𝐒𝐂𝐈𝐄𝐍𝐂𝐄 𝐒𝐏𝐄𝐂𝐓𝐑𝐔𝐌
Kanalga Telegram’da o‘tish
- This channel focuses on the Ethiopian University entrance exam to help students achieve better results. • It provides: • Various articles • Photos • Illustrations • Foreign and domestic reference books • Weekly short tests • Education news.
Ko'proq ko'rsatish890
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-17 kun
-530 kun
Postlar arxiv
Physics🧑🏫አንድ 12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪ የግድ ሊያውቃቸው የሚገቡ የ Physics ፎርሙላወች!!!
📘Mechanics
1. Kinematics:
v = u + at s = ut + 1/2at^2 v^2 = u^2 + 2as2. Newton's Laws:
F = ma F_net = F_applied - F_friction3. Work and Energy:
W = Fd cos(θ) KE = 1/2mv^2 PE = mgh W_net = Δ KE4. Momentum:
p = mv F = Δ p/Δ t p_initial = p_final (conservation of momentum)5. Circular Motion:
a_c = v^2/r F_c = mv^2/r📘Thermodynamics 1. Laws of Thermodynamics:
First Law: Δ U = Q - W Second Law: Δ S ≥ 02. Ideal Gas Law:
PV = nRT3. Heat Transfer:
Q = mcΔ T (for temperature change) Q = mL (for phase change)📘Waves and Oscillations 1. Simple Harmonic Motion:
x(t) = A cos(ω t + ϕ) T = 2π√(m/k)2. Wave Speed:
v = fλ3. Sound Intensity:
I = P/A📘Electricity and Magnetism 1. Ohm's Law:
V = IR2. Power in Circuits:
P = IV P = I^2R P = V^2/R3. Coulomb's Law:
F = k|q_1 q_2|/r^24. Electric Field:
E = F/q = k|q|/r^25. Magnetic Force:
F = qvBsin(θ)📘Optics 1. Lens Formula:
1/f = 1/d_o + 1/d_i2. Magnification:
M = -d_i/d_o = h_i/h_o3. Snell's Law:
n_1sin(θ_1) = n_2sin(θ_2)📘Modern Physics 1. Photoelectric Effect:
E_photon = hf = hc/λ2. Einstein's Mass-Energy Relation:
E = mc^2https://t.me/omo_academy https://t.me/omo_academy
86ቱ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ስም ዝርዝር
ኦሮሞ
አማራ
ሶማሌ
ትግራይ
አፋር
ሲዳማ
አገው
ዎላይታ
ከምባታ
ሀዲያ
ጋሞ
ጉራጌ
ኢሮብ
አርጎባ
ቱለማ
ስልጤ
ሺናሻ
አኝዋክ
ኑዌር
ሀመር
ኩናማ
ጉምዝ
በርታ
በና
አሪ
ሙርሲ
ቡሜ
ካሮ
ፀማይ
ኮንሶ
ዳሰነች
ቦረና
ገርባ
አላባ
አርቦሬ
ባጫ
ቤንች
ባስኬቶ
ቡርጂ
ጫራ
ጋዋዳ
ጌዲኦ
ጊዶሌ
ጎፋ
አደሬ
ከፊቾ
ኮንታ
ኒያንጋቶም
ናኦ
ቀቤና
ሱርማ
ጠንባሮ
የም
ወርጂ
ዲዚ
ዶንጋ
ዳውሮ
ዲሜ
ምዓን
ኮሞ
ማረቆ
ሞስዬ
ኦይዳ
ቦዲ
ፈዳሼ
ኮሬ
ማሌ
ማኦ
መሰንጎ
መዠንገር
ቀዋማ
ቀጨም
ሸኮ
ዘየሴ
ዘልማም
ሽታ
ቤተ እስራኤል
ማሾላ
ኮጉ
ድራሼ
ገባቶ
ጌዲቾ
ብራይሌ
ሙርሌ
ኮንቶማ
ምንጭ - የኢትዮጵያ ታሪክ
https://t.me/omo_academy
https://t.me/omo_academy
https://t.me/omo_academy
✅ Maths Formula on Trig function
⭐ Sin(A+B) = SinACosB+CosASinB
⭐ Sin(A-B) = SinACosB-CosASinB
⭐ Cos(A+B) = CosACosB-SinASinB
⭐ Cos(A-B) = CosACosB+SinASinB
⭐ tan(A+B) = tanA+tanB/1-tanAtanB
⭐ tan(A-B) = tanA-tanB/1+tanAtanB
⭐ SinC+SinD = 2Sin(C+D/2) Cos(C-D/2)
⭐ SinC-SinD = 2Cos(C+D/2) Sin(C-D/2)
⭐ CosC+CosD = 2Cos(C+D/2) Cos(C-D/2)
⭐CosC-CosD = 2Sin(C+D/2) Sin(D-C/2)
⭐CosC-CosD = -2Sin(C+D/2) Sin(C-D/2)
⭐ 2SinACosB = Sin(A+B)+Sin(A-B)
⭐ 2CosASinB = Sin(A+B)-Sin(A-B)
⭐ 2CosACosB = Cos(A+B)+Cos(A-B)
⭐ 2SinASinB = Cos(A-B)-Cos(A+B)
⭐Sin2A = 2SinACosA
⭐ Cos2A = Cos²A-Sin²A = 2Cos²-1 = 1-2Sin²A
⭐ tan2A = 2tanA/1-tan²A
⭐Sin2A = 2tanA/1+tan²A
⭐Cos2A = 1-tan²A/1+tan²A
⭐ Sin(A+B)Sin(A-B) = Sin²A-Sin²B
= Cos²B-Cos²A
⭐Cos(A+B)Cos(A-B) = Cos²A-Sin²B = Cos²B-Sin²A
⭐Sin3A = 3SinA-4Sin³A
⭐Cos3A = 4Cos³A-3CosA
⭐ tan3A = 3tanA-tan³A/1-3tan²A
⭐ Sin²θ+Cos²θ = 1
⭐ Sin²θ = 1-Cos²θ
⭐Cos²θ = 1-Sin²θ
⭐ 1+tan²θ = Sec²θ
⭐Sec²θ-tan²θ = 1
⭐ tan²θ = Sec²θ-1
⭐ 1+Cot²θ = Cosec²θ
⭐Cosec²θ-Cot²θ = 1
⭐Cot²θ = Cosec²θ-1
https://t.me/omo_academyየክለሳ ንባብ ስልት
ከዋናው ጥናት በኋላ ፈተናው ሲቀርብ የክለሳ ዝግጅት ማድረግ የተለመደ ነው። ነገር ግን ከየት ነው የሚጀመረው? ቢቢሲ የትምህርት ባለሙያዎችን፣ የዩኒቨርሲቲ መምህራንን፣ የሥነ ምግብ ተመራማሪዎችን፣ ውጤታማ ተማሪዎችን እንዱሁም የሥነ
አእምሮ ባለሙያዎችን አነጋግሮ ይጠቅማል ያላቸውን 12 ነጥቦች አዘጋጅቶላችኋል።
በእነዚህ ምክሮች መሠረት የማስታወስ ችሎታችሁንና የትኩረት አቅማችሁን ታዳብራላችሁ።
1. ቁርስና ጠቃሚ ምግቦች
ሰውነታችን በአግባቡ ሥራውን እንዲሰራ ኃይል ያስፈልገዋል፤ አንጎላችን ደግሞ ትኩረት እንዲኖረውና የማስተዋል አቅማችን
እንዲጨምር በቂ የሆነና ያልተቆራረጠ የኃይል አቅርቦት ይፈልጋል።
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ቁርሳቸውን ተመግበው ወደ ፈተና የሚገቡ ተማሪዎች የተሻለ ውጤት ያስመዘግባሉ። የተመጣጠነ ምግብ ተመግበው ለፈተና የሚቀርቡት ደግሞ የበለጠ የማስታወስና የማስተዋል አቅም ይኖራቸዋሌል። ስለዚህ ሁሌም ቢሆን
ፈተና ያለባቸው ተማሪዎች እንደ የገብስ ገንፎ፣ ዳቦ፣ ሩዝና ደንች ያለ በካርቦሃይድሬት የበለጸጉ ምግቦችን በቁርስ ሰዓት ተመግበው ቢወጡ ይመከራል።
እርጎ፣ እንቁላል፣ አሳ፣ ጎመን፣ ቲማቲምና አቮካዶ ዓይነት ምግቦችም እጅጉን ጠቃሚ ናቸው።
2. በጠዋት ወደ ጥናት መግባት
ሁሌም ቢሆን ነገሮችን አስቀድሞ መጀመርን የመሰለ ነገር የለም። ለፈተናም ቢሆን ጥናት በጠዋት ተነስቶ መጀመር በፈተና ወቅት የተረጋጋ መንፈስ እንዲኖረን ይረዳል።
ጠዋት ላይ ጭንቅላታችን እረፍት አድርጎ በአዲስ መንፈስ ሁለንም ነገር ስለሚጀምር፤ በዚህ ሰዓት ማጥናት ውጤታማ ያደርጋል። በተለይ ደግሞ የክለሳ ጥናቶችን ለከሰዓት ማሸጋገር ተገቢ አይደለም።
ጠዋት ጥናት የምንጀምርበትና የምናበቃበት ሰዓት ከፈተናው በፊት ባለት ሁለት ወይም ሦስት ሳምንታት ውስጥ ተመሳሳይ
ለማድረግ መሞከርም ውጤታማ ያደርጋል።
3. ምን ላይ ትኩረት ማድረግ እንዳለባችሁ ወስኑ
በመጀመሪያ ፈተናው የጽሁፍ ነው ወይስ የተግባር? ወይስ ቃለመጠይቅ ነው የሚለውን መለየት ወሳኝ ነው። ሁሉም ዓይነት
ፈተናዎች የራሳቸው የሆነ የተለያየ አይነት አቀራረብ አላቸው። በምሳሌ አስደግፎ ማብራሪያ መስጠት የሚጠይቅ ዓይነት ፈተና
ከሆነ ከዚህ በፊት የተሠሩ ፈተናዎችን እያመሳከሩ ጥቂት ቦታዎች ላይ በትኩረት መዘጋጀት።
ምናልባት ፈተናው ምርጫ አልያም አጭር መልስ የሚፈልግ ዓይነት ከሆነ ቀለል ያለና አጠቃላይ መረጃዎችን ለመያዝ
መሞከር።
4. እቅድ ማዘጋጀት
ምናልባት ነገሮችን ቦታ ቦታ ለማስያዝና እቅዴ ለማውጣት የምናጠፋው ጊዜ የባከነ መስሎ ሊሰማን ይችላል። ነገር ግን እውነታው በተቃራኒው ነው። ምክንያቱም ምን ማጥናት እንዳለባችሁና መቼ ማጥናት እንዳለባችሁ እቅዳችሁ ይነግራችኋል።
ከዚህ በተጨማሪም ምን ያክል እንደተጓዛችሁ ለመመዝገብና ለመከታተል ይረዳል።
የትኞቹን ማስታወሻ ደብተሮች መቼ መመልከት እንዲሆንባችሁ፣ የትኞቹን መጻህፍት ለተጨማሪ ማብራሪያ እንደምትጠቀሙ
እንዲሁም የፈተና ጥያቄዎችን መቼ መለማመድ እንዲለባችሁ በእቅዱ ውስጥ ማስገባት ውጤታማ ያደርጋል።
እዚህ ጋር መርሳት የሌለብን ለእረፍትና አካላዊ እንቅስቃሴም ቦታ መስጠት እንዲለብን ነው።
5. ከፋፍሎ ማጥናት
የክለሳ ጥናትን ከፋፍሎ ማካሄድን የመሰለ ነገር የለም። አንዴ የትምህርት ዓይነት ላይ 10 ሰዓት ሙሉ ከማሳለፍ በየቀኑ አንድ ሰዓት በማጥናት በ10 ቀን መጨረስ ይበልጥ ውጤታማ ያደርጋል።
ያጠናነውን ነገር ለማስታወስና በቀላሉ ለመሸምደድ ጭንቅላታችን ጊዜ ይፈልጋል። ከፋፍሎ ማጥናት ደግሞ ለዚህ ፍቱን መድሃኒት ነው። ከፋፍሎ ማጥናት እጅግ ውጤታማው መንገድ እንደሆነም በመላው ዓለም የተሰሩ የተለያዩ ጥናቶች
ያመክታሉ።
6. ራሳችሁን ቶሎ ቶሎ ፈትኑ
የሥነ አዕምሮ ጥናት ባለሙያዎች እንደሚለት የማስታወስ ችሎታን ለማዳበርና በራስ መተማመናችንን ለመጨመር ራስን
መፈተን ውጤታማ ያደርጋል።
ከዚህ በተጨማሪ እየተዘጋጀንበት ያለነውን ጉዳይ በደንብ እንደናውቀው ከማድረጉ በተጨማሪ የረሳናቸው አልያም
የዘለልናቸው ርዕሶችን ለመዳየት ይረዳናል።
7. መምህር መሆን
ከባዱን የክለሳና ራሳችሁን የመፈተን ሥራውን ካከናወናችሁ በኋላ ጓደኞቻችሁን ሰብሰብ አድርጋችሁ በጭንቅላታችሁ
የሚመጣውን ነገር በሙሉ ንገሯቸው። ራሳችሁን በመምህር ቦታ አድርጋችሁ እውቀታችሁን ለማካፈል ሞክሩ።
ምን ያህል እንደምታስታውሱ ለማወቅ ከመርዳቱ በተጨማሪ ጓዯኞቻችሁንም ትጠቅሟቸዋላችሁ።
8. ከተንቀሳቃሽ ስልካችሁ ራቅ በሉ
ስልኮች በጣም ብዙ ጥቅም አላቸው። ነገር ግን በጥናት ወቅት ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸው ነው የሚያመዝነው። በተለይ ደግሞ ማህበራዊ ሚዲያዎችን የምትጠቀሙ ከሆነ።
ብዙ ጥናቶች እንዳረጋገጡት ብዙ ጊዜያቸውን ስሌካቸው ላይ የሚያሳልፉ ተማሪዎች የትምህርት ውጤታቸው ሁሌም ቢሆን
ዝቅ ያለ ነው።
9. ሙዚቃ መቀነስና በጸጥታ ማንበብ
በጸጥታ ውስጥ ሆነው ጥናታቸውን የሚያከናወኑ ተማሪዎች ሙዚቃ እየሰሙ ከሚያጠኑት ጋር ሲወዳደሩ በእጅጉ የተሻለ
የማስታወስና የትኩረት አቅም እንዳላቸው ማረጋገጥ ተችሏል።
10. ቋሚ እረፍትና አካላዊ እንቅስቃሴ
ውጤታማ የክለሳ ጥናት ማለት እረፍት አልባ ጥናት ማለት አይደለም። በጥናታችን መሀል መሀል ላይ ጥሩ አየር ለማግኘትና
ሰውነታችንን ለማፍታታት ወጣ ብሎ እንቅስቃሴ ማድረግ የማስታወስ ችሎታችንን በደንብ ከፍ ያደርገዋል። ከዚህ በተጨማሪ
ሰውነታችን እና ጭንቅልታችን በእጅጉ የተሳሰሩ በመሆናቸው እንቅስቃሴ ስናደርግ የደም ዝውውራችን ይስተካከላል፤ ይህ
ደግሞ በቂ ኦክስጅን ወደ ጭንቅሊታችን እንዲሄድ ይረዳል።
አካሊዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ተዘርዝሮ የማያልቅ ጥቅሞች ያሉት ሲሆን ጭንቀትን መከላከልና በራስ መተማመንን መጨመር
ከነዚህ መካከል ይጠቀሳሉ።
11. እንቅልፍ
ከፈተና በፊት ያለችውን ምሽት ጥሩ እንቅልፍ አግኝቶ ማሳለፍ ተገቢ እንደሆነ ብዙዎች ይስማማሉ። ነገር ግን ጥሩ እንቅልፍ
ፈተናው ሲቃረብ ብቻ ሳይሆን ከሳምንታት በፊት ገና ዋናው ጥናት ሲደረግና ክለሳ በሚደረግበት ወቅትም እጅግ ወሳኝ ነው።
በጠዋት ተነስቶ ውጤታማ የክለሳ ጥናት ካደረጉ በኋላ በጊዜ ተኝቶ ጥሩ እንቅልፍ ማግኘት ሰውነታችንና ጭንቅልታችን በደንብ ተግባብተው እንዲሰሩ ይረዳቸዋል። ሌሊቱን በሙሉ ለማጥናት ሙከራ አታድርጉ ይላሉ የዘርፉ ባለሙያዎች። ምክንያቱም ራሳችን ላይ ጫና እያሳደርን ስለሆነ።
12. መረጋጋትና በጎ በጎውን ማሰብ
እስካሁን የተዘረዘሩትን ነገሮች ሁሉ ተግባራዊ ካደረጋችሁ ምንም የሚያሳስባችሁ ነገር ልኖር አይገባም። ዘና ብላችሁ ወደ ፈተና
መግባት ብቻ ነው የሚቀራችሁ። ምናልባት ጥሩ ያልሆነ አጋጣሚ ቢገጥማችሁ እንኳን እሱን ረስታችሁ ለቀጣዩ በጥሩ መንፈስ
ለመዘጋጀት ሞክሩ።
❝በመጨረሻም በእያንዳንዱ ጥሩ የፈተና ጊዜ ለራሳችሁ ሽልማት መስጠት አትርሱ።❞
