ar
Feedback
​🌹قَـــنَـــاةُ بِـــنـــتْ مُـــحَـــمَّـــد 🌹

​🌹قَـــنَـــاةُ بِـــنـــتْ مُـــحَـــمَّـــد 🌹

الذهاب إلى القناة على Telegram

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
1 376
المشتركون
+1824 ساعات
+3637 أيام
+64630 أيام
أرشيف المشاركات
ክፍል ➋ 📜የኪታቡ ስም፡ اِنْتَبِهْ أَنْتَ مُرَاقَبْ!! (ኢንተቢህ አንተ ሙራቀብ) 🎙አቅራቢ ፡በኡስታዝ ዐብዱረዛቅ አል-ባጂ
✈️⬜️ስለ ቀልባችን☑️
➡️ Share: t.me/Sle_qelbachn1

የዛሬ ጧት አንዳንድ ጧቶች ፀሐይ ከመውጣቷ በፊት ልብህን የሚያስታግስ አንድ መልዕክት ይዘው ይመጣሉ፦ «አትጨነቅ… አላህ አለ።» ትናንት የተሰበረውን ልብ ዛሬ መልሶ ማበጀት ይችላል። ትናንት የተዘጋው
የዛሬ ጧት አንዳንድ ጧቶች ፀሐይ ከመውጣቷ በፊት ልብህን የሚያስታግስ አንድ መልዕክት ይዘው ይመጣሉ፦ «አትጨነቅ… አላህ አለ።» ትናንት የተሰበረውን ልብ ዛሬ መልሶ ማበጀት ይችላል። ትናንት የተዘጋውን በር ዛሬ መክፈት ይችላል። ትናንት የከበደውን ነገር ዛሬ ማቅለል ይችላል። ስለዚህ ይህን ጧት በፍርሃት አትጀምሪው፤ በተወኩል ጀምረው። የልብህን ሁሉ ለእሱ አስረክበው። ምክንያቱም የአላህ እቅድ ሁሌም ከእኛ ፍርሃት የበለጠ ውብ ነው። اللهم اجعل هذا الصباح بدايةً لكل خير، وفرجًا لكل هم، وطمأنينةً لكل قلب. አላህዬ ጧታችንን የመልካም ነገር መጀመሪያ፣ የጭንቀት መፍትሔ እና የልብ ሰላም ያድርግልን። አሚን

"የራስ ዋጋ" እውነተኛ መውደድ የሚገለፀው መጀመሪያ ራስን በመውደድ ነው፤ ሰዎች አንችን ከማክበራቸው በፊት አንች ራስሽን አክብሪው። እነሱ ሁኔታሽን አይተው ነው የሚለዋወጡት። የአንድን ዕቃ ዋጋ የሚ
"የራስ ዋጋ" እውነተኛ መውደድ የሚገለፀው መጀመሪያ ራስን በመውደድ ነው፤ ሰዎች አንችን ከማክበራቸው በፊት አንች ራስሽን አክብሪው። እነሱ ሁኔታሽን አይተው ነው የሚለዋወጡት። የአንድን ዕቃ ዋጋ የሚያወጣው ሻጩ ነው፤ ካላዋጣው እኮ መቼም አይሸጥም፤ የራስሽን ዋጋ የምታወጭው አንች ነሽ! ቦታሽን እወቂ! ራስሽን ከምንም ነገር በላይ አክብሪው እህቴ!

በህይወትሽ ፈተናተከበዛብሽ አትዘኝ አትተክዥ የጨረቃውበት የሚደምቀው ጨለማ በዙሪያዋ የጨለማው ቁጥር በጨመረ ግዜ ነው እና ፡፡ የሰውነትሽን ቁስል በልብስ እደምሸፍኝው ሁሉ የልብሽንም ቁስል በፈገግታ
በህይወትሽ ፈተናተከበዛብሽ አትዘኝ አትተክዥ የጨረቃውበት የሚደምቀው ጨለማ በዙሪያዋ የጨለማው ቁጥር በጨመረ ግዜ ነው እና ፡፡ የሰውነትሽን ቁስል በልብስ እደምሸፍኝው ሁሉ የልብሽንም ቁስል በፈገግታ ሸፍኝው የውስጥኝን ሀዘን ሰወች እዳውቁልሽ አትጣሪ ምክናየቱም ከሚያክሙሽ በላይ በቁስልሽ ላይ እሾኽየሚተክሉብሽ ስለሚበዙ

☀️ሁሉም ሰው የሚስቅ ፊት ማየት ይችላል ነገር ግን የተሰበረ _ልብን_ ማየት ግን አይችልም። _ልባችሁን ጠብቁ_.....
☀️ሁሉም ሰው የሚስቅ ፊት ማየት ይችላል ነገር ግን የተሰበረ _ልብን_ ማየት ግን አይችልም። _ልባችሁን ጠብቁ_.....

ፈጥኖ ማን ይመልስ ! ✈️✈️ ትክክለኛውን  መልስ ያገኝ ሰው  add የሚለውን በመጫን ስጦታ ያገኛል። 📝 ጥያቄ በቁርዓን ውስጥ "ዙን-ኑን" የዓሳ ነባሪው ባለቤት በሚል ስያሜ የተጠሩት ነብይ ማን ናቸው ?

👆እራሳችሁን ፈትሹበት [ክፍል ❶➏]    ⭕️ባይሆን ቪድዮ አቁሞ አስተንቶ መመለስ አይቻልም በሚሰጣችሁ ሰከንድ ብቻ    👉ከ❶❸ ጥያቄ ስንት እዳመጣችሁ ከስር አስቀምጡልኝ ከተመቻችሁ ይቀጥላል...   ➥ሌሎች ማጋራታችሁንም አትርሱ    https://t.me/+SpJHRe6JfQQ0NGI0

​ ​🏠 የሕይወት እውነተኛው ጣዕም! አስባችሁታል? ከውሎ ውጥንጥርና ከባድ ጣጣ ደክሞና ዝሎ ወደ ቤቱ ሲገባ… ቤቱ ግን ባዶ ሆኖ ይጠብቀዋል። ያ ጭንቀት፣ ያ ጥቁር ዝምታ ከምን ጋር ይመሳሰላል? ​ግን ደግሞ የቤቱ ድምቀቶች፣ እነዚያ ውድ የሕይወት ጌጦች ሲኖሩ… የትኛውንም ድካም በአፍታ የሚያስረሳው ያ የፍቅር እቅፍ ምንኛ ያስቀናል! ​እናንተስ ላጤዎች (የብቸኝነት ማዕበል የሚፈታተናችሁ)… ቤታችሁ ሲገባ የሚሰማችሁ ስሜት ምን ይመስላል?

​✨ አዲስ ብስራት ለእውቀት ፈላጊዎች በሙሉ! ✨ ​በኢስላማዊ እውቀት ህይወትዎን ማሳመር ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ «ኢብኑ ዐብባስ» Online መድረሳ በሩን ክፍት አድርጎ ይጠብቅዎታል። ​📚 የምንጀም
​✨ አዲስ ብስራት ለእውቀት ፈላጊዎች በሙሉ! ✨ ​በኢስላማዊ እውቀት ህይወትዎን ማሳመር ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ «ኢብኑ ዐብባስ» Online መድረሳ በሩን ክፍት አድርጎ ይጠብቅዎታል። ​📚 የምንጀምረው ትምህርት፦ ​«ኹዝ ዐቂደተክ» (كتاب خذ عقيدتك من الكتاب والسنة) 🎙 ትምህርቱ የሚሰጠዉ :- በኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ኬሚሴ" ​📌 ለመመዝገብና በቂ መረጃዎችን ለማግኘት፦ 🔰 ​ ለወንዶች፦ @Yufa4 ​ 🔰 ለሴቶች፦ @bint_Adem15 🔰 @Riiche1 ​🔰 «እውቀትን መፈለግ በምእመናን ላይ ግዴታ ነው!» የዕድሉ ተጠቃሚ ይሁኑ፤ ለወዳጅ ዘመድዎም ያጋሩት!

🛡️ በመውደቅና በመነሳት መካከል ያለው ጉዞ🛡️ አንድ አማኝ በዚህች ምድር ላይ ያለው ቆይታ የዕድሜ ልክ "ጂሃድ" (ትግል) ነው። ይህ ትግል ከጠላት ጋር ሳይሆን ከገዛ ነፍሱ ጋር የሚደረግ የቤት ስራ ነው። ⚔️ ነፍስህ ሁልጊዜም ወደ ስሜትና ወደ ምቾት ታዘነብላለች፤ አንተ ደግሞ ወደ አላህ ትእዛዝ ትጎትታታለህ። አንዳንድ ጊዜ ታሸንፋታለህ፤ ብዙ ጊዜ ደግሞ ታሸንፍሃለች። ነገር ግን ዋናው ቁምነገር መሸነፍህ ሳይሆን፣ ተስፋ ቆርጠህ ትግሉን አለማቆምህ ነው። ትልቁ ስኬት አሸናፊ ሆነህ፣ ከነፍስህ ግፊት ነፃ ወጥተህ አላህን መገናኘት ነው። ⛔️ ከቀጥተኛው መንገድ (እስቲቃማ) በኋላ ወደ ኋላ መመለስ እጅግ ያማል። ምክንያቱም አንተ ቀደም ሲል የታዛዥነትን (ጧዓን) ጥፍጥና ቀምሰሃል፤ የሱጁድን ሰላም፣ የቁርአንን ብርሃንና የዱዓን እርካታ አውቀሃል። ከዚያ ብርሃን ወጥተህ ወደ ርቀት መራራነትና ወደ ጨለማው ስትመለስ የሚሰማህ የልብ ስብራት ከባድ ነው። ⚠️ ወዳጄ መለየት ያለብን ሁለት ነገሮች፦ "ፉቱር" መዘናጋት ድካም እና "ኢንቲካሳ" ወደኋላ መመለስ ብዙዎቻችን በሁለቱ መካከል ያለውን ልዩነት ባለመረዳት ሰይጣን እንዲያታልለን በር እንከፍታለን፦ 1. ፉቱር (መንፈሳዊ መዘናጋት/ድካም)፦ ይህ በሰው ልጅ ተፈጥሮ ውስጥ ያለ ነው። የትርፍ (ናፊላ) ስራዎች ላይ መስነፍ፣ ቁርአን የመሐፈዝ ፍላጎት መቀነስ፣ ዚክር ላይ መዛል... ይህ መንፈሳዊ ድካም ነው። መፍትሄውም ነፍስን መታገልና በትንሽ በትንሹ ወደ ነበረችበት መመለስ ነው። 2. ኢንቲካሳ (ወደ ኋላ መመለስ/ማፈንገጥ)፦ አደገኛ የሚሆነው ግን አላህ ግዴታ (ዋጅብ) ያደረገብህን ትተህ "መንፈሴ ደክሟል" ወይም "ኢንቲካሳ ውስጥ ነኝ" ብለህ ማመካኘት ስትጀምር ነው። አላህ የደነገገብህን "ፈርድ" ስራዎች ጥለህ ለወንጀልህ "ኢንቲካሳን" እንደ ሽፋን አትጠቀምበት። ድካምህ ለሀራም ስራዎች ሰበብ ሊሆን አይገባም። ⚠️ወዳጄ ሰላት የመጨረሻው ቀይ መስመርህ ናት! መንፈስህ ቢዝል፣ ልብህ ቢደርቅና ስሜትህ ቢያሸንፍህ እንኳ ሰላትህን በፍጹም እንዳትለቅ! ሰላት በአንተና በአላህ መካከል ያለ የመጨረሻው የቃል ኪዳን ገመድ ነው። ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ *«በእኛና በእነሱ(በካፊሮች) መካከል ያለው ቃል ኪዳን ሰላት ነው፤ የተዋትም በእርግጥ ካደ ከፈረ።»* ✨ በየቀኑ ለነፍስህ ንገራት!"ነፍሴ ሆይ! ብትደክሚም ዋጅቦችን አትተይ፤ ብትሰለችም ከአላህ አትራቂ። ዛሬ ብትወድቂ ነገ ተነስተሽ ታገዪ፤ ዋናው ነገር አላህ ዘንድ በሽንፈት ሳይሆን በሙከራና በትግል ላይ ሆነሽ መገኘትሽ ነው!"በላት አላህ በቀጥተኛው መንገድ ላይ የምንጸና፣ ስንወድቅም ፈጥነን የምንነሳ ባሮች ያድርገን። የቴሌግራም ቻናል፦ t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy

የጧት መልዕክት👇 ጧት ሲመጣ አላህ ሌላ ዕድል ሰጥቶናል። ትናንት ያልተሳካውን ዛሬ እንደገና ለመጀመር፣ የደከመውን ልብ ለማሳረፍ፣ የራቀንን ከአላህ ጋር ለማቀራረብ። አላህ ይላል፦ ﴿ وَالصُّبْ
የጧት መልዕክት👇 ጧት ሲመጣ አላህ ሌላ ዕድል ሰጥቶናል። ትናንት ያልተሳካውን ዛሬ እንደገና ለመጀመር፣ የደከመውን ልብ ለማሳረፍ፣ የራቀንን ከአላህ ጋር ለማቀራረብ። አላህ ይላል፦ ﴿ وَالصُّبْحِ إِذَا تَنَفَّسَ ﴾ «ንጋትም በሚተነፍስ ጊዜ እምላለሁ።» ስለዚህ ዛሬን በተስፋ ጀምሪ። የልብሽን ሸክም ለአላህ አስረክቢ፤ የማትችዪውን እሱ ያስችልሻል፣ የማታውቂውን መንገድ እሱ ያሳይሻል። አዲስ ጧት ነው… አዲስ ተስፋም አለ። አላህዬ ዛሬን ከትናንት የተሻለ ያድርግልን። አሚን።

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ፕሮግራማችን ቀጥታ ስርጭት ☎️ የመጀመሪያው ፕሮግራም ተ ጀ መ ረ በኡስታዝ ኸድር ቢን አህመድ ሐፊዘሁላሁ ተዓላ ገባ ገባ በሉ ሸር ሸር አድርጉ https://t.me/+eBmwYuwue7xiZTY0 https://t.me/+eBmwYuwue7xiZTY0

🔭 ዛሬ ምሽት 3:00 እንዳያመልጣችሁ ! ሳምንታዊ የጥያቄና መልስ ውድድር ዛሬ ምሽት 3:00 ላይ ይቀጥላል። ✈️ ይሳተፉ፣ ይማሩ፣ እውቀትዎን ይፈትሹ ይሸለሙ ! ለመቀላቀል እና ለመሳተፍ ከታች ይጫ
🔭 ዛሬ ምሽት 3:00 እንዳያመልጣችሁ ! ሳምንታዊ የጥያቄና መልስ ውድድር ዛሬ ምሽት 3:00 ላይ ይቀጥላል። ✈️   ይሳተፉ፣ ይማሩ፣ እውቀትዎን ይፈትሹ ይሸለሙ ! ለመቀላቀል እና ለመሳተፍ ከታች ይጫኑ  👇 👉 t.me/FKR_ESKE_JENET

+1
​صَلُّوا عَلَى حَبِيبِكُمْ ​ ​اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ وَبَارِكْ عَلَى نَبِيِّنَا مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِهِ وَصَحْبِهِ أَجْمَعِينَ