናር ማይከፍሉት የፍቅር አባት ደጁን ስንመታ ይከፍትልናል መሻታችንን እየፈጸመ ይባርከናል ተንስኡ ለጸሎት ሊቀ መዘምራን ቲዎድሮስ ዮሴፍ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች    •➢ ሼር // SHARE 👇👇👇 @yemezmur_getimoche @yemezmur_getimoche @yemezmur_getimoche

የመስቀሉ ፍቅር ሲገባን 
የመስቀሉ ፍቅር ሲገባን (4) እመቤታችንን እንወዳታለን የመስቀሉ ፍቅር የገባቸው (4) እመቤታችን አለች ከጎናቸው አባ ሕርያቆስ አባታችን የመስቀሉ ነገር ቢገባው ልቤ አፈለቀ አለ መልካም ነገር ከእመቤቴ ጋራ ሲነጋገር ከድንግል ማርያም ጋር ሲነጋገር ነይ ነይ እምዬ ማርያም ነይ ነይ ቤዛዊት አለም አንድ ወልዳ ስሙን አበዛችው (2) አንዱ ሃገር ስትሄድ መድሃኒአለም አለችው አንድ ወልዳ ስሙን አበዛችው (2) አንዱ ሃገር ስትሄድ ኢየሱስ አለችው አንድ ወልዳ ስሙን አበዛችው (2) አንዱ ሃገር ስትሄድ ክርስቶስ አለችው አንድ ወልዳ ስሙን አበዛችው (2) ለመናኒው ፀሎት ልዩ እጣን የዋሻው ሻማ ነሽ እመብሃን መአዛሽ ሸተተኝ ከግሸን ትናፍቂኛለሽ ምን ልሁን ትርቢኝማለሽ ምን ልሁን ዳዊት በመዝሙሩ ያነሳሻል የያዕቆብ ድንኳን ነሽ ይልሻል የእግዚአብሔር ሃገር የሚሉሽ እመቤቴ ማርያም አንቺ ነሽ (2) ቤተልሔም ስሄድ አይሻለሁ ቀራኒዮ ስሄድ አይሻለሁ ፍጹም አትለይም ከልጅሽ፥ የአንቺስ ልዩ ነው ፍቅርሽ (2) ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች    •➢ ሼር // SHARE 👇👇👇 @yemezmur_getimoche @yemezmur_getimoche @yemezmur_getimoche