የቀጠናው ተመልካች
الذهاب إلى القناة على Telegram
በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።
إظهار المزيدلم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
4 294
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-137 أيام
-8030 أيام
أرشيف المشاركات
4 297
🇺🇸🇺🇦 ድርድሮች በአጣብቂኝ ሁኔታ ውስጥ ገብተዋል።
ሩሲያ ዶንባስን በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታቶች ለመያዝ፣ ጥቃቱን ለመቀጠል እና ደቡብ ዩክሬንን ለመጠየቅ ትፈልጋለች፣ - FT።
- ዩክሬን በዶንባስ ላይ በሚደረጉ ስምምነቶች ካልተስማማች፣ ፑቲን ጥቃቱን ለመቀጠል እና አዳዲስ፣ የበለጠ ጥብቅ የግዛት ጥያቄዎችን ለማቅረብ ዝግጁ ነው።
- ደቡብ ዩክሬንን (ወደ ኦዴሳ ያለውን አቅጣጫ) እና ሰፊ "Buffer Zone" መፍጠርን ጨምሮ፣ - Finincial Times ጽፏል።
- ከኢራን ጋር የተካሄደው ጦርነት ካበቃ በኋላም ቢሆን፣ በአሜሪካ ሸምግልና በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል የሰላም ድርድሮችን የመቀጠል እድሉ ዝቅተኛ ነው።
- ትራምፕ የሰጡትን መግለጫዎች ቢሰጡም፣ ከግጭቱ ተሳታፊ ከሆኑት ወገኖች መካከል አንዳቸውም “ድርድሩን መቀጠል ብዙ ጥቅም እንዳለው አያምኑም”።
- በኪየቭ፣ ትራምፕ የሰላም ስምምነት ጥያቄዎቹን እንዲያቃልል በፑቲን ላይ ጫና ባለማድረጉ ተበሳጭተዋል።
- "የአሜሪካ ወገን ከሩሲያ ጋር በሚደረጉ ድርድሮች ላይ ምንም እድገት አላሳየም" ሲል አንድ የዩክሬን ባለስልጣን ተናግሯል።
"ሊወያዩበት የሚችሉት ነገር ሁሉ ቀድሞውኑ ተደርጓል።"
- ድርድሩ ከተቋረጠ እና መላው ዶንባስ በኃይል ከተያዘ፣ ሩሲያ ለቀጣይ አዳዲስ ቅድመ ሁኔታዎችን እንደምታመጣ፣ ኪየቭ እና ኦዴሳ መሸነፋቸውን አምነው እጅ እንዲሰጡ እንደምታስገድድ፣ ያ ካልሆነ ፑቲን ጦርነቱን የሚቀጥል መሆኑን ለዩክሬን ለማቅረብ እንዳሰበች ጽሑፉ ያስነብባል።
- ያ ከመሆኑ በፊት ዩክሬን ዶንባስን እና መላውን ምሥራቅ ዩክሬንን በሰላም ለሩሲያ አሳልፋ ሰጥታ ጦርነቱን እንድታቆም ሩሲያ ትፈልጋለች።
4 297
🇺🇸🇮🇱⚡️🇮🇷 ኢራን ለኒውክሌር ጦር መሳሪያ "በሚያስደነግጥ ሁኔታ" ተቃርባለች ሲል የአሜሪካ ባለስልጣን አስጠንቅቋል።
የኢነርጂ ሚኒስቴሩ Chris Wright ለሕግ አውጭዎች እንደተናገረው፣ ኢራን በጦር መሳሪያ ደረጃ ያለውን ዩራኒየም ለማምረት "በሚያስደነግጥ ሁኔታ ቅርብ ነች" ብሏል።
ኢራን የጦር መሳሪያ ደረጃ ማበልፀጊያ ላይ ለመድረስ "ሳምንታት" ሊቀራት እንደሚችል እና እዚህ ደረጃ ላይ ከደረሰች፣ ኒውክሊየሩን ባታመርተውም፣ ለማምረት የሚያግዳት ነገር አይኖርም ሲል ተናግሯል።
Wright አክሎም፣ ኢራን ባሁኑ ሰዓት ዩራኒየሙን 60 በመቶ ያበለፀገችው ሲሆን፣ ለጦር መሳሪያ ደረጃ ከሚያስፈልገው 90 በመቶ ደረጃ ጋር በጣም ቅርብ ያደርገዋል፣ ሁኔታውም "በጣም አሳሳቢ ነው" በማለት ፍራቻውን ገልጿል።
ኢራን ተፍረክርካለች፣ ተደምስሳለች የሚባለው የተጋነነ እና ከውነት የራቀ ነው፣ በአጭር ጊዜ መሳሪያውን ልታመርት ጫፍ ላይ ናት፣ ዓለም አቀፍ ሀገራት ኢራንን በማስቆም ላይ ከአሜሪካ ጎን ሊሰለፉ ይገባል፣ ሲልም ጥሪውን አቅርቧል።
4 297
🇺🇸🇷🇺 የሩሲያው LAVROV የትራምፕ አስተዳደር የዓለምን የኃይል አቅርቦት ገበያ ለመቆጣጠር ሞክሯል ሲል ከሷል።
LAVROV እንዳለው፣ አሜሪካ እንደ LUKOIL እና ROSNEFT ያሉ የሩስያ ግዙፍ የኃይል ኩባንያዎችን ከዓለም አቀፍ ገበያዎች ማስወጣት እንደምትፈልግ ተናግሯል።
ይህን ያለው፣ በሩሲያ የነዳጅ እና የጋዝ መሠረተ ልማቶች ላይ የዩክሬ ጥቃቶች እየተባባሱ መምጣታቸውን ተከትሎ ነው።
4 297
🇺🇸 / 🇮🇷 በኢስፋሃን አቅራቢያ ከሚገኙት የኢራን የመሬት ውስጥ ሚሳኤል ጣቢያዎች አንዱ፣ በጦርነቱ ወቅት ወደ 20 የሚጠጉ የተለያዩ ጊዜያት በቦምብ ተመትቷል፣ በአማካይ በየሁለት ቀኑ አንድ ጊዜ፣ ከ B-2s እና B-52s በተለያዩ ዓይነት ቦንቦች ተደብድቧል። ተራራን ፈልፍሎ በሚያፈነዳው Bunker Busterም ሲመታ ቆይቷል። ጣቢያው ግን ወደመተኮሱ ለመመለስ ግማሽ ቀን እንኳን አይፈጅበትም ነበር። ከድብደባው በኋላ መተኮሱን ይጀምራል። አንድ የኢስፋሃን ነዋሪ እንዲህ አለ - 'ይህ ተራራ በየምሽቱ ማለት ይቻላል በቦምብ ሲደበደብ እናያለን፣ ጭሱ ሲነሳ እናያለን። ነገር ግን በማለዳ ከእንቅልፋችን ስንነቃ ሚሳኤሎች ወደ ሰማይ ሲወጡ የምናየው ከእነዚህሁ ተራሮች ነው።'
4 297
🇺🇸🇮🇱🇸🇦❌🇮🇷❗️ - የ"2026 የኢራን ጦርነት" ኦፊሴላዊው የዊኪፔዲያ ገጽ፣ ሳውዲ አረቢያን እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶችን ጨምሮ የባህረ ሰላጤ ሀገራትን፣ ከተዋጊዎቹ አንጃዎች መካከል ይዘረዝራል።
አሜሪካ፣ እስራኤል፣ ሳዑዲና ኤሜሬት በአንድ ወገን ናቸው።
ዊኪፒዲያ ሳዑዲና ኤሜሬት ኢራንን የደበደቡ መሆናቸው ከታወቀ በኋላ፣ ጦርነቱን የተመለከተውን ኦፊሴላዊ ገጹን በዚህ መልኩ እንዲስተካከል አድርጎታል።
4 297
🇮🇱📞🇺🇸 - አንድ እስራኤላዊ ባለስልጣን ለCNN እንደተናገሩት፡
"ስምምነት የማይኖር ከሆነ (ከኢራን ጋር) ደስተኞች እንሆናለን፣ በሆርሙዝ ላይ ያለው ከበባ ከቀጠለ ደስተኞች እንሆናለን።"
"እኛ እጃችን ምላጩ ላይ ነው። ስምምነት ከሌለ ደስተኞች እንሆናለን፣ በሆርሙዝ ላይ ያለው ከበባ ከቀጠለ ደስተኞች እንሆናለን፣ ኢራን ጥቂት ተጨማሪ ጥቃቶችን ካስተናገደች ደስተኞች እንሆናለን።
4 297
🇮🇷⚡️🇺🇸 Robert Kagan በ The Atlantic ላይ በጻፈው መጣጥፉ፣ አሜሪካ በኢራን ሽንፈትን እንዳስተናገደች አምኗል።
"ዩናይትድ ስቴትስ ኢራንን ማንበርከክ አልቻለችም እና አሁን የማይቀር ሽንፈትን ፊት ለፊቷ ትመለከታለች" ብሏል፣ ታማኙ ኒዮካን እና ጽዮናዊው Robert Kagan በመጣጥፉ።
የሚከተሉት ነገሮች ጨርሰው ከሆኑ (አሁን እየሆኑ ናቸው) አሜሪካ ትሸነፋለች፣ ይላል።
🔴 ኢራን የሆርሙዝ ባሕርን ከተቆጣጠረች ይህም ለአሜሪካ እና ለእስራኤል ጥቅም ከባድ ጉዳት ነው
🔴 ቀደም ሲል ይተማመኑበት የነበረውን የአሜሪካ የፀጥታ ከለላ አቅመ ቢስነት የተመለከቱ የአረብ ሀገራት፣ አሁን ኢራንን ማስተናገድ ከጀመሩ (ጀምረዋል)።
🔴 ከባሕረ ሰላጤው በሚገቡ የኃይል ምርቶች ላይ ጥገኛ የሆኑ ሁሉም ሀገራት፣ ምርቶቻቸውን ለመጫንና ለማሳለፍ ከኢራን ጋር የራሳቸውን ድርድር ማድረግ ከጀመሩ (እያደረጉ ናቸው)።
🔴 በዚህ ጦርነት ምክንያት የተፈጠረው የአሜሪካ የጦር መሳሪያ እና የጦር መሳሪያ ክምችት ከፍተኛ መሟጠጥ፣ አሜሪካ በሌሎች የዓለም ክፍሎች ለሚከሰቱ ቀውሶች ምላሽ የመስጠት አቅሟ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ካሳደረ (በጣም እያሳደረ ነው)፣ ኢራን አሸንፋለች ማለት ነው።
አሁን የሚታየው ነገር መጪውን ዘመን አስሎ የሚሞርድ ነው። በዚህ ውስጥ ኢራን በተሻለ የመውጣት ዕድል አላት የሚል ሰፊ ግምት አለ። ሁኔታውን በዚሁ ለምትቀጥለው ዩናይትድ ስቴትስ ግን፣ እጅግ አሳሳቢ ነው።
ነገሩን በፍጥነት አርግባ የመውጫ ቀዳዳ (Exit Strategy) ማበጀት ያድናታል።
"አሜሪካ በአንድ ወቅት በባሕረ ሰላጤው የነበራትን የበላይነት ቦታ ማጣት፣ ከብዙ ጉዳቶች ውስጥ፣ የመጀመሪያውና አንጋፋው ነው" ሲል ካጋን ተናግሯል።
ዶናልድ ትራምፕ በፋርስ ባሕረ ሰላጤ ስላጋጠመው መፍረክረክ የፈለገ ሊክድ ይችላል፣ ነገር ግን በአሜሪካ ውስጥ ያሉ ጠንከር ያሉ ጽዮናውያን እና የኢራን ጠላቶች፣ ግድግዳው ላይ ተጽፎ በግልጽ የሚታየውን ግላጭ እውነታ እያነበቡት ይመስላል።
4 297
🇺🇸🇻🇪 ፕሬዚዳንት ትራምፕ ቬኔዝዌላን እንደ 51ኛ የአሜሪካ ክፍለ ሀገር አድርጎ ለጠፈ።
በትናንትናው ዕለት፣ "ለቬኔዝዌላ ፕሬዝዳንትነት ተወዳድሬ የሀገሪቱ መሪ እሆናለሁ" ማለቱ ይታወሳል።
ትራምፕ ወደ ሥልጣን ከመጣ ጀምሮ በቬኔዝዌላ "ጤናማ ባልሆነ ፍቅር" ተለክፏል የሚሉት ብዙ ናቸው።
እንዲህ ሲል፣ ለመጀመሪያ ጊዜው አይደለም።
4 297
🇺🇸 🇮🇷 ሪፖርተር - "የአሜሪካውያን የፋይናንስ ሁኔታ ከኢራን ጋር ስምምነት ለማድረግ ምን ያህል ያነሳሳሃል?"
ትራምፕ "ትንሽ እንኳን አያነሳሳኝም.... ስለ አሜሪካውያን የገንዘብ ሁኔታ አላስብም"
📎
4 297
🇺🇸🇮🇷 - ፕሬዝዳንት ትራምፕ፡ "ኢራን በወታደራዊ መስኩ ጥሩ እየሰራች ነው" የሚል ሪፖርት የሚያደርግ ማንኛውም ሰው፣ "ምናባዊ ክህደት" እየፈፀመ እና "ጠላትን እየረዳ እና እያበረታታ" ነው ብለዋል።
ይህን ያለው፣ የአሜሪካ ሚዲያዎችን በወረፈበት የዛሬ ልጥፉ ነው።
4 297
⚡️🇮🇷🇮🇶🇵🇰 ሮይተርስ፡ ኢራቅ እና ፓኪስታን ከኢራን ጋር የነዳጅ ዘይት እና የተፈጥሮ ጋዝ በባሕረ ሰላጤው በኩል ለመጫን ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
ይህም፣ ቴህራን በሆርሙዝ ባሕር በኩል ባለው የኃይል ፍሰት ላይ፣ ሚናዋ እና ጡንቻዋ እየፈረጠመ መምጣቱን አጉልቶ ያሳያል።
4 297
🇺🇸🏴⚔️🇮🇷 ትራምፕ "ጥሩ ስምምነት ካልሆነ በስተቀር ከኢራን ጋር ስምምነት አንፈጽምም" ብሏል።
"ኢራንን በተመለከተ የቻይና ፕሬዝዳንት እርዳታ ያስፈልገናል ብዬ አስባለሁ" ያለው ትራምፕ፣ "የኔቶ ህብረት አሳዝኖኛል እና ከእነሱ እርዳታ አያስፈልገንም" ሲል ተናግሯል።
ኢራንን በተመለከተ "አሁን ላይ ይሄ ነው የሚባል ዕርዳታ አያስፈልገንም፣ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ፣ በሰላማዊም ሆነ በሌላ መንገድ፣ እናሸንፋለን" ሲል አክሎዋል።
4 297
⭕️ CNN የሳተላይት ምስሎችን በመጥቀስ፣ ከኢራን ካርግ ደሴት ከ12 እስከ 20 ካሬ ኪሎ ሜትር ሥፋት ያለው እና ወደ ሳውዲ አረቢያ ውሃ እየተንሳፈፈ ያለ የፈሰሰ የነዳጅ ብክለት መኖሩን ዘግቧል።
4 297
🇸🇦⚡️🇮🇷 ትኩስ ዜና | ሮይተርስ ሳዑዲ ዓረቢያ በጦርነቱ ወቅት በኢራን ላይ በድብቅ ጥቃት ሰንዝራ እንደነበር በምርመራ ደርሼበታለሁ አለ።
የሮይተርስ ምርመራ እንዳመለከተው፣ ሳውዲ ዓረቢያ በመጋቢት ወር መጨረሻ ላይ፣ አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ባደረጉት ጦርነት፣ በድብቅ የአየር ድብደባ እንደፈፀመች እና ይህም በኢራን ግዛት ላይ የመጀመሪያው የሳዑዲ ወታደራዊ ጥቃት እንደሆነ ዘግቧል።
የኢራንና የምዕራባዊያንን ምንጮች ጠቅሶ ሮይተርስ እንደዘገበው፣ ጥቃቶቹ ከፍተኛ እንደነበሩና፣ ያንን ተከትሎ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች እና የሳዑዲ ዛቻዎች ተፋፍመው እንደነበር ዘግቧል።
በመጨረሻም በሚያዝያ ወር፣ ጦርነቱ ቀጠናዊ እንዳይሆን በመስጋት፣ የአሜሪካ-ኢራን የተኩስ አቁም ከመታወጁ በፊት፣ በቴህራን እና በሪያድ መካከል መደበኛ ባልሆነ መንገድ ዲፕሎማሲያዊ መግባባት እንዲፈጠር ሆኗል።
ሮይተርስ እንደዘገበው ሪያድም ከቴህራን ጋር የለየለት ጦርነት ውስጥ ላለመግባት ስትል ዲፕሎማሲያዊ ቻናሎችን እንደዘረጋች ዘግቧል።
4 297
🇺🇸🇺🇦የፔንታጎን ኃላፊ ፒት ሄግሴት: በዩክሬን የሚገኘው የአሜሪካ ጦር በድሮን ውጊያ ልምድ እያገኘ መሆኑን ተናግረዋል።
"ብዙ ትላልቅ ባለስልጣናት እዚያ (በዩክሬን) ነበሩ እና ከፍተኛ መጠን ያለው መረጃ ደርሶናል።
እንዲያውም ከእነዚህ የድሮን ፍልሚያዎች፣ ከመከላከልም ሆነ ከማጥቃት ዘርፍ እንዲማሩ በግሌ፣ ተጨማሪ ሠራተኞችን ዩክሬን እንዲሄዱ አጽድቄያለሁ" ሲል ተናግሯል።
4 297
+9
— 🇮🇷 — : የኢራን IRGC አካል የሆነው፣ 'ሙሐመድ ረሱሉላህ' የተባለው አንዱ ክፍለ-ጦር፣ ዛሬ፣ የአሜሪካንን ወረራ በመከላከል ላይ ሲሰለጥን የሚያሳዩ ምስሎች ተለቀዋል።
