የክብሩ ነፀብራቅ✨
الذهاب إلى القناة على Telegram
ልጁም የእግዚአብሔር የክብሩ ነጸብራቅና የአምላካዊ ባሕርዩ አምሳያ ነው፡፡ ወልድ አምላክ በመሆኑም ይህን ዓለም በሥልጣኑ ኃይል ይቆጣጠረዋል ፤ በሥርዓት እንዲመራም ያደርገዋል ። እኛን ከኃጢአት ለማንጻትና የተመዘገበብንን የበደል ደብዳቤ ለመደምሰስ ከሞተ በኋላ ፥ አሁን በአባቱ ጎን ባለው ከፍተኛ ሰማያዊ የክብር ቦታ ተቀምጧል ። [ሕያው ቃል ዕብራውያን 1:3]
إظهار المزيدلم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
358
المشتركون
+324 ساعات
+137 أيام
+9030 أيام
أرشيف المشاركات
359
Another blessing is on the way. Can't wait to experience Christ through this upcoming song.
359
A Life in the Emotion Versus a Life in the Spirit
The Christian life should not have any period of spiritual coldness. However, in order to teach us the function of faith and the will, in the practical experience of our spiritual life, God often allows spiritual depression to come to us. When our faith is put to the test, the outward, burning sensations may be gone, but we should not be discouraged. A Christian life is full of joy during times of abundance, and it is at least full of peace during other times. It is wonderful to have special joy and happiness, but it is not abnormal if one does not have these feelings some of the time. When these feelings are gone, an inward peace should be sustained. It is not necessary for us to constantly feel a sense of enlightenment and joy. It is more important to be without barrier or burden in our spirit and to have no nagging feeling that God is far from us. If there are such barriers, they must be removed.
On the one hand, it is easy to develop barriers between us and God. These barriers can be removed, and the way to remove them is by foot-washing. On the other hand, there is nothing unusual about not having third-heaven, supernatural feelings of elation. We should not seek for these supernatural experiences all the time. The first time you pass through a big crisis, you may have some supernatural sensations. If you have such an experience, you should thank the Lord. But such an experience will not last for lofor
For example, when you were first saved, when you first experienced the overcoming life, or when you first consecrated yourself, you may have been extremely exuberant. But these feelings do not remain with you forever. On the one hand, we have to remove all barriers in our fellowship with the Lord, and on the other hand, we have to live by faith when this special joy is absent. Special and extraordinary joy is like the over-intoxication of wine, whereas the freshness of life is like the invigoration of spiritual energy.
Extracted from “Talks (2)”, CWWN, (Set 2) Vol. 42: Conferences, Messages, and Fellowship (2), Chapter 40, a message given by Brother Watchman Nee at 17 October 1936 In the dormitory, Kulangsu, Amoy, published by Living Stream Ministry.
359
ከላይ የቀጠለ......በዕድሜያቸው ማጠናቀቂያ ላይ የሁለቱ የውስጥ ሰላምና ፍጻሜ ፍጹም ተራራቀ። ሰሎሞን በውጭ የሚታየውን፣ በዓለም ላይ ወደር የሌለውን ታላቅ የወርቅ መቅደስ ቢሠራም፣ በዕድሜው መጨረሻ ላይ ግን የራሱ የውስጥ መቅደስ—ማለትም ልቡ—በባዕዳን አማልክትና በምድራዊ ፍላጎቶች ረክሶና ዝሎ አረፈ! ብክነት!። ዳዊት ግን በውጭ የሚታይ የድንጋይ መቅደስ ለመሥራት ባይታደልም፣ የውስጥ ማደሪያው እስከ መጨረሻው ትንፋሹ ድረስ ለእግዚአብሔር የታመነ፣ ሕያውና ሁሌ የሚቀጣጠል የሚነድድ ነበር[ትኩስ እንደሆነ ዕድሜውን ጨረሰ🔥]። ለዚህም ነው ሰሎሞን በከንቱነት፣ በማያልቅ ምኞቱና በጣዖት አምልኮ ዘመኑን አስበልቶ አጠናቅቆ የገነባው ታላቅ ብልጽግና ከእሱ በኋላ ለትውልድ ያተረፈው የመንግሥት ክፍፍልና የጦርነት ቀንበር ሲሆን፤ ዳዊት ግን ስሙ ከእግዚአብሔር ዘላለማዊ ዕቅድ ጋር ተሳስሮ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ ሲመጣ “የዳዊት ልጅ” [ማቴዎስ 1፥1] ተብሎ የተጠራው። ጌታ ሆይ ጊዜው ሳይመሽ ከሃሳብህ ጋር ስፋን አቆራኘን አጣብቀን!🤲🙇♂️🙇 በመክብብ 1 እና 2 የምናየው ሰሎሞን፣ በምድር ላይ ያለውን ነገር ሁሉ የጨረሰ የተሳካለት ነገር ግን ውስጡ ባዶ የሆነ “ባለጸጋ ድሃ” ሲሆን፤ ዳዊት ግን በምድረ በዳ የተንከራተተ፣ ነገር ግን እግዚአብሔር የውስጥ ሙሉነቱ የሆነ “ባለጠጋ” ነው። ዓለምን በጥበብና በሃብት እንደልቡ የቃኘው ሰሎሞን በመጨረሻ መክብብን ሲያጠናቅቅ የደረሰበት መደምደሚያ፣ አባቱ ዳዊት ገና በወጣትነቱ በበግ ጥበቃ ላይ እያለ ያውቀው የነበረውን መሠረታዊ እውነት ነው፦ “የነገሩን ሁሉ ፍጻሜ እንስማ፤ ይህ የሰው ሁለንተናው ነውና፤ እግዚአብሔርን ፍራ፥ ትእዛዙንም ጠብቅ።” [መክብብ 12፥13] ሰሎሞን ዘመኑን በሙሉ የሕይወትን ትርጉም ለመረዳት ሲደክም ኖረ፤ ዳዊት ግን ዘመኑን በሙሉ የሕይወትን ባለቤት በማወቅ ውስጥ ኖረው።
የእግዚአብሔር ህልውና ከህይወት ኪሳራ ያድናል! 🤲🙇♂️🔥🙌🌨️☁️በመጨረሻም ይህንን እላለው፦ የሰው ልጅ ሕይወት ወይ ለገዛ ስሙ የሚቆም መታሰቢያ፣ ወይም ለፈጣሪ አሳብ የሚሆን የክብር መሣሪያ ነው! የሰው ልጅ ስኬት የሚለካው ለራሱ ባከማቸው ነገር ሳይሆን፣ በዘመኑ የፈጸመው የማንን ሐሳብ ነው[የራሱን ወይስ የጌታውን] በሚል መለክያ ብቻ ነው። የእግዚአብሔርን ልብ ሳንሰማ የሚናገኘው ነገር ሁሉ ከማጣት የከፋ ነው፣ ከፈቃዱ ውጭ ያለ ረጅም ዕድሜ ስቃይና ድካም ማብዣ ነው፣ ያለ እሱ ምክር መሮጥ ትርፉ የነፍስ ዝለት ነው፣ የእግዚአብሔር ልብ ያላረፈበት ዕድሜ እሳት ስያገኘው እንደሚጠፋ እንደ ትልቅ እስር ጭድ ነው። ወዳጆች ሆይ፦ በመሮጥ እና በመፍጠን ብቻ በምታምን ዓለም ወዴት እየፈለስን እንደሆነ ማሰብ ነፍስን ማትረፍ ነው፣ የምታደርጉትን ማንኛውንም ነገር ለምን እና ለማን እንደምታደርጉት ማስተዋል ጥበብ ነው። ፈቃዱ በለለበት አትሰንብቱ! Ruuun, run away! @አቤንኤዘር ማቴዎስ [Abi Kidan]
359
በማትረፍ መክሰር
የዳዊትና የልጁ ሰሎሞን ታሪክ በብሉይ ኪዳን ያከተመ፣ ጊዜ ያለፈበትና የጥንት ታሪክ ብቻ አይደለም። በጥልቀት ካስተዋልነው ይህ ታሪክ ዛሬም በውስጣችን የሚጮኽ፣ የሁላችንንም የዕለት ተዕለት የውስጥ ትግል የሚያሳይ፣ እግዚአብሔር ለእኛ የሚናገርበት ሕያው ታሪክ ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ የዳዊትን ሕይወት በአንድ አጭር ዓረፍተ ነገር ሲቋጨው “ዳዊት በዘመኑ የእግዚአብሔርን አሳብ ካገለገለ በኋላ አንቀላፋ” [የሐዋርያት ሥራ 13፥36] ይላል። እጅግ የሚያስገርመው ደግሞ ሰሎሞን የሕይወቱ መገባደጃ ላይ በስተርጅናው ዕድሜው የጻፈው መክብብ ምዕራፍ 1 እና 2 የገዛ ልቡ የፈተለውን የማያልቅ ምኞት፣ የጥበብና የሃብትን ጫፍ ለመድረስ ያደረገውን ብርቱ ጥረት የሞላበት ብክነትና የውስጥ ጩኸት[ባዶነት] ገልጦ ያሳያል። በሰዋዊ ሚዛን ሰሎሞን ከአባቱ ከዳዊት በብዙ ነገር እጥፍ ይበልጥ ነበር፡—በዕውቀት፣ በናኘ ሀብት፣ በንጉሣዊ ቅንጦትና በምድራዊ ሥልጣን፣ ባገባቸው ሴቶች ብዛት[imagine 1000] ዳዊትን ይበልጠው ነበር ግን........። ነገር ግን በእግዚአብሔር መለኮታዊ ሚዛን ላይ ሲቀመጡ የሁለቱ ሕይወት የሰማይና የምድርን ያህል ይራራቃል። የዳዊት ሕይወት በእግዚአብሔር ፊት ትልቅ ክብደት(Weight) ሲኖረው[ሚዛን ስደፋ]፣ የሰሎሞን ሕይወት በብዛት “ከንቱነት”(vanity) የወረረው፣ “ነፋስ እንደመከተል ነው” እንዳለው እንደዛው ሆኖ ተገኘ።🥹
ይህ ትልቅ መራራቅ የመጣው በአንድ ቀን ክስተት ሳይሆን የመኖራቸውን ትርጉም ከመዘኑበትና ሕይወታቸውን ካስኬዱበት ረጅም መንገድ ነው። ዳዊት የራሱ ድብቅ ዓላማ ወይም የግል ሥርወ-መንግሥት የመመስረት ፍላጎት አልነበረውም Even ንጉስ ለመሆን ከመቀባቱ በፊት እንኳን ንጉስ አድርገኝ ብሎ ጸልዮ አያውቅም፤ ጉዳዩ በሙሉ እግዚአብሔርን ማወቅና ህልውናውን መጠማት መለማመድ ብቻ ነበር፤ ከተቀባም በኋላ ሕይወቱ በሙሉ እግዚአብሔር ለእሱና ለሕዝቡ ለእስራኤል የነበረውን ዘላለማዊ ዕቅድ የመፈጸም ታማኝ ጉዞ ነበር። ዳዊት ህይወቱን የተረጎመው[define ያደረገው] ከአምላኩ አንጻር ነበር።እግዚአብሔርንም ያየው በብዙ ምርምርና ድካም የሚደረስበት እጅግ እሩቅ አድርጎ ሳይሆን እንደ ቅርብ ጓደኛ፣ ሁል ጊዜ ፊትለፊቱ እንደሚያየው እንደ መልካም እረኛ፣ ሁሉ ነገሩን የልቡን አውጥቶ እንደሚተነፍስለት እንደ ልብ ወዳጅ አድርጎ ነው። ለዳዊት እግዚአብሔር እጅግ ቅርብ ነው። ከዚህ የተነሳ ልቡ ከእግዚአብሔር ጋር በፍቅር ተጠላልፎ ነበር። ሰሎሞን ግን በመክብብ 1 እና 2 ላይ “ሠራሁልኝ”፣ “አከማቸሁልኝ”፣ “ልቤን ደስ አሰኘሁት” [መክብብ 2፥4-10] እያለ በገነባው የሃብት ምሽግ ውስጥ ለብቻው ተዘግቶ፣ ራሱን በራሱ ድካም ለማርካት የሚታገል ብቸኛ ሰው ነበር ምክንያቱም በሂደት የሕይወቱን ትርጉም ከእግዚአብሔር ላይ አንስቶ በምድራዊ ክብር ውስጥ መፈለግ ጀምሮ ነበር[at the end most probably he repented]። እግዚአብሔር የሰጠውን ታላቅ አእምሮ ተጠቅሞ የሕይወትን ምሥጢር በጥበብና በምክንያት[reasoning] ብቻ ሊፈታት ቢሞክርም፣ የሰው ልጅ አእምሮ ያለ መለኮታዊ ፍቅርና መገለጥ መጨረሻው ባዶነት፣ ድካምና ተስፋ መቁረጥ መሆኑን በገዛ ሕይወቱ በተግባር መሰከረልን። ሰሎሞን የገዛ ልቡን ምኞት ሲያሳድድ፣ ዳዊት ግን የእግዚአብሔርን ሐሳብ አገልግሎና ፈጽሞ አለፈ። መታደል አይደል!✨🙌
ይህ ለሕይወታቸው ትርጉም የሰጡበት መንገድ በእግዚአብሔር ፊት ሕይወታቸው ትልቅ የዋጋ ልዩነት እንዲፈጠር አደረገ። የሚገርመው እግዚአብሔር በሰሎሞን፡ ዓለምን ባስደነቀ ስኬቱ፣ ብዙዎች ለመስማት በሚጓጉለት ጥበቡ፣ በያዘውና እንደ ተራ ድንጋይ በረከሰ ወርቅ ክምችት፣ ወይም በሠራው ታላቅ መቅደስ ቅንጣት ታህል አልተደነቀም ትኩረቱን አልሳበም። ነገር ግን እግዚአብሔር በዳዊት ልብ ልቡ አርፎ ነበር፣ የዳዊት ልብ በእግዚአብሔር ፊት ትኩረት እገኘ💖! ለዚህ ነው ሁልጊዜ ከእሱ በኋላ የተነሱትን ነገሥታት ሲመዝን ዳዊትን እንደ ዋና እና ፍጹም መለኪያ ያነሳ የነበረው። ምክንያቱም ሰሎሞን በመክብብ 2 ላይ ሁሉንም ምድራዊ ተድላ፣ ዕውቀትና ስኬት በሕይወት ላብራቶሪው ፈትኖና ጨምቆ ሲጨርስ ያገኘው ውጤት “ተስፋ መቁረጥ” ብቻ ነበር፤ በጥበቡና በሀብቱ ምሽግ ውስጥ ራሱን የቻለና የቁም ነገር ባለቤት ስለመሰለው ልቡ በእግዚአብሔር ፊት አልተሰበረም ነበር። ዳዊት ግን ፍጹም[Perfect] ሰው አልነበረም፤ እንደማንኛውም ሰው በትልልቅ ኃጢአቶች ውስጥ ወድቋል፣ ስህተቶችንም ሠርቷል። ነገር ግን በሳተና በወደቀ ቁጥር ልቡ ተሰብሮ፣ በእውነተኛ ንስሐ ወደ እግዚአብሔር ይሮጥ ነበር[የአምላኩ ጥገኛ 🥹🥰]። እግዚአብሔር በዳዊት ሕይወት ውስጥ የወደደው የማይሳሳተውን ማንነቱን ሳይሆን ፍጹም ትሑትና ምስኪን ጥገኝነቱን ነው🎯። “የእግዚአብሔር መሥዋዕት የተሰበረ መንፈስ ነው፤ የተሰበረውንና የተዋረደውን ልብ እግዚአብሔር አይንቅም” [መዝሙር 51፥17]
359
ለርሃብተኞች......
እውነተኛ እና ንጹህ የሆነ[ከአንድ ሃይማኖት ጎራ ያለፈ] የእግዚአብሔር ክብር ርሃብ ላላቸው፣ የክርስቶስ አካል እና ሁለንተናዊት የቤተ-ክርስቲያን መታደስ ናፍቆት ላላቸው፣ የትውልዳችን መንፈሳዊነትና ዘመናዊነት የሚመስል ግን እግዚአብሔር አልባ የሆነ ልምምድም ሆነ ከንቱ መንፈስ አልባ የሰው ስርዓት በመንፈስ ቅዱስና በመጽሐፍ ቅዱስ ብርሃን ጠርቶ የማየት ጉጉት ላላቸው፣ በአባቶቻችን ዘመን የነበረው ሕልውናው[Presence]፣ የሚዳሰስ ክብሩ፣ ከሰው እውቀትና ጥበብ ሳይሆን ከሰማይ የሆነ አሰራርና ግለት በዘመናችን ለምን ቀረ ብለው በቅንዓት ለሚቀጣጠሉ፣ የመንግስቱ ክብር፣ የቤተ-ክርስቲያን አስፈሪነቷ ወደየት ገባ፣ የመንፈስ ቅዱስ የተገለጠ ኃይሉ ለምን በኛ ዘመን ተዳፈነ ለሚሉ፣ ባዶ ጩኸትና ወከባ ሳይሆን እውነተኛ ክብሩ፣ እውነተኛ ኢየሱስ ለናፈቃቸው ለዘመኔ ለእኔ ቢጤ ርሃብተኞች ብቻ! [በትህትና ሌሎች Scroll አድርጉና ዕለፉት]፦
ከሰሞናዊ ግርግር እና ውዝግብ የተነሳ “ርሃባችሁ” እንዳይከስም ጠብቁት! ለክብሩ ያላችሁን ጥማታችሁን “ምንም!” እንዲነካባችሁ አትፍቀዱለት! ለብዙዎች ሞኝነት፣ አእምሮ ማጣትና ቅዱስ ቃሉን አለማወቅ የሚመስለውን ቅዱስ ርሃባችሁን ከበፊቱ ይልቅ አሳድጉት[በጸጋ]፣ አወቅን እንደሚሉት ሰዎች “ርሃባችሁ ላይ አትደጉ!”፣ ተምረናል[ከሰው] እንደሚሉት እንደ ጥበበኞቹ¡ ለእግዚአብሔር ባላችሁ ስስነታችሁ ላይ አትደጉበት። በመቀጣጠላችሁ[fervency] ላይ ውኃ ለመቸለስ በሚሯሯጡ በአንዳንዶቹ፣ የጸሎት ግለታችሁን ልማዳዊና[Normal] ስርዓታዊ ብቻ ለማድረግ በእውቀት መሳይ ውድቀት ለማጥመድ በሚፈልጉ፣ መንፈስ ቅዱስ በሐዋርያት ዘመን፣ በአባቶች ዘመን እንደሰራ ታሪክ ብቻ በሚያወሩ ነገር ግን በእኛ ዘመን ያ አቅሙን በመጠራጠርና ባለማመን በጥቅስ ለመሸፋፈን በሚፈልጉት ምክንያት በውስጣችሁ ጌታ ያስቀመጠው የሚጎተጉታችሁ ቅዱስ ርሃብ እንዳይሞት በብርቱ ጸሎትና በጸጋው ጠብቁት!
በእርግጥም እየሆኑ ያሉት ነገሮች ተስፋ አስቆራጭ ናቸው፣ የትውልዳችን ውድቀት አስፈሪ ነው፣ የቤተ-ክርስቲያን ሙቅ ወይም በራድ አለመሆኗ እጅግ አሳሳቢ ነው፣ ከልባችን ጀምሮ እስከ መድረኮቻችን ድረስ ኢየሱስ ክርስቶስ መታጣቱ አስደንጋጭ ነው፣ የቤተ-ክርስቲያን ድፍረት ማጣት፣ ማመቻመች፣ ከምድራዊ ነገሮች ጋር መጋባቷ አሳዛኝ ነው። ነገር በዚህ ሁሉ ድንግዝግዝ መሐል ክብሩን የሚራቡ ሰዎች መኖራቸው አንድ ልብ የሚያሞቅ ነገር ነው ምክንያቱም እግዚአብሔር እርሱንበማይራቡ ሰዎች ሰርቶ አያውቅምና! ርሃብተኞች ከፊት ይልቅ የምትጮሁበት ጊዜ አሁን ነው።
ከአንድ ወዳጄ ጋር ሳወራ ያየሁት ነገር በጣም ልቤን ነው የያዘው። እንዲህ ነው፦ ያው የሰሞኑን መግለጫዎችን ሰምታችሁታል[የሚደገፍ ግን ያልጠራ ነው]። ወዳጄ ከአንድ ጓደኛው ጋር ስለ መንፈስ ቅዱስ እና ጸጋ ስጦታዎች በ Telegram እያወራ ነበር እና ውይይታቸው ጓደኛውን “በእግዚአብሔር ታምናለህ?” ይለዋል፣ ጓደኛው “አዎ” ይላል፣ ቀጥሎ “ከሆነ እግዚአብሔር ዛሬም እንደሚሰራ ታምናለህ?” ይለዋል፣ ሲመልስለት “አላውቅም I don’t Know” ብሎ መለሰለት። አስቡት ይህንን የመለሰለት አሕዛብ ሳይሆን በቤተ-ክርስቲያን ውስጥ ያለ ወጣት ነው🥹። ካለንበት ሁኔታ አንጻር እንደዚህ ያለ እምነት ማጣት፣ መንፈስ ቅዱስን መጠራጠር በእኛ እና ቀጣይ በልጆቻችን ላለመፈጠሩ ምንም ዋስትና የለንም። ለዚሁ ነው መጮኽ ያለብን! ዛሬ የመንፈስ ቅዱስን ቦታ በተለያዩ ሰው ሰራሽ ስርዓቶችና ሃሳቦች ተክተን፣ የእርሱን ቦታ እኛ ሞልተን ነገ አይቀሬ ለሆነ “ትውልድ የለም” ለሚባል ውድቀት በር እየከፈትን እንደሆነ ልብ ማለት አለብን፣ ይህ ትንቢት ወይም መገለጥ ሳይሆንበተለያዩ ታላላቅ ሃገራት በተለያዩ ዘመናት የተፈጸሙ ውድቀቶች ናቸው። መንፈስ ቅዱስ ሁሌ ከኛ ጋር ቢሆንም ብዙ Denominational በሆኑ[im not supporting non denominationalism] አብያተ-ክርስቲያናት መንፈስ ቅዱስ የተረሳ ርዕስ መሆኑ መደበቅ የማንችለው እና ግልጽ ግን ደፍረን የማናወራው እውነት ነው። በጣም በብዙ አብያተ-ክርስቲያናት ኢየሱስ፣ መንፈስ ቅዱስ እና መጽሐፍ ቅዱስ ዳር ይዞ የቆመበት ጊዜ መሆኑ በጣም ግልጽ ነው። የትውልድ ውድቀትንእያየን እንኳን ለምን ይሆናል? መንፈስ ቅዱስ ኃይልህ የት አለ? እያልን አይደለም ይህ ደግሞ እጅግ አሳሳቢው ነገራችን ነው፣ ሁሉን ነገር በእውቀት እና በራሳችን ዘዴ ካላስተካከልን በቀር መንፈስ ቅዱስ የሚፈለግበት ጉዳይ እየጠፋብን ነው።😭
ንጹህ እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ክብሩን የምትራቡ ይህንን እያያችሁ ውድቀት ከመቼውም ጊዜ በላይ የርሃባችሁን መጠን ያለልክ አሳድጉት እግዚአብሔር የሚፈልገው እሱ ነውና! ለመውለድ እንደደረሰች ሴት ምጥ ይያዛችሁ! “አባ ክብርህን” ማለታችሁን ቀጥሉ! እውነተኛ እርሱን የሚራቡ ሰዎች ክብሩ የሚገለጥባቸው ናቸው።
በመጨረሻም እንደ ደካማና እንደ ሞኝ ይህንን እላለሁ “እግዚአብሔር አብ፣ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ” ትናንት ዛሬ እስከ ዘላለም ያው ነው። ትናንት የሰራበት አቅሙ አልደከመም አይደክመውምም! ዛሬ እንደደከምን ትናንትም እንደዚህ እንደነበርን አይምሰላችሁ! ዛሬ በእውቀት መፈላለጥ[I appreciate] ብቻ ሆኖ የሚዳሰስ ሕልውናውን እንዳጣን አይምሰላችሁ፣ የኛ ትውልድ በድካማችን እና በልማድ “ኃይሉን” መካድ ብንዳዳም ኃይሉ እንደዛው ነው አለ! በሃሰተኛ መዝሙር፣ ነብይ፣ ሐዋርያ፣ እረኛ፣ ወንጌላዊ፣ ሰባኪ እና አስተማሪ ተከበን እውነተኛና የክርስቶስ መልክ ያላትን ቤተ-ክርስቲያን ማየት ብናፍቅም፣ ብርቅ ቢሆንብንም “ርሃባችሁን” አስቀጥሉት! እግዚአብሔር ሁል ጊዜም ለርሃብ መልስ አለው!🥹ዘማሪት አስቴር አበበ “በዘመኔ አያለሁ” ያለቻቸው ኃያላን ከተደበቁበት እንዲወጡ ርሃባችሁን አስቀጥሉት! በመንፈስ ቅዱስ ቅንጣት ታህል ጥርጣሬ አይግባችሁ! ርሃባችሁን በቃሉ ተንከባከቡት፣ ኮትኩቱት፣ አሳድጉት! ብቻ ብዙ ነገር ማለት አልፈልግም ግን “ክብሩን መፈለጋችሁን” እንደ አለማደግ ወደሚታዩበት እድገት አትደጉ።
እግዚአብሔር ለርሃብ መልስ አለው!
359
Rev. Dr. Shelvie Summerlin
መፅሐፍ ቅዱሳን ከዘፍጥረት እስከ ራዕይ ከ 1,025 ጊዜ በላይ ደጋግሞ አንብቧል ። በ America ሀገር በ 100 የሚቆጠሩ ቤተክርስቲያንን ተክሏል ።
Bible ይነበብ !🙌
359
መዝሙር 103
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ነፍሴ ሆይ፥ እግዚአብሔርን ባርኪ፥ አጥንቶቼም ሁሉ፥ የተቀደሰ ስሙን።
² ነፍሴ ሆይ፥ እግዚአብሔርን ባርኪ፥ ምስጋናውንም ሁሉ አትርሺ፤
³ ኃጢአትሽን ሁሉ ይቅር የሚል፥ ደዌሽንም ሁሉ የሚፈውስ፥
⁴ ሕይወትሽን ከጥፋት የሚያድናት፥ በምሕረቱና በቸርነቱ የሚከልልሽ፥
⁵ ምኞትሽን ከበረከቱ የሚያጠግባት፥ ጕልማስነትሽን እንደ ንስር ያድሳል።
⁶ እግዚአብሔር ይቅርታ አድራጊ ነው፤ ለተበደሉ ሁሉ ይፈርዳል።
359
እነሆኝ ጌታዬ! 🙇
ከእስራቴ ፈትተሄኝ፣ በደምህ አፅድተኸ አፀድቀኸኝ 🩸፣ በላዬ ላይ ተቀምጠህ ልትከብር ከወደድክ....
እነሆኝ ጌታዬ! 🙇
የክብርህ ዙፋን እኔ ላይ ይዘረጋ ፣ አንተን ተሸክሜ መዞር የማይገኝ ማዕረግ ዕድልም ነው። ✨✨
ልክ እንደ ኦሪቱ ባሪያ፣ ጌታውን ወዶ "ከቤትህ አልወጣም" ብሎ ለዕድሜ ልክ ባርነት በፈቃዱ ጆሮውን እንደሚበሳ ⛓️፣ እኔም በፍቅርህ ተማርኬ ጆሮዬን በስቼ ለዘለዓለም ያንተ የፈቃድህ ባርያ ሆኛለሁ። ስምህን ተሸክሞ፣ ፈቃድህን ተግብሮ፣ አንተን አክብሮና አንግሶ መኖር ክብርም ዕድልም ነው። 💎
አንድ ዕድል ብቻ እንደተሰጠው እና እንደምያመልጠው ሰው እንሰፈሰፋለው ፡ ምቹ ጊዜና ቦታ ሳገኝ ሳይሆን ጊዜና ቦታ ፈጥሬ አገለግልሃለሁ! 🥺❤️
“እንዲህም አላቸው፦ በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ፥ በዚያን ጊዜም የታሰረችን አህያ ውርንጫም ከእርስዋ ጋር ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁ አምጡልኝ።” — ማቴዎስ 21፥2 የኔ ጌታ የኔ ኢየሱስ 🥺🙇❤ 💝 ✒️ Abi-Kidan
359
መንፈሳዊ ጸሎት
አንድ አማኝ በእውነት ወደ መንፈሳዊው ዓለም ሲገባ፣ ምን ያህል ባዶ እንደሆነ ይረዳል፤ ለሌሎች የሚሰጠው የሕይወት በረከት እንደሌለውና በራሱ ውስጥም ጠላትን የሚቃወም አንዳች አቅም እንደሌለው ይገነዘባል። ያኔ በራሱ ተነሳሽነት እግዚአብሔርን የሕይወቱ ምንጭ ያደርገዋል፤ ጸሎትም የማይተው የሕይወቱ ክፍል ይሆናል። እውነተኛ ጸሎት የጸላይውን ባዶነትና የመላሹን (የእግዚአብሔርን) ባለጸግነት የሚገልጽ ነው። አንድ ሰው "ባዶ" እስኪሆን ድረስ ሥጋው በመስቀል ካልተገደለ፣ ጸሎቱ ምን ፋይዳና ዓላማ ይኖረዋል?
መንፈሳዊ ጸሎት ማለት ከሥጋ ያልሆነ ጸሎት ማለት ነው። ይህም አማኙ ራሱ የሚያስበው፣ የሚመኘው ወይም ለማድረግ የሚወስነው ነገር አይደለም። ይልቁንም በእግዚአብሔር ፈቃድ መሠረት የሚለማመደው ነው። መንፈሳዊ ጸሎት በመንፈስ የሚጸለይ ጸሎት ነው። ይህም ማለት አንድ ሰው መጀመሪያ የእግዚአብሔርን ፈቃድ በመንፈሳዊ ግንዛቤው (Intuition) ይረዳል፣ ከዚያም ስለዚያ ጉዳይ ይጸልያል። መጽሐፍ ቅዱስ
"በጸሎትና በልመና ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ" (ኤፌ. 6፡18)በማለት ያዝዛል። በመንፈስ ካልጸለይን በሥጋ እየጸለይን ነው። ወደ እግዚአብሔር በምንቀርብበት ቅጽበት አፋችንን መክፈት የለብንም፤ ይልቁንም እንድናውቅ የሚፈልገውን ነገር እንዲያሳየንና እንዴት መጸለይ እንዳለብን እንዲያስተምረን መጀመሪያ እግዚአብሔርን መጠየቅ ይኖርብናል። ለምንፈልገው ነገር ደጋግመን መጸለይን ሞክረነዋል፤ አሁን ደግሞ እግዚአብሔር ስለሚፈልገው ነገር ለምን አንጸልይም? በጸሎት ውስጥ ለሥጋ ስፍራ የለውም። ዋናው አንተ የምትፈልገው ሳይሆን እግዚአብሔር የሚፈልገው ነው። በእውነት መንፈሳዊ ያልሆኑ ሰዎች፣ እውነተኛ መንፈሳዊ ጸሎት ሊኖራቸው አይችልም። መንፈሳዊ ጸሎቶች ሁሉ መነሻቸው እግዚአብሔር ነው። ምን መጸለይ እንዳለብን የሚያሳየን እግዚአብሔር ነው። እርሱ ፍላጎቱን ያሳየናል፣ በመንፈሳዊ ግንዛቤያችንም ውስጥ ያንን ጉዳይ እንደ ሸክም እንድንቀበለው ያደርገናል። ይህ የመንፈስ ሸክም ለጸሎት የቀረበልን ጥሪ ነው። ነገር ግን ብዙ ጊዜ በቸልተኝነት ምክንያት በመንፈሳችን ውስጥ የሚመጡ ጥቃቅን ስሜቶችን እናመልጣለን። በመንፈሳችን ካለን ሸክም በላይ መጸለይ የለብንም። በመንፈሳዊ ግንዛቤ (Intuition) ያልተጀመረና ያልተነሳሳ ማንኛውም ጸሎት፣ ከአማኙ ራሱ የሚመነጭ የሥጋ ጸሎት ነው። ዋችማን ኒ (Watchman Nee) "መንፈሳዊው ሰው" (The Spiritual Man) ከተሰኘው መጽሐፍ የተወሰደ
