ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ

ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ

الذهاب إلى القناة على Telegram

ይህ ቻናል በአላህ ፈቃድ በማህበረሰባችን ውስጥ በሰፊው ስለተሰራጨው ታላቁ ሙንከር ስለ(ሽርክ) እና የተፈጠርንበት አላማ ስለሆነው ስለ (ተውሒድ) እንድሁም ስለሱና እና ቢድዓ እና ሌሎችም ኸይር ነገሮች የሚለቀቅበት ቻናል ነው።

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
320
المشتركون
+124 ساعات
-47 أيام
+5530 أيام
أرشيف المشاركات
أعلام السنة المنشورة.pdf

Repost from Dr. Seid Musa
قال الشيخ إبراهيم المحيميد - حفظه الله تعالى - : "هذه البلاد المباركة أسسها المحمدان ابن سعود وابن عبدالوهاب على تحقيق الركن الأول في الإسلام قولا وعملا واعتقادا' ومضمونها الدعوة للتوحيد الصافي النقي أولا، ثم القضاء على البدع والمحدثات ' وسار ولاة أمورنا علماء وأمراء على هذا من ثلاثة قرون حتى هذه الساعة ' وأي دعوة لإحياء البدع والخرافات في ديار ابن سعود من أي شخص مهما كان منصبه الشرعي هي محاولة لهدم الأساس الذي قامت عليه هذه البلاد المباركة، وقدمت في سبيل دعوة الرسل النقية دماء زكية وهدمت مدنها " فمنذ تأسيسها لاقبور تعبد ولازوايا صوفية تقرر فيها البدع والمحدثات وستبقى بإذن الله هي الحصن الحصين لدعوة أهل السنة ' وانتشر هذه الأيام مقطع لصاحب منصب شرعي يؤصل لبدعة المولد النبوي ويساوي بين صلاة التهجد وبين الاحتفال بالمولد النبوي وأن لكلا الفعلين أصلا يستند عليه، ومستنده في تجويز المولد أن الله أمرنا بالفرح بفضل الله ورحمته' ولسان حاله يقول دعوا الناس يحتفلون بمولده من باب الفرح ' والجواب على هذه الشبهة من أوجه : الوجه الأول : أن صلاة التهجد ليست ببدعة من العمل، ووجه ذلك أن النبي فرض عليه قيام الليل في مكة حرسها الله، وواظب عليه، وفي المدينة كان يجتهد في رمضان عامة، والعشرة الأواخر خاصة، ما لا يجتهد في غيره، فعن أم المؤمنين عائشة - رضي الله عنها - قَالَتْ: كَانَ رَسُولُ اللَّهِ ﷺ يَجْتَهِدُ فِي رَمضانَ مَا لا يَجْتَهِدُ في غَيْرِهِ، وَفِي العَشْرِ الأَوَاخِرِ منْه مَالا يَجْتَهدُ في غَيْرِهِ" فقيام الليل كان فرض عليه في أول الأمر ، ولايفهم من أحاديث الاجتهاد في رمضان إلا كثرة النفل " سواء سمي تهجدا أو لم يسم، سواء كانت تصلى متواصلة أو متقطعة ' السؤال أين وجه البدعة هنا ؟ الوجه الثاني : أما تجويزه لبدعة المولد استنادا لقوله تعالى (قُلْ بِفَضْلِ اللَّهِ وَبِرَحْمَتِهِ فَبِذَٰلِكَ فَلْيَفْرَحُوا هُوَ خَيْرٌ مِّمَّا يَجمعون) وأن من الفرح الاحتفال بمولده فالجواب عنه أن الفرح عمل قلبي، والمولد عمل بدني، ومن شروط القياس استواء الفرع بالأصل. الوجه الثالث : قيام الليل صلاة والتهجد كذلك صلاة وتخصيصها بالعشر الأواخر لفعل الرسول وقيام المقتضى في كثرة التنفل لهذا الفعل وهو تحري ليلة القدر . الوجه الرابع : والله لو صح القياس لكان يتعين اليوم منعه لما يحدث في الموالد من غلو وبدع لا ترضي الله ورسوله' الوجه الخامس: التهجد دعاء وسجود وركوع ودموع وإنابة وتوبة، والموالد ضلالات ومحدثات ورقص وضرب بالدفوف وغلو لجناب الرسول . أين الثرى من الثريا ؟".

«ስም አልጠራም» ----------------- ደሊልና ስሜት የተምታታባችሁ፡ የምትበጠብጡን መንጋ መስርታችሁ፡ መስመር አትሳቱ ተው ስንላችሁ፡ ምክርን እንደ ቅናት እየቆጠራችሁ፡ እስከዛሬ ድረስ ምን አተረፋችሁ⁉️ ጥቅምና ጉዳት ፍፁም የማትለዩ፡ በሐቅ መረጃ የማትወያዩ፡ በጥላቻ ብቻ የምትሰቃዩ፡ ሆስፒታል ግቡና ከአንገት በላይ ታዩ፡ በምንኖርባት በዚህች ጠፊ ሀገር፡ ጎምዝዞ ቢመርም እውነትን መናገር፡ መከራ ቢዘንብም ወንዙን ለመሻገር፡ ከጫጩቶች መሐል ፈንግል ባይወራም፡ ስምን ከነቦታ ለመጥራት ባልፈራም፡ መንጋ ተፈታተሽ እኔ ስም አልጠራም፡ .....ኑር.... t.me/nuredinal_arebi t.me/nuredinal_arebi

فإن السلفية عمل وليست دعاوىٰ فَاسْتَمْسِكْ بِالَّذِي أُوحِيَ إِلَيْكَ ۖ إِنَّكَ عَلَىٰ صِرَاطٍ مُسْتَقِيمٍ وأما أقوال الناس فيك وافترائهم وظنونهم السيئة فمرض وهَمٌّ  يحملونه ويتأذون به هم وتسلّى بتسلية الله لك ولأمثالك إِنَّ رَبَّكَ يَقْضِي بَيْنَهُم بِحُكْمِهِ ۚ وَهُوَ الْعَزِيزُ الْعَلِيمُ (78) فَتَوَكَّلْ عَلَى اللَّهِ ۖ إِنَّكَ عَلَى الْحَقِّ الْمُبِينِ (79) سورة النمل لن يضروكم إلا أذى ينبغي أن ينزل السلفيون هؤلاء منزلة الكلاب تنبح هي ثم تسكت لكن الكلب إذا زجرته ورميت عليه زاد نباحاً فألقمه إن شئت عظماً لعله يسكت. أو كلما طن الذبابُ زجرته * ..... إن الذباب إذاً علَى لعزيز! أحسن لك أن لا ترد الجواب على اللئيم فالسكوت أضر عليه من الجواب لأن الجواب يفتح له المجال يسب ويشتم أكثر فأكثر. وصدق من قال: «ولقد أمرُّ على اللئيم يشتمني، فمضيت ثم قلت لا يعنيني» (ولا يقصدني) أيها السلفي፡ أثبت فإنك علىٰ الحق المبين.. ولا يغرنّك الأدعياء من #اللتمين #والحدادىين الكذابين والمدسوسين المفتونين الذين يدّعون السلفية #زورًا #وتلبيسًا علىٰ الناس وعند الله تجتمع الخصوم "ሰለፍያ ማለት በተግባር የሚገለጽ እንጂ በባዶ የይገባኛል ጥያቄ (ወሬ) አይደለም።" (ወደ አንተ የተወረደውን አጥብቀህ ያዝ። አንተ በቀጥተኛው መንገድ ላይ ነህና።) [ሱረቱል ዙኽሩፍ፡ 43] ሰዎች ስለ አንተ የሚናገሩት ንግግር፣ የሚያወሩት ቅጥፈት እና መጥፎ ጥርጣሬያቸው፤ እነሱው ራሳቸው ተሸክመውት የሚሰቃዩበትና የሚጎዱበት በሽታ እና ጭንቀት ነው። ስለዚህ አላህ ለአንተ እና ለመሰሎችህ በሰጠው መጽናኛ ተጽናና። (ጌታህ በመካከላቸው በፍርዱ ቀን ይፈርዳል። እርሱም አሸናፊው ዐዋቂው ነው። በአላህም ላይ ተመካ። አንተ ግልጽ በሆነው እውነት ላይ ነህና።) [ሱረቱል ነምል፡ 78-79] (ማስከፋትን እንጂ ምንም አይጎዱአችሁም...) [ሱረቱ አሊ-ዒምራን፡ 111] ሰለፍያዎች እነዚህን ተሳዳቢ ሰዎች ልክ እንደሚጮህ ከዚያም ዝም እንደሚል ውሻ ሊቆጥሯቸው ይገባል። ውሻን በጮህክበት እና በተቆጣኸው ቁጥር ጩኸቱን ይጨምራል። ከፈለግክ ግን ዝም እንዲል አጥንት ወርውርለት። እንደተባለውም ግጥም፦ ዝንብ ባንጫጫ እና በጮኸ ቁጥር የምመልስለት ከሆነ...እንግዲያውስ ዝንቡ ትልቅ ክብር አገኘ ማለት ነዋ!!! ለመጥፎ ሰው መልስ አለመስጠትህ ለአንተ የተሻለ ነው። ዝምታ ከመመለስ የበለጠ ይጎዳዋል። ምክንያቱም መልስ መስጠትህ አብዝቶ እንዲሳደብ እና እንዲዘልፍ በር ይከፍትለታል። እውነተኛው ተናጋሪ ገጣሚ እንዲህ እንዳለው ነው፦ «አንድ ባለጌ ሲሳደበኝ አለፍኩት። መንገዴንም ቀጠልኩና እኔን አይመለከተኝም እኔን አስቦ አይደለም አልኩኝ።» አንተ ሰለፊ ሆይ! ፅና! አንተ ግልጽ በሆነው እውነት ላይ ነህና። ከሰዎች ዘንድ ሰለፍይ ነን እያሉ በውሸት እና በማደናገር ከሚሞግቱት አጭበርባሪ #ለተምዮች እንዲሁም ውሸታም ከሆኑ #ሐዳዲዮች ሰርገው ገቢዎች እና ፈተና ውስጥ ከወደቁት ሰዎች አትታለል። የሚሟገቱ ባለጋራዎች ሁሉ ነገ አላህ ዘንድ ይሰበሰባሉ።" የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/Abulabas1444 https://t.me/Abulabas1444

የነገሮችን መጠራቀም ተጠንቀቁ። እነዚህ መጠራቀሞች የፈነዱ እለት ወዳጅ አይለዩም፣ የልብ ሰውንም አያስቀሩም። … የቸልተኝነት፣ የራስ ወዳድነትና የብዙ ጥፋቶች መደጋገም የሆነ ቀን የለየለት መጠላላትን ያመጣል።  "ለዚህች ጥፋት?" ትሉ ይሆናል በሰዓቷ ምክንያት…   እነርሱ ጋር ግን ትዕግስት  እንዲያጡ ያደረጋቸው የተጠራቀሙና የተቆጠሩ ጥፋቶች አሉ። ይሻሻላሉ ተብለው የተጠበቁ እልፍ ትዕግስቶችም ነበሩ… t.me/abdu_rheman_aman t.me/abdu_rheman_aman

     እንግዲያውስ አላህ አይተወንም!!!    ብቸኝነት ላደከማቸው፤ በኃላፊነት ሸክም ለተጫኑ፤ ረጅም ጊዜ በመጠበቅ ለሰለቹ፤ መጨረሻው በማይታወቅ መንገድ ፊት ለፊት በመቆም በፍርሃት ለተዋጡ ሁሉ...…… ከኡሙ ኢስማኢል ሀጀር የተላለፈ መልእክት;       "እንግዲያውስ አላህ አይተወንም!!"    ኢብራሂም ዓለይሂ ሰላም በጌታው ትዕዛዝ ምንም ዓይነት ሰው፣ ተክልም ይሁን ውሀ በሌለበት ምድረ በዳ ሸለቆ ከጨቅላ ህፃኗ ጋ ብቻዋን ትቷት ሄደ።   እሷ ግን ፍርሃቷን አልደበቀችም፤ የሌላት ጥንካሬ እንዳላትም አላስመሰለችም። ይልቁንስ እንዲህ ስትል ጠየቀች፦    "ይህንን እንድታደርግ ያዘዘህ አላህ ነውን???" የአላህ ትዕዛዝ መሆኑን ባወቀች ጊዜ;; በጉዞው አስቸጋሪነትም ይሁን በባይተዋርነት መከራ የማይናወጥ የፅናት ቃል ተናገረች;      "እንግዲያውስ አላህ አይተወንም!!"    ሀጀር ፈረጁ በየት በኩል እንደሚመጣላት አታውቅም ነበር: ግና ፈረጁ ያለው በማን አጅ እንደሆነ ጠንቅቃ ታውቃለች።    እንዲሁ ተቀምጣ ተኣምር እስኪመጣላት አልጠበቀችም፤ በሰፍዋ እና በመርዋ መሃል ተመላልሳ ሮጠች። አንዴ… ሁለቴ በተመላለሰችበት መንገድ ምንም ነገር ካለማግኘቷም ጋ ተስፋ ባለመቁረጥ ተመላልሳ በፍጥነት ትሮጣለች።    ፍርሃቷን ይዛ ትሮጣለች፤ ምንም ካለማግኘቷም ጋ እየሮጠች ትፈልጋለች። ይህ ሁሉ ሲሆን ልቧ ጌታዋ ላይ ከነበረው መተማመን አልተወገደም። በመጨረሻም……………      የዘምዘም ምንጭ ፈለቀ፤ የሀጀር ሩጫም እስከ ዕለተ ቂያማ ድረስ አላህ የሚመለክበት ስርዓት ሆኖ ቀጠለ። ትልቁ ትምህርት ያለው እዚህ ጋ ነው፦    ፈረጁ እንደሚመጣ እርግጠኛ መሆን ማለት: ከፍርሃት ነፃ መሆን ማለት አይደለም።    ባይሆን; ፍራቻህ አላህ ላይ ከሚኖርህ መተማመን የበለጠ ሀይል እንዲኖረው አለመፍቀድ ማለት ነው። ወዳጄ………    ዛሬ አንተም በራስህ ምድረ በዳ ሸለቆ ትሆን ይሆናል;    ማንንም በማያየው ብቸኝነት ውስጥ፤  ትከሻህን በሚያደቅ ኃላፍትና ስር፤  በጣም በሚያም መለያየት፤   ረዥም ጊዜ በቆየ መጠባበቅ፤  ከፊትህ በተዘጋጉ በሮች ወይም  አላህ ብቻ በሚያውቀው ውስጣዊ ትግል እየኖርክ ይሆናል። እናማ…………     የእፎይታ ጊዜ በመዘግየቱ "አላህ ትቶኛል" ብለህ እንዳታስብ!!     ያፈሰስካቸው እምባዎች ፍሬ አለማየትህ እርግጠኝነትህን እንዳይሸረሽረው!!   የምትችለውን ያህል ጥረት አድርግ፤ በእጅህ ያሉ እርምጃዎች ሁሉ ተግባራዊ አድርግ።    ከአንተ ቁጥጥር ውጭ የሆኑ ነገሮች; የነገሮች ሁሉ ተቆጣጣሪ ለሆነው ስጥ!! ሀጀርን ተመልከት፦    ፍለጋዋ ስትጀምር ውሀው የቱጋ እንደሆነ አታውቅም ነበር፤ በአላህ ዕውቀት ግን ውሀው በጣም ቅርብ ነበር!!    በተስፋ መቁረጥ እና በእርግጠኝነት መሃል ያለው ልዩነትም ይህ ነው፦ መፍትሔው በማይታይህ መንገድ እየሄድክ በፅኑ ልብ;       "አላህ አይተወኝም!!" ማለት የሀጀር ጌታ የአንተም ጌታ ነው;    ከበረሃው እምብርት ዘምዘም ያፈለቀው አላህ: ለአንተም በመከራዎችህ መሃል በር የመክፈት ሀይል አለው!!    ከችግር በኋላ እፎይታ፤ ከመደናበር በኋላ እርጋታ እንዲሁም ከረዥም ጥበቃ በኋላ ፈረጅን የሚያመጣው እሱ ነው። መድረሻህን ስላልታየህ ብቻ; ጉዞህን አታቋርጠው!!     ምንም እንኳ እስካሁን ፈረጁ ጋ ባትደርስም: ምን አልባት ፈረጁ ከምታስበው በጣም የቀረበ ሊሆን ይችላል።          አብሽር አላህ አይተወንም!!!

قال ناصر السنة الإمام أبو إسماعيل الهروي رحمه الله : "عرضت على السيف خمس مرات، لا يُقال لي: ارجع عن مذهبك، لكن اسكت عمّن خالفك، فأقول: لا أسكت" [سير أعلام النبلاء ٥٠٩/١٨]. አል ኢማም ናሲሩ ሱና አቡ ኢስማዒል አል-ሀረዊ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ይላሉ፦ 👉"አምስት ጊዜ ለግድያ ቀርቤያለሁ። በዚህ ጊዜ ከአቋምህ (ከመዝሀብህ) ተመለስ አልተባልኩም፤ ነገር ግን አንተን ከሚቃረኑ ሰዎች ላይ ዝም በል እባል ነበር። እኔም <<ዝም አልልም!>> እል ነበር።" ምንጭ፦ ሲየሩ አዕላሚ ኑበላዕ (18/ 509]) ወንድሜ! ዝም ካልክ ሁሉም ወዳጅህ ነው። ከተናገርክ ግን ከመጠላትም አልፈህ ለእስርም ከዚያም አልፎ #ለግድያም ትጋለጣለህ።

የለተምዮች የመንሐጅ አረዳድ፦ ለተምይ፦ ለምን የእከሌን ሸይኽ ሂስ (ጀርህ) አንተ ዘንድ (ሰለፊ) በሆነው በእከሌ ሰው ላይ አትቀበልም?? ፍትሀዊ ሰለፍይ፦ አላሳመነኝም! ለተምይ፦ አንተ አላሳመነኝም በሚል ሰበብ እውነትን (ሃቅን) እየገፋህ ነው! ፍትሐዊ ሰለፍይ፦ እሽ! ታዲያ አንተስ ለምን የሸይኽ ረቢዕን ሂስ (ጀርህ) በሸይኽ ሙሐመድ ብን ሃዲ ላይ አልተቀበልክም?? ለተምይ፦ ሸይኽ ረቢዕ ምንም መረጃ የላቸውም። ፍትሐዊ ሰለፍይ፦ አንተምኮ ምንም መረጃ የለውም በሚል ሰበብ እውነትን (ሀቅን) እየገፋህ ነው። ለተምይ፦ አላሳመነኝም የሚለው ቃል ዑለማዎች ያወገዙት ቃል ነው። ፍትሐዊ ሰለፍይ፦ አላህ ሱብሀነሁ ወተዐላ በቁርዓኑ እንዲህ ብሏል፦ የሁድ ህዝቦችም የሁድን አሉት፦ የሁድ ሆይ! ግልጽ ማስረጃ አላመጣህልንም፤ እኛም አንተ ስላልክ ብቻ አማልክቶቻችንን የምንተው አይደለንም። ተመልከት! እነሆ የዓድ ህዝቦች ለነብዩ የሁድ ግልጽ ማስረጃ አላመጣህልንም (አላሳመንከንም) እያሉት ነው። አይ ለተሞዎች! አጅብ ነው! አንዳንዶች ተቃዋሚህን የምትሞግትባቸው ቃላት በሸሪዓ ቃል በቃል የተቀመጡ (ተውቂፍይ) እንደሆኑ ያስባሉ። ወይም ደግሞ እነሱ እንደሚሉት ግዴታ እከሌ መረጃ የለውም ብለህ እንድትናገር ይፈልጋሉ። ይህንንም የሚያስቡት አንድ ሰው አላሳመነኝም ካለ፤ ያ አለማሳመን ሁልጊዜም በስሜት መነዳት እና በእልህ ላይ ብቻ የተገነባ ነው ከሚል የተሳሳተ እሳቤ በመነሳት ነው። ስለዚህ፦ በሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ሃዲ ጉዳይ ሞግቷቸው። መረጃ የለውም ማለታቸውን ካመኑበት የራሳቸውን መከራከሪያ አፈረሱ ማለት ነው።ከካዱ ደግሞ መልስ አጥተው #ተሸነፉ ማለት ነው። ቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/Abulabas1444 https://t.me/Abulabas1444

«መጅኑኑ ለይላ » --------------------------- «ሲጀመር ስማቸው #ለይላ የሚባሉ ሴቶች ፍቅራቸው ከባድ ነው እናቴ #ለይላ ነችና ስሜታችን ቢለያይም በተወሰነ መልኩ #ቀይስን እኔ እረዳዋለሁ» ....ኑር...✍️ .....«🌷መጅኑኑ ለይላ🌷» ከፍቅር ቃሬዛ ወድቆ ለደከመ፡ ተስፋው ህልም ሆኖ ለተከረከመ፡ ፈውሱን ላላገኘ ድኖ ላልታከመ፡ ለይላን ላፈቀረ ለይላን ለታመመ፡ በሷ የተጎዳ በሷ የዘመመ፡ ህይወቱን ኗሙሉ ሌላ ያልጠቆመ፡ ለይላ ላይ ጀምሮ ለይላ ላይ ለቆመ፡ በህይወት እስካለ አያስብም ሌላ፡ የልቡ ብርሀን አንድ እሷ ነች ለይላ፡፡ ፍቅር በሚሉት ጉድ የተጠለፈ ሰው፡ እብድ ነው የሚሆን ውስጡን እየባሰው፡ አፍቃሪውን ማጣት ሰርክ እያስለቀሰው፡ እውነተኛ ሆኖ ማነው የሞከረው፡ ፍቅርን በተጨባጭ መንስ ነው የኖረው፡ ጠባሳ አስከትሎ ከሚሰረስረዉ፡ ከመዉደድ በሽታ ማነዉ ሚሽረዉ!! አያልቅም ቢነገር አይቻልም ይቅር፡ ረቂቅ ነው ጫፉ የዛ መጅኑን ፍቅር፡ ♦️.....መጅኑኑ ለይላ....!! የምን ደማከሴ የምን እጣን ቅጠል፡ የምን ማፅናኛ ነው የምን ቃል መቀጠል የምን ሌላ ምኞት የምን ውል ማንጠልጠል፡ አቢድ ያሰመረው ሀኪም የቀመመው፡ በለይላ ተለክፎ ለይላን ለታመመው፡ ሲያስባት ለኖረ ቀንም ሆነ ሌሊት፡ ለቀይስ አይነት መጅኑን ምኑ ነው መዳኒት!! መዳኒቷ እርሷ ነች መዳኒትም የለው! በሷ እንደታመመ በሷ ነው ሚድነው፡፡ .....አይ ፍቅር ..የስራህን ይስጥህ...‼️ የውደታን ሸማ የናፍቆትን ጠረን፡ የማፍቀርን ዋጋ በደማቁ አስምረን፡ የቀይስን ሁኔታ እንየው መርምረን፡ የአፍቃሪነት ሰንደቅ የታሪክ ውብ አርማ፡ የሙሀባ ወጀብ አስደናቂ ፊርማ፡ ፍቅሩን ሳያገኛት በዕብደት ቢለይም፡ ቀይስ ግን ፍቅሩ እንጂ እብደቱ አይታይም፡ ጠሸሸ አይባልም በፍቅር ያበደ፡ ቀይስ ነው አርዓያው ለይላን የወደደ፡ ናፍቆት በደም ስሩ ስር እየሰደደ፡ እንባው በፊቱ ላይ ቦይ እየቀደደ፡ በየጎዳናው ላይ ለይላን ያስታውሳል፡ አፍቃሪ ውብ ፍቅሩን መቼ እንደት ይረሳል፡ ዛፍና ቅጠሉ እሷን ይመስለዋል፡ ጣራ ግድግዳዋን ሔዶ ይስመዋል፡ ይህንን እያዩ ይሉታል ያመዋል፡ እሱ ከፍቅር ውጭ ሌላ ይታየዋል!?   ♦️መጅኑን....ለይላ....‼️ በንፁህ ልቦና ፍቅርን የወደደው፡ ከወዳጁ ርቆ መኖር የከበደው፡ ቀይስ ይባላል ስሙ በለይላ ያበደው፡ ልቡና ምላሱ አያስብም ሌላ፡ አብዶላታልና መኖር እስኪጠላ፡ ይሔ ነው በአጭሩ ያ መጅኑኑ ለይላ፡ ........ሲያሳዝን.....⁉️ ⛔️አፍቃሪ=ቀይስ ኢብኑ ሙለወህ ♦️ማራኪ=ለይላ ቢንት መህዲ«የቀይስ የአጎት ልጅ እንደሆነች ይነገራል።» ስለ መጅኑን ለይላ የማያ'ቅ አለ ብዬ አላስብም።ግና ለፅሁፉ ድባብ መጅኑን ለይላን በመስመሮች ገድበን በወፍ በረር እንቃኘው እስኪ......ተከተሉኝ። አይመችም ኑሮው አይጥምም አየሩ፡ የሚወዱት ሰው ሄደው ካልዘየሩ፡ ተወደጅ በአፀፈው ካልመጣ ለፍቅሩ፡ ምኑ ላይ ነው ደስታው በዱንያ መኖሩ ! ....መጅኑን ለይላ የስነ-ግጥም ሰውና ከልቡ አፍቃሪ ነበር።  ትክክለኛ ስሙ ቀይስ ኢብኑ ሙለወህ ሲሆን "መጅኑን ለይላ"«የለይላ እብድ»ያሉት ለፍቅር ብለው ልባቸውን ከሰጡ ልብ ገባሪዎች አንዱ ስለነበር እና በለይላ ፍቅር አብዝቶ ስለሚመሰጥ ነው። .....ለይላ የሀብታም ልጅ፤መልኳም ልዕልትን የምታስንቅ ውብ እንስት ነበረች። ቀይስ ግን በተቃራኒው ትንሽዬ ጎጆ ቀልሶ የሚኖር ድሃ ነበር። ....ድሀ አፍቃሪ እንጂ በብዛት ፍቅሩን አያገኝም ግን እውነተኛ አፍቃሪ በብዛት ድሀ ነው ልበል....⁉️ ለይላና መጅኑኗ በየጫካው በየ ጋራ ሸንተረሩ ተሯሩጠው፣አፈር አቡክተው፣ጭቃ ጠፍጥፈው፣ውሃ ተራጭተው ያደጉ የፍቅር ተምሳሌቶች ናቸው። ......የሁለቱን ፍቅር ሀገር ያወቀውና ፀሐይ የሞቀው የሚቀናበት ጉዳይ ሆነ።  የለይላ ቤተሰቦች ሀብታም ለሆነ ሰው እሷን መዳር ይፈልጉ ነበርና ከሚስኪኑ ቀይስ ይልቅ ለአንድ ባለፀጋ ይድሯታል። የእነዚህ ጣምራውያን ግንኙነትም አከተመ(ፍቅራቸው ባይቋጭም)!.... ከዕለታት አንድ ቀን የለይላ ውሻ አውላላ ሜዳ ላይ እያለከለከ ሲሄድ ቀይስ ይመለተከዋል። መጅኑንም ለይላ የት እንደደረሰች ለማወቅ ተከተለው።በመሀል ሀርመው ኢማም ተከትለው የሚሰግዱ ሰዎችን ሳያያቸው አቋርጦ ያልፋል። .....ሲመለስ ሰጋጆቹ ይይዙትና "አንተ!ያምሀል እንዴ⁉️ሰላታችንን አቋረጥክ እኮ‼️ብለው በቁጣ ስሜት ተናገሩት። .....በዚህ ጊዜ #አፍቃሪው #ቀይስ ዘመን ተሻጋሪ መልስ መለሰላቸው እንዲህም አለ:- ....እኔ የለይላ ፍቅር ባተሌ ነኝ።"እኔ ለይላን እንደምወዳት አላህን ብትወዱ ኖሮ፤እናንተን እንዳላየኋችሁ እናንተም እኔን አታዩኝም ነበር...በማለት ዘመን ተሻጋሪ ንግግሩን ታሪክ ያወሳለታል።    የዚህ ጀግና አፍቃሪ በፍቅር የተጎዳ ሰው ታሪኩ ብዙ ነውና እንዳስፈላጊነቱ ይቀጥላል...... የኔ ጥያቄ ግን....⁉️ ብዙ የፍቅር ታሪኮችን በወፍ በረር ለመቃኘት ሞክሪያለሁ...የሚገርመኝ አንድ ሚስጥር አለ ...በፍቅር ምክንያት #የሚያብደው፣ #የሚሞተው፣ #የሚታመመው፣ ህይወቱ የሚበላሸው ግን አብዛኛው #ወንድ ብቻ ነው ለምን...⁉️ .....ኑር...✍️ t.me/nuredinal_arebi t.me/nuredinal_arebi

Repost from N/a
➲ የሱና ቴሌግራም ቻናላችሁን እና ግሩፓችሁን ባጭር ግዜ ዉስጥ በነፃ ማሳደግ የሚያስችል ዌቭ በአዲስ መልክ ጀምረናል 🍖በነፃ ነዉ ፈጥነው ያስመዝግቡ 🍒       ➦ ከ #300 በላይ ተከታዮች ከ #500 እና #1000 በላይ ተከታዮች ላላቸው  🍯 የሱና ቻናል ለማስመዝገብ አናግሩኝ  👉 @Quran_mylife1

ለጦሳ ማዶዎቹ አድርሱላቸው፦ 👉 ልብ በሉ የሸይኹን ንግግር መዐየን ከሆነ ተፍሲል(መለየት) ማድረግ ግድ እንደሆነ ይናገራሉ። 👉 አሁን ሰዎች ባጠቃላይ ሁጃ ደርሷቸዋል ካላችሁ ለምን ተውሂድ እና ሽርክን ታስተምራላችሁ??? 👈 ሸይኽ ፈውዛን አላህ ይጠብቃቸውና እንደእናንተ ሽርክ የሰራን ሰው በጅምላ ካፊር አይሉም። ይህ ድምፅ ምስክር ነው የሌላ ሸይኽን ንግግር እያስተማሩ ካላችሁ ኢጅማዕ የምትሉት ሙግት ብቻ ሊሆን ነው ።ነገርግን መጨረሻ ላይ የራሳቸውን አቋም ይናገራሉ لابد من التفصيل እያሉ ይናገራሉ ሁጃ የቆመበትን ሁጃ ካልቆመበት መለየት እንዳለብን ጠንከር አድርገው ይናገራሉ። እውነቱ ይህ ነው አላህ ቀጥተኛውን መንገድ ይምራን በዛው ፀንተን የምንሞት ያድርገን።

#ላሚየቱ_ብኒ_ተይሚያ በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር

خطبة الجمعة  بعنوان (بدعة الحتفال بالمولد النبوي)             في مسجد  الصفا بمدينة هرا                                                                 🕌  ሃራ መስጂደ ሶፋ                                           ربيع الأول 8 لِعَامِ. ١٤٤٨ه‍                                   🎤    በወንድም አቡ ፈውዛን                       https://t.me/abufwzan31

በነብዩ ያገኘነው ክብር ተነግሮ አያልቅም ስማቸው ይበቃልና የፍቅር ጣዕሙ አይለቅም፡ ሙሀመድ....ﷺ ሙሀመድ....ﷺ ሙሀመድ...ﷺ እስኪ ሰለዋት እናውርድባቸው #ሸር አድርጓትማ ...አልናፈቋችሁም..ወይ⁉️ ....🎙የፋሩቅ አባት t.me/nuredinal_arebi t.me/nuredinal_arebi

✅እኔ እኮ የገረመኝ ለተሚያ ለመሆን አማረኛ አለመቻል መስፈርቱ ነው መሰል?!እ አረ ልጀ ፊደል ቁጠሩ መጀመሪያ እንደት አይነት እዳ ነው ሰወች!! እኛ እብን ውናውር የሚባል ኡስታዝ የለንም እንደ!!
✅እኔ እኮ የገረመኝ ለተሚያ ለመሆን  አማረኛ አለመቻል መስፈርቱ ነው መሰል?!እ       አረ ልጀ ፊደል ቁጠሩ መጀመሪያ እንደት አይነት እዳ ነው ሰወች!!    እኛ እብን ውናውር የሚባል ኡስታዝ የለንም             እንደ!!       ግዕዝ ነው እንደ ያ 'ጀመዓ?!❓❗️           ሙመይዓ ማለት :-ቆልጦ የሚያቃልጥ😔😔   አማረኛው የገባው   ካለ ያስረዳኝ  ይሄ አገባባዊ ም፤ አውዳዊ ፍችም የለው ።     https://t.me/Umu_Reyan_channel_No1 https://t.me/Umu_Reyan_channel_No1

ኡስታዝ አቡ ዒምራን አላህ ይጠብቅህ። በርታልኝ የኔ ጀግና።

ኢኽዋን ለተውሒድ ደዕዋ እንቅፋት የሚሆነው ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ ጉዳዩ የሺርክና የቢድዐ ጉዳይ እንደሆነ እያዩ ''በትንንሽ ነገሮች አንጨቃጨቅ" በማለት እውነታውን የሚያስቀይሱበት ምክንያቱ ከዚህ የመነጨ ነው። (ኢብኑ ሙነወር፣ ጥቅምት፡ 28/2012) = https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

ለምንድን ነው የመውሊድ ተቃውሞ ኢኽዋኖችን ምቾት የሚነሳቸው? ~ በርካታ የኢኽዋነል ሙስሊሚን አስተሳሰብ አራማጆች በመውሊድ ቢድዐ ላይ የሚደረገው ዘመቻ ክፉኛ ሲረብሻቸው ይታያሉ፡፡ አብዛኛው የመውሊድ አፈፃፀም ውስጥ ሺርክ እንዳለበት እያወቁ "ለምን በትንንሽ ነገሮች እንጨቃጨቃለን?" ይላሉ። የሺርክ ጉዳይ ለነሱ ከትንንሽ ነገሮች ውስጥ ነው። የተውሒድ ዋጋው ከነሱ ቡድናዊ አላማ በታች ነው። ራሳቸውን መካከለኛ ለማድረግ የመውሊድ ፅንፈኛ ደጋፊዎችን በስሱ ከነኩ በኋላ (እሱም ከስንት አንዴ ከኖረ ነው) ያለ የሌለ ሃይላቸውን መውሊድን በሚነቅፉት ላይ ነው የሚያደርጉት፡፡ መውሊድ ላይ የሚሰነዘረው ተቃውሞ ክፉኛ እንዲረብሻቸው የሚያደርጓቸው ብዙ ምክንያቶች አሉ፡፡ ለምሳሌ ያክል፡- 1. ኢኽዋነል ሙስሊሚን እንደ ቡድን መሰረቱ ሱፊያ ነው፡፡ የቡድኑ መስራች ሐሰን አልበና የሻዚሊያ ጦሪቃ ቅርንጫፍ የሆነው የ“ሐሷፊያ ጦሪቃ” ተከታይ የነበረ ሲሆን ራሱ እንደገለፀው “የሐሷፊያን አስተሳሰብ የጠገብኩ ሆኜ ወደ ደመንሁር ወረድኩ” ይላል፡፡ [ሙዘኪራቱ ዳዕዋ ወዳዒያ፡ 31 - 34] ከቡድኑ አመራሮች አንዱ የሆነው ሰዒድ ሐዋ “የኢኽዋነል ሙስሊሚን ንቅናቄ ራሱ ሱፊ ነው የመሰረተው፡፡ አሉታዊ ጎኖቹን በመተው የተሶውፍን እውነታ ወስዷል” ይላል፡፡ [ጀውለቱን ፊል ፊቅሀይን፡ 154] አንዳንዶች ይሄኛው አቋሙ ከመመለሱ በፊት የነበረበት ነው ቢሉም እውነታው ግን እንደዚያ አይደለም። እስከ ፍፃሜው ተሶውፍ ላይ እንደዘለቀ ታላላቅ የኢኽዋን ቁንጮዎች መስክረዋል፡፡ ስለዚህ ዛሬ የኢኽዋን ፀሐፊዎች በተለያየ ስልት ከሱፍዮች የሚከላከሉት ከራሳቸው፣ ከመሪዎቻቸው እና ከቡድናቸው ለመከላከል ነው፡፡ ሱፍያ ተነካ ማለት ኢኽዋን ተነካ ማለት ነው፡፡ ሙስሊሞች ሱፍያን ተፀየፉ ማለት የኢኽዋን መሰረቱ ተናጋ ማለት ነው፡፡ አንዳንዶች “እነሱ ነፍስን ማጥራት ላይ የሚያተኩረውን፣ ንፁሁን ተሶውፍ ነው የተከተሉት” ይላሉ፡፡ እውነታው እንደዚያ እንዳልሆነና ተሶውፍን ከነሺርኩ ከነ ግሳንግሱ የሚያራምዱ እንደሆኑ በተከታዮቹ ነጥቦች የምናይ ይሆናል። 2. የቡድኑ መስራች ሐሰን አልበና ረቢዑል አወል አንድ ካለ ጀምሮ እስከ 12 ድረስ መውሊድን ያከብር እንደነበር ራሱ ፅፏል፡፡ [ሙዘኪራ፡ 58] ዛሬም ድረስ ለመውሊድ ሽንጣቸውን ገትረው የሚሟገቱ ኢኽዋኖችን የምናየው ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ 3. በርካታ ሱፍዮች ዘንድ ነብዩ ﷺ ከመውሊዱ ጭፈራ ላይ ይገኛሉ ተብሎ ይታመናል፡፡ ነብዩ ﷺ ፈፅሞ ከእንዲህ አይነቱ የባእድ አምልኮ ድግስ ላይ አይገኙም፡፡ ይሄ ቅጥፈታዊ እምነት በኢኽዋነል ሙስሊሚን መስራቹ ሐሰን አልበናም ጭምር ሲስተጋባ የነበረ ነው፡፡ ይሄው እነ ሐሰን አልበና መውሊድ ላይ ሲያንጎራጉሯቸው ከነበሩ ስንኞች ውስጥ እንዲህ የሚል ይገኝበታል፡- هذا الحبيب مع الأحباب قد حضرا … … لا شك أن حبيب القوم قد حضرا “ይህ ወዳጃችን (ነብዩን ነው) ከወዳጆች ጋር ተገኝቷል። … … ያለጥርጥር የሰዎቹ ወዳጅ ተገኝቷል፡፡” [ሐሰን አልበናህ ቢአቅላሚ ተላሚዘቲሂ ወሙዓሲሪሂ፡ 71-72] ይህ እምነት ዛሬም ድረስ ከሱፍዮች ዘንድ በሰፊው ያለ ነው፡፡ በመውሊድ ጭፈራቸው መሃል መብራት አጥፍተው ነብዩ መጡ ይሉና “መርሐባ ነቢ መርሐባ! መርሐባ!” እያሉ ይዘፍናሉ፡፡ በዚህን ጊዜ ታዳሚው እንዳለ ይቆማል፡፡ ክቡሩ ነቢይ ﷺ የነሱን በሺርክ የተጨማለቀ፣ በውዝዋዜ የታጀበ ድግስ ሊታደሙ መሆኑ ነው፡፡ “አይ ይሄ'ኮ ስማቸው ሲወሳ ለአክብሮት ያክል የሚፈፀም እንጂ ቦታው ላይ ይገኛሉ ተብሎ አይደለም” የሚል ሊኖር ይችላል፡፡ ቦታው ላይ ይገኛሉ የሚል እምነት እንዳለማ ይሄው የሐሰን አልበናን ንግግር አጣቀስኩልህ፡፡ በሃገራችንም በሰፊው የሚታወቅ እምነት ስለሆነ መወሻሸት አያስፈልግም፡፡ ደግሞስ በየደዕዋው ላይ፣ በየ መስጂዱ፣ በየ መድረኩ ስማቸው ሲወሳ ትቆማላችሁ እንዴ? ውሸት! በነገራችን ላይ ነብዩ ﷺ በህይወት ሳሉ ማንም እንዲቆምላቸው አይወዱም ነበር፡፡ አነስ ብኑ ማሊክ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ፡- “እነሱ (ሶሐቦች) ዘንድ ዱንያ ውስጥ እንደ ነብዩ ﷺ ሊያዩት የሚወዱት ሰው አልነበራቸውም፡፡ ሆኖም ግን መጥላታቸውን ስለሚያውቁ ለሳቸው አይቆሙም ነበር፡፡” [አሶሒሐህ፡ 358] ሌላ በነገራችን ላይ! ይህንን ነብዩ መጡ እያሉ መነሳትን - የሚሰማ ጠፋ እንጂ - ከመውሊድ አክባሪዎች ውስጥ ሳይቀር የኮነኑት ነበሩ፡፡ ሀይተሚ እንዲህ ይላል፡-“የዚህ አምሳያው ብዙዎች የነብዩ ﷺ ልደትና እናታቸው እሳቸውን መውለዷ ሲወሳ የሚያደርጉት መቆም ሲሆን ይህም ምንም አይነት መረጃ ያልመጣበት ቢድዐ ነው፡፡ ሰዎች ይህን የሚያደርጉት እሳቸውን ﷺ ለማላቅ ነው፡፡ መሃይማኑ ከአዋቂዎቹ በተለየ በዚህ ድርጊታቸው ይታለፋሉ (መዕዙሮች ናቸው፡፡)” [አልፈታዋ አልሐዲሢያህ፡ 58] 4. መውሊድን ያክል እጅግ በርካታ ቢድዐዎችን አቅፎ የያዘን ቢድዐ አቅልሎ ማቅረብ ቡድናዊ ስሜት እየጋረዳቸው እንጂ ላስተዋለ ሁሉ በቀላሉ የሚታይ ነው፡፡ በስፍራዎቹ የሚፈፀሙትን አላስፈላጊ የወንድና የሴት ቅልቅል፣ በመስጂድ ውስጥ መጨፈር፣ መስጂዶችን በጫትና በተረፈ ምግብ ማቆሸሽ፣ አንዳንድ ቦታ ዝሙት፣ … ይቅርና ብዙ ከባባድ ሺርክ ይፈፀማል፡፡ ግና በርካታ ኢኽዋኖችን የሺርክ ጉዳይ ሲያስጨንቃቸው አይታይም፡፡ እንጂማ በነቢዩ ﷺ እና በ“ወልዮች” ላይ ብዙ ድንበር ይታለፋል፡፡ በመውሊድ ቦታዎች ላይ ብዙ አይነት ሺርክ ይፈፀማል፡፡ ለቀብር ሱጁድ ይወረዳል፡፡ ጦዋፍ ይደረጋል፡፡ ለበረካ እየተባለ የቀብር አፈር እየተበጠበጠ ይጠጣል፡፡ ከዘመናት በፊት ያለፉ ሙታኖችን ሰዎች ይማፀናሉ፡፡ ስለት ይፈፅማሉ፡፡ ያርዳሉ፡፡ በሺርክ የተሞሉ መንዙማዎች ይቀነቀናሉ፡፡ ይህን ሁሉ ጥፋት አጭቆ የያዘን ቢድዐ የሚያወግዙ ሰዎችን ነው እንደ ጠርዘኛ የሚስሉት፡፡ መውሊድ በመጣ ቁጥር ሰዎችን ከዚህ ጥፋት ስላስጠነቀቁ ነው ጨቅጫቃ የሚያደርጉት፡፡ “ረቢዕን የመጨቃጨቂያ ወር አደረጉት” ይላሉ፡፡ የጥፋቱን ጠንሳሾችና አራጋቢዎች እንዳላዩ እያለፉ ከሺርክና ቢድዐ የሚያስጠነቅቁ ሰዎችን ማብጠልጠል መንስኤው ምን እንደሆነ አይጠፋንም፡፡ እውነት ለህዝብ ብትቆረቆሩ ኖሮ ወገናችንን ከዚህ በሺርክ ከተወረረ በዓል ለማዳን ድርሻ በነበራችሁ ነበር፡፡ “ወላኪን ላ ሐያተ ሊመን ቱናዲ!” “ይህን ሁሉ ጉድ እያወቁ እንዴት ለመውሊድ ይሟገታሉ?” የሚሉ የዋሆች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ጉዳዩ ከራስ የመከላከል ጉዳይ ነው። የኢኽዋን ቡድን መስራች ሐሰን አልበናና ጭፍሮቹ መውሊድ ላይ ሲያቀነቅኑት ከነበሩ ዜማዎች ውስጥ እነዚህ ነበሩ፡- هذا الحبيب مع الأحباب قد حضرا …وسامح الكل فيما قد مضى وجرى “ይህ ወዳጃችን ከወዳጆች ጋር ተገኝቷል፡፡ #ያለፈ_የሆነውን_ሁሉ_ይቅር_ብሏል፡፡” [ሐሰን አልበናህ ቢአቅላሚ ተላሚዘቲሂ ወሙዓሲሪሂ፡ 71-72] ይሄ ከኢስላም የሚያስወጣ ትልቁ ሺርክ አይደለምን? ከአላህ ውጭ ወንጀልን የሚምር አለ ወይ?! አላህ ምን እንዳለ አስተውሉ፡- وَمَنْ يَغْفِرُ الذُّنُوبَ إلاَّ اللهُ “ከአላህ በስተቀር ወንጀሎችን የሚምረው ማነው?” [ኣሊ ዒምራን፡ 135] ነብዩም ﷺ "አላህ ሆይ! ... ካንተ በስተቀር ወንጀሎችን የሚምር የለም" ይላሉ። [አልቡኻሪይ፡ 8585] [ሙስሊም፡ 2705]