ar
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

الذهاب إلى القناة على Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
4 321
المشتركون
+824 ساعات
-47 أيام
-7130 أيام
أرشيف المشاركات
🇱🇧⚡️🇮🇱 የእስራኤል ጦር፣ በደቡብ ሊባኖስ የመኖሪያ መንደሮችን ሲደበድብ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ለቋል። የተኩስ አቁም ስምምነት አለ ቢባልም፣ ጦሩ ሊባኖስን ማጥቃቱን ቀጥሎበታ። በትናንትናው ዕለት የሊባኖስ መንግሥት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና በተለይ ለአሜሪካ 'አቤት' ቢልም፣ የእስራኤልን ጥሰት በማስቆም ላይ የተወሰደ ጭብጥ እርምጃ እስካሁን የለም። በሌላ በኩል ሂዝቦላ፣ 'አፀያፋዊ እርምጃ' ያለውን በመውሰድ ላይ ይገኛል።

🇮🇷 ውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ተሳፍሮበት የመጣው አይሮፕላን፣ በአሜሪካ ቦንብ የተገደሉትን 168 የሚናብ ትምህርት ቤት ሴት ሕፃናት ተማሪዎችን ለማስታወስ፣ Minab 168 ተብሎ በተሰየመ በረራ ነው፣
🇮🇷 ውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ተሳፍሮበት የመጣው አይሮፕላን፣ በአሜሪካ ቦንብ የተገደሉትን 168 የሚናብ ትምህርት ቤት ሴት ሕፃናት ተማሪዎችን ለማስታወስ፣ Minab 168 ተብሎ በተሰየመ በረራ ነው፣

🇮🇷 🇷🇺 የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ አባስ አርጋቺ፣ በአሁኑ ሰዓት St. Petersburg አየር ማረፊያ አቀባበል እየተደረገለት ይገኛል። በመጪዎቹ ጥቂት ሰዓታት፣ ከፑቲን ጋር እንደሚወያዩ ተነግሯል።

🇸🇾🕊🇺🇸❌🏴❗️ - ሶሪያ በዋሽንግተን የእራት ዝግጅት ላይ የደረሰውን ጥቃት አጥብቃ አውግዛለች፣ ሁሉንም ዓይነት ጥቃቶች አጥብቃ ውድቅ እንደምታደርግ ገልጻለች። ▶️ ደማስቆ ከዩናይትድ ስቴት
🇸🇾🕊🇺🇸❌🏴❗️ - ሶሪያ በዋሽንግተን የእራት ዝግጅት ላይ የደረሰውን ጥቃት አጥብቃ አውግዛለች፣ ሁሉንም ዓይነት ጥቃቶች አጥብቃ ውድቅ እንደምታደርግ ገልጻለች። ▶️ ደማስቆ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ያላትን አጋርነት አረጋግጣለች፣ ሽብርተኝነትንም የመቋቋም እና ሲቪሎችን የመጠበቅ አስፈላጊነት ላይ አፅንዖት ሰጥታለች።

- 🇺🇸 / 🇮🇷 ትኩስ፡ ኢራን ጦርነቱን በቋሚነት ለማቆም እና የሆርሙዝ ወሽመጥንለመክፈት ያለመ አዲስ ፕሮፖዛል ለአሜሪካ አቅርባለች። የኒውክሌር ጉዳዩ በጭራሽ አልተጠቀሰም - Axios 

—❗️🇺🇸/ 🇮🇷 ትኩስ፡ ፕሬዝዳንት ትራምፕ፣ ነገ ሰኞ ከከፍተኛ የፀጥታ ባለስልጣናት እና ጄኔራሎች ጋር፣ ከኢራን ጋር ስለከሸፈው ድርድር እና ጦርነቱን ለመቀጠል ሊወሰዱ ስለሚችሉት እርምጃዎች፣ ከፍተኛ ስብሰባ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል - Axios

🇮🇱 ሰበር: የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ፣ በእስራኤል በተከሰሰበት የሙስና ወንጀል ምህረት አይቸረውም። Breaking: Benjamin Netanyahu will not be given a pardon in his corruption case in Israel.

ማሊ ወደ ቀደመው፣ 2013 እንደ ፈረንጆች፣ ሁኔታ ተመልሳለች። ለሁለት ተከፍላለች። ሰሜኑን በፈረንሳይ የሚደገፉት የሳህል አልቃዒዳዎች፣ ደቡቡን የመንግሥት ኃይሎች ይዘዋል።

+2
🇲🇱  የማሊ የሽግግር መንግሥት በቃል አቀባዩ በኩል፣ በትናንትናው ዕለት ስለተገደሉት የመከላከያ ሚንስትሩ፣ ጄኔራል ሳዲዮ ካማራ ሞት ያረጋገጠ መሆኑን በመግለጫው አስታውቋል። ጄኔራል ሳዲዮ በፈረንሳይ የሚደገፈው እና "በሳህል የአልቃዒዳ ክንፍ" የሆነው፣ ጀመዓት ኑሥራ አል ኢስላም ወል ሙስሊሚን (JNIM) በተባለው አማፂ ቡድን በትናንትናው ዕለት በተፈፀመ የአጥፍቶ መጥፋት ጥቃት መገደላቸው ነው የተሰማው።  

🇮🇷 IRGC ጎረቤት አገራትን አስጠንቅቋል! "በኢራን ላይ ለሚሰነዘር ጥቃት ተባባሪ ከሆናችሁ፣ ነዳጅ አምራችነታችሁን ቻው በሉት።"
🇮🇷 IRGC ጎረቤት አገራትን አስጠንቅቋል! "በኢራን ላይ ለሚሰነዘር ጥቃት ተባባሪ ከሆናችሁ፣ ነዳጅ አምራችነታችሁን ቻው በሉት።"

🇱🇧 🇮🇱 አስደንጋጭ የሂዝቦላህ FPV ድሮን ተንቀሳቃሽ ምስል፣ ቁስለኛ ወታደርን የሚያነሱ የእስራኤል የጦር አባላትን ሲያጠቃ ያሳያል። ባለፉት ጥቂት ቀናት 168 የእስራኤል ወታደሮች በሂዝቦላህ ጥቃት እንደቆሰሉ የእስራኤል ጦር ሬዲዮ ተናግሯል

🇮🇷 🇺🇸 STEW PETERS፡ "የኢራን LEGO ቪዲዮዎች በአሜሪካ ፕሬዝዳንት ላይ ከተካሄዱት እጅግ በጣም ውጤታማ የሥነ-ልቦና ጦርነቶች፣ በታሪክ፣ ከፍተኛው መሆን አለባቸው።"

🇲🇱🇷🇺 በማሊ የሩሲያ ወታደሮች፣ በፈረንሳይ የሚደገፉትን 'በሳህል የአልቃዒዳ ክንፍ' አማፂያንን ሲዋጉ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ለቅቀዋል።

🇮🇷🇷🇺 — Kremlin: የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን፣ በነገው ዕለት፣ የኢራኑን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አባስ አራጋቺን በሞስኮ ተቀብለው ያነጋግራሉ።

🇲🇱⚡በማሊ ሁለተኛ ትልቅ ከተማ፣ Kidal፣ ሠፍረው የነበሩ የሩሲያ ወታደሮች፣ በፈረንሳይ ለሚደገፉት በሳህል የአልቃዒዳ አማፂያን እጃቸውን ከሰጡ በኋላ በበርካታ ወታደራዊ መኪኖች ተጭነው ከተማውን ለቅቀው ወጥተዋል። በማሊ እየሆነ ያለው እየወጡ እንዳሉት መረጃዎች ከሆነ፣ ለሩሲያ እያመጣ ያለው ፖለቲካዊ እና ገፅታዊ ኪሳራ ከባድ ይሆናል።

🇲🇱⚡- ሰበር: Assimi Goita, የማሊ መሪ ከዋናው ከተማ Bamako አቅራቢያ ከምትገኘው Kati ከተማ, በተደጋጋሚ ጥቃት ምክኒያት ወዳልታወቀ ሥፍራ ጥሎ መሸሹ ታወቀ። Radio France
🇲🇱⚡- ሰበር: Assimi Goita, የማሊ መሪ ከዋናው ከተማ Bamako አቅራቢያ ከምትገኘው Kati ከተማ, በተደጋጋሚ ጥቃት ምክኒያት ወዳልታወቀ ሥፍራ ጥሎ መሸሹ ታወቀ። Radio France International reports ሩሲያ፣ የአልቃዒዳ ክንፍ የሆነውን የሳህል አማፂ ቡድንን፣ የዩክሬን እና የፈረንሳይ ወታደሮች በውጊያ እየረዱ ናቸው ስትል ከሳለች። በሌላ በኩል፣ ሩሲያ፣ ከማሊ መንግሥት ጎን በመቆም አማፂያኑን በመዋጋት ላይ ናት።

🇺🇸❌🇮🇷🇨🇳 - FOX NEWS ቻይና ኢራንን እየረዳች እንደሆነ የአሜሪካውን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን ጠይቋል
ቻይና አሁን ኢራንን እየረዳች ነው ብለው ያስባሉ?
ዶናልድ ትራምፕ፡ 
እየረዱ ሊሆን ይችላል ብዬ አስባለሁ፣ ግን ብዙ አያሳስበኝም። የበለጠ ሊረዱ ይችላሉ። በድጋሜ፣ ምንም አይመስለኝም ቢረዱም። እኛ ሌሎች ሀገሮችን እንረዳለን። ዩክሬንን ረድተናል፣ ያን ያህል መርዳት ባይኖርብንም። መርዳት አልነበረብንም።

🇦🇪 የኤሜሬት F-16 ተዋጊ ጀቶች የሶሪያን ፕሬዝዳንት ለጉብኝት በመጣ ጊዜ አይሮፕላኑን አጅበውት ታይተዋል። ፎቶዎቹን በአትኩሮት ለተመለከተ፣ አንድ ነገር ያስተውላል። የጀቶቹን ምንነት የሚለይ ም
+2
🇦🇪  የኤሜሬት F-16 ተዋጊ ጀቶች የሶሪያን ፕሬዝዳንት ለጉብኝት በመጣ ጊዜ አይሮፕላኑን አጅበውት ታይተዋል። ፎቶዎቹን በአትኩሮት ለተመለከተ፣ አንድ ነገር ያስተውላል። የጀቶቹን ምንነት የሚለይ ምንም ዓይነት ምልክት አይታይባቸውም። seriel ቁጥራቸው፣ ሎጎው እና ባንዲራው በቅብ ተሸፍኗል። ይህ የሆነበት ምክኒያት በኢራን ዳግም ለሚደረገው ወታደራዊ ዘመቻ፣ አይሮፕላኖች የኤሜሬት መሆናቸው እንዳይታወቁ ሊሆን ይችላል፣ የሚሉ ምልከታዎች አሉ። * ባንዲራና ሎጎ የሚታይበት አንደኛው ምስል የበፊት ነው።

🇲🇱 🇫🇷 🇷🇺 የማሊ መከላከያ ሚንስትር Sadio Kamara፣ በትናንቱ የአማጺያን ጥቃት መገደሉ ተሰማ። ከሳህል በረሃ የተነሱት የማሊ አማጺያን፣ በቀጠናው የአልቃዒዳ ክንፍ ሲሆኑ በትናንትናው ዕለት በርካታ ትልልቅ የማሊ ከተሞችን ከተቆጣጠሩ በኋላ ዋናው ከተማ Bamako መድረስ ችለዋል። የማሊ መንግሥትን የሚረዳው የሩሲያ Africa Corps የተባለው ኃይል፣ በዋና ከተማው የአማጺያኑን ጥቃት በአየር ጭምር መመከት የቻለ ቢሆንም፣ እየወጡ እንዳሉ መረጃዎች፣ እነዚሁ የሩሲያ ኃይሎች አብዛኞቹን ከተሞች ለቅቀው ሲወጡና ገሚሱ ሲማረኩ የሚያሳዩ ተንቀሳቃሽ ምስሎች በማህበራዊ ሚዲያ ሲሰራጩ ታይተዋል። አማጺያኑ የአልቃኢዳ በቀጠናው ቅርንጫፍ ይሁኑ እንጂ፣ በፈረንሳይና በእንግሊዝ እንደሚደገፉ የማሊ መንግሥት ተናግሯል። ይህንም፣ አማጺያኑም ሆኑ የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አልደበቁም። ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ፈረንሳይ በአካባቢው የነበራት ተጽእኖ፣ በተለይ በማሊ፣ በተደረጉ ተከታታይ መፈንቅለ-መንግሥቶች ምክኒያት የጠፋ ሲሆን አዲሱ አገዛዞች በይፋ ፈረንሳይን ከሀገራቸው አስወጥተው ከሀገሪቱ ጋር የነበራቸውን ማንኛውንም ግንኙነት አቋርጠው ነበር። በምትኩም፣ ከሩሲያ ጋር ቁርኝት ፈጥረዋል። ይሄ፣ ምዕራባዊያንን አስቆጥቶ የነበር ሲሆን፣ አሁን በበቀል በሳህል አልቃኢዳ በኩል እርምጃ እየወሰዱ ይመስላል ተብሏል። በአሁኑ ሰዓት የማሊ መንግሥት ዋና ከተማውን ላለማስነጠቅ እና በሥልጣኑ ለመቆየት ከፍተኛ የሞት ሽረት ትግል ላይ ነው።

🇮🇱 🤝 🇦🇪 Axios: እስራኤል Iron Dome የተሰኘውን የአየር መከላከያ ሥርዓቷን እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ወታደሮቿን፣ በድብቅ ወደ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ አሰማርታለች። ከኢራን ጋር
🇮🇱 🤝 🇦🇪 Axios: እስራኤል Iron Dome የተሰኘውን የአየር መከላከያ ሥርዓቷን እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ወታደሮቿን፣ በድብቅ ወደ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ አሰማርታለች። ከኢራን ጋር በተደረገው ጦርነት እስራኤል በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የአየር መከላከያ ሥርዓቷን ከሀገሪቱ ውጭ አሰማርታለች። Iron Dome ከእስራኤል ኦፕሬተሮች ጋር በመሆን በቀጠናው በኢራን ጥቃት ከፍተኛ ጉዳት ወደ ደረሰበት የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ተልኳል።