ar
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

الذهاب إلى القناة على Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
4 303
المشتركون
+824 ساعات
-47 أيام
-7130 أيام
أرشيف المشاركات
⚡️🇸🇦🇾🇪 በሪያድ የሚገኘው የአርማኮ ነዳጅ ማከማቻ፣ በአሁኑ ሰዓት እየነደደ ይታያል። የዋና ከተማው ሰማይ በአብዛኛው በጥቁር ጭስ መሸፈኑን መረጃዎች ያሳያሉ።

🇸🇦🇾🇪⚡️በአሁኑ ሰዓት የሪያድ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ፣ እሳት እየነደደበት ይታያል።
+1
🇸🇦🇾🇪⚡️በአሁኑ ሰዓት የሪያድ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ፣ እሳት እየነደደበት ይታያል።

🇮🇱🇮🇷 የእስራኤል የፀጥታ ተቋማት፣ በኢራን ጦርነት ወቅት ለኢራን ሰፊ የስለላ ሥራ ሲሠሩ የነበሩ ያሏቸው የእስራኤል ወታደራዊ ክፍሎች ላይ፣ ምርመራ እያካሄዱ እንደሆነ አስታወቁ። ዝርዝር ከመግለፅ የታቀቡት የፀጥታ ባለስልጣናቱ፣ በIDF ውስጥ ለኢራን በስፋት የስለላ ሥራ ሲሰሩ የነበሩ የጦሩ አባላት እንዳሉ ተናግረው፣ ሁሉንም ነገር ምርመራው ሲያልቅ ግልጽ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል - Jeruselam Post

🇺🇦🇺🇸⚡️🇷🇺 ሰላም የሚገኘው በኃይል ነው። ኃይል ደግሞ በጽናት ነው። አሜሪካ፣ አመሰግናለሁ! ዘለንስኪ። ኪየቭ ዋሽንግተንን፣ የፀረ-ሩሲያ ማዕቀቦችን በማውጣቷ አመስግናለች።
🇺🇦🇺🇸⚡️🇷🇺 ሰላም የሚገኘው በኃይል ነው። ኃይል ደግሞ በጽናት ነው። አሜሪካ፣ አመሰግናለሁ! ዘለንስኪ። ኪየቭ ዋሽንግተንን፣ የፀረ-ሩሲያ ማዕቀቦችን በማውጣቷ አመስግናለች።

+2
🇸🇦🇾🇪⚡️🇾🇪❌🇸🇦 — በሪያድ፣ የሚሳዬል ጥቃቶች እና የአደጋ ጊዜ ደውሎች አሁን ድረስ ከተማውን እየናጡ ይገኛሉ። የአንሷረላህ (ሁቲ) ባለስቲክ ሚሳኤሎች፣ የአሜሪካ ጦር/የሮያል ሳዑዲ አየር መቃወሚያ ሚሳዬሎችን አልፈው ሲወርዱ እንዳዩም፣ የዓይን እማኞች ከቦታው እየዘገቡ ናቸው።

🇸🇦🇾🇪⚡️ሰበር ዜና፡ በሳዑዲ ዓረቢያ ዋና ከተማ ሪያድ፣ ምሽቱን በርካታ ፍንዳታዎችን መስማታቸውን በዚያ ያሉ ሐበሾች ነግረውኛል። በዋና ከተማዋ ሪያድ፣ ፍንዳታ ሲሰማ ይሄ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። እንደ ሌሎች ተጨማሪ ዘገባዎች፣ በዋና ከተማው የሚገኘው ኪንግ ካሊድ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን፣ በአሁኑ ሰዓት አውሮፕላኖችን ማሳረፍ ትቷል።

🇺🇸/🇩🇰/🇬🇱 ቻይና እና ሩሲያ ቂጣ ሆኑ። ከአሁን በኋላ፣ ባሕር አሰሳ፣ ቤዝ ለማቋቋም መሞከር፣ በዚያ ማለፍ፣ ኢንቬስትመንት ማድረግ፣ የለም! የደሴቲቱን፣ ከሞላ ጎደል፣ ባለቤትነት አሜሪካ ተረክባለች። የፕሬዝዳንት ትራምፕን አመራር አለማድነቅ አይቻልም። አመራሩ፣ የቬኔዝዌላን ባለቤትነት ሙሉ በሙሉ፣ ከነ አንጡረ- ሀብቷ፣ መረከብም የቻለ ነው። ቬኔዝዌላ፣ የOPEC አባል የሆነች፣ እጅግ ሀብታም ነዳጅ አምራች ሀገር ናት። ዛሬ ያለ አሜሪካ ይሁንታ፣ አንዲት የንግድ ፈቃድ ለማንም አይሰጥም። ወደ ሥልጣን በመጣ በሁለት ዓመቱ፣ ትራምፕ ይህን ማድረግ ችሏል። ያቃቱት፣ ኢራኖች ብቻ ናቸው።

—❗️🇺🇸/🇩🇰/🇬🇱 ሰበር ዜና ፕሬዝዳንት ትራምፕ፣ አሜሪካ በግሪንላንድ ደኅንነት ላይ ሙሉ ቁጥጥር እንደሚኖራት፣ ከዴንማርክ እና ከግሪላንድ ጋር በተደረገ ስምምነት መረጋገጡን አስታወቀ። ከእ
—❗️🇺🇸/🇩🇰/🇬🇱 ሰበር ዜና ፕሬዝዳንት ትራምፕ፣ አሜሪካ በግሪንላንድ ደኅንነት ላይ ሙሉ ቁጥጥር እንደሚኖራት፣ ከዴንማርክ እና ከግሪላንድ ጋር በተደረገ ስምምነት መረጋገጡን አስታወቀ። ከእንግዲህ ወዲህ የደሴቲቱ ደህንነት የሚጠበቀው፣ ለዚህም ኃላፊነቱን ሙሉ በሙሉ የምትወስደው እና ያሻትን ማድረግ የምትችለው አሜሪካ እና አሜሪካ ብቻ ናት፣ ሲል ተናግሯል። ከአሁን ጀምሮ፣ ዩናይትድ ስቴትስ በተገቢው የግሪንላንድ አካባቢዎች 'ትልቅ ወታደራዊ ኃይል' ማሰማራት ትጀምራለች፣ ብሏል።

🇷🇺🇪🇺⚡️የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን፡
ሩሲያ በአውሮፓም ሆነ በአውሮፓ አገራት ላይ ምንም ዓይነት የጥቃት ፍላጎት እንደሌላት በድጋሚ ለመግለጽ እፈልጋለሁ። ለዚህ ምንም ዓይነት መሠረት የለንም። ከአውሮፓ ጎረቤቶቻችን ጋር ለመተባበር እና ግንኙነቶችን ለማደስ ዝግጁ ነን ።
ትናንት ያልኩት ሆነ፣ ፑቲን አልቆረጠለትም፣ ስለዚህ በተከፋፈለ ልብ ነው የሚዋጋው። አውሮፓዊያን ቆርጦላቸው፣ በአንድ ልብ እየተዋጉ ነው። እሱ ዛሬም፣ ስለ አብሮነት ያወራል፣ በጦርነት መሃል። እነሱ ይሄን መስማት አይፈልጉም!

🇮🇷🇺🇸🇮🇱⚡️በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢራናውያን፣ ከበርካታ ወራት ጦርነት በኋላ፣ ዛሬ በተለያዩ የኢራን ከተሞች ባደረጉት የእምቢተኝነት ሰልፍ ላይ፣ ትጥቅ ለመያዝ ዝግጁ መሆናቸውን እና ከመንግ
🇮🇷🇺🇸🇮🇱⚡️በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢራናውያን፣ ከበርካታ ወራት ጦርነት በኋላ፣ ዛሬ በተለያዩ የኢራን ከተሞች ባደረጉት የእምቢተኝነት ሰልፍ ላይ፣ ትጥቅ ለመያዝ ዝግጁ መሆናቸውን እና ከመንግሥታቸው ጋር እንደሆኑ ገልጸዋል። በየቀኑ የሚደረጉ ያልተቋረጡ ሰልፎችም፣ ዛሬ 200ኛ ቀናቸውን ይዘዋል - AP

🇺🇸🇮🇷⚡️የአሜሪካ የጦር ሚኒስትሩ ፒት ሄግሲት፣ The Washington Post ጋዜጣ፣ በኢራን ጦርነት የሞቱ የአሜሪካን ወታደሮች ቁጥር ብዛት ከተገለጸው በላይ ነው፣ ማለቱን ውድቅ አድርጎ፣
🇺🇸🇮🇷⚡️የአሜሪካ የጦር ሚኒስትሩ ፒት ሄግሲት፣ The Washington Post ጋዜጣ፣ በኢራን ጦርነት የሞቱ የአሜሪካን ወታደሮች ቁጥር ብዛት ከተገለጸው በላይ ነው፣ ማለቱን ውድቅ አድርጎ፣ Washingron Post "ከኢራን መንግሥት ሚዲያ የከፋ ነው" ሲል ተናግሯል።

🇸🇦⚡️🇾🇪 ሳዑዲ ዓረቢያ፣ አንሷረላህ (ሁቲ) በግዛቷ ላይ የባለስቲክ ሚሳዬል ጥቃቶችን እንዲያቆምላት በቀጥታ ጠየቀች መባሉ ተሰማ። ይህን ያለችው፣ በርካታ ሀገራትን በተዘዋዋሪ መንገድ ለእርዳታ ጠይቃ 'እምቢ' ወይም 'አንችልም' ከተባለች በኋላ ነው። 

🇸🇦⚡️🇾🇪 ሳዑዲ ዓረቢያ፣ አንሷረላህ (ሁቲ) በግዛቷ ላይ የባለስቲክ ሚሳይል ጥቃቶችን እንዲያቆምላት በቀጥታ ጠየቀች፣ መባሉ ተሰማ። ይህን ያለችው፣ በርካታ ሀገራትን በተዘዋዋሪ መንገድ ለእርዳታ ጠይቃ 'እምቢ' ወይም 'አንችልም' ከተባለች በኋላ ነው። 

🇸🇦⚡️🇾🇪 ሳዑዲ ዓረቢያ፣ አንሷረላህ (ሁቲ) በግዛቷ ላይ የባለስቲክ ሚሳይል ጥቃቶችን እንዲያቆምላት በቀጥታ ጠየቀች፣ መባሉ ተሰማ። ይህን ያለችው፣ በርካታ ሀገራትን በተዘዋዋሪ መንገድ ለእርዳታ ጠይቃ 'እምቢ' ወይም 'አንችልም' ከተባለች በኋላ ነው። 

🇸🇦⚡️መሐመድ ቢን ሰልማን፣ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች፣ ሞዴሎች እና ዘፋኞች መግለጫ እንዲሰጡ እና ለሳውዲ ዓረቢያ እንዲጸልዩ አዘዘ። በአሁኑ ሰዓት፣ በተለያዩ ሶሻል ሚዲያዎች፣ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች፣ ፈሞዴሎች እና ሙዚቀኞች፣ በዘመቻ መልክ፣ ለሳዑዲ ዓረቢያ እየጸለዩ ናቸው።

🇸🇦⚡️መሐመድ ቢን ሰልማን፣ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች፣ ሞዴሎች እና ዘፋኞች መግለጫ እንዲሰጡ እና ለሳውዲ ዓረቢያ እንዲጸልዩ አዘዘ። በአሁኑ ሰዓት፣ በተለያዩ ሶሻል ሚዲያዎች፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ፈሞዴሎች እና ሙዚቀኞች ለሳዑዲ ዓረቢያ እየጸለዩ ናቸው።

🇾🇪🇸🇦| አሁን፡ ሌላ ትልቅ መጠነ- ሰፊ የየመን የሚሳኤል/የድሮን ጥቃት፣ በሳዑዲ ዓረቢያ ላይ ተጀምሯል። ጅዳ፣ ጣኢፍ፣ ያንቡ ካሚስ ሙሻይት፣ በአደጋ ሳይረኖች ውስጥ ናቸው።

⚡🇸🇦🇾🇪 በጅዳ ሳዑዲ ዓረቢያ፣ የአደጋ ጊዜ ሳይረኖች በአሁኑ ሰዓት በመጮኽ ላይ ናቸው።

🇺🇸🇪🇷 ኤርትራዊያን ወንድም እህቶቻችን፣ እንኳን ደስ ያላችሁ 💐

🇺🇸🇪🇷 ሰበር ዜና፡ የትራምፕ አስተዳደር ዛሬ በኤርትራ የመከላከያ ሰራዊት እና በሌሎች በርካታ የኤርትራ አካላት ላይ የጣለውን ማዕቀብ ማንሳቱን አስታወቀ። በ 2021 በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ጦርነት ውስጥ የኤርትራ ተሳትፎን በተመለከተ በባይደን አስተዳደር የተጣሉትን እርምጃዎችንም ሙሉ በሙሉ መቀልበሱን አስታውቋል። ተንታኞች እንደሚሉት፣ ይህ እርምጃ ኤርትራ በቀይ ባሕር የመርከብ መተላለፊያ ላይ ያላትን ስትራቴጂካዊ አቀማመጥ ግምት ውስጥ በማስገባት፣ የአሜሪካን ግንኙነት ለማጠናከር የተወሰደ እርምጃ ነው ብለው ያምናሉ።