قناة أبي الفردوس نظيف بن علي الحبشي
الذهاب إلى القناة على Telegram
ይህ የወንድም አቡል_ፊርደውስ ቻናል ነው! በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል ላይ፦ 。አስተማሪ የሆኑ ሸሪዐዊ ትምህርቶች፣ 。ልብን የሚያርሱና እውቀትን የሚጨምሩ ፈዋኢዶች፣ 。ወቅታዊ የዲን ምክሮች በስፋት ይቀርቡበታል። አሁኑኑ ይቀላቀሉን፣ ለወዳጅ ዘመዶዎም ያጋሩ! https://t.me/nezifali123
إظهار المزيدلم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
329
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-17 أيام
+330 أيام
أرشيف المشاركات
Repost from قناة أبي الفردوس نظيف بن علي الحبشي
📚 የሚፍታሁ ተጅዊድ ደርስ 📚
ዛሬ እንደሚታወቀው ከምሽቱ 3:30 (በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር) የቀጥታ ስርጭት የተጅዊድ ትምህርት (ደርስ) አለን።
📖 የደርሶቹ መለቀቂያ ቻናል:
ቀደም ብለው የተለቀቁ ደርሶችን ለመከታተል ወይም ለተጨማሪ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦
👉 https://t.me/nezifali123
💬 ማሳሰቢያ:
እባክዎ መልዕክቱን ለሌሎችም ሼር (Share) በማድረግ ተደራሽ ያድርጉ፤ የአጅሩ ተካፋይ ይሁኑ!
የዑጁብ (በራስ የመመካት/የመደነቅ) በሽታ መድሃኒት
ምስጋና ሁሉ ለአላህ ይገባው፤ በላከው መልእክተኛ፣ በቤተሰቦቻቸው እና በባልደረቦቻቸው ላይ ሰላምና እዝነት ይውረድ።
ከዚህ በመቀጠል፡
አስ-ሰመርቃንዲ «ተንቢሁል ጓፊሊን» (ገፅ 252) በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ እንዲህ ብለዋል፡
«በልቡ ውስጥ ያለውን ‘ዑጁብ’ (በራስ የመመካትና የመደነቅ ስሜት) መስበር የሚፈልግ ሰው አራት ነገሮችን አጥብቆ መያዝ አለበት፡1.ስኬቱን ሁሉ ከአላህ ብቻ እንደሆነ ማየት፡ መልካም የመስራት እድልና ስኬት (ተውፊቅ) ከአላህ ዘንድ የተቸረው መሆኑን የተገነዘበ ሰው፣ አላህን በማመስገን (ሹክር) ይጠመዳል እንጂ በራሱ ጥረት እንደመጣ አድርጎ አይኮራም። 2.አላህ የለገሰውን እልፍ አእላፍ ጸጋዎች መመልከት፡ የጌታውን የውለታ ብዛት ያየ ሰው፣ ያንን በማመስገን ስለሚጠመድ የሰራው መልካም ስራ ምንም ያህል ቢሆን በጸጋዎቹ ፊት አነስተኛ ሆኖ ይታየዋል፤ በራሱ ስራ ከመመካትም ይታደገዋል። 3.ስራው እንዳልተቀበለለት መፍራት፡ መልካም ስራው በአላህ ዘንድ የመቀበሉን ነገር በመስጋትና በመፍራት የተጠመደ ሰው፣ በራሱ የመደነቅ ቦታ አይኖረውም። 4.ያለፉ ወንጀሎቹን ማሰብ፡ ከዚህ ቀደም የፈጸማቸውን ስህተቶች የሚያስታውስና የመጥፎ ስራዎቹ ሚዛን ከመልካም ስራዎቹ በላይ ከብዶ እንዳይገኝ የሚሰጋ ሰው፣ በራሱ መመካቱ ይረግፋል። ደግሞስ በቂያማ ቀን ከመጽሐፉ ምን እንደሚወጣ ሳያውቅ ሰው እንዴት በራሱ ስራ ይደነቃል? የሰው ልጅ እውነተኛ ስኬቱና ደስታው የሚለየው እኮ መጽሐፉን በእጁ ተቀብሎ ካነበበ በኋላ ነው!»
ኢማም አህመድ «አል-ዙህድ» በተሰኘው መጽሐፋቸው (ቁ. 2353) ላይ እንደዘገቡት፡ረጃእ ቢን ሀይዋ እንዲህ ብለዋል፡ «ሞትን አብዝቶ የሚያስታውስ ሰው፣ የዱንያን ሀሰተኛ ደስታና ምቀኝነትን መተው አይቀርም።» እኔም እላለሁ፡ ሞትን ማሰብ ኩራትንና በራስ መመካትንም (ዑጁብንም) ጭምር ያጠፋል! https://t.me/nezifali123/221
علاج العُجُب
الحمد لله والصلاة والسلام على رسول الله وعلى آله وصحبه ومن والاه
أما بعد :
قال السمرقندي في تنبيه الغافلين ص252 :"
من أراد أن يكسر العجب فعليه بأربعة أشياء:أولها: أن يرى التوفيق من الله تعالى، فإذا رأى التوفيق من الله تعالى فإنه يشغل بالشكر ولم يعجب بنفسه. الثاني: أن ينظر إلى النعماء التي أنعم الله بها عليه فإذا نظر في نعمائه اشتغل بالشكر عليها واستقل عمله ولم يعجب به. الثالث: أن يخاف أن لا يتقبل منه، فإذا اشتغل بخوف القبول لا يعجب بنفسه. الرابع: أن ينظر في ذنوبه التي أذنب قبل ذلك، فإن خاف أن ترجح سيئاته على حسناته فقد قل عجبه، وكيف يعجب المرء بعمله ولا يدري ماذا يخرج من كتابه يوم القيامة؟ وإنما يتبين عجبه وسروره بعد قراءة الكتاب "
قال أحمد في الزهد [ 2353]:حَدَّثَنِي حَجَّاجٌ ، عَنِ الْمَسْعُودِيِّ ، عَنِ ابْنِ عُتْبَةَ ، عَنْ رَجَاءِ بْنِ حَيْوَةَ قَالَ : مَا أَكْثَرَ رَجُلٌ ذِكْرَ الْمَوْتِ إِلاَّ تَرَكَ الْفَرَحَ وَالْحَسَدَ. أقول : والعجب أيضاً ! منقول من أبي جعفر https://t.me/nezifali123/220
https://forms.gle/v3AteFBu6izr2rEA7
የፊደላት ባህሪ ፈተና ነው እየገባቹህ ተፈተኑ
https://t.me/nezifali123/203
ለወንድማችን ኡስታዝ ዐብዱልመናን
الله أكبر الحمد الله
🥰أخي الفاضل
🎉بارك الله لكما وبارك عليكما وجمع بينكما في خير
🎉🎊 አሏህ የተባረከ ትዳር ያድርግልህ !!
قال ابن شاهين رحمه الله تعالى في كتابه شرح مذاهب أهل السنة (33):
ኢብኑ ሻሂን (አላህ ይዘንላቸውና) «ሸርሑ መዛሂቢ አህሊስ-ሱና» በተሰኘው መጽሐፋቸው ቁጥር (33) ላይ እንዲህ አሉ።
حَدَّثَنَا عَبْدُ اللَّهِ بْنُ سُلَيْمَانَ بْنِ الْأَشْعَثَ السِّجِسْتَانِيُّ،
ዐብዱልላህ ኢብኑ ሱለይማን ኢብኒል-አሽዐስ አሲጂስታኒ ነገሩን፡
حَدَّثَنِي أَبِي، عَنْ سُلَيْمَانَ بْنِ حَرْبٍ، قَالَ: አባቴ ከሱለይማን ኢብኑ ሀርብ ዘግቦልኝ እንዲህ አለ፡
قَالَ حَمَّادُ بْنُ زَيْدٍ:
ሐማድ ኢብኑ ዘይድ እንዲህ አለ፡
"مَثَلُ الْجَهْمِيَّةِ مَثَلُ رَجُلٍ قِيلَ لَهُ: أَفِي دَارِكَ نَخْلَةٌ؟ قَالَ: نَعَمْ.
«የጀህምያዎች ምሳሌ፤ አንድን ሰው "በቤትህ ውስጥ የተመር ዛፍ አለን?" ተብሎ ተጠይቆ "አዎ አለ" እንዳለው ሰው ምሳሌ ነው፤
قِيلَ: فَلَهَا خُوصٌ؟ قَالَ: لَا.
"ታዲያ ዝንጣፊ/ቅጠል አላት?" ተባለ፤ "የላትም" አለ።
قِيلَ: فَلَهَا سَعَفٌ؟ قَالَ: لَا.
"ታዲያ የዘንባባ ጭራንፎ አላት?" ተባለ፤ "የላትም" አለ።
قِيلَ: فَلَهَا كَرَبٌ؟ قَالَ: لَا.
"ታዲያ የግንድ ቅርፊት አላት?" ተባለ፤ "የላትም" አለ።
قِيلَ: فَلَهَا جِذْعٌ؟ قَالَ: لَا.
"ታዲያ ግንድ አላት?" ተባለ፤ "የላትም" አለ።
قِيلَ: فَلَهَا أَصْلٌ؟ قَالَ: لَا.
"ታዲያ ስር አላት?" ተባለ፤ "የላትም" አለ።
قِيلَ: فَلَا نَخْلَةَ فِي دَارِكَ.
"እንግዲያውስ በቤትህ ውስጥ ምንም የተመር ዛፍ የለም!" ተባለ።
هَؤُلَاءِ الْجَهْمِيَّةُ، قِيلَ لَهُمْ: لَكُمْ رَبٌّ؟ قَالُوا: نَعَمْ.
እነዚህም ጀህምያዎች እንደዚሁ ናቸው፤ "ጌታ አላችሁን?" ተብለው ሲጠየቁ "አዎ" ይላሉ፤
قِيلَ: يَتَكَلَّمُ؟ قَالُوا: لَا.
"ይናገራልን?" ሲባሉ "አይናገርም" ይላሉ።
قِيلَ: فَلَهُ يَدٌ؟ قَالُوا: لَا.
"እጅ አለው?" ሲባሉ "የለውም" ይላሉ።
قِيلَ: فَلَهُ قَدَمٌ؟ قَالُوا: لَا.
"እግር አለው?" ሲባሉ "የለውም" ይላሉ።
قِيلَ: فَلَهُ إِصْبَعٌ؟ قَالُوا: لَا.
"ጣት አለው?" ሲባሉ "የለውም" ይላሉ።
قِيلَ: فَيَرْضَى وَيَغْضَبُ؟ قَالُوا: لَا. "ይወዳል፣ ይቆጣል?" ሲባሉ "አይቆጣም/አይወድም" ይላሉ።
قِيلَ: فَلَا رَبَّ لَكُمْ"
"እንግዲያውስ እናንተ ምንም ጌታ የላችሁም!" ይባላሉ።»
https://t.me/Abumuhemed1
اللامية المنسوبة إلى شيخ الإسلام
بصوت الأخ أبي الفردوس الحبشي وفقه الله
https://t.me/nezifali123/199
ليلة الجمعة ويومها.
إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا (56)
أكثروا من الصلاة والسلام على خليل الله وحبيبه ورسوله وجليسه على العرش يوم القيامة.
صلى الله عليه وسلم.
📚 የሚፍታሁ ተጅዊድ ደርስ 📚
ዛሬ እንደሚታወቀው ከምሽቱ 3:30 (በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር) የቀጥታ ስርጭት የተጅዊድ ትምህርት (ደርስ) አለን።
📖 የደርሶቹ መለቀቂያ ቻናል:
ቀደም ብለው የተለቀቁ ደርሶችን ለመከታተል ወይም ለተጨማሪ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦
👉 https://t.me/nezifali123
💬 ማሳሰቢያ:
እባክዎ መልዕክቱን ለሌሎችም ሼር (Share) በማድረግ ተደራሽ ያድርጉ፤ የአጅሩ ተካፋይ ይሁኑ!
