የቀጠናው ተመልካች
الذهاب إلى القناة على Telegram
በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።
إظهار المزيدلم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
4 294
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-137 أيام
-8030 أيام
أرشيف المشاركات
4 295
🇨🇳🇺🇸⚡️- "ለሁለቱም ህዝቦቻችን ደህንነት እና ለሰው ልጅ የወደፊት ተስፋ ሲባል፣ ለሁለትዮሽ ግንኙነታችን ብሩህ የወደፊት ተስፋን በጋራ መገንባት እንችላለን?
እነዚህ ለታሪክ፣ ለዓለም እና ለሰዎች ወሳኝ ጥያቄዎች ናቸው" - የቻይና ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ።
4 295
🇨🇳⚡️- "መላው ዓለም ስብሰባችንን እየተከታተለ ነው።
በአሁኑ ጊዜ በአንድ ምዕተ ዓመት ውስጥ ያልታየ ለውጥ በዓለም ዙሪያ እየተፋጠነ ነው፣ እና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታው ተለዋዋጭ እና አስጨናቂ ነው።
ዓለም ወደ አዲስ መንታ መንገድ ደርሳለች።"
- የቻይና ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ።
4 295
🇺🇸🤝🇨🇳ሰበር_ዜና፡ የዶናልድ ትራምፕ እና የሺ ጂንፒንግ ታሪካዊ መገናኘት!
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ፣ በቤጂንግ በሚገኘው የሕዝብ ታላቅ አዳራሽ ፊት ለፊት በይፋ መገናኘታቸው ተዘገበ። መሪዎቹ በዛሬው ዕለት ግንቦት 6 ቀን (May 14) ከፍተኛ የዲፕሎማሲያዊ ውይይት ከመጀመራቸው አስቀድሞ፣ በታላቁ አዳራሽ ደጃፍ ላይ እጅ ለእጅ በመጨበጥ የክብር አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ይህ የሁለቱ ኃያላን አገራት መሪዎች ግንኙነት በንግድ፣ በቴክኖሎጂ ሽኩቻ፣ በደኅንነት ጉዳዮች እና ወቅታዊ በሆኑ ዓለም አቀፍ ግጭቶች ዙሪያ የዓለም ትኩረት በከፍተኛ ሁኔታ ባረፈበት ወቅት የተከናወነ በመሆኑ፣ የዓመቱ ቁልፍ ዲፕሎማሲያዊ ኩነት ተደርጎ ተወስዷል።
በቤጂንግ ከተማ ከፍተኛ የፀጥታ ጥበቃ በተደረገበት የክብር አቀባበል ሥነ-ሥርዓት ላይ ሁለቱ መሪዎች ሰላምታ የተለዋወጡ ሲሆን፣ ወዲያውኑም ዝርዝር አጀንዳዎችን በዝግ ለመምከር በሕዝብ ታላቅ አዳራሽ ውስጥ ወደሚካሄደው መደበኛ ውይይት አምርተዋል።
4 295
— 🇮🇷/🇮🇱/🇦🇪 የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ አባስ አራጋቺ፦
'የኢራን የደህንነት መሥሪያ ቤቶች ከረጅም ጊዜ በፊት ለአመራራችን ያስተላለፉትን እና የደረሱበትን ነገር አሁን ኔታንያሁ በይፋ አረጋግጦልናል።
ከታላቁ የኢራን ህዝብ ጋር ጠላት መሆን ሞኝነት የተሞላበት ቁማር ነው።
ይህን በማድረግ ላይ ከእስራኤል ጋር መቆራኘት፣ ይቅር የማይባል ነው።
መከፋፈልን ለመዝራት ከእስራኤል ጋር የሚመካከሩ ተጠያቂ ይሆናሉ።'
4 295
+1
— 🇦🇪/🇮🇱 ሰበር፦ የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ኔታንያሁ ከኢራን ጋር በተደረገው ጦርነት ወቅት አቡ ዳቢን በሚስጥር ጎብኝቷል በሚል የወጣውን ሪፖርት ውድቅ አድርጋለች።
ይህ መግለጫዋ ግራ የሚያጋባ ሆኖ ተገኝቷል፣ ምክንያቱም የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ጉብኝቱን በኦፊሴላዊ X ገጻቸው ላይ ባወጡት መግለጫ አረጋግጠዋል።
4 295
🇺🇸⚔️🇮🇷 የአሜሪካ አምባሳደር እስካሁን ከእስራኤል ጎን ለቆሙት ለባሕረ ሰላጤው አረብ ግዛቶች እንዲህ ብለው ተናግረዋል፦ "በኢራን እና በእስራኤል መካከል መምረጥ ግድ አለባችሁ።"
Middle East Eye: “በእስራኤል የአሜሪካ አምባሳደር ማይክ ሃካቢ፣ ከፋርስ ባሕር ጠረፍ ጋር ድንበር የሚያዋስኑትን የአረብ ሀገራት፣ ከኢራን ጋር ሽርክና ወይም ከእስራኤል እና ከአሜሪካ ጋር ስልታዊ ትብብር መካከል መምረጥ እንዳለባቸው አስጠንቅቀዋል።”
4 295
🇦🇪🇮🇱 • ከኢራን ጋር ጦርነት በተባባሰበት ወቅት ኔታንያሁ በሚስጥር የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስን ጎብኝተው ከሼክ መሐመድ ቢን ዛይድ ጋር ተገናኝተዋል።
• በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት በተለቀቀው መረጃ መሠረት፣ የኔታንያሁ ጉብኝት በ“እስራኤል” እና በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መካከል ባለው ግንኙነት ላይ ታሪካዊ መሻሻል አስገኝቷል።
• በኤሜሬት እና በ“እስራኤል” መካከል ያለው ህብረት ከኢራን ጋር በመፋጠጥ ብቻ የተገደበ ሳይሆን እንደ የመን እና የአፍሪካ ቀንድ ወደመሳሰሉ ሌሎች መድረኮች ይዘልቃልም፣ ተብሏል።
4 295
— 🇮🇱 እስራኤላዊው ጋዜጠኛ ኢታይ ብሉመንታል እስራኤል ውስጥ በከባድ ሳንሱር ምክንያት የጋዜጠኝነት ሥራ የማይቻል ሆኖ እንደቀረ ቅሬታውን አሰምቷል።
በእስራኤል ውስጥ ያሉ አብዛኛዎቹ ጋዜጠኞች አብዛኛውን ጊዜያቸውን የሳንሱር ሕጎችን በማሰስ ያሳልፋሉ ይላል።
4 295
🇭🇺❌🇷🇺— ፒተር ማጋር ቪክቶር ኦርባንን ተክቶ የሃንጋሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ገና ከመሆኑ፣ ሃንጋሪ በዩክሬን ላይ የሩሲያ ድርጊቶችን ለመቃወም የሩሲያውን አምባሳደር ዛሬ አስጠርታለች።
**
በአንድ ሌሊት መገልበጥ ማለት ይሄ ነው። ትናንት Orban ሥልጣን ላይ እያለ ሃንጋሪ የሩሲያ አንደኛ ደጋፊ ነበረች። ዛሬ ሌላው ሲመጣ ሃንጋሪ የሩሲያ አንደኛ ነቃፊ ሆነች። በሃንጋሪ ጉዳይ አውሮፓውያን ሩሲያዎችን አሸንፈዋል።
4 295
🇬🇧 ኪንግ ቻርልስ ምንም እንኳን መንግሥታቸው አንድ ጊዜ ትቶት የነበረውን እና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች አቤቱታ የፈረሙበትን የዲጂታል መታወቂያን ጉዳይ፣ መንግሥታቸው ወደፊት እንደሚገፋበት አስታውቀዋል።
**
ስለ ዲጂታል ID ጥሩነት መጥፎነት ምንም ሳይነገርህና እንድታመዛዝን ሳይፈቀድልህ በግዴታ የምትወስድበት ሀገር ኢትዮጲያና 'ሦስተኛ ዓለም' ደሃ ሀገሮች ይመስሉኛል። እኛ ቤተ-ሙከራዎች ነን!
4 295
— 🇮🇷 ትኩስ ዜና፦ የኢራኑ ጠቅላይ መሪ አያቶላህ ኻማኔይ ታላቅ የቀብር ሥነ ሥርዓት ዝግጅት፣ ወደ መጨረሻው ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ታውቋል።
መጨናነቅን ለማስወገድ እና ህዝቡን ለመቆጣጠር፣ ሠፊ የሎጂስቲክስ ዝግጅቶች እየተደረጉ ነው።
ከኢራናውያን በተጨማሪ፣ ከ1 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የኢራቅ ዜጎች ለቀብሩ ቀድሞውኑ ተመዝግበዋል።
4 295
— 🇮🇷/🇦🇪 የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በመላ ሀገሪቱ በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ የነዳጅ ማጠራቀሚያዋን፣ በፀረ-ድሮን የዓሣ ማጥመጃ መረቦች እና የሽቦ አጥሮች መሸፈን እና ማጠር ጀምራለች።
4 295
🇺🇸🇺🇦 ድርድሮች በአጣብቂኝ ሁኔታ ውስጥ ገብተዋል።
ሩሲያ ዶንባስን በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታቶች ለመያዝ፣ ጥቃቱን ለመቀጠል እና ደቡብ ዩክሬንን ለመጠየቅ ትፈልጋለች፣ - FT።
- ዩክሬን በዶንባስ ላይ በሚደረጉ ስምምነቶች ካልተስማማች፣ ፑቲን ጥቃቱን ለመቀጠል እና አዳዲስ፣ የበለጠ ጥብቅ የግዛት ጥያቄዎችን ለማቅረብ ዝግጁ ነው።
- ደቡብ ዩክሬንን (ወደ ኦዴሳ ያለውን አቅጣጫ) እና ሰፊ "Buffer Zone" መፍጠርን ጨምሮ፣ - Finincial Times ጽፏል።
- ከኢራን ጋር የተካሄደው ጦርነት ካበቃ በኋላም ቢሆን፣ በአሜሪካ ሸምግልና በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል የሰላም ድርድሮችን የመቀጠል እድሉ ዝቅተኛ ነው።
- ትራምፕ የሰጡትን መግለጫዎች ቢሰጡም፣ ከግጭቱ ተሳታፊ ከሆኑት ወገኖች መካከል አንዳቸውም “ድርድሩን መቀጠል ብዙ ጥቅም እንዳለው አያምኑም”።
- በኪየቭ፣ ትራምፕ የሰላም ስምምነት ጥያቄዎቹን እንዲያቃልል በፑቲን ላይ ጫና ባለማድረጉ ተበሳጭተዋል።
- "የአሜሪካ ወገን ከሩሲያ ጋር በሚደረጉ ድርድሮች ላይ ምንም እድገት አላሳየም" ሲል አንድ የዩክሬን ባለስልጣን ተናግሯል።
"ሊወያዩበት የሚችሉት ነገር ሁሉ ቀድሞውኑ ተደርጓል።"
- ድርድሩ ከተቋረጠ እና መላው ዶንባስ በኃይል ከተያዘ፣ ሩሲያ ለቀጣይ አዳዲስ ቅድመ ሁኔታዎችን እንደምታመጣ፣ ኪየቭ እና ኦዴሳ መሸነፋቸውን አምነው እጅ እንዲሰጡ እንደምታስገድድ፣ ያ ካልሆነ ፑቲን ጦርነቱን የሚቀጥል መሆኑን ለዩክሬን ለማቅረብ እንዳሰበች ጽሑፉ ያስነብባል።
- ያ ከመሆኑ በፊት ዩክሬን ዶንባስን እና መላውን ምሥራቅ ዩክሬንን በሰላም ለሩሲያ አሳልፋ ሰጥታ ጦርነቱን እንድታቆም ሩሲያ ትፈልጋለች።
4 295
🇺🇸🇮🇱⚡️🇮🇷 ኢራን ለኒውክሌር ጦር መሳሪያ "በሚያስደነግጥ ሁኔታ" ተቃርባለች ሲል የአሜሪካ ባለስልጣን አስጠንቅቋል።
የኢነርጂ ሚኒስቴሩ Chris Wright ለሕግ አውጭዎች እንደተናገረው፣ ኢራን በጦር መሳሪያ ደረጃ ያለውን ዩራኒየም ለማምረት "በሚያስደነግጥ ሁኔታ ቅርብ ነች" ብሏል።
ኢራን የጦር መሳሪያ ደረጃ ማበልፀጊያ ላይ ለመድረስ "ሳምንታት" ሊቀራት እንደሚችል እና እዚህ ደረጃ ላይ ከደረሰች፣ ኒውክሊየሩን ባታመርተውም፣ ለማምረት የሚያግዳት ነገር አይኖርም ሲል ተናግሯል።
Wright አክሎም፣ ኢራን ባሁኑ ሰዓት ዩራኒየሙን 60 በመቶ ያበለፀገችው ሲሆን፣ ለጦር መሳሪያ ደረጃ ከሚያስፈልገው 90 በመቶ ደረጃ ጋር በጣም ቅርብ ያደርገዋል፣ ሁኔታውም "በጣም አሳሳቢ ነው" በማለት ፍራቻውን ገልጿል።
ኢራን ተፍረክርካለች፣ ተደምስሳለች የሚባለው የተጋነነ እና ከውነት የራቀ ነው፣ በአጭር ጊዜ መሳሪያውን ልታመርት ጫፍ ላይ ናት፣ ዓለም አቀፍ ሀገራት ኢራንን በማስቆም ላይ ከአሜሪካ ጎን ሊሰለፉ ይገባል፣ ሲልም ጥሪውን አቅርቧል።
4 295
🇺🇸🇷🇺 የሩሲያው LAVROV የትራምፕ አስተዳደር የዓለምን የኃይል አቅርቦት ገበያ ለመቆጣጠር ሞክሯል ሲል ከሷል።
LAVROV እንዳለው፣ አሜሪካ እንደ LUKOIL እና ROSNEFT ያሉ የሩስያ ግዙፍ የኃይል ኩባንያዎችን ከዓለም አቀፍ ገበያዎች ማስወጣት እንደምትፈልግ ተናግሯል።
ይህን ያለው፣ በሩሲያ የነዳጅ እና የጋዝ መሠረተ ልማቶች ላይ የዩክሬ ጥቃቶች እየተባባሱ መምጣታቸውን ተከትሎ ነው።
4 295
🇺🇸 / 🇮🇷 በኢስፋሃን አቅራቢያ ከሚገኙት የኢራን የመሬት ውስጥ ሚሳኤል ጣቢያዎች አንዱ፣ በጦርነቱ ወቅት ወደ 20 የሚጠጉ የተለያዩ ጊዜያት በቦምብ ተመትቷል፣ በአማካይ በየሁለት ቀኑ አንድ ጊዜ፣ ከ B-2s እና B-52s በተለያዩ ዓይነት ቦንቦች ተደብድቧል። ተራራን ፈልፍሎ በሚያፈነዳው Bunker Busterም ሲመታ ቆይቷል። ጣቢያው ግን ወደመተኮሱ ለመመለስ ግማሽ ቀን እንኳን አይፈጅበትም ነበር። ከድብደባው በኋላ መተኮሱን ይጀምራል። አንድ የኢስፋሃን ነዋሪ እንዲህ አለ - 'ይህ ተራራ በየምሽቱ ማለት ይቻላል በቦምብ ሲደበደብ እናያለን፣ ጭሱ ሲነሳ እናያለን። ነገር ግን በማለዳ ከእንቅልፋችን ስንነቃ ሚሳኤሎች ወደ ሰማይ ሲወጡ የምናየው ከእነዚህሁ ተራሮች ነው።'
4 295
🇺🇸🇮🇱🇸🇦❌🇮🇷❗️ - የ"2026 የኢራን ጦርነት" ኦፊሴላዊው የዊኪፔዲያ ገጽ፣ ሳውዲ አረቢያን እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶችን ጨምሮ የባህረ ሰላጤ ሀገራትን፣ ከተዋጊዎቹ አንጃዎች መካከል ይዘረዝራል።
አሜሪካ፣ እስራኤል፣ ሳዑዲና ኤሜሬት በአንድ ወገን ናቸው።
ዊኪፒዲያ ሳዑዲና ኤሜሬት ኢራንን የደበደቡ መሆናቸው ከታወቀ በኋላ፣ ጦርነቱን የተመለከተውን ኦፊሴላዊ ገጹን በዚህ መልኩ እንዲስተካከል አድርጎታል።
4 295
🇮🇱📞🇺🇸 - አንድ እስራኤላዊ ባለስልጣን ለCNN እንደተናገሩት፡
"ስምምነት የማይኖር ከሆነ (ከኢራን ጋር) ደስተኞች እንሆናለን፣ በሆርሙዝ ላይ ያለው ከበባ ከቀጠለ ደስተኞች እንሆናለን።"
"እኛ እጃችን ምላጩ ላይ ነው። ስምምነት ከሌለ ደስተኞች እንሆናለን፣ በሆርሙዝ ላይ ያለው ከበባ ከቀጠለ ደስተኞች እንሆናለን፣ ኢራን ጥቂት ተጨማሪ ጥቃቶችን ካስተናገደች ደስተኞች እንሆናለን።
