ar
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

الذهاب إلى القناة على Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
4 321
المشتركون
+824 ساعات
-47 أيام
-7130 أيام
أرشيف المشاركات
🇸🇦 🇦🇪 🇰🇼 🇧🇭 🇶🇦⚡️🇮🇷 ሳዑዲ አረቢያ በኢራን ጦርነት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የመጀመሪያውን የባሕረ- ሰላጤ አገራትን መሪዎች ስብሰባ፣ ዛሬ ልታስተናግድ ነው -- ሮይተርስ።
+1
🇸🇦 🇦🇪 🇰🇼 🇧🇭 🇶🇦⚡️🇮🇷 ሳዑዲ አረቢያ በኢራን ጦርነት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የመጀመሪያውን የባሕረ- ሰላጤ አገራትን መሪዎች ስብሰባ፣ ዛሬ ልታስተናግድ ነው -- ሮይተርስ። የማክሰኞው ስብሰባ፣ የባሕረ- ሰላጤው ግዛቶች በሺዎች በሚቆጠሩ የኢራን ሚሳኤሎች እና ድሮኖች በኋይል እና በሲቪል መሠረተ ልማቶች ላይ ለደረሰው ጉዳት ምላሽ እንዲሰጥ ያለመ እና በዘላቂነት ቀጠናው ምን ለማድረግ አስቧል በሚለው ዙሪያ የሚያጠነጥን ነው ተብሏል።

🇺🇦 ⚡️🇷🇺 ከቅርብ ጊዜ ወዲህ፣ ሩሲያ ለዩክሬን ድንበር ዘለል ጥቃቶች ከምንጊዜውም በላይ ተጋላጭ ሆናለች። ከዩክሬን በረጅም ርቀት፣ ውስጥ ሩሲያ ግዛት  የሚገኙ የየብስም የባሕርም የነዳጅ ማውጫዎች እና ማጣሪያዎች፣ የመሳሪያ ፋብሪካዎች፣ የወታደራዊ እና የኢኮኖሚያዊ መሠረተ- ልማቶች ቀን በቀን የዩክሬን ኢላማዎች ከሆኑ ሰነባበቱ። የሩሲያ ጦር በመሬት ቢገፋም፣ የዩክሬን ጦር ኋላውን ማጥቃቱን ቀጥሏል። ሩሲያ ነዳጅ ወደ ውጭ መላክ እስኪያቅታት በዩክሬን እየተመታች ሲሆን፣ ለዚህ በከፍተኛ ደረጃ እያደገ ለመጣው የዩክሬናዊያን ጥቃት ሩሲያ እንግሊዝን ተጠያቂ በማድረግ ላይ ናት። ቢሆንም፣ የዩክሬንን ጥቃት በማርገብ ላይ እስካሁን ያመጣው ምንም ለውጥ የለም። በዚህ የተነሳ ሩሲያ ጦርነቱ ከገፋ ልትሸንፍ ትችላለች የሚለው አስተሳሰብ በአውሮፓዊያን ዘንድ አይሏል። ለዩክሬን ያላቸውን ድጋፍም አጠናክረው በመቀጠል ላይ ናቸው።

- 🇮🇱 / 🇵🇸 Tamir Pardo፣ የቀድሞው የሞሳድ ዋና ኃላፊ (2011-2016) በዌስት ባንክ ጉብኝት ወቅት ስለ ፍልስጤሞች -
"እናቴ ከሆሎኮስት የተረፈች ነች፣ እና እዚህ ያየሁት ነገር ባለፈው ምዕተ-ዓመት በአይሁዶች ላይ የደረሰውን ስደት ያስታውሰኛል።"

🇺🇸 🇮🇷 የሁለተኛው ዙር ድርድር ቢፈርስም፣ አሜሪካ እና ኢራን ከሚታየው በላይ ወደ ስምምነት እየቀረቡ መሆኑን CNN ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል። "የተጠናከረ ዲፕሎማሲ ከመጋረጃው በስተጀርባ የቀጠለ ሲሆን፣ ሁለቱም ወገኖች ደረጃ በደረጃ በሚተገበር ስምምነት ላይ እየተወያዩ ነው። የመጀመሪያው ምዕራፍ፣ ጦርነቱን ያለ ቅድመ ሁኔታ ማቆምን እና ከጦርነቱ በፊት ወደ ነበረው ሁኔታ መመለስ፣ እንዲሁም የሆርሙዝ ወሽመጥን ያለገደብ መክፈትን ያካትታል። የኢራን የኑውክሌር ጉዳይ በኋላ ላይ የሚኬድበት ጉዳይ ነው ተብሏል። አስታራቂዎቹ ሁለቱም ወገኖች ላይ ጫና እያደረጉ ሲሆን፣ መጪዎቹ ቀናት ወሳኝ እንደሚሆኑ ይጠበቃል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ Wall Street Journal እንደዘገበው፣ ትራምፕ በኢራን የድርድር ሓሳብ ላይ ጥርጣሬ እንዳላቸው እና ዋሽንግተን በሚቀጥሉት ቀናት የራሷን አጸፋዊ ሓሳብ እንደምታቀርብ ተናግሯል።

🇮🇷 የኢራን ምክትል ፕሬዝዳንት መሀመድ ረዛ አረፍ - "ቀደም ሲል ይሰድቡን እና ያዋርዱን እና የጀት ነዳጅ ወደ እኛ ለመላክ ፈቃደኛ ያልነበሩ ሀገራት፣ አሁን መርከቦቻቸውን በሆርሙዝ ባሕር እንድናሳልፍላቸው እየለመኑን ነው።"

🇩🇪 🇮🇷 🇺🇸 የጀርመኑ ቻንስለር ፍሬድሪክ መርዝ፣ "ኢራን አሜሪካን እያዋረደች ነው" አለ -- ሮይተርስ "ኢራናውያን በመደራደር ረገድ በጣም የተካኑ ናቸው፣ ወይም ይልቁንም ላለመደራደር በጣ
+2
🇩🇪 🇮🇷 🇺🇸 የጀርመኑ ቻንስለር ፍሬድሪክ መርዝ፣ "ኢራን አሜሪካን እያዋረደች ነው" አለ -- ሮይተርስ
"ኢራናውያን በመደራደር ረገድ በጣም የተካኑ ናቸው፣ ወይም ይልቁንም ላለመደራደር በጣም የተካኑ ናቸው፣ አሜሪካውያን ወደ ኢስላማባድ እንዲጓዙ እና ከዚያም ምንም ውጤት ሳይኖራቸው እንደገና እንዲመለሱ አድርገዋቸዋል። በጦርነቱም አሜሪካ ምንም ስትራቴጂ ሳይኖራት ስለገባች፣ ኢራን የበላይ ስትሆን እንድናይ ሆኗል"
ሲል በማርስበርግ ከተማ ለተማሪዎች ባደረገው ንግግር ተናግሯል።
"አንድ ሙሉ ሀገር በኢራን አመራር፣ በተለይም በእነዚህ አብዮታዊ ጠባቂዎች እየተባለ በሚጠራው፣ ተዋርዷል። እናም ይህ በተቻለ ፍጥነት እንደሚያበቃ ተስፋ አደርጋለሁ"

🇲🇱 ❗️❗️ በዚህ ሰዓት በ Bamako ማሊ ውስጥ በመንግሥት ኃይሎች እና በሩሲያ ጦር ላይ በአማፂያኑ ሙሉ ጥቃት እየተካሄደ ነው። በመኪና የተጠመዱ ቦንቦች ፈንድተዋል፣ ዋናውን አየር ማረፊያ ለመያዝ 'በሳህል የዓልቃኢዳ ክንፍ' አማፂያን ትንቅንቅ ላይ ናቸው።

🇲🇱⚡- ሰበር : ተከታታይ ፍንዳታ በማሊ ዋና ከተማ Bamako፣ በ Senou ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ፣ እየተሰማ ይገኛል። ውጊያው ዋና ከተማው አየር ማረፊያውን ለመያዝ እየተደረገ እንዳለ የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ምሽቱን የሩሲያ ወታደሮች በፈረንሳይ የሚደገፈውን የዓልቃኢዳ አማፂ ቡድን አየር ማረፊያው ዙሪያ በሄሊኮፕተር ጭምር እየተዋጉ ሲሆን፣ ሁኔታው በሰዓታት ሊለዋወጥ እንደሚችል መረጃዎች ያሳያሉ።

🇺🇸 "የዋይት ሃውስ የፕሬስ ሴክሬታሪ እየተባለ የሚጠራው፣ አሜሪካን ሊያስተምር እና ስለ ጨዋነት ሊነግር ይፈልጋል?' - Hakim Jeffries የዲሞክራቲክ ፓርቲ መሪ "ጥፊ ከዚህ! ስለምንጠቀምበት ቋንቋ ልትነግሩን ከመሞከራችሁ በፊት፣ የራሳችሁን ቤት አጽዱ!"

🇺🇸 ዋይት ሃውስ "ውሸቶች እና ሽሙጦች ሁከትን እየነዱ ነው።"​ "በፕሬዚዳንቱ፣ በቤተሰቦቻቸው እና በደጋፊዎቻቸው ላይ የተዘበራረቀ ውሸት እና ስድብ እብድ ሰዎች እብድ ነገሮችን እንዲያምኑ አድርጓቸዋል። በእነዚህ ቃላት የተነሳ፣ ሁከት እንዲፈጽሙ ተነሳስተዋል። መቆም አለበት!" -

🇮🇷 የኢራን የፓርላማ አባል ማኑቸህር ሞታኪ፡ "ኢራን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ እንኳን አያስፈልጋትም፣ ምክንያቱም እያንዳንዱ ኢራን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ነው። እኔ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ነኝ፣ አንተ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ነህ፣ ሁላችንም የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ነን - ልንሸነፍ አንችልም። የኢራን ሕዝብ ከሌላው የተለየ አገር እና ሕዝብ ነው፤ ለውጭ ኃይሎች ትእዛዝ ፈጽሞ አይገዛም!" ብለዋል። 

🇱🇧 🇮🇱 የሂዝቦላ ሚዲያ ክንፍ፣ ተሰብስበው በቆሙ "ወራሪዎች" ባላቸው የእስራኤል ወታደሮች ላይ በድሮን እርምጃ ወሰድኩኝ በማለት፣ ጥቃቱን የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ለቋል።

🇮🇷 ለ 67ኛ ቀን በተከታታይ፣ በኢራን የምሽት የመንግሥት ድጋፍ ሰልፎች እንደቀጠሉ ናቸው። ዛሬም ምሽቱን በቴህሬን ሰልፎች ተካሄደዋል።

⚡️🇲🇱 ጋኦ፣ ማሊ፣ አብዛኛው የከተማው ክፍል በፈረንሳይ በሚደገፈው በአልቃዒዳ እጅ ወድቋል። የሩስያ ወታደሮች፣ በሌሎች ከተሞች እንዳደረጉት፣ በጋኦ ወደ ኋላ ላለማፈግፈግ ወስነዋል። ከማሊ አጋሮቻቸው ጋር በከተማው ወሰን ውስጥ በሚገኝ የጦር ሰፈራቸው ውስጥ ታግደው እንደተቀመጡ ናቸው። ማሊያውያንን እና ሩሲያውያንን ከቦታቸው ለማስወጣት መሞከር፣ ለአልቃዒዳ ብዙ ዋጋ ስለሚያስከፍለው፣ ከብበው ብቻ በዚያው ትተዋቸው እንዳሉ ነው። የቀናት ጉዳይ እንጂ፣ የሩሲያ ወታደሮች እጃቸውን መስጠታቸው እና ከተማውን ለአልቃዒዳ ማስረከባቸው አይቀርም።

⚡️🇷🇺🇮🇷 የሩሲያው ፕሬዝዳንት ፑቲን ለኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ እንደተናገሩት፣ ኢራን በአዲሱ ጠቅላይ መሪ መሪነት አሁን ያጋጠማትን ተግዳሮቶች ታሸንፋለች ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።
"የኢራን ሕዝብ ነፃነቱን እና ሉዓላዊነቱን በጀግንነት ሲጠብቅ እያየን ነው"ብለዋል
ፑቲን።

🇲🇱 የማሊ ወቅታዊ ሁኔታ ይህን ይመስላል። በፈረንሳይ እና በእንግሊዝ የሚደገፉት "የሳህል አልቃዒዳ ክንፍ" አማፂያን እየገሰገሱ ሲሆን፣ ምሽቱን ተጨማሪ ግዛቶችን ይዘው አድረዋል። በሌላ በኩል በሩ
🇲🇱 የማሊ ወቅታዊ ሁኔታ ይህን ይመስላል። በፈረንሳይ እና በእንግሊዝ የሚደገፉት "የሳህል አልቃዒዳ ክንፍ" አማፂያን እየገሰገሱ ሲሆን፣ ምሽቱን ተጨማሪ ግዛቶችን ይዘው አድረዋል። በሌላ በኩል በሩሲያ የሚደገፉት የመንግሥት ኃይሎች በዋና ከተማዋ ዙሪያ እየተፋለሙ ነው። የሩሲያ ኃይሎች አማፂያንን ከዋናው ከተማው Bamako ማስወጣት መቻላቸውን ቢገልፁም፣ እየወጡ እንዳሉ መረጃዎች ግን፣ በመሬት የሚታየው ምስል አሳሳቢ ደረጃ እንደደረሰ ነው።

🇱🇧⚡️🇮🇱 የእስራኤል ጦር፣ በደቡብ ሊባኖስ የመኖሪያ መንደሮችን ሲደበድብ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ለቋል። የተኩስ አቁም ስምምነት አለ ቢባልም፣ ጦሩ ሊባኖስን ማጥቃቱን ቀጥሎበታ። በትናንትናው ዕለት የሊባኖስ መንግሥት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና በተለይ ለአሜሪካ 'አቤት' ቢልም፣ የእስራኤልን ጥሰት በማስቆም ላይ የተወሰደ ጭብጥ እርምጃ እስካሁን የለም። በሌላ በኩል ሂዝቦላ፣ 'አፀያፋዊ እርምጃ' ያለውን በመውሰድ ላይ ይገኛል።

🇮🇷 ውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ተሳፍሮበት የመጣው አይሮፕላን፣ በአሜሪካ ቦንብ የተገደሉትን 168 የሚናብ ትምህርት ቤት ሴት ሕፃናት ተማሪዎችን ለማስታወስ፣ Minab 168 ተብሎ በተሰየመ በረራ ነው፣
🇮🇷 ውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ተሳፍሮበት የመጣው አይሮፕላን፣ በአሜሪካ ቦንብ የተገደሉትን 168 የሚናብ ትምህርት ቤት ሴት ሕፃናት ተማሪዎችን ለማስታወስ፣ Minab 168 ተብሎ በተሰየመ በረራ ነው፣

🇮🇷 🇷🇺 የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ አባስ አርጋቺ፣ በአሁኑ ሰዓት St. Petersburg አየር ማረፊያ አቀባበል እየተደረገለት ይገኛል። በመጪዎቹ ጥቂት ሰዓታት፣ ከፑቲን ጋር እንደሚወያዩ ተነግሯል።

🇸🇾🕊🇺🇸❌🏴❗️ - ሶሪያ በዋሽንግተን የእራት ዝግጅት ላይ የደረሰውን ጥቃት አጥብቃ አውግዛለች፣ ሁሉንም ዓይነት ጥቃቶች አጥብቃ ውድቅ እንደምታደርግ ገልጻለች። ▶️ ደማስቆ ከዩናይትድ ስቴት
🇸🇾🕊🇺🇸❌🏴❗️ - ሶሪያ በዋሽንግተን የእራት ዝግጅት ላይ የደረሰውን ጥቃት አጥብቃ አውግዛለች፣ ሁሉንም ዓይነት ጥቃቶች አጥብቃ ውድቅ እንደምታደርግ ገልጻለች። ▶️ ደማስቆ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ያላትን አጋርነት አረጋግጣለች፣ ሽብርተኝነትንም የመቋቋም እና ሲቪሎችን የመጠበቅ አስፈላጊነት ላይ አፅንዖት ሰጥታለች።