የክብሩ ነፀብራቅ✨
الذهاب إلى القناة على Telegram
ልጁም የእግዚአብሔር የክብሩ ነጸብራቅና የአምላካዊ ባሕርዩ አምሳያ ነው፡፡ ወልድ አምላክ በመሆኑም ይህን ዓለም በሥልጣኑ ኃይል ይቆጣጠረዋል ፤ በሥርዓት እንዲመራም ያደርገዋል ። እኛን ከኃጢአት ለማንጻትና የተመዘገበብንን የበደል ደብዳቤ ለመደምሰስ ከሞተ በኋላ ፥ አሁን በአባቱ ጎን ባለው ከፍተኛ ሰማያዊ የክብር ቦታ ተቀምጧል ። [ሕያው ቃል ዕብራውያን 1:3]
إظهار المزيدلم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
358
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+127 أيام
+9330 أيام
أرشيف المشاركات
358
ኢየሱስ የነፍሴ መልሕቅ ⚓
---
የእግዚአብሔር ቃል ሐሰት ሊሆን አይቻልም፤ በእርሱ ለተማፀን ተጠብቆልን ባለ ተስፋችንም ማመንን ላጸናን ለእኛ ታላቅ ደስታ አለን። ይህችም ተስፋ ነፍሳችን እንዳትነዋወጥ እንደ መልሕቅ የምታጸና ናት።
ወደ ዕብራውያን 6:18-19
@ShekinnahKBR
358
Repost from Good Christian Books Shelf
“ቅጥር የሌለው ቤት ገንዘቡ እንዲሠረቅ፥ እንደዚሁም ሚስት የሌለችው ሰው ተቸግሮ ይኖራል”🥰
ተናጋሪው ጋሽ ሲራክ ናቸው😁
358
አንዳንድ ሰዎች ግን ይፃፉ👌.....ይህስ ምን ይባላል እሽ በስመአብ..🫡🫠🫠🤌
ብስለት (Maturity) ማለት ሁሉን ማወቅ አይደለም፤ ይልቁንም ምን ያህል እንደማናውቅና አቅመ-ቢስ እንደሆንን መረዳት ነው። ሰው ራሱን ይበልጥ ባወቀ ቁጥር፣ የራሱን ውስንነት አጥብቆ ይገነዘባል። ያኔ ነው እምነት ጊዜያዊ ከሆነ ስሜት ወጥቶ የሕይወት solid መሠረት የሚሆነው። 😊
በልጅነት ዘመናችን እግዚአብሔርን የምንፈልገው «ምን ይሰጠኛል?» ብለን ለበረከቱ ነው፤ መንፈሳዊ ብስለት ውስጥ ስንገባ ግን፣ እርሱን የምንፈልገው «ማንነቱ» ራሱ በቂያችን ስለሚሆን ነው!
አንዳንዴ ሕይወት ክፉኛ የምትፈትነን ለዚህ ነው። 100% እርግጠኛ ነን ያልነው ነገር ሲፈርስ፣ በእጃችን የጠነከረ የመሰለን ነገር አፈትልኮ ሲወጣ... ይህ ተስፋ እንድንቆርጥ ሳይሆን፣ «በእርግጥ የተደገፍኩት በምኑ ላይ ነው?» ብለን ራሳችንን እንድንጠይቅ የተሰጠን መለኮታዊ wake-up call ነው!
ምክንያቱም እውነተኛ Security ማለት ሁኔታዎች ፈጽሞ እንዳይለወጡ ኮንትራት ማሰር አይደለም፤ ይልቁንም ሁኔታዎች ሁሉ ቢለወጡም፣ ፈጽሞ የማይለወጥ መሠረት እንዳለን ማወቅ ነው።
በሂደት የምንረዳው አንድ ጥልቅ እውነት አለ፦
እግዚአብሔር እኛን ለሁሉ ነገር በቂ (self-sufficient) እንድንሆን አያሳድገንም፤ ይልቁንም በእርሱ ብቻ እንድንበቃ (dependent on Him) ያስተምረናል! 🙌🏾
ይህ የእምነት ብስለት ነው። የሚመጣውን ሁሉ ከመፍራት ይልቅ፣ በሚመጣው ማዕበል ሁሉ ውስጥ ልባችን ለማን እንደተሰጠ ማስታወስ። እኛን ተራ የሆነ የነገ ስጋት ሊገዛን አይችልም፤ ምክንያቱም ዛሬ የተሰጠንን ጊዜያዊ በረከት ብቻ ሳይሆን፣ ከበረከቱ በላይ የሆነውን ታላቁን «ሰጪ» እናውቀዋለን።
እውነተኛ ሕይወት ማለት ይሄው ነው፦
የሚለወጠውንና አላፊውን ነገር በእጅ ይዞ፣ ፈጽሞ የማይለወጠውን ጌታ ግን በልብ ማሳረፍ! 🫶🏾
—
@ShekinnahKBR
#የክብሩ_ነጸብራቅ #Maturity #TrueSecurity #SpiritualGrowth #AuthenticFaith
358
መውጊያን ማቀፍ...
ስንቶቻችን ነን ገፍቶ በጣለን እጅ ላይ መልሰን ለመደገፍ የምንሞክረው? ሰላማችንን በነጠቀን፣ ነፍሳችንን ባደረቀው drain ባደረገው እና ክፉኛ ባደማን ነገር ላይ «ምናልባት ዛሬስ ያክመኝ ይሆን?» ብለን ተመልሰን የምንወድቀው? የሰበረንን ሰው፣ ያደቀቀንን toxic ልማድ፣ ወይም ዋጋ ያሳጣንን ዓለም መልሰን የራሳችን comfort zone እና መጠገኛ ልናደርገው እንሞክራለን።
ነገር ግን ነፍስ እውነተኛ ዕረፍት የምታገኘው አንድ መለኮታዊ የውሳኔ ቀን ላይ ስትደርስ ነው፦ ለያዕቆብ ቤት ቃሉ «ከእንግዲህ ወዲህ በአቈሰሉአቸው ላይ አይደገፉም!» እንደሚል፣ እኛም በሙሉ ልብ «ከእንግዲህ ወዲህ ባቆሰለኝ ላይ አልደገፍም!» ስንል ነው። What a decision! 🙌
በቃ! ይሄኮ ትልቅ የነፍስ አብዮት ነው። "ከእንግዲህ ዋጋ በሚያሳጣኝ የሰዎች ይሁንታ (validation) ላይ አልደገፍም፤ ነፍሴን በሚያደማው ጫጫታ ላይ አልወድቅም፤ I'm done leaning on what breaks me!" ብሎ ማረፍ። 👌
ቃሉ ሲቀጥል «በእስራኤል ቅዱስ በእግዚአብሔር ላይ በእውነት ይደገፋሉ» ይላል።
በእውነት መደገፍ ማለት ምን ማለት ነው?
በሰዎች ፊት እንደምንለብሰው fake strength፣ በእግዚአብሔር ፊትም «ምንም አልሆንኩም...» ብሎ ማስመሰል አይደለም። በእውነት መደገፍ (authentic dependency) ማለት— ቁስልን ሳያሹ፣ እንባን ሳያደርቁ፣ ድካምን ሳይሸሽጉ «አቅም አጥቻለሁ፤ I am exhausted፣ አባቴ ሆይ አንተ አቅፈህ እለፈኝ» ብሎ በፊቱ ዝርር! ማለት ነው። ልክ ጥገኛ ሕፃን በእናቱ ደረት ላይ እንደሚደገፍ፣ የተሰበረች ነፍስን ይዞ በጸጋው ሆስፒታል ውስጥ ማሳረፍ ነው።
Guys... ዛሬ ያደማን፣ የሰበረንና ገፍቶ የጣለን ምድራዊ መደገፊያ ሁሉ ይቅርብን። የተሰበረውን ወደማይጠግነው ዓለም ተመልሰን አንመልከት። ደም እያፈሰሱ መውጊያን ማቀፍ ይብቃ!
እውነተኛው ወጌሻ❤️🩹፣ የማያቆስለው፣ የቆሰለውንም የሚፈውሰው የነፍስ ሐኪም... እውነተኛ ዕረፍት የሆነው አባት እጆቹን ዘርግቶ ይጠብቀናል—Let’s lean on Him for real! 🤍🔥❤️🩹
«በዚያም ጊዜ እንዲህ ይሆናል፤ የእስራኤል ቅሬታ... ከእንግዲህ ወዲህ በአቈሰሉአቸው ላይ አይደገፉም፤ ነገር ግን በእስራኤል ቅዱስ በእግዚአብሔር ላይ በእውነት ይደገፋሉ።» — ትንቢተ ኢሳይያስ 10፥20@ShekinnahKBR #የክብሩ_ነጸብራቅ #ኢሳይያስ10 #እውነተኛ_ጥገኝነት #TrueRest #LeanOnHim
358
“አንተን ታምኛለሁና በማለዳ ምሕረትህን አሰማኝ፤ አቤቱ፥ ነፍሴን ወደ አንተ አንሥቻለሁና የምሄድበትን መንገድ አስታውቀኝ።”
— መዝሙር 143፥8
የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ 🙌
@ShekinnahKBR
358
በማለዳ በእውነተኛ ማንነት እግዚአብሔርን እንፈልግ 🧎♂️🧎♂️🧎♂️
አልዋሽህም ደህና ነኝ ብዬ🥺
በእግዚአብሔር ፊት "አባቴ ወይ ደክሞኛል እርዳኝ" እንደማለት ጉልበታችንን የሚያድስ ምን አለ ! 🙌@ShekinnahKBR
358
Astuye ስትዘምር፦
አልዘልቅም ፡ ስል ፡ ዘለቅኩ
.
.
በብዙ ፡ በረታሁ ፡ በእርሱ ፡ ስለተያዝኩ
በብዙ ፡ ጀገንኩኝ ፡ በእርሱ ፡ ስለተያዝኩ
አቤት ግን የእግዚአብሔር ምህረት ስንቴ በቃኝ! ጨረስኩ! ባልንበት እንደገና በኃይ አስታጥቆን አስቀጠለን😭
@ShekinnahKBR
358
አትሂድ ከደጄ ወዳጄ ቤቴ ግባ🧎♂️🧎♂️🧎♂️
እግርህን ልጠበው እባክህ አረፍ በልና
እንግዶችን ልሸኝ ገፍተው ከእልፍኝ ያራቁህን
ደምቀህ እንዳትታይ በምክር የሚያቀሉህን
🔥☁🧎♂🙇🏾🙇🏾
@ShekinnahKBR
358
«በሰላም ያዋልከኝ ሆይ በሰላም አሳድረኝ… !» በምትል የውርወራ ጸሎት የት ልንደርስ ነው ወገን?ነገሩኮ ያሳቃልም፣ ያስቃልም፣ ያሳቅቃልም ያሳዝናልም! ጠላት ነፍሳችንን ለማድከም እና ትውልዳችንን ለማደንቆር ቀንና ሌሊት full-time እየሠራ፣ እኛ ግን በሰላሳ ሰከንድ jet በሆነች ጸሎት ልናሸንፈው አንችልም። እግዚአብሔርኮ ቶሎ ትእዛዝ ሰጥተነው የምንሄደው የጊዜያችን ለዛውም የትርፍ ሰዓታችንን ለማኝ አይደለም፤ እርሱ ልባችንን የሚፈልግ አባት ነው: የተሻለና ምርጡ ይገባዋል። Take God seriously, take prayer seriously! የሕሊና ዕዳ ለመክፈል ሳይሆን፣ ከሕያው አምላክ ጋር ለመገናኘት እንጸልይ። @ShekinnahKBR
